You are on page 1of 9

ስም ክፍል ቁጥር

ሀ/ የሚከተሉተን ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ዐረፍተ ነገሮቹ የያዙት ሀሳብ ትክክል ከሆነ ‹‹እውነት ›› ስህተት
ከሆነ ደግሞ ‹‹ ሐሰት ››በማለት በተሠጠው ክፍት ቦታ ላይ ፃፉ፡፡ እያንዳንዱ ጥያቄ 2 ማርክ አለው የተፈቀደው 1 ሰዓት

1. ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እርስ በእርስ የሚዛመዱ ፅንሰ ሀሳቦች ናቸው፡፡

2. የዜጎች የግልና የቡድን መብቶች ከአድሎ በፀዳ መልኩ መከበሩ ለሀገር ፍቅር ስሜትን ከፍ ያደርጋል፡፡

3. ሕገ መንግስት ስልጣንን፣ ሀላፊነትና የስልጣን ገደብን ለይቶ አያስቀምጥም፡፡

4. የሀገራችን የመንግስት አወቃቀር ፌደራላዊ በመሆኑ ከአንድ በላይ ሕገ መንግስት አሉት፡፡

5. ለመንግስት ባለስልጣናት ሥልጣንና ሀላፊነት በህግና ደንብ ተዘርዝሮ መሰጠቱ የዴሞክራሲ ስርአት መለያ

አይደለም፡፡

6. እኩልነት ሲባል ሚዛናዊ አሠራሮችን መከተልና መሠረታዊ መብቶችና ጥቅሞችን ማስጠበቅ ነው፡፡

7. ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተመሳሳይነት እንጂ ልዩነት የላቸውም፡፡

8. ሕገመንግስት ዜጎች በመብታቸው እንዲጠቀሙ እንጂ ግዴታቸውን አያስቀምጥም፡፡

9. የክልል ሕገ መንግስታት የፌደራልን ሕገ መንግስት ሊተኩ አይችሉም፡፡

10. የክልሎችን ሕገ መንግስት የሚያወጣው ከፍተኛው የፌደራሉ የተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡

ለ/የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካነበባቹ በኋለ በ‹‹ሀ›› ስር ለተዘረዘሩትከ‹‹ለ›› ሥር ካሉትአንቀፆች ጋር በማዛመድ በተሰጠዉ


ክፍት ቦታ ላይፃፉ፡፡(እያንዳንዱ ጥያቄ 1 ማርክ አለው)

‹‹ሀ›› ‹‹ለ››

11. የመምረጥና መመረጥ መብት ሀ. ዴሞክራሲያዊ መብቶች

12. በሕይወት የ መኖር መብት ለ. ሰብአዊ መብቶች

13. መንግስት የሚያወጣው አጠቃላይ ሕግ ሐ. ፖሊሲ

14. ከፍተኛ የመንግስት የ ስልጣን አካል መ. የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች/ም/ቤት

15. መልካም ጉርብትና ፣ወንድማማችነት ሠ. የውጭ ግንኙነት ፖሊሲመሠረቶች

አዘጋጅ፡ 1
16. በትውውቅና በዝምድና መስራት ረ. በሰዎች መካከል ልዩነት መፍጠር

17. በሁለት ሰዎች መካከል የሚያዝ ጉዳይ ቀ. የጓደኛ ሚስጥር


18. የዜግነት ግዴታ ሰ. ፌደራላዊ ስረዓት

19. በክልል መንግስታት የተዋቀረ ሸ. ግብር መክፈል

20. አድሏዊ አሰራር በ. ሙስና

ሐ/የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ትክክለኛውን መልስ የያዘውን ፊደል በመምረጥ በተሠጠው ቦታ
ላይ ፃፉ፡፡( እያንዳንዱ ጥያቄዎች 1 ማርክ አለው)

21.ተገቢነት ያለው ሚዛኑን የጠበቀ፣ትክክለኛ የሆነ ምን


ይባላል?

ሀ.አድሎ

ለ.ሙስና

ሐ.ፍትሐዊነት

መ.መልሱ የለም
22.አንድን ስራ ለመስራት ፣ለማሰራት ፣ለመፈፅም ፣ለማስፈፀም የሚያስችል ሀይል ወይም መብት ምን
ይባላል?

ሀ.ገንዘብ

ለ. ስልጣን

ሐ. መሳሪያ

መ. ሁሉም መልሶች ናቸው

23. የማንኛውም የስልጣን ገደብ የሚካተተው በምን ነው?

ሀ. በደንብ

ለ. በሕግ

ሐ. በመመሪያዎች

መ. በህገ መንግስት
አዘጋጅ፡ 2
24. የዴሞክራሲያዊ ስርአት ጠቀሜታን የማይገልፀው የቱ ነው ?

ሀ.አድሎያዊ አሰራርን ያባብሳል

ለ. በህዝቦች መካከል የሚታዩ ልዩነቶችን የሚያስፋፋ መሆኑ

ሐ. በህዝቦች መካከል አንድነትን ይሽረሽራል

መ. ሁሉም መልሶች ናቸው

25.የክልል ሕገ መንግስታት አስፈላጊነትን የማይገልፀው የቱ ነው?

ሀ.የራሳቸውን ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተመርኩዘው ህጎችን ለማዘጋጀት

ለ. የራሳቸውን ሀብት ለማስተዳደርና ለመጠቀም ያስችላል

ሐ.ፍትህንና ሌሎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በቅርበት ለማግኘት

መ.መልሱ አልተሠጠም

26. ከሚከተሉት መካከል መሠረታዊ የእኩልነት መብት ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ.የሃይማኖት እኩልነት

ለ.የቋንቋ እኩልነት

ሐ.የፆታ እኩልነት

መ.መልሱ አልተሰጠም
27. በሕዝብ ተመራጮች ላይ የስልጣን ገደብ መጣል የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

ሀ.የሕዝብ አደራን ለማስጠበቅ

ለ. የዜጎች መብት እንዳይጣስ

ሐ. አድሎአዊ አሰራርን ለማስፋፋት

መ.ሀ እና ለ መልሶች ናቸው

28.ሕግን አለማክበር ከሚያስከትለው ጉዳት ውስጥ የማይካተተው የቱ ነው ?

አዘጋጅ፡ 3
ሀ. ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ያጠናክራል

ለ. ንብረት የማፍራትና የመጠቀም መብትን ያጠናክራል

ሐ.የዴሞክራሲ ስረአትን ያደክማል

መ. ሁሉም መልሶች ናቸው


29. ---------የሰዎችን ድርጊት ትክክል፣ወይም ስህተት፣ጥሩ ወይም መጥፎ ነው ብለን የምንለካበት መሣሪያ ነው፡፡
ሀ. ሕግ ለ. ሥነ ምግባር ሐ. የስልጣን ገደብ መ. ሁሉም መልሶች ናቸው
30. በከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ሊፈፀሙ የሚችሉ የሙስና አይነቶች ውስጥ ሊካተት የሚችለው የቱ ነው
ሀ.የመንግስትና ንብረትን ለግል ጥቅም ማዋል
ለ. አረጋውያንና አካል ጉደተኞችን በቅድሚያ ማስተናግድ
ሐ.የመንግስትን ንብረት ለሕዝብ ጥቅም ማዋል
መ. ለ እና ሐ መልሶች ናቸው
31. ከሚከተሉት ውስጥ መሠረታዊ የእኩልነት መብት ያልሆነው የቱ ነው ?

ሀ.የቋንቋ እኩልነት ለ. የፆታ እኩልነት ሐ.የሃይማኖት እኩልነት መ.መልሱአልተሠጠም

32. ከሚከተሉት መካከል በአገልግሎት ሰጪነቱ ልዩ የሆነው ተቋም የቱ ነው?


ሀ. ፍርድ ቤት ለ. ትምሀርት ቤት ሐ. ጤና ጣቢያ መ. ቀበሌ

33. በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ሕገ መንግስት ስለ አካል ጉዳተኞች መብት የተገለፀው አንቀፅ ስንት ነው?
ሀ. አንቀፅ 51 ለ.አንቀፅ 41 ሐ. አንቀፅ 45 መ. አንቀፅ 42
34.የእኩልነትና እኩል ተጠቃሚነት መብቶች መከበር የሚያስገኘው ጠቀሜታ?

ሀ.የዜግነት ስሜትን ያሰድጋል

ለ.የሀገርን እድገትያፈጥናል

ሐ. የተቆርቋሪነት ስሜትን ይፈጥራል


መ.ሁሉም

35. ከሚከተሉት መካከል የግብር ምንጭ የሆነው የቱ ነው?


ሀ. እርሻ ለ. ደመወዝ ሐ. ንግድ መ. ሁሉም መልስ ናቸው

አዘጋጅ፡ 4
መ/ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በተገቢው ቃል ወይም ሐረግ ሙሉ፡፡( እያንዳንዱ ጥያቄዎች 1 ማርክ አለው)

36. ከህብረተሰቡ ተሰብስቦ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ---------------- ይባላል።

37. ማንኛውም ሰው ከህግ በታች መሆኑን የሚገልፅ ሀሳብ ----------------- ይባላል።

38. አገልግሎት ሰጪ ተቋማትለህብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት -------- ሊሆን ይገባል

39. ህብረተሰቡ የሚቀበለው ማንኛውም በጎ ምግባር------------- ይባላል

40 ህግን ለማስከበር መጀመሪያ ------------ ማክበር ያስፈልጋል

አዘጋጅ፡ 5
አዘጋጅ፡ 6
አዘጋጅ፡ 7
አዘጋጅ፡ የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ክፍል 3
አዘጋጅ፡ የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ክፍል 4

You might also like