You are on page 1of 25

ማር ውሀ አፓርታማ እና ንግድ ስራ

አክሲዮን ማህበር

መመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ


ደንብ

ነሐሴ 2012 ዓም
ባህርዳር
መመስረቻ ጽሑፍ

እኛ ከዚህ በታች ስማችን፣ ዜግነታችንና አድራሻችን የተገለፀው መስራቾች በኢትዮጲያ ሕግ፣ በተለይም
በ1952 ዓ.ም በወጣው የንግድ ህግ መሰረት የአክሲዮን ማህበር ለማቋቋም በመወሰን ይህን የመመስረቻ
ጽሁፍ እና ከዚህ ጋር የተያያዘውን የመተዳደሪያ ደንብ አውጥተን የማህበሩን ካፒታል በስማችን አንጻር
የተመለከተውን አክሲዮን ለመግዛት ተስማምተናል።

አንቀጽ አንድ

የባላክሲዮኖች ስም፣ ዜግነት፣ አድራሻ

ተ. ቁ ስም ዜግነት አድራሻ

ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ የቤት


ቁጥር

1 ዶ/ር እንየው አባተ በላይ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ጣና 16 አዲስ

2 ንጉስ ሀይሉ ተገኘ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ህዳር 11 11 አዲስ

3 ዶ/ር አዱኛ እውነቱ ማዘንጊያ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ጣና ሽምብጥ አዲስ

4 ዶ/ር ሙሉጎጃም መንግስቱ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ጣና ሽምብጥ አዲስ


ዘለቀ
5 ቢልልኝ መንግስቱ ዘለቀ ኢትዮጵያዊ ምስ/ጎጃም የጁቤ 02 አዲስ

6 ዶ/ር በእውቀቱ ዘላለም ዘለቀ ኢትዮጵያዊ ምስ/ጎጃም ደ/ማርቆስ 03 አዲስ

7 በሀይሉ ቢሰነብት ሞሴ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ሹምአቦ 10 አዲስ

8 በእውቀቱ ድረስ መሰሉ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ፋሲሎ 01 አዲስ

9 አሳቤነህ አለማየሁ ምኑየ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ህዳር11 04 አዲስ

10 ሀብታሙ ጤናው ጥላሁን ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ጣና ምድረገነት አዲስ

11 ደመቀ ብርሀኑ አማረ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ጣና ምድረገነት አዲስ

12 ትልቅ ታሪኩ አላምነህ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ፋሲሎ 03 አዲስ

13 ጌታቸው አበ መዋኸኝ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ሹም አቦ 10 አዲስ


14 እይላቸው አንተነህ ውባለም ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ጣና 16 አዲስ

15 እንዳለው ምኑየ ቢያድግልኝ ኢትዮጵያዊ ምስ/ጎጃም የጁቤ 02 አዲስ

16 ይግዛው ካሴ ትዝዙ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ፋሲሎ 03 አዲስ

17 ግዛቸው ተፈራ ቀለምወርቅ ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ዳግማዊ ምድረገነት አዲስ


ምኒልክ

18 ላመስግን ባንታምላክ አንተነህ ኢትዮጵያዊ ምስ/ጎጃም ኮርክ ኮርክ አዲስ

19 ይበልጣል ትሳሴ ደመቀ ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባ ጉለሌ 03 አዲስ

20 አበባው ቁምሌ ደነቀው ኢትዮጵያዊ ባ/ዳር ዳግማዊ 14 አዲስ


ምኒልክ

አንቀጽ ሁለት

የማህበሩ መጠሪያ

የማህበሩ መጠሪያ ስም ማር ውሃ አፓርታማና ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር ነው።

አንቀጽ ሶስት
የማህበሩ ዋና መ/ቤትና ቅርንጫፎች

የማህበሩ ዋና መስሪያቤት በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጣና ክፍለ ከተማ በቀበሌ 16 የቤት
ቁጥር አዲስ ነው፡፡ ማህበሩ ቅርንጫፍ ድርጅቶችን በኢትዮጲያ ውስጥና ከኢትዮጲያ ውጭ ሊያቋቁም
ይችላል።

አንቀጽ አራት

የማህበሩ አላማዎች

የማህበሩ የተቋቋመበት ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡


 ጥራት ያላቸው የመኖሪያና የንግድ አፓርታማዎችን መገንባት
 ህጋዊ የሆኑ የመኖሪያና ንግድ ቤቶችን መሸጥ እና መለወጠ
 በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራት
 ትምህርት ቤቶችን መገንባት እና በትምህርት ዘርፍ መሰማራት
 በማእድን ቁፋሮ እና ሽያጭ ኢንቨስትመንት ስራ መሰማራት
 ጤና ጣቢያዎችን፣ ክሊኒክ እናሆስፒታል ማቋቋም አገልግሎት መስጠት
 መድሃኒት ሽያጭ ላይ መሰማራት
 በአስመጭ እና ላኪ ዘርፍ መሰማራት(import and export)
 ትራንስፖርት ዘርፍ መሰማራት
 ሆቴል እና ቱሪዝም መሰማራት
 አግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራት
 የጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ መሰማራት

አንቀጽ አምስት

የማህበሩ ዋና ገንዘብ

1. የማህበሩ የተፈረመው ካፒታል ብር 800,000/ስምንት መቶ ሺህ ብር/


2.የተከፈለው የማህበሩ ዋና ገንዘብ ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ተከፍሏል፡፡
3. የማህበሩ የተፈረመ ካፒታል እያንዳንዳቸው ብር አስር ሺህ (10,000 ብር) ዋጋ ባላቸው በጠቅላላው 80 እጣዎች
ተደልድሏል።
4. የማህበርተኞች የአክሲዮን ድርሻ የመዋጮ መጠን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል።

የማህበሩ አባላት የአክሲ የአንድ ጠቅላላ መዋጮ


ዮን አክሲዮን
ድርሻ ዋጋ የተፈረመ የተከፈለ ያልተከፈለ

በጥሬ በዓይነት በጥሬ በዓይነት በጥሬ ገንዘብ በዓይነት


ገንዘብ ገንዘብ

1 ዶ/ር እንየው አባተ በላይ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

2 ንጉስ ሀይሉ ተገኘ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

3 ዶ/ር አዱኛ እውነቱ ማዘንጊያ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

4 ዶ/ር ሙሉጎጃም መንግስቱ ዘለቀ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

5 ቢልልኝ መንግስቱ ዘለቀ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

6 ዶ/ር በእውቀቱ ዘላለም ዘለቀ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

7 በሀይሉ ቢሰነብት ሞሴ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

8 በእውቀቱ ድረስ መሰሉ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም
9 አሳቤነህ አለማየሁ ምኑየ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

10 ሀብታሙ ጤናው ጥላሁን 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

11 ደመቀ ብርሀኑ አማረ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

12 ትልቅ ታሪኩ አላምነህ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

13 ጌታቸው አበ መዋኸኝ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

14 እይላቸው አንተነህ ውባለም 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

15 እንዳለው ምኑየ ቢያድግልኝ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

16 ይግዛው ካሴ ትዝዙ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

17 ግዛቸው ተፈራ ቀለምወርቅ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

18 ላመስግን ባንታምላክ አንተነህ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

19 ይበልጣል ትሳሴ ደመቀ 4 10,000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

20 አበባው ቁምሌ ደነቀው 4 10000 40000 የለም 10000 የለም 30000 የለም

ድም 80 200,000 800,00 200,000 600,0000


ር 0

አንቀጽ ስድስት

አክሲዮኖች

1. የማህበሩ አክሲዮን ከ 1 እስከ 80 ቁጥር ተሰጥቷቸዋል፡፡


2. የአክሲዮን የማስተላለፍ ተግባር ተሰጥቷቸዋል፡፡
አንቀጽ ሰባት
የባላክሲዮኖች ኃላፊነት
ባላአክሲዮኖች ሃላፊነታቸው በማህበሩ ውስጥ ባላቸው የአክሲዮን ድርሻ ልክ ነው፡፡

አንቀጽ ስምንት

የሂሳብ አመት

የሂሳብ አመቱ የሚጀምረው በየአመቱ ከ ሀምሌ 1 ጀምሮ ሲሆን የሚያልቀው ሰኔ 30 ነው።


አንቀጽ ዘጠኝ

የትርፍ አከፋፈል

1. በየሂሳብ ዓመቱ መጨረሻ የማህበሩን ንብረት እና እዳ የሚያሳይ የሂሳብ ሚዛን /ባላንስ ሺት/
ተዘጋጅቶ ለዳይሬከተሮች ይቀርባል፡፡

2. የማህበሩ አመታዊ የሂሳብ ሁኔታ የሚያሳዩ ሰነዶች፣ ማለትም የሂሳብ ሚዛን /ባላንስ ሽት/ የትርፍና
ኪሳራ መግለጫ የንብረት ቆጠራ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖረት እና የኦዲተሮች ሪፖርት በማህበሩ
መዝገብ ላይ ለተመዘገቡ ባለአክሲዮኖች ቢያንስ ከመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ቀን ቢያንስ 15
ቀን አስቀድሞ በሬኮማንዴ ይላካል፡
3. ከዚህ በታች ከንዑስ አንቀጽ 4/ሀ እና ለ/ሥር የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በዓመቱ ሂሳብ
መግለጫ ውስጥ እንደተመለከተው የማህበሩ የአመቱ የተጣራ ትርፍ፣ ጠቅላላ ወጪና ዋጋ፣ አላቂ
ለሚሆኑ ነገሮች መተኪያ ገንዘብ /አሞርታይዜሽን፣ አላዋንስ እና ለሌሎች መዋጮዎች ታክስና
ያለፈው ዓመት ግዴታዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚታየው የተጣራ ገቢ ነው፡፡
4. ከተጣራው አመታዊ ትርፍ ላይ

ሀ/ የጠቅላላ ካፒታሉን 20% እስከሚያክል ድረስ በየአመቱ 5% ለህጋዊ መጠባበቂያ ይያዛል፡

ለ/ በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ የጸደቁ ሌሎች ልዩ የመጠባበቂያ ሂሳቦችና የአሞርታይዜሽን ወጪዎች ከተቀነሱ
በኋላ ተራፊው በተከፈለው የአክሲዮን ድርሻ ልክ ለባለ አክሲዮኖች ይከፋፈላል፡፡

አንቀጽ አስር

የአስተዳደር አካሎች

የማህበሩ የአስተዳደር አካሎች

ሀ/ የባለአክሲዮኞች ጠቅላላ ጉባዔ

ለ/ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሐ/ የቁጥጥር ኮሚቴ እና

መ/ ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡

አንቀጽ አስራ አንድ

ጠቅላላ ስብሰባ

1. የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ከፍተኛው የስልጣን አካል ነው፡፡ይህም ጉባኤ መደበኛና ድንገተኛ
ስብሰባ በደንቡና በንግድ ሕጉ መሰረት ያካሂዳል።

2. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ከመካከሉ ይመርጣል፣ ይሾማል፣ ይሽራል፡


3. የውጭ ኦዲተሮችን ይሾማል፣ ይሽራል፣ አባላቸውንም ይሽራል፡፡

4. የቁጥጥር አባላትን ይሾማል፣ ይሽራል፡፡

5. አኪሲዮን እንዲሸጥ ይፈቅዳል፡፡

6. የዉጭ ኦዲተሮችን ይሾማል ይሽራል፡፡

7. ከንግድ ህጉ ተቃራኒ ካልሆነ በቀር ማንኛዉንም ጉዳይ ላይ ስለማህበሩ ዉሳኔ ማሳለፍ ይችላል፡፡

8. በመደበኛም ሆነ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሰበሰብ ጥሪ የሚደረገው ከስብሰባው ቢያንስ 15 ቀናት


በፊት ከአጀንዳዉ ጋር በኢሜል በሚላክ ደብዳቤ ሆኖ በስልክም እንደ ተጨማሪ ማሳሳሰቢያ ስብሰባ
መኖሩን እንዲያዉቁት ይደረጋል፡፡በሌሎች ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥሪ ይደረጋል፡፡በመደበኛ ጠቅላላ
ጉባኤ በሚጠራበት ጊዜ የማህበሩ አመታዊ ሂሳብ ሁኔታ የሚያሳዩ ሰነዶች ማለትም፡- የሂሳብ ሚዛን
/ባላንስ ሽት/፣ የትርፍና ኪሳራ መግለጫ፣ የንብረት ቆጠራ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖረት እና
የኦዲተሮች ሪፖርት በማህበሩ መዝገብ ላይ ለተመዘገቡ ባለአክሲዮኖች ቢያንስ ከ 15 ቀናት አስቀድሞ
በኢሜል ወይም በፖስታ ይላካል::

9. የዳየሬክተሮች ቦርድ በሌላ ጊዜ እንዲሆን ካልወሰነ በቀር የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በአመት አንድ ጊዜ
ይካሄዳል፡፡ ሆኖም አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ በሚደረግበት ጊዜ ጥር ወርን ማለፍ የለበትም፡፡
ድንገተኛ ስብሰባ ግን በማንኛውም ጊዜ ሊጠራ ይችላል፡፡

10. ጠቅላላ ጉባኤ የሚካሄደው ከጠቅላላ አባሉ ከ 50 በመቶ በላይ በስብሰባው መገኘቱን በማረጋገጥ
ይሆናል፡፡ ይህ ካልሆነ ለሁለተኛ ጊዜ ጥሪ እንዲተላለፍ ተደርጎ በሁለተኛው ስብሰባም በተመሳሳይ
መልኩ ከ 50 በመቶ መገኘቱን በማረጋገጥ ውይይቱን መጀመር ይቻላል፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ
ለሶስተኛ ጊዜ ጥሪ እንዲተላለፍ ተደርጎ በዚህ ስበሰባ በተገኘው የሰው ሀይል ጉባኤውን ማስኬድ
ይቻላል።

11. የጉባኤ ውሳኔዎችን ለማጽደቅ ቆጠራው በአክሲዮን ድምጽ የሚወሰን ሲሆን ማንኛውም ውሳኔ ተፈጻሚ
የሚሆነው ከ 60 በመቶ በላይ ድጋፍ ማግኘት ሲችል ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን የማህበሩ አባላት ድምጽ
እኩል በሚሆንበት ጊዜ የቦርዱ ፕሬዜዳንት ተጨማሪ የወሳኝነት ድምጽ ይኖረዋል፡፡

12. በውክልና ከጉባኤው የተገኘ ማንኛውም አካል ባለአክሲዮኑ ባለው የአክሲዮን ድርሻ መጠን ድምጽ
የመስጠት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. የተያዙትን አክሲዮኖች ወይም የወከሉትን ቁጥር የሚቆጣጠሩ ከባላአከክሲዮኖች ወይም እንደራሴዎች
መካከል ሁለት ድምጽ ተቀባዮች ይሾማል።
14. ማንኛውም ባለአክሲዮን ወይም እንደራሴ በምስጢር እንዲሆን ካልጠየቀ በቀር ማንኛውም ውሳኔ
ሚተላለፈው በድምጽ ቆጠራ ነው፡፡

15. ጉባዔው በሚከሄድበት ጊዜ የጠቅላላ ጉባዔው አጀንዳ ሊሻሻል ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን
እንዲመረጡ የተፈቀደላቸው ይበልጡን /የማጆሪቲ/ የአክሲዮን ድርሻ የያዙት ሲስማሙበት ብቻ ነው፡፡

16. ባለአክሲዮኖች ወደ ስብሰባ ሲመጡ እስከ አከሲዮን ድርሻቸዉ በማህበሩ መዝገብ መመዝገብ አለባቸዉ፡

17. ምልዓተ ጉባዔው /ኮረም/ እና የድምጽ ብልጫ በሚመለከት በ 1952 ዓ.ም.በኢትዮጵያ የንግድ ህግ
ቁጥር 421፣425 እና 428 የተደነገገው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት

የዳይሬክተሮች ቦርድ

1. ማህበሩ የሚተዳደረው በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ በሚመረጡ ቢያንስ 3 ቢበዛ 12 አባሎች ባሉት
የዳይሬክተሮች ቦርድ ነው፡፡ የቦርዱም የስራ ዘመን ሶስት አመት ነው።

2. የማህበሩ የመጀመሪያ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሚከተሉት ናችው፡፡

1. ንጉስ ሀይሉ _____________________________ ፕሬዝዳንት

2. ዶ/ር እንየው አባተ __________________________ም/ ፕሬዝዳንት

3. በሀይሉ ቢሰነብት ___________________________ ጸሃፊ

4 ትልቅ ታሪኩ _________________________________ አባል

5 ይግዛው ካሴ _______________________________አባል

የማህበሩ የባንክ ፈራሚዎች 1. ዶ/ር አዱኛ እውነቱ

2. አሳቤነህ አለማየሁ እና

3. ንጉስ ሀይሉ በጣምራ ፊርማ ያንቀሳቅሱታል።

3. የዳይሬክተሮች ቦርድ ከአባሎች አንዱን ፕሬዚዳንት አድርጎ ይመርጣል፡፡


4. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የተመረጠበት ጊዜ ካበቃ እንደገና ሊመረጥ ይችላል፡፡
5. ዳይሬክተር መለወጥ ቢያስፈልግ የንግድ ህግ ቁጥር 351/አስተዳዳሪ ስለ መለወጥ/ ድንጋጌ ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡ ዳይሬክተሩ ከስራው ላይ ቢቀር የንግድ ህግ ቁጥር 358/ድንጋጌ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም
ከስራው ላይ የቀረ ዳይሬክተር በሌላ ዳይሬክተር ያልተወከለን ዳይሬክተር ለመወከል ይቻላል፡፡
6. እያንዳንዱ የተመረጠ ዳይሬክተር የስራ ዘመኑም ሲያልቅ አክሲዮኑ በንግድ ህግ ቁጥር 349 ስር
በተገለፀው ሁኔታ ይመለስለታል፡፡ በንግድ ህግ ቁጥር 359 እና 360 ድንጋጌ መሰረት የዳይሬክተሮች
ምዝገባ ይኖራል፡፡
7. በህግ መመስረቻ ጹሁፍ እና በመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በጠቅላላ የባላአክሲዮኖች ጉባዔ ውሳኔ ለሌላ
ውሳኔ ለሌላ የማህበሩ አካል ተለይቶ ካልተሰጠ በቀር በተለየ ስራና ሁኔታ የሚያስፈልገው የማህበሩ
ስልጣን ሁሉ የዳይሬከተሮች ቦርድ ስልጣን ይሆናል፡፡ በንግድ ህግ ቁጥር 362፣364፣ 446 እና 447
ስር የተገለጹት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የዳይሬከተሮች ቦርድ ከዚህ የሚከተለው ስልጣንና
ተግባር ይኖረዋል፡፡

ሀ/ የማህበሩን አስተዳደር መቆጣጠር

ለ/ በጠቅላላው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ከተወሰነው ሳያልፍ የማህበሩን የንግድ ስራ ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ
እርምጃዎችን መውሰድ፣

ሐ/ የማህበሩን ስራ አስካያጆች ለመሾም እንደአፈላጊነቱ ጸሐፊዎችን፣ሠራተኞችን ለመቅጠር፣ ለማሰናበትና


ለማገድ እንዲሁም ደመወዝ፣ አበል ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችና የስራ ሁኔታዎችን ለመወሰን፣

መ/ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ማፍራትና መሽጥ፣

ሠ/ በአገር ውስጥ ከሚገኝ ማንኛውም ባንከ የገንዘብ ድርጅት ወይም ተቋም ለማህበሩ አላማዎች ማከናወኛ
የሚውል ብድር በመያዣ ወይም ያለመያዣ ለመበደር፣ ለመደራደር፣ ለመዋዋልና ለመፈረም፣

ረ/ በኢትዮጲያ ውስጥ ወይም ከኢትዮጲያ ውጪ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መቋቋምን መወሰን፣

ሰ/ ማናቸውንም ተስማሚ ሆኖ ያገኘውንና የማህበሩን ገንዘብ ስራ ላይ ሰለማዋል ሃሳብ ለጠቅላላ የባላ


አክሲዮኖች ስብሰባ ማቅረብ፣

8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ስልጣኑን ለየፕሬዚዳንቱ ለመስጠት ይችላል፡፡

9. ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት ስራ አስኪያጅ ዳይሬክተርና ማናቸውም ሌላ በዳይሬክተሮች ቦርድ


ስልጣን የተሰጠው ዳይሬክተር በማህበሩ ስም ሊፈርም ይችላል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአንድነት ወይም
በነጠላ በማህበሩ ስም ለመፈረም የሚችል ተጨማሪ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ስራ
አስኪያጆችንም ለመሾም ይችላል፡፡
10. አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሰባ በየፕሬዝዳንቱ ወይም በስራ አስኪያጁ ሊጠራ
ይችላል፡፡ የዳይሬክተሮች ስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ ኢትዮጲያ ውስጥ ለሌላ ዳይሬክተር አይሰጥም፡፡
ዳይሬክተሮች የማህበሩን ስራ ያካሂዳሉ፡፡ ውሳኔአቸውንም በንግድ ህግ አንቀጽ 358 ድንጋጌ መሰረት
ይመዘገባል፡፡
11. የዳይሬክተሮች ቦርድ ፀሃፊ ይሾማል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔዎች ለፕሬዝዳንቱና በፀሀፊው
ተፈርመው በቃለ ጉባዔ መዝገብ ውስጥ ተመዝገበው ይቀመጣሉ፡፡
12. ዳይሬክተሮች በንግድ ህግ አንቀጽ 365 መሰረት በአንድነትና በነጠላ ለማህበሩና ለዕዳ ጠያቂዎች
ኃላፊነት አለባቸው፡፡
13. ቦርዱ በክፉ ልቦና በተንኮል፣ ወይም ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ካልሰራ በቀር የተጣለበትን ሃላፊነት
በመወጣት ወይም በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት ባገኘው ስልጣን ለስራው ስራ በህጋዊ መንገድ
ላከናወነው በግሉ ምንም ሃላፊነት አይኖርበትም፡፡
14. የማህበሩ ዳይሬክተሮች በማንኛውም ሁኔታ ከማህበሩ ገንዘብ ሊበደሩ ወይም ለግል ዕዳዎች በማህበሩ
ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡
15. የዳይሬክተሮች የአገልግሎት ክፍያ በየአመቱ በመደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ ይወሰናል፡፡ ይህም ክፍያ
ከጠቅላላ ወጨ ውስጥ ይጠቃለላል፡፡

አንቀጽ አስራ ሶስት

ሥራ አመራር

1. የማህበሩ የአስተዳደር ሥራ በዳይሬክተሮች ቦርድ ተመርጦ የአገልግሎት ክፍያው እና አገልግሎት


የሚሰጥበት ሁኔት የሚወስንለት የስራ አስኪያጅ ዳይሬክተር ወይም ዋናውን ስራ አስኪያጅ
ይሆናል።

2. የስራ አስኪያጅ ዳይሬክተር ወይም ዋና ስራ አስኪያጅ በመመስረቻ ጹሁፍ፣ በመተዳደሪያ ደንብ


እና የዳይሬክተሮች ቦርደ በሚሰጡ መመሪያዎች መሰረት የማህበሩን ስራዎች ይሰራል፡፡
ማናቸውንም ለማህበሩ ስራ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
3. ዶ/ር አዱኛ እውነቱ የአክሲዮን ማህበሩ የመጀመሪያ የስራ አስኪያጅ ዳይሬክተር ወይም ዋና ስራ
አስኪያጅ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
4. የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ስራ አስኪያጁንያካትታል።

ዶ/ር አዱኛ እውነቱ ________ስራ አስኪያጅ

አቶ አሳቤነህ አለማየሁ ____ገንዘብ ያዥ

አቶ በእውቀቱ ድረስ _______ ሂሳብ ሹም

ዶ/ር ሙሉጎጃም መንግስቱ ______ ቁጥጥር


አንቀጽ አስራ አራት

ተቆጣጣሪዎች/ኦዲተሮች/

1. ማህበሩ በዓመት 1 (አንድ ጊዜ) በሚያደርገው ስብሰባ የማህበሩን ኦዲተር ወይም ኦዲተሮች
ይሾማል፡፡የሚሾመው ኦዲተር ወይም ኦዲተሮች በሂሳብ ምርመራ ሥራ የተፈቀደለት ሰው ወይም
ድርጅት ይሆናል፡፡ የእነዚህም ኦዲተሮች ተግባር ስልጣንና ሃላፊነት በህግና በተለይም በንግድ
ህግ ቁጥር 386 እና 460 መሰረት ይሆናል፡፡

2. የኦዲተሮችም የአገልግሎት ዋጋ በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ይወሰናል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የማህበሩ ቆይታ

ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ሲሆን በንግድ ህግ ቀጥር 495 ሥር በተገለጹት ምክንያቶች የሚፈርስ
ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

የማህበሩ የስራ ሪፖርት

1. እያንዳንዱ የሂሳብ ማጠቃለያ በሚዘጋበት ጊዜ ዳይሬክተሮች በማህበሩ ያሉትን ልዩ ልዩ ንብረቶችና


ዕዳዎች የሚያመለክትና የንብረቱን ዝርዝር የሚይዝ መዝገብ ያደራጃል፡፡

2. ዳይሬክተሮች የአመቱን የሂሳብ ሚዛን ሪፖርት ያደራጃሉ፡፡


3. ለጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ከመደረጉ 30 ቀናት በፊት የንብረት ዝርዝር መዝገብ፣ የሂሳብ ሚዛን፣የትርፍና
ኪሣራ ሂሳብ፣ የዳይሬክተሮች ሪፖርት፣ ለኦዲተር ተዘጋጅተው መስጠት አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ
እነዚሁ ሰነዶች ለሚመለከተው ንግድ ሚኒስቴር መተላለፍ አለባቸው፡፡

አንቀፅ አስራ ሰባት


ጠቅላላ
በዚህ የመመስረቻ ፁሁፍ ውስጥ ባልተገለጹት የማህበሩ ጉዳዮች ላይ ሁሉ እንደአስፈላጊነቱ የንግድ ህጉ
ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ይሀ የመመስረቻ ጹሁፍ ዛሬ ------------------------በመስራች አባሎችና
ፈራሚዎች በባህርዳር ከተማ ተፈረመ፡፡
መስራች አባላት፡-

ተ.ቁ ሙሉ ስም ፊርማ

1 ዶ/ር እንየው አባተ በላይ

2 ንጉስ ሀይሉ ተገኘ

3 ዶ/ር አዱኛ እውነቱ ማዘንጊያ

4 ዶ/ር ሙሉጎጃም መንግስቱ ዘለቀ

5 ቢልልኝ መንግስቱ ዘለቀ

6 ዶ/ር በእውቀቱ ዘላለም ዘለቀ

7 በሀይሉ ቢሰነብት ሞሴ

8 በእውቀቱ ድረስ መሰሉ

9 አሳቤነህ አለማየሁ ምኑየ

10 ሀብታሙ ጤናው ጥላሁን

11 ደመቀ ብርሀኑ አማረ

12 ትልቅ ታሪኩ አላምነህ

13 ጌታቸው አበ መዋኸኝ

14 እይላቸው አንተነህ ውባለም

15 እንዳለው ምኑየ ቢያድግልኝ

16 ይግዛው ካሴ ትዝዙ

17 ግዛቸው ተፈራ ቀለምወርቅ

18 ላመስግን ባንታምላክ አንተነህ

19 ይበልጣል ትሳሴ ደመቀ

20 አበባው ቁምሌ ደነቀው


መተዳደሪያ ደንብ
ይህ የመተዳደሪያ ደንብ የመመስረቻ ሰነዱ አካል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን አግባብ ባላቸው የህግ ድንጋጌዎች
መሰረት ይመራል ይተዳደራል፡፡

አንቀጽ አንድ

የባለ አክሲዮኖች /ማህበርተኞች/ መብትና ግዴታዎች/

የባለአክሲዮን መብት፡-

እያንዳንዱ ባለአክሲዮን ፡-

ሀ/ በልዩም ሆነ በመደበኛ ጉባኤዎች በመገኘት ሃሳብ የመስጠት፣የመቃወም፣ ድምፅ የመስጠት፣

ለ/ የማህበሩን ውሳኔ የመጠየቅና የማግኘት

ሐ/ የማህበሩን የተጣራ ትርፍና ማህበሩም ሲፈርም በሚደረገው የሂሳብ ማጣራት ድርሻን የመካፈል

መ/ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርደ እጩ ሆኖ የመቅረብ

ሠ/ ካፒታል በመጨመሩ ተጨማሪ አክሲዮኖች የሚታደሉ ቢሆን የቀደምትነት ድርሻን የማግኘት

ረ/ አግባብ ባለው ህግ፣ የመመስረቻ ጹሁፍና በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ በሚሰጡት መብቶች የመጠቀም
መብት ይኖረዋል፡፡

የባለአክሲዮን ግዴታ

እያንዳንዱ ባለአክሲዮን፡-

ሀ. አክሲዮን ማህበሩ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የመገኘት ግዴት አለበት

ለ. የዳይሬክተሮች ቦርድ በሚወስነው ተገቢ ውሳኔ ተገዥ የመሆን ግዴታ አለበት

ሐ እያንዳንዱ አባል በየወሩ ብር 1000(አንድ ሺህ) የማዋጣት ግዴታ አለበት። አስፈላጊ በሆነ ጊዜ

በጠቅላላ ጉባኤ ተወስኖ ተጨማሪ ክፍያ ወይም መዋጮ ሊኖር ይችላል።

ሐ. አክሲዮን ማህበሩ በሚያደርገው ወርሃዊ መዋጮ በወቅቱ ተገኝቶ ክፍያውን የመክፈል ግዴታ አለበት
ይህ ካልሆነ ግን ለአንድ ወር ክፍያ መዘግየት በየወሩ የሚከፍለውን 10% ቅጣት ይኖርበታል።ቅጣቱን
እናወርሃዊ ክፍያውን በአንድ ወር ውስጥ ካልከፈለ በወሩ ልክቅጣቱ እየተባዛ ይከፍላል።

መ. እያንዳንዱ ባለአክሲዮን ለተከታታይ ሶስት ወራት ወርሃዊ ክፍያውን ቢያቋርጥ/መክፈል ባይችል/


የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አመራር ያለአባሉ ውሳኔ ከአባልነቱ እንዲወጣ ይደረጋል።
ሠ. ማንኛውም የአክሲዮን ማህበር አባል በራሱ ፍላጎትም ይሁን በቦርዱ ውሳኔ ከአባልነቱ ቢወጣ አክሲዮኑን
ለሌላ አካል ሽጦና አስተላልፎ የመውጣት ግዴታ አለበት።

አንቀጽ ሁለት

የአክሲዮን ዋጋ /ፕሬሚየም/

አክሲዮኖች ከተጻፈባቸው ዋጋ በላይ ወጭ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ ሶስት

አክሲዮን ስለማስተላለፍ

አክሲዮኑን ለሌላ ማስተላለፍ የተከለከለ አይደለም። ቅድሚያ የሚሰጠው ለአሉት ባለ አክሲዮኖች ይሆናል፡፡

አንቀጽ አራት

ለጋራ ባለቤትነት፣ ለመያዣና የአላባ መብት

1. አክሲዮኖችን በጋራ ባለ አክሲዮኖች ወኪል ይሾማል፡፡ የሾሙትን ሰው ስምና አድራሻም በባለ አክሲዮኖች
መዝገብ ያስመዘግባሉ፡፡ ማህበሩ መጥሪያዎቹን የሚልከው ለዚሁ ለተሾመው ለባለ አክሲዮኖች ተወካይ
ይሆናል፡፡

2. በመያዣም ሆነ በአላባ አከሲዮን ያስያዘው ስው ስምና አድራሻ ያስያዘበትን ምክንያትና መብቱን ጨምሮ
ማስመዝገብ አለበት ማህበሩም ማስጠንቀቂያዎቹን /ኖቲስ/ የሚልከው ለባለ አክሲዮኑና ለመያዣ/አላባ/
ተጠቃሚው ነው፡፡

አንቀጽ አምስት

ስለስራ አስኪያጅ

1. የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የባላአክሲዮኖች ዝርዝር የያዘውን መዝገብ በማህበሩ ዋና መ/ቤት እንዲገኝ


ያደርጋል መዝገቡ በህግ በመመሥረቻ ፅሁፍና በመተዳደሪያ ደንቡ የሚጠይቁትን ጉዳዮች ሁሉ የያዘ መሆን
አለበት፡፡

2. በመዝገቡ ውስጥ ጉድለት/ስህተት/ መኖሩ እንደታወቀ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ይህን ጉድለት በሰላሳ
ቀናት ውስጥ እንዲስተካከል /እንዲታረም/ ያደርጋል፡፡

3. መዝገቡን ለመመርመርና ከውስጡም ቅጂዎችን ለመውሰድ መከፈል የሚኖርበትን ሂሳብ የዳይሬክተሮች


ቦርድ ይወሰናል፡፡ ሆኖም ባለአክሲዮን የሆነ ሰው ያለክፍያ መዝገቡን ሊመለከተው ይችላል፡፡
አንቀጽ ስድስት

ድርሻቸውን ያልከፈሉ ባለአክሲዮኖች ግዴታ

1. በየጊዜው መክፈል ያለበትን የአክሲዮን ዋጋ ያልከፈለ ባለአክሲዮን በወቅቱ ባልከፈለው ገንዘብ


ላይ 10 % ወለድ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡

2. የመክፈያ ጊዜው ካለፈ በኋላ ድርሻውን በወቅቱ ላልከፈለ ባለአክሲዮን ማህበሩ ክፍያው
እንዲደረግ ይጠይቃል፡፡ ባለአክሲዮኑ ደብዳቤ በደረሰው 30 ቀናት ቀን ውስጥ ክፍያውን
ባያጠናቅቅ ማህበሩ ያልተከፈለባቸውን አክሲዮኖች በሃራጅ ለመሽጥ ይችላል፡፡

አንቀጽ ሰባት

የጠፉ አክሲዮኖች ስለተመለከተ

ማህበሩ የሚያድላቸው አክሲኖች ጉዳት ቢደርስባቸው፣ ቢበላሹ፣ ቢጠፉ፣ ወይም ቢሰረቁ የዳይሬክተሮች
ቦርድ በሚሰጠው መመሪያ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ባልበለጠ ክፍያ እንደገና ይታደላል፡፡

አንቀጽ ስምንት

ጉባዔዎች

1. የዳይሬክተሮች ቦርድ በሌላ ጊዜና ቦታ እንዲሆን ካልወሰነ በቀር የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በየአመቱ አንድ
ጊዜ በዋናው መስሪያ ቤት ይካሄዳል፡፡ ሆኖም የአመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ በየበጀት አመቱ መጀመሪያ
ሀምሌ ወር ማለፍ የለበትም፡፡ ድንገተኛ ግን በማንኛውም ጊዜ ሊጠራ ይችላል፡፡

2. በመደበኛም ሆነ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሰበሰብ ጥሪ የሚደረገው ከስብሰባው አንድ ወር በፊት


በአገሪቱ ውስጥ በሚታተም ህጋዊ ጋዜጣ ጥሪ በማድረግ ነው፡፡

3. የመደበኛውም ሆነ ድንገተኛ ጠቅላላ ስብሰባ በምልዓተ ጉባዔ አለመሟላት ምክንያት ሊካሄድ ካልቻለ
ሁለተኛ ጥሪ ስብሰባው ከመካሄዱ 15 ቀናት በፊት ይተላለፋል በሁለተኛው ስብሰባ ጥሪ ምላዕተ ጉባዔ
ካልሞላ ስብሰባው ቀጥሎ ውሳኔዎች ማስተላለፍ ይቻላል፡፡

4. አግባብ ባለው ህግ፣ በመመስረቻ ጹሁፍና በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በሌላ ጉባኤዎች ይውሳሉ
ከሚባሉ ጉዳዮች በስተቀር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ጉዳዮች ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ
ይችላል፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ

ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሰበሰብ የሚደረግ ጥሪ

ስራ አመራሩ /ስራ አስኪያጅ/ የተመዘገቡ በላአክሲዮኖች ወይም ተወካዮቻቸው በጉባዔ እንዲገኙ ተመዝግቦ
ባለው አድራሻቸው በተራ የፖስታ መልዕክት አማካኝነት ጥሪ ያደርግላቸዋል፡፡በተጨማሪም ህጋዊ
ማስታወቂያ ለማውጣት በተፈቀደለት በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኙበት ቦታ በማከፋፈል ጋዜጣ
አማካኝነት ጥሪው ሊገለጽ ይችላል፡፡

ቀሪው መልዕከት አግባብ ባለው ህግ፣ የመመስረቻ ጹሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የሚጠየቀውን መረጃ
/ኢንፎርሜሽን/ሁሉ ያሟላ መሆን ይኖርበታል፡፡

አንቀጽ አስር

በጉባዔ ላይ ስለ መገኘት መቆጣጠሪያና ቃለ-ጉባዔዎች

1. በንግድ ህጉ አንቀጽ 403 መሰረት በእያንዳንዱ ጉባዔ ላይ የተገኙትን ማህበርተኞች መቆጣጠሪያ ሰነድ
መያዝ አለበት፡፡

2. በስብሰባ ላይ የተደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች በንግድ ህጉ አንቀፅ 411 እና 412 መሠረት በቃለ-
ጉባዔው ተመዝግበው እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ አስራ አነድ

የማህበሩን ሰነዶች የመመርመር መብት

ማንኛውም ማህበርተኛ በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ሰነዶች በማንኛውም
ጊዜ ለመመርመር ወይም ኮፒዎችን የመውሰድ መብት አለው፡፡ ሊሰጡት የሚችሉ ሰነዶች የሚከተሉት
ናቸው፡፡

1. የሂሳብ ሚዛን፣ የትርፍ ኪሳራ መግለጫዎች

2. ያለፉትን ሶስት የሂሳብ ዓመታት በሚመለከት ዳይሬክተሮችና ኦዲተሮች ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀረቧቸው
ሪፖርቶች

3. በእነዚሁ ጠቅላላ ጉባዔዎች የተያዘ ቃለ-ጉባዔዎችና የተገኙ አባላት ዝርዝር

አንቀጽ አስራ ሁለት

የእንደራሴነት ስልጣን

1. አንድ ባለአክሲዮን ማህበርተኛ ያልሆነ ሌላ ሰው በምትኩ በስብሰባዎች ላይ እንዲገኝ እንደራሴነት


ስልጣን ሊሰጥ ይችላል፡፡
2. ስልጣኑ በግልጽ በወካይ ካልተገለጠ በስተቀር በጉባዔው እንደራሴነት የተገኘው ሰው መብትና ግዴታ
በሚመለከት ከባለ አክሲዮኖች እንደ አንድ ይቆጠራል፡፡

3.በጉባዔ የመተካት ውክልና በጹሁፍ ሆኖ ቀን የተጻፈበትና በወካዩ ባለአክሲዮን የተፈረመ መሆን አለበት፡፡

ይህ አይነት የእንደራሴነት /ውክልና/ ከ አንድ አመት በላይ ሊያገለግል አይችልም፡፡

አንቀጽ አስራ ሶስት

አጀንዳ

1. የአጀንዳው ግልባጭ ከመጥሪያው ጋር ተያይዞ ለባለአክሲዮኖች ጋር ይላካል፡፡


2. ጉባዔው በሚከሄድበት ጊዜ የጠቅላላ ጉባዔው አጀንዳ ሊሻሻል ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን
እንዲመረጡ የተፈቀደላቸው ይበልጡን /የማጆሪቲ/ የአክሲዮን ድርሻ የያዙት ሲስማሙበት ብቻ ነው፡፡
3. የማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ከመደረጉ 15 ቀናት በፊት የተጻፈባቸው አክሲዮን ባለሃብቶች በማህበሩ መዝገብ
መመዝገብና ላምጪው የሚል የተጻፈባቸውን የያዙ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖቹን ማስገባት አለባቸው፡፡
አንቀጽ አስራ አራት

ፀሀፊ

የዳይሬክተሮች ቦርድ ፀሐፊውን ይሾማል፡፡ ፀሐፊው በጉባኤው ላይ የመገኘት ማስረጃ ወረቀት/አቴንዳንስ


ሺት/ያዘጋጃል፡፡ ህግ የሚጠይቃቸውን ቃለ ጉባዔዎች ይይዛል፣ ተገቢ ለሆነው የመንግስት ባለልጣን መስጠት
ያለባቸውን ደብዳቤዎች ያደርሳል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የሥራ አመራር

1. በጉባዔዎች ሁሉ ሰብሳቢ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፕሬዝዳነት ነው፡፡ እርሱም የሌለ እንደሆነ ከዳይሬክተሮቹ
በስራ ቀደምትነት ያለው /ሲኒየር/ ሰብሳቢ ይሆናል፡፡ ሁለቱም የሌሉ ቢሆን ካሉት ዳይሬክተሮች በስራ
ቀደምትነት ያለው ይሰበስባል፡፡

2. የተያዙት የአክሲዮኖች ወይም የተወከሉትን ቁጥር የሚቆጣጠሩ ከባላአከክሲዮኖች ወይም እንደራሴዎች


መካከል ሁለት ድምጽ ተቀባዮች ይሾማል፡፡

3. ማንኛውም ባለአክሲዮን ወይም እንደራሴ በምስጢር እንዲሆን ካልጠየቀ በቀር ማንኛውም ውሳኔ
የሚተላለፈው በድምጽ ቆጠራ ነው፡፡
ምልአተ ጉባዔው /ኮረም/ እና የድምጽ ብልጫን በሚመለከት በ 1952 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጲየ የንግድ
ህግ ቁጥር 421፣ 425 እና 428 የተደነገገው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

የዳይሬክተሮች ቦርድ ስልጣንና ግዴታዎች

1. የዳይሬክተሮች ቦርድ በህግ፣ በማህበሩ መመስረቻ ጹሁፍ፣ መተዳደሪያ ደንብና በጉባኤው ውሳኔዎች
የተሰጡትን ስልጣንና ግዴታዎች ይፈጽማል
2. የዳይሬክተሮች ቦርድ በተለይም የሚከተሉት ሥልጣንና ግዴታዎች ይኖሩታል፡
ሀ/ የማህበሩን ስራ ይመራል
ለ/ ጠቅላላ ጉባዔው በሚሰጠው መመሪያ መሰረት የማህበሩን አላማ ግቡን የሚመታበትና
የሚሰምርበትን እርምጃወዎች ሁሉ ያከናውናል፡፡
ሐ/ የስራ ኃላፊዎችን ይሾማል፣ ደመወዛቸውን ይተምናል፡፡ ስጦታን ስንብትንና ጡረታን
በሚመለከት ይወስናል፡፡
መ/ የማህበሩን የማይንቀሳቀሱም ሆነ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ይገዛል በዚህም እስከ ብር 1
ሚሊዮን ብር ድረስ በቦርዱ ውሳኔ መሰረት ግዥ የሚፈጽም ሆኖ ከብር 1 ሚሊዮንብር በላይ
ለሆነ ግዥ ግን የጠቅላላ አባሉ ውሳኔ መኖር አለበት
ሠ/ የብድርና የመያዣ ውሎችን ይዋዋላል፤ ለማህበሩ ተቀጣሪዎች የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት
የተለያዩ እቅዶችን ያዘጋጃል፡፡
ረ/ በኢትዮጲያ ወይም ከኢትዮጲያ ውጭ የማህበሩ ቅርንጫፎች እንዲከፈቱ ይወስናል፡፡
ሸ/ ተገቢ/ጠቃሚ የመሰለውን ሃሳብ፣ የማህበሩን ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግን ጨምሮ ለጠቅላላ
ጉባዔው ያቀርባል፡፡
4. ዳይሬክተሮች በማህበሩ ሥራ አስኪያጆችን ወይም ወኪልነት የጋራ ሃላፊነት አለባቸው፡፡
አንቀጽ አስራ ሰባት

ስለዳይሬክተሮች መምረጥና መሻር

1. በተደጋጋሚ መመረጥ ያላቸው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ የአስተዳዳሪዎች የስራ ዘመንሶስት አመት ነው፡፡
ሆኖም ተተኪዎች ተመርጠው እስከሚረከቧቸው ድረስ በስራ ይቆያሉ፡፡ የዳይሬክተሮች ምርጫ የሚከናወነው
በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ነው፡፡

2. አንድ ወይም ከዚያ በላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ቢጎድሉት/ቢወጡ/ ቀሪዎች ግማሽ በላይ ከሆኑ
በወጡት ምትክ ከባለአክሲዮኖቹ መካከል መርጠው ይሾማሉ፡፡ ቀሪዎቹ ዳይሬክተሮች ከግማሽ በታች ከሆኑ
የጎደሉትን ለመሙላት ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራል፡፡ የተሾመም ካሉ ለአመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ቀርበው ውሳኔ
ይሰጥባቸዋል፡፡ ሹመቱ የፀደቀ እንደሆነ የተተካው ሰው ያቋረጠውን የአገልግሎት ዘመን ይሸፍናል፡፡ ሹመቱ
የጸደቀ እንደ ሆነ የተተካው ሰው ያቋረጠው የአገልግሎት ዘመን ይሽፍናል፡፡ ሹመቱ ተቀባይነት ካላገኘ
ክፍት ቦታው በአመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ይተካል፡፡

አንቀጽ አስራ ስምንት

ስለዳይሬክተሮች የአክሲዮን መዝገብ

የዚህ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ አምስት ድንጋጌዎች እንዳግባቡ የዳይሬክተሮችና የአክሲዮኖቻቸውን


አመዘጋገብ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ


የዳይሬክተሮች የስራ ዋጋና አበል
1. አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በሚቀጥለው የሂሳብ ዓመት ለዳይሬክተሮች ቦርድ ሊከፈል የሚገባው አበል
ይወስናል፡፡ የመጀመሪያው የዳይሬክተሮቸ ቦርድ ተመራጮች ለመጀመሪያው የሂሳብ ዘመን ብር 500
በየወሩ አበል ያገኛሉ፡፡

2. በተጨማሪም አባላቱ የሚከተለውን ክፍያ ያገኛሉ፡፡

ሀ/ የተጣራው አመታው ትርፍ ከተከፈለው ዋና ገንዘብ እስከ ሰባ በመቶ/70%/ የሆነ እንደሆነ፣አንድ


በመቶ1 % ይሆናል፡፡

ለ/ የተጣራው ትርፍ ከተከፈለው ዋና ገንዘዘብ ከ ሰባ በመቶ/70% / በላይ ከሆነ 2 በመቶ/2%/ ይሆናል፡፡


ሆኖም ለባለአአክሲዮኖች የትርፍ ክፍያ ካልተደረገ በተራ ቁጥረ 2 ሀ እና ለ የተጠቀሰው ጥቅም
ለዳይሬክተሮች አይከፈላቸውም፡፡ ሆኖም የተጣራ ትርፍ ወደ ኩባንያው ካፒታል ወይም ወደ ተቀማጭ
ሂሳብ እንዲዘዋወር ከተወሰነ የዳይሬክተሮቹ ከተጣራ ትርፍ ጥቅም የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡

አንቀጽ ሃያ

የዳይሬክተሮች ቦርደ ጉባዔ

1. በሌላ ጊዜ ወይም ቦታ እንዲሆን ካልተወሰነ በስተቀር የዳይሬክተሮች ቦርድ ወር በገባ 10 ቀን በማህበሩ


ዋና መስሪያ ቤት ጉባኤ ያደርጋል፡፡ ሆኖም የቦርዱ እጅግ ቢዘገይ ጉባዔ በሁለት ወር ውስጥ ቢያንስ አንድ
ጊዜ መሆን አለበት፡፡

2. ከዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ በሚደረገው የመጀመሪያው የቦርድ ስብሰባ የዳይሬክተሮች ሰብሳቢ
/ፕሬዝዳንት/ ይመረጣሉ፡፡ ሰብሳቢው ለአንድ አመት ወይም የሚተካው ሰው ቦታውን ተረክቦ ስራውን
እስከሚጀምር ድረስ ያገለግላል፡፡ ቦርዱ የሾመውን ሰብሳቢ ሊሽረው ይችላል፡

3. የማህበሩ ፀሐፊ የጉባዔውን መዛግብት ይይዛል፡፡


አንቀጽ ሃያ አንድ
ስለ ስራ አመራር
1. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ስራ አስኪያጅ ይሾማል፡፡

2. ስራ አስኪያጁ የማህበሩን ዓላማና ተግባር በሚመለከት የሚመለከቱትን ሥራዎች ለማከናዎን ሙሉ


ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ሀ/ ከዳይሬክተሮች ቦርድ የተሰጠውን አጠቃላይ መመሪያ በመመርኮዝ ማህበሩን ለመምራት በተሰጠው


ስልጣንና ሃላፊነት መሰረት ማህበሩ ለተቋቋመበት አላማ ግብ መምታት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

ለ/ የማህበሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ያቅዳል፡፡ ያስተባብራል፣ ይመራል፤ ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፡፡

ሐ/ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በሚያዘው መሰረት ዓመታዊ በጀት፣ የስራ ፕሮግራምና የሂሳብ ሪፖርት
እንዲሁም ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ካዘጋጀና ከመረመረ በኋላ ለቦርዱ ያቀርባል፡፡

መ/ ሠራተኛ ይቀጥራል፣ ዕድገት ይሰጣል ያስተዳድራል፣ የደመወዝ ክፍያን የስራ ሁኔታዎችን ይወስናል፡፡
ለዋናው ስራ አስኪያጅ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑትን ሃላፊዎች መርጦ እንዲሾሙ ለቦርዱ ያቀርባል፡፡

ሠ/ በዳይሬክተሮች ቦርድ በተፈቀደው የስራ ፕሮግራም መሰረት የማህበሩ የሂሳብ አያያዝ ደንብና ስርዓት
በሚፈቅደው መሰረት ወጭዎችን ያጸድቃል፡፡

ረ/ የማህበሩን አመታዊ ሂሳብ የሚመረምሩ የውጭ ኦዲተሮችን ምርጫና ሹመት በሚመለከት ለቦርዱ
ሃሳብ/ምክር/ ያቀርባል፡፡

ሰ/ ግዥእና ሽያጭ በተመለከተ ከስሩ ለሚገኙት ሠራተኞች መመሪያ ይሰጣል፣ይቆጣጠራል፡፡

ሸ/ የማህበሩን አላማ ለማሳደግ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን ያቋቁማል፡ይመራል፣ ይቆጣጠራል፡፡

ቀ/ የስራ መጓተትን የሚያስቀርና ትርፋማነትን የሚጨምር የተቀላጠፈ የቁጥጥር መዋቅር አሰራር ያዘጋጃል፡፡

በ/ የሰራተኞች ህጎችና የማህበር መተዳደሪያ ደንብ በሚፈቅዱት መሰረት በሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ


እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡

ተ/ ከላይ ከተጠቀሱት ተግባሮች ጋር የተዛመዱ ሌሎች ስራዎችንም ያከናውናል፡፡

3. የዳይሬክተሮች ቦርድ የቅርብ ክትትል በማድረግ የተሰጠውን ስልጣን በከፊል ወይም በሙሉ፣
የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥንና ማስያዝንም ጨምሮ፣ ለዋናው ስራ አስኪያጅ ውከልና መስጠት ይችላል፡፡
4. ዋናው ስራ አስኪያጅ ወይም እርሱ የሚወክለው ተወካይ በማንኛውም የዳይሬክተሮች ቦርድ ጉባዔ ላይ
ይገኛል፡፡ በውይይቱም ተካፋይ ሊሆን ይችላል፡፡

አንቀጽ ሃያ ሁለት
ስለ ኦዲተሮች
1. ኦዲተሮችና ረዳት ኦዲተሮች በህግ፣ በማህበሩ መመስረቻ ጹሁፍና በመተዳደሪያ ደንቡ የተጠቀሱት
ስልጣንና ግደዴታዎች አሏቸው፡፡

2. ማንኛውም ኦዲተር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ስልጣኖችና ግዴታዎች ይኖሩታል፡

ሀ/ የማህበሩን መዛግብትና ሰነዶችን መመርመር፣

ለ/ የማህበሩን ንብረት፣ ሂሳብ ማመዛዘኛ ትርፍና ኪሳራውንም የሚያሳዩትን መዛግብት ትክክለኝነት ማረጋገጥ

ሐ/ የዳይሬክተሮች ቦርድ የሰጠው ሪፖርት የማህበሩን ትክክለኛ ገጽታ የሚያሳይ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡

መ/ ስራውን ለማከናወን አስፈላጊ ነው ብሎ የሚያምንበትን መዝገብ፣ ሰነድ፣ ቃለ-ጉባኤና ሌሎች


መረጃዎችን ባሉበት ማየትና መመርምር፡፡

ሠ/ በአመታዊና በማናቸውም ጉባዔ መገኘት

ረ/ ሌሎች ግዴታዎችንም መፈጸም፡፡

አንቀጽ ሃያ ሶስት

ስለተጨማሪ ኦዲተሮች

የካፒታሉ ከ ሀያ አምስት በመቶ /25 % ያላነሰ ይዞታ ያላቸው ባለአክሲዮኖች በራሳቸው ወጪ ተጨማሪ
ኦዲተሮች ሊሾሙ ይችላሉ፡፡ የተጨማሪ ኦዲተሮች ሊሾሙ ይችላሉ፡፡ የተጨማሪ ኦዲተሮች ስልጣንና ግዴታ
ቀደም ሲል ከተመረጡት ኦዲተሮች ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡ የተጨማሪ ኦዲተሮችን የስራ ዋጋና አበል
በሚመለከት ማህበሩ በከፊል ወይም በሙሉ ይከፍል እንደሆነ ጠቅላላ ጉባዔው ይወሰናል፡፡

አንቀጽ ሃያ አራት

ሕጋው የመጠባበቂያ ገንዘብ

1. ከተጣራ ትርፍ በየዓመቱ 5% ለህጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ ይነሳል፡፡ ይህም የሚሆነው ህጋው የሆነው
የመጠባበቂያ ገንዘብ የማህበሩን ዋና ገንዘብ 20% እስኪደርስ ነው፡፡
2. ከዳይሬክተሮች ቦርድ ወይም ከማንኛውም ኦዲተር ሃሳብ የቀረበለት እነደሆነ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው
ተጨማሪ ወይም አማራጭ የመጠባበቂያ ገንዘብ እንዲኖር መወሰን ይችላል።
አንቀጽ ሃያ አምስት
የሂሳብ አያያዝ ስርዓት
1.ማህበሩ በህጉ መሰረት ተቀባይነት ያለዉ የሂሳብ አያያዝ ስርዓት ይኖረዋል፡፡
2.ማህበሩ ሂሳቡን በአመት አንድ ጊዜ መዝጋት ይኖርበታል፡፡
አንቀጽ ሃያ ስድስት
ስለ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል
1. የማህበሩ እዳዎችና ወጪዎች ከተቀነሱና እንዲሁም የመጠባበቂያ ገንዘብ ከተነሳ በኋላ ከትርፍ ቀሪ
የሆነውን ገንዘብ ለባለአክሲዮኖች እንዲከፋፈል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡

2.ትርፉም የሚከፋፈለው ባለአክሲዮኖች በከፈሉት ገንዘብ መጠንና በወል በተጠቀሰው የቀደምትነት መብት
መሰረት ነው፡፡

3. የትርፍ ድርሻዎች የሚከፈልበት ቀንና የአከፋፈሉ ሁኔታ በአመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ናቸው፡፡

አንቀጽ ሃያ ሰባት
ስለማህበሩ መፍረስና ሂሳብ ማጣራት
1. ማህበሩ በህግ በተመለከተው እና በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ መሰረት ይፈርሳል፡፡

2. ማህበሩ እንዲፈርስ ጠቅላላ ጉባዔው በወሰነ ጊዜ ማህበሩ ሶስት ሂሳብ አጣሪዎች ይሾማል፡፡

3. ማህበሩ እንዲፈርስ ትዕዛዝ የተሰጠው በፍርድ ቤት ውሳኔ ሲሆን የዳይሬክተሮች ቦርደ ጠቅላላ ጉባዔውን
ጠርቶ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በተሰጠ --30 ቀን ውስጥ ሶስት ሂሳብ አጣሪዎች ይሾማል፡፡

4.ማንኛውም የማህበሩ አባልም ሆነ ኦዲተር የሂሳብ አጣሪዎችን ሹመት በመቃወም ያመለከተ እንደሆነ
የቀረበው መቃወሚያ በቂ ምክኒያት ያለው ሆኖ ካገኘው ጠቅላላ ጉባዔው ሹመቱን ሊሽረው ወይም
ሊያስቀረው ይችላል፡፡

ሹመቱ በተካሄደት ጊዜ በጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ የተሰጠበት ካልሆነ፣ለሂሳብ አጣሪዎች የሚከፈለው አበል
ማህበሩ በፈረሰበት ጊዜ ለዋናው ስራ አስኪያጅ በሚከፈለው አበል ልክ ነው፡፡
አንቀጽ ሃያ ስምንት

የኦዲተሮች ሥልጣንና ግዴታዎች

1. የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ለሒሳብ ዓመቱ የሚያገለግሉ ኦዲተሮች ይመርጣል።


2. ሂሳብ አጣሪዎች ከዳይሬክተሮች እጅ የማህበሩን ሀብቶችና ሰነዶች በሃላፊነት ይቀበላሉ። ዳይሬክተሮቹም
የመጨረሻው የሂሳብ ማጠቃለያ ጊዜና የሂሳቡ ማጣራት በተጀመረበት ጊዜ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ
ያደረጉትን የስራቸውን መግለጫ/ሪፖርት/ ያቀርቡላቸዋል።
3. የኦዲተሮች ስልጣንና፣ ግዴታዎችና መብቶች በንግድ ህጉ በተወሰነው መሰረት ይሆናል፡፡
4. ያለው ገንዘብ የማህበሩን ዕዳዎች ለመክፈል በቂ ሆኖ ያልተገኘ እንደሆነ ሂሳብ አጣሪዎቹ ባላአክሲዮኖቹ
በአክሲዮኖቻቸው ላይ ያልከፈሉትን ድርሻ እንዲከፍሉ ይጠይቋቸዋል፡፡
5. ሂሳብ አጣሪዎች በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ወይም በጠቅላላ ጉባዔ ስልጣናቸውን የሚቀንሱ ውሳኔዎች
ካልተደረጉ በቀር የሂሳብ ማጣራቱን ተግባር ለመልካም ለማካሄድ ሙሉ የሆነ ስልጣን አላቸው፡፡ በተለይም
የማህበሩን ሃብት በጅምላ ለመሸጥ የተለያዩ ጉዳዮችን በስምምነት ለመጨረስ፣ ለመግባባትና ለመዋዋል
ይችላሉ፡፡ በፍርድ ቤትም የማህበሩ ነገር ፈጅ ይሆናል፡፡
6.ተጀምሮ ለነበረው ውል አፈጻጸም ወይም የሂሳብ ማጣራቱ ጥቅም ያስገደደ ካልሆነ በቀር አዲስ ስራዎች
ለመጀመር አይችሉም፡፡ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ከተደነገጉት ውሳኔዎች ውጭ ለሚሰሯቸው ስራዎች
በአንድነትና በነጠላ ሀላፊዎች ናቸው፡፡
7. ጠቅላላ ጉባዔ የሚመርጣቸውን የሂሳብ አጣሪዎች ስልጣን ሊወስን ይችላል፡፡

አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ
የማጠቃለያ ድንጋጌ
በመመስረቻ ጹሁፉ ወይም በዚህ መተዳደሪያ ደንብ በግልጽ ያልተካተቱ ጉዳዮች በንግድ ህጉ መሰረት
ይወሰናል፡፡
መስራች አባላት፡-

ተ.ቁ መስራች አባላት ፊርማ

1 ዶ/ር እንየው አባተ በላይ

2 ንጉስ ሀይሉ ተገኘ

3 ዶ/ር አዱኛ እውነቱ ማዘንጊያ

4 ዶ/ር ሙሉጎጃም መንግስቱ ዘለቀ

5 ቢልልኝ መንግስቱ ዘለቀ

6 ዶ/ር በእውቀቱ ዘላለም ዘለቀ

7 በሀይሉ ቢሰነብት ሞሴ

8 በእውቀቱ ድረስ መሰሉ

9 አሳቤነህ አለማየሁ ምኑየ

10 ሀብታሙ ጤናው ጥላሁን

11 ደመቀ ብርሀኑ አማረ

12 ትልቅ ታሪኩ አላምነህ

13 ጌታቸው አበ መዋኸኝ

14 እይላቸው አንተነህ ውባለም

15 እንዳለው ምኑየ ቢያድግልኝ

16 ይግዛው ካሴ ትዝዙ

17 ግዛቸው ተፈራ ቀለምወርቅ

18 ላመስግን ባንታምላክ አንተነህ

19 ይበልጣል ትሳሴ ደመቀ

20 አበባው ቁምሌ ደነቀው

You might also like