You are on page 1of 7

Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

ጠያቂ

1. ተውኔቱ ተጀምሮ መርማሪው እስከሚገባበት ጊዜ ባለው አቶ ባንቲደሩ ምን አይነት ሰው ሆኖ ቀረበ?

መልሳችሁ የአቶ ባንቲደሩን ንግግሮችና ድርጊቶች፣ እምነትና አስተሳሰብ ሁሉ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መሆን

አለበት። መልሳችሁ ከተውኔቱ በተወሰዱ ምስረጃዎች ላይ የተመረተ የተብራራ መልስ መሆን አለበት።

ይህ “ጥያቄ” የተሰኘው ተውኔት በ መንግስቱ ለማ በ አዛማጅ ትርጓሜ ወደ አማረኛ ከመቶርጎሙ በፊት

እንግሊዛዊው ደራሲ ጂበ ፕርስትሊ “ኻን ኢንስፔክተር ኮልስ” በሚለው መጽሃፉ አስቀድሞ ጽፎት ነበር።

የሁለቱም መጽሃፍ አጠቃላይ ይዘት ተመሳሳይ ነው። የተጨመረውም የተቀነሰውም ነገር ጥቂት ነው

እናም የኛ ህዝቦች በሚረዱት መልኩ ነው የተደረሰው። በአጭሩ ታሪኩ የተከናወነው በ አንድ ሳሎን ውስጥ

በ አንድ ምሽት ነው። ይህ ተውኔት ትምህርታዊ የሆነ ተውኔት ነው ምክንያቱም በ ውስጡ የሃገራችህንን

የቀድሞ ሁኔታ ዘርዝሮ ያብራራልናል ለምሳሌ ፊውዳላዊ አገዛዝ። የዚህ ተውኔት ዋና ገጸ ባህርያቶች የአቶ

ባንዲተሩ ቤተሰቦች እና መርማሪው ናቸው። በዚህ ጽሁፍ ውሥጥ አቶ ባንቲደሩ ምን አይነት ሰው እንደሆነ

መርማሪው ከመምጣቱ በፊት በጥልቀት አብራራለው። መርማሪው መርዶ ይዞላቸው ከመጣ በኋላ

እስካሁን የነበራችው ደስታ አፈር ድሜ በልትዋል። ለደስታቸው መጥፋት መንስኤ የሆነው የ አንድ

ምስኪን ብላቴና በ አጭሩ እና በ አሰቃቂ ሁኔታ መቀጨት ነው ለዚህም የ ሁሉም የቤተሰብ አባላት

ሃላፊነት አለባቸው። የዚህ ተውኔት ዋና ጭብጦች ዘውዳዊ አገዛዝ እና የመደብ ክፍፍል

የሚያስከተልዋቸው ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ ተጽእኖዎች በ ሚስኪኑ ህዝብ ላይ።

1966 ዓ.ም ለኢትዮጲያኖች በጣም የተለየች አመት ናት። ይህች አመት የተለየችበት ምክንያቱም ለ 3000

ዓመት ስንገዛ ከነበረው የፊውዳላዊ እና የካፒታሊዝም አገዛዝ በ አቢዮት አመራር የተላቀቅንባት ስለሆነች

ነው። ይህ የዘመን ሽግግር ብዙ ለውጦችን ይዞ መትጥዋል። ከዚህች ቀን በፊት እጅግ በጣም አስከፊ የዘር

እና የመደብ ክፍፍል ይታይ ነበር። በዚህ ስርአት ውስጥ የመሳፍንትና የመኳንንት ዘር ወይም ደም ያለባችው

ሰዎች ምንም ሳይሰሩ እንደ አራስ ህጻን ይቀለባሉ። አቶ ባንቲደሩ የዛ የድሮው አገዛዝ ነዋሪ

እንደመሆናችው መጠን አስተሳሰባቸው እና ንግግራቸው ልክ እንደዛው ነው። አቶ ባንቲደሩ በጣም

ሃብታም ከበርቴ እና የተከበሩ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ናቸው። እኒህ የቤት አባወራ በስራቸው ትልቅ አትራፊ
Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

የ ንግድ ድርጅት ነው የሚያስተዳድሩት እና የዛሬን አያርገውና እዚህ የ ሀብት እና የድሎት ማማ ላይ

ከመውጣታቸው በፊት ችግር ጠብሷቸው እና ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ቀንና ማታ አሰሪያቸው

እየጨቆኗቸው ሲሰሩ ከርምዋል እና አንድ የ ህይወት መርህ አላችው ካልሰራህ አትበላም እና ሁሉም ሰው

በፈጣሪ ዘንድ እኩል አይደለምም መታየትም የለበትም።

ወደ መጀመርያው የተውኔት ክፍል ስንመለስ ሁሉም ሰው ማለትም የአቶ ባንቲደሩ ቤተሰቦች በአንድ

ጠረቤዛ ዙርያ ተሰባስበው ማእድአቸውን እያጣጣሙ እና ወይናቸውን እየተጎነጩ ነበር። ከመምሸቱ በፊት

ቀትር ላይ የልጃቸው ሃመልማል የ ቀለበት በአል ተካሂዶ ነበር በዚህ ስነስርአት ላይም ከ ጎልማሳው እና

መልከ መልካሙ አሠግድ ጋራ ቃልኪዳን አስራለች። ዝምታው ሲደራበት አባወራው አቶ ባንቲደሩ ለ ልጅ

አሰግድ ወይን እንዲጠጣ ጥያቄ በማቅረብ ጋበዘው ይህ ደግሞ የ አቶ ባንቲደሩ እንግዳ ተቀባይነትና

አክባሪነት ማመላከቻ ነው። ይህ ባህሪው ከ ኢትዮጲያዊነቱ የወረሰው መገለጫው ሳይሆን አይቀርም።

ወሬው እየደራ ይመጣል ሁሉንም ሰውን እያሳተፈ። በመሃል ሃምልማል አሰግድን ትወቅሰዋለች

ለምንድነው መጥተህ ያልጠየከኝ ክረምቱን በማለት ከዛ እናትየዋ ንግግርዋን በማቅዋረጥ ለ አሰግድ

መደገፈፍ ትጀምራለች እንዲህ በማለት “ሃመልማል እንግዲህ አትጨቅጭቂው። ስትጋቡ የሱ ችግር

ይገባሻል። ከፍተኛ ስራ ያላቸው ወንዶች ጊዜያቸውን ሚያጠፉት በ ስራ ነው”። በ አሽሙር ባልዋን

እያናገረችው ነበር ማለትም እሱም ቢሆን ለ እሱዋ ቢዙ ጊዜ አይሰጣትም ሁሌ ስራው ላይ እንዳተኮረ

ነው። ይህ የስራ ሰው እንደሆነ ያመላክታል። ይህ ሁሉ ሲሆን አቶ ባንቲደሩ ምንም ቃል አልተነፈሱም ነበር

ሚስታቸው ተናገር እስክትለው ድረስ ይህም ሚያሳየው የ አቶ ባንቲደሩ በልጁ ትዳር እና ህይወት ጣልቃ

መግባት እንደማይፈልግ ነው ልክ እንደ እናትዋ።

ዲስኩሩን በመስጠት ላይ እያለ በ መሃል ስለ ቀለበት በአሉ በቂ እና አጥጋቢ አለመሆን ለ አሰግድ በመንገር

ቅር እንዳልተሰኘ ይጠይቀው ጀመር። አቶ ባንቲደሩ በበኩላቸው ሙሉ ለሙሉ ደስተኛ አይመስሉም።

ለምን ቢባል ድግሱን እንዲታደሙ የተጠሩት ሰዎች በጣም ስላነሱበትና እና የ አሰግድ ወላጆች እክል

አጋጥምዋቸው ፕሮግራሙን መታደም ስላልቻሉ ትንሽ ቅር ተሰኝተው ነበረ። ለ አለመደሰቱ ሌላ ማስረጃ

ሚሆነን “ ምናልባትም ያንጊዜ እናንተ ያሁኖቹ ወጣቶች እንዲህ እንደዛሬው ያለ ሳይሆን ከዚህ አሥር እጅ

የሚያመጣ ድግሥ ትደግሳላቹ”። ይህ ቀን ከምንም ቀን በተለየ ለ እሳችው የ ደስታቸው ቀን ነው። አባት

ልጁ ለ አቅመ ሄዋን ደርሳ ስትታችለት ከ ማየት የሚሰጠው ውስጣዊ ደስታ በላይ የለም። ያም ሆነ ይህ
Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

አነስ ያለ ድግስ ያዘጋጀበት ምክያት ያሉበት ወቅት የ መንግስት ሽግግር እና አመቺ ያልሆነ ስለሆነ ድል ያለ

በአል ቢደግሱ የ ሰው አይን ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አደጋ ላይ ልትወድቅ ትችላለች።ያለው እንዳለ

ሆኖ አቶ ባንቲደሩ ከ መደሰት ሚያግዳችው አንዳችም ነገር የለም።

ወይ በደስታ ብዛት ወይ አፍ ለቆበት ይሁን አይታወቅም አቶ ባንቲደሩ ሲለፈልፉ ነበር ያመሹት።

በንግግራቸው ውስጥ በ ጋብቻቸው በጣም እንደተደሰቱና ሁለትም የሚመጣጠኑ እንደሆነ አስረግጠው

ይነግራቸዋል። ማለት የፈልገውም ልጁ ምትዳርለት ከፈለገው ዘር ልክ “እንደ ነጋሲ” ልጅ እንደሆነና

እንደተስማማው ነው። ከዚህ ንግግር ምንረዳው ነገር ቢኖር አብዛኛው እንደ አቶ ባንቲደሩ ያሉ ሰዎች በ

ዘር ሃረግ እና ክፍፍል እንደሚያምኑ እና ከ ዘራቸው ውጪ እንደማይጥማቸው ነው። እንደዚ አይነት

አስተሳሰብ ነው ወደ ኋላ እንድንቀር ያደረገን። ልክ እንደ ሃገር እንደማሰብ እንደ ግለሰብና ዘር እያሰብን

እርስ ለ እርስ እንባላለን። ሲቀጥል ደግሞ አቶ ባንቲደሩ ስለ አሰግድ አባት ድርጅቶች በ እሱ ስም አለመኖር

ያልተመቻቸው አሉ ሲል እራሱን ለማለት ፈልጎ ነበር። ማለትም አንድ ቀን አያርገውና ሃብታቸው በ እነሱ

ስም ሳይዘዋወር ቢቀርና የ ሴት ልጁ ሕይወት አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል።

በ ወይዘሮ ጉልትነሽ አማካኝነት አቶ ባንቲደሩ ንግግሩን እንዲያቆም ይገደዳል። ሚስቱ ራሱ ሳትታዘበው

አተቀርም በዛ በደስታ ጊዜያቸው ስለ ንግድ ሲያወራ። አቶ ባንቲደሩ ሲታይ ሲታይ ለ ሚስቱ ጥሩ ባል

ይመስላል ምክንያቱም በ ጸባይ ነው ምትለውን እሺ የሚላት መንስኤው ሊሆን የሚችለው እሷ ከ እሱ

በለጥ ካለ የ ዘር ሃረግ ሲለተገኘች ነው ወይም ደሞ እሷ ባሏ ላይ ጀነን ማለት ልማዷ ነው። ዲስኩሩ ካለቀ

ትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ሌላ ሊናገር የሚፈልገው ነገር ነበረው እና ከ አነጋገሩ ተነስተን እጅግ በጣም

አስፈላጊ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን ምክንያቱም የ ንዴቱ ጥግ የሚወዳትትን ልጁን እስከመቆጣት

አድርሶታል። እንደንግግሩ ከሆነ ሚያወራው አሁን እየተካሂያደ ስላለው ህዝቦች መበጣበጥና ምንም አይነት

ወሬ እንዳያምኑ ሊያስጠነቅቃቸው እና እንዳይሽበሩ ሊነግራቸው ፈልጎ ነበር። ይህ ሚያሳየው አቶ

ባንቲደሩ ለ እራሱ እና ስለ ቤተሰቡ ደህንነት ተቆርቋሪ የሆነ ሰው እና እነሱን ከ ክፉ ነገር ለመጠበቅ ምንም

ያህል መጽዋት እንደሚከፍል ነው። በ እንደዚህ አይነት አለመረጋጋት ውስጥ ደሃው ማህረሰብ

ሚያነጣጥረው ሃብታሞች እና ህይወታቸውን ያመሰቃቀለባቸውን ሰዎች ስለሆነ እነሱ ደግም ታዳኝ

መሆናችው እርግጥ ነው።


Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

በማስቀጠል እንደ አቶ ባንቲደሩ ንግግር ከሆነ አዲሱ የመጣው መንግስት የ ሾሳሊዝም መንግስት ስለሆነ

ያካበቱትን ሃብት አንድ በ አንድ ለ ድሃው እና ሰርቶ ለማይበለው ህብረተሰብ የሚያከፋፍልባችው

ስለመሰላቸው እንዲህ ብለው ተናግረው ነበር “ እኛም የንግድና የኢንዱስትሪ ባለበቶችና አሰሪዎች በሙሉ

ተባብረን ጥቅማችንን ለማስከበር ቆርጠን ተነስተናል” በዚህ ጥቅስ ምንረዳው ነገር ቢኖር አቶ ባንቲደሩ

እና መሰሎቹ ትልቅ ፍርሃት እና ስጋት ላይ እንደወደቁ ነው አዲስ በመጣው የመንግስት አሰራር።

ምክንያቱም በ ማንኛውም ሰአት እና ጊዜ እስከዛሬ ሲንሰፈሰፉለት የነበረው ጥሪት ለ ተራው ህዝብ

ተከፋፍሎ ባዶ እጃቸውን እንዳይቀሩ ስለፈሩ። ነገር ግን እስካሁን ቁርጠኝነታቸው እና ተሰፈኛነታቸው

እንዳለ ነው ማለትም ሁሉም ነገር ያልፋል እና ነገሮች ወደ ቀድሞው ሁኔታቸው ይመለሳሉ ብለው እምነት

ስለጣሉ። በተጨማሪም ይህ ማንነቱ ለ ጥቅሙ ሟች እንደሆነ በ አግባቡ ይጠቁመናል። ተስፈኛነቱ ደሞ

ጎልቶ የሚታየው ሁሌ የሚያስበው ደግ ደጉን ብቻ ነው ለምሳሌ ያህል “ ካሁን ቀጥሎ የሚመጣው ጊዜ

በትርፍ ላይ ትርፍ የሚደረብ የሚደራርብበት የጥጋብ ዘመን ብቻ ነው” ከፊለፊቱ ተገትሮ የሚጠብቀውን

ፍዳ ወይም የ ነገሮች መቀያየር ሳያገናዝብ እራሱን እና ቤተሰቡን ለማረጋጋት ይሞክራል።

ምስጋና ለልጅ መላአኩ አባቱን ስለ ወታደሮቹ ማጉረሙረም በማንሳቱ ምክንያቱም እስካሁን ስለ አቶ

ባንቲደሩ ያላወቅናቸውን ባህርያቶች በ ዝርዝር ልናውቅ ችለንበታል ለነገሩ እሱ ባያስታውሰውም መናገሩ

አይቀሬ ነበር ምክንያቱም በዛን ጊዜ የ ወታደሮቹ ነገር እጅግ በጣም ሊወራበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

ማውራቱን የጀመረው በ ውትድርና ውስጥ ተሰማርተው ያሉ ሹማምንቶችን በማጣጣል እና በ ንቀት ነበር

እንዲህ በማለት “ ዝቅተኛ መኮንኖች ተራ ወታደሮች” እና ይህ የ ቃላት አጠቃቀም ለ አቶ ባንቲደሩ

ያልሆነ ገጸ-ባህርይ ያላብሰዋል ማለትም ከ እሱ በታች ላሉት ሰዎች እና ህዝቦች የሚሰጠውን የ ወረደ

አመለካከትና እና ግምት ያሳያል። እና ማለት የፈለገው ነገር እነሱ ምንም ቢያጉረመርሙና ሁካታ ቢፈጥሩ

ምንም ሊያመጡ አይችሉም እንዲሁ ጩሀት ብቻ ናቸው ነው ሚለው። “ አልጋው ሊነቀንቁት

አይችሉም” ሲል በመጀመርያ ተለዋዋጭ ዘይቤ ተጠቅሟል የተጠቀመበትም ምክንያት አልጋ የሚወክልልን

የ ንጉሳዊ ወይም የ ዘውዳዊ አገዛዝ ሲሆን አልጋን የተጠቀመበት ምክንያት ዙፋን ወይም ወንበር

እንደመጠቀም አልጋ ሁላችንም እንደምናቀው አግዳሚ እና ጠፍጣፋ ነው እና ነቅንቆ ለመጣል አዳጋች እና

የማይቻል ነው። ልክ እንደዛው የ ንጉሱ ማለትም የካፒታሊዝም አሰራር መቼም ቢሆን አይፈነቀልም

“ጀነራሎቹ የ ሙጥኝ” ስላሉበት። እነ ተራ ወታደሮች እና መኳንንቶች ከጀነራሎች አንጻር ከቁምም


Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

አይቆጠሩም ለዛ ይህን ሁሉ የሚናገረው እነሱን ለማረጋጋት ነው። ወደ መሃል “ በማን መሬት ቆመሽ

ንጉሱን ታሚያለሽ” በሚለበት ጊዜ ለማስተላለፍ የፈለገው መልክት አንደኛ እነዚ በጥባጮች የቆሙበት

መሬት ላይ ምንም አይነት መብት የላቸውም ልክ ሃገራቸው የእነሱ እንዳልሆነ ነገርና እና አፍ እላፊ

እካፈታለው ቢሉ ከ አመራሮች ጋር ድራሻቸው እንደሚጠፋ ነው የሚናገረው። በምን እንደሆነ ባላቅም

እርግጠኛ የሆነው “ አልጋው እንዲነቀነቅ የሚፈልግ ማንም ሰው የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ዘውድ

አንድ ቀን በሰላም ሊውል አይችልም” ሲል ነበር። ከዚህ ጥቅስ መረዳት ምንችለው አንደኛ ነገር ቢኖር

ህዝቡ ለ ንጉሱ ክብር እና ፍራቻ አላችው ንጉሱ በፈጣሪ ተቀብተው ዙፋን ላይ ስለተቀመጡ ወይ ደግሞ

ቅሬታ ቢኖራቸው እንኳን ሚሰማቸው ስለሌለ ዝምታን በመምረጥ ኑራዋችውን ይገፋሉ። በተጨማሪም

አቶ ባንቲደሩ ሁሉም ሰው እንደሱ በ ኑሮው ደስተኛ የሆነ ስለሚመስለው ነው ማንም ሰው አልጋው

እንዲነቃነቅ አይፈልግም ይላል። ሲቀጥል አቶ ባንቲደሩ ነገሮችን ቀለል አድርጎ ነው ሚመለከተው አሁን

ለምሳሌ “ ወታደሩም ደሞዝ አነሰኝ ነው የሚለው፤ ሲጨምሩለት ወደ የሰፈሩ ይመለሳል” በሚልበት ጊዜ

ጉዳዩን እንዲህ እንደሚናገረው ተራ ነገር አድርግቶታል ግን ይሄ ጉዳይ በጣም ጊዜ ተስጥቶት ሊታስበትበት

እና መፍትሄው በ ሴኮንድ ሊገኝለት የማይችል ለ ዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ችግር ነው። ነገሮች

እንዲሁ ቢቀሩ ለሱ እልል ነው ምክንያቱም ከማንም በላይ የሚጠቀሙት በ እሱ አይነት የ ኑሮ ደረጃ ያሉት

ግለሰቦች ናቸው።

ውይይቱ እንደቀጠለ ነው አቶ ባንቲደሩም አቁም ሳይባል ሚቋጭ አይመስልም። አሁን ላይ ወሬያቸው ስለ

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነው። አቶ ባንቲደሩ ለ ተማሪዎቹ ያለውን ንቀትና ጥላቻ በዛ ባሉ ምሳሌያዊ

አነጋገሮች ነበር የገለጸው ለምሳሌ ያህል “ ተማሪ? ተልባ ቢንጫጫ በ አንድ ሙቀጫ” በሚልበት ጊዜ

ተማሪዎቹን ዝቅ ዝቅ አድርጎ እያያቸው ነው። ማለትም እንደፈለጉ ሁካታ ቢፈጥሩም ምንም ጠብ

ሚልላቸው ነገር የለም እንዲው በ ከንቱ ነው ሚደክሙት። አቶ ባንቲደሩ ተማሪዎችን ሚያነጻጸራቸው

ጥቃቅን ከሆኑ ፍጥረታቶች ጋራ ነው የነሱን ስልጣን አለመኖር ጎልቶ ለማሳየት ሆን ተብሎ የገባ ነው። በሱ

ረገድ የ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጥቅም የለውም እንዳውም እሱ የሚያስበው ከ እነሱ የ ቀለም እውቀት

ይልቅ እነሱ ከሕይወት የቀሰሙት ተሞክሮ ይበልጣል። “ የጠቅል የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ብ

እስክሪፕቶ አይገለበትም”ይህ አባባል በ ውስጡ ከፊል-ሙሉ ዘይቤ ይዞ ይገኛል ምክንያቱም እስክሪፕቶ

ተማሪዎችንን እና ትምህርትን ስለሚወክልልን። የዚህ አረፍተ-ነገር ዋና ጭብጡ የጠቅል የቀዳማዊ


Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

ሃይለስላሴ መንግስት በ ተማረው ህብረተሰብ ሊሻር አይችልም ሲጀመር የተጠነሰሰው በ ድሮ ዘመን በ

አልተማረው ህዝብ ስለሆነ ያሁንን ህዝብ በ ተማረ ጭንቅላት ሊታለል ወይም ሃሳቡን ሊቀይር አይችልም

ነው ሚለው። ወይ ደግሞ የ ኢትዮጲያ ሰው በ ዱላ እና በ ኋይል እንጂ በ ትምህርት እና ዴሞክራሳዊ በ ሆነ

መንገድ አያምንም ሊሆን ይችላል።

አቶ ባንቲደሩ በ ንግግሩ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ጥሏል የ ሚናገርው ነገር በሙሉ ደግ ደጉንና ወደፊት ምን

እንደሚከሰት ሳያውቅ ዝም ብሎ በሃሰት ልጆችን ተስፋ ያድላቸዋል። አሁን ለምሳሌ “በ 1986 ዓመት

ምህረት ገደማ ብዙ ታላላቅ ለውጥ ተደርጎ ታያላቹ።” በማስቀጠል አቶ ባንቲደሩ ነገሮችን ከ ተፈጥሮ እና

ከ ፈጣሪ ጋር የማያያዝ አዝማማያ አለበት። በተደጋጋሚ “የተፈጥሮ ህግ ነው” ሲል ይስተዋላል።

አይፈረድበትም እሱ ብቻ አይደልም በ ጥንት ዘመን አብዛኛው ዜጋ እያንዳንድዋን ድርጊት የፈጣሪ እጅ

አለበት ብሎ ያምን ስለነበር እሱ ይቅርና ንጉሱ እንኳን በ ፈጣሪ ነው የተሽሙት ብለው ያስባሉ። ወደ እዚ

ተውኔት ስንመለስ ደራሲው ለማለት የፈለገው አቶ ባንቲደሩ ያካበቱት ሀብት በ ፈጣሪ ዘንድ እንደ መብት

ተለግሶላቸውና እነሱ በሚሞቱበት ወቅት ወደ ተተኪዎቻቸው ይሽጋገራል ልክ እንደ “ፈረስ ኮርቻ”።

በተጨማሪም “ የዝጌር ፍጥረት እኩል አደለም’ ብሏል ማለትም በመሃከላችን ልዩነት ሊፈጠር የሚችለው

በ ህይወታችን ምን ማረግ እንዳለብን የወሰንን ቀን ነው። የሰራ ያገኛል ዝም ብሎ ደሞ የሚጋደመው የ

እጁን ድህነት ያገኛል። በ አቶ ባንቲደሩ ውስጥ የሱን ትወልድ መመልከት እንችላለን። የሱ ትውልድ

አስተሳሰብ ከዘመኑ ጋር አብሮ ያልዘመነ ነው። ከዚህ በኋላ ያሉት ወሬዎች በሙሉ የሚሰብኩት ስለ

የወደፊቱ ሰላም እና የ ብልጽግና ዘመን ነው ልክ እንደ ምርቃት ልንወስደው እንችላለን።

በተደጋጋሚ ስለ ዘር ማንሳቱን በተለያያ አጋጣሚ አላቆመም። የ አሰግድ ወላጆች በ ጋብቻው ደስተኛ

ያልሆኑ ይመስለዋል በተለይ ወይዘሮ ሙሉሸዋ ምክንያቱም እሷ የመጣችው ከ አቶ ነጋሲ የ ዘር ሀረግና

ዘራቸው የጥንት ነው ማለትም የሚመደቡበት ከ ከፍተኛው መደብ ነው እና ልጃቸውም እንዲጋባ

ምትፈልገው በለጥ ካለ ዘር ነው። ይሄ ለ አቶ ባንቲደሩ ትልቅ ራስ ምታት ነው የሆነበት ምክንያቱም እሱ

እዚ ደረጃ የደረሰው ከ ባዶ ተነስቶ ባይሆንም ሰርቶ ለፍቶ ነው። ይህ የ ዘር ነገር በ ራስ መተማመኑን

እንዳሳጣው ግልጽ ነው። የሱ ዋናው አስተሳሰቡ የሚታየው እዚህ ላይ ነው “ ሰው ለራሱና ለቤተሱቡ

እስካሰበ ድረስ ምንም ቢደርስበት ለ ክፉ አይሰጠው”። ሲጀመር እሱ ለራሱ እና ለ ቤተሰቡ ብቻ ነው

ሚያስበው ስለሌላው ማህረስብ ግድም እንኳን አይሰጠውም ሁሉም ሰው የራሱ የሚለው ችግሮች አሉበት
Kaleab Mebratu Gebreigziabher Amharic Written Task

እና ችግሩን ተጋፍጦ ማሽነፍ ፋንታው የራሱ ነው። ከሁሉም ሰው ጋር አንድ ሆኖ መታየት የሚፈልግ

አይነት አደለም ልክ እንደ “ንቦች በ አንድ ቀፎ” ውስጥ። እሱ እዚ ደረጃ ሊደርስ የቻለው ስነፍ ስላልሆነ

ነው እና በዚህ ጊዜ ስኬቱን ሊጋሩት የሚችሉት እሱ እና ቤተሰቦቹ ናቸው ብሎ ያምናል።

በማጠቃልያ ይሄ ተውኔት በ ድሮው ማህረስብ ወስጥ የነበረውን ግዙፍ የሆነውን የ ዘር እና የ መደብ ክፍፍል

በሰፊው ይዳሥሥልናል። በተጭማሪም በ ነባሩ እና በ ዘንድሮው ህዝብ መካከል ያለውን ሰፊ የ አሰተሳስብ

ልዩነት እንድናይ ረድቶናል። ይህን ለማረግ አቶ ባንቲደሩን እንደ ምሳሌ ልንወስድ እንችላለን ምክንያቱም

እሳቸው የ ነባሩን ማህረሰብ ስለሚወክሉልን።በ አጭሩ አቶ ባንቲደሩ በ አሁን ባለው ስርአት በጣም

የተስማማቸው እና እንዲሁ ቢቀጥል የሚመኙ፣ ትልቅ ቦታ ለመድረስ ቀንና ለሊት የደከሙ፣ በ ዩኒቨርስቲ

ሳይሆን በ ሕይወት ዲግሪ የጫኑ፣ ከበታቾቹ ላሉት ክብር ማይለግሱ፣ ለጥቅማቸው ሟች እና በ

መጨረሻም ከሁሉም ነገር በፊት ለ ቤተሰቦቻቸው ቅድምያ እንደሚሰጡ ልንመለከት እንችላላን።

መርማሪው ከመምጣቱ በኋላ ሌላ ማናቃቸው እና ጥያቄው ውስጥ ያልተካተቱ ባህሪዎቹ ይገለጥሉናል

ማለት ነው።

You might also like