You are on page 1of 1

2015 ዓ.

ም የአብዮት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ 1 ኛ ወሰነ ትምህረት የ 3 ኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ ማጠቃለያ ፈተና (የማታ)
የሚይዘዉነጥብ 20 የተሰጠው ሰአት 30’ የጥያቄ ብዛት 20
ስም _______________________________________________ ክፍል ____________ ቁጥር______________
I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትክክል ካነበባችሁ ትክክል የሆነውን”እውነት” ስህት የሆነውን ደግሞ “ሀሰት” በማለት መልሱ
_______________1.ኬክሮስና ኬንትሮስ ፍፁማዊ መገገኛን ለመግለጽይጠቅማል፡፡

_______________2. አኩሪ ዘተርና ተልባ የአትክልትና ፍራፍሬ ምሳሌ ናቸው፡፡

_______________3. ቦሌ ክፍለ ከተማ በስተሰሜን አዲስ አበባ ይገኛል፡፡

_______________4. ማንኛውም ነገር ቦታ ሊይዝ የሚችልና መጠነዉስ ያለው ነገር ቁስ አካል ይባላል፡፡

_______________5. ምግብን ማድረቅ ሳይበላሽ ረዘም ላለ ጊዜ ለማቆየት ይጠቅማል፡፡


II. በ”ሀ” ስር ለተዘረዘሩት የምግብ ምድቦች በ”ለ” ከተዘረዘሩት ጠቀሜታቸው ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”

________1. ስጋ ሀ. በሽታን ለመከላከል

________2. ወተትና የወተት ውጤቶች ለ. ለእድገት ይጠቅማል

________3. አትክልትና ፍራፍሬዎች ሐ. ሀይልና ሙቀት ይሰጣል

________4. እህልና ጥራጥሬዎች መ. ሰውነትን ለመገንባት


III. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘዉን ፊደል በመምረጥ በክፍት ቦታው ላይ ፃፍ/ፊ፡፡
---------1. ፈሳሽ ወደ ጋዝ የሚቀየርበት ሂደት -------- ነዉ፡፡
ሀ. ብርደት ለ. ቅልጠት ሐ. ትነት መ. ማጥለል
---------2. ከሚከተሉት መካከል በምግብ ብክለት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነዉ፡፡
ሀ. ኮሌራ ለ. ወስፋት ሐ. ተቅማት መ. ሁሉም
---------3. ከሚከተሉት መካከል አንዱ በምግብ ብክለት መከላከያ ዘዴ ነዉ ፡፡
ሀ. ፀጉር መሸፈን ለ. ማሸግ ሐ. ማቀዝቀዝ መ. ጫዉ መነስነስ
----------4. ከሚከተሉት ዉስት ጠጣር የሆነዉ የቱ ነው?
ሀ. ዳቦ ለ. ሻይ ሐ. ዘይት መ. ቤንዚን
----------5. የኬንትሮስ አጠቃላይ ልኬት በድግሪ ሰንት ነዉ?
ሀ. 90 ለ. 180 ሐ. 360 መ. 0
----------6.ቅርጽም ሆነ ይዘት ያለዉ ቁስ አካል ምን ይባላል?
ሀ. ጠጣር ለ. ጋዝ ሐ. ፈሳሽ መ. ዘይት
IV. ለባዶ ቦታዉ ተሰማሚ የሆነ መልስ ሙሉ
1. ዜሮ ድግሪ ኬንትሮስ መሬትን ምስራቃዊና ምእራባዊ ንፍቀ ክበብ በማለት የሚከፍል ---------------------ነዉ::
2. ማንኛዉም ሊጠጣ ወይም ሊበላ የሚችል ነገር ሁሉ ----------------ይባላል::
V. ለሚከተሉት ጥያቄ አጭር መልስ ስጡ
1. የቁስ አካል ሁነቶችን ዘርዝሩ::

2. ቁስ አካል ከሚባሉት መካከል ቢያንስ 4 ቱን ጥቀሱ::

3.መሰረታዊ አቅጣጫዎች የሚባሉት ምን ምን ናቸዉ?


አዘጋጅ፤ መምህር ብርሃነመስቀል

You might also like