Professional Documents
Culture Documents
facebook.com/fanabroadcasting/posts/pfbid02UXf8Dpnu8sRTG9Fgqm4jaue6qCRukXzDrTG3Qp9sZxcXmdXp2cK3Dz
2Dt877EmWml
በአዲስ አበባ ከያዝነው ወር ጀምሮ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት
ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
በኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሴ እንደገለጹት÷ ተጠሪነታቸው ለከተማ አሥተዳደሩ በሆኑ
የመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞችን በወሳኝ ኩነት ሥራው ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡
ለዚህም ኤጀንሲው እና የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በሥራው አተገባበር
ላይ የየራሳቸውን ድርሻ ለይተው ተፈራመዋል ነው ያሉት፡፡
የመንግስት ሠራተኞችም÷ ለወሊድ እረፍት የሚወጡ ወላጆች (አባት እና እናት) የልጆቻቸውን የልደት ምዝገባ
ማስረጃ እንዲሁም ለጋብቻ እረፍት የሚወጡ ተጋቢዎች የጋብቻ ምዝገባ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ይገደዳሉ
ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የቅርብ የቤተሰብ አባል ህልፈት በመከሰቱ እረፍት የሚወጡ የሞት ምዝገባ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ፣
የጉዲፈቻ እና የፍቺ ኩነት ሲከሰትም በተመሳሳይ ሁኔታ የምዝገባ ማስረጃውን ማቅረብ አስገዳጅ ነው ተብሏል፡፡
ልደት በ90 ቀናት እንዲሁም ጋብቻ፣ ሞት፣ ፍቺ እና ጉዲፈቻን በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ይጠበቃል ነው
ያሉት፡፡
ሠራተኞች ምዝገባውን ማከናወን ያለባቸው በሚሠሩበት መስሪያ ቤት ሳይሆን በሚኖሩበት ወረዳ መሆኑንም
አስረድተዋል።
ኤጀንሲው እስካሁን በአዲስ አበባ ከሚገኙ የጤና ተቋማት፣ ዕድሮች እና ፍርድ ቤቶች ጋር የወሳኝ ኩነት ሥራውን
እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
1/5
All reactions:
296 296
13
Like
Comment
Share
13 comments
Oldest
Natinael Samuel
እኔ ደሞ አስቤዛ ይሰጣችኋል የምትሉ መስሎን
Like
Reply
4h
2/5
Getachew Tefera
Kkkkkkk ለደትና ሞት መመዝገብ አልነበረም እንዴ ስራው ወደ ሰራተኛ ምዝገባ ዞረሳ
Like
Reply
4h
Edited
Melese Gobezie
hulam yemiwotaw heg seratgnawun lemasakek eng lmetekmema kere
Like
Reply
4h
የወይራው መዶቃድቅ
ቢሔራችውን ለመለየት ነው??
Like
Reply
4h
Nebiyu Negede
የጨነቀለት አለ አዝማሪው
Like
Reply
4h
3/5
Kelelaw Gedle
የግድያና ሞት መጠን ለመመዝገብ አይበዛባችሁም
Like
Reply
4h
Top fan
Muzei Abbas
የምታቀርቡት መረጃ ለህዝቡ ምንም የማይፈይድ ነው
Like
Reply
4h
Hawult Tesfa
ጅል አይሙት አሉ ይልቅስ ገበያውን አረጋጉ
Like
Reply
4h
Asnakech Gelan
Like
Reply
4h
4/5
Wondu Wagaye Yanda
Please understand the people first then everything will be comes later
Like
Reply
4h
Üm Zøllå Yē Kīrkös
በ ሸገር ከተማስ
Like
Reply
3h
Teshme Konjo
ባለግዜ አጀንዳ መፍጠሩ ነው በቤቱ ሰራተኛው ዱሮም ዱሮ ነው አሁን የነሱን ኢ-ፍታዊ ያሃብት ክፍፍል
ማዘናጊያ ስራ ቆሞ ባለ ጉዳይ ይንገላታል እግዚኦ
Like
Reply
2h
Write a comment…
5/5