Professional Documents
Culture Documents
Translation 2011 3
Translation 2011 3
እዚህ እንዲታወቅ የሚፈለገው ነገር አቶ ኃይለ ማርያም ፍቃዴ (ከዚህ በኋላ "ውል ተቀባይ" ተብሎ በሚጠራው) በአንድ ወገንና
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ባሕር ዳር ቅርንጫፍ (ከዚህ በኋላ "ዋስትና ሰጭ" ተብሎ በሚጠራው) በሌላ ወገን ለሊቦ
ከምከም ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት (ከዚህ በኋላ "ቀጣሪው" ተብሎ ለሚጠራው) በአንድነትም ሆነ በተናጠል
የገንዘብ መጠኑ ብር 268,000 (ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ብር) እንደ አቅራቢና እንደ ዋስትና ሰጪ ክፍያውን ሊፈጽሙ ውል
መግባታቸውን ነው፡፡
ስለዚህ ተቋራጩ ለቀጣሪው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ለሊቦ ከምከም ወረዳ ሊያቀርብ ታህሳስ 25/2011 ዓ.ም. የጽሑፍ ውል
የያዘ ሲሆን ለዚህም ሥራ ቀጣሪው ለውል ተቀባዩ ብር 268,000 (ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ብር) ለመክፈል የተስማማ
ሲሆን ክፍያውን የሚፈጽመው ግን ውል ተቀባዩ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ያለው የቅድመ ክፍያ ዋስትና ውል ይህን የዋስትና
ውል ተቀባይነት እንዳያገኝ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች በስተቀር ሁሉም ስምምነቶችና ሁኔታዎች አባሪ በሆኑበት ሁኔታ ሲያቀርብ
ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም የዚህ ዋስትና ውል ተፈጻሚነት ከታህሳስ 25/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 30 ቀናት የጸና ይሆናል፡፡
ስለዚህ የቀደመው ግዴታ ሁኔታዎች በሙሉ የሚመለከቱት ውል ተቀባዩ ለተጠቀሰው የብር 268,000 (ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት
ሺ ብር) ቅድመ ክፍያ ውል ደንቦች፣ ስምምነቶችና ሁኔታዎች በቅድመ ክፍያ ስምምነቱ መሠረት በአግባቡ በእውነተኛነትና በቅን
ልቦና ተገዥ እንዲሆን ማድረግ ሲሆን ውል ተቀባዩ ግዴታውን መወጣት ካልቻለ ግን ዋስትና ሰጭው ቀጣሪው በውሉ
የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን እስከሚሟላ ድረስ የሚጠይቀውን ገንዘብ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ዋስትና ሰጭው ክፍያውን በውሉ
እስከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ድረስ ሲፈጽም ውሉ ውድቅ የሚደረግ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ውሉ በጽናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
ይህ የዋስትና ውል በዋስትና ሰጭው የተፈጸመው የቀጣሪውን መብት ሙሉ ለሙሉ ለማስጠበቅ ሲሆን የሚከተሉት ግልጽ
ሁኔታዎች አሉት፡-
ቅደመ ሁኔታዎች
1. ይህ የዋስትና ውል ዋና ቅጅ የውሉ ጊዜ ሲያበቃ ለዋስትና ሰጭው ይመለሳል፡፡ ዋስትና ሰጭው ውሉ ከሚያበቃበት ቀን
በፊትም ሆነ በውሉ ማብቂያ ጊዜ ውስጥ የይገባኛል ጥያቄ ከቀጣሪው ካልደረሰው በስተቀር ይህ ውል ለዋስትና ሰጭው
ቢመለስም ባይመለስም ውድቅ ይሆናል፡፡
2. ቀጣሪው ወይም የቀጣሪው እንደራሴም ሆነ ተወካይ ኪሣራ የሚያስከትል ድርጊት ወይም ስህተት ካገኙ ቀጣሪው
ወዲያውኑ ሙሉ መረጃ የያዘ የጽሑፍ መግለጫ ለዋስትና ሰጭው ዋና ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡
3. የዚህ ውል ደንቦች የሚጣሱ ከሆነ ከውሉ የሚመነጩ የውል ተቀባዩን መብቶችና ንብረቶች ዋስትና ሰጭው ይቀዳጃል፡፡
ለዚህም ምሥክርነት ውል ተቀባዩና ዋስትና ሰጭው ይህን የዋስትና ውል በታህሳስ 24/2011 ዓ.ም. ተፈራርመዋል፡፡
ባለ 5 ብር የቀረጥ
ቴምብር አለበት
ስለትርጉሙ ትክክለኛነት