You are on page 1of 6

Ermias Legesse Wakjira

facebook.com/kalkidan.legesse.58/posts/pfbid0KMNojUdLoiiCoVCqkKFYJD6qy2aGaHdAop4At4CbBtZz6gEQTs6xRx
4nsRHKMSPjl

እንዴት ሰው በስተርጅና በዚህ ልክ ይዋሻል?

1.የአንዳርጋቸው ፀሀይ እየጠለቀች ይሆን?

ሰሞኑን በህይወት ዘመኑ ራሱን አንድ ማድረግ ያቃተው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስራ በዝቶበታል። ከመቼውም
ጊዜ በተለየ እባብ እንደነከሰች ፍየል እጅግ ተቅበዝብዟል። በተለይ በየቀኑ የሚያወጣቸው መጣጥፎች
ለተመለከተ ተራራ ለመውጣት አስቦ መሬቱን በእጆቹ እየቧጠጠ የሚጓዝ ሰው አስመስሎታል። ይህም ሆኖ
ቧጥጦ እና ተጋግጦ የያዛቸው ሰምበሌጦች የሚያድኑት አልመሰለውም።

እኔም ባለኝ አስተማማኝ መረጃ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አደጋ ላይ ነው። አብይ አህመድ "አይኑን ማየት
አልፈልግም" በማለት ለወራት ፊት ነስቶታል። በሌላም በኩል ከዚህ በፊት ገልጬው እንደነበረው በደህንነቱ
መስሪያቤት የስለላ ሰርቪላንስ ውስጥ ከገባ ሶስት ወር ሆኖታል።

አሁን አሁን የአንዳርጋቸው ህይወት ተመልሳ ትራጄዲ ውስጥ ለመግባት እየቃተተች ይመስላል። በቅርብ ጊዜ
የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ባደረገው ግምገማ "አንዳርጋቸው ከሻዕቢያ ጋር ሆኖ አገር ሊያተራምስ ነው" የሚል
መረጃና ማስረጃ ቀርቦበታል። ከፖለቲካ ነጋዴነት ፣ባንዳነት እና የውጭ ዜግነት ጋር ተያይዞም ስሙ በተደጋጋሚ
ተነስቷል። አስገራሚው ነገር ሪፖርቱን እንዲያቀርብ የተደረገው የስለላው መስሪያቤት የበላይ ኃላፊ ተመስገን
ጥሩነህ መሆኑ ነው።

ይህ ብቻ አይደለም ። ብልጽግና የሰሜኑን ጦርነት ስታነሳ አንዱ የገመገመችው "በጦርነቱ ወቅት ህውሃት እና
የትግራይ ህዝብ የማይለይ አደገኛ ቃላት በጥቅም ላይ አውለናል" የሚል ነበር። ሰሞኑን እንደ በቀቀን የተነገረውን
በመድገም ተስተካካይ የሌለው ጓድ ሬድዋን ሁሴን በፓርላማ የገለጠው ይህንኑ ነበር። ታዲያ አላካኪዋ ብልጽግና
ራሷን ወደ ጎን ትታ " በጦርነቱ ወቅት አብዛኛውን ወንጀለኛ ቃላት የተጠቀሙት የፓርቲያችን አመራሮች
ሳይሆኑ ሌሎች አካላቶች ናቸው" ብላለች። ይህም በጦርነቱ ወቅት የተፈጠረው የጎራ መደበላለቅ የሃሳብ
አንድነት እንዳይኖረን እድርጓል በማለት ገምግማለች። ከእነዚህ የክፉ ቃላቶች በስተጀርባ በግንባር ቀደምትነት
የተጠቀሰው ደግሞ አንዳርጋቸው ጽጌ ነው። አረመኔያዊ ጭካኔ! እናም በአሁን ሰዓት "አንዲ" ኢትዮጵያን ለቅቄ
ልውጣ ቢል ይፈቀድለታል ወይ የሚለው በጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል።

2. የአንዳርጋቸው የዛሬ ቅጥፈት

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ በጻፈው መጣጥፍ ላይ ውስጡ እያወቀ ሆን ብሎ ማህበረሰብን በሚንቅ መልኩ


የሚያጭበረብር መረጃ ሰጥቶ ተመልክቻለሁ። መረጃውን የሰጠው ሰውየው ከዛሬ አራት አመት በፊት ካዘጋቸው
" ፍኖተ ካርታ" ጋር አያይዞ ነው። ዛሬ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለእኔ በደንብ በሚገባኝ መልኩ ለአራት ዓመታት
ደብቆ ያቆየውን ሰነድ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። አስቀድሜ እንደጠቀስኩት አንዳርጋቸው ይፋ ባደረገበት በዚህ
ሰነድ ላይ በመንደርደሪያነት የተጠቀመው በውሸት የታጨቀ መረጃ ነው። እኔንም በስም ጠቅሶ ሊቀጥፍ
ሞክሯል። እናም ለዚህ ምላሽ መስጠት ስለሚያስፈልግ የሚከተለውን ለማለት እፈልጋለሁ።

አንዳርጋቸው በመጣጥፉ ላይ እንዲህ ይላል፣

1/6
" ከሚድያዎችም ሰንዱ በኢሳት ጋዜጠኞች እጅ ቢገባ እነሱ ከርቀት የሚመለከቱት ሃገር የገጠመውን ተጨባጭ
ችግሮች እንዲረዱ በማድረግ በሚድያ ስራቸው የተለየ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩባቸው የሚገቡ ነጥቦች
ያመላክታቸዋል በሚል እምነት እንዲደርሳቸው አድርጌያለሁ። በተለያዩ አጋጣሚዎች ኤርምያስ ለገሰ
አንዳርጋቸው የላከው ሰንድ በሚል የሚጠቅሰው ይህን ሰንድ ነው። አይቶት ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር
የለም” ይላል።

እስቲ በዝርዝር እንመልከተው ።

2.1. የዛሬ አራት ዓመት አንዳርጋቸው ጽጌ ሰነዱን ወደ እኛ ማምጣት ለምን ፈለገ?

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያዘጋጀውን ሰነድ ተለይተን የተወያየነው በታማኝ በየነ የቴሌ ኮንፍረንስ አዘጋጅነት እኔ፣
ምናላቸው ስማቸው እና ሀብታሙ አያሌው ነበርን። እንድንወያይ የተለየነው ሰዎች ደግሞ በወቅቱ በአብይ
አህመድ አካሄድ ላይ ብርቱ ጥያቄ የምናነሳ የተቋሙ ባልደረቦች ነበርን። አካሄዱም ላይ በቅድሚያ ታማኝ በየነ
ሁለት ኮፒ ሰነዱን አምጥቶ ለእኔ እና ለሀብታሙ እንድናነበው ሰጠን። እኔ የወትሮ መቀመጫዬ ላይ፣ ሀብታሙ
የኢሳት ካፊቴሪያ ቁጭ ብለን አነበብነው። በመጣጥፉ ጥልቀት እጅግ በመገረም ማስታወሻ ወስደን፣ ጥያቄዎች
ይዘን መነጋገር ጀመርን። ትንሽ ቆይተን ለታማኝ ግብረ መልሳችንን ነገርነው ተለያየን።

የዛው እለት ከሰዓት ታማኝ በየነ ደውሎልን " አንዳርጋቸው ሊያናግራችሁ ይፈልጋል! ጥያቄዎቻችሁንም
ሊመልስላችሁ ነው" በማለት ነገረን። እኛም ደስተኛ ሆንን። ያጋጣሚ ነገር በጋራ ምሳ ልንበላ በምናላቸው
ስማቸው መኪና እየተጓዝን ስለነበር አሌክሳንድሪያ ክላይድስ ሬስቶራንት አጠገብ የሚገኝ ሾፒንግ ሴንተር
አቆምን። በመሃላችን አዲስ የተጨመረ አንድ የተቋሙ ባልደረባ ነበር።

አንዳርጋቸው ገለጻውን ጀመረ። እኔም የእለት ውሎዬን (ዲያሪ መሰል) የማሰፍርባት የስልኬን ኖት ቡክ አውጥቼ
መጻፍ ጀመርኩ። ጥያቄዎቼንም አዘጋጀሁ።

አንዳርጋቸው ንግግሩን የጀመረው እንዲህ በማለት ነበር፣

" ሰነዱን ለአብይ አህመድ ሰጥቼው ነበር። ይሁን እንጂ አብይ አህመድ የምትነግረውን አይሰማም! በአንድ ጆሮ
የሰማውን በሌላው ጆሮ ያፈሰዋል። እሺ! እሺ! ይላል እንጂ ሌላ ሰው የነገረውን አያዳምጥም። ከምትገምቱት
በላይ አብይ አህመድ ግትር እና የተመከረውን ትቶ ያልተመከረውን የሚሰራ ሰው ነው" በማለት ተናገረ።
ያልጠበቅነው ስለነበር ሁላችንም በመገረም እርስ በርስ ተያየን። በግሌ አብይ አህመድ በዚህ መጠን ግትር ነው
የሚለውን ለመቀበል ተቸግሬ ነበር።

አንዳርጋቸው እንዲህ በማለት ቀጠለ፣

" በመሆኑም በአብይ አህመድ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና ማሳደር አለብን። በእናንተም በኩል የአገሪቱን ሁኔታ
በደንብ ስለምታውቁና በፕሮግራማችሁ ላይ ደጋግማችሁ ስለምታነሱ ይህን ማሳካት እንችላለን። ሰነዱ
እንዲደርሳችሁ ያደረኩት ለዛ ነው። በደንብ ዝርዝር እቅድ አዘጋጅታችሁ እንድትሄዱበት ነው" አለን።

እኛም ተስማማን።

እነሆ ዛሬ አንዳርጋቸው ጽጌ በወቅቱ አሳካዋለው ያለውን ግብ ሸምጥጦ ሌላ ዝባዝንኬ ጻፈ። "ሰነዱን የላኩላቸው
ከርቀት የሚመለከቱት ሃገር የገጠመውን ተጨባጭ ችግሮች እንዲረዱ …" በማለት አቅጣጫ ለማስቀየስ ሞከረ ።

አንዲ! እኛ ምንም እንኳን አዲስአባን የአያቶቼ ጥጃ ማሰሪያ ብለን መዲናችንን በስጦታ ጠቅልለን ለአብይ
አህመድ ባንሰጥም የአዱ ገነት ልጆች ነን! የሆነው ሆኖ እኛ የአገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ የመገንዘብ ችግር
አልነበረብንም። እንደውም ቀድመን መገንዘባችን እና መባነናችን ከሁሉም አቅጣጫ በብረት ሰንሰለት እንድንገረፍ
አድርጎናል። አንዳርጋቸውም ለይቶ እኛን የፈለገን በወቅቱ የጎነጎነውን ሴራ በማን በኩል ባስፈጽመው የተሻለ

2/6
የፖለቲካ ገበያ እፈጥራለው ከሚል ሂሳብ ተነስቶ ነው። በአጭሩ እንዳርጋቸው የወጠነው እኛን የማስፈጸሚያ
መሳሪያ ሊያደርገን ነበር ። ዛሬ ሌሎችን እንደሚያደርገው። እርግጥ በተግባር ሲታይ ከአሁኖቹ የእኛ የሚለየው
አጀንዳውን እኛ አስቀድመን የጀመርነው በመሆኑ አንዳርጋቸው ወደ እኛ መጣ እንጂ እኛ ወደ እሱ አልሄድንም።

(በነገራችን ላይ አንዳርጋቸው ሰነዱን ከማዘጋጀቱ በፊት እኔ እና ሀብታሙ አያሌው "ፖለቲካችን" በሚለው


ሳምንታዊ ፕሮግራም " አሃዳዊ ማነው?" የሚል ፕሮግራም ሰርተን ነበር። እናም ፕሮግራሙን ተመልክቶ
የቅድሚያ ቅድሚያ አድናቆቱን ያዥጎደጎደው አንዳርጋቸው ጽጌ ነበር። ፕሮግራሙ አስቀድሞ የተሰራ ቢሆንም
ከሞላ ጎደል አንዳርጋቸው ዘግይቶ ካዘጋጀው ሰነድ ጋር የሚጣጣም ነበር። )

( ዛሬስ አንዳርጋቸው ጽጌ ምን እያደረገ ነው? አብይ አህመድን ያስፈራራልኛል የሚለውን ከሻዕቢያ የስለላ ተቋም
የሚላክለትን እንደ ወረደ ያቀርባል። ተጽእኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ (ሁሉም አይደለም) ሻዕቢያ
ዳረጎት እየሰጣቸው ባላቸው ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች እንዲተላለፍ ያደርጋል። አስቂኙ ነገር አንዳርጋቸው
ከጀርባ ይህን ተንኮል እየሰራ የአቢቹን ስልክ ቀን ከሌት ይጠባበቃል! አማላጅ ይልካል። ወይ ፍንክች የበሻሻ ልጅ!)

2.2. ለምን የእኔን ስም ለይቶ ተጠቀመ? ለምን ሰነዱን ስለማንበቤ እና አለማንበቤ ጥርጣሬ ውስጥ ሊከት ፈለገ?

አንዳርጋቸው ጽጌ በዛሬው መጣጥፉ ላይ ፣

"በተለያዩ አጋጣሚዎች ኤርምያስ ለገሰ አንዳርጋቸው የላከው ሰንድ በሚል የሚጠቅሰው ይህን ሰንድ ነው።
አይቶት ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር የለም። " ይላል።

2.2.1. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተፈረካክሶ ቁዘማ ውስጥ የገባው የመደመር ካምፕ "የልቅሶ እዝኑን" እኔን አድርጓል።
የተጣበቀበት የጦር ፣ ቀረፋ፣ ባናና ማስቲካ በመድረቁ እኔን "የጋራ ጠላት" ማጣበቂያ አድርጎ እየወሰደ ነው ።
እሱን ካላጠፋን ሰላም አናገኝም በሚል ከዋሽንግተን ዲሲ እስከ እስራኤል፤ ከአዲስአበባ እስከ ጎንደር፣ ከጎንደር
እስከ አስመራ የተዘረጋ የስም ማጠልሸት ዘመቻ ከፍተውብኛል። ባለፉት ሁለት አመታት በወያኔነት እና ጁንታነት
ሲፈርጁኝ የነበሩ አካላት ዛሬ ደግሞ " ዋቅጅራን" እያጣቀሱ በተረኝነት እና ከኦሮሞ ብልጽግና ባለስልጣናት ጋር
ተገናኘ በማለት ሊከሱኝ ቀን ከሌት በመንቻካ አንደበታቸው ያንቋርራሉ። እነሱ ወደ ቆሻሻቸው እና ትፋታቸው
መመላለስ ባህሪያቸው ስለሆነ ሌላውንም በእነሱ ትንሽነት ሊመዝኑት ይፈልጋሉ።

(በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይም ኤርምያስ ከዘመዶቹ (የኦሮሞ ብልጽግና ጋር ተገናኘ) በሚል ጊዜውን እየጠበቀ
ስለሚወራው ወሬ በስፋት ተመልሼ መምጣቴ ስለማይቀር በዚህ ልለፈው። )

2.2.2. የዛሬ ስድስት ወር ገደማ አንዳርጋቸው ጽጌ አንዳፍታ በሚባል ሚዲያ ላይ ቀርቦ ስለ ሰነዱ ተጠይቆ ነበር።
በወቅቱ ለሚዲያው በሰጠው ምላሽ የእኔን እና የሀብታሙ አያሌውን ስም በመጥቀስ በሰነዱ ላይ እንደተወያይን
ይናገራል። ሚዲያው በሰራው የፊት ገፅ ( ተምብኔል) ላይ የሰፈረው ምስል እና ርዕስም ያንን የሚያመላክት ነበር።

2.2.3. እንዳርጋቸው በዛሬው መጣጥፉ ላይ "በተለያዩ አጋጣሚዎች ኤርምያስ ለገሰ አንድ አንዳርጋቸው የላከው
ሰነድ በሚል የሚጠቅሰው ይህን ሰነድ ነው" በማለት ይገልጻል። ይህ አገላለጥ በአንድ በኩል ትክክል ነው። በተለያዩ
አጋጣሚዎች ሰነዱ የት ደረሰ? በማለት ጠይቄያለሁ። በተቃራኒው አንዳርጋቸው ጽጌ ለሶስት አመታት ትንፍሽ
ብሏት አያውቅም። በሌላም በኩል ሰነዱ የት ደረስ በሚል በተለያዩ አጋጣሚዎች የምገልጸው እኔ ብቻ
አይደለሁም። ለምን የእኔን ስም ብቻ አንጠልጥሎ ማንሳት ተፈለገ? አንዲ እኛ አዲስአበቤዎች የዝንብ ጠንጋራ
ሳይቀር እናውቃለን ሲባል አልሰማህም?

2.2.4. እንዳርጋቸው በዛሬው ጽሁፉ ላይ "ኤርምያስ ሰነዱን አይቶት ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር የለም "
በማለት እጅን በጭንቅላት የሚያስጭን ቅጥፈት እና ነውሩን በአደባባይ ይገልጣል። አንድ ያልሆነው አንዲ ይህን
ሲናገር በአንድ በኩል ሰነዱ እንዲደርሳቸው አድርጌያለሁ ማለቱን ይዘነጋል። ከላይ እንደ ጠቀስኩት በሌሎች

3/6
ሚዲያዎችም ላይ ወጥቶ በሰነዱ ላይ መነጋገራችንን ምስክርነት መስጠቱንም ይረሳዋል። በሌላ በኩል ኤርምያስ
ሰነዱን አይቶት ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር የለም ይላል። ቂል አትበሉኝ እና መቼም እንዲህ አይነት እርስ
በርስ የሚደባደብ መረጃ ለመስጠት አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ይጠይቃል ።

የሆነው ሆኖ ከዚህ የአንዳርጋቸው ቅጥፈት የምገነዘበው በርካታ ቁምነገሮችን ነው። የመጀመሪያው ቁምነገር
አንዳርጋቸው ከኤርምያስ እና ጓደኞቹ ጋር ተገናኝቼ በሰነዱ ላይ መክሬያለሁ ቢል እንደ ውሻ አጥንት
እየወረወረ ከገረደው አብይ አህመድ ጋር ሊጣላ ነው ። ይህ ደግሞ የሰሞኑ ግቡን እና አልሞት ባይ ተጋዳይነቱን
በዜሮ ያባዛበታል። አብይ አህመድ የእኔን ስም ሲሰማ ዛር እንደያዘው ወይዘሮ እንደሚንዘፈዘፍ ጠንቅቆ ያውቃል።
ሌላው ቢቀር "አዲስአበቤነት" የሚለው ማንነት እና ለዛ በጽናት መታገል ብቻ ያንዘረዝረዋል። ስለዚህ ለአንዲ
ከእነ ኤርምያስ ጋር ተገናኝቼ ሳሴር እና አቅጣጫ ስሰጥ ነበር ማለት በራስ አንገት ላይ እባብ እንደመጠምጠም
ይሆንበታል።
አንዳርጋቸው ማስተላለፍ የፈለገው ሁለተኛ መልዕክት እነ ኤርምያስ ባለፉት አራት ዓመታት በሚዲያ ስራቸው
ተጽእኖ መፍጠር የቻሉበት አንዱ ምክንያት ከሰነዱ የተቀዳ ነው ከሚለው ጋር እንዳይያያዝበት ነው። በርግጥ
እዚህ ላይ እውነቱን መስክሮ ለመሄድ የአንዳርጋቸውን ሰነድ ካነበብን በኋላ ቢያንስ አምስት ፕሮግራሞች
ሰርቻለሁ። አንድ ከሌሎች ባልደረቦቼ ጋር በመሆን "ዕለታዊ" ፣ አንድ "ፖለቲካችን"፣ አንድ "ሁለንተናዊ ዕይታ"
እና ሁለት " አውደ ኢኮኖሚ" ሰርቼበታለሁ። ከእኔ አልፌ ለአውደ ኢኮኖሚ ተሳታፊ ለሆነው ምሁር ሰነዱን ኮፒ
አድርጌ ሰጥቼዋለሁ። ከዛም በኋላም የሰነዱ ጭብጦቹ ላይ ተመርኩዤ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ሰርቼያለሁ።

አሁንም እውነት ለመመስከር የአንዳርጋቸው ሰነድ አብዛኛው የሁኔታዎች ግምገማ የሰፈረበት ላለፉት አራት
ዓመታት የሚዲያ ስራ ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥሉት አራት አመታትም እንደ አቅጣጫ የሚያገለግል ነው ። እኔ
ላለፉት አራት ዓመታት ሰነዱ ከራሴ ፍላጎት ጋር ስለሚስማማ እንደ ፍኖተ ካርታ በመውሰድ የራሴን ስትራቴጂ
እና ታክቲክ በመጨመር ተጠቅሜበታለሁ። ለወደፊቱም መሰረታዊ የስርዓት ለውጥ እስኪመጣ እና የዘር
ፖለቲካው እስኪቀየር ድረስ እጠቀምበታለሁ። የዘር ፖለቲካን የምትጠየፉም ሞክሩት!

All reactions:

582 582
4

45

Like

Share

4 comments

All comments


4/6
Soliyana Alemayehu
ሰነዱን ልቀቀውና እኛም እናንብበው።

Like

7h

Zion Kinf
አንበሳ ኤድሚ

Like

6h

5/6
Engida Tadesse
በስድሳዎቹ ትውልድ ውስጥ እንኳን ልትወለድ ያልተጸነስክ፣ ነገር' ግን የነሱን ፖለቲካዊ ንቃትና አካሄድ'
#ነቄ' ብለኽ እንደነሱም ፖለቲካዊ ሽብልቁን ቀድመህ የምትረዳ' ኤርምያስ ሆይ!! የስድሳዎቹን ትውልድ
ለመረዳት' አንድም ልዩ ንቃትን መታደል ያስፈልጋል' አንድም እዛ ትውልድ ላይ የነበረን የትግል ስልት
ንባብን ይጠይቃል።ለማንኛውም የዛሬውን የአንተን ጽሁፍ' ሳነብ፣ የአቶ አንዳርጋቸውን ሳላነብ፣ "እባብ
ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ" ብሂልን ያሳያል። ነቅተኽበታል! እሱም የያዛችሁትን ተጽእኖ አሳዳሪ ሚድያ'
ባይወደውም፣ እንደ ማጥቂያ ኑክሌር ቦምብ አብይን ለማስፈራርያ እየተጠቀመበት ይገኛል ማለት ይቻላል
በጽሁፍህ መሰረት እንደተረዳሁት።
ምናልባት ግን! የአንዲን ጽሁፍ ጠቅላል ይዘት ባናየውም' አሁን በአብይ አህመድ ፊት መንሳትም ይሁን
ወይም እንደ አንድ ተቆርቁሪ ዜጋ' የኢትዮጵያ መጻኢ ዕድል አስጊ እንደሆነበት ሰው' አስተያየቱን
መስጠቱና ካስተያየቱም አስጊውን ጉዳይ አንገዋሎ ማየቱና በአስጊው ጉዳይ ላይ ተነስቶ አገሪቱን ማዳኛ
እንደ ግብዓት መጠቀም አይቻልም ወይ'? የሚለውም ጉዳይ ያሳስበኛል።

መቸም' አንዳርጋቸው' ብዙ በመጽሃፉ ላይ የተምታታባቸውን ታሪክ ወለድ ተረቶችን ደርቶ' የኦሮሞ ስረወ
መንግስት እንዳለውና ጥገቶቹና ጥጃዎቹ የታሰሩበትን የቱለማ ኦሮሞ መንደሮችን በተረቶቹ' አብይ
አህመድ ሲተኛ እንደ ህጻናቶች እንዲነበብለት በማድረጉ ጭምር አንድ ሰሞን ቤተ መንግሥተኛ' የቅርብ
ሰው እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም ዛሬ አንተ ከጽሁፉ ወስደህ ካፒታላይዝድ በማድረግ ለትግሉ
የሚጠቅመውንም ጉዳይ ልትሰራበት ትችላለህ ብየ አምናለሁ።

አንዳርጋቸው ቢሸመግልም ወይም መርሳት ቢያመጣም የጨረሰ የአራዳ ልጅ' ስለሆነ የበሻሻው
የሚበልጠው በታንኩና በባንኩ እንጂ በአራዳነት አይደርስበትም፣ እንኳን እሱ' ኢሱም ቢሆን!!።
በሞርም ይሁን ሰይብል ባንከረባብት ቁማር ጨዋታ ሊያላትማቸው የሚችል አቅም ያለው ሰው
ይመስለኛል። ሁለት የአራዳ ልጆች ብቻ' ተነቃቅታችኋል!! ግን! መጪውን አደገኛ ሁኔታ በመገመት'
ምንም ቢሆን በበሻሻው ሰው ጨካኝነት እንዳይመታ' አብሮ' ከአብይ ጋር ያበላሸውን ሀጥያት እንዲያነጻ
ዕድል መስጠት የተሻለ ነው። በመጠኑም ቢሆን ከብርሃኑ ነጋ እሱ ይሻላልና ነው። መልካም ቀን

Like

11h
Edited

Liyu Belay G Mariam


ኤርሚ ሰነዱን ልቀቅልን

Like

4h

6/6

You might also like