You are on page 1of 2

የግብረ ገብ ጥምህርት 5 ኛ ክፍል ጥያቄና ምልስ

1. ጊዜንና ጉልበትን ለአንድ የተወሰነ ስራ ወይም ተግባር የማዋል ጥረት ወይም ልምድ ጠንክሮ መስራት
ይባላል፡፡
2. አጠቃላይ ሐሳብን ለማገኘት የምንጠቀመው የፍጥነት ንባብ የአሰሳ ንባብ (Skimming) ይባላል፡፡
3. የተለየ ወይም የተወሰነ መረጃን ለመፈለግ የምንጠቀመው የፍጥነት ንባብ አይነት መቀኘት ወይም
የዳሰሳ ንባብ (Scanning) ይባላል፡፡
4. ትልቅ የህይወት አጋርና ምርኩዝ ማንበብ ይባላል፡፡
5. ውሳኔ መስጠት በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ ጠቃሚ ችሎታ ነው፡፡
6. ግብረ ገባዊ ውሳኔ አስፈላጊነት ጥቅም ፃፉ፡፡
 የግበረ ገባዊ ውሳኔ አስፈላጊነትና ጥቅም ችግሮችን ብልሃት በተሞላበትና በቀላሉ ለመፍታት
ይጠቅማል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
 በራስ መተማመንን ያዳብራል
 ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ለማፍራት
 የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅና
 የቤተሰብን ደህናነት ለማስጠበቅ ይጠቅማል
7. ውሳኔ ለመስጠት መደረግ ያለበት ቅድመ ሁኔታ ግለፁ፡፡
I. ችግሮችን መለየት
II. ለማነቃቂያ ሊሆኑ የሚችሉ አማራጮችን መለየት
III. ሊከሰቱ የሚችሉ ውጤቶችን መለየት
IV. መወሰንና መከተል
V. የውሳኔውን ውጤት መገምገም ናቸው፡፡
8. ጓደኛ ለማህበራዊ እድገት የሚሰጠውን ጥቅም ጻፉ፡፡
እውነተኛና ትክክለኛ ጓደኛ ከወንድም ጋር እኩል ነው፡፡ በደስታ ጊዜ አብሮ የሚደሰት በችግር ጊዜ
ደግሞ አብሮ የሚቸገር ነው፡፡ በመሆኑም በመመካከር፣ ጥሮና መጥፎውን ለመለየት፣ አብሮ
ለማጥናት፣ ለሀገር እደገት፣ ለቤተሰብ ግንባታ፣ አብሮ ለመስራት፣ለመረዳዳትና ለመተጋገዝ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ ስለሚያበረክት ለማህበራዊ እድገት ከፍተኛ አበርክቶ አለው፡፡
9. ውጤታማ ንባብ ለማንበብ የሚያስፈልጉ ምሮችን ፃፉ፡፡
 የት እንደምናነብ ማሰብ
 በምናነብበት ጊዜ ድምፅ አለማሰማት
 ትኩረት ማድረግ
 የምናነበውን ነገር መወሰን

1|Page
 ለማንበብ በቂ ጊዜ መመደብ
10. እያንዳንዱ ተማሪ ጎበዝ ወይም ታታሪ የመሆን አቅም አለው ሲባል ምን ማለት ነው
 ትምህርት በሚሰጥት ጊዜ በሰዓቱ ትምህርት ገበታ ላይ ከተገኘ
 ትኩረቱን በትምህርቱ ላይ ብቻ ካደረገ
 ያልገባውን ከጠየቀ
 በጋራ ለማጥናት ፈቃደኛ ከሆነና ከተገበረው
 ጠንክሮ ሳይታክት ከሰራ እያንዳንዱ ሰው ጎበዝ የመሆን እምቅ አቅም አለው፡፡ ወይም ማንም
ሰው በተፈጥሮ ሰነፍ አይንም፡፡ የተሰጠውን አእምሮውን የመጠቀም እና ያለመጠቀም ጉዳይ
ነው፡፡

2|Page

You might also like