You are on page 1of 2

17/8/2016

ለኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ላቀረብኩት አቤቱታ አሰሪዬ መስሪያ ቤት በላከዉ የጽኁፍ መልስ ላይ መልስ ማቅረብን ይመለከታል

እኔ ፍቃዱ ፈለቀ ዳዉድ የተባልኩት አቤቱታ አቅራቢ በምሰራበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ
አስኪያጅ ጽ/ቤት ከደመዎዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ የደረሰብኝን በደል ለኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በቀን
24/7/2016 ዓ.ም በጽኁፍ ማመልከቻ ከ 3 ገጽ የተለያዩ አባሪ ደብዳቤዎች ጋር ማቅረቤ ይታዎሳል፡፡ በዚህም
መነሻነት አቤቱታዬን በማዬት የአ/አ/ከ/አ/ስ/ጽ/ቤት መልስ እንዲሰጥ በጠዬቃችሁት መሰረት ላቀረበዉ ቀድሞ
የፈጸመብኝን አስተዳደራዊ በደል የሚያረጋግጥ እና የደገመ ምላሽ ተከታዩን መልስ ያቀረብኩ መሆኔን
እገልጻለኁ፡፡

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ስከታተል የቆዬሁትን የማስተርስ ዲግሪ ትምህርት በማጠናቀቅ ነሀሴ
1/2015 ዓ.ም በአ/አ/ከ/አ/ስ/ጽ/ቤት በአካል በመገኜት ምደባ እንዲሰጠኝ ሳመለክት ጽ/ቤቱ ያጠናቀኩትን
ትምህርት መሰረት ያደረገ ምደባ ለመስራት እንዳልቻለ በመግለጽ በቀን 5/12/2015 ዓ.ም በቁጥር
አአ/ከስአ/4877/ ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉኃብት ልማት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ምደባ እንዲሰጠኝ ቢጠይቅም
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉኃብት ልማት ቢሮ በቀን 9/12/2015 ዓ.ም በቁጥር 09-ጠ 11-40/12/169 መልሰዉ
ለአ/አ/ከ/አ/ስ/ጽ/ቤት በፃፉት ደብዳቤ ቀድሞ በነበረኝ የስራ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት በጽ/ቤቱ ዉስጥ
እንድመደብ በመግለጻቼዉ ትምህርት ከመሄዴ በፊት እሰራበት በነበረዉ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል እና
ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዉስጥ በደረጃ 13 ክፍት መደብ ላይ ተመድቢያለሁ፡፡

እዚህ ላይ በዳይሬክቶሬቱ ዉስጥ ጠፋ የተባለዉን የደረጃ 11 የመክሰም ሂደት በዝርዝር መረዳት


የተፈጸመብኝን በደል ፍንትዉ አድረጎ ያሳያል፡፡ ጽ/ቤቱ በሰጠዉ የመልስ ሰነድ የመጀመሪያ ገጽ 2 ኛ ብሎ
ባስቀመጠዉ ሃሳብ ላይ እነድተገጸዉ እኔ ትምህርት ላይ ሳለሁ በ 2014 ዓ.ም የጽ/ቤቱ የቢፒ አር ጥናት ክለሳ
ተደርጓል፡፡በተደረገዉ ክለሳም እሰራበት በነበረዉ ዳይሬክቶሬት ዉስጥ እኔ እሰራበት የነበረዉ ደረጃ 11
በዳይሬክቶሬቱ ዉስጥ ካለዉ የስራ ጫና አኳያ ዝቅተኛ እና የማይመጥን መሆኑ ስለታመነበት ደረጃ 13 ሆኖ
እንዲሻሻል ስለተወሰነ እና ተግባራዊም በመደረጉ በዳይሬክቶሬቱ ዉስጥ አጣን ብለዉ የገለጹት ደረጃ 11
በእርግጥም ሊጠፋ ችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት የተመደብኩበትን የደረጃ 13 ደመዎዝ ያለምንም ማቅማማት
ከትምህርት የተመለስኩ መሆኔን ታሳቢ በማድረግ በደረጃዉ አንድ እርከን ገባ ብሎ የሚገኜዉን ደመዎዝ
ሊከፍሉኝ ሲገባ ባለመክፈል በከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ዉስጥ እንድሰቃይ አድርገዉኛል፡፡ እዉነታዉ ይህ ሆኖ
ሳለ እና በቀደመዉ የትምህርት ዝግጅቴ እንዲሁም የስራ ልምዴ እንድመደብ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሓብት
ልማት ቢሮ በወሰነዉ መሰረት የተከለሰዉ የቢፒ አር ጥናት አሻሽሎ ባመጣዉ ደረጃ 13 ላይ ተመድቤ ሳለ የቢፒ
አር ጥናቱን መከለስ በማገናዘብ በተማርኩት የማስተርስ ትምህርት መሰረት ለመመደብ ተቼገርን በማለት
ፐብልክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮን እንዲመድበኝ የጠየኩትን ያህል በተከለሰዉ የቢፒ አር ጥናት ደረጃ
11 ተሻሽሎ እና አድጎ ደረጃ 13 መሆኑን በመረዳት እና ጥያቄዬን በፍትሃዊነት በመመለስ ፋንታ እዉነትን
በማድበስበስ መግለጽ እና በከሰመዉ ደረጃ 11 ላይ ልንመድበዉ የሚገባ ቢሆንም ብሎ ማለት እና የከሰመዉን
ደረጃ 11 ወዴት ነህ ብሎ መፈለግ እና ለእኔ በመሻት መመኜታቼዉ የተፈጸመብኝን አስተዳደራዊ በደል በግልጽ
የሚያሳይ እና የሚያረጋግጥ ነዉ፡፡ ስለሆነም ይህ ድርጊታቼዉ መልስ በሰጡበት ሰነድ ሁለተኛ ገፅ ላይ
በቼልተኝነት ወይንም በታቀደ አግባብ ምንም አይነት አስተዳደራዊ በደል አልፈጸምንም ብለዉ የገለጹት ሃሳብ
ረብ የለሽ እና ሀሰተኛ መሆኑን አስረጂ ነዉ፡፡

በመጨረሻም የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሓብት ልማት ቢሮ ማብራሪያ እንዲሰጥ የተጠየቀበት ደብዳቤ ላይ
በቢፒ አር ጥናት ክለሳ መሰረት የነበርኩበት ደረጃ 11 ተሻሽሎ ደረጃ 13 መኆኑን እና መክሰሙን እኔም ባለኝ
የቀደመ ስራ ልምድ እና ትምህርት ዝግጅት የሚገባኝ በመሆኑ መመደቤን አለመግለጻቼዉ ጥያቄዬን
በፍትሀዊነት ለመመለስ ምንም ፍላጎት እንደሌላችዉ እና እዉነትን መደበቃቼዉን የሚያጋልጥ ሲሆን
ለተጠየቀዉ ማብራሪያ መልስ ብሎ የጻፈዉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሓብት ልማት ቢሮም በደብዳቤዉ
የመጀመሪያ አንቀጽ ላይ እንደገለጸዉ ቀድሞ ከነበሩበት ደረጃ በላይ መድቡኝ ብሎ መጠየቁ በማለት መግለጹ
ጥያቄዬን በዉል አለመረዳቱን የሚያሳይ ሲሆን ይህም የሰጠዉን መልስ የተሳሳተ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ምክንያቱም የእኔ ጥያቄ ጽ/ቤቱ በቋሚነት የመደበብኝ እና እየሰራሁበት ያለዉ የደረጃ 13 ደመወዝ
ከትምህርት መመለሴን ታሳቢ በማድረግ አንድ እርከን ገባ ብሎ ይከፈለኝ የሚል እንጅ ጽ/ቤቱ ከመደበብኝ
ደረጃ 13 በላይ ሌላ ደረጃ ይሰጠኝ የሚል አይደለም፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የጥያቄዬን ትክክለኛነት እና በጉዳዩ ላይ አላግባብ
የደረሰብኝን የረጅም ጊዜ መጉላላት እንዲሁም የኢኮኖሚ ጫና በመረዳት ሊከፈለኝ ሲገባ ያለአግባብ
ሳይከፈለኝ የቀረዉን አንድ እርከን ገባ ብሎ የሚገኜዉን የደረጃ 13 ደመወዝ እንዲከፈለኝ እና ከነሀሴ 1/2015
ዓ.ም ጀምሮ አንድ እርከን ገባ ብሎ በሚገኝ የደረጃዉ ደመወዝ ሊከፈለኝ ሲገባ የቀረብኝ የዬወሩ ልዩነት
ተሰልቶ እንዲከፈለኝ ዉሳኔዉን እንዲያሳልፍ እጠይቃለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር!

ፍቃዱ ፈለቀ

You might also like