You are on page 1of 1

ቀን 22/11/2014 ዓ.

ለልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት

አ.አ

ጉዳዩ፡- ቅሬታ ማቅረብን ይመለከታል

ከላይ በርዕሱ ለለመግለፅ እንደተሞከረው አለም፣ሰይድ እና ጓደኞቻቸው ካፌ እና ሬስቶራንት


ህ/ሽ/ማህበር በወረዳ 07 ተክለሀይማኖት አካባቢ ባለው ሰርቶ ማሳያ ህንፃ ላይ በ 2012 ዓ.ም የቦታ ድጋፍ
የተደረገልን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የወረዳ 07 የስራ፣ኢንዱስትሪ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ፅ/ቤት
በ 2012 ዓ.ም ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት ከልብስ ስፌት ወደ ካፌ እና ሬስቶራንት ከቀየረልን ቡሀላ እንዲሁም
በ 2013 ዓ.ም ባቀረብነው የሽግሽግ ጥያቄ ግንቦት 2014 ዓ.ም ከአንደኛ ፎቅ ወደ ግራውንድ እኛ እና ሌሎች
11 ኢንተርፕራይዞችን ያወረደን ቢሆንም ምንም በማናውቀው ምክናየት እኛን ብቻ በመለየት ወደ 2012
ዓ.ም ወደነበራችሁበት ዘርፍ እና ወደ አንደኛ ፎቅ በሶስት(3) ቀን ውስጥ እንድንመለስ በደብዳቤ
አሳውቀውናል፡፡ሆኖም ግን የማህበሩ አባላት በ 2012 ዓ.ም የነበረንን የልብስ ስፌት ማሽን ከሸጥን ቡሀላ እና
ከግለሰብ 60,000 ሽህ ብር ተበድረን የከፈትነውን ካፌ እንድሁም ከአንደኛ ፎቅ ወደ ግራውንድ ስንወርድ
ለኪችን ማሰሪያ 20,000 ሽህ ብር ወጭ ካደረግን ቡሀላ ገና በአግባቡ ያለብንን እዳ ሳንከፍል፣ከራሳችን አልፎ
ለአምስት (5) የስራ -አጥ ዜጎች የስራ እድል ፈጥረን እና የስራ እድል ፈጠራ መመሪያ በግልፅ የአንድ ቤተሰብ
አባል በጋራ ሆኖ መደራጀት እንደሚችል አስቀምጦት ሳለ እንዴት የማይታወቁ የአንድ ሙስሊም ቤተሰብ
አባላቶች ይደራጃሉ እየተባልን በእምነታችን ጭምር ተለይተን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሳንቆጠር ከዛሬ
ሁለት አመት በፊት ወደነበራችሁበት ዘርፍ ተመለሱ እየተባልን ተረጋግተን እንዳንሰራ እና ማህበሩ እንዲበተን
ከሌላው በተለየ ከፍተኛ ጫና እየተፈጠረብን ስለሆነ በእናንተ በኩል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠን በአክብሮት
እንጠይቃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

አለም ሻፊ(የማህበሩ ስራ አስኪያጂ)

You might also like