Professional Documents
Culture Documents
New
New
ሰኔ 2013 ዓ.ም
ማዉጫ
መግቢያ
ምዕራፍ 1. የዉርስ ህግ በጠቅላላዉና የአወራረስ ሥርዓት በኢትዮጵያ
1.1 ስለዉርስ ህግ በጠቅላላዉ
1.2 የዉርስ ህግ መሰረታዊ ዓላማ
ምዕራፍ 2. የኢትዮጵያ የዉርስ አስተላለፍ ሥርዓት በጠቅላላዉ
2.2.1 ዉርስ የሚከፈትበት ጊዜና ስፍራ
2.2.2 የች ዉርስ አከፋፈት በህግ መወሰኑ አስፈላጊነት
2.4 ለመዉረስ የሚያስፈልግ ችሎታ
የቀጠለ…
3.1 ጠቅላላ
3.2 ያለኑዛዜ ዉርስ /ፍ/ህ/ቁ. 842-856
3.3 የኑዛዜ ዉርስ
3.3.1 የኑዛዜ ዓይነቶች
3.3.1.1 በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ /የፍ/ህ/ቁ.881
3.3.1.2 በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ /ፍ/ህ/ቁ. 884- 891/
3.3.1.3 በቃል የሚደረግ ኑዛዜ /ፍ/ህ/ቁ. 892-894/
3.4 የኑዛዜ መሻር
3.5 የኑዛዜ ዉድቅ መሆን
3.6 ኑዛዜ መኖሩን ስለማስረዳት
ምዕራፍ 4 ዉርስ ማጣራትና ዉርስን ማስተዳደር
4.1 የዉርስ አጣሪዎች ግዴታዎችና ኃላፊነቶች
4.2 ከዉርስ ማጣራት ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮች
ምዕራፍ 5 የዉርስ ይርጋ
5.1 ይርጋ ለምን አስፈለገ?
5.2 ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ መቆጠር አጀማመር
5.3 የይርጋ መረጥ
5.4 ከዉርስ ሀብት ጋር የተያያዙ የይርጋ ገደቦች
5.5 ስለዉርስ የተደነገጉ የይርጋ ገደቦች የዉይይት ሀሳቦች
የቀጠለ…
መግቢያ
የሰው ልጅ ወደዚች ምድር ከተቀላቀለበት እለት አንስቶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ መብቶችና
ግዴታዎች አሉት፡፡ ለምሳሌ የመኖር መብት፣ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት፣ ሀሳብን የመግለፅ
፣መልካም ስም የመቀጠል፣ ች ንብረቱን በተመለከተ የገለፃቸዉ ሀሳቦች፣ ከግዴታዎቹ መካከል
ደግሞ የፍትሀብሄር ዕዳ የመክፈል ግዴታ ወዘተ…
ስለ ዉርስ ሲናነሳ ዉርስ በባህሪይዉ ሁለት ዓበይት ጉዳዮችን ያቅፋል፡፡ ሞትና ሀብት ናቸዉ፡፡ ሁለቱ
በሌሉበት ዉርስ አይኖርም፡፡
ሞት የሰዉን ልጅ ተፈጥሮአዊ ሰዉነት (personality) የሚያስቀር ወሳኝ ኩነት ነዉ፡፡ ሰዉነት ከሌለ
መብቶች ማረፊያ ያጣሉ፡፡
የቀጠለ…
የሟች ንብረት እንዲሁም መብትና ግዴታዎቹ በውርስ ሕግ መሠረት ለወራሾች
የሚተላለፉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ መልካም ስም የመቀጠል፣ ች ንብረቱን በተመለከተ
የገለፃቸዉ ሀሳቦች፣የፍትሀብሄር ዕዳ የመክፈል ግዴታ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ
አጠቃላይ ደንብ ነው፡፡
ነገር ግን ሁሉም መብትና ግዴታዎች ሊወረሱ ወይም ለወራሾች ሊተላለፉ አይችሉም፡፡
ለምሳሌ በሞት ምክንያት ቀሪ የሚሆኑ መብቶችና ግዴታዎች መካከል የመኖር
መብት፣ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት ሀሳብን የመግለፅ መብት እና ሌሎችም
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ መብቶች በባህሪያቸዉ ግለሰባዊ በመሆናቸዉ ለሌሎች
የማይተላለፉ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም በች ሞት ምክንያት ቀሪ የማይሆኑና ማረፊያ ያጡት መብቶች በሙሉ
ከች ሰዉነት ተነስተዉ ች ትቶት ባለፈዉ ሀብት ላይ ያርፋሉ፡፡
የቀጠለ…
በህብረተሱ ዉስጥ ለዘመናት የሰፈነዉ ፍላጎት የች ሀብት ከሥጋ ዝምድና
ሳይወጣ ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረግ ነዉ፡፡
የዉርስ ህግ የች ሀብት በህይወት ላሉ ሰዎች የሚተላለፍበት መመሪያ ሲሆን
ዝርዝር ሁኔታዉ ግን ከሀገር የሚለያይበት ሁኔታ ይኖራል፡፡
በኢትዮጵያ የዉርስ አወራረስ ስርዓት ሲናነሳ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 34 (5) አብሮ
ይነሳል፡፡ ይህም የግልና የቤተሰብ ህግን በተመለከተ በተከራካሪዎች ሙሉ ፈቃድ
በመረጡት የአወራረስ ደንብ መዳኘት እንደሚችሉ መብት ያጎናፅፋቸዋል፡፡ በህገ
መንግስቱ አንቀፅ 78 (5) ህገ መንግስቱ ከመፅደቁ በፊት ዕዉቅና አግኝተዉ
ሲሰራባቸዉ የነበሩ የሃይማኖትና የባህል ፍርድ ቤቶች ዕዉቅና በማግኘታቸዉ
በአዋጅ ቁጥር 188/1992 በፌዴራል የሸርያ ፍርድ ቤት የተመ ሲሆን በዚሁ
መሰረት በደቡብ ክልልም ተል፡፡
በኢትዮጵያ 3 ዓይነት አወራረስ ዓይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም 1ኛ ባህላዊና ልማዳዊ
2ኛ ሀይማኖታዊ 3ኛ በፍትሀብሄር ህጉ የተመለከቱ የተለያዩ ባህሪይና ዉጤት
ያላቸዉ የአወራረስ ስርዓቶች ተግባራዊ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
የቀጠለ…
በዚህ ላይ ለምሳሌ የፌዴሬሽን ም/ቤት ዉሳኔ የሰጠበት የወ/ሮ ከድጃ በሽር ጉዳይ ነዉ፡፡
በዚህ ጉዳይ ወ/ሮ ከድጃ በሽር በሸርያ ፍርድ ቤት የች የአቶ ሰማን አበጋዝ ህጋዊ ምስት
ስለመሆ የምስክር ወረቀት ከተቀበለች በላ ይህንን ማስረጃ በማያያዝ የች ወራሾች
የሚስትነት ንብረት ድርሻዋን እንዲያካፍሉ በመደበኛ ፍርድ ቤት ክርክር ትጀምራለች፡፡
በዚህን ጊዜ የች ወራሾች ከሳሽ የሚስትነት ማስረጃ ከሸሪያ ፍርድ ቤት ያወጣች
መሆኑን በመጥቀስ ጉዳዩ መታየት ያለበት በሸሪያ ፍርድ ቤት ነዉ ሲሉ ተከራከሩ፡፡
የወረዳዉ ፍርድ ቤት ከሳሽ በሸሪያ ፍርድ ቤት ክስ መቀጠል እንዳለባት በመጥቀስ የንብረት
ድርሻ ክስ ዉድቅ ያደርግባታል፡፡ በይግባኝ ሰሚዉና በሰበር በመፅናቱ ጉዳዩ ለፌዴሬሽን
ም/ቤት ቀርቦ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 34(5) እና የፌዴራል ሸሪያ ፍርድ ቤቶችን አም
ለማጠናከር የወጣ አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀፅ 4(2) በመጥቀስ ሙሉ ፈቃድ
ባልሰጠችበት በሸሪያ ፍርድ ቤት እንዲትዳኝ መወሰኑ የህገ መንግስታዊ ድንጋጌ ጥሰት ነዉ
ሲል ህገ መንግስታዊ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
በዚህ ስልጠና በፍትሀብሄር ህጉና ተያያዥነት ባላቸዉ በሌሎች ህጎች የተመለከቱ የዉርስ
ህግ ድንጋጌዎችን በሰባት ምዕራፎች ከፍለን እንመከታለን፡፡
ምዕራፍ 1 የዉርስ ህግ በጠቅላላዉና የአወራረስ ሥርዓት
በኢትዮጵያ
ዉርስ ምንድነዉ?
ለዉርስ አንድ ወጥ ትርጉም መሰጠት ያስቸግራል
ዉርስ አንድ ሰዉ ትቶት የሞተዉ ሀብት እና ዕዳ ነዉ፡፡
ዉርስ በህይወት ያሉ ሰዎች ከች ሀብት ላይ ሊደርሰን ይገባል የሚሉት ንብረት
ነዉ፡፡
ውርስ ምንድን ነው የሚለውን ትርጉም በሃገራችን የውርስ ሕግ ውስጥ በቀጥታ
ተተርጉሞ ባናገኘም ከሕጉ ጠቅላላ መንፈስ ግን ትርጉሙን መረዳት እንችላለን፡፡
ይህም ውርስ ማለት የአንድ በሞት የተለየን ሰው ንብረት እና ኃብት እንዲሁም
ሊተላለፍ የሚችሉ መብት እና ግዴታዎች በሕይወት ላሉ አንድ እና ከዚያ በላይ
ለሆኑ ሰዎች የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡
የቀጠለ…
እዉቁ የህግ መዝገበ ቃላት Black's Law Dictionary “succession is the transmission
of the rights and obligations of the des eased to the heirs, also the estates,
right and charges which a person leaves after his death” በማለት ይገልፀዋል፡፡
የቃሉ ትርጉም በግርድፉ “ውርስ ማለት የሟች መብትና ግዴታዎች እንዲሁም
ዉርስ ከች አንፃር እና ከወራሾች አንፃር የተለያየ እይታ ቢኖረዉም ዉርስ ማለት ሰዉ
ትቶት ሲሞት በህይወት ላሉ ሰዎች የሚተላለፍ ሃብት ነዉ፡፡
የቀጠለ…
የዉርስ ህግ ምንድነዉ?
የውርስ ሕግ ጠቅለል ባለ አገላለፅ የሟች (አውራሽ) መብቶች እና ግዴታዎች በሕይወት ላሉት
ወራሾቹ የሚተላለፍበት መንገድ የያዘ ሕግ ነው፡፡ የሟች ውርስ መች እና እንዴት ይከፈታል፣
ወራሾች እነማን ናቸው፣ ወራሽነትን የሚያሳጡ ነገሮች ምንድን ናቸው፣ የሟች ኑዛዜ ምን
ማሟላት አለበት፣ ውርሱ እንዴት እና በማን ይጣራል፣ የውርስ ክፍያ እንዴት እና በማን
ይፈፀማል እና የመሳሰሉትን የሚመራ ሕግ የውርስ ሕግ ነው፡፡
ለዉርስ ያልተገባ ነዉ የሚያሠኙ ምክንያቶች በሁለት የተከፈሉ ሲሆን
የመጀመሪያዉ የወንጀል ድርጊቶችን ፈፅሞ በፍርድ ጥፋተኛ መባልና መቀጣት
/የፍ/ህ/ቁ.838/ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በህጉ በግልፅ የተመለከቱት ሌሎች
ተግባራትን መፈፀም /የፍ/ህ/ቁ.840/ ናቸዉ፡፡
እነዚህ ችን ለመዉረስ ያልተገባ ነዉ የሚያሠኙ ተግባራት 1ኛ በፍ/ህ/ቁ.838
እንደተመለከተዉ ችን ወይም ወደ ታች የሚቆጠር ተወላጆችን ወይም ወደ ላይ
የሚቆጠሩ ወላጆች አንዱን ወይም የችን ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል
ወይም በመግደል ሙከራ የተፈረደበት ወይም በሀሰት በመወንጀል በመመስከር
ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱን የሞት ፍርድ ወይም ከ10 ዓመት የበለጠ ፅኑ እስራት
ቅጣትን ለማስከተል የሚያሰጋ ሆኖ የተቀጣ ማንኛዉም ሰዉ እንዲሁም በፍ/ህ/ቁ.
840 የችን ሰዉነት ሁኔታ ምክንያት በማድረግ አዉራሹ ከመሞቱ በፊት ባሉት 3
ወራት ኑዛዜ እንድያደርግ ፣እንዳይለዉጥ ፣እንዳዳይሽር ያደረገ እንድሁም አስቦ
ያለች ፈቃድ የመጨረሻ ኑዛዜን ያበላሸ፣እንዳይገኝ ያደረገ፣ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን
በማወቅ በሀሰት ኑዛዜ የተጠቀመ የወራሽነት መብት ያጣል፡፡
የቀጠለ…
3.1 ጠቅላላ
ች ከሞተ በላ የዉርስ ስርዓት የሚፈፀመዉ ቢያንስ በሶስት ዓይነት መንገድ
እንደሆነ የፍ/ህጉ ይደነግጋል፡፡
-1ኛዉ ች የተወዉ ኑዛዜ ካለ በኑዛዜ
- 2ኛዉ ኑዛዜ ከሌለ ያለ ኑዘዜ እንዲሁም ች በከፊል
ኑዛዜ የተወና በከፊል ንብረቱ ያለ ኑዛዜ መከፋፈል
እንዳለበት የተወዉ ኑዛዜ ካለ ዉርሱ በከፊል በኑዛዜ
- በከፊል ያለ ኑዛዜ ይፈፀማል፡፡/ፍ/ህ.ቁ.829/
3ኛዉ የዉርስ ስርዓት ክፍት የዉርስ ሁኔታ /Vacant Succession/ ሲሆን ይህም ች
ኑዛዜ ካልተወ፣ያለኑዛዜ ወራሽ ከሌለዉና የሀገሪቱ ህግም በዚህ ሁኔታ
ንብረቱ ለማን መተላለፍ እንደሚገባዉ ሳይደነግግ ክፍት አድርጎ ሲተዉ
ነዉ፡፡ በመሆኑም የኢትዮያ የዉርስ ህግ የአወራረስ ስርዓት 1ኛዉንና 2ኛዉን
የአወራረስ ስርዓት የተከተለ ይመስላል፡፡
በዚህ መሰረት ግልፅ ኑዛዜ ስለመኖሩ የሚከተሉትን አራት ነገሮች መላት አለባቸዉ፡፡
1. ተናዛዡ እየተናገረ የሚናገረዉ ሳይጨመር ሳይቀነስ ሳይለጥ ሌላ
ሰዉ የፃፈዉ ወይም ተናዛዡ ራሱ የፃፈዉ
2. አራት ምስክሮች ባሉበት በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፊት
መነበብ እና ወድያዉኑ መፈረም
3. የማንበብ ፎርማሊቲ ማላቱን ማመልከት
4. ኑዛዜዉ የተፃፈበትን ቀን ማመልከት
እዚህ ላይ የሚነሳዉ ክርክር ኑዛዜ መሻር የሚችለዉ ተናዛዡ ብቻ ነዉ፡፡ ነገር ግን ሲሽር በምን መንገድ
ይሽራል የሚለዉ ነዉ፡፡ በፍ/ህ/ቁ. 898 /1/ ተናዛዡ ኑዛዜዎቹ ዋጋ ያላቸዉ እንደሆኑ በሚያስልፈገዉ
ፎርም ዓይነት ግልፅ አድርጎ በማሳወቅ ኑዛዜዉን የሻረዉ እንደሆነ ነዉ ይላል፡፡ እዚህ ላይ ዋጋ ያላቸዉ
እንደሆኑ በሚያስፈልገዉ ፎርም የሚለዉ አባባል በቃል የተደረገን በቃል በግልፅ የተደረገን በግልፅ በራስ እጅ
ፅሁፍ የተደረገን በራስ እጅ ፅሁፍ በተደረገ ፎርም ዓይነት ብቻ ነዉ ወደሚለዉ ትርጉም ይወስደናል፡፡
በመሆኑም ከኑዛዜ መሰረታዊ ባህሪይ በመነሳት መተርጎም ያለብን የተናዛዡን ኑዛዜ የመሻር ስልጣን
በሚያጣብብ መልኩ ነዉ ወይስ ሰፋ ባለ ሁኔታ የሚለዉ መታየት አለበት፡፡
ብዙዎች የሚስማሙበት ግን ች ከሞተ በላ እንዳይፈፀም የሚፈልገዉን ኑዛዜ በግልፅ እስከሻረ ድረስ
የኑዛዜ ህጉን ድንጋጌ አጥብቦ በመተርጎም ዉጤት መስጠት ተገቢ አይደለም የሚል ነዉ፡፡ በዚህ ላይ
በሰ/መ/ቁ. 96364 በቅፅ 17 በወ/ሮ እልፍነሽ ወርቁና በወ/ሮ ኤልሳበጥ አስራት መካከል በተደረገ ክርክር
አንድ ተናዛዥ ኑዛዜዉን መሻር ሲፈልግ በማያሻማ ሁኔታ በመግለፅ ከሻረ ኑዛዜዉ ዋጋ ያላቸዉ እንደሆኑ
በሚያስፈልገዉ ፎርም ዓይነት ግልፅ አድርጎ አልሻረም ሊባል እንደማይቻል ተወስል፡፡
ኑዛዜዉን በተዘዋዋሪ መንገድ የመሻር መገለጫዎች ኑዛዘዉን ማጥፋት ፣ መሰረዝ ወይም በኑዛዜ
የተሰጠን ነገር ለሌላ ማስተላለፍ ሲሆኑ ተናዛዡ እነዚህን ግዙፍ ተግባራት ካከናወነ ኑዛዜዉን ለመሻር ግልፅ
ፍላጎት እንዳለዉ ይገመታል፡፡ የፍ/ህ/ቁ 899/2/ 899/3/
ነገር ግን እነዚህ የህግ ግምቶች ሊስተባበሉ የሚችሉ የህግ ግምቶች በመሆናቸዉ በሌላ ተቃራኒ ማስረጃ
ማስተባበል ይቻላል፡፡
3.2.2 ኑዛዜ ዉድቅ መሆን
ኑዛዜ ዉድቅ መሆንና ኑዛዜ መሻርን አንድ አድርጎ መመልከት አለ፡፡ ሁለቱ የተለያዩ ፅንሰ ሀሳቦች ናቸዉ፡፡
ኑዛዜ መሻር በተናዛዡ የሚፈፀም ተግባር ሲሆን ኑዛዜ ዉድቅ የሚሆነዉ በዉርስ ህግ ድንጋጌዎች ነዉ፡፡ ኑዛዜ ዉድቅ
የሚሆንባቸዉን ሁኔታዎችን የሚደነግገዉ ህገ አዉጭዉ ነዉ፡፡
በዉርስ ህጉ ኑዛዜ ዉድቅ የሚሆንባቸዉ ሁኔታዎች
1. የቃል ኑዛዜ ሲሆን ኑዛዜ ያደረገዉ ሰዉ ኑዛዜ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ በህይወት መኖር
ከላይ የተጠቀሱ ኑዛዜዉ ከተደረገ በላ የተፈጠሩ ክስተቶች ጋር ተያይዞ ጥንቃቄ መወሰድ
ያለባቸዉ ነጥቦች
ች ኑዛዜ ካደረገ በላ ልጅ ቢወለድም ዳኞች ኑዛዜዉን አይተዉ በፍ/ህ/ቁ.905 መሰረት
ኑዛዜዉ በከፊል ዉጤት እንድኖረዉ የማድረግ ስልጣን አላቸዉ፡፡
ከተናዛዡ በፊት የሞተዉ ሰዉ ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሲሆን የኑዛዜ ስጦታዉ
ተጠቃሚዉ ከተናዛዡ ቀድሞ ቢሞትም የእሱ ተተኪዎች በዉርሱ ሊከፈሉ እንደሚችሉ
እንዲሁም የልዩ ኑዛዜ ስጦታ ተደርጎለት ከሆነ ች የስጋ ዘመድ ወራሽ በማጣቱ ንብረት
ለመንግስት የሚገባ በሆነ ጊዜ የልዩ የኑዛዜ ስጦታ ተጠቃሚዉ ወራሾች እሱን ተክተዉ በች
ዉርስ ሊካፈሉ እንደሚችሉ የፍ/ህ/ቁ.908 ይደነግጋል፡፡
የቀጠለ…
በዚህ በሰነድ ማስረጃ ላይ ክርክር ቢነሳ በተለይም በሰነዱ ላይ ያለዉ ፊርማ የች
አይደለም ቢባልና ሰነዱ ለፎረንስክ ቢላክ ፎረንስክ መረማሪዎች ፊርማዉ የማን እንደሆነ
ለመለየት አልተቻለም የሚል ምላሽ ሰጡ፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰነዱ ላይ የፈረሙ ምስክሮችን
ጠርቶ በመስማት ኑዛዜዉ በትክክል በች መደረጉ ተረጋግል በማለት ቢወስን ኑዛዜን
ለማስረዳት በዉርስ ህጉ የተደነገገዉን ድንጋጌ አይቃረንም?
ምዕራፍ 4 ዉርስ ማጣራትና ዉርስን ማስተዳደር
የች ዉርስ ማጣራት ስራ በች ዉርስ ስርዓት አፈፃፀም ዉስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ በመሆኑም የዉርስ
ማጣራቱን ተግባር ኃላፊነት ወስዶ የሚያስፈፅም አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሖኑ ሰዎች መኖር አለባቸዉ፡፡
እነዚህ የሚመረጡ ሰዎች የዉርስ አጣሪዎች ይባላሉ፡፡
6.1 ዉርስ ማጣራት
ዉርስ ማጣራት ማለት /የፍ/ህ/ቁ.944/
- የች ወራሾች እነማን እንደሆኑ አጣርቶ መወሰን
- የዉርስ ሀብት መጠን ዓይነትና ግምት እንዲሁም የሚገኝበትንቦታ አጣርቶ መወሰን
- ሌሎች ሰዎች ከች የተበደሩትን ገንዘብ መሰብሰብና ከች ዉርስ ላይ የሚከፈሉ እዳዎችን አጣርቶ መክፈል
በፍ/ህ/ቁ. 949 መሰረት ዳኞች ዉርስ አጣሪ የሚሾሙ ሲሆን በ951 ደግሞ ከላይ በሶስት መንገድ
የተሰየሙ ዉርስ አጣሪዎችን የመተካት ስልጣን እንዳላቸዉ የሚደነግግ ነዉ፡፡ ሁለቱ ፅንፀ ሀሳቦች
የተለያዩ ናቸዉ፡፡
ፍርድ ቤቱ በች በህግ፣ኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት የተሰየመን ዉርስ አጣሪ በማንሳት ሌሎችን
የሚሰይመዉ /የፍ/ህ/ቁ/951/
- ዉርስ አጣሪዉ የተሰየመበት ኑዛዜ ዋጋ ያለዉ ኑዛዜ መሆኑ አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ
- በሌላ ምክንያት ዉርስ አጣሪዉን በመለየት ላይ አጣራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም
- ብዙ ያለኑዛዜ ወራሾች ኖረዉ በፍ/ህ/ቁ.947 በሚመነጭ የአጣሪነት ስልጣን በጋራ
ተግባብተዉና ተስማምተዉ መስራት ሳይችሉ ሲቀሩ
- ከወራሾቹ አንዱ ለአቅመ መጠን ያላደረሰ፣በህግ ወይም በፍርድ የተከለከለ፣
የታወቀ እብድ መሆን ወዘተ… ምክንያት ጥቅሙን ማስከበር ሳይችል ሲቀር
- ዉርስ ማጣራቱ ስራ ልዩ ችግር ያስነሳና ልዩ ሙያ ያላቸዉን ችግሩን መቅረፍ
የሚችሉ ሰዎችን መሰየም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
- በህግ፣በች ኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት የተሰየመ ዉርስ አጣሪ ቸልተኛ፣ ትጉህ
ያልሆነ፣ የማጭበርበር ባህሪይ የሚታይበት፣ሀቀኝነት የማይታይበት ችሎታ
የሌለዉ ሲሆን ነዉ፡፡
4.1 የዉርስ አጣሪዎች ግዴታዎችና ኃላፊነቶች
ማንኛዉም ጉዳይ አንድ ሰዉ በህግ በዉል በፍርድ ቤት ዉሳኔ መብት ያገኘ እንደሆነ
መብቱን የሚጠይቅበትና በስራ ላይ የሚያዉልበት የተወሰነ የጊዜ ገደብ ይሰጠዋል፡፡
ባለመብቱ በህግ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ መብቱን ለመጠየቅ ተገቢዉን ትጋት
ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በጊዜ ገደቡ ዉስጥ መብቱን ካልተጠቀመ መብቱ በይርጋ
ይታገዳል፡፡
ይርጋ የሚለዉ ቃል መነሻዉ ረጋ ከሚለዉ የአማርኛ ቃል የመጣ እንደሆነና ትርጉሙም የሰዉ
ሀሳብ ከመዉጣት ከመዉረድ በሀሳብ ከመዞር ከመባከን ከመናወጥ ፀጥ አለ ማለት ነዉ ሲል
ደራሲ ተሰማ ኃብተ ሚካኤል “ ከሰተ ብርሃን ተሰማ ”በ2000 ዓ.ም ባሳተሙት የአማርኛ
መዝገበ ቃላት ገልፆታል፡፡
በመሆኑምበአንድ ጉዳይ ላይ ክስ የማቅረብ ወይም መብት የመጠየቅ ጉዳይን አስመ
ልክቶ በጉዳዩ ላይ ክስ የሚያቀርብበት ሰው ስለጉዳዩ ያለውን ሀሳብ ከመውጣት ከመ
ውረድ በሀሳብ ከመዞርና ከመባከን ከመናወጥ ከረጋ (ፀጥ) ካለ በኋላ ሊከሰስ ወይም
ሊጠየቅ እንደማይገባ ያመለክታል በሚል ልንወስደው እንችላለን፡፡
በሌሎች ፅሁፎች ላይም ይርጋ ማለት አንድ መብቱ ወይም ጥቅሙ የተነካበት ሰው በሌ
ላ ሰው ላይ ክስ፣ አቤቱታ ወይም የይገባኛል ጥያቄ እንዲያቀርብ በሕግ ተለይቶ የተቀመ
ጠ የክስ (አቤቱታ) ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡
ይርጋ በፍትሀብሄር ጉዳይ በተከራካሪ ወገን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የሚቀርብ
የቀጠለ
የተለያዩ የህግ ምሁራን በህግ ይርጋ እንዲኖር የተፈለገባቸዉን ሶስት ምክንያቶች እንዳሉ
ይገልፃሉ፡፡
አንደኛዉ ከሳሽ በተገቢ ትጋትና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል
ነዉ፡፡
ሁለተኛዉ ደግሞ ተከሳሽ በጊዜ ቆይታ ምክንያት ዘግይተዉ የሚመጡ ክሶችን
ለመከላከል ማስረጃዎችን እንዳያጣ ለማድረግ ነዉ፡፡
ሶስተኛዉና የመጨረሻዉ ደግሞ ዘግይተዉ የሚቀርቡ ክሶች ፍትህ ከማስገኘት
ይልቅ ለበቀልና ለማጥቅያ መሳሪያነት እንዳያገግሉ ለመከላከል ነዉ፡፡
የቀጠለ
እንግዲህ ስለ ይርጋ በጠቅላላዉ ይህን ያህል ካልን በመቀጠል ከዉርስ ጋር የተያያዙ የይርጋ
ገደቦችን በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
5.4 ከዉርስ ሀብት ጋር የተያያዙ የይርጋ ገደቦች
አንድ ወራሽ የዉርስ ንብረት በሌላ ወራሽ የተያዘዉ እንድከፈለዉ የሚቀርብ ክስ ይርጋ
ከዉርስ ሀብት ጋር በተያያዘ ወራሽ ነኝ የሚል ወገን መብቱና ንብረቱ በሌላ ወራሽ
መያዛቸዉን ካወቀ ከ3 ዓመት በላ የሚያቀርበዉ የወራሽነት ክሰ በይርጋ
ይታገዳል፡፡ የፍ/ህ/ቁ.1000(1) ሰ/መ/ቁ. 26422 ቅፅ 6 በዚሁ መዝገብ ወ/ሮ ስንልሽ
ማዝንጊያ በእነአቶ ተስፉ ማዝንጊያ ላይ ባቀረበችሁ ክስ የአዉራሻቸዉ የሆነ
የዉርስ ንብረት በእጃቸዉ ያለዉን ያካፍሉ የሚል ሲሆን ተከሳሾች በፍርድ ቤት
ዉርስ አስወስነዉ ከ10 ዓመት በላይ በእጃቸዉ ያደረጉትን መጠየቅ አይችሉም
በማለት 1000 (1) በመጥቀስ ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የፍ/ህ/ቁ/1000(2)
በመጥቀስ ይርጋን ዉድቅ አድረገ፡፡ ጠቅላይ ፍ/ቤት አፀና፡፡ የፌዴራል ሰበር የስር
ፍርድ ቤት የጠቀሰዉ አንቀፅ 1000 (2) ማለትም ከዘር የወረደ ርስት በማለት
የወሰነዉ አግባብነት የለዉም በማለት የፍ/ህ/ቁ.1000 (1) በመጥቀስ በይርጋ ክሱን
ዉድቅ አድርጎታል፡፡ በተጨማሪም በሰ/መ/ቁ. 20295 ቅፅ 6 በሆነዉ በአቶ ደጀነ
ለገሰ እና በአቶ መላኩ ጌታቸዉ መዝገብ ላይ ወራሽነትን ካረጋገጡ በላ ንብረት
ተይዞብኛል ይመልስልኝ የሚል ወራሽ የሆነ ሰዉ በሌላ ወራሽ በሆነ ሰዉ ላይ
የሚያቀርበዉ ክስ በ3 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ በፍ/ህ.ቁ.1000 ጠቅሶ
ወስኖበታል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በሰ/መ/ቁ 25567 ቅፅ 6 ላይ በወ/ሪት አይናለም አበበ እና አቶ
ደገፉ ጉርሙ በተከራከሩበት ወ/ሪት አይናለም የች የአቶ አበበ ጉርሙ ልጅ
አልወለደም ነገር ግን ወ/ሪት አይናለም የአቶ አበበ ልጅ ነች ተብሎ ወራሽነቱ
የተረጋገጠዉ በአግባቡ ስላልሆነ ዉሳኔዉ ይሻር የሚል ቀርቦ ወ/ሪት አይናለምም
በበኩü የዛሬ 21 ዓመት ህፃን ሆኜ ያስወሰንኩትን መቃወም አትችልም በሚል
በቀረበ ክርክር የወረዳዉ ፍ/ቤት ፍ/ህ/ቁ.1000 ለንብረት ተይዞብኛል ክርክር እንጅ
ወራሽ ናት አይደለችም ክርክር አያገለግልም በሚል ይርጋዉን ዉድቅ በማድረግ ልጅ
ባለመሆ ያለኑዛዜ ወራሸ አይደለችም በማለት ወሰነ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ይህን ዉሳኔ ሽሮ አመልካች ልጅ ስለሆነች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ናት አለ፡፡
በይግባኝ የተመለከተዉ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የከፍተኛዉን ዉሳኔ ሽሮ
የወረዳዉን አፀና፡፡ አቤቱታ የቀረበለት የፌዴራል ሰበር ችሎት የስር ፍርድ ቤት
የፍ/ህ/ቁ.1000 በጠባቡ መተርጎሙ አግባብ አይደለም አመልካች ወራሽነትን
አረጋግጣ ከ20 ዓመት በላይ የቆየ የባለሀብትነት ድርሻ ግልፅ ስለሆነ የተጠሪ ክስ
በ1000 መሰረት ክርክሩ በይርጋ ይታገዳል ሲል ወሰነ፡፡
በሌላ የይርጋ ክርክር የሰ/መ/ቁ. 25664 ቅፅ 6 በአቶ ተገኝ ይማምና በአቶ ካሳሁን ደሳለኝ
መዝገብ አቶ ካሳሁን ደሳለኝ በአቶ ተገኝ ላይ ች እህታቸዉ ልጅ ሳትወልድ ስለሞተች
በትዳር ያፈራችዉን ንብረት ግማሽ ድርሻ ያካፍል በማለት ክስ አቅርቦ ተከሳሽ የፍ/ህ/ቁ.
1000(2) እና 1845 ይርጋ አነሳ፡፡ ፍርድ ቤትም ዉርሱ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በማለት ወሰነ፡፡
ይግባኝ ሰሚዉም አፀናዉ፡፡ የሰበር ችሎቱ አቤቱታ ቀርቦለት ያስቀርባል በማለቱ
ተጠሪዎች(እነ ካሳሁን ) ክስ ያቀረብነዉ 15 ዓመት ሳይሞላ ነዉ በማለት 1000(2) በመጥቀስ
እንዲሁም የፍ/ህ/ቁ/1845 በዉል ላይ ለተመሰረቱ ጉዳዮች ይርጋ እንጂ ዉርስ አይመለከትም
ሲሉ ተከራከሩ፡፡ የሰበር ችሎት የፍ/ህ/ቁ. 1000(2) የሚነሳዉ ክርከሩ በወራሾች መካከል ቢሆን
ነዉ፡፡ በዚህ ጉዳይ የቀረበዉ ክርክር በወራሾች መካከል ባለመሆኑ 1000(2) ተፈፃሚነት
የለዉም፡፡ ጉዳዩ ተጠሪዎች ክስ ሳይመሰርቱ ከአስር ኣመት በላይ የቆዩ መሆኑ የተረጋገጠ
ስለሆነ የሚመለከተዉ ድንጋጌ የፍ/ህ/ቁ. የፍ/ህ/ቁ.1677 (1) እና 1845 ነዉ፡፡1677 ግዴታዎቹ
ከዉል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀፅ ደንቦች ይፈፀሙባቸዋል ይላል በመሆኑም የ1845 የ10
ዓመት ይርጋ ክሱን ያግዳል ሲል ወሰነ፡፡
በልዩነት ያስመዘገበዉ ዳኛ ለዚህ ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነዉ ድንጋጌ ይህ አይደለም 1000 (1
እና 2) ነዉ ይህን ከተከተልን ክሱ በይርጋ አይታገድም በሚል በልዩነት ሲያዝመዘግብ ግን
ዉሳኔዉ በአብላጫዉ ተወሰነ፡፡
ወራሽ የሆነ ሰዉ ወራሽ ባልሆነ ሰዉ ላይ የዉርስ ንብረት ይለቀቅልኝ በሚል በሚያቀርበዉ ክስ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነዉ
የ10 ዓመት ይርጋ የሚቆጠረዉ ወራሽ ወራሽነት ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ንብረቱ ወራሽ ባልሆነዉ ሰዉ እጅ
ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ፡፡ ሰ/መ/ቁ.47201 ቅፅ 11
የቀጠለ
በተጨማሪም የፍ/ህ/ቁ. 1001 (1) እና (2) አንድ ህጋዊ ወራሽ ወራሽ ባልሆኑ
ሰዎች የተያዘን ንብረት ለማስመለስ የሚያቀርበዉ ክርክር የጊዜ ገደብ
በሚመለከት ነዉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ክርክሩ ወራሽ ባልሆነ ሰዉ ላይ ህጋዊ ወራሽ
ያቀረበዉ ቢሆንም የክርክሩ ነጥብ የተያዘ ንብረት ይመለስ ሳይሆን የች
ንብረት ዉርስ ክፍያና ሊደርሰኝ የሚገባዉ ድርሻ ይሰጠኝ የሚል በመሆኑ
አግባብነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ የፍ/ህ/ቁ. 1080 ነዉ በመሆኑም ክሱ በይርጋ
ሊታገድ አይገባም ሲል ወሰነ፡ የፍ/ህ/ቁ. 1080 “ የክፊያዉ ጠያቂ ክፊያዉን
ካወቀ ከአንድ ዓመት በላ ወይም በማናቸዉም ሁኔታ ች ከሞተበት ጊዜ
ጀምሮ በአስር ዓመት ጊዜ ዉስጥ ካልቀረበ ዉድቅ ይሆናል” ይላል፡፡ የፍ/ህ/ቁ.
1845 ደግሞ ተፈፃሚ አይሆንም የተባለዉ ህግ በሌላ አካኀን ካልወሰነ በቀር
ስለሚል እና ህግ ደግሞ ከላይ በተጠቀሱ ድንጋጌዎች ይርጋን ያስቀመጠ በመሆኑ
ነዉ የሚል ይገኝበታል፡፡
የፍ/ህ/ቁ.1080(1) ተፈፃሚነቱ አስቀድሞ የዉርስ ማጣራት ተደርጎ እንደገና
ክፍፍሉም በወራሾች መካከል ተደርጎ አንዱ ወራሽ በክፍፍል ሳይሳተፍ ቀርቶ
ወይም ወኪልም ያልተመደበ እንደሆነ የተደረገዉን ክፍፍል በመቃወም ፈራሽ
እንዲሆን ጥያቄ የሚቀርብበትን ይርጋ የሚመለከት እንደሆነ በቅፅ 10 የሰ/መ/ቁ.
40418 በአቶ ተስፋዬ ሞላና በአቶ እሸቱ ምኔ መዝገብ ላይ ተወስlል፡፡
የቀጠለ…
በኑዛዜ የተገኘ ንብረት በሆነ ጊዜ ኑዛዜዉ እንድፈጸም በ10 ዓመት ዉስጥ ጥያቄ ካልቀረበበት
በይርጋ ይታገዳል፡፡ ሰ/መ/ቁ.38152 ቅፅ 8
በስጦታ ሰጭ ላይ በተደረገ የመንፈስ መጫን ምክንያት የስጦታ ዉሉ ይፍረስ ጥያቄ
የማቅረቢያ ጊዜ ስጦታዉ በተደረገ በ2 ዓመት ዉስጥ ሲሆን አጠቃላይ የስጦታ ዉል
በመቃወም የሚቀርብ ክስ በፍ/ህ/ቁ. 1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዳል፡፡ ሰ/መ/ቁ.
105652 ቅፅ 18
በፍ/ህ/ቁ. 973/1/ ስለኑዛዜ መነበብ እንድሁም ኑዛዜዉ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ወይም የተወከሉ
ሰዎች ኑዛዘዉ አይፀናም ወይም አንዱ በኑዘዜዉ የተነገረዉ ቃል አይፀናም በማለት ክስ
ለማቅረብ ያላቸዉን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለክፊያዉ በዉርስ አጣሪዉ የቀረበዉን
የድልድልን አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜ ከተነበበት አንስቶ በ15 ቀናት ዉስጥ ለዉርስ
አጣሪ ወይም ለሽማጊሌ ወይም ለፍርድ ቤት መግለጫ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ መግለጫዉም
የሚቀርበዉ በፅሁፍ ነዉ፡፡ የሰ/መ/ቁ. 82585 ቅፅ 15 ወ/ሮ ሱዛን ምንታልባን 3 ሰዎች እና
አቶ ሙራድ አሊ /ፍ/ህ/ቁ.973 (1‚3) እና 974 (1) (2) ልዩነትና አንድነት/
በንዑስ አንቀፅ 3 ደግሞ መግለጫ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ አስከ 3 ወር ክስ ለፍርድ ቤት
ወይም ለሽማጊልና ዳኞች መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ክስ ካልቀረበ በድልድል አመዳደብ
ሀሳብ ላይ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡ የድልድላ አመዳደብ ሀሳብ የንብረት
ክፍፍል እንዳልሆነ መታወቅ ያለበት ነዉ፡፡ ይህ የድልደላ አመዳደብ ሀሳብ እቅድ ነዉ፡፡
የቀጠለ
ኑዛዜን ስለመቃወም የተቀመጠ ይርጋ የዉርስ አጣሪ የችን ኑዛዜ በማፈላለግ ባገኘ ጊዜ
ያለኑዛዜ ወራሾች የሚናገርበት ች በሞተ በ40 ቀን ነዉ፡፡ ች ኑዛዜ ያልተወ እንደሆነ
የዉርሱን አደራረግ እና አከፋፈል ዓይነት እንዴት ሊፈፅም እንዳቀደ ዉርስ አጣሪ ያለ ኑዛዜ
ወራሾች የሚያሳዉቅበት ች በሞተ በ40 ቀን ነዉ፡፡ የፍ/ህ/972
ከዉርስ ሀብት ጋር በተያያዘ ወራሽ ነኝ የሚል ወገን መብቱና ንብረቱ በሌላ ወራሽ
መያዛቸዉን ካወቀ ከ3 ዓመት በላ የሚያቀርበዉ የወራሽነት ክሰ በይርጋ ይታገዳል፡፡
የፍ/ህ/ቁ.1000(1)
ክርክሩ ትክክለኛ ወራሽ በሆነና ባልሆነ ሰዉ መካከል ሲሆን ክስ ሳይመሰርቱ ከአስር ኣመት
በላይ የቆዩ መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ የሚመለከተዉ ድንጋጌ የፍ/ህ/ቁ. የፍ/ህ/ቁ.1677 (1)
እና 1845 ነዉ፡፡1677 ግዴታዎቹ ከዉል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀፅ ደንቦች
ይፈፀሙባቸዋል ይላል በመሆኑም የ1845 የ10 ዓመት ይርጋ ክሱን ያግዳል፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰዉ ወራሽ የሆነ ሰዉ ወራሽ ባልሆነ ሰዉ ላይ የዉርስ ንብረት ይለቀቅልኝ
በሚል በሚያቀርበዉ ክስ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነዉ የ10 ዓመት ይርጋ የሚቆጠረዉ ወራሽ
ወራሽነት ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ንብረቱ ወራሽ ባልሆነዉ ሰዉ እጅ ከተያዘበት
ጊዜ ጀምሮ ነዉ፡፡ ሰ/መ/ቁ.47201 ቅፅ 11
የዉርስ ይርጋ ማጠቃለያ የቀጠለ..…
በኑዛዜ የተገኘ ንብረት በሆነ ጊዜ ኑዛዜዉ እንድፈጸም በ10 ዓመት ዉስጥ ጥያቄ ካልቀረበበት በይርጋ ይታገዳል፡፡
ሰ/መ/ቁ.38152 ቅፅ 8
በስጦታ ሰጭ ላይ በተደረገ የመንፈስ መጫን ምክንያት የስጦታ ዉሉ ይፍረስ ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜ ስጦታዉ በተደረገ
በ2 ዓመት ዉስጥ ሲሆን አጠቃላይ የስጦታ ዉል በመቃወም የሚቀርብ ክስ በፍ/ህ/ቁ. 1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ
ይታገዳል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 105652 ቅፅ 18
ኑዛዜዉ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዘዉ አይፀናም ወይም አንዱ በኑዘዜዉ የተነገረዉ ቃል
አይፀናም በማለት ክስ ለማቅረብ ያላቸዉን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለክፊያዉ በዉርስ አጣሪዉ የቀረበዉን የድልድልን
አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜ ከተነበበት አንስቶ በ15 ቀናት ዉስጥ ለዉርስ አጣሪ ወይም ለሽማጊሌ ወይም
ለፍርድ ቤት መግለጫ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ መግለጫዉም የሚቀርበዉ በፅሁፍ ነዉ፡፡በንዑስ አንቀፅ 3 ደግሞ መግለጫ
ከተሰጠበት ቀን አንስቶ አስከ 3 ወር ክስ ለፍርድ ቤት ወይም ለሽማጊልና ዳኞች መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ክስ
ካልቀረበ በድልድል አመዳደብ ሀሳብ ላይ ክስ የማቅረብ መብት በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡ የድልድላ አመዳደብ ሀሳብ
የንብረት ክፍፍል እንዳልሆነ መታወቅ ያለበት ነዉ፡፡ ይህ የድልደላ አመዳደብ ሀሳብ እቅድ ነዉ፡፡ በኑዛዜዉ ንባብ ሥነ
ሥርዓት ያልነበሩ ወይም በኑዛዜዉ ንባብ ሥነ ሥርዓት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎችና እንዲሁም ኑዛዜዉ በሌለበት
በዉርስ አጣሪዉ የቀረበን የድልድል አመዳደብ ሃሳብ መቃወም የሚቻለዉ በፍ/ህ/ቁ. 973 /1/ መሰረት ይህ ሀሳብ
ከተነገራቸዉ ቀን አንስቶ ነዉ፡፡ ይሁን እንጅ ስለክፊያዉ አመዳደብ ሃሳብ መግለጫ ላይ ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከ5 ዓመት
በላ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ች ከሞተበት ከ5 ዓመት በላ በማናቸዉም ምክንያት መቃወሚያ ሊቀርብበት
አይችልም፡፡ የፍ/ህ/ቁ/974/2 የሰ/መ/ቁ. 82585 ቅፅ 15 ወ/ሮ ሱዛን ምንታልባን 3 ሰዎች እና አቶ ሙራድ አሊ
/ፍ/ህ/ቁ.973 (1‚3) እና 974 (1) (2) ልዩነትና አንድነት/
ከዉርስ መነቀል ምክንያት የሚቀርብ ክስ ይርጋ በተመለከተ የስጦታ ክፍያ እንድቀር የሚደረገዉ ክስ ወደ ላይ
በሚቆጠረዉ ስጦታ አድራጊ ወላጅ አባት በሞተ በ2 ዓመት ዉስጥ እና የስጦታዉ መከፋፈል ከተደረገበት ቀን
አንስቶ በ10 ዓመት ዉስጥ ካልቀረበ ክስ የማቅረብ መብት ቀሪ ይሆናል፡፡
አመሰግናለሁ
የቀጠለ…