Professional Documents
Culture Documents
ብሔረ ጌ
ይህች መጽሏፍ
በመጀመሪያ 1900 ዓ.ም. በሮማ ከተማ ታተመ።
2
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መግሇጫ
ሀ - በዙች መጽሏፍ ውስጥ በአሁኑ መን ዯብዜ ብሇው የሚታዩ አንዲንዴ ቃሊት ዯራሲዋ
በአጋጁት ጊዛ የነበረውን ስሜት እንዲይቀንሱ በማሇት ሇንባብ እንዱስማሙ ተስተካክሇው
እንዲለ ተጽፈዋሌ።
ሇ - መጽሏፊቱ በአገሊሇጽ ዴርብርብ ቃሊትን ስሇምታበዚ ያረፍተ ነገሮቹ እጥረት ሇአሳብ ቦይነት
እንዱመች በማሇት መሰረቱን አሌሇቀቀም።
ሌብ ወሇዴ ታሪክ
4
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያ ተማርኮ የቀረው ዯጃዜማችም አረመኔው ወዲገሩ እንዯተመሇሰ በማረከው እጅ ተሸጠ።
ማራኪው ሰው ግን ሲማርከውም ሲሸጠውም ትሌቅ ሰው መሆኑን ሳያውቅ እንዱያው
እንዯማንም ሰው ነው የሸጠው።
ያንኑ መከረኛ ዯጃዜማች የገዚ አረመኔ ግን ቁመቱን ዚሊው አምሮ ባየው ጊዛ “ማሇፊያ
ብርቱ ባሪያ አገኘሁ” ሲሌ ዯስ አሇውና ብርቱ ብርቱ ሥራ እያ እንዯ ሇጓሚ ሣር ያሳጭዯው፡
እንዯቋሚ እንጨት ያስፈሌጠው እንዯጎረድማን ዴንኳን ያስጭነው ተራዲም ያሸክመው ጀመር።
እርሱ ግን ያሌሇመዯው ነገር ነውና ከዙህ ሁለ ስራ አንዴ የሚሆንሇት ነገር አጣ። ሣር ሌጨዴ
ቢሌ የሇሰሇሰው የጨዋ ሌጅ እጁ እንዯሽንኩርት ተሊጠ። ብርጭቆ ብርላ ይጨብጥበት በነበረው
ጣቱ ምሳር ቢጨብጥበት ጉብር አወጣ፤ ይህም ሆነ ያም ሆነ ያው የጥንት ዯጃዜማች
/የነበረው/ የዚሬው ባሪያ አዱሱ ጌታው እንዲይቆጣው ምናሌባትም ባሌተወሇዯ አንጀቱ
እንዲይገርፈው እየተገጠጠ ሥራውን “አሌሁህ አሌሁህ” ይሌ ጀመር። ነገር ግን ያኮረሰው እጁ
ጭራሹን ተሞሸሇቀ። ተራዲ የሚሸከምበት ጫንቃውና አጉርቦ የነበረው ሁለ ተገሸሇጠና
የማይሆንሇት ሆነ። ጌታው ግን ሇሥራው የሇገመ መስልት ይቆጣውና ሇመግረፍ ያንገራግረው
ጀመር። ይኸው አዱስ ገብ ባሪያ ግን “እንግዱህ የምታዯርገውን አዴርግ እንጂ ተችልኝ
የምሠራሌህ ነገር አሊገኝም” አሇና ጫንቃውንም እጁንም አሳየው።
ከዙህ በኋሊ ጠራና “አንተ ካፊር እኔ ተማረከህ ሰው ብዘ ገንብ አፍስሼ ገዚሁህ፣ አሁን
የፈቀዯኝን ብሠራህ ይቻሇኛሌ፤ ነገር ግን ታሳዜነኛሇህ። አሁንም ወዯ መድችህ ሊክና እሌፍ
ወቄት ወርቅ አስመጥተህ ስጠኝና አገርህ እንዴትሄዴ እሇቅሃሇሁ” ብል ነገረው። ያ ዯጃዜማች
ግን እንኳን አገሩ ጠፍቶ ንጉሡ ሙቶ ከብቱ ተርፎ በሬው ሊሙ ተነዴቶ ይቅርና ይኽም
ባይሆን ታገሩ በጌትነቱ ሳሇ ሇጀግና መስጠት፣ ሇዴኃ መርጠብ፣ ሇተራበ ማብሊት፣ ሇታረ
5
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ማሌበስ እንጂ ገንቡን ወዯ ኋሊ ማዴረግ ሇነገ ማሇት አያውቅም ነበርና “የምከፍሇውም የሇኝ፣
ዴኃ ነኝ፣ እንዯ ወዯዴህ አዴርገኝ” ብል መሇሰሇት።
6
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እናቲቱም ባሎን እያሰቡና እየተከዘ መበሊሊት ሆነ። በማግሥቱም ሁለም እየሥራቸው
ይሠማራለ።
7
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መጥቻሇሁና ይፍቀደሌኝ” አሇ። ባሇቤቱ ግን ዋሕዴን ተግር እስከ ጥፍሩ ከራሱ እስከ ጠጉሩ
አመሳቅል አየውና ዯንቆት “እንዳታ! ጎረድማን እንዱህ ኑሮ! ጫኝ እንዱህ ነው እንጂ!
ምንኛውን” እያሇ ይጉተመተም ገባ። ዋሕዴም ነገሩን እንዯናቀበትና እንዲሌተቀበሇው ባየ ጊዛ
“ጌታው ከወፍራም አባያ የቀና ኮሳሳ በሬ አብሌጦ ያርሳሌ። እንዯዙሁም ሇጋነቴን አይተው
ካሌናቁኝ ጭነት አይቸግረኝ” አሇው።
8
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አባቴ፤ ጥንቱንም ቢሆን መስጠት መሇገሥ ያውቅ ነበር እንጂ ገንብ መቆጠብ አያውቅም
ነበርና ገንብ ከወዳት እናግኝ? አሁን ንጉሡ ሰጥቶ እንዲያስፈታው እንዯሚያውቁት በሏን
ሞተ። አገር ጠፍቶ ሰዉ አሌቆ ከብቱ ተነዴቶ ክምሩ ተቃጥል ገንብ ከወዳት ይገኝ?
ሀብታሙ ነጋዳም እያነ የዋሕዴን ታሪክ አስተውል አዲመጠና ሲጨርስ “እኔ ጉዲይ
አሇብኝና ወዯ ዴንኳኔ እመሇሳሇሁ፤ አንተም ወዯ ቤትህ ተመሇስ፣ እግዙአብሔር ይሁንህ”
አሇና፣ ነጋዳ መቼም ሇምናሌባት ገንብ ከእጁ አይሇይምና ይዝት የነበረውን ገንብ እስከ
ከረጢቱ ተጁ ጣሇሇት። ሳይሇያዩ በፊት ግን ያው ሀብታም ዋሕዴን “ያባትህ ስም ማነው?
የገዚውስ አረመኔ ስም ማን ይባሊሌ? ያሇበት አገርስ ወዳት ነው?” ብል ጠየቀ። ዋሕዴም ያንን
ከረጢት ወርቅ እንዯሞሊበት፣ በእጁ እንዯያ ዯስ ብልት ከንፈሩም እየተንቀጠቀጠ አንዯበቱም
እየተርበተበተ ያባቱን ስም እስከቦታውና እስከ ምሌክቱ ነገረውና፣ ሁሇቱም ተሇያይተው
እየሰፈራቸው ሄደ።
9
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሊይ ዯስታ ተጨመረሇትና እየፈነዯቀ ሲሮጥ ከቤቱ ገባና ሇናቱና ሇእኅቱ ወርቁን ሆጭ
አዯረገሊቸው፤ ነገሩንም ነገራቸው።
10
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አጠራቅመው ሰዯው ሇማስሇቀቅ እንጂ ከዙያ በፊት አሇመሰዯዲቸውን ዏውቀው ነገሩ
ረቀቀባቸውና የሚመሌሱት ቃሌ አጡ። ብቻ እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀመር። በዙሁ መካከሌ
አንዴ ቃሌ የሚመሌስሇት ባጣ ጊዛ አባትዮው ወዯ ዋሕዴ ዝረና “አንተ ትሆን ሌጄ? ከወዳት
አገኘኸው?” አሇና ጠየቀው። በዙህ ጊዛ ዋሕዴ ምን ይመሌስ? እርሱ እንዲሌሰዯዯ ያውቃሌ።
በኋሊ ግን ገና አባትዮው ዓይን ዓይኑን እየተመሇከተ መሌስ ሲጠብቅ ሇዋሕዴ የዙያ የሇጋሥ
ሰው ነገር ትዜ አሇውና፣ “አሁንስ ገንብ የሰዯዯውንና አንተን ያስሇቀቀህን ሰው ዏወቅሁት።
አባዬ እኔ አሌምሰሌህ።” አሇና፣ የዙያን የሇጋሥ ነጋዳ ነገር፣ ሇእርሱም ገንብ መስጠቱን
ኋሊም ያባቱንና የገዚውን ያረመኔ ስም፣ ያሇበትንም ያገሩን ስም መጠየቁን ተረከሇት።
ዋሕዴ ግን ተመሌኩ በቀር የዙያን ሀብታም ነጋዳ እንኳን ስሙን አገሩንም ሇይቶ
አሊወቀም፤ አሌጠየቀም ነበርና ተጨነቀ። “እንግዱህ ያን ዯግ ሰው፣ ያን መሳይ ሇጋስ ሰው፣
ያባቴን ታዲጊ፣ የእናቴን፣ የእኅቴንና የኔን እንባ አዴራቂ ወዳቱን መሌሼ /የትኛውን አቅጣጫ
ይዤ/ ብሄዴ አገኘዋሇሁ? እርሱን ሇማግኘት ምን ባዯርግ ይሻሇኛሌ?” እያሇ ተጨነቀ።
በመጨረሻ “እርሱን ታሊገኘሁና ያባቴን በዯኅና መግባት የኛን ዯስታ የኛን ዓሇም ታሌነገርሁት
እግሬ እስቲነቃ፣ እስትሞትም ቢሆን ዓሇሙን እየዝርሁ እፈሌገዋሇሁ እንጂ ተቤቴ
አሌቀመጥም” ብል ሲያቆም ዋሕዴ ስንቁን ቋጥሮ ንጉን ይዝ በማግስቱ ከመድቹ ተሊቅሶ
ተሰነባበተና ሇመፈሇግ ተነሳ።
ይኽን በመከረ በማግስቱ ዋሕዴ ከዙያ ከተማ ወጣና በየትም ሳይሌ አንደን መንገዴ ይዝ
መዯብር ፍሇጋ ይጓዜ ጀመር። ይሄዴ ይሄዴና ከጉብታ ሊይ ወጥቶ ባገሩ ዘሪያ ወይ መዯብር
ወይም ነጋዳ ጉዝ ሇማየት ይመሇከታሌ። ሰውም ተመንገዴ ሲገጥመው መዯብርና ነጋዳ ብቻ
ነው የሚጠይቅ። “ነጋዳ በዙህ አሇፈ፣ ከዙህ ሠፈረ” ያለት እንዯሆነ ወዯዙያው ሲሮጥ እየሄዯ
ከነጋዳው መካከሌ ያን ዯግ አዴራጊ ነጋዳ ይፈሌጋሌ። መሌኩን ካሊየው በቀር ስሙን
አያውቅምና የሚፈሌገውን ሰው ተነጋዳዎቹ አንደን “እገላ ወዳት ነው? ወዳትስ ዯረሰ?” ብል
12
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
መጠየቅ አይሆንሇትም ነበር። ከዙያ መዯብር ሲያጣው ወዯ ላሊው መዯብር ሲሄዴ ሲሄዴ፣
ተመሸበት ሲያዴር፤ ዋሕዴ ሆየ አንዴ ቀን ሲጓዜ ውል መንዯር ተላሇበት ከምዴረ በዲ ዯረሰ።
ከዙያው ምዴረ በዲ መካከሌ በሩቅ ትሌቅ የነጋዳ ሠፈር አየ። ነጋዳ መሆኑንም በመዯብሩ
ሇየው። ዋሕዴ ያንን መዯብር ባየ ጊዛ አዯባበሩም መጠኑም ያን ሃብታም ባየ ጊዛ ያየውን
መዯብር መሰሇውና ሇጊዛው ዯስ አሇው። ተዙያ ሠፈር ሇመዴረስ አስቦ ይባክንና ይሮጥ ጀመር።
ወንዚወንዜ የበዚበት ሜዲ ነበረና ቢሇው ቢሇው ርቀቱ ያው ነው። መዯብሩ በመጫኛ አስሮ
ወዯኋሊ እንዯጎተቱት ሁለ ወዯ ኋሊ የሚርቅ እንጂ የሚቀርብ አሌመስሌ አሇው። መንገደ
ቢሄዯው ቢሄዯው አሌገፋህ አሇው። ጊዛው ግን ተማሸ፤ ፀሀዪቱም ተቆሇቆሇች፤ ዋሕዴ ግን
ከመዯብሩ ሳይዯርስ በፊት ምዴር መሸበት። በማኸሌ ቤት ጀንበር ጠሇቀችና ዴንግዜግዜ አሇ።
ቀጥልም ጨሇመና ሊይን ነሣ። በወፎች ጫጫታ ሥፍራ የፌንጣው ዴምጥና በያረንቋው፣
በየረግረጉ ያሇው ጉርጥና ጓጉንቸር ዋካታ ተተካበት። ይሌቁንም በዙሁ መካከሌ ባንዴ ወገን
ተኩሊው ባንዴ ወገን ቀበሮው ሲጯጯሁ ሳሇ ባንዴ ወገን ዯግሞ ጅቡ እሙኝ ይሌ፣ ነምሩ
ይጓጉር አንበሳው ይገሰሌ ጀመር። ይኸ ሁለ ሲሆን ዋሕዴ ብቻውን ከምዴረ በዲው መካከሌ
ሆኖ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ይጓዚሌ። ወዯ ምሽቱ አቅራቢያ የወፎች ጫጫታ እንዯ ባሌንጀራ
ሆኖት ነበር። ኋሊ ግን ያራዊት ዴምጥ በቀኝና በግራ ከበበው፤ ስሇዙህ ተጨነቀ። ከዙያው
እንዲያነጋ ቤት የሇ፣ ተምን ይጠጋና ይዯር? ተሜዲው ሊይ እንዲያዴር አራዊት ሉናጠቁት ሆነ።
ዋሕዴ በዙህ ጊዛ ምን ያዴርግ? ከዙያው ተኝቶ አውሬ ቢበሊውስ፣ ቢሆንሇት በቁሙ እየተከሊከሇ
መጓዘን መረጠና “ምንም ቢሆን ታየሁት መዯብር ሳሌዯርስ አሊዴርም” ብል ሲሄዴ ሲሄዴ
ጨሇማው እያዯረ ባሰ። ጥቅጥቅ ያሇ ጨሇማ ሆነበትና መንገደም ጠፋው፣ ሌቡም መባባት
ጀመረ። በቀኝም በግራም በፊትም በኋሊም ቢያይ ሁለም ጅብ፣ ሁለም ነምር፣ ሁለም አንበሳ
ሆኑበት። “ከአሁን አሁን ጅቡ ሳሊየው መጥቶ ጎኔን ይበትረኛሌ፤ ነምሩም ል ያንቀኛሌ
ወይም አንበሳው ይሰብረኛሌ ወይኔ ሆዬ! ዚሬ ታንደ ባመሌጥ መቼም ታንደ አሊመሌጥ” እያሇ
ነፍሱን ብንን ብንን ማዴረግ ብቻ ሆነ ሥራው። ምን ያዴርግ፣ ዋሕዴ ፍርደ ነው፤ ዯግሞም
ገና ጮርቃ ሌጅ ነው። ዋሕዴ ይኸ ሁለ ሲሆን ያንን መዯብር ያየበትን አንጣር ይዝ ቀስ በቀስ
እያሇ መጓዘን አሌተወም። አንዴ ጊዛ ግን በጨሇማው አሻግሮ አንዴ ቁጥቋጦ አየና አራት
እግር ያሇው የውነተኛው አንበሳ መሰሇውና ነፍስና ስጋው ተሇያየበት። ጉሌበቱ እየተብረከረከ
ትክ ብል ሲያየው ጊዛ ያው በፍርሀት የተፈጠረ አንበሳ የሚንቀሳቀስ፣ ልም ሉይው ሌበሌን
ሌተው የሚሌ መሰሇው፤ በዙህን ጊዛ ዋሕዴ ብሌኅት ያገኘ መስልት፣ ሇዙያ አንበሳ ብዘ ሰው
13
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የመጣበት እንዱመስሇው ብል ዴምጡን ባስራ አምስት አይነት እያረገ፤ አንዴ ጊዛ ቀጭን፣
አንዴ ጊዛ ጎርናና እያዯረገ አንዲንዴ መንጋ ሰው እየጮኸ “ክበብ፣ አያምሌጥህ አይዝህ፣ በዙያ
እሇፍ” እያሇ ዴምጡን አንደን በአንደ ሊይ እያነባበረ ይጯጯህ ገባ። ዋሕዴ ግን ብቻውን አንዴ
ፍጥሩን ነበር። ከጨሇማው ጋር እየተዯባሇቀ ይሳከር ተነበረው ተገዚ ጥሊው በቀር የዙያን ጊዛ
ምንም ባሌንጀራ አብሮት አሌነበረም። ያ በከንቱ የታማ ቁጥቋጦ ምንም ባሌንጀራ በአንበሳ ስም
ቢጠራ፣ ነፍስ የሇውምና አሌሸሽሇት ሲሌ ጊዛ ዋሕዴ መንገዴ ሰብሮ ይሄዴ ጀመር። ዘሮ ባየው
ጊዛ ግን ያው በገዚ ፍርሀቱ የፈጠረው የቁጥቋጦ አንበሳ የሚከተሇው መሰሇው። ዋሕዴ ሆዬ
ጉሌበቱም በፍርሀት እየተብረከረከበት መሄዴ ተሣነው። ከዚፍ ሊይ ወጥቶም እንዲያመሌጥ ከዙያ
ምዴረ በዲ እንዲጋጣሚ ሁለ እንኳን ትሌቅ ዚፍ የምጣዴ መሰቅሰቂያ የሚሆን እንጨትም
አሌነበረም።
ተዙህማ ወዱያ ዋሕዴ ተጨነቀ፣ ፍርሀቱም እያዯረ ነገሠበት፣ የሚያየውም ጥቁር ነገር
ሁለ አውሬ ብቻ መሰሇው።፡ ከፍና ዜቅ እያሇ በዲባቱ እያየ መንገደን እየሇወጠ ሲሄዴ በግራው
አንዴ ትንሽ ዋሻ መሳይ ዯርሶ ገች አሇበትና የዋሕዴ መብረክረክ ባሰ በዴንጋጤ ቀጭን ሊብ
መጣና በገሊውም በፊቱም ተሰራጨበት። “ታንደ አንበሳ ባመሌጥ ከሁሇተኛው ዯግሜ ዯረስሁ።
አሁንስ ቁርጥ ነው አሊመሌጥም” እያሇ ዋሕዴ ይጨነቅ ጀመር። ቁሞ እንዯ ቄጠማ እያረገረገ
ዴምጡን እንዯፊተኛው በያይነቱ ከፍና ዜቅ እያዯረገ በውኃ ጥማት የከረረው ጉሮሮው
እስቲነቃና እስቲሰነጠቅ ዴረስ “ክበብ፣ አያምሌጥህ” እያሇ ይጮህ ጀመር። ነገር ግን ሲያየው
ጊዛ ምንም አይሸሽሇትም። የናቀው መሰሇውና እንዯገና አጥብቆ ተንጠራርቶ ሲጮህ ጊዛ ያው
ነው። ኋሊ ግን ዴምጡም ሰሇሇበት ጉሮሮውም የባሰውን ተጋበት። ከዙያ ታስራ አምስት
ዓይነት ዴምጡ አንደንም ዓይነት ሇመጮህ ቸገረው። ያው የውሸት አንበሳም ንቆት ዜም ያሇው
መሰሇው። ዋሕዴ ከዙህ በኋሊ መጠርጠር ጀመረ። “ዴንገት ላሊ ነፍስ የላሇው ጥቁር ነገር
ይሆናሌ” ማሇት ጀመረ። ቀጥልም በውሌ ሇማስተዋሌ በጉሌበቱ ተንበረከከና ትክ ብል “ከአሁን
አሁን ይንቀሳቀስ ይሆን” እያሇ ሲመሇከት፣ እንዯገናም “ጥቂት ጥቂት የሚንቀሳቀስ ይሆን” እያሇ
ሲመሇከት ጥቂት ጥቂት የሚንቀሳቀስ መሰሇው። ዓይኑን ሳያጥፍ አተኩሮ እንዯገና ባስተዋሇ
ጊዛ፣ ይሌቁንም ከመንቀሳቀሱ ወዯ እርሱ መራመዴ የጀመረ መሰሇው። አተኩሮ ከማየቱ የተነሳ
በዓይኑ እንባ ሞሊበት። ዋሕዴ ግን ጊዛ ያጠፋሁ መስልት እንባውን መጥመቅ ትቶ ባየ ጊዛ፣
ይሌቁንም ያው እንባው እያዯናገረው የዙያን አውሬ ርምጃ ወዯ እርሱ የተፋጠነ አስመሰሇው፤
በመጨረሻ ግን ዋሕዴ ዓይኑን ከዙያው አውሬ ሊይ እንዯተከሇ ባባና ተተንበረከከበት ጠጠር
14
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አፍሶ ወዯፊቱ ብትን አዯረገ። ሇመከራ አጋዥ አይታጣምና ዋሕዴ ሊዯረገው ሁለ ነገር ምስክር
ሆና ተሸሽጋ ስታይ የነበረች አንዴ ዴርጭት “ተተሸሸግሁበት ተገሇጥሁ” ብሊም እንዯሆነ
አይታወቅ ሳር ቅጠለን በክንፏ አስሸብራ ተነስታ በረረች። ዋሕዴም ያው አውሬ ዯርሶ አነቀኝ
መስልት ትንፋሹን አቋርጦ እንዯሞተ ታሇበት ተንራጋና መንቀሳቀሱም ቀረ። ቆይቶ ቆይቶ
ግን “ነፍሴ አሇች ወይስ ሙቻሇሁ” ብል አሰበ። ቀጥልም በአውሬው መነከሱንና አሇመነከሱን
ሇማወቅና ሇመረዲት በጆሮው ቢያንቋቋም ምንም አሌሰማህ አሇው። ዓይኑን ግን አውሬ
ሲነክሰው ጨክኖ ማየቱን ቢፈራ ጨፍኖት ነበርና ሲፈራ ሲቸገር ገርበብ አዴርጎ ቢያይ ተፊቱ
እንኳን አንበሳ ምንም ጥንቸሌ አሌነበረም። ዋሕዴ ከዙያ ወዱያ ነፍስ አጋባና ጫን ተንፍሶ
ተነሳ። አሻግሮ ባየ ጊዛ ያ አውሬ ጥንት ተነበረበቱ አይንቀሳቀስ፣ ምን አይሌ፣ ዜም ብል
አየው። ዋሕዴ ከዙያ ወዱህ ትሌቅ አሳብ ገባውና “ወይስ ምንም አውሬ አሌመጣም ኑሯሌ፣
ወይስ አውሬም አይዯሌ ኑሯሌ? ይሁንና ሲመጣ ባይኔ አይቼዋሇሁ፤ ወይስ ነካክሶ ጥልኝ ሄዯ”
እያሇ ገሊውን ቢዲስስ አሌተነካም። “ምንም ይሆን በገዚ ፍርሃቴ ባብቼ ኑሯሌ መውዯቄ፣ እንኳን
ሰው አሊየኝ፣ በገዚ ፍርሃቱ ወንዴ ሌጅ ሆኖ እንዳት ይወዴቃሌ” እያሇ እየተዯመመ እንዯገና
ጉዝውን ያ።
ዋሕዴ እንዯገና በረታ፣ ከዙያ መዯብር ሳይነጋ በፊት ሇመዴረስ ተመኘ። ጊዛው ግን
ተዋርዶሌ፤ ተመንፈቀ ላሉት ዜቅ ብሎሌ። ዋሕዴ እንዯ ባሌንጀራ አዴርጎ ሲወዲቸው የነበሩት
እነስዴስቱም ጠፉ። ጨሇማውም እጅግ በረታ ። ነገር ግን አንዴ ጊዛ ተመንገደ ሲወጣ አንዴ
ጊዛም ጥቃሽ ሲያገኝ፣ ሲሄዴ ሲሄዴ የመዯብሩ እሳት ይታየው ጀመርና ዯስ ብልት እየተበራታ
ሲጓዜ ታንዴ ወንዜ ቁሌቁሇት ዯረሰ። ጥቂት ዜቅ እንዲሇ የሠፈሩም እሳት ሊይኑ በሸጡ ጀርባ
ተሠወረው። ጨረቃ የሇ የንጋት ኮከብ እንኳን ገና አሌወጣች ምንም ላቱ ቢዋገዴ ጨሇማው
ይሌቁን ባሰ እንጂ አሌተሻሇም። በዙያው ሊይ ዯግሞ የግራው የቀኙ ወንዚወንዘ ገረገንብ ጥሊ
ታከሇበትና ጨሇማው ዓይን ቢወጉ አይታይ ሆነ። ዋሕዴ በዙህ ጊዛ ቁሌቁሇቱን ተዲፋ።
መንገደ ግን ጠፋው፤ ምን ይሁን? ሳሌዯርስ አሌቀርም ብሎሌና ከፎከረበት የነጋዳ ሠፈር
ሇመዴረስ በዙያ ጥቅጥቅ ዴንጉር ጨሇማ ቁሌቁሇቱን በእጅና በእግሩ እየተተማተመ በቅምጡ
ሲንኳተት በንብርኩም ሲዴህ አንዲንዴ ጊዛም አሌሆንሇት ሲሌ ፊቱን ወዯመጣበት አዘሮ
እግሩን ወዯሚሄዴበት አስረዜሞ ማጭዴ እረስቶ እንዯመጣ ሇጓሚ በጁ ሣር ቅጠለን
እየጨበጠና እየሟጠጠ እየጓጠጠም እሾም አይቀረው እንዯ ሏር ጎፍሊ እየጨባበጠ በዯረቱ
ሲሳብ ሲጋፍና ሲጎተት ተወራጁ ወንዜ ዯረሰ።
15
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያ ወራጅ ውኃ ሇዋሕዴ ጥሩም ይሁን ዴፍርስ አሌታወቀውም። ገና በጥማት ሌሳኑ
ታስሮ ነበርና ተጎንብሶ እንዯ ገሌዲ ጠጅና እንዯ ገፈታማ ጠሊ ሇስም ያህሌ ተሊይ ያሰፈፈውን
አረንጓዳና ስሌባቦት እፍ እፍ እያሇ በትንፋሹ ገፈፈና የተቻሇውን ያህሌ አንስቶ ጥማቱ
እንዲሇፈ፣ “ተመስገን ጌታዬ” አሇና ተሹሌ ዯንጊያ ሊይ ቁጭ ብል የመሻገሪያውን መሌካ ያይ
ጀመር። ቢመሇከት ሁለም ጥሌቅ መሰሇው። ቋሚ ይሁን ጠሉቅ ውኃው አሌታወቅ አሇው።
መሻገሪያውም በሊይ ይሁን በታች አሌታወቅህ አሇው። ዜም ብል እንዲይገባ ዋሕዴ የዋና ነገር
አያውቅም ነበረና ፈራ። ይሌቁንም ያ ወንዜ ፏፏቴ አሌነበረውም “ዜም ያሇ ወራጅ ውኃ ሙለ
ነው” ሲለት ሰምቶ ነበርና ፈራ “ምን ሊዴርግ” እያሇ ገና በሌቡ ሲያመናምን እንዲጋጣሚ
እንዯእርሱ ውኃ ጥም የተባሰች በቅል ከመዯብር ችካሎን ነቅሊ አምሌጣ ዯረሰች። ዋሕዴ
“አውሬን ይሆን” ብል ሲዯናገጥ አፍንጫዋንና ከንፈሯን ስታማታ በቅልነቷን አውቆ ሲረጋጋ፣
ያችው በቅል ገስግሳ ከውኃው እስተንቢያዋ ገብታ ተነክራ ተዙያ ውኃ ትግፍሇት ጀመር። በዙህ
ጊዛ ዋሕዴ በዙያች በቅል ምክንያት የውኃውን ግሌብነትና ቁምነት አውቆ አስረገጠና “ቶል
በቅልዪቱ ጠጥታ የጠገበች እንዯሆነ አትያኝም ታመሌጠኛሇ” ሲሌ ወዯ በቅልዪቱ አንጣር
አዴርጎ ውኃውን በንጉ እየሇካ ተሻገረና ተማድው ዯረሰ። የዙያን ጊዛ በቅልዪቱ አንዴ አፍታ
ተዙያው ውኃ ግፋሇት አንገቷን አቅንታ ጆሮዋን እያርገበገበች ሇሁሇተኛው ገና “ሌበሌን
ሌተው፣ ይብቃኝ አይብቃኝ” ስትሌ ዋሕዴ ቶል ብል “እንቺ፣ እንቺ” እያሇ እያባባሇ ቀረበና
ያዚት። እርሷም ገራም ነበረች። ትራገጥ መስልት አስቀዴሞ በእጁ ይዲስሳት ጀመር። በቅልዪቱ
ግን መዴከሙን አውቃ “ይረፍብኝ” ብሊ ያነች መስሊ ዜም አሇችው። መገረሟን አስረገጠና
ዋሕዴ ወዯ ትሌቅ ዯንጊያ ስቦ አቀረበና ተቀመጠባት። ቀጥልም ወዯ መጣችበትም ወገን
አቃንቶ “እንግዱህ ወዯ ሠፈርሽ ውሰጅኝ” አሇና አሳቡን እርስዋ ሊይ ጣሇው። በቅልዪቱም
ዋሕዴ የሚሇው ነገር እንዯገባት ሁለ የመዯብሩን መንገዴ ይዚ ሳትነቀንቅ ይዚው ትጓዜ ጀመር።
ብቻ አንዲንዴ ጊዛ ሇምሇም ሣር ባየች ጊዛ ቆማ ትነቻቸፍና እርሷ በጠዲት ጊዛ እንዯገና
ተባሌንጀሮቿ ሇመዯባሇቅ መንገደን ትይዚሇች። ዋሕዴ ግን ቀስ አዴርጎ እንዲይወዴቅ ብቻ
ጋማዋን ተመጨበጥ በቀር አሌኯሇኯሊትም፤ “ሂጂ መጭ” አሊሊትም፤ እንዱያው እርስዋ
እንዲሇች ተዋት። ስሇምን እርሷ በፈቃዶ ነውና የተያችሇት መጭ እያሇ በግሩ መጎሳሰም
ወረታዋን ማጥፋት መሰሇው። “አሁንስ ቢሆን የማን እንግዲ በተቀባይ ቤት ገብቶ ያዜዚሌ?”
እያሇ ያስብ ነበር ። ያች የዋሕዴ በቅል ግን ተሁለም ሳትዯርስ እያገመች ስትወስዯውና
ከሠፈሩ ሉዯርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ያችኑ በቅል ሲፈሌጉ የነበሩ ጎረዲማኖች ደካ ሰምተው
16
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሲሮጡ ዯረሱ። በዙህ ጊዛ ዋሕዴ አሇመገንቡ በሰው በቅል መቀመጡን ያውቃሌና ፈርቶ
ተበቅልዪቱ ወረዯና ሇመሸሸግ አሰበ። ነገር ግን ጎረድማኖቹ በቅልዪቱን ከበው በመጫኛ ሲይዘ
እርሱም በዙያው ተገኘና ተያ። እንዲያመሌጥ እግሩ በጣሙን ተሳስሮ ነበርና ቸገረው።
ጎርድማኖቹ ግን ተበቅልዪቱ አጠገብ ባገኙት ጊዛ፣ እርሷን ከችካሌ አውሌቆ ሰርቆ ሉሄዴ ሳሇ
የዯረስንበት መስሎቸው “አንተ ላባ የታባትህ” እያለ በቆመጣቸው ይቸበችቡት፣ ፍዲውን
ያሳዩትና ይሰዴቡት ጀመር። ዋሕዴ ግን “እባካችሁ እንዴ ጊዛ ስሙኝ፣ ላባም አይዯሇሁ” እያሇ
ቢጮህ ቢቀባጥር ማን ይስማው፤ ምሊሹ “አንተ ላባ፣ አንተ ቀጣፊ፣ ስትሰርቅ ዯርሰንብህ
ላባም አይዯሇሁ ትሌ ጀመር” ብቻ ሆነ። ከዙህ ወዱያማ እየገፋፉ ወዯ መዯብሩ አዯረሱና
ገሚሶቹ በቅልዪቱን በካስማ ሲያስሩ፣ ገሚሶቹ ዋሕዴን ገሇበጡና አሰሩ። ያን የመሰሇ ቀንበጥ
ሇጋ ሌጅ የፊጥኝ ተገሌብጦ ምን ይቻሌ? መተንፈስም አቃተው። ትንፋሹም ባጭር ባጭሩ
ሆነ፣ ቅትት ቅትት የሚሌ ሆነበት። የዙያን ጊዛ ሊየው ሰው ዋሕዴ እጅግ ያስሇቅስ ነበር።
የፊጥኝ ባሎሇበት ነገር ተገሌብጦ እንዯሚታረዴ ፍየሌ እጅና እግሩን ተኮዴኩድ ተጋዴሞ
በቅልች አንዲንዴ እግራቸውን ብቻ በገመዴ ታስረው ጥሬ ተርግፎሊቸው ሲበለ ዋሕዴ
ተተጋዯመበት እንዯ ሆነ አየና “ምነው ባይሆን እንኳ እንዯናንተ እግሬን ብቻ ባሰሩና እንዯናንተ
ትንፋሼን በሙለ በተነፈስሁ” እያሇ በበቅልቹ ሳይቀር ይቀና ጀመር። መተንፈስ ግን
የማይሆንሇት ሆኖ ሉፈነዲ ዯረሰ። ያን የንጋት ኮከብ የመሰሇ ዓይኑን እያንከባሇሇ ዘሪያውን ሰው
ቢፈቅዴ ማን ይገሊግሇው? ማን ያማሌዯው? ማን ጥቂት እንኳ ገመደን ያሊሊሇት? በከንቱ
ነው። መከራው ሥቃዩ ተገዴሊቸው ሲነበብ እንዯሚሰማው እንዯ ሰማእታት ሥቃይ ሆነ እንጂ
ተዙያም አያንስ፤ ያ ወዯሌ ወዯሌ ነጋዳ ሁለ በክርንም በጡጫም በርግጫም ሲተካክዜበት
እንዲይነጋ የሇምና ሇዋሕዴ ነጋሇት። ሲነጋ ተኝቶ የነበር ነጋዳ ሁለ እየተነሳ እየመጣ ያን
በከንቱ የታማ ላባ እንዯ ቀረመት ፍሪዲ በዘሪያው ከቦ ሲያይ ፀሏይ ብሌጭ አሇችና ላሉቱን
ሁለ በእሾና በጋሬጣ የቆሰሇውን ገሊውን በዯም የተበከሇ ጋቢው፤ ቁሌቁሇቱን ሲወጣ ሲወርዴ
የተገጣጠበውን ጉሌበቱን፤ ዯረቱን፣ ጀርባውን አዩና እርግጥ በላባነቱ አቆሙት። “ተላሊም
ሥፍራ እንዯዙሁ ሲሰርቅ ተገኝቶ ገርፈው ሇቀውታሌ” አለ። እነዙያው ሰዎች እኩለም “አስረን
ተኝው ጋር እናጉው” አለ። ዋሕዴ ግን ዓይኑን መክፈት እስኪሳነው ዴረስ ዯክሞ መተንፈስ
አቅቶታሌ። እንኳን ቁሞ ከእነእርሱ ጋር ይጓዜ እውነትም በቅቶታሌ፤ በዙያን ጊዛ ገሚሱ ነጋዳ
“ሇአገሩ ሹም እናስረክብረው ወይ አስረን ተበቅል ጋር እንንዲው” እያለ ሲከራከሩ፣ እኩላቶቹ
በእግራቸው እየጎሰሙ “ማን ትባሊሇህ፤ ከወዳት መጣህ” እያለ ቢጠይቁት እንኳን መመሇስ
17
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይሆንሇት፤ ያን ያህሌ ሲረግጡትም ስቅቅ አይሇውም ሆነ። እንዯበዴን ወዱህና ወዱያም
ሲያገሊብጡትና ሲያንከባሌለት እንዯሬሳ ሆነ። በዙህ ጊዛ አብዚኞቹ፣ “ተዉ እንፍታና
እንተወው፣ የሞተ እንዯሆነ ሰበቡ በእኛ ይሆናሌ” አለ። ወዱህም ረፈዯባቸውና ከብት ማዋዚት
ጀመሩ። ወዱያውም ጫጫኑና ሇሹም ማስተሊሇፉ ስሇረፈዯ አሊዯርሳቸው ብል ዋሕዴን ተፍተው
ተዙያው እንዯተጋዯመ ትተውት ተጓዘ። ከመዯብሩ ሊይ አጋሰስ ታረከሰው ሳርና ከእርሱ በቀር
ምንም አሌቀረም።
19
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሳዴሩኝ” ብል ሇመነ። ዋሕዴ የተናገረው ነገር አሌገባቸውም። ነገር ግን በመሊ አሳዴሩኝ
ማሇቱን ዏወቁና ዯስ ብሎቸው በግራና በቀኝ ሆነው ከሩቅ መቻ እንዯተመሇሰ መዲቸው እጁን
ይው እየዯጋገፉ ከቤቱ አስገቡት። ምግቡንም አሳመሩና ከስቶ እንዲያዴርና ዋጋ
እንዲያፋርስባቸው አበለት፣ አጠጡት። ዋሕዴ በዯግነት የእግዙአብሔርን እንግዲ ሇማክበርና
ሇማስተናገዴ ያዯረጉት መስልት ይመርቃቸው ጀመር። እነርሱ ግን ወዱያው በሌቶ እንዯጨረሰ
ያን በጨሇማ ሲሄዴ ያዯረ ዕሇት የተሊሊጠውንና ከነጋዳ መዯብር የተዯበቀውን ሰውነቱን ቆስል
ሽሮ ባዩ ጊዛ ዘሪያውን ከበው እየዲሰሱ ያስተውለት ጀመር። ዴሮ እነርሱ “ዋጋ ያወርዴብናሌ
አያወርዴብንም” እያለ ሇነገው ገበያ ማሰናዲታቸው ኑሯሌ። ዋሕዴ ግን ይኸን ሁለ አሊወቀ
በቅን ሌቦናው የዲነውን ቁስለን ዴፍጥጥ ዴፍጥጥ እያዯረጉ፣ እየተመሇከቱ ሲነጋገሩ ሲያያቸው
ጊዛ ያኑሇት እየመሰሇው “አሁንስ ዴኛሇሁ፣ አያመኝም” ይሊቸዋሌ። እነርሱ ግን የሚሇውን
አይሰሙ፣ አያውቁ ዜም ብሇው የነገውን ገበያቸውን “ምን ያህሌ ብሇን እንሽጠው” እያለ
ያሰናዲለ። አስተኝተው እንዲይሾሌክና እንዲይጠፋባቸው ሲጠብቁ አሳዯሩና እጅግ ማሌዯው
ተነስተው ገንፎ አገንፍተው፤ ከሚጣፍጥ እንቅሌፋ ዋሕዴን ቀሰቀሱና ያበለት ጀመር። በሌቶ
እንዯጠገበ ወዱያው ሁሇንተናውን በቅሌጥም ያሻሹት ገቡ። ዋሕዴ ግን ምንም ቢሆን የጌታ ሌጅ
ነበርና ባይን እንኳ በሰንዯሌ ንጥር የጣፈጠ ቅቤ ነው እንጂ፤ ሰው እንዲሮጌ መጫኛና እንዯገረረ
ጀንዱ በቅሌጥምና በሞራ ሲጨማሇቅ አይቶ አያወቅም ነበር። ስሇዙህ “አይሆንም አታስነኩኝ”
እያሇ ተናገረ። እነእርሱም ምንም ቋንቋውን ባያውቁ ባኳኋኑና ባተያዩ መጠየፉንና
አሇመውዯደን አውቀውበታሌ። ነገር ግን አወዚዜተውና ሆደን በገንፎ ነርተው ሇገዢ ሳያሳዩት
ብዘ ገንብ እንዱያስነችፋቸው ያውቃለና እያዯናቆሩ፣ ምንም ቢሌ በዙያ በሚገማ ስብ
ሁሇንተናውን በካከለት። ዋሕዴ ግን እንዯማይተዉት ባወቀ ጊዛ ተረታና ዜም አሊቸው።
ዯግሞም ጣመኑ እንዱሇቀውና ያ የተገጣጠበው በውሌ እንዱዴን ብሇው ሇሱ ዯግ ውሇታ
መዋሊቸው መስልታሌ። ‹‹ወይ ግሩም! ወይ ግሩም!›› እንዳት የእግዙአብሔር እንግዲ
የተወዯዯበት አገር ነው” እያሇ አገር ይመርቃሌ። ወይ አሇመተዋወቅ!!
እነዙሁ ያሳዯሩት ሰዎች ወዯ ዯረቅ ረፋደ ሲሆን ዋሕዴን ባይን ጥቅሻ “ተነስ
ተከተሇን” አለትና ታጥቀው ወጡ። እሱም እንዯ መሌካም ሽርሽር “እሺ” ብል በመካከሊቸው
አዴርገውት ሲሄደ ሲሄደ ካንዴ ትሌቅ መንዯር ዯረሱ። ያ መንዯር በትሌቅ እርዴ እንዯ አንዴ
ምሽግ ተከሌሎሌ (ታጥሯሌ)። በዙያ እርዴ ውስጥ ትሌቅ የዯንጊያ ቅጥር ተክቦበታሌ። በዙያም
እዴሞ ሊይ የአጋምና የግራር እሾህ ሰው እንዲይሇው ተመስጎበታሌ። ከዙያ መካከሌ ትሌሌቅ
20
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሰቀሊ ቤትና ሁሇት ትሌሌቅ ቤተ ንጉሥ አዲራሽ ተገጥግጦበታሌ። የዙያ ቅጥር በር ሁሇት ብቻ
ነው። ከሁሇቱ በር አንደ ጠባብ ነው። አንዯኛው በፈረስ ተዚንቶ ሇመግባት የተመቸ ነው።
21
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ዋሕዴም ምንም በሰው እጅ ቢሆን “መድቼንና ያን ዯግ አዴራጊዬን ነጋዳ ሳሊይ
እንዯምን ክርስቶስ ታረመኔ ቤት ያስቀረኝ” እያሇ ያስብ ነበር። ሲኖር ሲኖር ግን ከዙያው ቤት
ብዘ ክርስቲያኖች ተሽጠው ባሪያ ሁነው ያሇበቱን ጌታ እያገሇገለ ሲኖሩ በቋንቋቸው
ዏወቃቸውና ይቀርባቸው ጀመር። አዩኝ አሊዩኝ እያሇ እየፈራ የተሸጡበትን ጊዛና አገራቸውን
ስማቸውንም ጠይቆ አወቀ።
ዋሕዴ ከቤቱ ከወጣ ዓመት ሆኖት ነበርና እናትና አባቱ፣ እኅቱም ወዳት እንዯሄዯ
ባሇማወቃቸው “ዯብዚው ጠፋ” ብሇው ገምተዋሌ። ስሇዙህ ሲሊቀሱ ባጁ ከረሙ። በኋሊ ግን
የዋሕዴ አባት “ሌጄ ጠፍቶ ሲቀር ዜም ብዬ ከሞቀ ቤቴ እቀመጣሇሁ፤ ሄጄ በየትም ብዬ
ሌፈሌገው እንጂ” አሇና ያ ዯግ ነጋዳ ከተሸጠበት ባርነት ባወጣው ጊዛ ሊገሩ መመሇሻ
የሰዯዯሇትን ፈረስ ጭኖ ስንቁንም ከዯኅራዩ ወዴል ተነሣ። ነገር ግን አንዴ የሚከተሇው ሰው
አሌነበረም። በጦርነቱ ከአሽከሮቹ እኩላቶቹ ተፊቱ እየተጣበሱ አሇቁ፣ እኩላቶቹም እንዯእርሱ
ተማርከው ተሸጠዋሌ። እርሱም አገሩን ቢመሇስ ሰዉ አሌቆ ንጉሡ ሙቶ ከብቱ ተነዴቶ መሬቱ
ጠፍ ሆኖ ቆይቶ በዴኅነት ሊይ ወዴቋሌ። ሴት ሌጁ ጦቢያ ብቻውን ሇመሄዴ እንዯተነሣ ባየች
ጊዛ በወጣበት ጠፍቶ እንዯ ወንዴሟ እንዯ ዋሕዴ እንዲይቀርባት ፈርታ ታሇቅስ ጀመር፤
ቀጥሊም “አባየዋ፣ አንተ በጌትነት የኖርህ እንዳት አሊንዴ ሰው ብቻህን ሇመሄዴ ይቻሌሃሌ?
ፈረስህንስ ማን ሣር አጭድ ያበሊሌሃሌ? ውኃ ማን በጊዛው ያጠጣሌሃሌ? አሁንም እባክህ
ሌከተሌህ ትተኸኝ አትሂዴ፣ ባይሆን እንኳ አፍህን አካፍትሃሇሁ፤ ፈረሱንም በሇኮው ይዤ
ተመስክ ሊይ አግጥሌሀሇሁ፤ ምንም ቢሆን ጥሇኸኝ አትሂዴ” እያሇች አሌቅሳ ነገረችው። እርሱ
ግን የእርሷን ጭንቀት፣ የእርሷን ጥበት ባየ ጊዛ እጅግ አነና እንዯእርስዋው እያሇቀሰ “ሌጄ
ሏሳብሽ የማይሳካ የማይወጠን ነው፤ አንቺ ሴት ሌጅ ገና ጮርቃ ነሽ፤ አንቺን ፀሏይና ብርዴ
22
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አግኝቶሽ፣ መንገዴ መትቶሽ፣ ውኃ ጥማትና ርኅብ ተጨምሮብሽ እንዳት ችሇሽ ከእኔ ጋር
አገር ሊገር መዝር ይሆንሌሻሌ? አይሆንም አትምጪ” አሇና ከሇከሊት። ጦቢያ ግን “አይሆንም
አሌቀርም” እያሇች እያሇቀሰች ሇመነችው። አባትዬው ግን ነገሩን አይቶ ጠንክሮ እንቢ በማሇት
“እንኳን ታግዢኝ ይሌቁንም ትዯክሚና ተመንገዴ ወንዴምሽን ዋሕዴን እንዲሌፈሌግ
ታዯክሚኛሇሽ” አሊት። ዯግሞም “ጦቢያ ገና አንቺ ሇጋ ቀምበጥ ሌጅ ነሽ ተከብክበሽ፣ በጌትነት
ጠጁ ተጉሮሮሽ፣ ብርላው ከጅሽ ሳይሇይ ያዯግሽ ነሽ። አሁን ጠጁ ቢቀር ውኃ አጥተሸ፣ ስጋጃና
ወሊንሳ በረገጥሽበት እግርሽ እሾህ አሜክሊ አቃቅማ የፀሏይ ረሞጫ ረግጠሽበት እንዳት
ትችይና ትመጫሇሽ? አሁንም ዏርፈሽ ተናትሽ ጋር ቅሪ” ብሎት ሉስማትና ሉነሳ በሆነ ጊዛ
ጦቢያ ይሌቁንም ክንደን ተጠማጥማ ይዚ እያሇቀሰች “አባዬ ሇእኔ አታስብ እንኳን ዴህነት
ጌትነት ይሇመዲሌ፤ ሁለንም ሌጅ ነኝና እሇምዲሇሁ፤ ዯግሞም ባሇጌ ጌታ ሲሆን አያውቅበትም
እንጂ፣ ሀብታም የጨዋ ሌጅ ቢያጣም ዴህነትና መከራም አይከፋበትም፤ ቶል ይሇምዯዋሌ።
እኔም ቶል ሇመሌመዴ አይሳነኝምና ውሰዯኝ ዯግሞም ሇእኔ ከዙህ ቀርቼ ባንተ በዯጉ አባቴና
በምወዯው ወንዴሜ አሳብ ተመጨነቅ ካንተ ጋር አገር ሊገር እየዝርሁ የሆንሁትን ብሆን
ይሻሇኛሌ” አሇችው። በዙህ ጊዛ አባትዮው “እኔስ እስኪ አንቺ እንዲሌሽው እሺ ብዬ ሌውሰዴሽ፤
ኧረ ሊንቺ ምን ይመስሌሻሌ? እናትሽን ሇብቻዋ ከአንዴ ቤት ግተንባት ስንሄዴ? ይኸን ነገር
ብናዯርግ ሇሰውስ ምን ይመስሇዋሌ?” ብል በተናገረ ጊዛ እናቲቱ ቀጠሌ አዴርጋ “ሰዉም
ያሇውን ይበሌ፣ ሇእኔ አታስብ፤ ዯግሞም የምታስተዲዴረኝ አንዱት ባሌቴት መሳይ አሊጣም፤
ብቻ እኔ የምፈራው ሌጅቱ ካንተ ጋር መገሥገሥ ያሌተቻሊት እንዯሆነ ነው እንጂ፤ እርሷ
ተተቻሊት ነው ሇእኔ መታሰቡ፤ ሇእኔ የሚያሳስብ ነገር የሇም አታስብ።” አሇችና ወዯ ሌጅዋ
ዘራ “እውነት አሁን ሌጄ እርግጥ ጉሌበትሽን ትተማመኝዋሇሽን?” ስትሌ ጠየቀቻት። ጦቢያም
ቶል ብሊ “አዎን እናቴ አንቺ ተፈቀዴሽሌኝ፤ አንቺ ሇብቻሽ መሆን ታሌሠጋሽ መሄዴ
ይሆንሌኛሌ፤ አባቴን ብቻ እሺ እንዱሇኝ አግዢኝ” አሇቻት። ገና አባቷ “ይሁን አይሁን” ብል
ሳይመሌስሊት፤ ጦቢያ አሳቡን አቋረጠችና “አባቴ አንዴ ነገር ብቻ” አሇችና ሌትናገረው አፍራ
ሳትጨርሰው እንዯመዲዲት አሇች። በዙህ ጊዛ ማፈሯን አባቷ ዏወቀና “ምን ሆንሽ ሌጄ እስኪ
ንገሪኝ” አሇ። ጦቢያ አነሣችና “አባዬ ካንዴ ሁሇት ይሻሊሌ፤ የሰው ጠሊት አንበሳ እንኳ ሁሇት
ሰው ሲያይ ያከብራሌ፣ አይናካም። ነገር ግን ሁሇቱም ሰዎች ወንዴ ቢሆኑ ነው የሚፈሩ እንጂ
ጠሊት ሴትን ከቁም ነገር አይጥፋትም። ስሇዙህ አንተን ስከተሌ የሴት ሌብስ ቀርቶብኝ እንዯ
እንዯ ብሇብስ ይሻሌ ነበር” እያሇች የምትሇውን ሇመጨረስ አፈረችና አንገቷን ወዯ ምዴር
23
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አነበሇች። አባቷ አወቀባትና “እንዯ እንዯ የምትይው እንዯ ወንዴ ሌሌበስና ሌከተሌህ ማሇትሽ
ይሆን?” ሲሌ ጠየቃት። ጦቢያም አፍራ ይሌቁንም በሁሇት እጆቿ ፊቷን ጋርዲ ቃሎን አቅጥና
“ይሻሌ መስልኝ ነዋ አባቴ” አሇች። አባትዮውም እርሷ እርግጥ በመነሣቷ እንዯ ቆረጠች አየና
“እሺ ተወዯዴሽው ምን ይዯረጋሌ? ተሰናጂና ቶል እንነሳ” አሇ። ጦቢያ ዯስ አሊትና የሏር ነድ
የመሰሇ ሳደሊዋን እንዯ ወንዴ ተቆርጣ የወንዴ ሙለ ሌብስ ሇበሰችና እናቷን አይዝሽ ብሊ
አረጋግታ ሁለም ተሰነባብተው ተሇያዩ።
26
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ይሁንና ላሉቱን እንቅሌፍ እንዳት ብል ይውሰዲቸው ያረመኔው አመጣጥ እየታሰባት
“እንዳት እናዴርግ? ወዳቱንስ መሌሰን እንሽሽ?” እየተባባለ ምንም ቀኑን ሁለ ሲጓዘ ውሇው
ቢዯክሙ ይኽን ብቻ ሲያስቡ እንቅሌፍ ባይናቸው ሳይኩለ አዯሩና ጎሕ እንዯመቅዯዴ ሲሌ
ተነሡ። ፈረሳቸውን አስጫኑና እነዙያ ያዯሩባቸው ሰዎች እንጀራውን፣ ዲቦ ቆልውን ባገሌግሌ፤
ጠጁን በቀንዴ አዴርገው አሰናዴተው ሰጥተዋቸው ተውዱሊው ሊይ ወዯለና ባሇቤቶቹን
መራርቀው ሉጓዘ ተነሡ። ነገር ግን ወዳት መሌሰው ይሽሹ? ካውራው መንገዴ ሆነው “የቱን
መሌሰን እንሂዴ? ወዯኋሊችን ተመሌሰን ወዲንደ ቆሊ እንግባና እንሸሸግ” ሲለ ገና አንደን ነገር
ሳይቆርጡ በቀኝም በግራም በፊትም በኋሊም አገሩን ጢስ እንዯ ጉም ያሊብሰው ጀመር።
አረመኔው ያፋቀ ያፋቀውን ወንዴ ባፎቁ (በጎራዳ) እየጎመዯ ሴትና ሌጁን እየማረከ፤ ቤትና
ክምሩን እያቃጠሇ፤ ከብቱን ፈረስ በቅልውን እያጋፈፈ እየነዲ ዜርዜሩን እየቀጨ ሇወገኑ
እያበሊ፤ የቀረውንም በግሩ እየዲሸ፤ ቤተክርስቲያኑን እያቃጠሇ፤ ደሩን እየመዯመዯ፤ አታክሌቱን
እየቆረጠ እየነፈጠ፣ ሇጎጆው እያዯረገ መምጣቱ ኑሯሌ። ይኽን ምጣት ባየ ጊዛ የጦቢያ አባት
ሌጁን ጦቢያን እንቅ አዴርጎ ከዯረቱ አስጠጋ ያና “ሌጄ አካላ ወዲጄ! ሇእኔ ብሇሽ መጣሽና
ተመከራ ሊይ ወዯቅሽብኝ ካረመኔ እጅ ሌትገቢብኝ ሆነ፣ እንግዱህ ወዳት ሊዴርስሽ? እኔስ
ተማርኬ ብሸጥ እግዙአብሔር መሌሶ በታምሩ አወጣኝ። ዯግሞም የገዚኝ አረመኔ ገንብ አይቶ
ሇቀቀኝ። አንችን ያገኘ ሰውማ ያንቺን መሌክ አይቶ እንዲንች ያሇ ወሊ በዙህ ዓሇም ታይቶ
አይታወቅ እንዯምን ይሇቅሌኛሌ? በቁመቱ ሙለ ወርቅና ብር፤ አሌማዜና ለሌ ቢሰጡም
አይሇቅሽ” እያሇ ያሇቅስ ጀመር። ጭንቀቱ ዯግሞ በሁሇት በኩሌ ሆነበት። ጦቢያ የሴት ሌብሷን
ጥሊ እንዯ ወንዴ ሇብሳ ነውና የተከተሇችው አረመኔው ወንዴ ወንደን አይምርም እንዯዯረሰ
በፈንዛ እያረዯ ይጥሇዋሌ ተብሎሌና፤ ሌብሷን አይቶ ወንዴ ነው ብል እንዲይገዴሌበት ፈራ።
ምንም በዙያን ጊዛ የሴት ሌብስ ባያገኝሊት የሴት ሌብስ እንዲያሇብሳት አረመኔ፣ ሴት አይቶ
እንዲይሇቅ የታወቀ ነውና ይዝ አገሩን እንዲይወስዴበትና ከዙያ አረመኔ አገር ሇሇዓሇም
እንዲትቀርበት ፈራ። አንደ ችግር ከአንደ እየባሰ ስሇታየው ያሇቅስ ጀመር። ጦቢያ ግን ምንም
የነገሩን መክበዴ ብታውቅ እርሷም እንዯርሱ እንዲባቷ ውኃ እየሆነችና እያሇቀሰች ታረጋጋው
ጀመር። “አባዬዋ፣ እግዙአብሔር ከዙህ ቀዯም ተአምር ሰርቶ አንተን ተባርነት አውጥቶ ዯስ
አሰኘን፤ እግዙአብሔር የማይጨርሰውን ነገር አይጀምርም። አሁንም እርሱ እንዯጀመረ
በታምሩና በምህረቱ ያዴነናሌ፤ ተክፉ ነገር ይሰውረናሌ፤ አሁንም አትባባ። አይዝህ! ክርስቶስ
አሊንዴ ጊዛ ተአምር አይሰራም ይመስሌሃሌን? እርሱ አይዯክም፣ አይሰሇች፣ አይረሳ፣ አያረጅ፣
27
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አይከሳ፣ አይወፍር፣ መቼም አንዴ ነውና ወረት የሇበት፣ ተወዯዯ አይጠሊ። አሁንም አይዝህ!
አሳባችንን ሇእርሱ እንተውሇት” አሇችና አረጋጋችው። በዙህ ጊዛ ግን ገና እነርሱ የሚሸሹበትን
ስፍራ ሳይመርጡና አንዴ ነገር ሳይቆርጡ በመካከሌ ቤት አገሩን የሚያቃጥሇው አረመኔ
መቃረቡ በጢሱ ይታወቅ ጀመር። ያዯሩበት መንዯር ሰው ያን ጢስ እያየ ተሸበረና መሸሽ
ጀመረ። ጎበዜ ጎበዘ አሮጌ አሮጌውን፣ ባሌቴት ባሌቴቱን፣ ሩጦ ሇማምሇጥ የማይቻሇውን ሰው
በጀርባው እያሇ መሮጥ የሚቻሇውን ሌጅ ሌጁን በፊቱ እያስቀዯመ እየገፋፋ እያስፈራራ፤ ሴት
ሴቱ ጨቅሊ ጨቅሊውን ሌጅ በዯረቱ ሊይ እየጣፈ በጀርባውም እያሇ፣ በጎንም ቢሆን
እያሟቀሇ፣ በርታ በርታ ያሇው ሽማግላ መሮጥ ያቃተውን ዯቦሌ ሌጅ በጫንቃው አሽኮኮ እያሇ
መቀዲዯም መሮጥ በየገዯለ በየደሩ በየጉሩ በየጢሻው መግባትና መሰማራት ሆነ። ጦቢያና
አባቷም ይኸን ባዩ ጊዛ “እንዱያው ቁሞ ተመያዜ እስቲዯርስብን ዴረስ ምንም ባናመሌጥ እንሽሽ
እንዯሰዉ እንምሰሌ” አለና የፈረሳቸውን ቅናት አጠባበቁና ሇመኮሌኮለ ጦቢያ አሌሇመዯችምና
አባትዮው ተኮርቻው ጦቢያ ተጎረዳው ወዱያ ሆኑና አስነስተው ሲጋሌቡ ሲገርፉ ሲኮሇኩለ
ከትሌቅ ሜዲ ሊይ ዯረሱ። ከዙያ ወረደና ጥቂት የፈረሳቸውን ሌጓም ሇቀው አስተነፈሱትና
እነርሱም ዏርፈው እንዯገና ኋሊ ኋሊቸውን እየዝሩ እያዩ ይጋሌቡ ጀመር። ፈረሱም እያሊበው
እንዯገና ጉሌበት ተሰማው። የጌቶቹን ብሶት የጌቶቹን ማፋጠን የጠሊታቸውን መዴረስ ያወቀ
መሰሇ። ሇራሱ ቀርቶ ሇእነርሱ ያሰበ መስል ሇብ አዴርገው “ዯንገሊሳ እንጋሌብህ” ቢለት ሌጓም
እየገፋ ይግሌ ጀመር። ሲለ ሲለ እየዝሩ ቢመሇከቱት ነገሩ እንዲሌሰሊ አዩት። ሂዯው ሂዯው
የሚዯርሱበትን አጡት እንኳን ላሊ የሚሸጡበት አገር ወሬሳ የማይመታው ቆሊ ይቅርና አንዴ
እንኳ ቁጥቋጦ ግንባራቸውን የሚተግኑበት ቅጠሌ ከዙያ ሜዲ አሌነበረም። ከዙያ እፍ ካሇ ሜዲ
መካከሌ አንዴ ብቻውን እንዯ ዏምዴ የቆመ ኮረብታ ነበረ። ተሊዩ ግን ከሻፎ ከሻፎ ዯንጊያ በቀር
ምንም ዚፍና ቅጠሌ አሌነበረበትም። እንኳን ሰው ሉዯርስበት ሣርና ቅጠሌ ሉበቅሌበት
የተጠየፈው ይመስሌ ነበር፤ ብቻ ከጫፉ በነጭ ኩስ የተጨማሇቀ አንዴ ብክን ያሇ ጎጆ
የተውተፈተፈበት አሮጌ ቅራት ነበር። ይህን ሊሞራው የማይነቀሌ እርስት ገዲሙ ኖሯሌ።
ይኽን ኮረብታ ጦቢያ ባየች ጊዛ ሊባቷ “አባዬ! ይኽ ወሬሳ የሚመታው ጦር መቼም ሁለም
በከብት ነው እንጂ በግር አይገሠግሥም። ከብት ያሇው ሰው ሜዲ ሜዲውን ይጋሌባሌ፤ መንዯር
መንዯሩን ይርፋሌ እንጂ ሰውና ከብት እህሌ፣ ወርቅና ብር ከላሇበት ኮረብታ ያሞራ ኩስ
ሉርፍ አይወጣም። ስሇዙህ እኛም ከዙያ ወጥተን መዓቱን ብናሳሌፈው ይሻሊሌ።” አሇችና
ነገረችው፤ አባቷም “እውነትሽ ነው ሌጄ ያሳዴግሽ ይኽም አሇና! እውነትሽ ነው፤ እንግዱያውስ
28
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ወዯዙያው እንጋሌብ” አሇና ወዯዙያው ገረፉ። ተኮረብታው ሥር እንዯዯረሱ የፈረሱ ነገር
ቸገራቸው። ሇገንብነቱም አይዯሌ፤ እንዱያው ቤቴ ቤቴ ሲሌ እስቲያሌበው ተሸክሞ ከዙያ
አዴርሷቸው እንዯ ክፉ አዴራጊ ሇጅብ ጥሇውት ስሇመሄዲቸው ነው እንጂ። ታዱያ ይሁንና
ሇእርሱ ሲለ እነርሱ ተመከራና ተሞት ሉወዴቁ አይቻሌም። እያኑ ሌጋሙን ሇቀው
ወዯሜዲው ገረፉና “እንዯሻህ ሁን እንግዱህ የኛነትህ ቀረ፤ ባይሆን እንኳ ዯህና ጌታ ይዜሌህ”
እያለ አባትና ሌጁ አቀበቱን ተያያዘት። አቀበቱ ግን ሰው ረግጦት አያውቅምና ስርጥ መንገዴ
እንኳ አሌነበረበትም። እነርሱን በመሰሊቸው አቋራጭ ሲለ ሲለ ሙትት ብሇው ዯክመው
ተጫፉ ዯረሱ። ከዙያም አርፈው የሚንጠባጠብ ወዚቸውን በሌብሳቸው ጫፍ እየጠራረጉ
ዘሪያውን ያዩ ጀመር።
የነገስታቱ ሌማዴ ሰፈር ሲጀመር ከዴንኳናቸው ሳይገቡ በፊት ሠፈሩንም ሇማየት ቢሆን
በዘሪያውም ጠሊት መኖሩንና አሇመኖሩን ሇመሰሇሌም ቢሆን ወይም በማግስቱ የሚጓዘበትን
አገር የቅርቡን ባይን የሩቁን በመነጠር ሇማየት ከፍ ታሇ ሥፍራ መርጠው ይወጣለ። ስሇዙሁ
ነገር መሥፈር በተጀመረ ጊዛ ንጉሡ ከጥቂት ባሇሟልቹ ጋር ታጅቦ ተነጥል በፈረስ ጋሇበና
ጦቢያ ካባቷ ጋር ከተሸሸገችበት ኮረብታ ሥር ዯረሰ። ከዙያው ሲዯርስ ወረዯና መነጥሩን አሲዝ
አቀበቱን ተያያው። አሳቡ መቼም አገር ሇማየት ነው። ይኽን አይተው እነዙያ አባትና ሌጁ
ምን ያዴርጉ ከዙያ ሸሽተው ወዳት ይዴረሱ? እንዱያው ክው ብሇው ዯረቁ ፈዘ። የጦቢያ
እንባም በዴንጋጤ እንዯተቆጡት ሌጅ ቀጥ ብል ቆመ። ሁሇቱም እንግዱህ በሞታቸው ቆረጡ ።
31
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አባትዮውም ቀረበና ጦቢያን “ሌጄ እንግዱህ ተሇያየን፤ እንግዱህ የፈጠረሽ አምሊክ እንዯ
ምህረቱ ያዴርግሽ። ሇእኔ ስትይ ከዙህ መከራ ወዯቅሽ” አሇና ግንባሯንም፣ ጉንጯንም፣ ራሷንም
ሳሳመና ያሇቀሰውን እንባ ፈርቶ ሇጠሊት ሊሇመታየት አዯራረቀና የሚመጣባቸውን ነገር ይጠብቅ
ጀመር። ንጉሡም እስተባሇሟልቹ አቀበቱን ጨረሰና ከጫፉ ብቅ አሇ። ገና በሩቅ ከላልቹ ሰዎች
በፊት ንጉሡ ጦቢያን እስከ አባቷ አየና “ምናምን ከላሇበት ተራራ ከሻፎ ዯንጊያ መካከሌ ምን
ሰዎች ቆመዋሌ?” ብል እየዯነቀው “ብቻቸውን ከዙህ ምን ያዯርጋለ?” እያሇ ግፋን ወዯ እነርሱ
ሄዯ።
32
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከንጉሡ ጋር አንዴ ተራቢ ነበርና ይኽን ቃሌ በሰማ ጊዛ ሇንጉሡና ሇባሇሟልቹ “ካፊሮች
አምሊካችን ከሰማይ ነው ይሊለና ተኮረብታው መውጣታቸው ሇሰማዩ እንዱቀርቡና ቶል
አምሊካቸው ሌመናቸውን ሰምቶ ከእኛ እንዱያዴናቸው ብሇው ይሆናሌ፤” ብል ተናገረ።
ቀጥልም ፊቱን ወዯ ምርኮኞቹ አዘሮ “አሁን ታዱያ ምነው አምሊካችሁ መጥቶ ከእኛ እጅ
አያዴናችሁ?” እያሇ ይብትባቸውና ያሊግጥባቸው ጀመር። ይኸው ተራቢ ባሣቂነቱ ተወድ ቀርቦ
ነው እንጂ እንኳን ሇቤተ መንግሥት ሇተራበ ጅብም ያስጠይፍ ነበር።
አስቀዴሞ ባቱና አንገቱ የሽመሊይ አሞራ ይመስሌ ነበር። ጉንጭና ጉንጩም በመድሻ
የሆነኝ ብሇው ያጣጉት ይመስሌ ነበር። ሲሥቅማ ቢታይ ጭራሹንም መሌኩ ሁለ ይሇዋወጥና
የጭሊዲውን ዜንጀሮ መሌክ ያስመሰግናሌ። ውቃቢ የሇውም ሊህይ የሇውም ውርፍ ያሇ ውርፍ
ነበር። ነፍሱ መኖሯ በመንቀሳቀሱና በመነጋገሩ ነው እንጂ መታወቋ በቀረውስ ከሊሉበሊ ዋሻ
ከሚጠራቀመው ሬሳ አንደ ሥፍራ ታጥቶሇት ከውጭ የቀረ ይመስሌ ነበር።
የዙህን ጅማታም ተረብ በሰማ ጊዛ የጦቢያ አባት በክርስቲያን ሃይማኖት መሣሇቁ ነድት
“አንተ የምተሣሇቅበት የክርስቲያን አምሊክ መዓቱንና ምህረቱን ሇማውረዴ የተራራው ቅርበት
የሜዲው ርቀት ያየሩ ምጥቀት የውቅያኖሱ ጥሌቀት ያብራጃው ዯግነት የገሞራው ብርታት
የበረድው ቀዜቃዚነት የጨሇማው ጥቁረት የወጀቡ ግነት አያሰናክሇውም። ሁለ ሇእርሱ አንዴ
ነው። ይኽ ሁለ ባንዴ ቃሌ ይቆማሌ፤ ይሠራሌ ይፈርሣሌ እንዲሌነበር ይሆናሌ። ከእምኀበ
አሌቦም ይመጣሌ። በእርሱ ፊት ሁለም አንዴ ነው። ሇእርሱ ኃይሇኛው፣ ዯካማው፣ ዯፋሩ፣
ፈሪው፣ ዴኃው፣ ሀብታሙ፣ ገዢው፣ ተገዢው ሁለም አንዴ ነው። ሁለም በእርሱ ፊት
ኢምንት ነው። በእርሱ ፊት ትንሽና ትሌቅ የሇም። በዙህ ዓሇም ያመነውም ያሊመነውም ትክክሌ
ይኖራሌ። ይወሇዲሌ፣ ያዴጋሌ፣ ያረጃሌ፣ ይሞታሌ። በወዱያኛው ዓሇም ግን ሁለም
እንዯምግባሩ እንዯ ሀይማኖቱ ወይ ካሳውን ወይ ፍዲውን ይቀበሊሌ። አሁን እኔና ሌጄ
እስትንሞት ዴረስ አምሊካችንን ከሌብ እናምነዋሇን። ብንሞት፣ ብትገለንም አሁን ባበሳችን፣
በኃጢአታችን እንሞታሇን እንጂ ሇክርስቶስ ማዲን አቅቶት መስማት ተስኖት እንዲሌሆነ
እናውቃሇን” አሇና ተናገረ።
በዙህ መካከሌ ጊዛ ፀሏይ እንዯመቆሌቆሌ ማሇት ጀመረች። ንጉሡም “አገር ሳናይ መሸብን
መነጥር አምጡ” አሇና አራቱንም ማዕን ያይ ጀመር። ቀጥልም የሠራዊቱን አሠፋፈር አምሮ
ባየ ጊዛ ዯስ እያሇው ፍግግ ፍግግ ይሌ ጀመር። እውነትም አምሮ ነበር። የሰፈረበቱ ሜዲ ባይነ
ኅሉና ተሇክቶ የማያሌቅ ነበር። ከዙያ ታለበት ኮረብታ በቀር አባጣ ጎርባጣ መሬት እግር
የሚጠሌፍና የሚያዯናግር ሥር ሊይን የሚቆረቁር ጠጠር አሌነበረበትም፤ ብቻ ነፋስ እርም ብል
የተወው የረጋ ባሕር ይመሰሌ ነበር። የሰማዩና የምዴሩ ዲርቻ እንዯ ፍቅር ከንፈር ተሳስሞ
34
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዯመሶብና እንዯ ሙዲይ ከንፈር ሇከንፈር ተጋጥሞ ሇመሊቀቅ የቸገረውና እንዲይሊቀቅ መሏሊ
የገባበት ይመስሌ ነበር እንጂ ላሊም አይመስሌ ነበር። ብቻ የፀሏዩ ጠዲሌ ዲኛ ሆኖ ሰማዩን
ከዙህ አትሇፍ ምዴሩንም ከዙህ አትውጣ ብል በየገዚ ቀሇማቸው ወሰን ሰጥቶ ያካሇሊቸው
ይመስለ ነበር። ከዙሁ ሜዲ ሊይ የዙያ ሁለ ሠራዊት ዴንኳን ተረጥርጦበታሌ። ሰፈሩ ከታችም
የተጀመረበት ተሊይም የተጨረሰበት ተቀኝም የተዯፋበት ተግራም የተነበሇበት አይታወቅም
ነበር። ተሠፈሩ መካከሌ ቆሞ ሇሚያይ ሰው በተራዚሚ የእንግሉዜ መነጥር እንኳ ከፊትም
የፊታውራሪውን ከኋሊም የዯጀኑን ተቀኝም የቀኛዜማቹን ተግራም የግራዜማቹን ሠፈር ሇማየት
አይሆንሇትም ነበር። ጊዛው ዴንግዜግዜ እያሇ በሄዯ ጊዛ ይሌቁንም ያ ሁለ ዴንኳን ዯመና
ያሊሰናከሇውን የታኅሣሥን ኮከብ ይመስሌ ጀመር።
35
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ከዴንኳኑ በዯረሰ ጊዛ ሳይገባ አዚዡን በፊት አስጠርቶ “እነዙህ ካፊሮች ከዙህ እንዲይርቁ
አዴርገህ ዴንኳን ስጥና እንዲይርባቸውና እንዯይጠማቸው አዴርገህ አስቀምጥ” አሇና ገባ።
አዚዡም አሣምሮ አስመችቶ አሳዯራቸው። አባትና ሌጁ ሇጊዛው ነገሩ ቸገራቸው። ንጉሡ እርሱ
ነው እንዲይለ ወዱህም ገና ሌጅ ነው፤ ቢገፋ ቢገፋ የሀያ አመት እዴሜ ቢኖረው ነው።
ወዱህም ሌብሱ አሌባላ ነው። ውቃቢው ግን እጅግ ያማረ፣ ንግግሩ የጠዲና የጣፈጠ፣ አተያዩ
የተሰራና የተቀጣ፣ መሌኩም የወይን ሇሊ የመሰሇ ዲማ ነበር። ምንም ያረመኔ ር ምንም ገና
ጢም ያሊቀነቀነ ሌጅ ቢሆን ጥሊው የከበዯ ግርማው የተፈራ ነበር፤ ሌብሱ ብቻ ምንም ያማረና
የጠዲ ቢሆን የዙህ ሁለ ሠራዊት አሳዲሪ አያስመስሇውም ነበር።
መቼም ነገሥታቱ ትሌቅ ዓመት በዓሌ ካሌሆነና ትሌቅ እንግዲ ካሌመጣ በስተቀር
ሲያያዜ በመጣው ሌማዴ መሠረት ሇራሳቸው ማጌጥ ነውራቸው ነው። ብቻ የነገሥታት
ጌጣቸው ጀግና መሸሇም ቤታቸውን ፈረስ በቅሎቸውን ማስጌጥ፣ አገራቸውን ማሌማት፣ ፍርዴ
አሇማጓዯሌ፣ የበዯሊቸውን መማር፣ ሀብታምና ዴኃ አሇመሇየት፣ በገዚ ራሳቸው አሇመኩራት
ነው እንጂ፤ በወርቅ፣ በብር፣ ባሌማዜ፣ በዕንቁና በግምጃ እንዯሥእሌ ቢሇበጡ ክብርና ጌጥ
እንዲይሆናቸወ ያውቃለ። ከቤተ መንግሥት ዯግሞም ጌጣጌጥ ሊዜማሪ ወይ ሇዴንክ ወይ
ሇቅሬና ሇማንራሽ ነው የሚሰጥ። ይኽውም እንዯ ጀግንነት ምሌክት ተቆጥሮ ይቀቡበታሌ።
ነገር ግን ነገሥታቱና የጨዋው ሌጅ ሁለ ጌጥም ባይኖረው እንዱያው በውቃቢው ይሇያሌ።
ዯግሞም ወርቀቦና ዯማስ ተሇበሰ አህያና መጋዣ ላጣውን ያሇ ጮላ ያምርበታሌ። በረጃጅም
ጥርሱ ታጌጠ እከካም ዜኆን በሇስሊሳ አንፋሮውና በትንንሽ ጥፍሮቹ የኮራ አንበሳ ያምራሌ።
ስሇዙህ ምንም ጌጥ ባይኖረው በንግግሩ በኳኋኑ በግንባሩ ጦቢያም አባቷም ንጉሡ እርሱ
መሆኑን ተረደት። አርቀው ሲያስቡ ንጉሡ ራሱ ሲያነጋግራቸው ማምሸቱ እየዯነቃቸው
የክርስቶስን ነገር ሲያዯንቁ ላቱን ሁለ አዯሩ።
ከግምጃው አጥር አጠገብ ጥቂት ተመሸ በኋሊ የሚዚወር ነፍስ አይገኝም ነበር። ጭር
ብል ወፍ ሇቅሞ የሚነሣበት ይመስሊሌ። ሰው አጥብቆ እንዲይነጋገር በኛ ይከሇክሊሌ፣ ብቻ
የሰውን ቁጣ የማይፈራ፣ የንጉሡን ቃሌ የማይሰማ፣ የዴንኳኑ መርገፍ ከነፋስ ጋር ሲጋፋና
ሲጣሊ ያመሻሌ፤ ያነጋሌ።
በዙያ ዕሇት ማታ ግብር ሉገባ እፍን እፍን ሲሌ ጥቂት ቀዯም ብል ንጉሡ ጥቂት ሇመናፈስ
ከዴንኳኑ ወጣ፣ ጦቢያ ታባቷ ጉሌበት ግንባሯን ተክሊ እየተከች ከተመሩበት ዴንኳን ዯጃፍ
ተቀምጣ ነበር። ንጉሡ እንዲጋጣሚ ወዱያና ወዱህ እየዝረ ሲያይ አያት። ገና በቀን ግዲዩ
ሲጣሌ ስታሇቅስ አይቷት ነበርና እንዯዙያው ታሇቅስ መሰሇውና ሇማረጋጋት ቀረብ አሇ። አባትና
ሌጁ ንጉሡ መሆኑን ባዩ ጊዛ ዯነገጡና ተነሡ ንጉሡ ግን በጣም ቀረብ አሇና “ከንጉሡ
ባነጋግራችሁና መሌኩን ትወዲሊችሁ?” ብል ጠየቃቸው። መቼም የጨዋ ሌጅ ንግግር
አይጠፋውምና የጦቢያ አባት ቶል ብል “ጌታዬ ከእርስዎ ፊት በቀር የላሊ ንጉሥ ፊት ሌናይ
አንፈሌግም” አሇና መሇሰ። ንጉሡም እንዲወቁት ገባውና “እንግዱያውስ ከእኔ በስተቀር ላሊ ሰው
ካሌወዯዲችሁ እኔም አሌጥሊችሁም እመኑኝ” አሇና ወዯ ግብር ሄዯ። የእርሱ ንጉሥነት ሊባትና
ሌጁ ተተገሇጠሊቸው ግይቷሌ ሇንጉሡ ግን የጦቢያ ሴትነት ይገሇጥሇት ንዴ ገና ነበረ።
ሇ - የአዋጁ ቃሌ
39
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሆይ! በረፍሁ በገፈፍሁህ ፈንታ ካሣ እንዱሆንህና አገርህ እንዱያቀጥሌ የሁሇት ዓመት
የግብር ገንብና የዴግር አሥራት ምሬሃሇሁ።
ከዙህ አዋጅ ወዱያ አገር መዜረፍ ሰው መግዯሌ ቀረ። ጉዝውም ከዙህ እሇት ጀምሮ
ቀረ፤ ከዙያው ከተሠፈረበት ሊይ ዋና ትሌቅ ከተማ ተቆረቆረ። አንዴ ሊይ ተመቀመጥ የተነሣ
በግዴም በውዴም ንጉሡ ጧትና ማታ ጦቢያን እስታባቷ ያያቸው ነበርና ከቀን ብዚት ውቃቢው
ጦቢያን እጅግ ወዯዲት። እርሷም ጉዝው ቀርቶ የቀን ፀሀይ የላት አመዲይ ሲቀርሊት ጊዛ በእንባ
የታረሰው መሌታሕትዋ እያማረ፣ በርኅብና በጥም የተጎዲው ገሊዋ እየተመሇሰ ሄዯ:: ምንም
እርሷ እያፈረች ሴትነቷ እንዲይታወቅባት ራቅ ብትሌ፤ ንጉሡ ይሌቁንም ያፈቅራትና ያቀርባት
ጀመር። አባትየው ግን ንጉሡ እያዯር ሲያቀርባት ባየ ጊዛ የሌጁ የጦቢያው ሴትነት
እንዲይገሇጥባት ተጨነቀ። “አይዝሽ እንዲይገሇጥብሽ አረማመዴሽንም አነጋገርሽንም እንዯ ወንዴ
አዴርጊ” እያሇ ይመክራት ነበር። ነገር ግን ሌብስዋ ፈፅሞ እንዯ ወንዴ ነበርና የሴትነቷን ነገር
ማንም አሌጠረጠረም። ብቻ እንኳን ንጉሡ ላሊው ያያት ሰው ሁለ በመሌኳ ይወዲት ጀመር።
እውነትም ጦቢያ እጅግ የተዋበች እጅግ የተዯነቀች፣ ሊያት ሁለ የምታነሆሌሌና የምታነጋ
ነበረች። ዓይንዋ አስቀዴሞ የብር አልል መስል ካጥቢያ ኮከብ ጋር የተፎካከሩ ነበር። በዙያ ሊይ
ዯግሞ ሽፋሽፍቷ እንዯበሌግ ሣር ተጨብጦ የሚታጨዴ ይመስሌ ነበር። አፍንጫዋ ቀጥ ያሇ፣
ከንፈሯ መፈንዲት የጀመረ የማሇዲ ጽጌ ረዲ ይመስሌ ነበር። እንዯወንዴ የተቆጠረችው ጠጉርዋ
እንዯ ሰኔ ቡቃያ ወይም እንዲዱስ መሬት ጤፍ እየጋሸበ የሏር ነድ መሰሇ። በፀሏይና በውርጭ
40
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የተጎሳቆሇውና የጠቆረው ፊቷ እያሸሇተ ሀጫ በረድ ተመሰሇው ጥርሷ ጋር ገና ከሩቅ እየጠቀሰ
ከተሸሸገችበት ሴትነቷን ያሳጣባት ጀመረ። አጠረች ረመች፣ ወፈረች ቀጠነች፣ የማይለትን
ያካሊቷን ነገር መናገር በከንቱ ነው። እሞብርላ የመሰሇው አንገቷ እንዯዯከመው እያረፈ የወጣ
ነው። አሇአጥንት የተሰራው የእጇ ጣት እጀ ስራ ከበዚበት አመሌማል ጋር ይፎካከራሌ። እንዯ
ፈረስ ሇኮ ሳብ ረገብ ያሇው ዏጥንት የላሇበት ወገቧ ከንብ አውራ ጋር ይሇካካሌ። ባቷ፣ ተረከዞ
ይቆጡኛሌ ያሇ የተሠራ የተቀጣ ነው። ስትፈራ ስትቸር የምትገሌጠው ጥርስና ከናፍሯ ከዙያ
አተያይ ጋር ብርቱውን ያዜሊሌ፤ ሰነፉን ይገዴሊሌ። እንዱያው እግዙአብሔር ዯስ ያሇው እሇት
ተጨንቆና ተጠቦ ሠርቶ ነፍስ የራባት ትመስሊሇች እንጂ ጦቢያ እንዯ ሰው የተፈጠረች
አትመስሌም ነበር። በከንቱ ነው ጦቢያ ሥጋ ተመሌበሷ በስተቀር ዏመሎ ከነኪሩቤሌ የቅርብ
ዜምዴና የሚቆጣጠር ይመስሌ ነበር።
41
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጦቢያ ምንም አባቷ እሺ አንዲይሌ ብታውቅ ጊዛው ተመቻትና እየጠቀሰችና አንገቷን
እያነቃነቀች “አይሆንም በሌ” አሇችው።
43
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ያስፈራናሌ፤ ምንስ ቢሆን የአረመኔ ንጉሥ መሆኑ ቀረ እንዳ?” አሇና ነገራት። ጦቢያም
‹‹አባቴ ምን አዴርጌ ከወንዴ መካከሌ ተቀምጬ፣ እንዯ ወንዴ ተራምጄ፣ እንዯ ወንዴ ተናግሬ
ይሆንሌኛሌ? ዯግሞስ ጊዛው የበዚብኝ እንዯሆነ ዯግሞ ገመናችን ይገሇጥና የባሰ ነገር የመጣብን
እንዯሆን አሳዚኝ ነገር አይዯርስብንምን? የቆጡን አወርዴ ብሊ የብብቷን ጣሇች እንዯሚለ ሁለ
ዋሕዴ እንዱገኝ ስንጥር እስከኛውም የሰው መሳቂያ እንዲንሆን ብዬ እሰጋሇሁ። ግና ቢሆን ምን
አዯርጋሇሁ፤ ወንዴሜ ከተገኘሌን እሺ፤ ከዙሁ ገብቼ እንዯባሇሟልቹ እቀመጣሇሁ። ብቻ
እግዙእትነ ማሪያም ገመናዬን ትሸሽግሌኝ” አሇችና ሇአባቷ ነገረችው። አባትዬውም “እንግዱህ
ከጨከንሽ ወዱያ አዯራሽ እንዲይታወቅብሽ ንግግርሽም ቀጥ ያሇ አረማመዴሽም ሁሇንተናሽም
እንዯ ወንድቹ ይሁን” አሇና መከራት። ንጉሡ ከይሊሊ እንዯተመሇሰ “ምን መከራችሁ?” ብል
ጠየቀ። እነርሱም “እሺ ንጉሥ እንዲለን እንሆናሇን” አለ።
ይኽን ባዯረገ በበነጋው “ከአንዴ ዓመት ወዱህ ወንዴ ባሪያ የገዚህ አንዴ የጠፋኝ ሰው
አሇና ሰብስበህ ወዯ እኔ አምጣ። ይኽን ቃሌ በሰማህ ጊዛ እሇቱን ይህ ወዯ እኔ ተነሣ። ያን
የምፈሌገውን ሰው ይህ የመጣህ ሰው ይህ የመጣህበትን ዋጋ አሥር እጣፍ አዴርጌ ሰጥቼ
ወዱያው ሸሌሜ እሰዴሃሇሁ” አሇና በያገሩ፣ በያዯባባዩ፣ በየሸንጎው፣ በየጣቢያው ሁለ አዋጁን
ሇቀቀ። ከዙህ አዋጅ ወዱያ የሚገዚው አገር እጅግ ሰፊ ስሇሆነ አንዴ አምስት ስዴስት ወራት
ያህሌ አንዴም ባሪያ ይዝ የመጣ ሰው አሌነበረም። ይኽን ሁለ ቀን ጦቢያና አባቷ ዜም ብሇው
ከንጉሡ ጋር ተቀመጡ፤ ከቀን ብዚት የተነሣ ንጉሡ ጦቢያን አጥብቆ ወዯዲት እንዯብርቅ ያያት
ጀመር። ከጥንት ባሇሟልቹ አንዴም እንዯእርሷ አዴርጎ የሚያቀርበው የሇውም ነበር። ዯግሞም
ተመሌኳ ጠባይዋ፤ ከንግግሯ ውበቷ እየተባበረ ጦቢያ የሰው ሌብ ታናጋ ነበር። እንኳን
ንጉሡ የንጉሡ አጎት እስተ ሌጁ ከንጉሡ እሌፍኝ አይሇዩምና እያይዋት እጅግ ወዯዶት፤
እጅግም አቀረቧት። ይሌቁንም ያች የንጉሥ አጎት ሌጅ ሥራዋ አይኗን ከጦቢያ ሊይ መሰካት
44
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ብቻ ሆነ። ወሬዋ ሁለ የጦቢያ ነገር ብቻ ሆነ። በዙህ ጊዛ ጦቢያን ያየችው የንጉሡ የአጎት
ሌጅ በጦቢያ ሌቧ እንዯተሰቀሇና ፍቅር እንዲዯረባት ዏወቀው። ከዙህም ወዱያ ሇአጎት ሌጅ
“የገናው ባሌሽ እንዯዙህ እንዯ ጦቢያው ቢያምር ትወጃሇሽ?” እያሇ ፍቅሯን ሇማወቅ ባሽሙር
ይጠይቃት ጀመር። እርሷም አብረው ታዯጉ ንዴ እንዯ ወንዴሟ አዴርጋ ትወዯው ነበርና
ምሥጢር ታካፍሇው ነበር። ስሇዙህ ምሥጢር አዴረጋ አባቷ ካፊር ወዯዯች ብል እንዲይቆጣት
እርሱ እንዲይሰማ አዴርጋ በጦቢያ ፍቅር እንዲዯረባት ነገረችው። ከዙያ ወዱያማ እየጊዛው
እንዱህ ትሇው ገባች። “ከተወሇዴኩ እስከ ዚሬ ከአንተም ቤተ መንግሥት ቢሆን ከየትም ቢሆን
እንዯዙህ እንዯአዱሱ ባሇሟሌህ እንዯጦቢያ ያሇ ወሊ ከዙህ ቀረህ የማይለት አሊመሌ የተፈጠረ
ጎበዜ አይቼ አሊውቅም። እጅግ ሽንቅጥ ዓይናማ ነው። ምነው ካፊር ባሌሆነ!” እያሇች ትነግረው
ጀመር። ንጉሡም “እውነትሽ ነው እህቴ ባገራችን እንዯእርሱ ያሇ ሰው አይገኝም” ይሊታሌ።
ይህችው ያጎቱ ሌጅ ግን በመሸም በጠባም፣ በህሌሟም በውኗም፣ ከጦቢያ በቀር ላሊ የሚታያት
ነገር አጣች። በየጊዛው ከዙህ በቀር ሇንጉሡ ላሊ የማታጫውተው ሆነ። ይህን ሁለ ዯፍራ
የፍቅሯን ነገር ሇንጉሡ ማጫወቷ፣ ከጦቢያ ጋር እንዱያጋባት ተስፋ አዯርጋ ነው። ወይ
አሇማወቅ! ጦቢያ ግን ባትሇብስ ነው እንጂ እንዯእርሷው ሴት ነበረች።
45
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
የተነሳ ሇሰዉም ሇንጉሡም ይዯንቀው ነበር። የንጉሡ መዴ ግን አብሶ “ፍቅሬ በከንቱ
አሌቀረም” ስትሌ ዯስ ይሊትና ተስፋዋም እያዯረ ይገንባት ጀመር። ከንጉሡም ከእርሷም እያዯር
የጦቢያ ባሇሟሌነት በገነነ ጊዛ ባሇሟሌ የተባሇ ሁለ ቅናትና ምቀኝነት አዯረበት። “እንዳት
በኋሊችን ዯርሶ አንዴ ካፊር ይብሇጠን!” ብቻ ሆነ የባሇሟሌ ሁለ ንግግር። በዙሁ ብቻ ጧትም
ማታም ተጉተምታሚውና ተጉረምራሚው በዚ። ነገሩም አሌቀረ። ሇንጉሡ አጎት ነገሩን
አሳቅሇው ነግረው ጦቢያ በመከራ ሊይ እንዴትወዴቅ ወይም ከእሌፍኝ እንዲትገባ ሇማዴረግ
አሰቡ።
በዙሁ ምክር ያ ዴንክ አንደን ቀን ንጉሡ እንዯተኛ አይቶ ተፋጠነና “የንጉሡ መዴ
ቶል ና ትሌሃሇች” አሇና ሇጦቢያ ነገራት። ጦቢያም በቅንነት እሺ ብሊ ቶል ሄዯች ዯግሞም
ይህን ሁሊ ነገር አዘራ አሊየችም ነበር። ነገር ግን ገና ከተጠራችበት ዴንኳን ጥሌቅ እንዲሇች
ያው የንጉሡ አጎት ነገሩን ሰምቶ ዯረሰና ጦቢያ ተያች። ወዱያውም ባሇሟሌ የተባሇ ሁለ
ወሬውን በቶል ሇሁለ አዯረሰው። ዴሮ ያ ጦቢያ የሚባሌ አዱሱ ባሇሟሌ ሊቀንና የንጉሡን
መዴ ብቻዋን ካሇችበት ዯፈራት። ጭር ባሇበትም ጊዛ አይቶ አዯጋ ጣሇባት ተባሇ። ንጉሡም
ወዱያው ነገሩን ሰምቶ እውነት አሌመስሌህ አሇው። አጎቱ ግን እሳት ሇብሶ እሳት ጎርሶ ዯረሰና
“ይህ ካፊር ካሌተቀጣሌኝ እሞታሇሁ” አሇና፤ ሇንጉሡ ነገረ። ንጉሡም “ያን የመሰሇ እንዱያ
የረጋ ሌጅ ሲጠይቁት እንኳ ሇመመሇስ ያፍር የነበር፤ እንዳት ዯፍሮ እንዱህ ያሇ ነገር ሉሰራ
ይችሊሌ?” ሲሌ መሇሰ። አጎቱ ግን “እኔው በገዚ እጄ ዯርሼ ይዤዋሁና ካሌተቀጣሌኝ” አሇ።
ከዙህ በኋሊ ንጉሡ “ይህ ነገር ከሆነ እርግጡን ከእርሱ ከጦቢያ ጠይቄ አባቱንም እርሱንም
አንዴነት ተፊቴ አርቃሇሁ፤ መቅጣት ግን ገና ካገኘኋቸው ዕሇት ጀምሮ ምንም እንዲሊዯርጋቸው
ቃሌ ሰጥቻቸዋሇሁና አይሆንሌኝም” አሇ። ወዱያውም ጦቢያን ከተያበት አስመጣና “ከቶ ነገሩ
ምንዴር ነው? በምን ነገር ነው ከእህቴ ዴንኳን አሇወትሮህ የገባኸው?” አሇና ጠየቃት።
46
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጦቢያም ምንም በዙህ ነገር ሴት ናትና ሊሇፈውም ሇሚመጣውም ባትውሌበት በዙህ ምክንያት
የተሸሸገው ሴትነቷ እንዲይገሇጥባት ፈርታ ሁሇንተናዋ ይንቀጠቀጥ ጀመር። መሌኳም በፍርሀት
ተሇዋወጠ። ነገር ግን ከፊቷ ሊይ ከንጹሕነትና ከእውነተኝነት በቀር የሏሰተኝነትና የበዯሇኛነት
ምሌክት አይታይባትም ነበር። ይሁን እንጂ የምትመሌሰውን ነገር አጣች። “ተጠርቼ ነው
የሄዴሁ” እንዲትሌ ያጎቱን ሌጅ ማሳጣት መሰሊት። ጭራሹን ዜም ብሊ ሲያያት ጊዛ ንጉሡ
“ምነው ዜም ትሊሇህ? ነገሩን አትነግረኝም እንዳ? ጭምት ነህ፤ የተሠራህና የተቀጣህ ጭምት
ሌጅ ነህ ብዬ ሇብዘ ቁም ነገር ስመኝህ እንዱህ ታዯርግ?” ብል ሲናገር አባቷ ዯረሰና “ንጉሥ
ሆይ! የእኔ ሌጅ እንዱህ ያሇ የእረኝነት ሥራ አያዯርግምና የሰው ነገር አይስሙ፤ እኔን ይመኑ”
አሇና ተናገረ። አጎትዮው በዙህ ተናዯዯና “እኔ በገዚ እጄ ዯረስሁበት ስሌ እኔን ማሳበለ ነው
እኮ?” አሇ። ይህ ሁለ ሲሆን ጦቢያ አንገቷን ሰብራ ምዴር ምዴሩን ስታይ የነበረችው ቀና
አሇችና እንዱህ አሇች “ንጉሥ ሆይ! ጥንቱንም የቤተ መንግሥት ነገር ባሇማወቄ ስፈራ እኔን
ዴኃውን ያሌተገባሁትን እርስዎ መርጠው ከፊትዎ እንዲሌሇይና ከእሌፍኝዎ እንዲሻዬ እንዴገባ
ፈቀደሌኝ። አሁን ግን እውነት ከመሰሌዎ ማጥፋቴን ካወቁ ይቅጡኝ። ነገር ግን ታወቁኝ ጀምሬ
አስካሁን ግብሬ በጀም፣ አሌበጀም ያው ነው፤ ቢመስሌዎ ይተዉኝ ባይመስሌዎ ይቅጡኝ፤ ብቻ
በእኔ ኃጢአት አባቴን አይጥለብኝ፤ በሰጡነ ቃሌ ወንዴሜንም ፈሌገው ያስገኙሌኝና ሇአባቴ
ያስረክቡሌኝ። በእኔ ኃጢአት ወንዴሜ እንዯጠፋ አይቅር” አሇች። ንጉሡም “ይኸስ ይሁን ምነው
ነገሩን ከእህቴ ዴንኳን የገባህበትን አትነግረኝም?” አሇና አስጨንቆ ያዚት፤ እርሷ ግን ሰው
ሊሇማሳጣት ብሊ ጠቅጥቃ ዜም አሇች ንጉሡም ተቸገረ። ሆነም ሉሌ ቸገረው፤ ካንዯበቷ
የሚወጣው ነገር ሁለ የእውነት እንጂ አንዴ የሏሰት ቃሌ እንዯላሇበት ይታወቅ ነበር።
አሌሆነም እንዲይሌ ጦቢያ ሁለንም ጠንክራ ይዚ አሌናገር አሇች። በኋሊ ግን ነገሩ እንዯጠነከረ
አይቶ የጦቢያ አባት ሌቡ ተሸበረ። ተስፋውንም ቆረጠ። በዙህ ነገር የጠፋውም ሌጅ ሳይገኝ
እንዯሚቀር ጦቢያም ባሌዋሇችበት ነገር እንዯ ምትቀጣና እርሱም ራሱ ተሁሇቱም ሌጆቹ
አንደንም አጥቶ በሏንና በኃፍረት እንዯቤተ ክርስቲያን ውሻ ውቃቢውን ተገፍፎና ተባርሮ
እንዯ ሚሄዴ ዏወቀና ፈራ። ቀጥል ገና ይህ ሁለ ነገር ሳይዯርስበት በፊት ምሥጢሩን ሇንጉሡ
ሇማውጣት አሰበና “ሰዉ ሁለ ይከሌከሌሌኝ” አሇ። ሰዉ ሁለ እንዯወጣ አይቶ “ንጉሥ ሆይ!
ሰው ባሌዋሇበት ይሞት ንዴ ዚሬ ብቻም አሌተጀመረ፤ እርስዎም ምንም ብሌኅ ምንም መሏሪ
ንጉሥ ቢሆኑ እንዯ ሁለ ሥጋ ሇብሰዋሌና በሰው ሌብ ገብተው እውነቱንና ሏሰቱን ይሇዩ ንዴ
አይቻሇዎም። ሰው የነገረዎትን እንዯሚያምኑ የታወቀ ነው። አሁንም ነገሩን ሁለ ገሌጬ
47
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እነግርዎ ንዴ ምሥጢሩ ከእኛ እንዲይወጣ ቃሌዎን ይስጡኝ” አሇ። ንጉሡም እሺ ብል ቃሌ
ሰጠው። ከዙህ ወዱያ የጦቢያ አባት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ምሥጢሩን ሁለ ሇነገ
ሳይሌ የጦቢያንም ሴትነት ገሌጦ ነገረው።
ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዛ እጅግ አነ፤ እጅግም ነገሩ ዯነቀው። የጦቢያ ነገር
ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አሳነው። ወዱህም በወንዴ ተመስሊ መከራዋን እያየች
ወንዴሟን አገር ሊገር መፈሇጓ፤ ወዱህም እነዙያ ባሇሟልቹ በምቀኝነት ባሎሇችበት ነገር
አሻኩረው ሉያስቀጧት እንዯነበር ስታውቀው አሇማሳጣቷ ገረመው። ይኸው ንጉሥ ነገሩ ምንም
ቢያሳዜነው ባንዴ ወገን እጅግ በጦቢያ ሴትነት ዯስ አሇው። ፍቅሩ ጥንት በውቃቢ ብቻ
ሴትነቷን ሳያውቅ ነበር። አሁን ግን ያው ፍቅሩ ወዯ እውነተኛው ፍቅር ተሇወጠና ተስፋው
ላሊ ሆነ። ዴሮ በእርሷ ፍቅር ሌቡ ተሸወጠና ዯረቱን ይገምሰው ጀመር። ፍቅር እንዯ ቀጭን
ብርዴ በሁሇንተናው ገባበትና ያንከፈክፈው ጀመር። ነገር ግን አባትና ሌጁ እንዲያውቁበት
ተጠንቅቆ ይናገር ነበር። እነዙያን ቅናተኞች ባሇሟልቹን ሇመቅጣት ይወዴዴ ነበር። ነገር ግን
ምሥጢራቸው እንዲይወጣ ተነጋግረዋሌና የማይሆን ሆነ። ኋሊ ግን ንጉሡ አሰበ አሰበና ሇሰው
ይምሰሌ ሇቅጣት አስመስል ጦቢያ ዕሇቱን የባሇሟሌነቷን ሌብስ ሇውጣ እንዯ ጥንቷ ሇብሳ
ከእሌፍኝ ሌትወጣና ካባቷ ጋር በዴንኳን ርቃ ሌትሠፍር ወዯዯ። ሊባትና ሌጁ ይኽን አሳብ
ነገረና በምሥጢር አዴርጎ ብዘ ወርቅ ብዘ ከብት ሰጠና ዴንኳኑን ቤተሰቡን ጨምሮ “ሂደ
በሩቁ ስፍራ ተቀመጡ” አሇና ስፍራውን አሳይቶ ጦቢያ ከዴንኳን እንዲትወጣና ሰው
እንዲያያት፤ አባትዬው ግን ከአዯባባይ ተቀን አንዴ ጊዛ ብቻ እንዱወጣ አዴርጎ መካከረና
ሰዯዲቸው። የሚሰፍሩበት ስፍራ ግን ከንጉሡ ዴንኳን ፊት ሇፊት ነበር። ንጉሡ ባይሆን እንኳ
በመነጠር ጧትና ማታ ጦቢያን ማየት ተስፋ መሰሇው። ስሇዙህ ሇማየት ወዯ ሚመቸው ስፍራ
ሰዯዲቸው። የንጉሡ አጎትና እኒያ ባሇሟልቹ ጦቢያ የባሇሟሇነት ሌብሷን ትታ ከእሌፍኝ ወጥታ
ስትሄዴ ጊዛ የቅጣት መስሎቸው ዯስ አሊቸው። ያች የንጉሡ መዴ ግን የጦቢያን ከእሌፍኝ
መባረር በሰማች ጊዛ ዯንግጣ በሏን ጧትና ማታ ማሌቀስ እንጂ እህሌ ውኃ መቅመስ
ቸገራት። ንጉሡም እንዯ እህቱ ነበረና ተቸገረ ተጨነቀ። ይሌቁንም መጨነቁ የጦቢያ ፍቅር
እንዲዯረባት አይቶ ነው። በምሥጢር የጦቢያን ሴትነት እንዲይነግራት ምሥጢር እንዲይወጣ
ቃሌ አሇበት።
48
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ጦቢያ ከእሌፍኝ ከሄዯች አያሌ ቀን ሆነ፤ ባሇሟሌ የተባሇ በሠራው ሥራ ዯስ ብልት
ውስጥ ሇውስጥ እየሳቀ ሲቀመጥ ንጉሡ ባንዴ ወገን እንዲሊወቀ ሁለ ሊይ ሊዩን እየሳቀ
ትዜብቱን በሆደ እያሞራሞረ ተቀመጠ። ጦቢያ ግን ይህን ሁለ አሊቋረጠችውም በማንም ቂም
አሌያች፤ ብቻ “አዋጁ በየአገሩ ዯርሶ መቼ ወንዴሜ ዋሕዴ ይመጣሌኝ ይሆን?” እያሇች
ትመኛሇች። ተስፋዋ እርሱ ተገኝቶሊት በዯስታ ሁለም ባንዴነት ወዯ እናቷ መመሇስ ብቻ ነበር።
49
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ቀረበ። ጦቢያ እርግጥ ወንዴሟ መሆኑን ባወቀች ጊዛ ሇአባቷም መንገሩን ረሳች ብቻ ሁሇት
እጅዋን ወዯ ዋሕዴ ርግታ አእምሮዋ ጠፍቷት ወዯቀች። አባትዬው ግን ነገሩን አሊወቀ “ሌጄ
ምን ሆነችብኝ” ሲሌ እርሷን ሇማንሳት ወዯ ወዯቀችበት ተጎነበሰ። በዙህ ጊዛ ዋሕዴ አባቱ
መሆኑን ሇየውና የጫንቃውን ርኮት አምግዜጎ “አባዬዋ ከዙህ ምን አመጣህ?›” አሇና አቀፈው
አባትዬውም ገና ጦቢያን ከወዯቀችበት ሳያነሳ የጠፋው ሌጁ መሆኑን ባወቀ ጊዛ ል ወዯቀ።
ሦስቱም እየራሳቸው የናፍቆት ስስትና የዯስታ ዴንጋጤ ያዚቸውና ተፋዘ፤ ንግግርም
ተሳናቸው፤ ሁለም ዱዲ መሰለ፤ ይህ ሁለ ሲሆን ዋሕዴ ጦቢያን አሊስተዋሇም ነበር።
ጠጉርዋን ተቆርጣ እንዯ ወንዴ ሇብሳ ሇምዶን አጥሌቃ ባያት ጊዛ ላሊ ሰው መስሊው ነበር።
ኋሊ ግን ነፍሳቸው ጥቂት እንዯተመሇሰ እየተሊቀሱ መጠያየቅ ሲጀምሩ ነፍሳቸው ጥቂት
እንዯተመሇሰ እየተሊቀሱ መጠያየቅ ሲጀምሩ መቼም ንጉሡ ሁለንም በመነጥሩ ይመሇከት
ነበርና ያ የጠፋው ሰው መገኘቱን አወቀ። ወዱያውም ያው የተገኘው ሌጅና እርሱኑ ያመጣው
ሰው ወዯ እርሱ እንዱመጡ አ። ንጉሡ ዋሕዴን ባየ ጊዛ ዯስታ ፈነቀሇው። እውነትም
የጦቢያን ቁርበት ገፎ የሇበሰውን እንጂ ላሊም አይመስሌ ነበር። ጦቢያን ባሇሟሌ ሳሇች ያወቃት
ሁለ እንዯገና ንጉሡ ምሯት እርሷው ራሷ የመጣች መሰሇው እንጂ ላሊም አይመስሌ ነበር።
ጥቂት ዋሕዴና ጦቢያ የሚሇያዩበት በአተያይ በአነጋገርና በንቃት ብቻ ነበር። ጦቢያ ምንም
ሌሸሽግ ብትሇው ነገሯ ሁለ ወዯ ሴትነቷ ያዯሊባት ነበር። ንጉሡ ሇሰው ባያስታውቅ ነው እንጂ
ዯስ ብልት “እንግዱህ ሇአህቴ ባሌ አገኘሁሊት። መቼም እርሷ ላሊ መሆኑን አትሇየውም፤ ያው
የወዯዴሁት ጦቢያ ተመሇሰሌኝ ብሊ ነው ዯስ የሚሊት” እያሇ በሆደ ያሰናዲ ነበር።
ወዱያው ንጉሡ ዋሕዴን ሊመጣው ነጋዳ እስታነሳው ዴረስ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሸሌሞ
አሰናበተ ዋሕዴን ግን “አሳዴግሃሇሁ አስመችቼ አኖርሃሇሁ፣ ከእኔ ጋር ኑር” አሇው። ዋሕዴም
በበኩለ ተጨንቆ “ንጉሥ ሆይ፣ አንዴ ትሌቅ ውሇታ የዋሇሌኝ ነጋዳ ጠፍቶኝ እርሱን ካሊገኘሁ
አርፌ እንዲሌቀመጥ ምዬ ከቤቴ ወጣሁ። ይኸውና እርሱን ስፈሌግ ብዘ መከራ አገኘኝ፤
ቀጥልም ባሪያ ሆኜ ተሸጥሁ፤ አሁን እርስዎ ባያወጡኝ ከዙያው እንዯላልቹ መቅረቴ ነበር።
እንግዱህ ሇዙህ ካበቁኝ እርሱን ስፈሌግ እሞታሇሁ እንጂ ራሴን ወዴጄ ዯስ ካሇኝ ብዬ ከዙህ
መቀመጥ አይቻሇኝም፤ አይኑብኝ፣ እኔ ጌትነት ይቀርብኛሌ እንጂ ሇእርስዎ አሽከር
አይታጣም” አሇና ነገረው።
50
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ንጉሡ አስተውል ሰምቶ ቁም ነገረኛነቱን አዴንቆ ሲያቆም “በዙህስ ከሆነ አታስብ፤
እንዲገኘሁ እርሱንም በየትም አስፈሌጌ አስገኝሌሃሇሁ። አንተ ብቻ ከእኔ ጋር እንዴትቀመጥ፣
እሺ በሇኝ” አሇው። ዋሕዴም “ንጉሥ ሆይ ይኸንማ ታዯረጉሌኝ እንኳን በዯስታ እኖራሇሁ
ሲለኝ ባሪያ ቋሚ አዴርገው ቢገዘኝም ዯስ እያሇኝ እገዚሌዎታሇሁ ምን ከፍቶኝ” አሇና መሇሰ።
ንጉሡ ሇዋሕዴ እንዲዯረገው ሁለ ወዱያው እሇቱን “ነጋዳ የሆንህ ወረታህንም የረፋው ጊዛ
የተገፈፍህ ወረትህን እንዲስመሌስሌህ፤ ወረትህንም ያሌተቀማህ ሇእንግዱሁ በየሄዴክበት ሁለ
እንዲትነካ ዴብዲቤ እሰጥሃሇሁና ክተት፤ አዋጁን እንዯሰማህ ገስግሰህ ዴረስ” አሇና በያገሩ
አስነገረ።
52
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ንጉሡ የእዙህን ነጋዳ መገኘት እንዲወቀ ወዱያው አስጠራና እርሱ በገዚ አፉ “ይኽን
ያህሌ ከብት ይኽን ያህሌ ወርቅና ብር ጠፍቶብኛሌ” ብል በተናገረው መሰረት ሁሇት እጥፍ
አዴርጎ በሚገዚው አገር ነጋዴራስ አሰኝቶ ሹሞ ሇቀቀው። የሰው ውሇታ ክፉም ቢሆን በጎ
በወዱያኛው ዓሇም ብቻ ሳይሆን አንዲንዴ ጊዛም በዙህ ዓሇም ፍዲው ወይም ካሣው ባዴራጊው
ሊይ ይዯርሳሌ።
ጦቢያ ነገሩን በሰማች ጊዛ ዯነገጠች፤ ነገሩም ዯነቃት፤ ጦቢያ ከሌጅነቷ ጀምራ የኩራትና
የጌትነት ነገር አታስብም ነበርና ቶል እሺ አሊሇችም። ብቻ ታስብ ጀመረች። እንቢ እንዲትሌ ያ
ንጉሥ የዋሇሊትን ወንዴሟን ከባርነት ያዲነሊትን ወረታ ማጥፋት ሆነባት፤ ባንዴ በኩሌ የእርሷ
እንቢታ ሇአባቷና ሇወንዴሟ ጠንቅ እንዲይሆንባቸው ፈራች። እሺ ብሊ ያሌተጠመቀ፣ ክርስቶስን
ያሊወቀ ሰው ማግባት ሃይማኖት እንዯመሇወጥመና ከክርስቶስ እንዯመራቅ፣ በዙህ ኃሊፊ
መንግሥትም የወዱያኛውን የማያሌፈውን ክብር እንዯማቃሇሌ ያሇም ነገር ሆነባትና አይሆንም
በማሇቷ ቆረጠች። ከዙህ በኋሊ አስቀዴማ ወንዴሟንና አባቷን ከመከራ እንዱያዴንሊት ክርስቶስን
ተጨንቃና ተጠባ ሇመነች። ቀጥሊም ሇንጉሡ እንዱህ ብሊ ጻፈች።
“ንጉሥ ሆይ! የእኔን እጅ ስጠኝ ብሇው አባቴን ሇመኑ፣ ነገሩን በሰማሁት ጊዛ እጅግ ዯነቀኝ።
አሁንስ ጌታዬ እንዯ እርስዎ ያሇ ትሌቅ ንጉሥ፣ እንዯእርስዎ ያሇ ጌታ ዓሇምን በእጁ የጨበጠና
በእግሩ የረገጠ፤ አዲሙ የሰገዯሇት አጀማመሩ ያማረሇትና የገናው ያሌተገመገመበት ሕፃን
ንጉሥ እንዳት ተዋርድ እንዯ እኔ ያሇች ዴኃ ሌጅ ሇሚስትነት ይመኛሌ? ይህ ነገር ቢፈጸም
ሇእኔማ እጅግ ክብርና ከፍተኛ ማዕረግ ይሆንሌኝ ነበር። ነገር ግን ሇእርውስዎ መሆን
አሌገባምና ይተዉኝ። ሌቅርብዎ፤ እኔም የእዙህን አሊፊ ክብር፣ የእዙህን አሊፊ ዓሇም ዯስታ
ተመሌክቼ፤ ክርስቶስን ያሊወቀና ያሌተጠመቀ ንጉሥ ማግባት ክርስቶስን መክዲትና
የሇዓሇሙን ሕይወታዊ ክብሬን መናቅ ይሆንብኛሌ፤ ስሇዙህ እጄን ወዯ እግዙአብሔር
እረጋሇሁ እንጂ ሊሌተጠመቀና ክርስቶስን ሊሊወቀ እጄን አሌሰጥም፤ እንዱያውም በእውነቱ
መሏሊ አሇብኝና አይሆንሌኝም፤ አይኑብኝ። ትሌቅ ውሇታ ሰርተው እኛን ዯስ ስሊሰኙንና
ወንዴሜንም ከባርነት ስሊወጡሌኝ ወረታውን ቸሩ እግዙአብሔር ብቻ እንጂ ሰው ችል
አይከፍሌዎም። እርስዎ ባያውቁት ክርስቶስ ያውቅዎታሌና ወረታዎን ይክፈሌዎ” አሇችና
በመጨረሻው “ንጉሥ ሆይ! ካንዳ ሁሇቴ ወዯቤታችሁ በዯኅና እንዴትመሇሱ አዯርጋሇሁ ብሇው
54
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ቃሌ ሰጥተውን ነበር፤ አሁንም በሰጡን ቃሌ መሰረት ወዲገራችን ሇመሄዴ አንዴነት ያሰናብቱን
ንዴ በትህትነና እሇምናሇሁ” ስትሌ ጻፈች። ወረቀቱንም ሸሽጎ እንዱሰጥ አዯራ ብሊ ሇዋሕዴ
አሳሇፈችው።
ንጉሡ ግን ከዙህ ዕሇት ጀምሮ ብሌኅቱን ሳያስታውቅ ትሌቅ ዓመት በዓሌ አሇብኝ እያሇ
ያሳሊ፣ ጠጁን ያስጥሌ፣ ጠሊውን ያስጠምቅ፣ ፍሪዲውን ያሰበስብ፣ ሁሇንተናውን ያሰናዲ ጀመር።
ዯግሞ ላት ላቱን በስውር ትሌቅ የገዲም መምህር እየመጣ የሃይማኖትን ነገር፤ የጌታችን
መውረዴና መወሇዴ፤ መሞቱንም ያስተምረው ጀመር። የአጎቱንም ሌጅ በጦቢያ አስመስል
ከዋሕዴ ሇማጋባት “የወዯዴሽውን ጦቢያን እንዲጋባሽ ክርስቲያን ሁኚ እኔም የክርስቲያን ወገን
ሇማግባት ክርስቲያን መሆኔ ነው” ብል ነግሮአት አብራው ትማራሇች። ንጉሡም፣ ያቺም ያጎቱ
ሌጅ የክርስቶስ ሃይማኖት/ትምህርት/ ገባቸው። ከዙህ ወዱያ ንጉሡ ውስጥ ሇውስጥ
በየመሣሪያው ሁለ ሊይ መስቀሌ ያስቀርጥበት ጀመር። ሶበዴአት በነበረበት ሥፍራ፣ በሰንዯቅ
አሊማው ሁለ መስቀሌና ሰፍነግ፣ ጦር፣ አክሉሇ ሶክ ያስጠሌፍበት ጀመር። በየነጋሪቱም
55
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
በየመሇከቱም በየጋሻውም ሁለ ሊይ የጣዖት ስም ነበረበትና ያንን እያስጠፋ የክርስቶስን ስም
አስጻፈበት።
ንጉሡ በሩቁ ሁለንም ሲመሇከት ነበርና የሰውን መጠራቀም ባየ ጊዛ የአዋጅ ነጋሪውን አሇቃ
በወርቅ ሇምዴ፣ በወርቅ ጫማ፣ በወርቅ ዜናር፣ በሏር ቀሚስ፣ በአረንጓዳ ሱሪ አንቀሌቅል
ሸሌሞ፤ በወርቅ የተሟሸ ንግ አሲዝ የአዋጁን ቃሌ ጽፎ ሰጥቶ ሰዯዯውና በአጀቡ ከአዯባባዩ
ዯረሰ። በአዋጅ ነጋሪው ጀርባ አሇፈና ሲቆም ጊዛው መዴረሱን ሇማስታወቅ ነጋሪት መቺው
ምቱን ያፋጥን ጀመር። የአዯባባዩም ሰው ምን ይሆን ሲሌ ሇመስማት ይጋፋና ይንሸቀሸቅ
ጀመር። ቃሌ እንዲያመሌጠው አንደ በአንደ ሊይ እየወጣ እየተዚሇሇ ጆሮውን አቁሞ ሲጠብቅ
አዋጅ ጯሂው (አዋጅ ነጋሪው) ከትሌቅ ዯንጊያ ሊይ ወጣና ፊት እንዯሌማደ ሦስት ጊዛ
እየተንጠራራ ‹‹ስማ! ስማ! ስማ! መሰማሚያ ይንሣው የንጉሥን ጠሊት” ብል እንዯጨረሰ
ዋናው አዋጅ እስነጋሪ ወረቀቱን እያነበበ ይመራው ጀመር። ቃለም እንዱህ ይሌ ጀመር።
‹‹ሠራዊቴ ሆይ! አገሬ ሆይ! ዓሇምን ምዴርን ሰውን አራዊትን እንስሳትንና በዙህ ዓሇም
ያሇውን ፍጥረት ሁለ አንዴ አምሊክ ብቻ ነው የፈጠረው፤ ሁሇተኛ ፈጣሪ ከዙህ ቀዯም
አሌነበረም። ሇእንግዱህም አይመጣም። ይኽው አምሊክ ብቻ ከዓሇም በፊት እንዯነበረ ዓሇምንም
አሳሌፎ ይቀራሌ። በሦስትነቱ ስናምን አብ ወሌዴ መንፈስ ቅደስ እንሊሇን። በአንዴነቱም
በሦስትነቱም አንዴ አምሊክ መሆኑን እናምናሇን።
56
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
‹‹ይኸው አምሊክ አዲምንና ሔዋንን ፈጥሮ እንዱወሌደ እንዱዋሇደ ዓሇምን እንዱሞለ
አ። በዙህ ጊዛ እንኳን አዲምና ሔዋን አራዊቱ እንስሳቱ፣ አዕዋፉ አምሊካቸውን ዏውቀው
አመሰገኑ። ከብዘ መን በኋሊም ሰዉ ከመራባትና ዓሇሙን ከመሙሊቱ የተነሣ ቋንቋው በዜቶ
እየራሱ ሆነ። እንዯ ቋንቋውም ብዚት ሃይማኖቱም አምሌኮቱም ተሇወጠ። የእውነተኛውን
አምሊክ ረስቶ ሇየራሱ ጣዖት አበጀ። በዙህ ጊዛ እግዙአብሔር አብ አንዴ ሌጁን ‘ሂዴ’ ብል ወዯ
ምዴር ሊከው። ይኽው ሌጁ ከሰማየ ሰማያት ወርድ ከዴንግሌ ማርያም ተወሌድ እንዯእኛ ሰው
ሆኖ አስተማረ፤ ተሰቀሇ፣ ሞተ።
“እኔም ከአያት ከቅዴም አያቴ በቆየኝ ዴንቁርና ሇጣዖት ስሰግዴ ኖርሁ። አሁን ግን
ክርስቶስ ሌብ ሰጠኝ ከዴንቁርና አወጣኝ፣ የእውነተኛውን ፈጣሪ እንዲውቅ አዯረገኝ።
የእውነተኛው ሃይማኖት የክርስቶስ ወገን መሆን ነውና የእኔ ሃይማኖት ነው ዕወቀው። እኔን
የወዯዴህ እንዯእኔ ተጠመቅ። እኔን ያሌወዯዴህ ተሇይ። ክርስቲያን መሆን የወዯዴህ ወዯቀኝ፣
እንዯጥንትህ መኖር ያዯሊብህ ወዯ ግራ ሥፈር›› አሇና ጨረሰ።
ከዙህ አዋጅ ወዱያ ግራ ሠፋሪ ጠፋ፣ ሁለም ወዯመጠመቁ አዯሊ፤ ክርስቲያን መሆኑ
ተረገጠ፤ ሁለም አስቀዴሞ እንዲወቀው ሆነና ረጋ። ንጉሡ ዯስ አሇው። “ብቻዬን እቀር ይሆን!”
ሲሌ ይፈራ የነበረ ቃለ እንዯተዋጣሇት ሃይማኖቱ እንዯተከበረሇት ባየ ጊዛ ወዱያው፤
ክርስቲያን ይግዚ እንጂ አይገዚ” ብል ዯነገገ። ከዙህ ሕግ የተነሳ በየአገሩ እንዯ ባሪያ ተሸጦ
የነበረ ክርስቲያን ሁለ ከባርነት ወጣ።
ዋሕዴ ከዙህ በኋሊ ነጋዳ ዯብዴቦ ጥልት የሄዯ ጊዛ አስታመው ያዲኑትን ሰዎች ሌጅ
ከተሸጠበት አስመጥቶ ስሇ እናት አባቱ ወረታ የእርሱ እንዯራሴ አዴርጎ ሾመው
58
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
እንዱች ያሇች ጽጌ ከወዳት በቀሇች
እንዱያው መሊክ ኑራ ከሊይን ወረዯች።
አሊመሌ ተፈጥራ ሰውን አስጨነቀች።
እንኳን ወንደንና ሴቱን አነጋች
ይኽም ሁለ ሆኖ መኩራት አሊሰበች።
ሳደሊዋን ትታ ጠጉሯን ተሸሇተች።
ጠሌሰሟን አውሌቃ አጎዚ ዯረበች
ሥጋጃዋን ንቃ አቃቅማ ረገጠች
ከዘፋኗ ወርዲ ተኮረብታ ወጣች።
እንኳን ሇመዋረዴ ሇሞት ያሌተገባች
ዓሇም ሲሰግዴሊት በዴንክ ተከሠሠች።
በምቀኛ ተንኮሌ ተሌፍኝ ተሰዯዯች
ሇወንዴሟ ስትሌ በወንዴ ተመሰሇች
ዲሩ ግና ቢሆን ወንዴ ሁናም አሌቀረች
የሁሇት አገር መንግሥት አንዴነት ገጠመች።
እርሷ ጦር አትፈራም ከሰሌፍ ትገባሇች።
ይኸው ጀግና ቀዴማ ንጉሡን ማረከች።
እንኳን ሇወዯዲት ባሎን ታኮራሇች።
ጦቢያ ዘራ ዘራ ውዴ አትርፋ ገባች።
ዜናብ እንዲጣ እህሌ
በበሌግ የበቀሇ
ባንቺ አፈጣጠር
ፍጥረት ነሆሇሇ
=
ተዪው አታቋጥሪው
ይነሁሌሌ ፍጥረቱ
ባንቺው ተሰገዯ ፍጥረት ሠራዊቱ።
አንዴ ዏመሌ አገኘሁ
ከሠራ አካሊትሽ
እግዛር የሠራውን
ሌብ ማፈራረስሽ።
=
ሇጋ ያሌጠና፣ ጮርቃ
ሇፎ እግረኛ ወታዯር
ለሌ የከበረ ዴንጋይ
60
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ሊህይ የገጽታ ወዜ
ልላ ሠራተኛ፣ አገሌጋይ
መሌታሕት ጉንጭ
መርግ ናዲ
መቁነን ዴርሻ፣ ሌክ
መዲፍ ማኽሌ እጅ
ሸጥ ተረተር
ቀ
62
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ቀሊወጠ በፍርሃት ሁናቴ ዓይኑን ግራና ቀኝ አንከራተተ
ቀንበጥ የሇጋ ሇጋ
ቅናት ቀበቶ
ቋጫ ጮጮ የስፌት አሆላ
በነቻ መጣምር
በጢኀ በርጭቅ ደባ
/የ/ባሕር ዏረብ ነት ዓይነት፣ የበግና የፍየሌ ቆዲ፣ ከውጭ አገር ይመጣ የነበር
63
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ብርኩማ ባሇሶስት እግር ካንዴ ግንዴ የተጠረበ መቀመጫ፣ ትራስ
ብሶት ችግር
ተሇጠሇጠ ዧ ብል ተነጠፈ(ተረጋጋ)
ተሳነ አቃተ
ተትበሇበሇ ተርመሰመሰ
ተከባከበ በምቾት ያ
64
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ተዲፋት መቆሊቆያ
ተገተረ ሳይነቃነቅ ቆመ
ነቸፈ ቦጨቀ
65
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
አሞራሞረ አወጣ አወረዯ፣ አውጠነጠነ
አሞጭ የቅጠሊቅጠሌ ሥር
አሜከሊ እሾህ
አሸነጠ ታጠቀ
አቃቅማ ኩርንችት
66
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ዕዴሞ የግንብ ቅጥር
አንቧቀሰ አዚጋ
አኮረሰ አጎረበ
አንገራገረ አስፈራራ
አንጣር አቅጣጫ
አገ ረዲ
አጉዴኖ አሻርፎ
አጋፈፈ ረፈ፣ ቀማ
አፋቀ ጎበ
ኢምንት የላሇ
68
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ኮረምቱ አፍሊ ዜኆን/ጎረምሳ/
ኮዯኮዯ አሰረ
ወረት ሸቀጥ
ወርቀ ቦ ባሇወርቅ ካባ
፪ የራስ ሊይ ቆብ
ወሊ ቆንጆ፣ ሸጋ
ነፈጠ ገነጠሇ
ዲሸ ረጋገጠ
ገሌዲ ገንዲ
ገረገንብ የግዴንፍር ሥር
70
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ገጠጠ ፊት ነሣ
ግፋን ወዯፊት
ጽጌ- አበባ
71
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss
ፈ
ፋና መብራት
ፋና ወጊ መብራት ይዝ ቋሚ
72
Telegram: Amharic Books t.me/amharicbookss