You are on page 1of 2

ቀን 22/10/2014 ዓ.

ለመንታ የጥበቃ የሰው ሀይል አገልግሎት የተወሰነ የግል ማህበር አገልግሎት ፅ/ቤት

አመልካች፡- አቶ ከበደ ሙለታ

አድራሻ፡-በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 14 የቤ/ቁ 803

ነዋሪ ስሆን የማመለክተው ጉዳይ ከዚህ እንደሚከተለው ነው አምልካች በውሀና ፍሳሽ መ/ቤት
ከ 1999 ዓ.ም ነሀሴ 16 ጀምሮ እስከ 2001 ዓ.ም ለሁለት አመት ድርጅቱ በኮንትራት ቀጥሮኝ
ስሰራ እንደነበርኩ ይታወቃል በመሆኑም ደጀን የጥበቃና የሰው ሀይል አገልግሎት የተወሰነ የግል
ኩባንያ ድርጅቱን ሲረከብ አዘዋውሮኝ ስሰራ ስለነበር ከእነስ ጋር በመዘዋወር እስከአሁን ድረስ
ከኤጀንሲ ወደ ኤጀንሲ እየተዘዋወርኩ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እስከአሁን ድረስ እያገለገልኩ
እገኛለው ነገር ግን በስራ ገበታዬ ላይ እያለው ምንም በማይታወቅ ሁኔታና ባልተረዳሁት
አግባብ ግንቦት 1 ቀን አሰሪው በስራ ምድቤ ላይ በመምጣት የዝውውር ደብዳቤ ሲያመጣልኝ
እን ደግሞ ይህንን ደብዳቤ ያለጥፋትና ያለበቂ ምክንያት ዝውውሩን ተቀበል ሲለኝ እኔ
አልቀበልም ምክንያቱም አግባብ ባለው መልኩ የተፃፈ ደብዳቤ ስለሆነ እኔ ደብዳቤውን
ሳልቀበል ቀርቼ ስለነበረ መደበኛ ስራዬ ላይ ገብቼ እየሰራው እያለ በድጋሚ በ ግንቦት 5 መደበኛ
ስራዬ ላይ ስገባ መዝገቡ ተደብቆብኝ ስለነበር እኔም ሳልፈርም መስራት የለብኝም በማለት
ስራውን እንዳቋርጥ አድርጎኛል ይህንን የማስጠንቀቂያየተቀበልኩት ግንቦት 28 ከቀኑ 10 ሰአት
ሲሆን ፈርሜ ተቀብያለው አሁንም ቢሆን ያለአግባብና ያለ ምክንያት አሰሪው ሆን ብሎ እኔንና
ቤተሰቤን ለመበደል ስራውን ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ያለ በቂ ምክንያት በጠቅላላ 1 አምት ከ
6 ወር የሰራሁበትን በየጊዜው እያስቆረጠብኝ 6798 ብር ከ 60 ሳንቲም አስቆርጦብኛል ይህንኑ
ድብቅ አላማውን ለመሸፈን በተለያዩ ጊዜያቶች በስራ ምድቤ ላይ ከስራ አባርርሀለው ለምን
ይህንን ድርጅት ለቀህ አትሄድም በማለት ሰብአዊ መብቴን ነክቷል እኔ የግል ተበዳይበተለያ ጊዜ
ለዚሁ ተቋም አቤቱታ ባቀርብም ድርጅቱ ከግለሰብ ጋር በመወገንና በቸልተኝነት ለእንግልት
ለወጪ ተዳርጌአለው አሁንም ቢሆን እኔ የምጠይቀው ጥያቄ

1. ሰኔ 2/10/2014 ኣ.ም ይህኑ ችግሬን አስመልክቼ ለዚሁ ድርጅት ያለአግባብ የተቆረጠብኝ


ብር እንዲመለስልኝ የሚል ሲሆን
2. ወደ መደበኛ ስራዬ እንድትመልሱኝ የሚል ደብዳቤ መፃፌ ይታወቃልነገር ግን እስካሁን
ድረስ የተቆረጠብኝ ብር አልተሰጠኝም የስራ ምድቤ ላይም ልመለስ አልቻልኩም
አሁንም ቢሆን በ 5 ተከታታይ ቀን ውስጥ መልስ ካልተሰጠኝ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ
ህግ እንደምሄድ
3. ነሀሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እና በ 8/09/2014 ዓ.ም በጠየኩት ጥያቄ መሰረት መልስ
ባለማግኘቴ ምክንያት ለውሃና ፍሳሽ ደብዳቤ በመፃፍ የተቋሙን ጥያቄ በአግባቡ መልስ
ባለመስጠታቸው ምክንትና ያለአግባብ ከስራ ዝውውር ስለተሰጠኝ የግንቦት ወር ደሞዜ
ጭምር እንዲከፈለኝ የሚልና አግባብ ባለው መልኩ ደሞዜ ተስተካክሎ እንዲከፈለኝ
ስል በአክብሮት እጠይቃለው

አመልካች

ከሰላምታ ጋር

You might also like