Professional Documents
Culture Documents
Law of Human Resource
Law of Human Resource
እና ሕጋዊነቱ
Print
Email
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው ገበታ ለሃገር መርሃግብር የመንግሥት ሠራተኞች የወር
ደሞዛቸውን ለገሱ የምትል ዜና በተደጋጋሚ በመስማቴ እና እውነት በዚህ የኑሮ ውድነት
እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዛቸውን የሚለግሱት ጎርጎራ፣ ወንጪ አሊያም ኮይሻ ላይ
ሆቴል መሰራቱ ከጊዚያዊ ችግሮቻችን ይበልጣል ብለው አምነው ወይስ በአለቆቻቸው ተፅዕኖ
ሥር በመሆናቸው ተገድደው የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ውስጤ ሲመላለስ በመቆየቱ ነው፡፡
መልካም ንባብ!
ለጠቅላይ ሚኒስትራችን ምስጋና ይግባቸውና አይነ-ግቡ የሆኑ የቱሪስት መዳረሻዎችን ከቤተ-
መንግሥታቸው ጀምረው እየገነቡልን ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ስራዎች የሃገርን ገፅታ ከመገንባት
ጀምሮ ታሪክን ጠብቆ በማቆየት በቱሪዝም እንደሃገር የሚገኘው ገቢ ከፍተኛ እንዲሆን
በማድረግ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው መሆናቸው በስፋት ይጠቀሳል ይሁን እንጂ
በተቃራኒው ቅንጦት ነው፣ በዚህ ሰዓት ሰላም እና በልቶ ማደር እንጂ ቅንጡ ሆቴል የሚፈልግ
ኢትዮጵያዊ ከቁጥር አይገባም ስለሆነም ያለጊዜው የመጣ ፕሮጀክት ነው በማለት
የሚተቹትም አልጠፉም፡፡
ቤተመንግሥትን ከማስዋብ የተጀመረው ፕሮጀክት አሁን አድማሱን አስፍቶ ሃገራዊ ቅርፅን
በመላበስ በሶስት ክልሎች ማለትም አማራ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ያሉ የመስህብ ስፍራዎችን
ወደማልማት ተሸጋግሯል፡፡ ለዚህም እውን መሆን ገበታ ለሃገር በሚል በገቢ ማሰባሰቢያ መልክ
የ 10,000,000 ብር እና 5,000,000 ብር የሚከፈልበት እራት ግብዣ በጠቅላያችን
ተሰናድቷል፡፡ በዚህ አላበቃም በኢትዮ ቴሌኮም አማካኝነት ዜጋው ልቡ በፈቀደ መጠን ገንዘብ
እንዲለግስ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ተዘጋጅቷል፤ የባንክ አካውንትም በተለያዩ ሚዲያዎች
ይፋ በማድረግ ገቢ ማሰባሰብ ስራው ቀጥሏል፡፡ ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ ይፋ ሲደረግ ያልተገለፀ
ነገር ግን በተግባር እየሆነ ያለ አንድ እውነት አለ፡፡ ይህም የመንግሥት ሠራተኛው ለፕሮጀክቱ
የወር ደሞዙን እንዲሰጥ ማድረግ፡፡ የእንትን ሚኒስቴር ሠራተኞች እና አመራሮች ለገበታ
ለሃገር የወር ደሞዛቸውን ለገሱ የሚል ዜና በየዕለቱ እየሰማን ነው፡፡ ለመሆኑ የሠራተኛ
ደመወዝ የሚቆረጠው እንዴት ነው?፣ አንድ የስራ ሃላፊ ስለፈለገ ወይም መስሪያቤቱ
አመራሮች ተወያይተው ስላፀደቆ የሠራተኛን ደመወዝ መቁረጥ ይቻላል እንዲቆረጥብን
አንፈልግም የሚሉ ሠራተኞች ሲኖሩ እንዴት ይደረጋል?፣ የሚሉ ጥያቄዎች በዚህ ጽሑፍ
መልስ ለመስጠት ይሞከራል፡፡
ማጠቃለያ
የመንግሥት ሃላፊዎች የሚወስኗቸው እያንዳንዱ ውሳኔዎች ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን
ማረጋገጥ ለሚመሩት ተቋምም ሆነ ለሚያስተዳድሩት ሠራተኛ ደህንነት መጠበቅ እጅግ
ወሳኝ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በአንዳንድ ሃገራት በዓላትን አስታኮ በቦነስ መልክ
ሠራተኞች የሚያወጧቸውን ወጪዎች እንዲሸፍኑ የ 2 እና 3 ወር ደመወዝ መስጠት
የተለመደ አሰራር ነው ይሁን እንጂ በእኛ ሃገር ነባራዊ ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ
የሠራተኛውን ደመወዝ ፈቃዱን ሳይጠይቁ መቁረጥ ከህግ ውጪ ከመሆኑም ባሻገር በስራው
እርካታ የራቀውን ሠራተኛ ከመፍጠር አልፎ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ
ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ሠራተኛውም በመሪዎች ተፅዕኖ ሥር
ወድቆ በጀርባ ሆኖ ከማጉረምረም ይልቅ መብቱን እና ግዴታውን ጠንቅቆ በማወቅ በህግ
ለተሰጠው መብት መታገል እና ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል፡፡
Last modified on Wednesday, 09 September 2020 19:07
READ 5301 TIMES
IN LABOR AND EMPLOYMENT BLOG
TAGGED UNDER
CIVIL SERVANT
SALARY
Abel Zewdu
ጸሐፊው በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን ከ 5 አመት በላይ በተለያዩ መሥሪያ
ቤቶች በሕግ ባለሙያነት እንዲሁም በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡ ጸሐፊው አሁን ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሲሆኑ
በተጨማሪም በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ላይ በየሳምንቱ አርብ ጠዋት የሚቀርብ "ሕጉ ምን ይላል" የተሰኘ
ፕሮግራም እያሰናዱ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡