You are on page 1of 5

የተፈቀደው ጊዜ 60 ደቂቃ

ስም _________________________________________ክፍል___________ቁጥር__________

ሀ/ የሚከተሉተን ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ዐረፍተ ነገሮቹ የያዙት ሀሳብ ትክክል ከሆነ ‹‹እውነት ›› ስህተት
ከሆነ ደግሞ ‹‹ ሐሰት ››በማለት በተሠጠው ክፍት ቦታ ላይ ፃፉ 12 ማርክ አለው፡፡

1. የስልጣን ገደብ ለዜጎች ለህይወታቸውና ለንብረታቸው ህጋዊ ጥበቃና ዋስትና ይሰጣል።

2. የአካል ጉዳተኞችን ማግለል ቤተሰብን እንጂ ሀገር አይጎዳም ፡፡

3. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት የስልጣን አካላት በሁለት ይከፈላሉ፡፡

4. ነፃ የፖለቲካ ስልጣን ውድድር ማንኛውም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

5. በፌደራል ሥርአት በሚተዳደሩ ሀገሮች ውስጥ ከአንድ በላይ ህገ መንግስታት ይኖራሉ፡፡

6. ህገ ወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ አለመቃወም የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫ ነው፡፡

7. ለሙስና መፈፀም ምክንያት ከሆኑት ነጥቦች መካከል ግልፅ የሆኑ ህጎች አለመኖራቸው ነው፡፡

8. የአዲሱ የሀገር ፍቅር ስሜት መገለጫ ከሆኑት መካከል አንዱ አርያነት ያለው ተግባር መፈፀም ነው፡፡

9. የፍትህ አካላት በሦስት ዋናዋና ደረጃዎች ይከፈላሉ፡፡

10. ችግሮችን በውይይት መፍታት በሠላም አብሮ ለመኖር ጠቀሚ እሴት ነው፡፡

11. የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ እውን የሚሆነው በመንግስት በጎ ፈቃድ ብቻ ነው፡፡

12. የሰው ልጅ ሰው ሆኖ በመፈጠሩ በተፈጥሮ የሚያገኛቸው ነፃነቶች ሰብዓዊ መብቶች ይባላሉ፡፡

ለ/የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካማንበብ በኋለ በ‹‹ሀ›› ስር ለተዘረዘሩት ከ‹‹ለ›› ሥር ካሉት አንቀፆች ጋር አማዛመድ 5
መርክ አለው።

‹‹ሀ›› ‹‹ለ››

13.ግለሰባዊ ክብርና የመንፍስ ጥንካሬ መለኪያ ነው፡፡ ሀ) ሃላፊነት

14.ሁሉንም ዜጎች በእኩል ተጠቃሚ ማድርግ ለ.ቃል ኪዳን

15.የሙያ ስነ ምግባር ሐ) የሙያ አሰራር መከተል

16. በግልና በጋራ የሚፈፀም የተግባር ክዋኔ መ.ሙያው የሚጠይቀውን ክህሎት

17. የሙያ ችሎት ሠ) የኢኮኖሚ ነክ ዓላማ

1
መ/ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ በ‹‹ሀ›› ስር የተዘረዘሩትን ከ‹‹ለ››ስር ካሉት ቃላት ወይም
ሐረጎች ጋር በማዘመድ በተሠጠው ክፍት ቦታ ላይ ፃፉ 16 መርክ አለው፡፡

‹‹ሀ›› ‹‹ለ››

18. መረጃ ሀ. እውቀትን መሻት

19. ቅድመ ንባብ ለ. ሳይንሳዊ መሰረት የሌላቸው

20.ኋላቀር አስተሳሰብ ሐ.ትምህርት ቤት

21. እውቀትን መሻት መ.ላቅ ያለ እውቀት ለማግኘት ይጠቅማል

22. ጥናትና ምርምር ሠ. ጋዜጣና ሬዲዮ

23. የእውቀት ዋነኛ ምንጭ ረ. ስለ ራሳችንና ስለአካባቢያችን ያለንን ግንዛቤ

24. የመረጃ ምንጮች ሰ. ዋናን መረጃ ለማግኘት ይጠቅማል

25. የገረፍ ገረፍ ንባብ ሸ.ለንባብ ራስን ማዘጋጀት

መ) የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካነበባቹ በኋላ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል በመምረጥ በመልስ

መስጫ ቦታ ላይ ሙሉ 13 መርክ አለው።

26. .ከሚከተሉት ውስጥ በራስ መተማመን ለማጎልበት የሚጠቅመው የትኛው ነው?

ሀ.የራስን ችሎታ አለማወቅ ለ. እውነታን መቀበል

ሐ.ራስን አለመገምገም መ.አንድን ሥራ በእቅድ አለመስራት

27. ከሚከተሉት የቁጠባን ባህል ለማዳበር የሚረዳው የቱ ነው ?

ሀ.ፍላጎትን ከገቢ ጋር ማጣጣም

ለ. ከገቢ በላይ መጠቀም

ሐ.መሠረታዊ ፍላጎትን በመቀነስ የተገኘውን ሁሉ መቆጠብ

መ.የተገኘውን ገቢ ሙሉ በሙሉ መጠቀም

2
28. ከሚከተሉት ቁጠባን በትክክል የሚገልፀው የትኛው ነው ?

ሀ.በተገኘ ገቢ በአግባቡ በመጠቀም ለወደፊት የሚሆን ገንዘብና ንብረት ማስቀመጥ

ለ.ለዛሬ ከሚያስፈልግ ነገር ለነገ ማሳደር

ሐ.ከቤተሰብ መሠረታዊ ፍላጎት በመቀነስ መቆጠብ

መ.አንድ ሰው መቆጠብ ያለበት የግል ሀብቱንና ንብረቱን ብቻ መሆን አለበት

29. በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረተና በተግባር የተፈተነ አሳማኝ ነገር ምን ይባላል?

ሀ.ግምት ለ. አስተያየት ሐ. መላ ምት መ.ተጨባጭ እውነታ

30. በራስ እውቀት ፣ክህሎትና አቅም መፈፀም የሚቻልን የራስን ጉዳይ የሌሎችን ድርሻ ሳይጠብቁ በራስ
የመፍታት ችሎታ ምን ይባላል ?

ሀ. ራስን መቻል ለ. የጥገኝነት ስሜት ሐ. የሀላፊነት ስሜት መ. የተረጅነት ስሜት

31. ከራስ አቅም በላይ ባልሆኑ ጉዳዮች የሌሎችን የሃሳብና እውቀትና ድጋፍ የሚፈልግ ግለሰብ ባህሪ?

ሀ.በራስ መተማመን ለ. ለራስ ተገቢ ክብር መስጠት ሐ. የጥገኝነት ስሜት መ. ራስን ማወቅ

32. ከሚከተሉት ውስጥ የንቁ ሕዝባዊ ተሳትፎ ምሳሌ የሚሆነው የትኛው ነው?

ሀ.በሕዝባዊ አጀንዳዎች መሳተፍ ለ. በአካባቢ ልማት ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን መሳተፍ

ሐ.ህዝባዊ እና ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ መ. ሁሉም መልሶች ናቸው

33. የዜጎችን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የሚቋቋሙ አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምን ተብለው
ይጠራሉ ?

ሀ.መንግስታዊ ድርጅቶች ለ.የንግድ ድርጅቶች

ሐ. ሲቪክ ማህበራት መ. የህብረት ስራ ማህበራት

34. በአንድ ወቅት ተቀባይነት የነበረው ከጊዜ በኋላ ግን ተቀባይነትን ያጣ ወይም በተጨባጭ ማስረጃ ላይ
ያልተመሰረተ አስተሳሰብ ምን ይባላል?

ሀ. ተቀባይነት ያለው አስተሳሰብ ለ.ዘመናዊ አስተሳሰብ ሐ. ኋላቀር አስተሳሰብ

መ.በእውቀት ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ

3
35. ከሚከተሉት ውስጥ የሕዝብን ሠላም ሊያውክ የሚችለው የትኛው ነው?
ሀ.በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ወሬ ለ. የሳይንሳዊ አስተሳሰቦች መስፋፋት

ሐ.የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት መ.ኋላቀር አስተሳሰቦች መወገድ

36. የሲቪክ ማህበራት ከሌሎች ድርጅቶች የሚለይበት ባህሪ ያልሆነው?

ሀ.የግል ጥቅምን መሰረት አድርጎ አለመደራጀት

ለ.ለትርፍ ሳይሆን ሌሎችን ለመርዳትና ለማገልገል መደራጀት

ሐ. ከሃይማኖታዊና መንግስታዊ አመለካከት ነፃ አለመሆን

መ.በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የጋራ ዓላማ ይዞ መደራጀት

ሠ/የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ከፍት ቦታውን በተገቢው ቃል ወይም ሐረግ ሙሉ 4 ማርክ
አለው፡፡

37. .------------- አንድን ስራ ለመስራት የሚነደፍ የአሰራር ስልት ነው?

38. አንድ ሀገር ከሌላ ሀገር ጋር የምታደርገው ግንኙነት ፖሊሲ------------- ይወሰናል?

39. --------------ዜጎች በአካባቢያቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው?

40.ሀገርን እንደራስ አድርጎ የመውደድ ስሜት ምን--------------- ይባላል?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

4
የመልስ መስጫ ቦታ

ስም ---------------------------------------- ክፍል ---------

እውነት ወይም ሀሰት አዛምድ ክፍል 1 ምርጫ ባዶ ቦታ ሙሉ

1. ------------ 13.----------- 27.----------- 37.---------------------


2. ------------ 14.----------- 28.----------- 38.---------------------
3. ------------ 15.----------- 29.----------- 39.---------------------
4. ------------ 16.----------- 30.------------ 40.-----------------------
5. ------------ 17.----------- 31.-----------
6. ------------ ክፍል 2 32.-----------
7. ------------ 18.----------- 33.----------
8. ------------ 19.----------- 34.-----------
9. ------------ 20.----------- 35.-----------
10. ------------ 21.----------- 36.----------
11. ------------ 22.------------
12. ------------ 23.------------
24. -----------
25.------------
26.------------

ከሚከተሉት ውስጥ የሕዝብን ሠላም ሊያውክ የሚችለው የትኛው ነው?


ሀ.በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ወሬ ለ. የሳይንሳዊ አስተሳሰቦች መስፋፋት

ሐ.የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት መ.ኋላቀር አስተሳሰቦች መወገድ

You might also like