You are on page 1of 5

Magaala Shaggar Kutaa Magaala Laga Xaafoo Laga Daadhii Waajjira Kutaa Magaalaa Duuba.

Shagger City Adm. Lege Tafo Lege Dadi Sub City at the Back of Sub –City Office
በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ጀርባ
 011-86 84 024 0911-50 31 18 ,0913- 17 29 13, 0912- 11 95 12 Email. rehobot @gmail.com
የ 2015 ዓ.ም የ 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የሞዴል ፈተና

ስም --------------------------------------------------- ክፍል -------- መ.ቁ/code/004

መመሪያ 1፡:: በጅምር የቀሩትን ምሳሌያዊ አነጋገሮች የሚያሟሉትን አባባሎች ምረጥ/ጭ፡፡

1. ቀጥኜ ቢያየኝ ---------------------------

A. ናቀኝ B. ሳቀብኝ C. ዛተብኝ D. ጅማት ለመነኝ
2. ሲሮጡ የታጠቁት
-----------------------
A. ይወልቃል B. ሲሮጡ ይፈታል C. ይስማማል D. ይፈጥናል
3.
ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ -----------------------------

A. ለሃምሳ ሰው ጌጡ B. ለሃምሳ ሰው ያንሳል C. ለሃምሳ ሰው ያጣላል D. ለሃምሳ ሰው ቅምሻ ነው፡፡

መመሪያ 2፡ ተስማሚ የሆነውን አያያዥ ቃል ምረጥ/ጭ፡፡

4. ጎመን መመገብ የብረት ንጥረ ነገር ያስገኛል----------------- ጉበትን አያክልም፡፡

A. ስለሆነም B. እንዲሁም C. ይሁን እንጂ D. አለበለዚያ
5. አብዲሳ ጎበዝ እግር
ኳስ ተጫዋች ነው፤-------- ህዝቡ ይወደዋል፡፡
A. ስለሆነም B. አለበለዚያ C. ይሁን እንጂ D. ነገር ግን
6. ነፍሰጡሯ
ወንድ ---------------- ሴት መንታ ልጆች ተገላገለች፡፡
A. ወይም B. ሆኖም C. እና D. እንደ
መመሪያ 3 ፡ ከቀረቡት አማራጮች ልዩ የሆነው የቱ ነው?

7. A. ፓፓያ B. ብርቱካን C. ማንጎ D. ቲማቲም

8 A. ምንም B. ባዶ C. ጥቂት D. አልቦ
9 A. ጤፍ B. እህል C. ሽንብራ D. ገብስ

መመሪያ 4 ፡ ትክክለኛ ቦታው ላይ መግባት የሚችለውን ስርዓተ ነጥብ ምረጡ፡፡

10. ---- ትምህርት የዕድገት መሠረት ነው ---- አለ አየለ፡፡

A. ፡ B. ፣
C. ፤ D. “ ”
11. አጭበርባሪ ሌባ ጥፋልኝ ወዲያ -----------------

A. ፡፡ B. ፤ C. ! D. ፣

መመሪያ 5፡ ከታች ለቀረቡት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ምረጥ/ጭ፡፡

1
Magaala Shaggar Kutaa Magaala Laga Xaafoo Laga Daadhii Waajjira Kutaa Magaalaa Duuba.
Shagger City Adm. Lege Tafo Lege Dadi Sub City at the Back of Sub –City Office
በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ጀርባ
 011-86 84 024 0911-50 31 18 ,0913- 17 29 13, 0912- 11 95 12 Email. rehobot @gmail.com
12. የአንቀጽን ዋና ሀሳብ ጠቅልሎ የሚይዘው ምን ይባላል?
13. የጉዞው ቀን መቆረጡን B.
A. ኃይለቃል ሰማችሁ
ዝርዝር? ለተሰመረበት
ዓ.ነገር አውዳዊ ፍቹ
C. ዋና አ.ነገር D. A እና C
A. መሰረዙን B. መራዘሙን C. መቅረቱን D. መወሰኑን
14. የዓ.ነገሩ ባለቤት ድርጊት ፈጻሚ የሚሆንበት ግስ ምን ይባላል?
A. ተገብሮ ግስ B. ገቢር ግስ C. ኃላፊ ግስ D. የዋህ ኃላፊ ግስ
15. ተቀመረ፣ ተመከረ፣ ተፈታ፣ ተከበረ… የሚሉት ምን አይነት ግሶች ናቸው?
16. A. የአሁን ጊዜ ግስ B. ገቢር ግስ C. ተገብሮ ግስ D. የትንቢት ጊዜ ግስ
ፈቀደ፣ ሰማ፣ አጠኑ፣ ሰበሰበች… የሚሉት ምን ዓይነት ግሶች ናቸው?
A. ገቢር ግስ B. ኃላፊ ግስ C. ተገብሮ ግስ D. የትንቢት ጊዜ ግስ
17. ቤካ ሳያሰልስ ጥናቱን ያጠናል፡፡ ለተሰመረበት አውዳዊ ፍቹ፡-
A. እያረፈ B. ሳያቋርጥ C. በፍጥነት D. በደቦ
18. በአሉታዊ አረፍተ ነገሮች ማሰሪያ አንቀጽ ላይ ያለው ቅጥያ የቱ ነው?
A. አል…ም B. አይ…ም C. አት…ም D. ሁሉም
19. የቃላት ተጨማሪ/ተደራቢ፣ ዘወርዋራ ፍቺ ምን ይባላል?
20. አቶ
A. ጉተማ
ፍካሬያዊየሰፈራችን
ፍቺ አስታራቂ ናቸው፡፡
B. እማሬያዊ ፍቺየተሰመረበትን የሚተካው ፍቺ ስም፡-
ተውላጠ
C. ዘወትራዊ D. ተለምዷዊ ፍቺ
A. እሱ B. እሳቸው C. አንተ D. እኛ
21. የማይጠብቅ ድምፅ ያለው የቱ ነው?
A. ጥጃ B. ላም C. በሬ D. ሰንጋ
22. ጥሩ ስራ ያልያዝኩት ጠንክሬ ባለመማሬ ነው፡፡ የዚህ ዓ.ነገር መንስኤ/ምክንያት፡-
23. A. ጥሩ ስራ አለመያዝ B. ጠንክሮ መማር C. ጠንክሮ አለመማር D. ጥሩ ስራ መያዝ
በርትታችሁ አጥኑ፡፡ ይህ ዓ.ነገር ምን ዓይነት ዓ.ነገር ነው?
A. ሐተታዊ B. አጋኗዊ C. ትዕዛዛዊ D. ጥያቄያዊ
24. በርትቼ ስላጠናሁ ለሚኒስትሪ ፈተና ዝግጁ ነኝ፡፡ የዚህ ዐ.ነገር አይነቱ፡-
A. አጋኗዊ B. ትዕዛዛዊ C. ጥያቄያዊ D. ሐተታዊ
25. መነሻ ቅጥያ ያለው ቃል የቱ ነው?

A. ከሄደ B. ልባም C. ቤቱ D. ሰው
26. ትክክለኛ ቅደም ተከተል የትኛው ነው?
A. ቡቃያ፣ እሸት፣ እምቡጥ፣ አበባ C. አበባ፣ እምቡጥ፣ ቡቃያ፣ እሸት
B. ቡቃያ፣ አበባ፣ እምቡጥ፣ እሸት D. እምቡጥ፣ ቡቃያ፣ አበባ፣ እሸት

27. “ልጅዎን ለልጄ” የሚባለው ለመቼ ነው?

A. ለለቅሶ B. ለሠርግ C. ለበዓል D. ለልደት
28. ለበግ በጎች ከሆነ ለአንበሳ ምን ይሆናል?
A. እነ አንበሳ B. አንበሳት C. አናብስት D. አናብስቶች
29. መልካም ብሎ ክፉ ካለ ገበና ብሎ ምን ይላል?
A. ሚስጥር B. ግልፅ C. ድብቅ D. ጓዳ
30. አረፍተ ነገሮች ከአገልግሎት አንጻር በስንት ይከፈላሉ?
A. በ 3 B. በ 5 C. በ 4 D. በ 8
31. በርትቼ አጥንቻለሁ -------------- ግን ፈርቻለሁ፡፡

2
Magaala Shaggar Kutaa Magaala Laga Xaafoo Laga Daadhii Waajjira Kutaa Magaalaa Duuba.
Shagger City Adm. Lege Tafo Lege Dadi Sub City at the Back of Sub –City Office
በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ጀርባ
 011-86 84 024 0911-50 31 18 ,0913- 17 29 13, 0912- 11 95 12 Email. rehobot @gmail.com
A. ! B. ፡፡ C. ፡- D. ፤
32. ስለ- ባህል- ኣችን የሚለው ተያይዞ ሲጻፍ፡-

A. ስለባሎቻችን B. ስለባህላዊአችን C. ስለባህሎቻችን D. ስለባህላችን

መመሪያ 6፡ ለፈሊጣዊ አነጋገሮቹ ፍቺዎቻቸውን ምረጥ/ጭ፡፡

33.. ልበ ሙሉ A. ደፋር B. ጀግና C. በራሱ የሚተማመን D. ሁሉም

34 እግረ ደረቅ A. እድለ ቢስ B. እድለኛ C. ፈጣን D. ታታሪ
35. የሰማይ ስባሪ A. የሰማይ ክፋይ B. ተራራ C. ግዙፍ D. ፀሀይ
መመሪያ 7፡ ለቀረቡት ሀረጎች የሀረግ አይነታቸውን ምረጥ/ጭ፡፡

36. በጣም ብልህ A. ስማዊ ሀረግ B. ቅፅላዊ ሀረግ C. ግሳዊ ሀረግ D. መስተዋድዳዊ ሀረግ
37. ታታሪ ሰው A. ግሳዊ ሀረግ B. መስተዋድዳዊ ሀረግ C. ቅፅላዊ ሀረግ D. ስማዊ ሀረግ

መመሪያ 8፡ ግጥሙን በማንበብ ከግጥሙ ለወጡ ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጥ/ጭ፡፡

የሀሰት ወገኞች ተመቸን እያሉ

ብዙ ጊዜ አድመው እየተማማሉ

እውነትን ካለም ላይ ሊያጠፏት ተነሱ

እውነት ግን ሁልጊዜ መከታ ለነሱ

ታግላ እያሸነፈች ስትኖር ረግታ

ጠላቶቿ ሁሉ በሷ ጥፋት ፈንታ

አንድ በአንድ ወድቀው እየተሰበሩ

ከስማቸው ጋራ ሁሉም ጠፍተው ቀሩ፡፡

38. የግጥሙ ሐረግ ብዛት ስንት ነው?

A. 8 B. 4 C. 6 D. 16
39. የግጥሙ ስንኝ ብዛት ስንት ነው?

A. 10 B. 8 C. 9 D. 16

40. የግጥሙ የመጨረሻ ስንኝ ቤት የሚሆነው የቱ ነው?

A. ቀሩ B. ሩ C. ሉ D. ጠፍተው ቀሩ
A. ስለ እውነት አሸናፊነት B. ስለ ሀሰት አሸናፊነት C. ስለእውነተኞች መሟሟት D. ስለጥበበኞች ጥንካሬ
41. ግጥሙ ስለምን ይገልፃል?

መመሪያ 9፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምንባቡ መሠረት መልስ/ሽ፡፡

3
Magaala Shaggar Kutaa Magaala Laga Xaafoo Laga Daadhii Waajjira Kutaa Magaalaa Duuba.
Shagger City Adm. Lege Tafo Lege Dadi Sub City at the Back of Sub –City Office
በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ጀርባ
 011-86 84 024 0911-50 31 18 ,0913- 17 29 13, 0912- 11 95 12 Email. rehobot @gmail.com
በእርሻው አቅራቢያ ፈረስ፣ ላምና በግ የሚግጡበት መስክ ነበር፡፡ ግን ፈረሱ ከነዚህ ጓደኞቹ ጋር እንደማይሰማራ ኮርቶ “ጌታዬን
በጀርባዬ እምሸከም እኔ ክብር የለኝምን ወይስ የጌታዬን ልጆች በሰረገላ ይዤ አልሄድምን ?” በማለት ከባልደረቦቹ ተለይቶ ራሱን
ከፍ ከፍ አደረገ፡፡

ላሚቱ ደግሞ እንደዚሁ በኩራት ከበጊቷ እንዳትበላ በማሰብ “የሚጠጣውን ወተት ለጌታዬ አልሰጥምን ወይስ ከወተቴ ቅቤና አይብ
አይገኝምን?” አለች፡፡ በጊቱም ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉትን የሁለት ባልንጀሮቿን ከቁም ነገር አላስገባችውም፡፡ ይልቁንም ራሷን
ከሁለቱ አብልጣ ጌታዋን እንደምትጠቅም አሳወቀች፡፡ “ ለጌታዬ ለሙቀት የሚሆነውን ጠጉር የብርድ ልብሱን፣ ስጋጃውን
አልሰጥምን? በክረምት ፈረስ ላይ ባይቀመጡ ወተት ሳይጠጡ እንደምንም ብለው ይኖራሉ፡፡ የሚሞቅ ልብስ ግን ከሌላቸው
በጤንነት መኖር አይሆንላቸውም” ብላ ተናገረች፡፡

42. በምንባቡ መሠረት የተጠቀሱት እንስሳት የትኞቹ ናቸው?

A. በግ፣ ፈረስና ላም B. በሬ፣ አህያና ፍየል C. በቅሎ፣ ግመልና ጥጃ D. ወይፈን፣ ጊደርና ዶሮ
43. ከእንስሳቱ ሁሉ መጀመሪያ እራሱን ከፍ ከፍ ያደረገው ማነው?

A. በግ B. ላም C. ፈረስ D. ከፍ ከፍ ያደረገ የለም

44. ብርድ ልብሱን ስጋጃውን አልሰጥምን በሚለው አ.ነገር ውስጥ የተሰመረበት ቃል ትርጉም፡

A. መጋረጃውን B. ብርድ ልብሱን C. ምንጣፉን D. አጎዛውን

45. ከእንስሳቱ ሁሉ የበለጠ አገልግሎት እሰጣለሁ ብሎ መጨረሻ የተናገረው

A. ፈረስ B. በግ C. ላም D. ፈረስና ላም
46. የጌታዬን ልጆች በሰረገላ ይዤ አልሄድምን በሚለው አ.ነገር የተሰመረበት ትርጉሙ

A. ኮርቻ B. ግላስ C. ርካብ D. ጋሪ መሰል መጓጓዣ

መመሪያ 0. ለሚከተሉት ቃላት ተመሳሳያቸውን ምረጥ/ጭ::

47. ሥር ማሽ A. አትክልት ተካይ B. መተተኛ C. ቀልደኛ D. ቁጡ

48. ማጀት A. መስክ B. አደባባይ C. ጓዳ D. ጉባኤ

49. ቀሽት A. ቆሽት B. ፉንጋ C. ምርጥ D. የተወለወለ

50. ደቦ A. ተናጠል B. ትብብር C. ማህበር D. ግብርና

መመሪያ 01 ፡ ለሚከተሉት ቃላት ተቃራኒያቸውን ምረጭ/ጥ፡፡

51. ዝግመት A. ቸልታ B. እርጋታ C. ፍጥነት D. እረፍት

52. አድልኦ A. ማበላለጥ B. እኩልነት C. ወገንተኝነት D. አንድነት
53. የሚሹት A. የሚፈልጉት B. የሚመኙት C. የሚወዱት D.የማይፈልጉት
መመሪያ 02፡ ለሚከተሉት ስነጽሑፋዊ ጥያቄዎች መልስ ምረጥ/ጭ፡፡

4
Magaala Shaggar Kutaa Magaala Laga Xaafoo Laga Daadhii Waajjira Kutaa Magaalaa Duuba.
Shagger City Adm. Lege Tafo Lege Dadi Sub City at the Back of Sub –City Office
በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ጀርባ
 011-86 84 024 0911-50 31 18 ,0913- 17 29 13, 0912- 11 95 12 Email. rehobot @gmail.com
54. ነጠላ ውጤት፣ ቁጥብነት፣ ጥድፊያ፣ ተውኔታዊነት የምን መለያ ባህሪያት ናቸው?
A. የረጅም ልቦለድ B. የግጥም C. የተውኔት D. የአጭር ልቦለድ
55. አበበ እንደ ንብ ታታሪ ነው፡፡ የሚለው በምን ዓይነት ዘይቤ የቀረበ ነው?
A. በለዋጭ B.በአነፃፃሪ C. በምፀት D. በእንቶኔ
56. የአንድ ልቦለድ ታሪክ መልዕክት (ዋና ፍሬ ነገር) ምን ይባላል?

A. ታሪክ B. ትልም C. መቼት D. ጭብጥ

57. አየለ አንበሳ ነው፡፡ የሚለው በምን ዓይነት ዘይቤ የተገለፀ ነው?

A. በአነፃፃሪ B. በሰውኛ C. በእንቶኔ D. በለዋጭ

58. ቀኑ ሲያለቅስ ዋለ፡፡ የሚለው በምን ዓይነት ዘይቤ የተገለፀ ነው?
A. በምፀት B. በሰውኛ C. በለዋጭ D. በአነፃፃሪ
59. አጭር ልቦለድ በስንት ቃላት ይጻፋል?
A. ከ 10 ሺ ባልበለጠ B. ከ 10 ሺ በሚበልጡ C. ከ 5 ሺ በሚበልጡ D. ከ 80 ሺ በሚያንሱ
60. በቃል ተደርሶ በቃል የሚከወነው የስነጽሁፍ ዘውግ (ዘር) የትኛው ነው?
A. ተውኔት B. ስነቃል C. ግጥም D. አጭር ልቦለድ

አዘጋጅ፡- የቋንቋ ት/ክፍል

You might also like