Professional Documents
Culture Documents
የቅጥር ዝርዝር 14
አሻራ ለመመዝገብ 15
ተቀናሽን ለመመዝገብ 16
ፍቃድ ለመመዝገብ 18
የሪፖርቶች አቀራረብ 29
የሪፖርት አቀራረብ ፅንሰ-ሃሳቦች 32
የሪፖርት መሥፈርቶች 32
ድርጅት 35
ታክሶች 36
የደምወዝ መዋቅር 37
i
ሥራን 37
የበዓል ቀናት 37
የጊዜ ወሰን 38
ፈረቃ 38
መርሃ ግብር 38
የትርፍ ሰአት ሥራ 38
አማራጮች 38
የፍቃድ አይነት 38
ጥቅማ ጥቅሞ 38
ዝምድና 39
የትምሕርት ደረጃ 39
የስራ ምድብ 39
የድርጅቱ መዋቅር አይነት 39
የማሰናበቻ ምክንያት 39
የጋብቻ ሁኔታ 39
የሙያ አይነት 39
ብሔር 39
ii
የ እ ን ግ ሊ ዝ ኛ ግ ብ ራ ዊ ስ ያ ሜ ተ ለ ዋ ጮ ች
የምስሎች ዝርዝር
ምስል 1 የአይታፕ መግቢያ ገጽ ............................................................................................................ 3
ምስል 2: የአይታፕ ቅድመ-ገጽ .............................................................................................................. 5
ምስል 3 የሚስጥር ቁልፍ መቀየሪያ ገጽ................................................................................................. 6
ምስል 4 የአይታፕ ሥርዓት ዋና ገጽ ..................................................................................................... 7
ምስል 5: ሳይድ ባር- ............................................................................................................................ 12
ምስል 6: የሰራተኛ - ዝርዝር ማሳያ ገጽ .............................................................................................. 13
ምስል 7: የሰራተኛ መመዝገቢያ........................................................................................................... 13
ምስል 8: የሰራተኛ የቅጥር ዝርዝር መመዝገቢያ .................................................................................. 14
ምስል 10: የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅማ መመዝገቢያ................................................................................... 16
ምስል 11: የሰራተኛ የሆላ ጥቅማ ጥቅማ መመዝገቢያ .......................................................................... 16
ምስል 18: የሰራተኛ የሆላ ክፍያ መመዝገቢያ ...................................................................................... 21
ምስል 19: ሳይድ ባር- የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ መምረጫ................................................................... 22
ምስል 20: የሰራተኛ የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ ...................................................................................... 22
ምስል 21: የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ - ማዘጋጃ ..................................................................................... 23
ምስል 22: የትርፍ ሰአት ስራ ማሳያ .................................................................................................... 24
ምስል 23: የትርፍ ሰአት ስራ መመዝገቢያ .......................................................................................... 24
ምስል 24: የተረኛ ሰራተኛ መመዝገቢያ............................................................................................. 25
ምስል 25: የተረኛ ሰራተኛ ደሞዝ ማሳያ ............................................................................................ 27
ምስል 26: ደሞዘ የሚከፈልበትን ቀን መምረጫ ................................................................................... 27
ምስል 27: ደሞዘ የሚከፈልበትን የክፍያ አይነት .................................................................................. 28
ምስል 28: ደሞዘ የሚከፈልበትን ሰራተኛ ............................................................................................. 28
ምስል 29: የደሞዘ ቅድመ እይታ ......................................................................................................... 29
ምስል 30 : የተከፈለው ደሞዘ .............................................................................................................. 29
ምስል 31: የሪፖርት አይነቶች ............................................................................................................. 30
ምስል 32: የደሞዘ መክፈያ ሪፖርት..................................................................................................... 30
ምስል 33: ዝርዝር ሪፖርት .................................................................................................................. 31
ምስል 34: የሰው ሃይል ሪፖርት ........................................................................................................... 31
ምስል 35: የሪፖርት አዘገጃጀት ............................................................................................................ 32
ምስል 36: ማቀናበሪያ .......................................................................................................................... 33
ምስል 37: የደሞዝ መክፈያ ................................................................................................................. 34
ምስል 38: የድርጅት ማቀናበሪያ .......................................................................................................... 35
ምስል 39: የድርጅት መረጃ ማቀናበሪያ ............................................................................................... 35
ምስል 40: መዋቅር መጨመሪያ ........................................................................................................... 36
ምስል 41: ባዮሜትሪክ ......................................................................................................................... 36
ምስል 42: የደሞዝ መዋቅር ................................................................................................................. 37
iv
የ አ ይ ታ ፕ ቅ ድ መ ገ ጽ
በዚህ መመሪያ ውስጥ የሚገኙት ማስገንዘቢያዎችና ጥቅሻዎች ከዚህ ምልክት ጎን
ተቀምጠዋል።
vi
መ ግ ቢ ያ
ምዕራፍ
1
መግቢያ
አይታፕ የተቀናጀ የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያና የደምወዝ ክፍያ መረጃ ማስተዳደሪያ ሥርዓት ሲሆን የተዘጋጀውም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስና የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሲሆን ዋናው አላማውም የፋይናሻል መረጃ
አያያዝ ስርዓትን ለመደገፍና ለማቀላጠፍ ነው።
የአይታፕ ዋና አገልግሎት በከተማ አስተዳድሩ ስር የሚገኙ ተቋሞችን የደምወዝ ወጪ መቆጣጠር ነው። ሥርዓቱ/
ሲስተሙ የተቋሞችን የሰራተኛ የስራ ሰአት ለመቆጣጠር ፣ ደምወዝን እና ከደምወዝ ክፍያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን
ሂሣብ እንቅስቃሴዎችን ለመመዝገብ ፣ የሂሣብ ሪፖርቶችን ለማሰናዳት በተጨማሪም ለማጠቃለያና ለአስተዳደር ሥራ
የሚያገለግሉ የተለያዩ ሪፖርቶችን ለማቅረብ ይረዳል።
ይህ የተጠቃሚዎች መመሪያ የሥርዓቱን አበይት አጠቃቀሞች ይተነትናል። በመመሪያው ውስጥ ከሚገኙት ርዕሶች
መካከል፤
ሥርዓቱን ማስጀመር
የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ ማስተዳደር
የደምወዝ ክፍያ ማስተዳደር
ሰራተኛ ማስተዳደር
ሪፖርቶችን ማቅረብ
የሥርዓቱን የተለያዮ ምርጫዎች ማቀናበር።
1
አ ይ ታ ብ ስ ር ዓ ት ን መ ጀ መ ር
ምዕራፍ
2
አይታፕን መጀመር
አይታፕ የተዘጋጀው በመረጃ መረብ መፈለጊያ /ብራውዘር/ ላይ እንዲሰራ ሆኖ ነው። በዋነኝነት ጉግል ክሮም
ብራውዘር ቨርዥን 50 እና በላይ ተመራጭ ነው። አይታፕ ውስጥ ለመግባት፤
በመጀመሪያ የመረጃ-መረብ መፈለጊያውን ይክፈቱ። ይህንን ለማድረግ ከዋናው መስኮት ጉግል ክሮምን ምስል
በመጫን ወይም በዋናው መስኮት የግራ ግርጌ የሚገኙትን የዊንዶውስ ‘Start′ ቀጥለውም ‘All
Programs′ የሚሉትን መቆጣጠሪያዎች ተጭነውና ከሚገኙት የኘሮግራሞች ዝርዝር Google Chrome
የሚለውን በመምረጥ ይሆናል።
በመረጃ መፈለጊያው የድህረ-ገጽ አድራሻ መፃፊያ ሳጥን ውስጥ ትክክለኛውን አድራሻ ከፃፉ በኋላ ከኪይቦርዶ
ላይ (Enter) የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። የድህረ-ገጹ ቋሚ አድራሻ የሚከተለው ነው።
http://www.itap.gov.et/
የድህረ-ገጽ አድራሻው ከክልል ወደ ክልል ሊለያይ ስለሚችል ትክክለኛውን አድራሻ
ከሥርዓት አስተዳዳሪው ጠይቀው መረዳት ይችላሉ። የመረጃ መረብ መፈለጊያው
ሲከፈት በቀጥታ ወደ አይታፕ መግቢያ ገጽ እንዲሄድ ለማድረግ ተጨማሪ
መግለጫውን ይመልከቱ።
በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጹትን ትዕዛዞች ከፈፀሙ በኋላ የሚከተለውን የአይታፕ መግቢያ ገጽ ያገኛሉ።
2
የ አ ይ ታ ፕ ቅ ድ መ ገ ጽ
3
የ አ ይ ታ ፕ ቅ ድ መ ገ ጽ
የአይታፕ ቅድመገጽ
የአይታፕ መግቢያ ገጽ ውስጥ ትክክለኛ የተጠቃሚ ስምና የሚስጥር ቁልፍ ካስገቡ በኋላ በምስሉ ላይ ወደሚታየው
ገጽ ይወሰዳሉ።
ምስል 2: የአይታፕ ቅድመ-ገጽ
የአይታፕ ቅድመ-ገጽ የተጠቃሚውን ስም ፣ የቋንቋ መምረጫና የገባው ተጠቃሚ መጠቀም የሚፈቀድለትን ዝርዝር
ትእዛዝ መስጫ ዝርዝሮች ያጠቃልላል።
ወደ አይታፕ መግቢያ ገጽ መመለስ ከፈለጉ ከሥርዓቱ ከበስተቀኝ በኩል የሚገኘውን የሰው ምስል
የሚመስለውን በመጫን ‘ከሥርዓቱ መውጫ′ የሚለውን አያያዥ ቃል በመጫን ወደ አይታፕ መግቢያ ገፅ መመለስ
ይችላሉ። የሚስጥር ቁልፍ ለመቀየርም ‘ቁልፍ መቀየሪያ′ የሚለውን አያያዥ ቃል በመጫን የሚስጥር ቁልፎን መቀየር
ይችላሉ።
5
የ አ ይ ታ ፕ ቅ ድ መ ገ ጽ
የሚመርጡት የሚስጥር ቁልፍ ተገቢ እንዲሆን ቢያንስ ሰባት ቢበዛ አስራ ስድስት ፊደላት ያሉትና
ፊደላቱም ቢያንስ አንድ ትልቅ (ወይም Capital፤ ለምሳሌ ‘A’) እና አንድ ትንሽ (ወይም Small፤
ለምሳሌ ‘a’) ከሆኑ የእንግሊዝኛ ፊደሎች እና ቢያንስ ከአንድ ቁጥር (ለምሳሌ ‘1’) የተውጣጡ
መሆን አለባቸው።
3
ዋ ና ገ ጽ ታ
ምዕራፍ
3
የአይታፕ ሥርዓት ዋና ገጽ
የአይታፕ ዋና ገጽ ከሶስት ክፍሎች የተውጣጣ ነው። ክፍሎቹም በሚከተለው ምስል ላይ ቀርበዋል።
ምስል 4 የአይታፕ ሥርዓት ዋና ገጽ እራስጌ
የትዕዛዝ መስጫ
ዝርዝር ይዘት
7
ዋ ና ገ ጽ ታ
ሰራተኛ መመዝገብያ
የተለያዩ የሰራተኛ መረጃ መመዝገብያ
የትርፍ ሰዓት ስራ
የትርፍ ሰዓት ስራ ለመመዝገብ
ከተጣመሩ ገጽዎች ለመውጣት ‘ዝጋ′ ወይም ‘ይቅር′ የሚሉትን ትዕዛዞች መጫን ይቻላል። የመረጃ
መረብ መፈለጊያ ውስጥ የተለመደውን ወደኋላ መመለሻ ትዕዛዝ መጫን በአይታፕ ውስጥ
የሥርዓት ስህተቶች ሊያስከስት ስለሚችል ‘ተመለስ′ የሚለው ትዕዛዝ ሲኖር እሱን በመጫን
ወይም ‘ዝጋ′ በሚለው ትዕዛዝ የተጣመሩ ገጽዎቹን ዘግቶ ከእንደገና ማስጀመር ይመረጣል።
ዝጋ የተከፈተውን ቅጽ ለመዝጋት
8
ዋ ና ገ ጽ ታ
9
ጥ ቅ ል የ አ ጠ ቃ ቀ ም ማ ብ ራ ሪ ያ
ምዕራፍ
4
ጥቅል የአጠቃቀም ማብራሪያ
የአይታፕ ሥርዓት ‘መደበኛ’ ወይም ‘አስተዳደራዊ’ ተብለው ሊከፋፈሉ የሚችሉ የተለያዩ ሥራዎችን
ይሰራል።
መደበኛ ሥራዎች
የአይታፕ ሥርዓት ሰራተኞችን
በተመለከተ የተለያዩ መረጃን
ሰራተኛ ማስተዳደር ለመመዝገብ ፣ ለማስተካከልና
ለመከታተል ይረዳል።
10
ጥ ቅ ል የ አ ጠ ቃ ቀ ም ማ ብ ራ ሪ ያ
አስተዳደራዊ ሥራዎች
የአይታፕ ሥርዓት የሚጠቀምባቸውን
እንደ በዓል ቀናት ፤ የሙያ አይነቶች ፤
ምርጫዎች ተቀናናሽ አይነቶች እና የመሳሰሉትን
መረጃዎችን ለመመዝገብና
ለማስተካከል ይረዳል።
11
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ምዕራፍ
5
መደበኛ ሥራዎች
በስርዓቱ ውስጥ ሰራተኛ የማስተዳደር ሥራዎች ከዚህ በታች በዝርዝር ይብራራል።
12
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
13
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ስም * የሚለው ከጎኑ ኮከብ (*) ስላለበት ሣጥኑን ሳይሞሉ ማለፍ አይችሉም! ኮከብ
ያልሰፈረባቸውን ግን የመሙላትና ያለመሙላት ምርጫ በእርስዎ ፍላጎት ላይ የሚወሰን
ነው፡፡
የቅጥር ዝርዝር
የቅጥርዝርዝር ውስጥ የቅጥር ሁኔታ፣ የቅጥር ቀን፣ የስራ ክፍል፣ ደምወዝ፣ የባንክ ቁጥር መመዝገብ
አለባቸው። የጡረታ መዋጮ የማይመለከተው ሰራተኛ ከሆነ/ነች እዚው ገጵ ላይ የጡረታ መዋጮ የማይመለከተው
የሚለው ላይ ቲክ ያድርጉ።
14
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
አሻራ ለመመዝገብ
የሠራተኛን የግል መረጃ ሞልተው ካጠናቀቁ በኋላ አሻራ የሚለውን በመጫን በሚመጣልዎት ቅፅ ላይ
የሠራተኛዎን የጣት አሻራ ማስገባት ይችላሉ፡፡
በዚህ ቅፅ (አሻራ) ላይ ከዚህ በፊት ተመዝግቦ የነበረውን የሠራተኛዎን የጣት አሻራም ማጥፋት
ይችላሉ፡፡ የሠራተኛዎን የጣት አሻራ ለማንሳት ሲፈልጉ በቅፁ ውስጥ የሚገኘውን ‹‹የጣት አሻራ አንሳ››
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ የሚፈልጉትን እንቅስቃሴ ከመዘገቡ በኋላ ‘መዝግብ’ የሚለውን
ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
15
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ማስታወሻ “ የጥቅማ ጥቅሙ አይነት ታክስ የሚጥልበት ከሆነ “ታክስ የሚጥልበት መጠን” የሚለው ላይ
ይመዝግቡ፡፡
ተቀናሽን ለመመዝገብ
በተመረጠው ሰራተኛዎ ላይ ተቀናሽ የሚሆኑ ዝርዝሮችን መሙላት ሲፈልጉ ‹‹ተቀናሽን›› ይጫኑ፡፡ ተቀናሽን
ከተጫኑ በኋላ በሚመጣልዎት ቅፅ ላይ እንዲቀነስ የፈለጉትን ዝርዝር ለማስገባት ’አዲስ ጨምር’ የሚለውን
ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
16
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
በዚህ ቅፅ ላይ ‹‹ከዚህ በፊት የተከፈለ›› በሚለው ዝርዝር ሥር ሠራተኛዎ ከዚህ በፊት የከፈለው የገንዘብ
መጠን ካለና እሱኑ መመዝገብ ከፈለጉ ከሥር ያለውን ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
በተቀናሽ ሥር የሚገኘውን ቅፅ ሞልተው ካጠናቀቁ በኋላ ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
17
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ፍቃድ ለመመዝገብ
የሠራተኛዎን የተወሰደ የዓመት ፍቃድና የዓመት ፍቃድ ክፍያ መመዝገብ ሲፈልጉ ‹‹ፍቃድ›› የሚለውን
ይጫኑ፡፡ ፍቃድ የሚለውን ሲጫኑ ‹‹የተወሰደ የዓመት ፍቃድ›› እና ‹‹የዓመት ፍቃድ ክፍያ›› የሚሉ ዝርዝሮች
ከአንድ ቅፅ ጋር ይመጣልዎታል፡፡
የተወሰደ የፍቃድ ዝርዝር ለመሙላት ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘አዲስ
ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ከተጫኑ በኋላ የሚመጣልዎትን ቅፅ ይሙሉ፡፡ ቅፁን ሞልተው
ካጠናቀቁ በኋላ ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የዓመት ፍቃድ ክፍያ ከመዘገብ በኋላ ክፍያውን ለማዘጋጀት ደሞዝ መክፈያ ላይ ሄደው የክፍያውን ዓይነት “የዓመት
ፍቃድ ክፍያ“ የሚለውን መርጠው ያዘጋጃሉ፡፡
18
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
የዓመት ፍቃድ ክፍያን መሙላት ሲፈልጉ ከላይ በኩል የሚገኘውን ፍቃድ በሚለው ገፅ ሥር የሚገኘውን
‹‹የዓመት ፍቃድ ክፍያ›› ይጫኑ፡፡ እሱኑ ሲጫኑ በሚመጣልዎት ቅፅ ሥር የሚገኘውን ‘አዲስ ጨምር’
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ከተጫኑት በኋላ የሚመጣልዎትን ቅፅ ይሙሉ፡፡ በቅፁ ላይ ያሉት
ዝርዝሮች በሙላ ከጎናቸው በቀይ ኮከብ ”የሰፈረባቸው ስለሆነ ሳይሞሉ ማለፍ አይችሉም!“ ቅፁን
ሞልተው ሲያጠናቅቁ ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫን ይጫኑ፡፡
19
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
የዓመት ፍቃድ ክፍያ ከመዘገብ በኋላ ክፍያውን ለማዘጋጀት ደሞዝ መክፈያ ላይ ሄደው የክፍያውን ዓይነት “የዓመት
ፍቃድ ክፍያ“ የሚለውን መርጠው ያዘጋጃሉ፡፡
ደመወዝ ማስተካከያ
ፍቃድ ከሚለው ዝርዝር ታች ”ደመወዝ ማስተካከያ“ የሚል ያገኛሉ፡፡ እሱን ሲጫኑ ‹‹የደመወዝ እድገት›› እና
‹‹ደመወዝ ማረሚያ›› የሚሉ ትእዛዝ መስጫ ይመጣልዎታል፡፡ በዚህ ቅፅ ሥር የተመረጠው ሰራተኛዎ
የተሳሳተ ደሞዝ ተሰቶ ለማረም አንዲሁም እስከ ዛሬ ድረስ ያገኛቸው የደመወዝና የስራ መደብ እድገቶች
ይመዘግቡበታል፡፡
20
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
21
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
1) በግራ በኩል ከሚገኙት ትዕዛዝ መስጫ ስብስቦች መካከል ‘የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ’ የሚለውን
ይጫኑ። ይህን እንዳረጉ ከታቹ ተጨማሪ የትዕዛዝ መስጫ ይዘረዝራል።
1 ‘ባለበት አፅድቅ’ ሰራተኛው የሰራበትን ቀን ያጸድቅና የቀረበትን ቀን ከደመወዙ እንዲቆረጥ ያደርጋል ሁኔታው
“በሄደት ላይ ያለ” የሚለው ወደ “የጸደቀ” ይቀየራል፡፡
2 ‘ቀሪ አጥፍተህ አፅድቅ’ የሚለው ሰራተኛው ምንም አይነት ቀሪ በማይኖርበት ጊዜ ሲሆን ሁኔታው “በሂደት ላይ
ያለ” የሚለው ወደ “የጸደቀ” ይቀየራል፡፡
3 ‘ወደ ነበረበት መልስ’ ወደ መጀመሪያው እንዲመለስ እስካሁን የተሰራው የሰአት መቆጣጠሪያ ወደ መጀመሪያው
ለመመለስ ማለት ሁኔታዉን ከ“የጸደቀ” ወደ “በሂደት ላይ ያለ” ይቀይረዋል፡፡
ዝርዝር ይዘቱን ለማየት እና የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያዉን ለማስተካከል ከተዘርዘሩት ሰራተኞች ላይ ይጫኑ።
የሚከተለው ገጽ ይከፈታል።
22
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
የተፈለገውን መረጃ ካቀረቡ በኋላ በገጽዎ ግርጌ የሚገኘውን የሚለውን ትዕዛዝ መስጫ
በመጫን እንቅስቃሴውን ሥርዓቱ ውስጥ ይመዝግቡ።
ትርፍ ሰዓት ስራ
የሰራተኛውን የትርፍ ሰዓት የምንመዘግብበት ሲሆን ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ስንጫን መመዝገቢያ
ያመጣልናል ፡፡
23
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
24
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ተረኛ/ምንዳ
ተረኛ/ምንዳ እንደ ትርፍ ሰዓት ሲሆን ለመመዝገብ ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ይጫናሉ ስም ቀንና የተረኛ
ዓይነት የሚል እናገኛለን፡፡የተረኛ ዓይነት ውስጥ ምንዳንም እናገኛለን፡፡ ተረኛ/ምንዳ ከመዘገብ በኋላ ክፍያውን
ለማዘጋጀት ደሞዝ መክፈያ ላይ የክፍያው ዓይነት “የተረኛ ወይም ምንዳን” ይመርጡና ያዘጋጃሉ፡፡
25
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
26
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
1. በስተግራ በኩል የሚገኘውን ደምወዝ መክፈያ የሚለውን ሲጫኑ ማዘጋጃ ያገኛሉ፡፡ ደምወዝ
ማዘጋጀት የፈለጉ እንደሆነ ‘አዲስ ደሞዝ ማዘጋጃ’ የሚለውን ይጫኑ፡፡
27
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
5. ‹‹ቅድመ እይታ›› የሠራተኞቾ ደምወዝ መክፈያ የሚመለከቱበት ክፍል ነው፡፡ ይህም ማለት
የሠራተኞችዎ የጡረታ ገንዘብና ወጪዎች በየክፍሉ ተተንትነው የሚቀርቡበት ክፍል ነው፡፡
28
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ይቀጥል የሚለው ፔሮል መስራት ጀምረን ልናስተካክል ሌላ ቦታ ገብተን ስንመለስ ካቆምንበት እንድንቀጥል
ይረዳናል፡፡
ለምሳሌ ፦ ተቀናናሽ ላይ የምናስተካክለው ነገር ቢኖር እሱን አስተካክለን ስንመለስ ይቀጥል የሚለውን ከፍተን
ካቆምንበት መቀጠል እንችላለን ካልፈለነው ግን ውጣ ብለን እንዳዲስ መጀመር እንችላለን፡፡
የሪፖርቶች አቀራረብ
የአይታፕ ሥርዓት በርካታና በይዘታቸው የተለያዩ የደምወዝ ክፍያ ሪፖርቶችን ለማሰናዳት ይረዳል። የአይታፕ
ሥርዓት ውስጥ የተካተቱት ሪፖርቶች በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ። እነዚህም፤ የደምወዝ መክፈያ ሪፖርቶች ፤
ዝርዝር ሪፖርቶች እና የአስተዳደር ሪፖርቶች በመባል ይከፋፈላሉ። ከዚህ ቀጥሎ በአይታፕ ውስጥ ሪፖርቶችን
29
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ከማቅረብ ጋር በተያያዘ ስለሪፖርት አቀራረብ ክፍሎችና በሥርዓቱ ውስጥ የተጠቃለሉት ሪፖርቶች ዝርዝር ከአጭር
ማብራሪያቸው ጋር ተቀምጠዋል።
ሪፖርት የሚለውን ውስጥ ሲገቡ የደሞዘ ፣መክፍያ ሪፖርት፣ ዝርዝር ሪፖርት እና የሰው ሃይል ሪፖርት
ይኖራሉ።
30
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ዝርዝር ሪፖርት -
31
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
የሪፖርት መሥፈርቶች
በአይታፕ ውስጥ አብዛኞቹ ሪፖርቶች ከመዘጋጀታቸው በፊት ተጠቃሚው/ዋ መሥፈርቶች ወይም የሪፖርት ዝርዝር
ይዘት ማመልከቻዎችን እንዲጠቁም/እንድትጠቁም ይጠየቃል/ትጠየቃለች። እነዚህ መሥፈርቶች የሪፖርቱን ወቅት እና
በረድፎቹ እንዲደረደሩ የተፈለጉትን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ሪፖርቶች በኤች. ቲ. ኤም. ኤል. ፣ በፒ. ዲ. ኤፍ. እና በማይክሮሶፍት ኤክሴል መልክ ይዘጋጃሉ። የኤች. ቲ. ኤም. ኤል.
(HTML) ሪፖርቶች በመረጃ መረብ መፈለጊያው (በሥርዓቱ የዝርዝር ይዘት ክፍል) ውስጥ ሲቀርቡ ሪፖርቱን በቀላሉ
ለማየትና ለመመርመር ይረዳሉ። የፒ. ዲ. ኤፍ. (PDF) ሪፖርቶች ደግሞ (Adobe Acrobat Reader) የሚባለው
ለህትመት ሥራ የሚያገለግል ሶፍትዌር ውስጥ የሚቀርቡ ናቸው። የኤክሴል ሪፖርቶች (Microsoft Excel) ውስጥ
የሚቀርቡ ናቸው። ሪፖርቶችን በኤክሴል ውስጥ ማቅረብ ከሥርዓቱ ውጪ መደረግ የሚፈለጉትን ለውጦችና
እርማቶች ለመጨመር ይረዳል። ከዚህም በተጨማሪ የኤክሴል ሪፖርቶች ለበጀት ጥራዞችና ለበጀት ማሳወቂያዎች
መደበኛ የሆኑ የሠንጠረዥ አወቃቀሮችን አስተካክሎ ለማተም ይጠቅማሉ። የ. ኤች. ቲ. ኤም. (HTML) ሪፖርቶችንም
ከሥርዓቱ ውስጥ በቀጥታ ማተም ይቻላል።
የሪፖርት አዘገጃጀት
ከዚህ በታች አንድ የአይታፕ ሥርዓት ሪፖርትን እንደምሳሌ በመውሰድ ስለሪፖርቶች አዘገጃጀት አጠር ያለ መግለጫ
ይሰጣል። ሪፖርቱን ለማዘጋጀት፤
2. እንደ ሪፖርቱ ዓይነት መቅረብ ያለባቸው መሥፈርቶች ይለያያሉ። የኤች. ቲ. ኤም. ኤል. (HTML)
ሪፖርት ለማዘጋጀት የኤች. ቲ. ኤም. ኤል. ሪፖርት ትዕዛዝ መስጫውን ይጫኑ። ሪፖርቱ
የዝርዝር ይዘት ክፍል ውስጥ ይቀርባል።
32
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
4. የፒ. ዲ.ኤፍ. (PDF) ሪፖርት ለማዘጋጀት የፒ. ዲ. ኤፍ. ሪፖርት ትዕዛዝ መስጫውን ይጫኑ።
ማቀናበሪያ
ማቀናበሪያ በሚለው ክፍል ሥር በርካታ ተግባራት አሉ፡፡ የሠራተኞቾን የደምወዝ መክፈያ ማቀናበሪያ፣
የድርጅቱ መረጃ፣ ደምወዝ ላይ የሚጣል ግብር ሠንጠረዥ፣ ብድር ፣የደምወዝ መዋቅር፣ የሠራተኞችዎ
የሥራ ኃላፊነት፣ የተለያዩ የክፍያ ዓይነቶችን የምናገኝበት የክፍያ ማጣመሪያ፣ የሥራ ሰዓት መቆጣጠሪያ
ወዘተ……
33
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
34
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ድርጅት
የድርጅቱ መረጃ ለመሙላት በስተግራ በኩል የሚገኘውን ‹‹ድርጅት›› የሚለውን ክፍል ይጫኑ፡፡
35
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ታክሶች
ደምወዝ ላይ የሚጣል ግብር የሚያሳይ ሠንጠረዥ እንዲመጣልዎ በማቀናበሪያ ሥር የሚገኘውን ታክሶች
የሚለውን ክፍል ይጫኑ፡፡ እሱን ሲጫኑ የደምወዝ ሠንጠረዥ ይመጣልዎታል፡፡ መጨመር የሚፈልጉትና
ያልተካተተ የደምወዝ መጠን ካለ ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘ጨምር’ የሚለውን
ትእዛዝመስጫ ከተጫኑ በኋላ የሚመጣልዎትን ቅፅ በመሙላት የደምወዝ መጠኑን ያስገቡ፡፡ አስገብተው
36
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
የደምወዝ መዋቅር
የደምወዝ መዋቅር ለመመዝገብ በስተግራ የሚገኘውን ‹‹የደምወዝ መዋቅር›› የሚለውን ክፍል ይጫኑ፡፡
አዲስ የደምወዝ መዋቅር ማስገባት ከፈለጉ ‹‹አዲስ መዋቅር›› የሚለውን ክፍል ይጫኑ፡፡ ቀጥሎ
የሚመጣውን ቅፅ ከሞሉ በኋላ ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
ሥራን
የሥራ መደብ መጠሪያና ምድብ ለመሙላት አልያም ለማሻሻል ከፈለጉ ‹‹ሥራ›› የሚለውን ክፍል ይጫኑ፡፡
ሥራን ከተጫኑ በኋላ በሚመጣልዎት ሠንጠረዥ ላይ የአንዱን ሠራተኛ ኃላፊነት በመጫን ወደ ዝርዝር
ተግባራት ይግቡ፡፡ ወደ ዝርዝር ተግባራቱ ሲገቡ 4 ተግባራት ይመጡልዎታል፡፡ የሥራ መጠሪያ፣ መግለጫ፣
የሥራው መስፈርቶችና ማረጋገጫ የሚሉ ተግባራት ውስጥ በመግባት የሚያመጣልዎትን ቅፅ ይሙሉ፡፡
ማረጋገጫ ጋር ሲደርሱ ‘አስገባ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የክፍያ ማጣመሪያ
ከሰራተኞች የሚቆረጥ የተለያየ የክፍያ ዓይነት (ተቀናናሾች አይነት )የምናገኝበት ክፍል ነው፡፡
የበዓል ቀናት
የበአል ቀናትን ለመመዝገብ ሲፈልጉ ‹‹የበዓል ቀናት›› የሚለውን ክፍል ይጫናሉ፡፡ የበዓል ቀናቱን
ለመመዝገብ በስክሪንዎ በስተቀኝ በኩል የሚገኝውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘ጨምር’
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ሲጫኑ በሚመጣልዎት ቅፅ ላይ የበዓሉን ስም እና በዓሉ የሚውልበትን ቀን
ይመዝግቡ፡፡ መዝግበው ሲጨርሱም ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
37
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
የጊዜ ወሰን
የትርፍ ሰአት ክፍያዎችንና የመደበኛ ስራ ክፍያዎችን መሙላት ሲፈልጉ ወደ ‹‹የጊዜ ወሰን›› ክፍል ያመራሉ፡፡
በቅፁ ላይ አዲስ መጨመር የሚፈልጉት የክፍያ አይነት ካለ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘አዲስ ጨምር’
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
ፈረቃ
በመ/ቤትዎ በፈረቃ የሚሰራ ከሆነና የፈረቃ ሰአት ድልድል ማድረግ ሲፈልጉ ‹‹ፈረቃ›› የሚለውን ክፍል
ይጫናሉ፡፡ በሚመጣልዎት ቅፅ ላይ ያልተካተተ የፈረቃ ሰአት ካለና ለመጨመር ከፈለጉ በስተቀኝ በኩል
የሚገኘውን ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ አዲስ ጨምር የሚለውን ትእዛዝ መስጫ
ከተጫኑ በኋላ በሚመጣልዎት ቅፅ ላይ አዲስ ፈረቃዎችን መጨመር ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቅፅ ላይ ‹‹የጊዜ
ክፍሎች›› የሚል ክፍል አለ፡፡ አዲስ የጊዜ ክፍል መጨመር ከፈለጉ ከቅፁ ታች ያለውን ‹‹አዲስ የጊዜ ክፍል
ጨምር›› የሚለውን በመጫን ቀጥሎ የሚመጣልዎትን ቅፅ ይሙሉ፡፡ ሞልተው ሲጨርሱ ‘ጨምር’
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ በስተመጨረሻም ወደ ፈረቃ ወደ ሚለው ገፅ በመመለስ ‘መዝግብ’
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
መርሃ ግብር
የስራ መርሃ ግብር የሚያሰፍሩበት ክፍል ነው፡፡ አዲስ መመዝገብ የሚፈልጉት መርሃ ግብር ሲኖር በስተቀኝ
በኩል የሚገኘውን ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ትእዛዝ መስጫውን እንደተጫኑ
በሚያመጣልዎት ቅፅ ላይ ‹‹የመርሃ ግብሩን ስም›› ‘ስም’ በሚለው ቦታ ላይ ያስፍሩ:: በተጨማሪነትም
‘አይነት’ በሚለው ቦታ ላይ የመርሃ ግብሩን አይነት ይምረጡ፡፡ በማስከተልም ‘ዙር’ በሚለው ቦታ ላይ
የዙሩን ብዛት ይሙሉ፡፡ እሱን ሞልተው እንዳጠናቀቁ ከሥሩ በሚገኘው ቅፅ ላይ የሚፈልጉትን የመርሃ
ግብር ድልደላ በሚፈልጉት መልኩ መሙላት ይችላሉ፡፡ ቅፁን ሞልተው እንዳጠናቀቁ ከስር የሚገኘውን
‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የትርፍ ሰአት ሥራ
የሠራተኞቾን የትርፍ ሰአት ክፍያ ለመቆጣጠር ‹‹የትርፍ ሰአት ሥራ›› የሚለውን ክፍል ይጫኑ፡፡ የትርፍ
ሰአት ሥራ ክፍያን ለመመዝገብ ወይም ለመጨመር በቅፁ በስተቀኝ በኩል ያለውን ‘አዲስ ጨምር’
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ እሱን ሲጫኑ በሚመጣልዎት ቅፅ ሞልተው ‘መዝግብ’ እና ‘ዝጋ’ የሚሉ
ትእዛዝ መስጫዎችን ይጫኑ፡፡
አማራጮች
አማራጮች በሚለው ክፍል ሥር የተለያዩ ዝርዝሮችን ያገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መሐል የፍቃድ አይነት፣ የጥቅማ
ጥቅም አይነት፣ የተቀናሽ መለኪያ አይነት፣ ዝምድና፣ የስልጠና ትምሕርት፣ የትምሕርት ደረጃ፣ የስራ ምድብ፣
የድርጅቱ መዋቅር አይነት፣ የማሰናበቻ ምክንያት፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ የሙያ አይነትና የብሔር አይነት
ይገኙበታል፡፡ ሁሉንም አንድ በአንድ እናያቸዋለን፡፡
የፍቃድ አይነት
የተለያዩ የፍቃድ አይነቶች የተዘረዘሩበት ቅፅ ነው፡፡ በቅፁ ላይ ያልተሞላ የፍቃድ አይነት ካለ በስተቀኝ
በኩል የሚገኘውን ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ
መስጫ ሲጫኑ የሚመጣልዎትን ቅፅ ይሙሉና ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
ጥቅማ ጥቅሞ
ሠራተኞችዎ የሚያገኙት ጥቅማ ጥቅም የሚዘረዘሩበት ክፍል ነው፡፡ ያልመዘገቡትን ጥቅማ ጥቅም
ለማስገባት ሲፈልጉ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘አዲስ ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘አዲስ
ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ከተጫኑት በኋላ የሚያመጣልዎትን ቅፅ ይሙሉና ‘መዝግብ‘ የሚለውን
ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የተቀናሽ መለኪያ አይነት
ሠራተኞችዎ ያለባቸውን የተለያዩ ተቀናሾችን የሚመዘግቡበት ክፍል ነው፡፡ ያልመዘገቡትን ጥቅማ ጥቅም
ለማስገባት ሲፈልጉ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ በማስከተል
በሚመጣው ቅፅ ላይ የሠራተኛውን ስም በማስገባት ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
38
ዝ ር ዝ ር መ ግ ለ ጫ
ዝምድና
የሠራተኛዎን በአደጋ ጊዜ ተጠሪ የሆነ የቅርብ ሰው የሚያሰፍሩበት ክፍል ነው፡፡ በዚህ ክፍል ላይ መጨመር
የሚፈልጉት የዝምድና አይነት ሲኖር በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ
ይጫኑ፡፡ በማስከተል በሚመጣው ቅፅ ላይ ስም በሚለው ቦታ የሚፈልጉትን የዝምድና አይነት በማስገባት
‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የትምሕርት ደረጃ
የሠራተኛዎን የትምሕርት ደረጃ የሚያሰፍሩበት ክፍል ነው፡፡ የሠራተኞችዎን የትምሕርት ደረጃ መጨመር
ሲፈልጉ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ በማስከተል በሚመጣው
ቅፅ ላይ ‘ስም’ በሚለው ቦታ የሚፈልጉትን የትምሕርት ደረጃ በማስገባት
‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የስራ ምድብ
የሠራተኛዎ ወይም የሠራተኞችዎን የሥራ መደብ የሚያሰፍሩበት ክፍል ነው፡፡ በቅፁ ላይ ያልመዘገቡት
ሠራተኛ ስም ካለ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘ጨምር’
የሚለውን ትእዛዝ ከተጫኑ በኋላ በሚያመጣልዎት ቅፅ ላይ የሠራተኛዎን ስም ካስገቡ በኋላ መዝግብ
የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የማሰናበቻ ምክንያት
በድርጅትዎ ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞችዎን ማሰናበት ሲፈልጉ የሚያሰናብቱባቸውን ምክንያቶች
የሚመዘግቡበት ክፍል ነው፡፡ በቅፆ ላይ ያልመዘገቡት ምክንያት ካለና መመዝገብ ከፈለጉ በስተቀኝ በኩል
የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ከተጫኑ
በኋላ በሚመጣልዎት ቅፅ ላይ የስሙን አይነት ያስገቡና ‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
የጋብቻ ሁኔታ
የሠራተኞችዎን የጋብቻ ሁኔታ የሚመዘግቡበት ክፍል ነው፡፡
የሙያ አይነት
የሠራተኞችዎን የሙያ አይነት የሚመዘግቡበት ክፍል ነው፡፡ አዲስ የሙያ አይነት መመዝገብ ሲፈልጉ
በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ በማስከተል በሚያመጣልዎት ቅፅ
ላይ ስም በሚለው ቦታ ላይ ማስገባት የሚፈልጉትን የሙያ አይነት ካስገቡ በኋላ ‘መዝግብ’ የሚለውን
ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
ብሔር
የሠራተኞችዎን የብሔር አይነት የሚመዘግቡበት ክፍል ነው፡፡ ያልመዘገቡት ብሔር አይነት ካለና መመዝገብ
ሲፈልጉ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን ‘ጨምር’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡ በማስከተል
በሚያመጣልዎት ቅፅ ላይ ስም በሚለው ቦታ ላይ ማስገባት የሚፈልጉትን የብሔር አይነት ካስገቡ በኋላ
‘መዝግብ’ የሚለውን ትእዛዝ መስጫ ይጫኑ፡፡
39