You are on page 1of 6

መመሪያ ቁጥር 940/2015

የሲሚንቶ ግብይትን ሇመቆጣጠር የወጣ መመሪያ ቁጥር 940/2015

በሀገራችን የግንባታ ዘርፍ ማዯግን ተከትል የሲሚንቶ ገበያ በተሇያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች በአቅርቦትና ፍሊጎት
መካከሌ ያሇው ሌዩነት እየሰፋ በመምጣቱ ሥርጭቱ እየተስተጓጎሇ እና የዋጋ ንረቱ እየተባባሰ በመምጣቱ የሲሚንቶ
ገበያውን ሇማረጋጋት የንግዴና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትና ስርጭትን አስመሌክቶ ያወጣው የአሠራር
መመሪያ ቁጥር 908/2014 በተግባር ሲፈተሽ ሲሚንቶን በቀጥታ ከፋብሪካው የመግዛት እዴሌ ያገኙ አካሊትና
ተጠቃሚዎች በዋጋም ሆነ በአቅርቦት ተጠቃሚ መሆን የቻለ ቢሆንም በተመረጡ አቅራቢዎች ሇህብረተሰቡ እንዱዯርስ
የተዯረገው የሲሚንቶ ሥርጭት የተጠቃሚውን ፍሊጎት ያሊሟሊ ከመሆኑም በሊይ ሇተሇያዩ ህገወጥ አሠራሮች የተጋሇጠ
መሆኑን በመገንዘብ፤

በአሁኑ ወቅት ሥራ ሊይ ያሇው የሲሚንቶ የሥርጭት ሥርዓት አፈፃፀሙ በርካታ ክፍተቶች ያለበት በመሆኑ የተሻሇ መፍትሄ
እንዱበጅ ከህብረተሰቡና ከተሇያዩ አካሊት የቀረቡ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በግብዓትነት በመውሰዴ፤

በሚኒስቴር መሥሪያቤቱ በኩሌ በተካሄዯው የአፈፃፀም ፍተሻ ጥናት በተሇዩ ችግሮችና የመፍትሄ ሐሳቦች ሊይ በሲሚንቶ
ዘርፍ ከተሰማሩት ባሇሀብቶችና ከሚመሇከታቸው የክሌልችና የከተማ አስተዲዯር የሥራ ሃሊፊዎች ጋር በተዯረገው
ውይይትም ሥራ ሊይ ያሇውን አሠራር ማሻሻሌ አስፈሊጊ መሆኑን በመግባባት፤

የንግዴና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአስፈፃሚ አካሊትን ሥሌጣንና ተግባር ሇመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014
አንቀፅ 19 (4) መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷሌ፡፡

1
ክፍሌ አንዴ

ጠቅሊሊ

1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የሲሚንቶ ግብይትን ሇመቆጣጠር የወጣ መመሪያ ቁጥር 940/2015” ተብል ሉጠቀስ ይችሊሌ፡፡
2. ትርጓሜ
የቃለ አገባብ ላሊ ትርጉም የሚያሰጠው ካሌሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-
1) "ሚኒስቴር’’ ማሇት በኢትዮጵያ ፌዯራሊዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ የንግዴና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፤
2) "ክሌሌ" ማሇት በኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 47 መሰረት የተቋቋመ
ክሌሌ ሲሆን ሇዚህ መመሪያ አፈፃፀም ሲባሌ የአዱስ አበባ እና የዴሬዯዋ ከተማ አስተዲዯሮችንም ይጨምራሌ፤
3) ”የሲሚንቶ ጅምሊ ነጋዳ” ማሇት የሲሚንቶ ምርቶችን ከአምራች ወይም ከአስመጪ ገዝቶ ሇቸርቻሪ ወይም
መንግስታዊ እና መንግስታዊ ሊሌሆኑ ተቋማት ወይም ሇህብረት ሥራ ማህበራት በጅምሊ የመሸጥ ህጋዊ የንግዴ
ፈቃዴ ያሇው ማንኛውም ሰው ነው፤
4) "የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዳ" ማሇት የሲሚንቶ ምርትን ከአምራች፣ ከአስመጭ ወይም ከጅምሊ ነጋዳ በመግዛት
ሇተጠቃሚ የመሸጥ ህጋዊ የንግዴ ፈቃዴ ያሇው ማንኛውም ሰው ነው፤
5) ”የሲሚንቶ አምራች” ማሇት የሲሚንቶ ምርትን በፋብሪካ የሚያመርትና ሇገበያ የሚያቀርብ ወይም ሇሽያጭ
ዓሊማ የሚያመርት ማንኛውም ሰው ነው፤
6) ”መጋዘን” ማሇት በፋብሪካዎችና በአካባቢው ንግዴን ሇማስተዲዯር ስሌጣን በተሰጠው አካሌ ዘንዴ የታወቀና
ሲሚንቶን ሇማከማቸት፣ ሇማከፋፈሌ እና ሇመቸርቸር የተዘጋጀ የማከማቻ ህጋዊ ፍቃዴ የወጣበት ቦታ ነው፤
7) ”ዴርጅት” ማሇት ሲሚንቶን ሇግንባታ ዓሊማ የሚጠቀም የህግ ሰውነት ያሇው ማንኛውም መንግስታዊ፣ የግሌ
ወይም መንግሥታዊ ያሌሆነ አካሌ ነው፤
8) ”የመንግስት ፕሮጀክቶች” ማሇት በፌዳራሌና በክሌሌ መንግስታት በጀት የሚገነቡ ግንባታዎች ናቸው፤
9) "ሰው" ማሇት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካሌ ነው፤
10) በዚህ መመሪያ በወንዴ ጾታ የተገሇጸው ሴትንም ይጨምራሌ፡፡

3. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ ሲሚንቶን በሀገር ውስጥ በሚያመርት፣ ከውጪ ወዯ ሀገር በሚያስገባ፣ በጅምሊ ወይም በችርቻሮ
በሚሸጥ፣ እና ሇግንባታ በሚጠቀም ማንኛውም ሰው ሊይ ተፈጻሚ ይሆናሌ፡፡

2
ክፍሌ ሁሇት

ስሇ ሲሚንቶ የግብይት ሥርዓት

4. የሲሚንቶ የግብይት አሠራር


1) የፌዳራሌና የክሌሌ የመንግስት ፕሮጀክት ገንቢና የስራ ተቋራጭ ከአሠሪ መ/ቤት ጋር የተገቡትንና በአስሪው
መስሪያ ቤቱ የበሊይ ኃሊፊ የተረጋገጠ የሥራ ውሌ ሇፋብሪካው በማቅረብና እንዱሁም ትሊሌቅ ሪሌ ስቴት
ገንቢና ኦፒሲ ሲሚንቶን በሚጠቀም በሚክሰር የተዘጋጀ ኮንክሪት የሚያመረት ዴርጅት ከፋብሪካው ጋር
የግዥና የሽያጭ ውሌ በመዋዋሌ በቀጥታ ከፋብሪካው ግዥ መፈፀም ይችሊሌ፡፡

2) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተገሇፀው እንዯተጠበቀ ሆኖ የፌዳራሌና የክሌሌ የመንግስት ፕሮጀክት ገንቢ
ሲሚንቶን በአቅራቢያው ከሚገኘው ጅምሊ አከፋፋይ ወይም ቸርቻሪ መግዛት ይችሊሌ፤
3) የሲሚንቶ ፋብሪካው በዚህ መመሪያ መሠረት ምርቱን በጅምሊና በችርቻሮ ከሚያከፋፍሌ ህጋዊ የንግዴ
ፈቃዴ ካሇው ነጋዳ ጋር ውሌ በመግባት ሲሚንቶ ሇገበያ እንዱቀርብ ያዯርጋሌ፡፡
4) በሲሚንቶ አምራች፤ በጅምሊ ነጋዳ፤ በዴርጅት እና በቸርቻሪ መካከሌ የሚዯረገው ውሌ የሲሚንቶ መግዣና
መሸጫ ዋጋን ማካተት አሇበት፡
5) የሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲስፈሊጊነቱ በዋና ዋና ከተሞች የማከፋፈያ መጋዝን ማዯራጀትና ከፋብሪካ ጭምር
በቀጥታ ሇተጠቃሚው ሲሚንቶ መሸጥ ይችሊሌ፡፡
6) የሲሚንቶ ፋብሪካ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው የፋብሪካ መጋዘን የሲሚንቶ የመሸጫ ዋጋ መሰረት ሽያጭ
ይፈጽማሌ፡፡
7) የሲሚንቶ ፋብሪካ ከፋብሪካው መጋዝን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ መነሻ በማዴረግ የትራንስፖርት ወጪ፣
የጫኝና አውራጅ፤ የትርፍ ህዲግና ላልች ወጪዎችን ታሳቢ ያዯረገ የዋና ዋና ከተሞች የጅምሊና የችርቻሮ
የመሸጫ ዋጋ ጣሪያ በማዘጋጀት ሇሚኒስቴሩ ያሳውቃሌ፡፡
8) በፋብሪካ፤ በጅምሊና በቸርቻሪ ነጋዳ መካከሌ የሚፈፀመው ግብይት የገዥውን የግብር ከፋይ መሇያ ቁጥር
ባካተተ ህጋዊ ዯረሰኝ መሠረት የሚከናወን መሆን አሇበት፡፡
9) ሕጋዊና ነፃ የሲሚንቶ ግብይትና ዝውውርን የሚገዴቡ አሠራሮችና ኬሊዎች መኖር የሇባቸውም፤

ክፍሌ ሦስት
የሚኒስቴሩና በክሌሌ ንግዴን ሇማስተዲዯር በህግ ስሌጣን የተሰጠው አካሌ ተግባርና ኃሊፊነት

5. የሚኒስቴሩ ተግባርና ኃሊፊነት

ሚኒስቴሩ የሚከተለት ተግባርና ሃሊፊነቶች ይኖሩታሌ፡-

3
1. የሲሚንቶ ምርት አቅርቦትን መነሻ ያዯረገ እንዯአስፈሊጊነቱ የግብይት እና የስርጭት የአሰራር ስርአት ይዘረጋሌ፣
አፈጻጸሙን ይከታተሊሌ፤
2. የፋብሪካ መጋዝን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ እንዯየአስፈሊጊነቱ በየስዴስት ወሩ እየወሰነ ያሳውቃሌ፤
3. ፋብሪካ የፋብሪካውን መጋዝን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ መነሻ በማዴረግ ሇየከተሞቹ የጅምሊና የችርቻሮ የመሸጫ
ዋጋ ጣሪያ ማውጣቱን ይከታተሊሌ፤ ሇሚመሇከታቸው ያሳውቃሌ፤
4. የሲሚንቶ ግብይት በወጣው ዋጋ መሠረት እየተፈፀመ መሆኑን ይከታተሊሌ፤
5. የሲሚንቶ ምርት አፈፃፀም፣ የስርጭትና የመሸጫ ዋጋ መረጃዎችን ይከታተሊሌ፤ ይቆጣጠራሌ፤ የክትትሌና
ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት ከሚመሇከታቸው አካሊት ጋር በመነጋገር ሇሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ ይሠጣሌ፤
6. በዚህ መመሪያ የተቀመጡት አሰራሮች በተገቢው ስሇመፈጸማቸው ይከታተሊሌ፤ ይቆጣጠራሌ፡

6. የክሌሌ እና የከተማ መስተዲዯር የንግዴ ተቆጣጣሪ አካሊት ተግባርና ኃሊፊነት


በክሌሌ እና በከተማ መስተዲዴር ንግዴን ሇመቆጣጠር በህግ ስሌጣን የተሰጠው አካሌ የሚከተለት ተግባርና ሃሊፊነቶች
ይኖሩታሌ፡-

1) በክሌለ ወይም በከተማው ሲሚንቶን በጅምሊና በችርቻሮ የሚሸጥ ነጋዳ ህጋዊ የንግዴ ፈቃዴ ያሇው መሆኑን
ይከታተሊሌ፤ይቆጣጠራሌ፤
2) በክሌለ ወይም በከተማው የተሇያየ አካባቢ በየወቅቱ ያሇውን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ይከታተሊሌ፤
ሇከተማው በተቀመጠው የዋጋ ጣሪያ መሠረት እየተፈፀመ መኆኑን ይከታተሊሌ፤ ከጣሪያው በሊይ ሆኖ ሲገኝ
እርምጃ ይወስዲሌ፤ ሇሚንስቴሩም ያሳውቃሌ፤
3) በክሌለ ወይም በከተማው የሲሚንቶ ነፃ ዝውውርን የሚገዴብ አሰራርና ኬሊ እንዲይኖር ያዯርጋሌ፤
4) በክሌለ ወይም በከተማው የጅምሊ አከፋፋይ እና ቸርቻሪ ነጋዳ ሽያጩን በህጋዊ ዯረሰኝ ብቻ ስሇማከናዎኑ
ይከታተሊሌ፤ ይቆጣጠራሌ፡፡

ክፍሌ አራት

የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ፣ ጅምሊና ቸርቻሪ ነጋዳ ግዳታ

7. የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ ግዳታ

እያንዲንደ የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ የሚከተለት ግዳታዎች አለበት፡-

1) በፋብሪካው የተመረተ ሲሚንቶን በዚህ መመሪያ አንቀፅ 4 በተዯነገገው አግባብ ሇነጋዳ እና ሇተጠቃሚ ሽያጭ
ይፈፅማሌ፤
4
2) በፋብሪካው የተመረጠና ሲሚንቶን በጅምሊና በችርቻሮ የሚሸጥ ነጋዳ በዚህ መመሪያ መሰረት መፈጸሙን
የማረጋገጥ ኃሊፊነት አሇበት፤
3) የፋብሪካ መጋዝን የሲሚንቶ ዋጋን መነሻ በማዴረግና የትራንስፖርት ክፍያ፤ የጫኝና አውራጅ፤ የመጋዘን ኪራይ
ወጪዎችንና የትርፍ ህዲግ በማካተት የሲሚንቶ ምርት በተሇያዩ ክሌልችና ከተሞች በጅምሊና በችርቻሮ
የሚሸጥበትን የዋጋ ጣሪያ በማዘጋጀት ሇሚንስቴሩ ያሳውቃሌ፤
4) የሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲስፈሊጊነቱ በየስዴስት ወሩ የፋብሪካ መጋዝን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ክሇሳ እንዱዯረግ
በጥናት የተዯገፈ ጥያቄ ሇሚኒስቴሩ ማቅረብ ይችሊሌ፤
5) በፋብሪካው፤በጅምሊ አከፋፋይ፤ በቸርቸሪዎች፤ እና በዴርጅቶች መካከሌ የሚገባው የግብይት ውሌ በዚህ መመሪያ
ተዯነገጉትን ግዳታዎች የያዘ እንዱሆን ያዯረጋሌ፤ ሇዚህ የሚሆን የውሌ ፎርማት በማዘጋጀት ሇጅምሊ አከፋፋይና
ቸርቸሪዎች እንዱዯርስ በማዴረግ ያስፈፅማሌ፤
6) የሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ የሲሚንቶ ግዥና ሽያጭ እንቅስቃሴቸውን የሚያሳይ መረጃ በአግባቡ የመያዝ፣
በተቆጣጣሪ አካሊትም ሲጠየቁ የማቅረብ ግዳታ አሇበት፣
7) የፋብሪካውን የምርት መጠንና የሥርጭት አፈፃፀም (ሇመንግስት ፕሮጀክት፤ ሇጅምሊ ነጋዳ፣ ሇቸርቻሪ እና ሇላሊ
ተጠቃሚ የተፈፀመውን ሽያጭ) እንዱሁም ከሥርጭት ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ችግሮችንና የመፍትሄ ሐሳቦችን
በተመሇከተ ሇሚኒስቴሩ በየወሩ ሪፖርት ያቀርባሌ፡፡

8. የሲሚንቶ ጅምሊና ቸርቻሪ ነጋዳዎች ግዳታ


እያንዲንደ የሲሚንቶ ጅምሊና ቸርቻሪ ነጋዳ የሚከተለት ግዳታዎች አለበት፡-

1) የሲሚንቶ ግብይቱን በዚህ መመሪያ መሠረት ያከናውናሌ፤


2) የሲሚንቶ ጅምሊ ነጋዳ ሲሚንቶ የሚገዛውን ቸርቻሪ ዴርጅት የግብር ከፋይ መሇያ ቁጥር በመመዝገብ በህጋዊ
ዯረሰኝ ሽያጭ ማከናወን አሇበት፤
3) በግዥ የተረከበውን ሲሚንቶ በተቀመጠው የዋጋ ጣሪያ መሠረት ሇማንኛውም ተጠቃሚ መሸጥ አሇበት፤
ሲሚንቶን ከህጋዊ መስመር ውጭ አሊግባብ አከማችቶ መያዝና ከተተመነው የዋጋ ጣሪያ በሊይ መሸጥ አግባብ
ባሇው ህግ ያስጠይቃሌ፤
4) የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዳ የያዘውን የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በንግዴ መዯብሩ በግሌፅ በሚታይ ቦታ ሊይ
መሇጠፍ አሇበት፤
5) የሲሚንቶ ግዥና ሽያጭ እንቅስቃሴውን መረጃ በአግባቡ የመያዝ፣ በተቆጣጣሪ አካሊት ሲጠየቅም የማቅረብ
ግዳታ አሇበት፡፡

5
ክፍሌ አምስት
ሌዩ ሌዩ ዴንጋጌዎች

9. አስተዲዯራዊና ህጋዊ እርምጃ

ይህን መመሪያ የሚተሊሇፍ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባሇው ህግ ተጠያቂ ይሆናሌ፡፡

10. የመተባበር ግዳታ

ማንኛውም ሰው ሇዚህ መመርያ ተፈፃሚነት የመተባበር ግዳታ አሇበት፡፡

11. የተሻሩ መመሪያዎች እና አሰራሮች

የሲሚንቶ አቅርቦትና ግብይት መመሪያ ቁጥር 908/2014 እና የስሚንቶ ግብይትና ዝውውርን አስመሌክቶ
መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የወጣው የህዝብ ማስታወቂያ በዚህ መመሪያ ተሽረዋሌ፡፡

12. መመሪያውን ስሇማሻሻሌ

ሚኒስቴሩ ይህንን መመሪያ እንዯአስፈሊጊነቱ ሉያሻሽሌ ወይም ሉሰርዝ ይችሊሌ፡፡

13. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከጸዯቀበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናሌ፡፡

ገብረመስቀሌ ጫሊ ሞጣል

የንግዴና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር


ታህሳስ 27/2015 ዓ.ም
አዱስ አበባ

You might also like