You are on page 1of 2

ከሥጋና እርድ ተረፈ ምርቶች የውጪ ንግድ 121 ሚሊዮን ዶላር ገቢ

ተገኘ
addismaleda.com/archives/30140

July 23, 2022

ዜናአቦል ዜና

በ አብርሀም አያሌው
23/07/2022

በ2014 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ የሥጋና እርድ ተረፈ ምርቶች 121 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን
የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ደበሌ ለማ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣
በ2014 በጀት ዓመት ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ምርቶችን በኹለት ንዑስ ክፍል ከፍሎ ወደ ውጭ አገራት በመላክ
የተሻለ ገቢ አስመዝግቧል ብለዋል።

ከሐምሌ 1/2013 እስከ ሰኔ 30/2014 ባሉት ጊዜያት በመጀመሪያው ንዑስ ክፍል 15 ሺሕ 510 ቶን የበግና
የፍየል ሥጋ፣ ከ 2 ሺሕ 1 መቶ ቶን በላይ የዳልጋ ሥጋ፣ ከ 2 ሺሕ 6 መቶ በላይ የእርድ ተረፈ ምርት፣ ከ 4 ሺሕ 9
መቶ ቶን በላይ የአህያ ሥጋ በድምሩ ከ22 ሺሕ 689 ቶን በላይ ሥጋና የእርድ ተረፈ ምርት ወደ ውጭ አገራት
መላክ መቻሉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

ከእነዚህ ምርቶች ከ119 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ከአፈጻጸም አንፃር 123 ነጥብ 6 በመቶ ነው
ማሳካት የተቻለው።

ኢንስቲትዩቱ በ2014 በጀት ዓመት 18 ሺሕ 348 ቶን ሥጋና የእርድ ተረፈ ምርት ለመላክ አቅዶ የነበረ ሲሆን፣
ከእቅድ አንፃር ከ 4 ሺሕ ቶን በላይ ምርት መላክ እንደተቻለ እና የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ
ተጠቅሷል።

በኹለተኛው ንዑስ ክፍል እንዲሁ ከ13 ነጥብ 4 ሺሕ 653 ቶን በላይ ማር፣ ከ233 ቶን በላይ ሰም፣ ከ342 ቶን
በላይ የዓሳ ምርት፣ ከ1 ነጥብ 229 ሚሊዮን ሊትር በላይ ወተት፣ ከ6 ሺሕ 468 በላይ ቶን መኖ፣ ከ123 ሺሕ
220 ቶን በላይ የዶሮ ምርት በአጠቃላይ 96 ነጥብ 62 ሺሕ 121 ቶን በላይ ምርት እንደተላከ እና ከ2 ሚሊዮን
ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተነግሯል።

በአጠቃላይ፣ ከኹለቱም ንዑስ ክፍል 121 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ 95 በመቶ የሚሆነው ምርት
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ ቀሪው 5 በመቶ እንዲሁ ወደ ተለያዩ የውጭ አገራት እንደተላከ
ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ጽሑፎች:
የሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የወጪ ንግድ ገቢ በ11 በመቶ ቀነሰ
በየመንደሩ በሚካሄድ እርድ ምክንያት አዲስ አበባ በየዓመቱ 1 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር እንደምታጣ ተገለፀ

1/2
ቄራዎች ድርጅት ለገና እስከ 3500 የእርድ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ

በ2013 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ የተለያዩ ምርቶች ተገኝቶ የነበረው 82 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር እና
በ2014 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብልጫ እንዳለው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከያዘው እቅድ አንፃር የተሻለ ገቢ ሊያስመዘግብ የቻለው ከዚህ በፊት
የነበሩ ክፍተቶችን በማስተካከል በሦስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራቱ ነው ተብሏል። ከዚህ በፊት
ክፍተት ይስተዋልባቸው የነበሩ የኮንትሮባንድ ንግዶች ላይ ቁጥጥር ማጠናከር መቻሉም ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረገ
መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በኹለተኛ ደረጃ በኢትዮጵያ የነበረውን ድርቅ ተከትሎ አርሶአደሩ ከብቶችን በስፋት ለገበያ በማውጣቱ እና
ግብዓቶች በሰፊው መቅረባቸውን ተከትሎ ፋብሪካዎች የሥጋ ምርቶችን እና የእርድ ተረፈ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ
አምርተው መላክ በመቻላቸው ነው ተብሏል።

በሦስተኛ ደረጃ ከዚህ በፊት በኮንትሮባንድ ሕገወጥ ንግድ ላይ ተሳትፈው ይሠሩ የነበሩ አካላት ላይ ከፍተኛ
ቁጥጥር በማድረግ እና ከሕገ ወጥ ንግድ እንዲወጡ በመደረጉ በ2014 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ማስገባት መቻሉ
ተነግሯል።

የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዘርፉን በማሳደግ እና አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሠራር
በመዘርጋት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንደሚሠራም ተጠቁሟል።

ቅጽ 4 ቁጥር 194 ሐምሌ 16 2014

- ይከተሉን -

መልስ አስቀምጡ

2/2

You might also like