You are on page 1of 3

አሳይ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የሕዝብ ት/ቤት

የ 2012 ዓ.ም ሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት ማጠናከሪያ ጥያቄ ለ 7 ኛ
ክፍል ክፍል-3

ስም___________________________ክፍል __________ ተ.ቁጥር_________


መመሪያ 1.የሚከተሉት ዐ.ነገሮች ትክክል ከሆኑ እውነት ስህተት ከሆኑ ሐሰት በማለት መልስ(ሽ)፡፡
1. እውቀት ከሚቆጠቡ ነገሮች አንዱ ነው፡፡
2. ስስታም ጥሩ የሆነ የቁጠባ ባህል ያለው ሰው ነው፡፡
3. በራስ አቅም መስራት የሚቻልን ነገር ከሌላ ሰው መጠበቅ የጥገኝነት ባህሪ ነው፡፡
4. በራስ የመተማመን ስሜትን ለማዳበር ትምህርት ቁልፍ መሣሪያ ነው፡፡
5. እያንዳንዱ ባለሙያ ሊላበሰው የሚገባ የሥራ ባህሪ የሙያ ብቃት ይባላል፡፡
መመሪያ 2፡- ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ከ "ለ" ክፍል በመምረጥ ከ"ሀ" ክፍል ጋር በማዛመድ
የመልሱን ፊደል በተሰጠው ባዶ ቦታ ላይ በመፃፍ መልስ(ሽ)፡፡
ሀ ለ
6. በረጅም ጊዜ የሚታይ ቁጠባ ውጤት ሀ. መሠረታዊ ፍላጎትን ማሟላት
7. ሐብትን አስፈላጊ በሆነ ጊዜም አለማውጣት ለ. የጡረታ አበል
8. በትንሽ ጊዜ ብዙ ሥራ መሥራት ሐ. ስስት
9. አንዱ የገንዘብ ምንጭ መ. የቁጠባ ምንነት
10. በአጭር ጊዜ የሚታይ የቁጠባ ውጤት ሠ. ቋሚ ንብረት ማፍራት
ረ. የዓይነት ቁጠባ
ሰ. የጊዜ ቁጠባ
መመሪያ 3፡- ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ የመልሱን ፊደል በተሰጠው ባዶ ቦታ ላይ
በመፃፍ መልስ(ሸ).
11. የቁጠባ ባህል ለግለሰብ ያለው ጥቅም ምንድ ነው?
ሀ. ቁጠባ ለሀገር እንጂ ለግለሰብ አይጠቅምም
ለ. የቁጠባ ባህል ዕሴቶችን ጠብቆ ለማቆየት
ሐ. መሠረታዊ ግላጎትን ያለብክነት ለማሟላት
መ. ከወርሃዊ ገቢ እኩል ገንዘብ ለማትረፍ

12. የኮንትሮባንድ ንግድን በተመለከተ ትክክል የሆነው ትኛው ነው ?


ሀ. ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥገኝነት ነው
ለ. የሀገርን ገቢ ከፍ ያደርጋል
ሐ. የዋጋ መዋዠቅን ያረጋጋል
መ. የሥራ አጥነትን ችግር ይቀርፋል
13. ለላቀ የሥራ ውጤት ክብር መስጠትን በተመለከተ ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. መሠረቱ አንድ ሰው የሚኖረው ትጋት ነው
ለ. በውስጡ የውድድር ስሜትን የያዘ ነው
ሐ. ሥልጡን የመሆን ምልክትና ውጤታማ ሰዎችን እንዲበረታቱ ያደርጋል
መ. ለላቀ የሥራ ውጤት ለራስ ብቻ የሚጠቅም ሥራ ማከናወኑ ነው
14. ከሚከተሉት አንዱ የዓይነት ቁጠባን አያመለክትም
ሀ. እንስሳትን ማርባት
ለ. ንብረቶችን ገዝቶ ማስቀመጥ
ሐ. በትንሽ ጊዜ ብዙ ሥራ መሥራት
መ. ተክሎችን መትከል
15. በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ጠንካራ የቁጠባ ባህል አለመኖር ምን ችግር ያስከትላል?
ሀ. የስስታሞችን ቁጥር ይቀንሳል
ለ. ዜጎች መሠረታዊ ነገሮችን በርካሽ ይገዛሉ
ሐ. ባንኮች ያለወለድ ያበድራሉ
መ.ኢንቨስትመንትን ያቀጭጫሉ
16. "የአበሻ ቀጠሮ" የሚለው አባባል መልክት ምንድ ነው?
ሀ. ሐበሻ የራሱ የሆነ የቀጠሮ ባህል አለው ማለት ነው
ለ. በኢትዮጵያ ለጊዜ ብዙም ትኩረት የማይሰጥ መሆኑን ያመለክታል
ሐ. ጊዜ ሁሉ ቆሞ ስለመይጠብቀን በቁጠባ መጠቀም አለብን ማለት ነው
መ. ሓበሻ ቀጠሮ አክባሪ ነው ማለት ነው፡፡
መመሪያ 2፡ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን ቃል ወይም ሐረግ በተሰጠው ባዶ ቦታ ላይ በመፃፍ
መልስ(ሸ)
17. ሦስቱ ዋና ዋና የቁጠባ ዓይነቶች______________________:_________________
ና________________________ናቸው፡፡

18. አንድን ስራ በተገቢው ጊዜ በተፈለገው ወቅትና ብዙ ሥራን በትንሸ ሰዓት ማከናወን


___________________________ይባላል
19. ለራስ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በራስ አቅም ማሟላት__________ ይባላል፡፡

መመሪያ 3፡አጭር መልስ


20. ገንዘብን በባንክ መቆጠብ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ ሁለት ምሳሌዎችን ፃፍ(ፊ)
____________________________________________________________
____________________________________________________________

አዘጋጅ፡- ድባቡ ወርቄ

You might also like