You are on page 1of 3

ቁጥር 01/11

ቀን 4/13/2011

ለደቡብ ሶዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት

ኬላ

ጉዳዩ ፡ በብልጫ ለከፈልነው ገንዘብ በግብር እንዲካካስልን ስለመጠየቅ

ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረግነው የህንጻ ኪራይ ስምምነት መሰረት ከጥቅምት 1 ቀን 2007
ዓ/ም ጀምሮ ለአምስት /5 / ተከታታይ ዓመታት በወር ብር 10,000.00 / አስር ሺህ/ ታክስን ሳይጨምር
በድምሩ ብር 600,000.00 ህንጻ ማከራየቴ ይታወቃል ፡፡

በዚህ ውል መነሻነት ባንኩ 2% / ሁለት ፐርሰንት/ ዊዝሆልዲንግ ታክስ ብር 12,000.00 / አስራ ሁለት ሺህ ብር
/ ቀንሶ ብር 588,000.00 /አምስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ብር / በጥሬ ገንዘብ ተቀብያለው፡፡

በዚህ ወቅት የሶዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ብር 600,000.00 /ስድስት መቶ ሺህ ብር / መሰረት
በማድረግ የሚከፈለው ግብር የተገኘው ገቢ በሚሸፍናቸው ዓመታት ተደልድሎ ግብሩ አስቦ ግብሩን ሰብስቧል
፡፡ ይሁን እንጂ ግብሩ ሲታሰብ የተቀነሰበኝን ቅድመ ግብር /ዊዝሆልዲንግ ታክስ ከተወሰነው ግብር ላይ ተቀናሽ
አልተደረገልኝም ፡፡

ሌላው ቅሬታ ያቀረብኩት ጉዳይ 10% ተርን ኦቨር ታክስ የተመለከተ ነው ፡፡ በተደረገው ውል መሰረት ብር
60,000.00 ተርን ኦቨር ታክስ ከባንኩ በወቅቱ መሰብሰብ ባለመቻሌ የተነሳ የሶዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን
ጽ/ቤት እኔ እንድከፍል በመጠየቁ የተነሳ ተርን ኦቨር ታክስ ብር 60,000.00 ከፍያለው ፡፡

በተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ እንደተመለከው አገልግሎት ሻጩ ወይም አከራዩ ስለታክሱ የመጀመሪያ ተጠያቂ
ስለሆነ እና ቀጣይ መሰብሰ እንደሚቻል በማሰብ ክፍያውን ፈፅሜያለው ፡፡

በመቀጠል የተርን ኦቨር ታክስ መክፈሌን ማስረጃ ለባንኩ በማቅረብ ገንዘቡን እንዲተካልኝ ጥያቄ አቀረብኩ ፡፡
ይህ በእንዲይ እያለ ከነሀሴ 7 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኜ ሂሳብ መዝገብ
መያዝ ጀመርኩ፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
አቅርቤ ባንኩ በጠቅላላ ኪራይ ገቢ ላይ ብር 90,000.00 ( 600,000.00*15% ) በቀን 10 / 08 / 2010 ዓ/ም
ከክፍያ ላይ ለተቀነሰ የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ተሰጠኝ ፡፡ ቀደም ሲል የከፈልኩት ብር 60,000.00 ተተካ
ማለት ነው ፡፡

ይህ በቅድሚያ የከፈልኩት ገንዘብ አሁን ወይም ወደፊይት ከሚኖርብኝ የመንግስት ግብርና ታክስ
እንዲቀናነስልኝ ጥያቄ በማቅረቤ በ 2010 የግብር ዘመን የነበረብኝን ግብር ብር 16,200.20 ተቀናሽ ሆኖ ቀረው
ብር 43,799.80 ለሚቀጥለው የግብር ዘመን እንደተዛወረ ይታወቃል ፡፡

ስለዚህ በ 2011 የግብር ዘመን ያለብኝ ግብር ብር 27,988.56 ተቀናሽ እንዲደረግልኝ እየጠየኩ ቀሪው ብር
15,811.24 ለሚቀጥለው የግብር ዘመን እንዲተላለፍልኝ ወይም በጥሬ ገንዘብ እንዲተካልኝ በማክበር
አመለክታለው ፡፡ ለተቀበልኩት ብር 600,000.00 ግብሩን በጥሬ ገንዘብ እንድከፍል የተደረገ በመሆኑ ቀደም ሲል
ዊዝሆልድ የተደረገው ብር 12,000.00 ለወደፊት የመንግስት ዕዳ ማካካሽ ይዋልልኝ ፡፡

በተጨማሪም ንብ ባንክ ከግንቦት 17 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ ለአምስት /5 / ተከታታይ ዓመታት ውሉ የፀና
ሆኖ በወር ታክስ ሳጨምር በወር ብር 8,695.65 የ 36 ወሩ የቅድመ ክፍያ ብር 313,043.40 ለመክፈል
መስማማታችን በባልስልጣኑ መ/ቤት ይታወቃል ፡፡

በዚህ ውል መነሻነት ባንኩ 2% / ሁለት ፐርሰንት/ ዊዝሆልዲንግ ታክስ ብር 6,260.87 / ስድስት ሺህ ሁለት
መቶ ስድሳ ብር ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም/ ቀንሶ ብር 306,782.53

ብቻ በጥሬ ገንዘብ ተቀበልኩ ፡፡ ታክሱን ግን አልተቀበልኩም ፡፡

ከዚያም ከነሀሴ 7 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆንኩ ፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ
ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት አቅርቤ ባንኩ በጠቅላላ ኪራይ ገቢ ላይ ብር 313,043.40
አስራ አምስት ፐርሰንት /15%/ ብር 46,956.51 በባንክ ተላከ ፡፡

ከዚያም ቫት ከመመዝገቤ በፊት ማለትም ከግንቦት 17 ቀን 2009 እስከ ነሀሴ 6 ቀን 2009 ዓ/ም የ 82 ቀናት
ገቢ ብር (289.855* 82 ) = 23,768.11 ግብርና ታክስ ታስቦ ለሶዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ፅ/ቤት ገቢ
ተደርጓል ፡፡ ቀሪው ማለትም ሂሳብ መያዝ ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ ( 1,080 – 82 ) የ 998 ቀናት ገቢ (ብር
289.855* 998 ) = 289,275.29 በሂሳብ መዝገብ አካተን በየግብር ዘመኑ ግብሩን እያስታወቅን እንገኛለን ፡፡

እኔም ህንጻ ኪራይ ገቢ ብር 289,275.29 እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 43,391.30 በድምሩ ብር


332,666.59 የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ሰጥተንበታል ፡፡
እዚህ ላይ የምጠይቀው ጉዳይ ዊዝሆልድ የተደረገው ገንዘብ ብር 6,260.87 / ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ስድሳ
ብር ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም/ ወደፊት ለሚኖርብኝ ማንኛውም የመንግስት ዕዳ ለማካካሻ እንዲውል በማክበር
አመለክታለው ፡፡

ከሰላምታ ጋር

አየለ አበራ ኢባሳ

የድርጅቱ ባለቤት

You might also like