You are on page 1of 8

ጠቅላላ

1.1 አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የስራ ተያዥ ማቅረብ ለሚያስፈልጋቸው የመንግሥት ሠራተኞች የወጣ አፈጻጸም


መመሪያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1.2 ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1.2.1 “የመንግስት ሠራተኛ” ማለት በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ
የሚሰራና የመንግሥትን ገንዘብና ንብረት በአደራ ተረክቦ የሚያንቀሣቅስ ነው፡፡

1.2.2 “የመንግሥት መ/ቤት” ማለት በየትኛውም የአስተዳደር እርከን ራሱን ችሎ በአዋጅ ወይም
በደንብ የተቋቋመ እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከመንግስት በሚመደብለት በጀት
የሚተዳደር መ/ቤት ነው፡፡

1.2.3 “ውል ሰጭ” ማለት በየደረጃው የሚገኝ መስሪያቤት ነው፡፡

1.2.4 “ውል ተቀባይ” ማለት በውል ሰጭው መስሪያቤት በዋስትና ግዴታ መቀበያ ሰነድ መሰረት
ስምምነት የሚወስድ ማለት ነው፡፡

1.2.5 “ዋስ/ተያዥ” ማለት ውል ተቀባይ ሠራተኛ በውል ውስጥ በገባው ግዴታ መሠረት
ሳይፈጽም ቢቀር ወይም አፍርሶ ቢገኝ እርሱን ተክቶ እንደውለታው ግዴታውን ለመፈፀም
የሚገደድ አካል ነው፡፡

1.2.6 “የዋስትና መቀበያ ሰነድ” ማለት በውል ሰጭ መ/ቤት እና ውል ተቀባይ ሠራተኛ መካከል
የሚደረገው ውል አንድ አካል ሆኖ ውል ተቀባይ ሠራተኛ በገባው ውል መሠረት ግዴታውን
በአግባቡ ሳይፈጽም ቢቀር ዋሶች በተናጠል ወይም በጋራ ዋስ የሆኑበትን የገንዘብ መጠን
ለውል ሰጭ መ/ቤት ገቢ ለማድረግ ተስማምተው የሚፈርሙበት ቅጽ ነው፡፡

1.2.7 “የጋራ ዋስ” ማለት አንድ ሠራተኛ ለሚረከበው ንብረት ወይም ለሚያንቀሳቅሰው ንብረት
እንደ መያዣ የሚያገለግሉና ለሚጠፋውም ጥፋት በጋራ የሚጠየቁ የግለሰቦች ስብስብ
ማለት ነው፡፡

1
1.2.8 “የተናጠል ዋስ” ማለት አንድ ሠራተኛ ከገንዘብና ንብረት ጋር ተያያዥነት ባላቸው የስራ
መደቦች ላይ ለሚረከበው ንብረት ወይም ለሚያንቀሳቅሰው ገንዘብ እንደመያዣ
የሚያቀርበውና በሠራተኛው የስራ አጋጣሚ ለሚፈጠር የገንዘብና የንብረት መጥፋት
ራሱን ችሎ የሚጠየቅ ማለት ነው፡፡

1.3 መመሪያው ተፈፃሚ የሚሆንባቸው አካላት

1.3.1 ይህ መመሪያ ተፈፃሚ የሚሆነው በክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ በሚተዳደሩ


መስሪያቤቶች ውስጥ በገንዘብ ያዥ፣ በዕለት ገንዘብ ተቀባይ፣ በንብረት ኦፊሰር፣
በአሽከርካሪ/መኪናና ሞተር/፣ በእቃ ግዥ ኦፊሰር፣ በጥበቃ ሰራተኛ፣ በቅየሳ ሰራተኝነት፣
በቤተመጽሃፍት ሰራተኝነት፣ በፋርማሲስትነት፣ በላቦራቶሪ ቴክኒሽያንነት እና በወርክሾፕ
ቴክኒሻንነት የስራ መደቦች ላይ ተመድበው እየሰሩ ባሉና ወደፊትም በእነዚህ የስራ መደቦች
ላይ በሚመደቡ ሰራተኞች ላይ ነው፡፡

1.3.2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1.3.1 ላይ ከተገለጹት የስራ መደቦች ውጭ ሆነው ከንብረትና
ከገንዘብ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች የስራ መደቦች ሲያጋጥሙ በመስሪያቤቱ የማኔጅመንት
አካል ውሳኔ ዋስትና እንዲገቡ ማድረግ ይቻላል፡፡ የሚገቡት የዋስትና መጠንም በማኔጅመንቱ
ውሳኔ ከላይ ለተዘረዘሩት የስራ መደቦች ከተገለጸው የአንዱን መውሰድ ይቻላል፡፡

ክፍል ሁለት
ሠራተኞች ዋስትና ስለሚያቀርቡበት ሁኔታ
2.1 የንብረት ኦፊሰሮች ፣ ፋርማሲስቶች፣ ላቦራቶሪ ቴክኒሽያኖች እና ወርክሾፕ ቴክኒሽያኖች

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በንብረት ኦፊሰርነት፣ በፋርማሲስትነት፣


በላቦራቶሪ ቴክኒሽያንነት እና በወርክሾፕ ቴክኒሽያንነት የስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ
የሚሰራ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ለሚረከበው ንብረት ለብር 55 ዐዐዐ (ሀምሳ አምስት

2
ሸህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 801 (ስምንት መቶ አንድ) እና በላይ
የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 1068 (አንድ ሽህ ስልሳ ስምንት) እና በላይ የሆ
1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 55 ዐዐዐ (ሀምሳ አምስት ሸህ) (ሀምሳ አምስት ሸህ) የሆነ ቋሚ
ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስነት ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር 55 ዐዐዐ
(ሀምሳ አምስት ሸህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስነት
ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.2 ገንዘብ ያዦች እና የዕለት ገንዘብ ተቀባዮች


በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በገንዘብ ያዥነት እና በዕለት ገንዘብ
ተቀባይነት የስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ የሚሠራ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ
ለሚረከበው ገንዘብ ለብር 8 ዐዐዐዐ (ሰማንያ ሽህ ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር
ደመወዝ ብር 1068 ( አንድ ሽህ ስልሳ ስምንት) እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር
ደመወዙ ብር 1410 (አንድ ሽህ አራት መቶ አስር) እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ
ብር 80000 (ሰማንያ ሽህ ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/
አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር 80000 (ሰማንያ ሽህ ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት
የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.3 የእቃ ግዥ ኦፊሰሮች

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በእቃ ግዥ ኦፊሰርነት ተቀጥሮ ወይም
ተመድቦ የሚሠራ ሠራተኛ ለብር 6 ዐዐዐዐ (ስልሳ ሽህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር
ደመወዝ ብር 928 (ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት) እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር
ደመወዙ ብር 1228 ( አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሀያ ስምንት) እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም
ግምቱ ብር 60000 (ስልሳ ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/
አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር 60000 (ስልሳ ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ
ግለሰብ በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.4 አሽከርካሪዎች (ለመኪና ብቻ)

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በአሽከርካሪነት የስራ መደብ ላይ


ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ የሚሠራ ማንኛውም አሽከርካሪ በስሙ ለተረከበው ተሽከርካሪ ለብር
6 ዐዐዐዐ (ስልሳ ሽህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 928 (ዘጠኝ መቶ ሀያ
ስምንት) እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 1228 ( አንድ ሽህ ሁለት

3
መቶ ሀያ ስምንት) እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 60000 (ስልሳ ሽህ) የሆነ
ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር 60000
(ስልሳ ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስትና
ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.5 የጥበቃ ሠራተኞች እና ሞተረኞች


በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በጥበቃ ሠራተኝነት እና በሞተረኝነት
ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ የሚሠራ ሠራተኛ ለብር 15 ዐዐዐ (አስራ አምስት ሽህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ
የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 595 (አምስት መቶ ዘጠና አምስት) እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ
ሠራተኞች ወይም የወር ደመወዙ ብር 801( ስምንት መቶ አንድ) እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ
ወይም ግምቱ ብር 15 ዐዐዐ (አስራ አምስት ሽህ) በላይ የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት
በዋስትና ማቅረብ /ማስያዝ/ አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር 15000 (አስራ አምስት ሽህ) የሆነ ቋሚ
ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.6 የቤተመፃህፍት ሠራተኞች

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤቶች ውስጥ በቤተ መፃህፍት ሠራተኝነት የስራ
መደብ ላይ ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ የሚሠራ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ለሚረከበው
ንብረት ለብር 1 ዐዐዐዐ (አስር ሽህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር ደመወዝ ብር 441 (
አራት መቶ አርባ አንድ ብር) እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞችን ይህ ካልሆነ የወር ደመወዙ ብር
692 ( ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት) የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም ግምቱ ብር 1 ዐዐዐዐ (አስር ሽህ)
የሆነ የቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር
10000 (አስር ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስትና
ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

2.7 ቀያሾች

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መ/ቤት ውስጥ በቀያሽነት ተቀጥሮ ወይም ተመድቦ
የሚሠራ ሠራተኛ ለብር 45 ዐዐዐ (አርባ አምስት ሽህ) የጋራ ዋስ የሚሆኑ የእያንዳንዳቸው የወር
ደመወዝ ብር 928 (ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት) እና በላይ የሆኑ 2 ቋሚ ሠራተኞች ወይም የወር

4
ደመወዙ ብር 1228 ( አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሀያ ስምንት) እና በላይ የሆነ 1 ቋሚ ሠራተኛ ወይም
ግምቱ ብር 45000 (አርባ አምስት ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት በዋስትና
ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡ ወይም ግምቱ ብር 45000 (አርባ አምስት ሽህ) የሆነ ቋሚ ወይም
ተንቀሳቃሽ ንብረት የሚያቀርብ ግለሰብ በዋስትና ማቅረብ/ማስያዝ/ አለበት፡፡

ክፍል ሦስት

የውል ሰጭ መስሪያቤት እና የዋሶች ግዴታ

3.1 የውል ሰጭ መ/ቤት ግዴታ

3.1.1 በዋስትና መቀበያ ሠነድ /ቅጽ/ ላይ የቀረቡት ዋሶች ውል ሰጭና ተቀባይ ባለበት በውዴታ
እንዲፈርሙ ማድረግ አለበት፡፡

3.1.2 የዋስትና መቀበያ ሰነዱ ከመፈረሙ በፊት ዋሶች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች
ማሟላታቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡

3.1.3 ሠራተኛው በስሙ የተረከበውን ገንዘብ ወይም ንብረት ያጠፋ ወይም ይዞ የተሰወረ እንደሆነ
ቀጣሪው መ/ቤት ሁኔታውን እንዳወቀ ወዲያውን ለዋሶች የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

3.1.4 ዋሶች ሠራተኛው ያጠፋውን ሀብትና ንብረት በጋራ ወይም በተናጠል በስምምነታቸው
መሠረት ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርጉ ጠይቆ ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ
መረጃዎችን በማጠናቀር ለፍትህ አካል ያቀርባል፡፡

3.1.5 ዋስትና በሚጠይቅ መደብ ላይ የነበረ ሠራተኛ መደቡን ሲቀይር ለተያዡ /ለዋሱ በመ/ቤቱ
በኩል እንዲያውቀው ማድረግ አለበት፡፡

5
3.2 የዋሶች ግዴታ

3.2.1 ዋስ ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በውል ሰጭ/በቀጣሪ መ/ቤት/ በኩል የተዘጋጀውን
የዋስትና መቀበያ ሰነድ /ቅጽ/ ውል ተቀባይና ውል ሰጭ ባሉበት በሙሉ ፍቃደኝነት
የመፈረም ግዴታ አለባቸው፡፡

3.2.2 ውል ተቀባይ በስራው አጋጣሚ በእጁ የሚገባውን ንብረትም ሆነ ገንዘብ ሆን ብሎም ይሁን
በስራው አጋጣሚ ቢጠፋበት ወይም ይዞ ቢሰወር ዋሶች ዋስ የሆኑበትን የገንዘብ መጠን
በጋራ ወይም በተናጠል ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

3.2.3 ዋሶች ዋስ ስለሆኑት ሠራተኛ በየጊዜው እየተከታተሉና የተለየ ሁኔታ በሚኖርበት ወቅትም
ለቀጣሪው /ውል ሰጭ/ መ/ቤት የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

3.2.4 ማንኛውም ዋስ መሆን የሚችል ሰው በህግ እገዳ ያልተጣለበትና የአእምሮ ችግር


የሌለበትና በራሱ አመዛዝኖ መወሰን የሚችል መሆን አለበት፣

3.2.5 ዋስ የሚሆነው ሰው የመንግስት ሠራተኛ ከሆነ ቋሚ የሆነና ጡረታ ለመውጣት 5 ዓመት


የቀረው መሆን አለበት፡፡

3.2.6 ዋስ የሚሆነው ሰው የመንግስት ሠራተኛ ከሆነ ደመወዙ በማንኛውም የዋስትና እዳ


ያልተያዘ መሆኑን ከሚሰራበት መ/ቤት የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡

3.2.7 ለዋስትና የሚቀርበው ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ንብረት ከማንኛውም እዳ ነፃ መሆኑን በህግ


ስልጣን በተሰጠው አካል በጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡

3.2.8 ማንኛውም ግለሰብ/የመንግሥት ሠራተኛ ለትዳር ጓደኛው/ዋ ዋስ ሆኖ መቅረብ


አይችልም፡፡

3.2.9 ለውል ተቀባይ አካል ዋስ ሆነው የሚቀርቡ ግለሰቦች ባለትዳር ከሆነ ባለቤቶቻቸው አብረው
እንዲፈርሙ ይደረጋል

6
ክፍል አራት

ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች

4.1 ለአንድ ሰው ዋስ የሆነ ግለሰብ ዋስትናውን እስካላነሳ ድረስ ለሌላ ሰው ዋስ መሆን አይችልም

4.2 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ ሠራተኞች ሌሎች ዋስትና
በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው ለሚሰሩ ሠራተኞች ዋስ መሆን አይችሉም፡፡

4.3 ውል ተቀባይ ተያዥ ያቀረበበትን የስራ መደብ ለቆ ተያዥ ወደ ሚጠይቅ ሌላ የስራ መደብ
ከተዛወረ ውሉን እንደገና ማደስ ይጠበቅበታል፡፡ይህን ካላደረገ ግን የመጀመሪያው ተያዥ በአዲሱ
የስራ መደብ ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጥፋት ሀላፊነት አይወስድም፡፡

4.4 ዋስ አቅርበው እየሰሩ የሚገኙ ሠራተኞች ከዋሶች መካከል አንደኛው ወይም ሁለቱም
ዋስትናቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ቢያወርዱ ሰራተኞች በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ
ውስጥ ምትክ ዋስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.5 ማንኛውም ዋስ የሆነ ግለሰብ ዋስትናውን በማንኛውም ጊዜ የማንሳት መብት አለው፡፡ ነገር ግን
ዋስትናውን አስካወረደበት ጊዜ ድረስ ለሚኖር ጉድለት ተጠያቂ ነው፡፡

4.6 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ ሠራተኞችም ሆነ ወደፊት


የሚመደቡ ሠራተኞች በእጃቸው ለገባው የመንግሥት ሀብትና ንብረት ተያዥ ማቅረብ ካልቻሉ
እንዲሰናበቱ ይደረጋል፡፡

4.7 ዋስትና በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ በቅጥርም ሆነ በዝውውር ሠራተኞችን አወዳድሮ


መመደብ ሲያስፈልግ የሚገቡት የዋስትና ግዴታ በሚወጣው ማስታወቂያ ላይ መገለጽ
ይኖርበታል፡፡

4.8 ይህ መመሪያ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እየተገናዘበ እንደአስፈላጊነቱ በአቅም ግንባታና ሲቪል
ሰርቪስ ቢሮ ሊሻሻል ይችላል፡፡

7
4.9 ይህ መመሪያ ጸድቆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

You might also like