You are on page 1of 2

ሆሊ ኤንጅልስ ት ቤት / - አዳማ

የ 2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር የ 7 ኛ ክፍል የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር የሙከራ ጥያቄ

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ‹‹እውነት›› ወይም ‹‹ሐሰት›› በማለት መልስ/ሺ/፡፡

____________ 1. ኃላፊነት አንድን ህጋዊ ተግባር በአግባቡ የመፈፀም ግዴታ ነው፡፡


____________ 2. ለአንድ አገርም ሆነ ግለሰብ የዕድገት መሠረቱ ያለፉ ታሪኮችን ማውራት ነው፡፡
____________ 3. ቃልኪዳን የሚገባ ሰው አስቀድሞ አቅሙንና ችሎታውን ማገናዘብ አለበት፡፡
____________ 4. እራስን በኢኮኖሚ መቻል ጥቅሙ ለራስ ብቻ ነው፡፡
____________ 5. የማንኛውም የሥራ ውጤት የሚለካው በሥራ ጥራቱ ብቻ ነው፡፡

II. በ“ለ” ስር የተዘረዘሩትን በ“ሀ” ስር ካሉት ጋር አዛምድ/ጂ/፡፡


“ሀ” “ለ”
_______ 6. ቅይጥ ኢኮኖሚ ሀ. እያንዳንዱ ሠራተኛ ሊኖረው የሚገባ ባህሪ
_______ 7. የኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች ለ. አንድን ወንጀለኛ ወንጀል በመፈፀም ላይ እያለ የመያዝ ሁኔታ
_______ 8. ኃላፊነት ሐ. ለላቀ የሥራ ውጤት የሚሰጥ ማበረታቻ
_______ 9. የሙያ ሥነ-ምግባር መ. ግዴታን መወጣት
_______ 10. እጅ ከፍንጅ ሠ. ሁሉን ዜጎች በእኩልነት ተጠቃሚ የማድረግ ሁኔታ
_______ 11. ሽልማት ረ. የእዝ እና ገበያ ተኮር ኢኮኖሚ ድምር
ሰ. ጠላት ወይም ተቀናቃኝ

III. ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል ምረጥ/ጪ/፡፡

_______ 12. ሳይሰሩ ከመብላት ፍላጎት የሚመጣ ክብረ ነክ ተግባር _______ ይባላል፡፡
ሀ. በራስ መተማመን ለ. ጥገኝነት ሐ. ራስን መቻል መ. ስራን ማክበር
_______ 13. የበጎ ባህሪ መገለጫ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የበታችን መናቅ ሐ. ታላላቆችን ማክበር
ለ. የታመሙትን መጠየቅ መ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡
_______ 14. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት የልማት ዓላማን አስመልክቶ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጥቂት ግለሰቦችን ኢኮኖሚ ማሳደግ ሐ. የህዝብ መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት
ለ. ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ መ. የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ማስፈን
_______ 15. የኃላፊነትን ድርሻ በብቃት የሚወጡ ሰዎች ባህሪን የማይወክለው የቱ ነው?
ሀ. የተከበሩና በአርዓያነት የሚጠቀሱ ናቸው ሐ. የሥነ-ልቦና እርካታ አላቸው
ለ. ተአማኒነት አላቸው መ. ኢ-ተአማኒነት ባህሪ አላቸው
_______ 16. ራስን ለመቻልና ለመከበር የሚያበቃ ተግባር ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ችሎታን መገንዘብ ሐ. አቅም ማወቅ
ለ. ራስን መሆን መ. በሌሎች ሐሳብና ፍላጎት መመራት
_______ 17. ከሌሎች ለመማር ዝግጁ የሆነ ሰው?
ሀ. ጥገኛ ነው ሐ. የላቀ የሥራ ውጤት ለማምጣት ዕድል አለው
ለ. በራሱ የሚተማመን ሰው ነው መ. ለ እና ሐ መልስ ናቸው
_______ 18. በኢትዮጵያ ባህላዊ የቁጠባ ዘዴዎች ከዘመናዊ የቁጠባ ዘዴዎች በተሻለ መልኩ የተስፋፋበት ምክንያት፡-
ሀ. አመቺ የመንግስት ፖሊሲ መኖር
ለ. የዘመናዊ የቁጠባ ተቋማት አለመስፋፋት
ሐ. የህዝቡ ባህላዊ የቁጠባ ዘዴዎች የመጠቀም ፍላጎት መጨመር
መ. ባህላዊ የቁጠባ ተቋማት የተሻለ ወለድ መክፈል

IV. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ባዶ ቦታውን በተስማሚው ቃል ሙላ/ዪ/፡፡

19. የፍርድ ክርክር የሚካሄድበት መድረክ ____________________________ ነው፡፡


20. የቁጠባ አይነቶች ስንት ናቸው? ______________ ግለፅ/ጪ/፡፡

You might also like