You are on page 1of 3

ኤስ ኦ ኤስ ኸርማን ግማይነር ት/ቤት፣ ባህር ዳር

በ 2012 ዓ.ም. የአምስተኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ ትምህርት በቤት ውስጥ የሚሰሩ ተግባራት።

የተከበራችሁ ተማሪዎች እና ወላጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በመቀጠል ተማሪዎች በሁለት ሳምንታት የምትሰሯቸው
ተግባራትን ልኬያለሁ። የመጀመሪያው ተግባር በደብትራችሁ የምትሰሩት ሲሆን ወደ ት/ቤት እንደተመለሳችሁ ታርሞ ውጤቱ
ይያዛል። ሁለተኛው ግን ሰርታችሁ ከ _____________________ ባለው ጊዜ በወረቀት/በቴሌግራም የምትመልሱት ነው።
በደብተራችሁ የምትሰሯቸውን መልመጃዎችም ሆነ የሚመለሰውን ጥያቄ በመጀመሪያው ዙር ከላኩላችሁ ማስተዋሻ ማጣቅሻ
መጠቀም ትችላላችሁ። በተጨማሪ መጽሐፋችሁ በየመልመጃዎች የተሰጡትን ምሳሌዎች በደንብ ተመልከቱ።

ኣላማዎች፣ ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፦


 የንባብ እና የጽህፈት ክህሎታቸውን ያዳብራሉ፣
 ለቃላት ተመሳሳይ ፍቺ ይሰጣሉ፣
 ለቃላት ተቃራኒ ፍቺ ይሰጣሉ፣
 የስም ገላጮችን ይለያሉ፣
 ከስርኣተ ነጥብ አይነቶች አንድ ነጥብን ተጠቅመው ቃላትን ያሳጥራሉ ፣
 የስም አይነቶችን ይለያሉ፣
 ስለኮሮና ቫይረስ ያላቸውን ግንዛቤ ይገልጻሉ።
ትእዛዝ 1፦ የአጋዘን አስተኔ የሚለዉን ምንባብ ደጋግማችሁ አንብቡ።ምንባቡን ከተረዳችሁት በኋላ የሚከተሉትን
መልመጃዎች በደብተራችሁ ስሩ።
u ገጽ 133፣ተግባር 1፣የአጋዘን አስተኔ ዝርያዎችን በሰንጠረዡ ጻፋ።
u ገጽ 133፣ተግባር 2፣ ከ ሀ - ሠ ያሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሠረት በጽሁፍ መልሱ።
u ገጽ 134፣ተግባር 1፣ቃላትን ከተመሳሳያቸው ጋር አዛምዱ።
u ገጽ 134፣ተግባር 2፣አጋዘን አስተኔ ከሚለው ምንባብ ውስጥ ቀለምን የሚገልጹ ቃላትን ዘርዝሩ ።
u ገጽ 135 ተግባር 1 አንድ ነጥብን በመጠቀም በአሀዝ(ቁጥር)ፃፉ።
ተግባር 2 ሙሉና ሽርፍራፊ ቁጥሮችን በፊደል ፃፉ።
ገጽ 138 ተግባር 1 በዐረፍተ ነገሮች ውሰጥ ያሉትን ባለቤቶች ለዩ።
ትዕዛዝ-2 ገጽ 139 ዋልያና ቀይ ቀበሮ የሚለውን ምንባብ ደጋግማችሁ ካነበባችሁ በኋላ ከስር የቀረቡትን መልመጃዎች
በደብተራችሁ ሰሩ።

 ገጽ 141 አንብቦ መረዳት፣ ተግባር 1 ከ ሀ-ተ ያሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሠረት በቃላችሁ ስሩ።
 ገጽ 142 በአንቀጽ ዉሥጥ የተጓደሉ ቃላትን ማሟላት በሚለው ርዕስ ስር የቀረበውን አንቀጽ
በተሠጡት ቃላት አሟልታችሁ ጻፉ።
 ገጽ 144 ሰዋሰዉ፣ተግባር አንድ እና ሁለትን በደብተራችሁ ስሩ።

ትዕዛዝ 3 ገጽ 145 በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ይዞታ የሚለውን ምንባብ በለሆሳስ አንብቡ። ከሥር የቀረቡትን
መልመጃዎች ሥሩ።

 ከገጽ 148-149 የተሠጧችሁን ተግባር 1 ና ተግባር 2 በምንባቡ መሠረት በቃላችሁ ሥሩ።


 ገጽ 150 ለቃላት ተመሳሳይ ፍች ከሠጣችሁ በኋላ እንደገና ዐ.ነገር ሥሩ። ከመልመጃው በፊት ምሣሌ
ተሠርቶላችኋል።
 ገጽ 153 ሰዋሰው፣የውልና የተጸውዖ ሥሞች እንደ ባለቤት በሚለው ሥር ያሉትን ተግባራት አንድ እና
ሁለትን ሥሩ።
አመሰግናለሁ፤እግዚአብሔር በሠላም ያገናኘን። አሜን።!!
አዘጋጅ፦ ገዳሙ ተረፈ

1
ኤስ ኦ ኤስ ኸርማን ግማይነር ት/ቤት፣ ባህር ዳር
በ 2012 ዓ.ም. የአምስተኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ ትምህርት በቤት ውስጥ ተሰርቶ የሚመለስ።
በደብተራችሁ የምትሰሯቸውን መልመጃዎችም ሆነ የሚመለሰውን ጥያቄ በመጀመሪያው ዙር ከላኩላችሁ ማስተዋሻ ማጣቅሻ
መጠቀም ትችላላችሁ። በተጨማሪ መጽሐፋችሁ በየመልመጃዎች የተሰጡትን ምሳሌዎች በደንብ ተመልከቱ።

የመመለሻ ጊዜ -
ስም__________________________________ ክፍል ______________ ቁጥር __________
የተፈቀደ ሰኣት፡ 50 ደቂቃ
ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች እንደየትእዛዛቸው በጥንቃቄ በማንበብ ሰርታችሁ መልሱ።
ወቅታዊ ጥያቄዎች 3%
1. የኮቪድ 19 ቫይረስ መንስኤው ምንድን ነው?____________________________________________
___________________________________________________________________________
____________________________________________________________________________
2. “C O V ID 19” የሚለውን ምህጻረ ቃል ትንትናችሁ ጻፉ።_________________________________
___________________________________________________________________________
3. ኮቪድ 19 ቫይረስ የሚተላለፍባቸውን መንገዶችን
ዘርዝሩ።________________________________________
______________________________________________________________________________
_______________________________________________________________________________

መመሪያ አንድ:-ከዚህ ቀጥሎ ለቀረቡት ቃላት ተመሳሳይ ፍቺ ስጡ። 10%


1. መሸመት ____________ 6. ችላ አለ ______________
2. ሰበብ ____________ 7. ነሲብ ______________
3. ማዕበል _____________ 8. አርኣያ _______________
4. መርህ _____________ 9. ተያቢ ________________
5. አኮቴት _____________ 10. ቧጋች _______________

መመሪያ ሁለት:- ከዚህ በመቀጠል ለቀረቡት ቃላት ተቃራኒ ፍቺቻውን ስጡ።10%


1. በኩር _________________ 6. ጊዜያዊ _________________
2. ህልም ________________ 7. ትሁት __________________
3. ገለባ __________________ 8. መረቀ __________________
4. ድል __________________ 9. ደፋር ___________________
5. ጊደር __________________ 10. ጠብ ____________________

መመሪያ ሦሥት:- ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ስሞች የወል፣የተጸውዖ፣የረቂቅ ስም በማለት ለዩ።6%


በሬ እሁድ ደስታ
ሄለን ሰው መጽሐፍ
አቢያታ ባሮ ሚያዚያ
ፖሊስ ነፋስ ወረቀት
ውሸት ሰይፋ ሠላም
2
የወል ስም የተጸውዖ ስም የረቂቅ ስም
1.____________ 1. ______________ 1. _______________
2.____________ 2. ______________ 2. _______________
3.____________ 3. ______________ 3. _______________
4.____________ 4. _______________ 4. ________________
5. ___________ 5. _______________ 5. ________________
6.____________ 6. ________________ 6. _________________
መመሪያ አራት፦ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።3%
1) 1.5 የሚለው ቁጥር ወደ ብር እና ሳንቲም ለውጠን ብናነበው የሚሰጠን ትርጉም የትኛውን ነው
ሀ. አንድ ብር ከአምስት ሳንቲም
ለ. አንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም
ሐ. አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር
2) “ሄደ” በሚለው ውስጥ ባለቤት ሊሆን የሚቼለው የቱ ነው
ሀ. እሱ ለ. ሄደ ሐ. እሱ መ. ባለቤት የለውም
3) አስቴር እና ዓለሙ ይትባረክ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ናቸው።የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት........... ነዉ።
ሀ. አስቴር ለ. ዓለሙ ሐ. አስቴር፣ዓለሙ፣ይትባረክ መ. አስቴር እና ዓለሙ ይትባረክ
4) ካሣ የገዛው በግ ታረደ።የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት........ ነው።
ሀ. ካሣ የገዛው በግ ለ. ካሣ ሐ. ታረደ መ. በግ
አዘጋጅ፦ ገዳሙ ተረፈ
0913436554

በቀጣይ ከምዕራፍ ስምንት የወጡ ጥያቄዎችን እልካለሁ። ማንኛውንም ጥያቄ ከላይ ባስቀመጥኩላችሁ ስልክ ወይም
gedterefe@gmail.com ወይም በቴሌግራም sosbahirdar ላይ መላክ ትችላላችሁ።

እግዚአብሔር በሠላም ያገናኘን።

You might also like