You are on page 1of 40

ሕይወተ ወራዙት

ክፍል አንድ
ምዕራፍ አንድ
[Type text] Page 1
መግቢያ

ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)


ወጣትነት የተለያዩ የስጋ ፍላጎቶች ስሜታዊነት የሚያይሉበት በመሆኑ ልዩ የሆነ ጥበቃ
የሚያስፈልገው የእድሜ ክልል ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል ቅዱስ ጴጥሮስን ‹‹ጠቦቴቼን ጠብቅ››
ብሎ አደራ የሰጠው ወጣቶች ነጻ ፈቃዳችንን ተጠቅመን በኃጢአት እንዳንወድቅ የሚጠብቀን
እረኛ ስለሚያስፈልገን ነው፡፡ ወጣቶች ክፉ የሆኑ የስጋ ፍትወታት (ፍላጎቶች) ስለሚያይሉብን
ለአያሌ ኀጢኣቶች የምንጋለጠው በዚህ ወቅት ነው፡፡ በዚህ የእሳትነት ዘመናችን
ለማኅበራዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ ሕግ ሁል ጊዜ እንጣላለን፡፡ የምንጣላውም ከሕጉ ወጣ ብለን
በምንሰራው ስራ ነው፡፡
ክፉ የሆነ የወጣትነት ምኞት ዝም ብለው ከተከተሉት በኀጢአት ባህር ያሰጥማል፡፡ ንስሀ
ካልገቡም ለሁለተኛ ሞት ያደርሳል፡፡ (ራዕ. 20፡14)፡፡ እኛ ወጣቶች በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ
ለመኖር የግድ ከኃጢኣት መለየት እና ከበደል መራቅ ይኖርብናል፡፡ ለዚህም ፍቅርን፣ ደስታን፣
ሰላምን፣ ትዕግስትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ የወሀትን፣ መፍራት እና ራስን መግዛት
ይጠበቅብናል፡፡ (ገላ. 5፡22) ይህ የሚሆነው ክፉ ከሆነ የጎልማሳነት ምኞት በመሸሽ የጭንቀት
ቀንም ሳይመጣ በጉብዝናችን ወራት እግዚአብሔርን ስናስብ ነው፡፡ መክ. 12፡2፣ 2 ጢሞ. 2፡12፡፡
ይህ እንዴት ይቻላል ብሉ በማር. 9፡23 ‹‹ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል›› ቆላ. 4፡13 ‹‹ኃይልን
በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ›› መልሳችን ነው፡፡
ሙሉ ሰው የሚባለው ወጣት ነው፡፡ ወጣት ማለት ሎጋ፣ ሸበላ፣ ልጅ እግር፣ መዘዞ፣ ቀንበጥ
ማለት ሲሆን በተጨማሪም ጎልማሳ ጎበዝ፣ ለዘር የበቃ፣ አፍላ ማለት ነው፡፡ ግእዙ ወጣት
ማለት ‹‹ወሬዛ›› ለብዙ ደግሞ ወራዙት ይሆናል፡፡ ሙሉ ሰው የሚባለው ንዋያት የተሟሉለት
ማለትም ሕዋሳት ተደራጅተውለት እንደ ልቡ ማሰብ፣ መንቀሳቀስ እና መናገር የሚችል ሰው
ነው፡፡ ሙሉ ሰው ኃላፊነት መውሰድ ይችላል፣ ስለ ራሱ መግለጥ ይቻለዋል፡፡
ዘመነ ወርዛዌ
የወጣትነት ዘመንን በቁጥር ሰፍሮ ከዚህ እስከዚህ ያለው ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን
አንዳንድ መጻሕፍት አሀዛዊ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እና ምሳሌአያዊ አስተምህሮ
ወጣትነት የሚባለው ከ 20-40 ዓመት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከነፋስ፣ ከእሳት፣ ከውኃ ከአፈር እና
አምስተኛው ከነፍስ ነው፡፡ እነዚህ አራቱ ባሕሪያት በሰው ሕይወት ውስጥ ይንጸባራቃሉ፡፡ በሚሞትበትም
ጊዜ አራቱም ወደነበሩበት ይመለሳሉ፡፡ ያን ጊዜ ሥጋ ይበሰብሳል፡፡ ብትንሣኤ ዘጉባኤ ደግሞ አራቱም
ባሕሪያት ከነፍስ ጋር እንደገና ተዋሕደው ይነሳሉ፡፡ ሰው በነዚህ አራቱ ባሕርያት እራሱን እንዲገዛ ተደርጎ
ነው የተፈጠረው፡፡ አራቱ ባሕርያት የሚጣሉ ናቸው፤ የሚታረቁም ናቸው፡፡ ለምሳሌ እሳት ስያይል በውሃ
እንድናበርድ፣ ነፋስ ስያይል በመሬትነታችን እንድንገታ ነው፡፡ እንዲህ ካልሆነ በሰው ሕይወት እንሰሳዊነት
ጠባይ ብቻ ይንጸባረቃል፡፡ በውስጣችን ስለመኖራቸውም መገለጫዎቹ እንደሚከተሉ ናቸው፡፡
ነፋስ፡- ሰው በመተንፈሱ ከነፋስ መፈጠሩ ይታወቃል

[Type text] Page 2


እሳት፡- በጤናማ ሕይወት የሚታየው ቋሚ የሰውነት ሙቀት መኖሩ ከእሳት መፈጠሩ ይታወቃል
ውኃ፡-ከሰውነት ብዙ ውኃ መኖሩ፣ መለስለሱ ከውኃ መፈጠሩ በዚህ ይታወቃል
መሬት፡- ሰው በሕይወት ሳለ መጠንከሩ፣ ሲሞት መበስበሱ፣ የመሬት ጠባያትን መያዙ ከመሬት
እንደተፈጠረ ይገልጻል (ዘፍ. 3፡19)
ማቴ. 15፡20
‹‹የዘመኖቻችን ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፡፡›› (መዝ. 89፡10) ይህን ዕድሜ አራቱ
ባሕርያት እኩል ይካፈሉታል፡፡ አራቱም በአንድነት ቢዘልቁም በተለየ መልኩ ጎልተው የሚታዩት ሃያ ሃያ
ዘመን አላቸው፡፡
ከ 0-20 ዓመት የነፋስ ባሕርይ- ዘመነ ነፋስ ይባላል፡፡ ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳል፡፡ ሕጻናት
እንደመሰላቸው ሽው ሽው ይላሉ፡፡ ዮሐ. 3፡8፡፡ ነፋስ ምንም እንደማያሳይ ሁሉ በምግበ ነፋስ ያሉ
ሕጻናትም ብዙ የሚያስተውሉት ነገር የለም፡፡ ዐለዋቂነት ያጠቃቸዋል፡፡ የያዙትን ውድ ነገር
(ሃይማኖት፣ ድንግልና...) ዋጋ ለሌለው ብልጭልጭ፣ ገንዘብ ወዘተ ነገር ለመለወጥ በቀላሉ
ይታለላሉ፡፡ ኤፌ. 4፡14፡፡ እስኪ ቆም ብለን የኛን ሕይወት እናስብ በዚህ እድሜ ያጣናቸው ነገሮች
የሉም ወይ?
ከ 20-40 ዓመት የእሳት ባሕርይ- ዘመነ እሳት ይባላል፡፡ ወጣት የሚያሰኘው ይህ ነው፡፡ ‹‹ፋይር
ኤጅ›› የሚባለው ከቤተ ክርስቲያን የተገኘ ነው፡፡ እሳት ብሩህ እንደሆነ ሁሉ ወጣቶችም ክፉ እና
ደጉን የሚያስለይ የእውቀት ብርሃን አላቸው፡፡ ሆኖም እሳት ያገኘውን ልብላ (ላቃጥል) እንደሚል
ወጣቶችም ሁሉ የሚያምራቸው እና ትምክህተኞች ናቸው፡፡
ከ 40-60 ዓመት የውኃ ባሕርይ- ዘመነ ማይ ይባላል፡፡ ብሩህነት ቀዝቃዛነት የውኃ ጠባይ እንደሆነ
ሁሉ በዚህ እድሜ የደረሱ ሰዎችም በነገሮች ሁሉ ረጋ ማለትን ማስተዋልን ይጀምራሉ፤ የወጣትነት
ዘመናቸውን ወደ ኋላ እየተመለሱ በግርምት ይመለከቱታል፡፡
ከ 60-80 ዓመት የመሬት ባሕርይ ዘመነ አፈር ይባላል፡፡ ደረቅነት፣ ጨለማነት፣ ቀዝቃዛነት የመሬት
ጠባይ እንደሆነ ሁሉ በዚህ እድሜ የደረሱ ሰዎች ለነገሮች ግትርነት፣ የሚያማርሩ፣ የሚያዝኑ፣
ለትንሽ ነገር የሚከፉ፣ ሞት ሞት የሚሸታቸው፣ ፍቅረ ንዋይን አጥብቀው የሚወዱ ወዘተ ናቸው፡፡
እድሜያቸው ለዚህ የደረሱ ሰዎች ለሀብት ሲጨነቁ አላያችሁም? አቅም ስለሌላቸው ገንዘብን ለሁሉ
ነገራቸው መሠረት አድርገው ስለሚያስቡ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የእድሜ ክልል ዓመቱን ጠብቆ ይከሰታል ማለት አይደለም ነገር ግን በመካከላቸው
ጦርነት ስላለ አንዱ ያለ ጊዜው ሊከሰት ሌላው ደግሞ ሊዘገይ ይችላል፡፡ የወጣትነት እድሜ ከ 20 ዓመት
ቀድሞ ሊጀምርም ይችላል ልክ እንደዛሬው ዘመን፡፡ ዘመኑ ክፉ ነውና እናስተውል፡፡
ስለ አራቱ ባሕርያት መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ ስነ ፍጥረት እና ሌሎችንም ያንብቡ፡፡
ዖዝያን የአስራ ስድስት ዓመት ሆኖ ሳለ ጎልማሳ (ወጣት) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ (2 ዜና. 26፡1)፡፡ ጎልማሳነት
ደግሞ እስከ አርባ ዓመት ሊቆይ እንደሚችል ‹‹ኢዮሳፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ አምስት ዓመት
ጎልማሳ ነበር፡፡ (2 ዜና. 20፡31)

[Type text] Page 3


ወጣቶች በመልካም አኗኗር ከኖሩ የ‹‹ልጅ አዋቂ›› ይባላሉ፡፡ ከፈቀዱ አረጋዊ መሆንና አረጋዊ ከደረሰበት
ፀጋ እና ክብር መድረስ ይችላሉ፡፡ የወጣት ሥራ የሚሰሩ ሽማግሌዎች እንዳሉ ሁሉ የሽማግሌ ሥራ የሚሰሩ
ወጣቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ወጣት ሆነው የሚያስታርቁ... (ተግ.ዘዮሐ.አፈ. 7)
አረጋዊ ዮሴፍ ሽማግሌ ሲሆን ድንግል ማርያምን ለመጠበቅ ተመርጧል፡፡ ወጣቱ ወንጌላዊ ዮሐንስም በቅቶ
ስለተገኘ ለአረጋዊ ዮሴፍ የተሰጠችውን ድንግል ማርያምን ከመስቀሉ ሥር በመገኘት በአደራ ተቀብሏል፡፡
ይህ የሆነው ፀጋን ለመቀበል በቅቶ መገኘት እንጂ እድሜ ወሳኝ አለመሆኑን ያስረዳል፡፡ ጸጋ እግዚአብሔር
በእድሜ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ድንግል ማርያም ትንሽ ብላቴና ሆና ሳለች ጸጋን የተመላች ተባለች፡፡ ወጣቶች
ከአረጋዊያን ሊበልጡ ይችላሉ፡፡ ‹‹መከበር በዘመን ብዛት አይደለም›› ጠቢቢ ሶሎሞን ‹‹ጥበብን
የሚያውቃት እድሜ የጠገበ አይደለም›› ይላልና፡፡
ጥሩ ወጣት መሆን ያስፈልጋል፤ ካልሆነም ብዙ ነገር ይታጣል፡፡ ለሌሎች ምሳሌ መሆን ይሳነናል፡፡
ሽማግሌው እንደ ወጣት ሊሆን ቢል ከቅጣት እንደማያመልጥ ሁሉ ወጣቶችም ሕግ ሲያፈርሱ የሚነቀፉበት
ብዙ ነገር አለ፡፡ ሽማግሌ በፍቅረ ንዋይ ቢፈተን እርጅናው ስለመጣበት ደክሞ የሚረዳው ይሻልና ገንዘብ
ካለኝ በገንዘቤ እጦራለሁ ብሎ ነው ይባላል፡፡ ወጣቶች ደግሞ ወጥተው ወርደው እራሳቸውን መርዳት
ስለሚችሉ በፍቅረ ንዋይ ቢያዙ ይነቀፋሉ፡፡ ዛሬ ስራ ትተው የሚሰርቁ፣ የሚዘርፉ፣ ሙስናው ወዘተ ምንጩ
ይህ እኮ ነው፡፡በዚህም ብቻ ሳይሆን ንጽሕናቸውን ባለመጠበቃቸው ፣ በሰካራምነታቸው፣ በስንፍናቸው እና
በመሳሰሉት መጥፎ ስራቸው ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ንጽሕናን ጠብቀን ለመኖር አንችልም እንዳይሉ
ንጽሕናን ለመጠበቅ ያላቸውን አጋዥ ኃይል መመልከት በተገባቸው ነበር፡፡ ወጣቶች አረጋዊያን የሌላቸው
ኃይለ ስጋ ስላላቸው ፍትወትን ለማሸነፍ ሲሉ መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ እና መጻሕፍትን መመልከት
ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመጠየቅም የተለያዩ ቅዱሳን ቦታዎችን በመሄድ በረከት ማግኘት
ይችላሉ ምክንያቱም ከቅዱሳን ቦታዎች የቅዱሳንን በረከት በቀላሉ ማግኘት ይቻላልና፡፡

ክፍል ሁለት
[Type text] Page 4
ምዕራፍ ሁለት
ወጣቶች እና ፈተናዎቻቸው
የወጣቶች ምኞት
በወጣትነት ዘመን አካላት እንደሚደራጁ እና አእምሮአቸው እንደሚዳብር ሁሉ ምኞታቸውም በዓይነት እና
በመጠን እየሰፋ እና እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህም በአመዛኙ ከመንፈሳዊነት ጋር የሚቃረን እና ሥጋዊ
በመሆኑ ‹‹እኩይ ፍትወት›› ይባላል፡፡ 2 ጢሞ. 2፡22 ‹‹አንተ ግን ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ሽሽ
በንጽሕናም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል፡፡›› እንዳለ ቅዱስ
ጳውሎስ፡፡ ወጣትነት የሚሠሩበት ዘመን እንጂ የሚመኙበት ዘመን አይደለም፡፡ እኛም ወጣቶች ምኞታችንን
ወደ ጎን በመተው የሥራ ሰዎች ልንሆን ያስፈልጋል፡፡ያለ ሥራ ምኞት የሚደረስበት አይደለም፡፡ ያዕ. 1፡13
ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና፤ እርሱ ራሱስ
ማንንም አይፈትንም ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብ እና ሲታለል ይፈተናል፡፡ ይህም ምኞት ወደ
ጥፋት የሚስብ የሚጎትት እና የሚያታልል ነው፡፡ ‹‹በገዛ ምኞት ሲሳብ›› ማለት ምኞት ከፍተኛ ጉልበት
እንዳለው ይጠቁማል፡፡በወጣትነት ዘመን ምንም አእምሮ የበሰለ ቢሆን ከዚያ የሚበረታው ግን ምኞት
ነው፡፡ ከወጣቶች እውቀት ይልቅ ምኞታቸው መበርታቱን ለማስረዳት ወጣቶች በዘመነ ኦሪት ይመሰላሉ፡፡
ሕገ ልቡና እንደመሰለው መኖር ሕግ ኦሪት የሰው ባሕርይ በኃጢአት የጎሰቆለ ስለነበር ሕጉን ፈጽመው
ለመጽደቅ አልተቻለም ነበር፡፡ ወጣቶችም እውቀታቸው እየጨመረ ቢመጣም ምኞታቸውም የዚያኑ ያህል
ስለሚበረታና ስለሚስባቸው እውቀታቸውን ተጠቅመው የሚያጽደቃቸውን ጎዳና ለመከተል ይቸገራሉ፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ. 7፡23 ‹‹በብልቶቹ ውስጥ ያለው ይህ የኀጢአት ሕግ (ምኞት) ወደ እርሱ ማረከኝ
ተበረታታብኝ›› ሊቁ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጎልማሶች ያረጋጉሽ
አይደለም የሰማይ መላእክት ጎበኙሽ እንጂ›› ብሎ ወጣቶች በምኞታቸው ተሸንግለው ሌላውን ለማታለል
እንደሚያባብሉ ይናገራል፡፡
ምኞት በውስጣችን እንዲኖር እና እንዲያድግብን የምንከባከበው ነገር መሆን የለበትም፡፡ ምኞት ተስፋ
አይደለምና፡፡ ጠቢቡ ሶሎሞን በምሳ. 21፡26 ‹‹ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፡፡›› ይላል፡፡ምኞት
አስደሳች እና ጣፋጭ ነገር ትመስል ይሆናል ነገር ግን አይደለችም፡፡ ‹‹ምኞት ስሕተት እና ውድቀት ናት
እንጂ ጣፋጭ አይደለችም›› (ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡ ምኞትን ማብዛት ልፋትን ወይም ተስፋ መቁረጥን
ማብዛት ነው፡፡ምክንያቱም ምኞትን ለማሳካት ብዙ መድከም ከማስፈለጉም በላይ ብዙ ምኞት ካልተሳካ
የሚያስከትለው ተስፋ መቁረጥም እንደዚሁ ይሆናል፡፡ ብዙ ወጣቶች የሚመኙት ጉዳት የሚያስከትልባቸው
እና ከጥቂት ጊዜ በኋላ በብርቱ የሚያስቀጣቸውን ነገር ነው፡፡የሚገርመው ግን ጓጉተው የሚፈልጉት እንጂ
ሲያገኙት ወዲያው የሚሰለቹት ወይም የሚጸጸቱበት ነው፡፡
ፈጣሪን ሳይጠጉ ምንም ነገር አርኪ እና በቂ መሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ መመኘት እና ለማግኘት ብቻ
ሳይሆን አስቀድመን ፈጣሪን መጠጋት ይኖርብናል፡፡ በወጣትነት የሚከሰት ምኞት አንድ ብቻ አይደለም፡፡
ወጣቶች ሁሉም ስለሚያምራቸው በአንድ መርጋት አይሆንላቸውም፡፡ተምሮ በመአረግ መመረቅ፣ አጭቶ
ማግባት፣ ሀብታም ነጋዴ መሆን፣ትልቅ ባለሥልጣን መሆን ተራ ጠብቀው ብታሰቡ የሚሳኩ ይሆናሉ
ካልሆነ ግን ‹‹ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ›› ይሆንብናል፡፡ ስለዚህ ወጣቶች አንድን ነገር መጀመር
ሳይሆን በእርጋታ ሆኖ እስከ መጨረሻ መፈጸም አለባቸው፡፡ ወጣቶች ምኞቶቻቸው ብዙ ከመሆናቸው
[Type text] Page 5
የተነሳ ሁለት የማይጣጣሙ ነገሮችን የሚመኙበት ጊዜ አለ፡፡ ሙሽራ ሲያዩ ማግባት እና መውለድን
ይመኙና በዚያው ቀን ደግሞ ልቡናቸው በመንፈሳዊ ነገር ተነክቶ መመንኮስ እና መመነን የሚመኙበት ጊዜ
አለ፡፡ ይህ ደግሞ በአንድ ሰው መፈጸም ስለማይቻል መታወክ ነው፡፡ ብንታገሥ ግን ከጊዜ ብዛት ራሱ
ይርቃል፡፡ ማቴ. 7፡25 ‹‹ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንንም ቤት ገፋው በዐለት ላይም
ስለተመሠረተ አልወደቀም፡፡›› በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል፡-
ቤት የወጣትነት ሕይወት ነው፡፡
ነፋስ ነፈሰ ማለት የአጋንንት ፈተና በወጣቱ ላይ ተነሳበት እና ከሴት ርቆ ንጽሕናውን ጠብቆ እንደ
እንጦንስ እና እንደ መቃርስ ለመኖር እንዲመኝ አደረገው ማለት ነው፡፡
ዝናብም ወረደ ማለት ያንኑ ወጣት እንደ እንጦንስ እና መቃርስ መኖር አይቻለኝም ባይሆን እንደ
ኢዮብ እና አብርሐም አግብቼ ልጆች ወልጄ በሕግ ሊኑር አሰኘው ማለት ነው፡፡
ጎርፍም ጎረፈ ማለት በመጨረሻ ተስፋ በመቁረጥ ሁሉንም አልችልም እስኪል ድረስ አደረሰው
ማለት ነው፡፡ዐለት የተባለው ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ወጣቶች ከፈቀዱ በእግዚአብሔር ቃል
ላይ መመስረት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕጉ ከውስጣቸው እንዳይጠፋ ማድረግ ይችላሉ፡፡
1 ዮሐ. 2፡14 ‹‹የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖር...›› ፡፡
በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስትምህሮ መሠረት ምእመናን በአምስት መደብ ይመደባሉ፡፡ ይህም መደብ
‹‹ጾታ ምእመናን›› ይባላል፡፡ እነዚህም
ካህናት
መነኮሳት
አዕሩግ (አረጋዊያን)
ወራዙት (ወንድ ወጣቶች)
አንስት ወጣቶች
እነዚህ አምስቱ የጾታ መደቦች በዐብይ ፈተና ይፈተናሉ፡፡
የካህናት ፈተናቸው ትዝኅርት (ትዕቢት)
የመነኮሳት ስስት
የአረጋዊያን ፍቅረ ንዋይ
የወጣቶች ዝሙት
የወጣት ሴት ፈተና ደግሞ ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥ)
ዮሐ. 5፡4 (ትርጓሜ) ይህ ማለት ግን ዋና ዋና ፈተናቸውን አንጓሎ መናገር ነው እንጂ እያንዳንዱ ጾታ
ምእመን የሚፈተነው በአንድ ነገር ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ በር የሚከፍቱ እና ለምእመኑ ረቂቅ
እና ከባድ ስለሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ካህኑ ሰማያዊ ስልጣን ስላለው ሲተብት ትዕቢተኛ መሆኑን ለራሱ
አያውቅም ሌሎችም እንዲሁ አያስተውሉትም፡፡ ሰውነቱ በደዌ የተጠቃ ሰው ጉንፋን እንኳን
አንደሚያይልበት እንዲሁ በዋና ፈተናው ድል የተደረገ ምእመን ሌሎች ጥቃቅን ፈተናዎች ይረባረቡበታል፡፡
ነገር ግን ዋናውን ፈተና ድል ካደረገ የሚመጡበትን ሌሎች ፈተናዎች በቀላሉ ድል ለማድረግ ይቻለዋል፡፡
ወጣቶች እድሜያቸው እየገፋ በመጣ ቁጥር ወጣትነታቸው ሲያልፍ የወጣትነት ፈተናቸውም አብሮ

[Type text] Page 6


እንደሚያልፍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈቀርቅ ‹‹በወጣትነት ወራት ደዌ ኀጢአት ትያዛለች... ከእርጅና ወራት
በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋ ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል››ይላል፡፡
2. የወጣትነት ምልክቶች
ብዙ የአካል ለውጥ ይታያል፡፡ ቀጭን ድምጽ (ሴት)፣ ጎርናና ድምጽ (ወንድ)፣ የአዳም ፍሬ የሚባለው
ማንቁርት ማደግ፣ ብጉር፣ በተለያዩ አካላት ፀጉር ማብቀል፣ ከራስ እስከ ጽሕም በግራ እና በቀኝ የሚወርድ
ለጊዜው ለስለስ ያለ እና ስስ ጠጉር ወይም ሪዝ ማቆጥቆጥ ይጀምራል፡፡ ይህን ፂሕም መከርከም እና መቀነስ
እንጂ ሴት እስኪመስሉ ድረስ ሙሉ በሙሉ ንጭት አድርጎ ማንሳት የሚገባ አይደለም፡፡ ለዚህም ‹‹ነገር ግን
ፂሕማችንን ላንላጭ የወንድ መልካችንን ወደ ሌላ ማለትም ሴት ወደ መምሰል እንለውጥ ዘንድ አይገባም››
(ዲዲስቅልያ. አንቀጽ 1፣ ፍት.መን. አን.11)፡፡ ሌሎች የአፍላ የጉልምስና ምልክቶች ደግሞ የሰውነት ጠረን
መለወጥ፣ የዘር ፍሰት ወይም ሕልመ ሌሊት ማየት መጀመር ናቸው፡፡
ሕልመ ሌሊት
ለዘር የበቁ ወጣቶች ዘር የሚከፍሉት ወይም የሚወጣቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ግን
ተኝተው ሳለ በጠለቀ እንቅልፍ ሆነው ሕልም በሚያልሙበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ሲሆን እንደ ጤናማ
የተፈጥሮ ሂደት ይቆጠራል፡፡ ይህ ባልጠበቁት ጊዜ ስከሰት በጣም ሊረብሻቸው ይችላል፡፡ ለዚህም ግንዛቤ
እንዲያገኙ እና አንደ አስደሳች ተግባር በመውሰድ እያወቁ ዘራቸውን በራሳቸው እጅ ማፍሰስ እንዳይጀምሩ
የእነ አውነን በዚህ ተግባራቸው መቀሠፍ እየጠቀሱ ኃጢአትነቱን አጥብቆ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘሌ. 15፡16 ‹‹የማንም ዘር ከእርሱ ቢወጣ ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል
እስከ ማታም ርኩስ ነው ዘር የነካ ልብስ ሁሉ ቁርበትም ሁሉ በውኃ ይታጠባል እስከ ማታም ድረስ ርኩስ
ነው፡፡››
ክፍል ሦስት
 ሕልመ ሌሊት ኃጢአት ነውን?
ሕልመ ሌሊት እንደ ኃጢአት እንዲቆጠር እና እንዳይቆጠር የሚያደርጉ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አጋንንት
የሰውን ልጅ በተኛበት ክፉ ክፉ ሕልም በማሳየት ይፈትኑታል፡፡ የዝሙት መልእክት ያላቸውን በሕልም
ያሳዩታል፡፡ ለምሳሌ የተራቆተች ሴት ገላ፣ እንደ ወንድ እና ሴት አለሌ ወዘተ...፡፡ በዚህ መልኩ የተከሰተ
ሕልመ ሌሊት ክፉ ሕልም ይባላል፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት ‹‹ሠይጣናት የሰውን ልጅ ቀን ቀን ክፉ ሀሳብ
በማሳሰብ እና በማሠራት በሌሊት ደግሞ ዝሙት የሞላበትን አስጸያፊ ሕልም በማሳየት ይዋጉታል፡፡››
ይላል፡፡ በዚህ መልኩ ሰይጣናት ያቀረቡለትን ረቂቅ ፈተና ከመቃወም ይልቅ ደስ እያለው የሚያጣጥም
ማለትም ከመጸጸት እና ከመቆጨት ይልቅ በደስታ ስለ ዝሙት የሚያሰላስል፣ የሚዳራ፣ የሚዘል፣ ወደ
ዝሙት ከሚያመሩ ማናቸውም ነገሮች የማይሸሽ ሰው እነዚህ ነቅቶ ሳለ ያልተቃወማቸውን ተግባራት
በሕልሙ በሚፈጽማቸው ጊዜ በተግባር እንደፈጸማቸው ያህል ኃጢአት ሆነው ይቆጠሩበታል፡፡ የህንንም
መጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ በማለት ይገልጸዋል ‹‹በቀን ነቅቶ ሳለ ኃጢአትን ወዶ የሚቀበልና ገልጾ
የማይናዘዛት ለዚያ ሰው የረከሰች ሀሳቡ፣ ሕልሙ፣ ኃጢአት ሆን ትቆጠርበታለች››፡፡

[Type text] Page 7


ከሥራ ብዛት ሕልም ይታያል (መክ. 5፡3)፡፡ እንዲሁም ከምኞት ብዛትም ሕልም ሊከሠት ይችላል፡፡ ክፉ
ምኞት በሕልምም ቢሆን ማርከሱ አይቀርም፡፡ ይሁ 1፡8 ‹‹እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ››
ነፍስ እንደ ሥጋ አትተኛም እንቅልፍም በእርሷ ዘንድ የለም፡፡ ስለዚህ ነፍስ በእንቅልፍ ልቤ ነው በማለት
ማመከኘት አትችልም፡፡ ነፍስ ከረከሠ ሕልም ምክንያት ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የምትችለው ሥጋ
ከእንቅልፍ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ተግባረ ዝሙትን በመቃወምና በመጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መሆኗን
ስተመሰክር ብቻ ነው፡፡
ሌላው ሕልመ ሌሊት እንደ ኃጢአት የሚያስቆጥረው ሁኔታ አብዝቶ መመገብ ነው፡፡ ጾም ለጽድቅ ሁሉ
መሠረት እንደሆነ እንደዚሁ አብዝቶ መመገብ የኃጢአት ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ሰው ሁሉ ለቁመተ ሥጋ
ያህል መመገብ ያሸዋል፡፡ መዝ. 103፡15 ‹‹እህልም ጉልበትን ያጠነክራል›› ነገር ግን በልክ መሆን አለበት፤
ራሳችንን መግዛት ያስፈልጋል፡፡ አብዝቶ መመገብ ነፍስን ለሥጋ ማስገዛት ነው፤ሰውነትንም እንደ ማምለክ
ይቆጠራል፡፡ ሲወጣ ሲገባ ስለ ምግብ ብቻ የሚያስብ፣ ስለ ምግብ ዓይነት የሚያወራ አይታችሁ አታውቁም፤
ለሆድ መገዛት ስንጀምር ነፍስን ማስራብ ይመጣል ያን ጊዜ ደግሞ የኃጢአት ባሪያ እንሆናለን፤ የወጣትነት
ጾሮች በተለይ ዝሙት በኛ ላይ ይሰለጥናል፡፡
ወጣቶች ይልቁኑም በዝሙት ሥራና ሀሳብ የሚፈተኑ ሰዎች በሚገባ መጾም አለባቸው፡፡ ካልሆነ ክር ላይ
ሰም እንደመጨመር ነው፡፡ አብዝቶ መመገብ ከወጣትነት ጋር የኃጢአት ሐሳቡን በግድ እንዲመጣ
ያደርጋሉ›› (ማር.ይስ.አን.20 ምዕ. 1)፡፡ አብዝቶ መመገብ እና ለመብል መሳሳት የኃጢአት ምንጭ
ከመሆናቸው ባሻገር በራሳቸው ኃጢአት ሆነው ይቆጠራሉ፡፡ ሕዝ. 16፡49 ‹‹አነሆ የእህትሽ የሰዶም
ኃጢአት ይህ ነበረ ትዕቢት፣ እንጀራ መጥገብ፣ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆቿ ነበረ፡፡››
ሰይጠነቀቅ ቀርቶ አብዝቶ ከመመገቡ የተነሳ ሕልመ ሌሊት ያገኘው ሰው እንደ ኃጢአት ይታሰብበታል፡፡
ምክንያቱም አብዝቶ መመገብ ኃጢአትን እንደሚወልድ እያወቀ ችላ ብሎ በመመገቡ ነው፡፡
‹‹ከሰውነት እንደ ምንጭ የሚነቃ ርኩስ ዘር በዝቶ ስለ ፈሰሰ ጎስቋላ ምንጣፍ፣ ልብሱ፣ በዝሙት ደስ የተሰኘ
እና ሥጋው ሁለንተናው የረከሰ ነው ሥጋ ሁል ጊዜ ያነቃዋልና ዘሩ በሚፈሰው በሌሊት ብቻ አይደለም፡፡
ሕሊናውንም ያረክሰዋል›› ማለት ነው፡፡ (ማር.ይስ. አን. 20)
አንድ ሰው በንቁ ልቡና ሳለ ወደ ኃጢአት የሚያመሩትን ነገሮች ተግቶ እየተቃወመ ነገር ግን በተኛ እና
ባንቀላፋ ጊዜ ዝንየት ቢያገኘው በተራክቦ ዘር በማፍሰስ ያያት ሕልሙ ዕዳ ሆና አትቆጠርበትም፡፡ ኃጢአት
ከልቡ በሚቃወምና ሰው ላይ ሕልመ ሌሊት እንደ ኃጢአት አትቆጠርበትም፡፡ ይህን ለማስረዳት አረጋዊ
በፊልክሲዩስ መጽሐፍ እንዲህ የሚል ሐተታ አስፍሯል፡፡‹‹ሰይጣን ጌታችንን የኔን ወገኖች አጋንንት ባንተ
ወገኖች ላይ አሰለጥናቸዋለው፣ ነገር ግን ወገኖቼ የአንተን አይችሏቸውምና ድል ይሆናሉ፡፡ እነርሱ ምንም
ባይችሏቸው እኔ ግን በሕልመ ሌሊት አስታቸዋለሁ፡፡›› አለው ጌታችንም ‹‹ጭንጋፍ አባቱን ለመውረስ
ከቻለ ሕልመ ሌሊት ወገኖቼ ላይ ዕዳ ሆና ትቆጠርባቸዋለች፡፡›› ጭንጋፍ አባቱን መስሎና አህሎ ባለመገኘቱ
የአባቱ የሆነውን ነገር መውረስ እንደማይቻለው እንደዚሁም በተግባር ያልተፈጸመች ሕልመ ሌሊት እንደ
ተግባር ኃጢአት ተቆጥራ አታስኮንንም ማለት ነው፡፡ እስከ አሁን በተነሳው መሠረት አንድ ሰው ያየው
ሕልመ ሌሊት ኃጢአት መሆኑን እና አለመሆኑን ማወቅ ይችላል፡፡ በርሱ ላይ የሚፈርድ ግን ኃጢአት
ይሰራሉ፡፡

[Type text] Page 8


ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) እና መንፈሳዊ ሥርዓቱ
በሕልመ ሌሊት የተመታ ሰው በዝያው ዕለት ሥጋወደሙ መቀበል አይችልም፡፡ ወደ ቤተ መቅደስም
መግባት አይችልም፡፡ ልብሱን ካጠበ ወይም ከቀየረና ገላውን ከታጠበ በኋላ በማግስቱ መግባት ይችላል፡፡
በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ግን ጸሎት፣ ትምህርትና የመሳሰሉት መንፈሳዊ ተግባራት በዕለቱም ቢሆን
ሊያከናውን ይችላል፡፡ (ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ላይ ያለውን ታሪክ ያስታውሱ)፡፡ ቤተ መቅደስ ውስጥ
መተኛት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ የሌሊት መርሐግብር ሲኖር ከአዋቂዎች ጀምሮ እስከ ተራ
ምእመን ድረስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ስንተኛ እናያለን፤ መተኛት ከሆነ ቤታችን መተኛቱ ይሻላል፡፡ በዚህ
ጊዜ አጋንንት በሕልመ ሌሊት እንዲመቱ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ
የምታገኘውን ፀጋ ሥርዓቷን ለማክበር ብለህ ቤተ መቅደስ አፍአ (በውጭ) ብትቆምም አታጣውምና፡፡
ስለዚህ ከልማድ እንራቅ አብረን ዋዜማ፣ ወይም ቅዳሴ የሄነው ጓደኛችን ከሕልመ ሌሊት ነጻ ሆኖ እኛ ግን
ነጻ ካልሆን ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲናችን ሥርዓቷ ማርኮህ ውስጥ ለመግባት ብትከጅል፤ ከጓደኛህም
በመቅረትህ ቢሰማህም ተው ይቅርብህ የመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት አይደለም ሥረዓቷን አክብር፣ ዛሬ
ሥርዓቷን ካላከበርክ ነጌ ደግሞ ዶግማዋን በቀላሉ ትጥሳለህ፣ ወይም የልማድ ክርስቲያን ሆነህ ትቀራለህ፡፡
ዛሬ መናፍቃን እና ተሀድሶ መናፍቃን መነሻቸው ይህ እኮ ነው፡፡ ሰይጣን ሰዎች ቤተ ክርስቲያን እንዳይመጡ
ማድረግ ስራው ነው፣ ከሄዱ በኋላ ግን እንዳይጠቀሙ ለማድረግ ሥርዓቷን እንዲጥሱ አምላካቸው
እንዲያዝንባቸው፣ በመላእክት እንዲቀሰፉ እና በመጨረሻም ዶግማዋን ችላ እንዲሉ ያደርጋል፡፡ ሃይማኖት
አለኝ የሚለውን ባለቤቱ ሳያውቅ ሃይማኖት አልባ ማድረግ ነው፡፡ ዛሬ ተሀድሶዎች ያደረጉት ይህንን ነው፡፡
ስለ ስርዓት ስያስተምሩ ችግር የለውም እያሉ ሕዝቡን አደንዝዘውታል፡፡ ብናስተውል ዛሬ እኮ ሃይማኖት
ያለው ሰው አታገኙም ደንዝዘናል፡፡
ሌላው ደግሞ በቤትህ እንኳን ተኝተህ ብታድር ተኝተህ ባደርክበት ልብስ ወደ ቤተ ክርስቲያን አትሂድ፡፡
ምክንያቱም አንተ ሳታውቅ ፈሳሽ ከሰውነትህ ወጥቶ ይሆናል፤ እንዲህም ለሕልመ ሌሊትም ተጋልጠህ
ይሆናልና፡፡ ***ሩካቤ ያደረጉ ባልና ሚስት መተጣጠብን ምክንያት በማድረግ ከመጸለይ ወደ ኋላ ማለት
የለባቸውም፡፡ ሩካቤያቸው ንጹሕ ስለሆነ መላ አካላችንን ካልታጠብን አንጸልይም አይበሉ፡፡ ለባልና ሚስት
ዘር የወጣበትና የነጠበበትን አካል ማለት ኃፍረተ ሥጋቸውን ብቻ መታጠብ ይበቃቸዋል፡፡
የሕልመ ሌሊት መፍትሔ
ብዙ ሰዎች ተግቶ ለመጸለይ፣ ለማስቀደስ፣ሱባኤ ላይ እያሉ፣ለመቁረብ በወሰኑ ጊዜ ሕልመ ሌሊት እንቅፋት
እየሆነ ይፈተኑበታል፡፡ በእርግጥ መብላት መጠጣት ሳያቆሙ ሙሉ ለሙሉ ከሕልመ ሌሊት መለየት
አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገር አይደለም፡፡ በተአምራት ግን በተአምረ ማርያም ላይ ተጽፎ
እናገኛለን፡፡ ያንን አናንብብ/እንስማ፡፡ እንግዲህ መፍትሔዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
 አባ ኢሳይያስ እንዲህ ይላሉ‹‹ሌሊት በሕልም ከሴት ጋር የተገኛህ መስሎህ ዘር ቢወርዲህ በመዓልት
አታስባት-በደስታ መላልሳ አታስባት፡፡
 ሕልመ ሌሊት በምታይበት ጊዜ ከነቃህ ቸል ብለህ ተመልሰህ አትተኛ ፈጥነህ ተነሥ ታጥበህ ጸሎት
አድርስ፡፡ ከተቻለ ስገድ ባይቻልህ ግን የባሕርይህን ድካም ፈጣሪህ ያውቀዋልና ይቅር በለኝ፣

[Type text] Page 9


እርዳኝ፣ አድነኝ፣ እያልክ ወደ እግዚአብሔር ለምን፡፡ እንዲህ በማድረግህ የሰይጣንን መንገድ
ትዘጋበታለህ፡፤

 ውኃ በብዛት አለመጠጣት ፍልክ. ክፍል 3 ‹‹እንደ ውኃ ጥም አካልን የሚደርቅ ከሕልመ ሌሊትና


ከዘር መፍሰስ የሚከላከል፣ በመዓልት ሐልዮ፣ ኃጢአትን የሚያጠፋ የለም፡፡›› ውኃ ሰውነትን
ያለሰልሳል፣ በውስጣችን ያለው እሳት ደግሞ ያፈለዋል ያን ጊዜ ዘርን ያነቃቃል ስሜታችንም
ያይላል፡፡
ማቴ. 12፡43-45 ‹‹ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤
አያገኝም፡፡ በዚያን ጊዜ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል-ሲመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ
ያገኘዋል፡፡›› ሰይጣን ከሚጾም ሰው ርቆ ይሄዳል፡፡
 በሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ እንዳትጠቃ ወደ ዝሙት ከሚያመራ ማናቸውም ነገር ሽሽ፡፡ በመሸ
ጊዜ የምታያቸውን ፊልሞች፣ ንባቦች፣ ሌሎችንም ነገሮች በጥንቃቄ መርምረህ ለፍትወት
የሚያጋልጡትን ሽሻቸው፡፡ ከዚያ ይልቅ ደጋግ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለማንበብ መትጋት
ያስፈልጋል፡፡(ኤር 51፡6፣ 1 ቆሮ 6፡18 10፡14 ፣ መዝ 37፡27 ፤ 2 ጢሞ 2፡22 ፤ ማቴ 10፡23 ፤
1 ጢሞ 6፡11)
 ከመኝታ በፊት ጠግቦ ላለመብላት ሞክር፡፡ ትኩስና የሞቁ ነገሮችን ላለመውሰድ መጣር፡፡ እንዲህ
ከሆነ ‹‹በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም››
 ከመንፈሳዊ መምህራንና ከአበው ካህናት ጋር እየተማከሩ በሚያቀርቡት የመፍትሔ ሀሳብ መጓዝ
ነው፡፡ ነገር ግን ከበሳል ሰው ጋር መሆን አለበት፡፡ (ፍልክ. ክፍ. 7)
 በቀንና ሌሊት ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ፡፡ ‹‹አጋንንት በሚዋጉበት ጊዜ ልቡናውን ያነፃ ያን ጊዜ በቀን
ንጽሕና የረጋ ሀሳብን በሌሊት ደግሞ ንጽሕና ጥርት ያለ ሕልምን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል››
(መጽሐፈ መነኮሳት)
 ከመኝታህ በፊት መጸለይ ያው የተለመደ ነው በሚል ማብራሪያ አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ከሰባቱ
የጸሎት ጊዜያት ውስጥ አንዱ የመኝታ ጊዜ ጸሎት ነውና፡፡ ስለዚህ ዝም ብለህ አትተኛ፡፡ ‹‹በሰላም
አሳድረኝ›› ማለት ከሕልመ ሌሊትም ለመትረፍ የሚረዳ ጸሎት ነውና፡፡
***ከዚህ ውጭ አንዳንድ ባህታውያንና መሪጌታ ተብዮዎች በተለያዩ መንገዶች መፍትሔ እያሉ ወጣቱን
በሰይጣን ሲያቆራኙ ይታያሉና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

[Type text] Page 10


ክፍል አራት
ግብረ አውናን
ሕልመ ሌሊት ወጣቶች በጠለቀ እንቅልፍ ላይ ሳሉ በሚያልሙበት ጊዜ ስለሚከሰት የ‹‹ፈሳሽ ነገር››
ከሰውነት መውጣት ነው፡፡ ነገር ግን በወጣትነት ወራት ስለ አባለ ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና
ለተቃራኒ ጾታ የሚኖር ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ከእንቅልፍ ውጭ ንቁ በሆኑበት ሰዓት በስሜት
እስኪረኩ ድረስ የጾታ ብልቶቻቸውን በመነካካትና በማሻሻት ለመደሰት የሚሞክሩ ወጣቶች አሉ፡፡ ይህ
ድርጊት በአብዛኛው በስውርና በግል ስለሚፈጸም በዚህ መጥፎ ልማድ የተለከፉት ወጣቶች መካሪ ሳያገኙ
ልማዳቸው አብሮአቸው ያድግና ለወደፊት ለኑሮአቸው ከባድ እንቅፋት ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር መላእክትን በተለያየ የምሕረት ግዴታዎች ቅዱሳን እንዳሉት ሁሉ በልዩ ልዩ መንገድ ሰውን
እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አግንንት አሉት፡፡ ከእነርሱም ውስጥ አንዱ ‹‹ሰይጣነ ዝሙት›› ነው፡፡
ሮሜ. 9፡22፡፡ ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትኑበት መንገድ ረቂቅና ልዩ ልዩ ነው፡፡ አንዳንዶች
የፈተና ስልቶች ፈጽሞ ከዝሙት ጋር ምንም ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም፡፡ ነገር ግን ላስተዋለ ቀጥተኛ
ዝምድና ያላቸው ናቸው፡፡አባቶቻችን ግን ይህን የሰይጣንን ሽንገላ በሕይወታቸው ስለተረዱት መንፈስ
ቅዱስም የገለጠላቸውን ጽፈውልን አልፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡ ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት
የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚሳብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው (መሻሻት፣
መነካካት፣ መዳበስ ማለት ነው)፡፡
ሕዝቅ. 23፡8 ‹‹ግልሙትናቸውን አፍሰውባት ነበር›› ማለት ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፉና
ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈጽሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ ነው፡፡ እንዲሁም በሕዝቅ. 23፡3 ‹‹የድንግልናዋን
ጡቶች ዳብሰው ነበር›› እንዲህ በማድረግ ጥሩ የእህትነት ወይም ወንድማዊ ቅርርቦሽ በማስመሰል እየተሻሹ
የወንድ ዘር ወይም የሴት ዘር የሚያፈሱ አሉ፡፡ ይህም በመኪና ውስጥ፣ በሰልፍ ላይ፣ ሰላምታ ስለዋወጡ...
ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡
 ወጣቶች ይህን የሚያደርጉት አስበውበት ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ልዩ ዘዴ በመፍጠር ምንም ሳያውቁና
በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገለባበጡና እያንኮራፉ በልዩ ልዩ
አጋጣሚ አጠገባቸው ለመተኛት የተገደደችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ፡፡ ይህ ያለ ሩካቤ የወንድ
ዘር የትም ከሚፈስባቸው ሕገ ወጥ መንገዶች አንዱ ነው፡፡
 ሌሎች ደግሞ በአድካሚ ጉዞ ወቅት ደጋፊ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ፣... ወዘተ እየመሰሉ
ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመዳበስ የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች
ውጫቸውን ላየ አዛኝ ሌላውን ለመርዳት የሚፋጠኑ ይመስላሉ፡፡ ይህ ችግሩ ወንዶች ይህን
በሚያደርጉበት ጊዜ ልባቸው በፍትወት እሳት እንደ ሰም እየቀለጠና አባለ ዘራቸው እየፈሰሰ መሆኑ
ነው፡፡ ሰውን ለመርዳት የሚፋጠኑትም ፍትወታቸው እስክትሟላላቸው ድረስ ብቻ ነው፡፡

[Type text] Page 11


 አንዳንዶች ደግሞ እነርሱ ለመነካካት ፈጽሞ እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ችግር አንደገፉ ወይም
እንዲገፋፉ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይጥራሉ፡፡ ይህ የሚሆነው በአብዛኛው ሕዝባዊ ስብሰባዎች
በሚደረጉባቸው ዕለትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው፡፡ ለምሳሌ በጥምቀት እና
መስቀል በዓላት፣ የተለያዩ የንግስ በዓላት ላይ፣ የሕዝብ አውቶብስ ላይ ይከሰታል፡፡ ስለዚህ
በአንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ላይ ከሌባ ብቻ ሳይሆን ሕዋሳትን ከሚዳብስ ሴሰኛም ራሳችን
ልንጠብቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ሌባ የራሱ ያልሆነውን የሰውን ገንዘብ ይሰርቃል ይህ ዓይነቱም
የራሱ ያልሆነውን የሰውን አካል ይነካካልና፡፡ ባሁኑ ጊዜ የሚነካካውም ሆነ የሚነካውም
የሚደሰትበት ዘመን ላይ ነን፡፡
 ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን ለማፍሰስ የመርካት ተግባር
የማይጠረጠሩ ዓይነት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ዕድሜያቸው በጣም የገፋ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ፣
አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች የሌሎችን
ሕዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት ‹‹ይህን አስበው አይደለም›› እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ
ይተረጎምላቸዋል፡፡ ነገር ግን ተው ይቅርብን እንደዚያ ዓይነት ነገር የለም፡፡
 ሌሎች ደግሞ በተለይ በሰንበት ትምህርት ቤት እና በግቢ ጉባኤያት ላይ የሚታየው ጥሩ እህት እና
ወንድም በመምሰል በሠላምታ ጊዜ ወጣ ያለ መተቃቀፍ፣ እጅ ለእጅ ተያይዞ መሄድ፣እጅ ትከሻ ላይ
መጫን እና ወገብ ይዞ መሄድ እና የመሳሰሉት ይታያሉ፡፡ ይህ ለጊዜው ክርስቲያናዊ ፍቅር
የሚመስል ነገር ግን በውስጡ ለፍትወት የሚውልበት ጊዜ ሰፊ ነው፡፡ የወንድ እና የሴት ሰውነት
ስነካካ ፍትወትን መቀስቀሱ አይቀርምና በገደብ እናድርገው፡፡ እውነተኛ ፍቅር በልባችን ካለ ብዙ
የፍቅር መገለጫዎች አሉና በእነዚያ እናድርግ፡፡ በግቢ ጉባኤያት እና ሰንበት ትምህርት ቤት ላይ
ሰው ወረተኛ የሚሆነው ለምን ይመስላችኋል? ገና እንደተለያየን የምንረሳሳው ለምን መሰላችሁ?
እስኪ ዝም ብላችሁ አስቡ መንገድ ለመንገድ ተቃቅፈን ስንጓዝ፣ አንገት ለአንገት ተቃቅፈን ሠላምታ
የምንለዋወጠው ለእውነተኛ ፍቅር ነው? መልሱን ለራሳችሁ ይሁን፡፡
 ሌሎች ደግሞ ታዳጊ ሕጻናት በማባለግ የወንድ ዘር ያፈሳሉ፡፡ በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕጻናትም
የእነዚህ ሰዎች ጥቃት ሰለባ ናቸው፡፡ ይህም ሕጻናቱን በመሳም (አፋቸው ውስጥ)፣ ሀፍረተ
ስጋቸውን በመዳበስ ወዘተ ናቸው፡፡ሕጻናቱ አነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያሰተውሉትም፣
አያውቁትም፣ ቢያውቁትም አይቃወሟቸውም፣ አይከሷቸውምም ወይም በትንሽ ነገር በቀላሉ
ሊባበሉና ሊታለሉላቸው ይችላሉ፡፡ ሕጻናቱ ጉዳቱ ስለማይታያቸው ያ የሚዳብሳቸውን ሰው
ይወዱታል፣ ደስ ስለምላቸው፡፡ ሕጻናትን ያጫወቱ፣ ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፉ በፍትወት
እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር የሚለውሱት ብዙ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት እኮ ብዙ ሕጻናት
ተደፍረዋል እየተባለ በተለያየ ሚዲያ የምንሰማው፡፡ ባሁኑ ጊዜ የሚታገቱ ሕጻናት፣ በጉድፈቻ
መልክ የሚሰበሰቡ ያለ እድሜያቸው ወሲብ የሚፈጸምባቸው እና ለግብረ ሰዶምነት የሚዘጋጁ
ናቸው፡፡

ጥያቄ?
 ሕጻን ሴት ከእናቷ ይልቅ አባቷን የምትቀርበው ለምን ይመስላችኋል?
 ሕጻን ወንድስ ከአባቱ ይልቅ ለእናቱ የሚቀርባት ልምንድነው?

[Type text] Page 12


ካላይ ያለውን ግንዛቤ በማንም ሰው ቢሆን ያለ አግባብ እንዳንተማመን የሚረዱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም
የምንውልበትን፣ የምንጓዝበትን፣ የምናድርበትን ቦታ ዚሪያውን እየቃኘን ወደ ዝሙት የሚመሩ ምክንያቶችን
ከወዲሁ አውቀን እንድንሸሽ ያግዘናል፡፡ አንዲሁም ሕጻናቶቻችንን በጥንቃቄ እንድንይዝ የሚያደርጉን ሲሆኑ
በዚህ መጥፎ ተግባር የተመረዙትን ሰዎች ደግሞ ስራቸው በብዙዎች ዘንድ መገለጡን አውቀው አደብ
እንድገዙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡

ሠይጣነ ዝሙት አንድን ሰው ያልተፈቀደለትን የሌላን ሰው አካል በዝሙት መንፈስ ለመንካት እንዲመኝ
እንደሚያነሳሳ ሁሉ ሰውዬው የራሱንም ሕዋሳት በዝሙት መንፈስ ሆኖ እንድደባብስ የሚገፋፋበት ጊዜ
አለ፡፡ ሰይጣኑ ሰው የራሱን ሰውነት ያለ ማቋረጥ እንዲያክ፣ እንዲያሻሽ አንዲደባብስ በማድረግ የራሱ
ሰውነት እንዲሸክረውና እንዲኮሰኩሰው በማድረግ ፈተና ያመጣበታል፡፡ መጽሐፈ መነኮሳት እንዲህ ይላል፡፡
‹‹ሰውነቱንም የሚያሻክርበት ጊዜ አለ፣ ያለ ማቋረጥም አንዲያክ ያደርገዋል፡፡ አንተም ስለዚህ በቆምክ ጊዜ
ሕዋሳትህን ትዳብሳለህ፣ ትንጠራራለህ፣ ወይም ትወጣጠራለህ፣ እግርህንም ታፋትላለህ፡፡ ይህ ርኩስ
መንፈስ ለመጀመሪያ ማሳከክ ሲጀምርና ሰውነትህን እንድትደባብስ ሲያደርግ ከሕዋሳቶችህ የሚመርጠው
የለም፡፡›› ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውዬው የሰይጣን ፈተና መሆኑን ካልተረዳ እንዲያው እንዳሳከከው ወይም
ሰውነት እንዲቆሸሸ ያስባል፡፡ ገፋ ካለም ወደ ሐኪም ዘንድ ይሄዳል፡፡ ሰውነት በማሳከክ የጀመረው ሰይጣነ
ዝሙት ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በዚህ ብቻ አይወስንም፡፡ እንደ መጽሐፈ መነኮሳት ገለጻ ወደ አባለ
ዘሩም ይሄድና ያን ሰው ያለመጠን እንዲያክ ያደርገዋል፡፡ ያንን ሰው በዝሙት ሐሳብ ተስቦ በዚህ መልኩ
ብልቱን እያሻሸ ዘሩን እስኪያፈስ ድረስ ዕረፍት ሳይሰጠው ፈተናውን ያስቀጥላል፡፡
 ማስገንዘቢያ፡- ከዚህ አንጻር ማሳጅ እና ፊዚዮ ቴራፒ ዓላማው ከዚህ ጋር የተያየዘ ነው፡፡ ሰይጣነ
ዝሙት ሰው የገዛ ሰውነቱ እንድከብደው በማድረግ እንዲታሽ ያደርጋል፡፡ ለዚህ መፍትሔው
ስግደት፣ ጾም እና ጠበል መጠመቅ ነው፡፡
በዚህ ዓይነት የዝሙት ዝንባሌ ተይዞ ከእንቅልፍ ውጭ ዘር እያወቁ ወደ ውጭ ማፍሰስ ግብረ አውናን
ይባላል፡፡ አውናን የተባለ ሰው ከሚስቱ ጋር ተኝቶ ሳለ ዘሩን ከሚስቱ ማኅፀን ውጭ ያፈሰው ስለ ነበር
ነው፡፡ ዝሙትን ወዶ ክቡር ዘርን የትም ማፍሰስ የአውናን ዘሩን ከማህፀን ውጭ መፍሰስ አንድ ናቸውና፡፡
ዘፍ. 38፡9
ግብረ አውናን ፈጽሞ ተገቢ አይደለም፡፡ ገበሬው ዘሩን በጎተራ አቆይቶ ያለቦታው፣ ያለጊዜው
እንደማይበትነው ሁሉ የሰው ዘር በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት ከጋብቻ በኋላ በሩካቤ ጊዜ በመልካሟ
ማሳ በሚስት ማኅፀን መዝራት አንጂ በልዩ ልዩ ምክንያት ሆን ብሎ ዘርን እንደ ጉድፍ ከማኅፀን በአፍአ
ማፍሰስ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡
የሰው ዘር ክቡር በመሆኑ ዘራቸውን በሜዳ ከሚያፈሱ ሰዎች ይልቅ ሰው የመሆን እድል የነበራቸው ነገር ግን
በየሜዳ ፈሰው የቀሩት ዘሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ዘር ያፈሰሱ ከሕገ እግዚአብሔር ሲወጡ፤ የፈሰሰው ዘር ግን
ምንም ካለመበደላቸውም ቢወለዱ ኖሮ ጳጳስና ንጉሥ የመሆን ዕድል ሊኖራቸው ስለሚችል ነው፡፡ በዝያን
ጊዜ ዘር ያፈሰሱትን ጊዜ ሳይሰጣቸው እግዚአብሔር ቀስፏል፡፡ ዘፍ. 38፡9-10 (ከመጽሐፍ ቅዱስ ሳያነቡ
አይለፉ)

[Type text] Page 13


መፍትሔው ደግሞ ‹‹እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ አንዚህም ዝሙትና ርኩሰት፣
ፍትወትም ክፉ ምኞትም፣ ጣኦትንም ማምለክም የሆነ መጎምጀት ነው፡፡›› (ቆላ. 3፡5)ነው፡፡ ብልቶቻችሁን
ግደሉ ማለት አትቀስቅሱ ማለት ነው፡፡ ዘርን ማፍሰስ ከጣኦት አምልኮ፣ ከክፉ ምኞት፣ ከርኩሰት፣
ከመጎምጀት ጋር ተሰልፎ እየተቆጠረ እንዴት ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡ በኤፌ. 4፡19 ‹‹ደንዝዘውም
በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ፡፡›› የሚለው ግብረ አውናን
ለሚፈጽሙ ሰዎች ሊጠቀስ ይችላል፡፡
በፍትወት ለተቃጠሉ ሰዎች ‹‹በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ፡፡››
ይላል፡፡ (1 ቆሮ. 7፡9) ስለዚህ በዝሙት ለሚቃጠሉ መፍትሔው ማግባት እንጂ መሰንጋት (ሴጋ መፈጸም)
አይደለም፡፡ ግብረ አውናን ምንም ዓይነት ኃላፊነት ሳይሸከሙ ያንን እርካታ ለማግኘት እንደመሞከር
ይቆጠራል፡፡ የምኞት ቃጠሎን ዘርን በማፍሰስ ለማብረድ መሞከር ስሕተት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ነገር
ሲያጋጥም ተቋቁሞ በማለፍ ፈንታ በተሳሳተ ጎዳና በመጓዝ ችግሩን ለማምለጥ መሞከር ጽንፈትንና
ደካማነትን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህን ዓይነት የለመደ ወጣት ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው ከመመከት
ይለቅ ሌላ የተሳሳተ አቋራጭ ሲማትር ይገኛል፡፡በዚህ ምክንያት ብዙ ወጣቶች ላለመማራቸውና ለሥራ
አጥነታቸው ወይም በሕይወታቸው ለገጠማቸው አንድ ችግር ተገቢና ጤናማ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ
ዱርዬነት፣ ሌብነትን፣ ሰካራምነትን፣ ስጋራ ማጨስንና ጫት መቃምን እንደ አማራጭ ይወስዳሉ፡፡
ማቴ. 5፡19 ላይ ሰይጣንም ቢሆን ሐሳቡ እስከሚፈጸምበት ድረስ በትንሽነቷ ንቀን እንድንፈጽማት ከግብረ
ሰዶምና ከዝሙት ታንሳለች በማላት ያሳስበናል እንጂ በዚሁ ኃጢአት የተያዙትን ሰዎች ደግሞ ያልሠሩትን
ግብረ ሰዶምና ዝሙት እንዲሠሩለት ‹‹አንደኛውን ዝሙት ይሻላል፣ ይህን የመሰለህ ኃጢአት እየፈጸምህ
ዝሙት አልሠራውም ለማለት ነው?›› እያለ ተስፋ ለማስቆረጥ እንደሚያምታታቸው መዘንጋት የለብንም፡፡
ዛሬ በዓለማችን ላይ ሴጋ የሚፈጽሙ ወንዶች ብቻ አይደሉም ሴቶችም ጭምር ናቸው እንጂ፡፡ በእድሜ
ደረጃም በሰባዎቹ የሚገኙ ሽማግሌዎች እና አሮጊቶችም ይፈጽማሉ፡፡ በቁጥር ሲገለጽም 2/3 ወጣት ልጃ
ገረዶች፣ 95 በመቶ ወጣት ወንዶች፣ 33 በመቶ በሰባዎቹ እድሜ የሚገኙ አሮጊቶች እና 43 በመቶ የሚሆኑ
ደግሞ ሽማግሌዎች ይህን ተግባር ይፈጽማሉ፡፡

[Type text] Page 14


ክፍል አምስት
ግብረ አውናን የሚያስከትለው ጉዳት
ግብረ አውናን ውጥረትን ለፈጠረ አንድ ችግር የተሳሳተ አማራጭን መጠቀም እንደመሆኑ መጠን በሕይወት
ዘመናችን ሁሉ ብርታትና ጥንካሬን የሚጠይቁ መንገዶችን እንድንሸሽ ያለማምዳሉ፡፡ ሰነፍ እንድንሆን
ያደርጋሉ፡፡ ግብረ አውናን ኃጢአት እንደመሆኑ መጠን በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ቅጣትን
ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም እንደ አውናን መቀሠፍ (ዘፍ. 38፡9)፣ ሰላም ማጣት፣ ቁጭት፣ ጸጸት፣ ጭንቀት፣
መረበሽ፣ ንጽሕ ያለመሆን ስሜት ወዘተ ያስከትላል፡፡ ካደገ ደግሞ ወደ ዝሙትና ግብረ ሰዶም መምራት፣
ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ጸጸት (ኀፍረተ አካልን ተናዶ እስከ መቁረጥ ሊያደርስ ይችላል)፣ አጉል ትሕትና
(መንፈሳዊ አገልጋዮች ከሆኑ አገልግሎቱ ንጽሕናን የሚፈልግ በመሆኑ ኑሮአቸውና መንፈሳዊ
አገልግሎታቸው ሳይጣጣም ሲቀር ማገልገል አይገባኝም በማለት ከትሩፋትና ከበጎ ሥራ ራሳቸውን
የሚያሸሹ አሉ)፡፡ ነገር ግን ክፉ ሥራን እንጂ የትሩፋት ሥራን መሸሽ በምንም መልኩ አይበጅም፡፡ በጋብቻ
ውስጥ አንዱ ለሌላው ወገን ደስታና እርካታ ማሰቡ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሴጋ ደግሞ የራስን ደስታና
እርካታ ብቻ የማሰብ ልምድን ያሳድጋል፡፡
ከግብረ አውናን እንዴት መላቀቅ ይቻላል
የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ በፍጹም የሚለቅ አይመስልም ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ
ያደርጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃል፡፡ ይህ ክፉ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ
በመጸጸት በጠንካራ መንፈስ ከተነሡ ሊያስወግዱት ይቻላል፡፡ ተስፈ አለመቁረጥ፡፡
መሰንጋት ልማድ ነው፡፡ ልማድ ደግሞ በልማድ ይሸነፋል፡፡ ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት
ከመነሣትህ በፊት ‹‹ይህን ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለሁ›› በማለት ራስን መጠየቅ
ያፈልጋል፡፡ መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትጸጸት ቀርተህ ሳይሆን ጣዕሙ ከልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ
ዘልቆ ወደ ልብህ ስላልገባ ነው፡፡ እሱን ለማውጣት መታገል ያስፈልጋል- በጾም፣ ጸሎት፣ ስግዳት፣
መጻሕፍትን ማንበብ፣ መዝሙራትን መዘመር... ግድ ይላል፡፡
‹‹ተዐቅቦ›› መከልከል- መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ወደዚህ መጥፎ ሀሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች
ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ከመሳሰሉት ነው፡፡ የሴቶችን ገላ በፊልም በአካልም ከማየት

[Type text] Page 15


መቆጠብ፣ በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርጽ መርዘህና
አትኩረህ አትመልከት፣ ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ስዕሎችን፣ ጽሑፎችንና ወሬዎችን መሸሽ ቦታ
አለመስጠት ንቆ ማለፍ ያስፈልጋል፡፡
ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ፡፡ ቦዘኔ አትሁን፣ ትጉህ ሠራተኛ ሁን፣
ሥራህም በእንቅስቃሴ የተሞላ ወይም አእምሮን ያለ ዕረፍት የሚያሠራ ይሁን፡፡ በትርፍ ሰዓትህ
የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሠራ ሥራ ፈጥረህ ሥራ፡፡
‹‹ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው›› የሚለውን ቃል አስብ፡፡ በዚህ ክፉ ልማድ ተጠምደህ ሳለ
ለብቻህ መሆንን አትውደድ፡፡ ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር
ይሁን፡፡ ከብቸኝነት ይልቅ መወያየትን ይልቁንም መንፈሳዊ ውይይትን ዘወትር አድርግ፡፡ በጸሎት
ከሚረዳህ መንፈሳዊያን መምህራንና አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ፡፡
እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለ ብቻ ወደ መኝታ አትሂድ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስትተኛ ውለህ እንቅልፍ
ያምርሃልና፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትተኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል፡፡
ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ሕሊናህ ይሳባል፡፡ ሰውነትህን በመዳበስ ፍትወትህን
ለማርካት ትጥራለህ፡፡ ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት በደንብ መድከምህንና ቶሎ ማሸለብ መቻልህን
መርምረህ ተኛ፡፡ አንተን/ አንቺን አጋጥሞህ/ሽ አያውቅም?
ጸሎት ማድረግንም አትርሳ የሚረሳ ነገር አይደለም፡፡ ስትተኛ በጀርባህ ወይም በሆድህ አትተኛ፡፡
ከዚህ ይልቅ በጎንህ ለመተኛት ሞክር፡፡ አመጋገብህ በልክ ይሁን፣ ጾምን በተገቢው መንገድ ጹም፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብብ፡፡ የመንፈሳዊ ሙያ ባለቤት ከሆንክ የምታውቀውን የዜማ ድምፅ
አውጥተህ አንጎራጉር:: ያም ባይሆን የምትችለውን መዝሙር ዘምር፡፡
እንዲህ ያለ ፈተና ሲነሣብህ አንድ ዓይት የዐካል እንቅስቃሴ (ሰፖርት) ሥራ፡፡ ወይም ወዲህና
ወዲያ ተንቀሳቀስ፡፡ ከዚህም ሁሉ ይልቅ ደግሞ ከሆነልህ መስገድ ይመረጣል፡፡ ሽንት መሽናትም
ጥሩ መድኃኒት ሊሆንህ ይችላል፡፡ በጊዜው ጠበል መጠመቀንንም ቸል አትበል፡፡ ደግሞ ጥንቃቄ
የተሞላበት ይሁን፤ ዓይኖችህን ከሴቶች አካል ንቀል፡፡
ሰውነትህ ሲበላህ ይልቁንም ወደ አባለ ዘርዕ አከባቢ ከሆነ ትኩረት ሰጥተህ አታስበው፡፡ ምክንያት
እንዳይሆንብህ ተጣጥበህ ንጹሕ ለመሆን ሞክር፡፡ የበላህ ቦታ ግን በምንም መልኩ አትከከው፡፡
ከዚያ ይልቅ መጽሐፈ መነኮሳት ‹‹ሕመም ወይም ማሳከክ በተሰማህ ቦታ ላይ በሕሊናህ
አማትብበት፡፡ በሕሊናም ማለቱ የሚያይህ ሰው ነገር እንዳይመራመርህ ለማድረግ ነው፡፡ በተረፈ
ግን አጥብቀህ ጸልይ፡፡››

 ትኩረት የሚሹ!!!
ከግብረ አውናን ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በጋብቻ ውስጥ ያሉ በማንኛውም መልኩ ሩካቤ ሲፈጽሙ
ኮንደም መጠቀም አይፈቀድም፡፡ ምክንያቱም እንደ አውናን ዘርን ከማኅፀን ውጭ ማፍሰስ ነውና፡፡ በትዳር
ያሉ ባልና ሚስት ኮንደምን የሚጠቀሙት ወሊድ ለመቆጣጠር ነው፡፡ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናችን
ሥርዓት መሠረት ማንኛውንም ወሊድ መቆጣጠሪያ መንገድ መጠቀም አይቻልም፡፡ ልጆች የእግዚአብሔር
ስጦታዎች እንጂ በእኛ ፎርሙላ የሚገኙ አይደሉም፡፡ ነገር ግን በባልና ሚስት መካከል የሚደረገው ወሲብ
ሥርዓት ያለው መሆን አለበት፡፡
[Type text] Page 16
ክፍል ስድስት
ምዕራፍ ሦስት

ምትረተ እስኪት- አባለ ዘርዕ መቁረጥ


በሀገራችን ሌላውን መስለብ እንደ ባህል የሚነገርላቸው አንዳንድ ጎሳዎች እና ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡
ዳዊትም ሜልኮልን ለማግባት የመቶ ፍልስጤማውያን ሸለፈት ሰልቦ ማምጣት ነበረበት፡፡ 1 ሳሙ. 18፡25-
27 ዛሬም በፍትወት ከመቃጠልና ከመበሳጨት የተነሣ ብዙ መንፈሳዊያንና ዓለማውያን ብልቶቻቸውን
በመቁረጥ አደጋ ላይ እየወደቁ ይገኛሉ፡፡ ድንግልናቸው እንዲጠበቅ ደግሞ የልጃ ገረዶችን ብልት
የሚተለትሉና የሚሰፉ ብዙ ጎሳዎች በሀገራችን አሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም የጽድቅ መንገድ አይደለም ከባድ
ስሕተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ነው፡፡ ፍትወት ከልክ በላይ ሆኖ ቢያስቸግርህ አካልን በመቁረጥ
ወይም ለማምለጥ አታስብ፡፡ ይህ የሰይጣን ወጥመድ ነው፡፡ መፍትሔው ማግባት ነው፡፡ 1 ቆሮ. 7፡9፡፡
ብልት መቁረጥ ማለት ሰርቆ የተያዘ ሰው ከሚደርስበት ድብደባ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ይህ ራስ አጥፊነት፣
ቀጪነት ነው፡፡
ሰው በዝሙት ጊዜ የሚበድለው በአባለ ዘሩ ብቻ ሳይሆን በልቡናውና በሕሊናውም ጭምር ነው፡፡ ሰይጣን
ብልት ካስቆረጠ በኋላ እንድንጸጸት በማድረግ ራሳችንን እንድናጠፋ ያነሳሳል፡፡ ልክ እንደ ይሁዳ፡፡ ማቴ.
27፡3-5 ሐዋ. 1፡16-20፡፡ በፍትወት መቃጠል የሚመነጨው ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው፡፡ ምትረተ
እስኪት ስሜታዊነትን፣ ሽንፈትን፣ ስንፍናን፣ ስልቹነትን፣ ታካችንትን፣ አርቆ አለማሰብን ያመለክታል፡፡
በጾም፣ በጸሎት እና በስግደት ማሸነፍ እያለ በቅጽበት ለመገላገል ማሰብ ነውና፡፡
በመጻሕፍትም ቢሆኑ ‹‹ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን ጀንደረባ ያደረጉ›› ማለቱ ስለ ብልት መቁረጥ
አይደለም፡፡ ‹‹ኀፍረተ አካሉን የቆረጠ ሰው ካህን ቢሆን ይሻር›› ‹‹ብልቱ የተቆረጠ ሰው ወደ
እግዚአብሐየር ጉባኤ አይግባ›› ዘዳ. 23፡1፡፡ ነገር ግን ያለውድ፣ በግድ፣ በጦርነትና በልዩ ልዩ ደዌ ምክንያት
አባለ ዘራቸው የተቆረጠ ሰዎች ከላይ የተጠቀሰው እገዳ አይመለከታቸውም፡፡

[Type text] Page 17


በመጽሐፈ መነኮሳት ‹‹አካል ብልት የጎደላቸውን ሰዎች አታዋርዳቸው›› (ማር.ይስ. አን. 2 ምዕ. 13)
በመጽሐፍ ቅዱስም አንድ ሰው የሰውን ብልት ቢይዝ እጁ ይቆረጥ ማለቱ ጥንቃቄ ሊደረግለት እንደሚገባ
እና ክብሩ ከእጅ የሚበልጥ መሆኑን ያሳያል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት እጃቸውን (አባ አትናቴዎስ)፣ ዐይኑን በወስፌ እንዳወጣ (ስምዖን ጫማ ሰፊ)፣ እግሩን
በእሳት እንዳቃጠለ (አባ መርትያኖስ) ብልትን መቁረጥ ከእነዚህ ይለያል፡፡ ምክንያቱም በዋናነት
የተሰናከሉት እነርሱ ራሳቸው አልነበሩም ይልቅ ሌሎች አካላቸውን በማየት ስለተሰናከሉ መሰናክል የሆነውን
አካላቸውን በማስወገድ ለሌሎች ያላቸውን ፍቅርና ኀዘኔታ ሕዋሳታቸውን እስከ ማስወገድ ደርሰው አሳዩ፡፡
እነዚህ አካላት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ኀፍረተ ስጋ ግን ከጥንትም ቢሆን በልብስ ይሸፈናል፡፡ ኀፍረተ አካል
ከሌሎች ሕዋሳት በላይ ሊታይ ይገባዋል፡፡ ሌሎች ንዑሳን አካላት ናቸው፡፡ ምክንያቱም ኀፍረተ ስጋ
ሕይወት መተላለፊያ ነው፡፡ 1 ቆሮ. 12፡23 ‹‹በምናፍርባቸው ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፡፡››
ተብሏልና፡፡
ከሰይጣነ ዝሙት ፈተና የተነሣ እንኳን አባለ ዘርን መቁረጥ ይቅርና ‹‹ምነው ከማህፀን ጃንደረባ ሆኜ
በተወለድሁ ኖሮ›› በማለት መመኘትም ስሕተት ነው፡፡ ለዚህም ‹‹ዝሙትን እንድትፈጽም ሰይጣን
ባስጨነቀህ ጊዜ አባለ ዘርዕን አትቁረጥ፡ ከእናትህም ሆድ ጀምሮ ጃንደረባ መሆንን አትፈልግ፡፡››
(ፊልክ.ተስእ.186) እንዲሁም በፈቃዱ ራሱን የሰለበ ለሦስት ዓመት ከቤተ ክርቲያን ይሰደድ፡፡
(ፍት.ነገ.አን.24)

ክፍል ሰባት
ምዕራፍ አራት
ለአቅመ ሔዋን የመድረስ ምልክት
ፈጣን የቁመት ማደግና የክብደት መጨመር ከመከሰቱም ሌላ የሽንጥ መርዘም፣ የደረት መጋጠሚያ
መጎድጎድ፡፡ በአንዳንድ ሴቶች ላይ ደግሞ ብጉር በሰውነታቸው በተለይ በፊታቸው ላይ በዝቶ የሚታይ
ሲሆን የፊት ቅርጽም ቀስ በቀስ እየተለወጠ ይሄዳል፡፡ በብብትና የብሽሽት (ኀፍረተ አካል) አካባቢ ጸጉር
መብቀል ጋር ዳሌዎች ይሰፋሉ፡፡ ልጃ ገረዶች የሚኖራቸው ሰፋ ያለ ዳሌ ወሊድን ብቻ ሳይሆን ከወለዱ
በኋላ ሕጻናትን ለማዘልና ለማቀፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል፡፡ የጡት መጎጥጎጥ ለአቅመ ሔዋን
የመድረስ ጉልህ ምልክት ነው፡፡ አንዲት ኮረዳ የሚኖሩአት ሁለት ጡቶች ልጅ በምትወልድበት ጊዜ ለሕጻኑ
ምግብ የሚሆነውን ወተት ማመንጨት ይጀምራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹ጡቷ ሁልጊዜ ታርካህ፣
በፍቅርዋም ሁል ጊዜ ጥገብ›› (ምሳ. 5፡19) ማለቱ ባልዋ የሚደሰተው ጡቶቿን በመሳም፣ በመነካካትና፣
በመዳባበስ ነውና፡፡ ለጡት ማነስ እና መተለቅ የሚያሳስብ አይደለም፡፡ የተፈጠረበትን ዓላማ ስለማያጓድል
ሊጨንቀን አይገባም፡፡ በጡት መያዣ የሚወጥሩ፣ ምናምን የሚወትፉ፣ ቀዶ ጥገና የሚያስደርጉ ሴቶች
አሉና፡፡ ነገር ግን ሠለስቱ ምዕት ‹‹ሌላ መልክ አትሻ(መነቀስ፣ መጠቆር፣ መታከም) በተፈጥሮ ያገኘኸው
ይበቃሃልና›› ብለው አስተምረዋል፡፡
ጡት በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል ስለሆነ ከመጨነቃችን የተነሳ የማናውቃቸውን ነገሮች እንደመሰለን መጠቀም
ጉዳት ላይ ሊጥለን ይችላል፡፡ ለጡት ካንሰር መጋለጥ...፣ አንዳንድ ሴቶች ደግሞ በጡታቸው ምክንያት

[Type text] Page 18


የሰውነት ቅርጻቸው የተበላሸ መስሎአቸው የሚጨነቁ፣ የዐይን ዝሙት በያዛቸው ወንዶች ዘንድ ቦታ ያጡ
ስለመሰላቸው ይጨነቃሉ፡፡ ውጫዊ አካል የሚመለከት ወንድ እውነተኛ ፍቅር በውስጡ የለም ያ አካል
ሲያልፍ እሱም አብሮ ያልፋል፡፡ ባሁኑ ጊዜ ለውጫዊ አካል የሚጨነቁ ሴቶች የበዙበት ምክንያት ውጫዊ
አካል ላይ ያተኮሩ ወንዶች ስለበዙ ነው፡፡ ነገር ግን ከቅርጽና ከውበት ይልቅ ጤንነት ይበልጣል፡፡ ሴቶች
በሚወልዱበት ጊዜ ልጆቸቻቸውን እያጠቡ የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ጡትን የሚተካ ምግብ የለምና፡፡
በፍት.ነገ. ‹‹ልጆቿን ለሞግዚት አትስጥ›› ይላል፡፡ምክንያቱም አንዳንድ ሴቶች መውለድን እንጂ ሕጻናትን
ማሳደግ አይፈልጉም- መከራን በመሰቀቅ፣ ዝሙትን በመውደድ እና እንዲሁም እግዚአብሔር የሰጠውን
ምግብ መከልከል ስለሆነ ግፍ ነው፡፡

የወር አባበ
ለአቅመ ሔዋን የደረሱ ሴቶች የሚያሳዩት ሌላው ምልክት የወር አበባ ነው፡፡ የወር አበባ የተለያዩ ስያሜዎች
አሉት፡፡
የሴቶች ልማድ ዘፍ. 18፡11 ልማደ አንስት
በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ዘፍ. 31፡35
የወር አበባ የተባለበት ምክንያት በየወሩ የሚታይ ስለሆነ አበባ መባሉ ፍሬ ለመስጠት የሚችል
እንቡጥ (አበባ) ስለሆነ ነው፡፡
አደፍ ተብሏል
ደመ ጽጌ ይባላል ‹‹የአበባ ደም›› ማለት ነው፡፡ የወንድ ዘር ባለማግኘቱ በደም መልክ ይወጣል፡፡
እስከሚጸንሱት በየወሩ ይታያል፡፡ በእርግዝና ወቅት ይቋረጥና ልጅ ከተወለደ(ች) በኋላ ጤናማ
ሂደቱን ይቀጥላል፡፡ ይህ ወርኃዊ ዑደት የሚጀምርበት፣ የሚቋረጥበት ዕድሜና መታየት ከጀመረበት
እስከሚቋረጥበት ድረስ የሚወስደው ጊዜ ከሰው ወደ ሰው ይለያያል፡
የወር አበባ ሴት ልጅ ፈጣሪ ለመደበላት ዕጥፍ የሕይወት ሚና ማለትም ሚስት እናት ለመሆን መድረሷን
የሚያመለክት በመሆኑ ሳትከፋ በጸጋ ልትቀበለው ይገባታል፡፡ መደንገጥ፣ መፍራት አያስፈልግም፡፡
ምክንያቱም አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ሲታያቸው የሚበሳጩ፣ በመታየቱም የሚከፉ፣ ባይታይ ደስ
የሚላቸው አሉ ነገር ግን ይህ በደል ነው፡፡ ወደ ትዳር ከገቡ በኋላ ባይታይ ግን ልጅ መውለድ የለምና ምን
ያህል ያስከፋ ይሆን? ስለዚህ እናቶች ለልጆቻቸው አስቀድመው በቂ ግንዛቤ ማስጨበጥ አለባቸው፡፡
ልጆችም ለቤተሰቦቻቸው በግልጽ ማማከር ይገባቸዋል፡፡ ዘፍ. 31፡35 ራሔል ‹‹በሴቶች የሚደርስ ግደዳጅ
ደርሶብኛል›› ብላ ለአባቷ እንደ ነገረችው፡፡
ድንግል ማርያም ግን ለ 64 ዓመታት ስትኖር ልማደ አንስት አላገኛትም፡፡ ሌሎችም ሳያዩ የሚያልፉ
ጤናማ ሴቶች የሉም፡፡ ምክንያቱም እሷ ልዩ ናት ከአዳም እና ከሔዋን የውርስ ኃጢአት(Orginal
Sin) ነጻ ስለሆነች ይህ አይመለከታትም፡፡
የወር አበባ መቼቱ አዳምና ሔዋን በኃጢአት ከወደቁ በኋላ ከገነት ውጭ ነው፡፡ በገነት በነበሩበት ጊዜ
ምንም እንኳን በሔዋን ባሕርይ ደመ ጽጌ የነበረ ቢሆንም ደሟ በአፍአ አይታይም ነበር፡፡ በምድር ላይ

[Type text] Page 19


ያለው ዝናብም በፊት እንዳልነበረ እና ከጥፋት ውኃ በኋላ ግን እግዚአብሔር ክረምትና በጋን ለማፈራረቅ
ለኖኅ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት ዝናብ መዝነብ ጀመረ (ዘፍ. 8፡22)፡፡ በፊት ውስጥ ለውስጥ ያረካት
የነበረው ውኃ ዝናብ ሆኖ እየመጣ ምድርን ከውጭ ያጨቀያት ጀመር፡፡ ምድር ለሔዋን ምሳሌ ናት ሰው
ምድር ይባላልና፡፡ ዝናብ የወር አበባ ምሳሌ ነው፡፡
በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥሙ የሕመም ስሜቶች አሉ፡፡ የጡንቻና የአጥንት መልፈስፈስ (ድካም)፣ የወገብ
ሕመም፣ የሆድ ቁርጠት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ትዝብት ላይ እስከ መውደቅ የሚያደርስ መቅበጥበጥ
አንዳንዴም የመደበር፣ በሆነው ባልሆነው በቀላሉ የመከፋት ስሜት ይነበባል፡፡ ዘፍ. 31፡35 ያንብቡ፡፡

የወር አበባ ርኩስ ነውን?


በብሉይ ኪዳን እርግጥ ነው ይባላል፡፡ ዘሌ. 18፡19፣ ዘሌ. 20፡18 እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡...
‹‹በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች››...‹‹ባለ መርገም ሴት››... ‹‹ከርኩሰትዋ ነጽታ››
በሐዲስ ኪዳን ግን ማለት አይቻልም፡፡ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ ክህደት ነው ምክንያም ጌታችን አምላካችን
በመስቀል ላይ ዋጋ ስለከፈለልን መርገም አይባልም፤ሆኖም ግን የወር አበባ ርኩሰት ባይሆንም አደፍ (አዳሪ)
ነው ማለትና ርኩሰት ነው ማለት መካከል ከፍተኛ ልዩነት አላቸው፡፡ ርኩሰት ውስጣዊ ነው፡፡ በንስሐ እንጂ
በውኃ አይጠራም፡፡ አደፍ ግን አፍአዊና በግዘፍ የሚታይ ነው፤ውኃ ያጠረዋል፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህርይ
ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም ሰውነት ሲያስወግደው ግን እንደ ቆሻሻ ይቆጠራል፡፡ ለምሣሌ፡- ዛሕል (ንፍጥ)፣
ሽንት፣ ምራቅ፣ ዓይነ ምድር (እዳሪ)፣ ላብ በሰው ባሕርይ በሰውነት ውስጥ ሳሉ ጠቃሚና አስፈላጊ ነበሩ፡፡
ሲያስወግዳቸው ግን እንደ ጉድፍ ይቆጠራሉ፡፡ ግን ርኩሰት አይባሉም፡፡ የወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ
መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡
በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው
ከሩካቤ፡- በሽታ ያስከትላል፣ የወንድ ዘር ክቡር ስለሆነ፣ ‹‹እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች
ኀፍረተ ስጋዋን ትገልጽ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ›› (ዘሌ. 18፡19)ይላልና፡፡ በዘሌ. 20፡18
‹‹ማንኛውም ሰው ከባለመርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ እርሷም የደሟን ፈሳሽ
ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፡፡›› በሐዲስ ኪዳንም እንደ ብሉይ
ኪዳን በድንጋይ ተወግረውና በእሳት ተቃጥለው እንዲጠፉ ባይደረግም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
በመተላለፋቸው በመንፈሳዊ ቅጣት(በቀኖና) መቃጣቸው አይቀርም፡፡
ከመጠመቅ፡ 1 ጴጥ. 3፡21 ‹‹ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት... የሰውነት እድፍ ማስወገድ
አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፡፡›› ስለዚህ ከጥምቀት በፊት የሰውነት
አደፍ ማሰወገድ ያስፈልጋል፡፡ የወር አበባ አደፍ ስለሆነ መጠመቅ አይቻልም፡፡ ፍትሐ.ነገሥ.

[Type text] Page 20


‹‹በምትጠመቀው ሴት በምትጠመቅበት ቀን አደፍ ቢመጣባት እስክትነጻ ድረስ ትቆይ›› አንዳንድ
ጊዜ በጠና የታመሙ ሰዎች በጸበል ለመፈወስ ክትትል ሲጀምሩ ልዩ ልዩ ፈተና ያጋጥማቸዋል፡፡
የወር አበባ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለማቋረጥ ወይም በተደጋጋሚ መከሠቱ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ
ከሰይጣን ጋር እልሕ መጋባትና ዝም ብዬ ብጠመቅ ምን አለበት? ማለት ሞኝነት ነው፡፡ ‹‹ክፉን
በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ›› (ሮሜ. 17፡21) ይላልና ‹‹ይህ ዓይነት ከጸሎትና ከደም
በቀር አይወጣም›› (ማቴ. 17፡21) መርሳት ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜ በተለየ መልኩ መጾም እና
መጸለይ ያስፈልጋል፡፡
ከመቁረብ፡- ለቁርባን የሚያሰፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ቢሆኑም ሴቶች ከወር አበባ
ሳይነጹ መቀበል አይችሉም፡፡ በወር አበባ ላይ እያለች እንድትቆርብ ያደረገ ካህን፣ ዲያቆን፣ ከክህነቱ
ይሻር፡፡ ፍት.ነገ. 6 ዘሌ. 7፡19-21፡፡ ስጋወደሙን መቀበል ቢኖርብንም በምንም አመካኝነት ቢሆን
በወር አበባ ላይ ሳለን መቁረብ አንችልም፡፡ በቁርባን የሚጋቡ ሰዎች የሰርግ ቀናቸውን
ከመወሰናቸውና የሰርግ ዝግጅት ከመጀመራቸው በፊት የሴቷን የወር አበባ ዑደት ለይቶ ማወቅና
ከሠርግ ቀኗ ጋር አንድ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንዲሁም የጋብቻ ቀናቸውንም በአባቶች ጸሎት
መወሰን እንጂ በዓለማዊ ዝግጅቶች መወሰን የለባቸውም፡፡ መጸለይ መፍትሔ ነው (የሰይጣን
አሰራር እንዳያዛባ)፡፡
ቤተ መቅደስ ከመግባት፡- ከግዳጅዋ ከነጻች ከሰባት ቀን በኋላ ገላዋን ታጥባ ትገባለች፡፡ ፍት.ነገ.
አን. 6፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን አትሂድ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያውን ቅጽር ከገባች
በኋላ መጠለያና በገራገር ውስጥ ሆና ትጸልይ፣ ትማር፣ ማንኛውንም መንፈሳዊ ነገር ትከታተል እንጂ
ወደ ቤተ መቅደስ ተደፋፍራ አትግባ ማለት ነው፡፡

ክፍል ስምንት
ምዕራፍ አምስት
ድንግልና
ድንግል የሚለው ቃል ‹‹ተደነገለ፣ ተጠበቀ›› መጠበቅ ማለት እንደ አገባቡም ፍቺው ሊለያይ ይችላል፡፡
ለዕቃ እንደሆነ ገና ከማምረቻ የወጣ፣ ምንም ያልተሠራበት፣ ያላደፈ፣ ያላረጀ፣ ያልተቀላቀለ ማለት ነው፡፡
በዚህ መሠረት እስኪ ለሰው ደግሞ ተጠቀሙ፡፡ ድንግል መሬት ሲባል ደግሞ ለምነቱ እንደተጠበቀ ያለ፣
ለእርሻ ያልዋለ ወይም ያልታረሰ፣ ያልተቆፈረ፣ ዘር ያላረፈበት፣ እንደተፈጠረ ያለ፡፡ ለሰው ስነገር ደግሞ
ወንድ የማታውቅ፣ በጥብቅ፣ ልጃገረድ ወይም ሴትን የማያውቅ ወንድ ማለት ይሆናል፡፡ ዘፍ. 24፡16 ራዕ.
14፡4፡፡ ነገር ግን አንዲትን ሴት ምኅተመ ድንግልና ስላላት ብቻ ሩካቤ አድርጋ አታውቅም ወይም ሩካቤ
ስላደረገች ማኅተመ ድንግልና የላትም ማለት አይቻልም፡፡ የወንዶች ድንግልና እንደ ሴቶች ተጨባጭ ጉልህ
የድንግልና ምልክት ስለሌላቸው ከሴት ጋር ሩካቤ ፈጽመው የማያውቁ ሆነው ሳለ ደናግል አይደሉም
ለማለት አይቻልም፡፡ ሩካቤን ፈጽመው የማያውቁ ሴቶች ስወለዱ ጀምሮ ማኅተመ ድንግልና የሌላቸው
ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ከጊዜ በኋላ በከባድ የአካል እንቅስቃሴ፣ በአደጋ፣ በሕክምና ወይም በዕድሜ ብዛት

[Type text] Page 21


ምክንያት ማኅተመ ድንግልና ሊፈርስባቸው ይችላል፡፡ እንዲህ ያሉ ሴቶች ማኅተመ ድንግልናቸውን ቢያጡ
ሩካቤ ፈጽመው እስካላወቁ ድረስ ደናግል መባላቸው የተጠበቀ ነው፡፡
ወንዶቸች ሩካቤ ፈጽመው ሳለ እንደ ሴቶች የሚገሠሥ ማኅተመ ድንግልና ስለ ሌላቸው ድንግልናቸው
አልፈረሰም እንደማይባል ሁሉ ሴቶች ሩካቤ ሥጋ እየፈጸሙ በልዩ ልዩ ምክንያት ማኅተመ ድንግልናቸው
ባይገሠሥ መደበኛ ሩካቤ እስከ ፈጸሙ ድረስ ደናግል ሊባሉ አይችሉም፡፡ አንዲትን ሴት ድንግል የሚያሰኛት
ሥራዋና ዝንባሌዋ ብቻ ነው፡፡
ማኅተመ ድንግልና ሕግ ይባላል፡፡ ምክንያቱም ‹‹አታመንዝር›› የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሕግ መፈጸምና
አለመፈጸምን የሚያስታውቅ የሕግ ምልክት በመሆኑ ነው፡፡ እስከ ጋብቻ በንጽሕና ተጠብቆ ከሚኖርበት
የድንግልና ሕግ ወደ ጥንድነት የሚተላለፉበት ጋብቻም ‹‹ሕግ›› ይባላል፡፡ ያገባ ለማለት ‹‹ሕጋዊ››
ይባላል፡፡ ለዚህ ነው አንድ ወንድ የአንድን ሴት ድንግልና ሲገሥ ሕጓን ወሰዳባት ማለት ትዳር እንዳትይዝ፣
ሕጋዊ ባል እንዳይኖራት አደረጋት ማለት ነው፡፡
በሌላ መልኩ ማኅተመ ድንግልና ዓይን ይባላል ወይም በዓይን ይመሰላል፡፡ ይህም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የተናገረውን ‹‹ድንግላናቸውን እንደ ዓይን ብሌን ይጠብቁ ዘንድ ላላገቡ ደናግል ምከራቸው
አስተምራቸው›› መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሴት በድንግልናዋ (በዓይን) ባሏን ታያለች እሱም እንዲሁ፡፡
ድንግልና ባልና ሚስት በተለየ መልኩ የሚተያዩበት የማይመረመር ‹‹ዓይን›› ነው፡፡ የኑሮ ደረጃቸውን
በድንግልና ሆነው መርምረውና ተመልክተው ያገቡ ሰዎች አይጸጸቱም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ደረጃው
ማግባት ይሁን መመንኮስ በሚገባ ለይቶ ማወቅ የሚችለው ንጽሕናውን ጠብቆ ለመኖር ከቻለ ብቻ ነው፡፡
ዓይን ታማሚ ብትሆን ሰውነት ሁሉ ጨለማ እንደሚሆን ሁሉ (ማቴ. 6፡22) ድንግልናም በሕገ ወጥነት
በዝሙት ሥራ ካጠፉት አንድ ሰው ሰውነቱ ሁሉ እንደጨለመበት ሊያምን ይገባል፡፡ምክንያቱም ድንግልና
ሃይማኖትና ምግባር መሠረታቸውን ለቀው እንዳይኖር የሚያደርግ ጽኑ መሠረት ነውና፡፡
የድንግልና ዓይነቶች
በሁለት ወገን ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው የድንግልና ዓይነት ድንጋሌ ሥጋ ነው፡፡ ሁለተኛውም
ድንጋለ ነፍስ ይባላል፡፡ ድንጋሌ ሥጋ ለድንጋለ ነፍስ መገለጫ ፣ ጥላ ወይም አምሳል ነው፡፡ አማናዊ
ድንግልና የምትባለው ድንግልና ግን የነፍስ ድንግልና ናት፡፡ (ዮሐ.ተግ. 28)፡፡ ድንጋሌ ሥጋ በግዘፍ
የሚታይ በገሢሥ (የሴቶች) የሚታወቅ ሲሆን ድንጋሌ ነፍስ ግን ረቂቅ ነው፡፡ ነፍስ ግን ድንግልናዋ በብዙ
ጎዳና ነው፡፡ አንድ ጊዜ በኃጢአት ተግባርና ሐሳብ የተወሰደበት ድንግልና በንስሐ ይመለስላታል፡፡ የነፍስን
ድንግልና የሚያጠፋው የኃጢአት ሥራና ሐሳብ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ በቅዱስ ጋብቻ የተወሰኑ ባልና ሚስት
በሚፈጽሙት ሩካቤ ድንጋሌ ሥጋቸው ሲጠፋ የነፍስ ድንግልናቸው ግን አይወገድም፡፡ ምክንያቱም በሕጋዊ
ባለትዳሮች ሩካቤያቸው ኃጢአት ባለመሆኑ ነው፡፡ እስኪ ይህን አስቡ ወደ ትዳር ዓለም ሳትገቡ
ድንግልናችሁን ያጣችሁ አልጸጸታችሁም? በድንግልና ሆናችሁ በጋብቻችሁ የስጋ ድንግልናችሁን ስታጡስ
ተጸጸታችሁ? በፍጹም አይጸጽትም ምክንያቱም የነፍስ ድንግልና ስላላጣችሁ ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት ግን
የስጋም የነፍስም ድንግልና ስላጣችሁ ጸጸት ይሰማችኋል ወይም ደግሞ በትዳር መገኘት የነበረበት ደስታ
የማይገኘው ለዚህ ነው፤ አንዳንዴ ጊዜ እንደውም በማግባታችሁ የምታዝኑበት ጊዜ የለም? ምክንያቱ እሱ
ነው ድንግልና! ከጋብቻ በፊት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በድንግልና ያገባች ሴት ‹‹ባልም ብታገባ ድንቅ
በሚሆን ድንጋሌ ነፍስ ድንግል ናት›› ይላል፡፡ (ዮሐ.ተግ. 28)

[Type text] Page 22


ድንጋሌ ነፍስ የሌለው ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም፡፡ ይህም ማለት የነፍስን ድንግልና
የሚያጠፋው ኃጢአት ብቻ በመሆኑ ኃጢአቱን በንስሐ ያላራቀ ወይም ንስሐ ያልገባ ሰው ወደ መንግሥተ
ሰማያት አይገባል ማለት ነው፡፡ ራዕ. 14፡4 ‹‹ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው ድንግሎች ናቸውና በጉ
ወደሚሄድበት የሚከተሉ እነዚህ ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኩራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ
እነዚህ ናቸው፡፡›› ዮሐ.ተግ. 28 ‹‹ድንጋሌ ነፍስ ከመርዓዊው ክርስቶስ ጋር አንድ ያደርጋል፡፡ ወደ
መንግሥተ ሰማያት ያስገባልና፡፡››
ደናግላንና አለባበሳቸው
ለዐቅመ ሔዋን የደረሱና ያልደረሱ ደናግላን የሆኑና ያልሆኑ ሴቶች ተለይተው የሚታወቁበት የፀጉር
አሠራር፣ አለጫጨትና የአለባበስ ሁኔታ በየሀገሩ ይገኛል፡፡ ጥንቱን የሀጋራችንንም ብሔር ብሔረሰቦች ባህል
ወደ ኋላ መለስ በሉና አስቡ፤ የዛሬው ግን....፡፡ ድሮ እስራኤላውያን ደናግል ለፍሬ አልደረስንም ሲሉ ወርቅ
እንደ አበባ የፈነዳበት ነጭ ሐር ለብሰው ይታዩ ነበር፡፡ ደናግላን የተለየ አለባበስ አንደ ነበራቸው መጽሐፍ
ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ትዕማር ድንግል በነበረች ጊዜ ብዙ ኅብር ያለውን ልብስ ለብሳ ነበር እንዲህ ያለውን
ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱት ነበርና፡፡ ነገር ግን በተደፈረችና ክብሯን ባጣች ጊዜ ‹‹ብዙ ኅብር
ያለውን ልብስዋን ተርትራ እየጮኸች ሄደች›› 2 ሳሙ. 13፡18-19፡፡ ዛሬስ ሴቶች እህቶች ቀሚሳቸውን
ቀድደው፣ አጭር ጣል የተደረገች ቀሚስ መሳይ ልብስ፣ የተወጣጠረች ቲሸርት፣ ዳሌ የምታሳይ አጭር
ነጠላ፣ የውስጥ ሰውነት የሚያሳይ ስስ ቀሚስ፣ ሰይጣን አምላኪዎች የሚያደርጉት የፀጉር አሠራር ምንን
ያሳያል? አንዲት ሴት ድንግል ሆና እያለች የተቀደደ ቀሚስ፣ አጭር ቀሚስ... ለብሳ ብትሄድ ሌላ መልእክት
የለውም ‹‹እኔ ድንግል አይደለሁም፣ እኔ ዘማ ነኝ፣ ተዋርጃለሁ፣ ሕጋዊ ትዳር መያዝ አልፈልግም...›› ማለት
ነውና ራሳችንን እንጠብቅ፤ እኛ ክርስቲያኖች አለባበሳችን አስተማሪ መሆን አለበት፣ ምሳሌ እንኳን ባይሆን
ለሌሎች መሰናክል መሆን የለብንም፡፡

መደንገል እስከ መቼ?


ይህ እንደ ሰው የአኗኗር ዘይቤ ይለያያል፡፡ ለአንዱ ጋብቻውን እስኪፈጽም ድረስ ሲሆን ለሌላው ደግሞ
እስከ ዕድሜ ልክ ይሆናል፡፡
እስከ እድሜ ልክ መደንገል
እስከ ሞት ድረስ ድንግልናቸውን መጠበቅ የሚኖራቸው በድንግልና ለመነኮሱት ነቸው፡፡ በርግጥ ምንኩስና
ድንጋሌ ሥጋ ያላቸው ሰዎች ብቻ የሚጓዙበት ጎዳና አይደለም:: ባለ ትዳር የነበሩ ወይም ሳያገቡ ለዝሙት
ተጋልጠው ድንጋሌ ሥጋቸውን ያጡ ሰዎችም በንስሐ ተመልሰውም ይኖሩበታል፡፡ እንደ ቀላል የሚታይ ግን
አይደለም፡፡የዓለምን ኑሮ እንደ ልብ ኖረው ሲሰለች ብቻ የሚገባበት አድርጎ ማሰብ ስሕተት ነው፡፡
ምንኩስና በድንግልና ሲሆን ብዙ ጸጋና ክብር ያመጣል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ከመመንኮስ በተጨማሪ የግድ
ድንግል ሆኖ መገኘትን የሚጠይቁ ብዙ ታላላቅ መንፈሳዊ የሹመት ደረጃዎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች
ይገኛሉ፡፡ በድንግልና መመንኮስ ጣዕመ ዓለምን ሳይቀምሱ በመሆኑ ከምንኩስናም በኋላ ለሚኖሩት
የንጽሕና ኑሮ አጋዥነት ይኖረዋል፡፡ ምክንያቱም ከመነኮሱበት ዓላማ ጋር የማይስማማ በልቡናቸው የሚቀር
የዓለማዊ ኑሮ አሻራ ባለመኖሩ ነው፡፡ ‹‹ያላዩት ሀገር አይናፍቅም›› ይባል የለ፡፡ በርግጥ ይህን የመሰለ
የምናኔ ኑሮ ለመኖር ስጦታ ያፈልጋል (1 ቆሮ. 7፡7)፡፡ ምንም እንኳን በጋብቻም ሆነ በምንኩስና መኖር

[Type text] Page 23


ሁለቱም የእግዚአብሔር ስጦታዎች ቢሆኑም በጋብቻ መኖር ለሁሉ የተሰጠ ሲሆን ምንኩስና ግን መመረጥና
መታደል የሚጠይቅ ነው (ማቴ. 19፡11)፡፡
ድንግልናን በሕይወት ዘመን በሙሉ ጠብቆ በምንኩስና መኖር ከስጦታነት በተጨማሪ በፈቃደኝነት ሊደረግ
የሚገባው ነገር ነው እንጂ የሚገደድበት ተግባር አይደለም፡፡ ወጣቶችም በኛ ውሳኔ እና በእግዚአብሔር
ፈቃድ ወደዚህ ሕይወት መግባት ይቻላል፡፡ የሚበልጥ ሕይወት ነውና፡፡(1 ቆሮ. 7፡38፣ ማቴ. 19፡21፣
ኤር. 1፡5፣ 1 ቆሮ. 7፡25-26)፡፡
እስከ ጋብቻ ጊዜ ድረስ መደንገል
በሀገራችን የድንግልና ሕይወት ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የተከበረና በማንኛውም ሰው ዘንድ ዋጋ ያለው
ነገር ነበር፡፡ እስከሚያገባ (ታገባ) ድረስ በድንግልና መቆየት ግዴታው (ዋ) ነበር ነውም፡፡ ይህንንም
ለማድረግ ሴቷና ወንዱ እንዳይተያዩ፣ እንዳይገናኙ እርስ በርሳቸው ስሕተት እንዳይሰሩ በማለት በልዩ ልዩ
ዘዴ ይጠብቁ ነበር፡፡ ቶሎ እንዲያገቡም ይደረግ ነበር፡፡
ባሁኑ ጊዜ ደግሞ እጅግ በዛ እንጂ በሁሉም ረገድ እስኪደራጁ ድረስ ሳያገቡ መዘግየት መልካም ሆኖ ሳለ ስለ
ንጽሕናቸው አጠባበቅ ደግሞ ምንም የተወሰደ እርምጃ ስለሌለ የድንግልና ሕይወት እየቀለለና ዋጋ እያጣ
መጥቷል፡፡በጨቅላ እድሜያቸው ያገቡ ልጆች ጋብቻቸውን እንዳይጸናና ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ ሁሉ
ሳያገቡ ድንግልናቸውን የሚያጡ ስድ የለመዱ የዛሬ ተጋቢዎችም ራሳቸውን ገትቶ መያዝ ስለማይሆንላቸው
ከትዳር በኋላ ስያዝኑና ሲያለቅሱ ማየት የዘወትር ክስተት ሆኗል፡፡
ለእስራኤላውያን ድንግልናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው በሕግ ተስጥቷቸዋል፡፡ ይህም ድንግልናውን
የሚያጠፋ ሁሉ በድንጋይ ተወግሮ፣ በእሳት ተቃጥሎ ይገደል ነበር፡፡ ዛሬ በገጠራችን አከባቢዎች አንድ ሰው
የትዳር አግኝቶ እስከሚያገባ ድረስ ድንግልናውን ጠብቆ ይኖር ነበር፡፡ ከትዳር በኋላ ወንድ ድንግልናውን
በከበረ ስጦታነት በረቂቅ መንገድ ለሚስቱ ሲያስረክብ ሴቲቱ ደግሞ ሕጓን ሊታወቅ በሚችል መልኩ
(በግዘፍ) ለባሏ ትሰጣለች፡፡ ይህ ሲሆን በባልና በሚስት መካከል ጥልቅ የሆነ መከባበር፣ መተሳሰብ፣
መተማመንና መፋቀር ይጎልብታል፡፡ ከዚህ ውጭ የሆነ ጋብቻ ግን እንደው መቻቻል እንጂ መፋቀር
የጎደለው ይሆናል፡፡ በእናንተ አከባቢ ያለ ድንግልና ከተጋቡ ሰዎች ምን አነበባችሁ? እናንተስ? ጋብቻ
በደናግላን ያምራል፡፡ የብዙ ቅዱሳን ወላጆችም በድንግልና ኖረው በቅዱስ ጋብቻ የተወሰኑ ናቸው፡፡
ድንግልናን እስከ ጋብቻ ድረስ ጠብቆ ማቆየት ለሰው ልጅ በሙሉ የተሰጠ ችሎታ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ
በውዴታ መደረግ ያለበት ነገር ብቻ አይደለም፡፡
በሀገራችን እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ድንግልናዋ የጠፋ ሴትን ማንም አያገባትም ይልቁንም ድንግልናዋን
የወሰደ ሰው በግድ እንዲያገባት ይደረግ ነበር፡፡ እሷም ባያገባት እንኳን ተመልሳ ትዳርን አታስብ፤ ያለ
ድንግልና የሆነ ጋብቻ ጣዕም የለውምና፡፡
ስለዚህ ወጣቶች ራሳችንን ጠብቀን ከኛ በታች ያሉ ታዳጊዎችንም አስተምረን የቀደመው ባህላችንን
እንመልስ እላለሁ፡፡
መላ ዘመንን በድንግልና ለመኖር መመረጥ
መላ ዘመንን በድንግልና ለመኖር መመረጥን የሚጠይቅ ቢሆንም እስከ ጋብቻ በንጽሕና ለመቆየት ግን ለሰው
ሁሉ የታወጀ ነው፡፡ ዘፀ. 34፡28፣ 1 ነገ. 19፡8፡፡ በድንግልና መኖር የማይቻል ነው የሚሉ አሉ፤ ነገር ግን
[Type text] Page 24
ሀሰት ነው ፈጣሪ የማይቻለውን ባልሰጠ (ባላዘዘ) ነበር፡፡ ሩካቤ ሥጋ እንደምንተነፍሰው አየር፣
እንደምንጠጣው ውኃ እና እንደምንመገበው መብል መቁጠር የለብንም፡፡ እነዚህን ያለገኘ ይሞታል፤ ሩካቤ
ሳይፈጽም ቀርቶ የሞተ የለም ነገር ግን ብዙ ሊፈተን ይችላል፡፡ ይህን ለማሸነፍ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት እና
እስከ ጋብቻ ምንም አልፈጽምም ብሎ አቋም መያዝ (መወሰን) ያንጊዜ መንፈስ ቅዱስ ያግዘናል፡፡
ባሁኑ ጊዜ ሳይንስ (የስነ ልቡና ትምህርት) ዝሙትን (sex) በፊት ያልነበረውን መሠረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ
አካቶ ታገኛላችሁ፡፡ ይህ ዓለም ዝሙትን ለማስፋፋት ምን ያህል እንደምትጥር ያሳያል (Maslow
hierarchy ማየት ይቻላል):: ከዚህ የተነሳ ያለ ሩካቤ ስጋ መኖር አይቻልም የሚሉ ሰዎች ከግትር
አቋማቸው እና ድክመታቸው ተነስተው ነው፡፡ የጤና ጉድለትም ይመስላቸዋል፡፡ ይህ በዝሙት መሸነፍን
ያሳያል፡፡ ዮሐ. 14፡12‹‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱም ደግሞ ያደርጋል፡፡ ከዚህም
የሚበልጥ ያደርጋል፡፡›› ሰው ድንግልናውን ለመጠበቅ ዝንባሌ ሲኖረው መንፈስ ቅዱስ ይደግፈዋል፡፡ ገላ.
5፡23፣ ፊል. 4፡13 ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡››
ድንግልናን መጠበቅ በኛ ዘምን የተጀመረ አይደለም፡፡ ነገር ግን አዳም ከመሳሳቱ በፊት ለሰባት ዓመት
ከሁለት ወር የኖረው በድንግልና ነው፡፡ ኖኅም ቢሆን ለጋብቻና ለፍሬ የበቃው ለአምስት መቶ ዓመታት
በደንግልና ከኖረ በኋላ ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት ድንግልናን ማጣት አይፈቀድም... ፡፡
መታጨት፣ ማጨትና ማግባት በድንግልና ሊደረጉ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ነውረኛ ያሰኛል፡፡ 2 ሳሙ. 13፡
12-14፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ እስራኤላዊ ሚስት አግብቶ ድንግልና ባያገኝባት ሚስቱን መክሰስ ይችል
ነበር፡፡ ዘዳ. 22፡13-19 በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ይላል (ዘዳ. 22፡20-24)፡፡ ምክንያቱም ለሌላ
ወንድ ድንግልናዋን ያስረከበች ሴት ከባሏ ጋር መኖር አትችልም፤ ሕሊናዋ የቀድሞውን ያስባልና ለእውነተኛ
ባሏ የሚፈለገውን ፍቅር ልትሰጠው አትችልም፡፡ በሀገራችን የሚነገረውን ልንገራችሁ ‹‹አንዲት ሴት
ድንግል ሳትሆን ከመጣች ባሏ ከእርሷ ጋር ምግብ መብላት እንኳን ያስጠለዋል›› ይባላል፡፡ ሌላውን የባልና
ሚስት ኑሮ ትተን ማለት ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በመካከላቸው ያለው ፍቅር ይቀንስና ከትዳራቸው ውጭ
መሄድ ይጀምራሉ በመጨረሻም ባሁኑ ጊዜ የፍርድ ቤት ዶሴ ላጨናነቀው ፍቺ ይደረጋሉ፡፡
በድንግልና ማግባት እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ ይመክረናል፡፡ 1 ቆሮ. 7፡28 ላይ ‹‹ድንግሊቱም ብታገባ
ኃጢአት አትሠራም፡፡›› ለወንዱም በ 1 ቆሮ. 7፡36 ላይ ‹‹ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ
ስለ ድንግልና ያፈረ ሰው ቢኖር የወደደውን ያድርግ›› ይላል፡፡ ይህ ማለት ከፈለገ ያግባ ካልፈለገ ደግሞ
አያግባ በድንግልና ይኑር ማለት ነው፡፡ ዛሬ ብዙዎች ትዳርን አይፈልጉም ግን ከማንኛውም ሰው ጋር ዝሙት
ይፈጽማሉ፡፡ አይ ኢትዮጵያ! ከጣሊያን ወራራ እና ከግራኝ በፊት የነበበረው መልኳን እግዚአብሔር
ያምጣልን፡፡ አሜን፡፡ ዛሬማ ዝሙት አንዱ መተዳደሪያ ሆኗል፤ ግብረ ሰዶምም በሌሎች ዓለማት ተጀምሮ
በሀገራችንም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች እና ሴቶች በዚህ እንደሚኖሩ ግልጽ ነው፡፡ ወንጌሉን ባንሰማ
እንኳን የሀገራችን ባህል ይፈቅዳል ወይ? በፍጹም ማንኛውም ብሔር ወይም ጎሳ ጋር ሂዱ በጣም የተጠላ
ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት ዝሙትን መፈጸምን ያመጣነው ከአሕዛብ እና ከውጭው ዓለም እንጂ የኛ
የኢትዮጵያውያን ባህል አልነበረም፡፡ ለዚህ እኮ ነው ዛሬ ጋብቻ ክብር የሌለው፣ የጋብቻ መስፍርትም
መልክ፣ ቁንጅና የሆነው፤ ለዝሙት ብቻ፡፡ መጨረሻው ፍቺ፡፡

[Type text] Page 25


ድንግልናን ጠብቆ መኖር የሚያስፈልገው የግድ ለመመንኮስ ብቻ ሳይሆን ዘግይተው ማግባትም እንደሚችሉ
ኃጢአት እንደማይሆንባቸው ይገልጻል፡፡ የድንግልና ሕይወት፣ የንጽሕና፣ የቅድስናና የታማኝነት ምሳሌ ሆኖ
በጽኑ ቃል ኪዳን መገኘትን የሚያመለክት በመሆኑ ልዩ ክብር አለው፡፡ እዚህ ላይ ለመጻፍ ይከብዳል እንጂ
ብዙ ነገር እነግራቸዋለሁ፡፡ በድንግልና ያልተጋቡ ሰዎች እድሜያቸውን በሙሉ ሳይተማመኑ ይኖራሉ፡፡
ምክንያቱም እሷም ብትሆን እስከ ትዳር መታገስ አቅቷት ድንግልናዋን ለሌላ ሰው በማስረከቧ አሁን ከእሷ
ጋር ያለው ባሏ አያምናትም፡፡ ምክንያቱም ማስተማመኛ የለውም እሷም እንዲሁ፡፡ ሌላው ደግሞ ሁለቱ
ተጋቢዎች በእጮኝነት ዘመናቸው ሳይታገሱ ቀርተው ዝሙት ፈጽመው ድንግልናቸውን ቢያጡ፣ ገና
ድንግልናቸውን ሲያጡ ፍቅራቸው ይቀንሳል፡፡ ይህ ለብዙዎች አይታወቅም፤ የድንግልና ዋጋ ብዙ ነውና፡፡
ከዚያ በተለያዩ ምክንያቶች የጋብቻ ጊዜያቸውን ያራዝመሉ በተለይ ወንድዬው፡፡ ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ
ጋብቻ ቢፈጽሙ እንኳን ደስታ የለውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሰጣቸው ፀጋ ያለጊዜው እና
ያለቦታው ጠፍቷልና፡፡ ወንድሞች እና እህቶች ነገን በደስታ ለመኖር ድንግልናችንን እንጠብቅ፣ ለታዳጊ
ወንድሞች እና እህቶችም በደንብ እንምከራቸው፡፡ አዳራ ዛሬ መልካም መስሎ የሚታይ ስሜት ነገ ጸጸት
ስለሚያስከትል ከወዲሁ እናስብበት፡፡ ‹‹በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል››
በእጮኝነት ደረጃ ያሉ ዛሬ ደግሞ በጓደኝነት ደረጃ! ያሉ ወጣቶች ከጋብቻ በፊት ጥንቃቄ ካለማድረግ የተነሳ
ዝሙት ካልፈጸሙ ወደፊት የማይጋቡ ይመስላቸዋል፡፡ በነገራችን ላይ በክርስትና የእጮኝነት ጊዜ እንጂ
የጓዳኝነት ጊዜ የሚባል ነገር የለም፡፡ ይህ እራሳችን የፈጠርነው ነው፡፡ አንድ ሰው በአንድ ጊዜ አንድ እጮኛ
ብቻ ይኖረዋል ብዙ ጓደኞች ግን ሊኖሩት ይችላል፡፡ባሁኑ ጊዜ አሕዛብ እና ክርስትና ያልገባቸው ዝሙትን
አንደ ፍቅራቸው መገለጫ ይጠቀሙበታል፡፡ ግን ገና ሲፈጽሙ በተለያየ መልኩ ፍቅራቸው ይሻክራል
መንፈስ ቅዱስ ይለያቸዋልና፡፡ በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ወጣቶች አብረው እስካሉ
ምንም አይመስላቸውም፤ ተመርቀው የተለያየ ቦታ ሲደርሳቸው መጠባበቅ የለም፡፡ ድንግልናቸውን ያለ ጊዜ
አጥተዋልና ምንም አይመስላቸውም፡፡ እና ወንድሞች እና አህቶች እጮኛችሁ ‹‹ካንቺ ጋር ወሲብ እንዳደርግ
የከለከልሽኝ ስለማትወጂኝ ነው›› ብልሽ አትስሚው እሱ እግዚአብሔር ያዘጋጀልሽ ወንድ አይደለምና
አስተምሪው ወይም ተይው፤ የማይወድስ አንቺ ሳትሆኚ እሱ ነውና፡፡ ሴቷም ወንዱን አፍ አውጥታ
ባትናገረውም የዝሙት ጥያቄ ካለቀረበላት ወደ ጋብቻ ገብተው የባልን ግዳጅ ሁሉ የማይፈጽም
ይመስላታል፡፡ ግን አይደለም ወንድሜ እንደዚያ አይነቷን ሴት አትቅረብ ለትዳር አትሆንህም፤
እስከሚዋሀዳት ድረስ አስተምራት ባታውቅ ነው አንተም እሷም ከነክብራችሁ ወደ ትዳር ብትገቡ ቅዱስ
እግዚአብሔር በጋብቻችሁ የስጋን ድንግልና ብታጡ እንኳን የነፍስ ድንግልናችሁን ጠብቆላችሁ በፍቅር
ትኖራለችሁ፡፡
ከጾታ ምድቦች በተለይ ካህን ድንግሊቱን እንጂ ጋለሞታይቱን (ፈት የሆነችውን) ማግባት አይችልም፡፡ ዘሌ.
21፡10-14፡፡ በዝሙት ሲዘሉ ከኖሩ በኋላ ከማግባት ድንግልናን ጠብቀው ከቆዩ በኋላ ማግባት ለሕሊና፣
ለጤና፣ ለተሳካና መልካም ትዳር እንዲሁም ለመንፈሳዊ ሕይወት ምቹና የተሻለ ነው፡፡ 1 ቆሮ. 7፡38
‹‹ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ፡፡›› ይላልና፡፡
ከጋብቻ በፊት ድንግልናን መጣል የበለጠ ሴሰኛ ያደርጋል
ያላዩት አገር አይናፍቅም እንደሚባለው ዝሙትን የማያውቁ ሰዎች ዝሙትን እንደቀመሱት አይሆኑም፡፡
ያላገቡ ሰዎች ስለወደፊት ትዳራቸው በማሰብ ድንግልናቸውን ይጠብቃሉ፤ እንዲህ በማለት ባሌ ደስተኛ

[Type text] Page 26


የሚሆነው በድንግልና ቢያገኘኝ ነው፣ ለራሳቸው ክብረ ተክሊል እንዳይቀርባቸው በመስጋት፣ ወይም
ስማቸው እና ለክብራቸው ሲሉ እንጂ ድንግልናቸውን ለመጠበቅ አስበው አይደለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት
ሴቶች እና ወንዶች ገና ትዳር ይዘው ድንግልናቸው ሲፈርስ ሴሰኞች ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሴቶች እና
ወንዶች ከሴት ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት አይፈጽሙ እንጂ ከላይ ያየነውን ግብረ አውናን ወይም ሴጋ
ሲፈጽሙ ይኖራሉ፡፡
በእጮኝነት እያለህ ያጨሃትን ሴት ሳታገባት አትድረስባት፡፡ ድንግልናዋ ቢያጓጓህ ብትደርስባት በሁለት
መንገድ ራስህን ጎድተሃል፡፡ የመጀመሪያው አመንዝራ ትባላለህ፣ የራስህንም ክብር ታጣለህ ሁለተኛው
እርሷንም ካንተ ወጥታ ለማመንዘር እንዲመቻት አድርገሃልና በራስህ ጠንቅ አመጣህ ማለት ነው፡፡
ምክንያቱም እርሷ አንተን የምትፈራበት አንተም እርሷን የምትጠብቅበት ምንም ምልክት የለህም፡፡ በገዛ
እጅህ አፍርሰሃልና፡፡ ማግባቷ የድንግልናዋን ያህል ጥበቃ ሊያደርግለት መቻሉን አትርሳ፡፡

ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅም

 በአግባብ ለመኖር፡- በድንግልና መኖር አግባብ ነው ዝሙት ግን ግብረ ገብነትን ማጣት ነው፡፡
ድንግልናን ጠብቆ ለመኖር የሚደረገው ትግል ሕጋዊ ሰው ሆኖ መኖርን ያለማምዳል፡፡
 ሳይባክኑ ለመኖር፡- ድንግልናውን የጠበቀ ወዲህና ወዲያ አይልም፡፡ ዝሙት ግን መባከን ነው፡፡
ዝሙተኛ ኃጢአቱን ለመደበቅ፣ ከዚህ በኋላ እግዞ,ዚአብሔር ምን ያመጣብኝ ይሆን? በማለትና
ዝሙቱ ቢታወቅ በሌሎች ዘንድ ምን ሊባል እንደሚችል በማሰብ በስጋትና በመባከን ይኖራል፡፡
መዝ. 6፡1-3፣ 1 ቆሮ. 7፡32-33፡፡ በጋብቻ ከመኖር በድንግልና መኖር የበለጠ ከሐሳብ ነጻ
ያደርጋል፡፡ ወጣቶችም በዚህ ሕይወት ለመኖር ከወዲሁ ከእግዚአብሔር ጋር ብነጋገሩ እና
ቢወስኑ እጅግ በሕይወታቸው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
 በጌታ ይጸናል፡- ብዙዎች ስለ ፍትወት ብለው ኮረዳና ጎልማሳ ፍለጋ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን
አንደተው የሚታወቅ ነው፡፡ ዛሬም የመናፍቃን ትልቁ አጀንዳ የሆነው ሴቶች ረጋፊ የሆነ
መልካቸውን ተጠቅመው ኦርቶዶክስ ወጣቶችን የነጠቁ ብዙ ናቸው፤ ወንዶችም እንዲሁ
እህቶቻችንን፡፡ ለመሆኑ የጋብቻ የመጀመሪያ መስፍርት እኮ ሃይማኖት ነው፡፡ ከዚያ የተረፈ
ገንዘብ፣ መልክ፣ ጎሳ፣ ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ የመሳሰሉት የጋብቻ መስፈርት ሊሆኑ አይችሉም፡፡
እግዚአብሔር እና ቅዱሳኑ በእነዚህ መስፈርቶች ውስጥ የሉምና፡፡ ለመሆኑ ላንተ (ላንቺ) የተዳር
[Type text] Page 27
መስፈርትሽ ምንድነው? ባሁኑ ጊዜ የተዳር መስፈርቱ ውጫዊ ነገር ስለሆነ የጋብቻ ክብር
ቀንሷል፡፡ ጋብቻ እኮ የመጀመሪያ ተቋም ነው በዚህ ዓለም ላይ ያለው ሕዝብ ሁሉ የተገኘበት፣
በገነት ውስጥ በእግዚብሔር የተመሠረተ፡፡ 2 ጴጥ.2፡1-2፣ 1 ቆሮ. 7፡37፡፡ ድንግልናን መጠበቅ
ራሱ ትዕግስት እና ጽናት ስለሚጠይቅ ይህን ይለማመዳሉና በእግዚአብሔር ለመጽናት ይረዳል፡፡
 ድንግልናን መጠበቅ ታማኝነትን ያረጋግጣል፡- ድንግልናን ጠብቀን እንድንይዘው በአደራ
የተሰጠን የከበረ ንብረት ነው፡፡ ባለአደራ ፈጣሪያችን፣ በሚያስፈልግ ጊዜና ሰዓት ለትዳር
አጋራችን እንድንሰጠው ይጠብቀናል፡፡ ድንግልናውን ያልጠበቀ ግን አደራ በሊታ፣ ታማኝነትም
የጎደለው ይሆናል፡፡ ድንግልና ሳይኖራቸው የተጋቡ ሰዎች ሳይተማመኑ ይኖራሉ፤ ይህ ደግሞ
ለአንድ ትዳር ትልቁ ፈተና ነው፡፡ ምክንያቱም ባልና ሚስት ተማምነው እና ተዋደው ይኖራሉ
እንጂ ተቻችለው አይደለም፡፡ የአንድ ሰው አካል ላይ ያሉ ብልቶች ተግባብተው፣ ተዋደው፣
አንድ ሆነው፣ ተማምነው ይኖራሉ እንጂ ግድ ተቻችለው አይደለም፡፡ ባልና ሚስትም እንዲህ
ናቸው፡፡ ሚስት ለባሏ እግዚአብሔር በአደራ የሰጣትን ድንግልና ስትሰጠው በአደራ ጠባቂነት
እንዲያያት፣ እንዲያምናት፣ እንዲያከብራት፣ እንዲወዳት ያደርገዋል፡፡ ያን ጊዜ ይዋደዳሉ፣
ይከባበራሉ፡፡ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰው ግን እንደ ተራ ነገር ይቆጥራል፡፡
ድንግልናን መጠበቅ ችሎታ ነው፡፡ ምክንያቱም በውስጡ ጽናት፣ ብርታት፣ ትዕግሥት፣
ታማኝነት አለበትና፡፡
 ድንግልናን መጠበቅ መጠንቀቅ ነው፡- ከበሽታ፣ ያለ አግባብ ወይም ሳያገቡ ከመውለድ፣ ክብርና
መልካም ስምን ከማጣት፣ ከመጸጸት ያድናል፡፡ ለወደፊት መንፈሳዊውም ሆነ ሥጋዊ ችግር
ከሚፈጥሩ የኑሮ ጠንቆች ሁሉ መቶ በመቶ ሊሰወር የሚችል መጠንቀቅ ቢኖር ድንግልናን
መጠበቅ ነው፡፡
 ልብ ሳይከፈል ፈጣሪን እጅግ አድርጎ ለማስደሰት፡- ባሏንም ታስደስታለች(ከዚህ ይጀምራልና)፡፡
ድንግልናን ካጠፉ በኋላ የሚደረግ ጋብቻ አግብቶ የፈታ ሰው እንደሚፈጽመው እንደ ሁለተኛ
ጋብቻ ይቆጠራል፡፡ስሙም የመዐስባን ጋብቻ መባሉ ለዚህ ነው፡፡ ለመመንኮስ ተስሎ የነበረ ሰው
ቢያገባ የተሳለው ስእለት እንደ መጀመሪያ ጋብቻ ተቆጥሮ የሚፈጽመው ጋብቻ ለሁለተኛ ጊዜ
እንደሚያገባ ሰው እንደሚቆጠርበት ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ያስረዳል፡፡ በ 1 ቆሮ. 7፡33-34
‹‹የተጋባች ግን ባሏን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለም ነገር ታስባለች፡፡›› ድንግልናቸውን
አጥተው የተጋቡ ባለትዳሮች ያጡበትን መንገድ በሕሊናቸው ማሰባቸው አይቀርም፡፡ ያንጊዜ
ደግሞ ላሉበት ትዳር ደስተኛ አይሆኑም፡፡ ምንም እንኳን በአካል መዋሐድ ቢችሉም የልቡና
ተዋሕዶ ለመፍጠር ይቸገራሉና ደስታቸው በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትዳር የሚመሩ
ሰዎች ብዙ ጊዜ ሰማያዊውን ዋጋ ትተው የዚህን ዓለም ቢዝነስ፣ ኑሮ፣ደስታ ወዘተ ሲያወሩ፣
ሲያስቡ እና ስያደርጉ ይኖራሉ፡፡ የትዳር መስፈርታቸውም ከእነዚህ የራቀ አይደለም፡፡
 ድንግልናን መጠበቅ ጋብቻ ሳይዘገይ በጊዜው እንዲፈጸም ይገፋፋል፡- ከጋብቻ በፊት ዝሙት
ከተፈጸመ ለጋብቻ ያለው ውስጣዊ ፍላጎት ይቀንሳል፤ እንደመታሰርም ይቆጥሩታል፡፡ ባሁኑ ጊዜ
የሚታዩ እውነታዎችም ይህን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ብዙ ዓለማዊ ፊልሞችም ከጋብቻ በፊት
ዝሙትን የሚያበረታቱ ስለሆኑ ወጣቱ ሊርቃቸው ይገባል፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤ
የጋብቻ ቀነ ቀጠሮ እንዲራዘም ከማድረጉም በላይ ለመለያየትም በር ከፋች ነው፡፡ ቢጋቡ እንኳን

[Type text] Page 28


የውጪው ሰው ምን ይለናል በማለት እንጂ ፈልገውት አይደለም፡፡ ከላይ እንዳልኳችሁ ዝሙት
እንደፈጸሙ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይለያቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ፍቅራቸው ይቀንሳል
መበሳጨት፣ መጨቃጨቅ፣ መነዛነዝ ይጀምራሉ፤ ይህ ጭቅጭቅም በትዳራቸው ውስጥም
ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና አንድነት የላቸውም፡፡
የአንድን ሰው ድንግልና ሊያሳጡ የሚችሉ ወቅቶች፣ ቦታዎችን እና አጋጠሚዎች ከሰንበት ትምህርት
ቤት ጓደኞቻችሁ፣ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ተመካከሩ፡፡ አደራ፡፡ እኔ ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ እነሆ!
አንዳንዶች ገና በልጅነትና በመጀመሪያዎቹ የወጣትነት አፍላ ጊዜያት ድንግልናቸውን ያጣሉ፡፡ ሌሎች
አስቸጋሪውን የወጣትነት ዕድሜ አጋምሰው ክብራቸውን የሚያጡበት ሁኔታ ይፈጠራሉ፡፡ ተገድደው
ሊደፈሩ ይችላሉ (ዘደ. 22፡24) ነገር ግን ሴቶች ራሳቸው ለመደፈር ሁኔታ ያመቻቹ መሆን
የለባቸውም (አለባበሳቸው፣ ውሎአቸው መታየት አለበት)፡፡ ከወንዶች ጋር ያለው አቀራረብ ገደብ
ሊበጅለት ይገባል፡፡ሰውን በማመን የተጎዱ ብዙ እህቶች አሉና፤ ሰውን መማን አያጸድቅም ማፍቀር
(መውደድ) ነው እንጂ!

ግን አንድ ጥያቄ ላንሳ! ከጋብቻ በፊት ድንግልናቸውን ያጡበትን ቀን በደስታ ነው ወይስ በሀዘን ነው
የሚያስቡት?

ክፍል አስራ አንድ


ምዕራፍ ስድስት
ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥ)
እግዚአብሔር የሰው ልጆች እንዲታረዙ አይፈልግም፡፡ ዘፍ. 3፡21 ‹‹የቁርበት ልብስ አለበሳቸው፡፡››፡፡
በልብስ የሚጠቀመው ሥጋ ቢሆንም የልብስ አስፈላጊነቱ ግን ለነፍስ ነው፡፡ አንድ ሰው ነፍሱ ስትለየው
አያፍርም፣ አይለብስምና፡፡ ጌታችን ለምትለብሱት አትጨነቁ ብሏል ብዙዎቻችን ግን የምንጨነቀው
የምንለብሰውን አጥተን ሳይሆን መምረጥ አቅቶን ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው ዛሬ ዓለም የትውልዱን ስነ ልቡና
ስለተረዳች በየጊዜ ፋሽኖችን የሚትለቅብን፡፡እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ልብሳቸው ሳያልቅ 40 ዓመት
እንደመራቸው ለሌለው መስጠት ይቻለዋል፡፡ ማቴ. 6፡28 መዝ. 22፡1፣ 1 ጢሞ. 6፡8፡፡ የሰው ነፍስ ስለ
አለባበስ በቂ ግንዛቤ አላት፡፡ አዳምና ሔዋን ጸጋቸው በተገፈፈ ጊዜ ‹‹የበለስ ቅጠሎችን ቆርጠው ለእነርሱ
ለራሳቸው ግልድም አደረጉ›› ዘፍ. 3፡7፡፡ እንዲሁም ነፍስ ልብስ አስፈላጊ መሆኑን ብቻ ሳይሆን መልበስ
ያለብንን የልብስ ዓይነትና በዋናነት መሸፈን የሚገባውን የአካል ክፍል ለይታ ማወቋ ነው፡፡
አዳምና ሔዋን እንሰሳትን አይተው እንደነሱ መልበስ የለብንም አላሉም ይልቅ ለራሳቸው አገለደሙ እንጂ፡፡
የሚገርመው ደግሞ ሌሎች ዕፀዋት እያሉ በለስን መምረጣቸው ሳያንስ ያን ሰፍተው ማገልደማቸው ነው፡፡

[Type text] Page 29


የበለስ ቅጠል ሰፋፊ ነው በዚያ ላይ ደግሞ ተሰፍቶ፡፡ ብርድ ለመከላከል ብቻ አልነበረም፡፡ ቢሆን ኖሮ ሌላ
አካላቸውን ጨምረው ባለበሱት ነበር፡፡ አዳምና ሔዋን ማገልደማቸው ብቻ በቂ ባለመሆኑ እግዚአብሔር
የቁርበት ልብስ አለበሳቸው ‹‹ግልድም ሰጣቸው›› አይልም፡፡ ዘፍ. 3፡21፡፡ ዛሬስ ምን ዓይነት ልብስ ነው
የለበስነው?
ከአዳምና ሔዋን ምን ዓይነት ልብስ መልበስ እንዳለብን እንረዳለን፡፡ ዛሬ ግን ብዙ ሴቶች ስሜታቸውን
እንጂ የነፍሳቸውን ፈቃድ አይከተሉም፡፡ለዚህ ማሳያው ነፍስ መሆን ያለበትን መጠቆሟን፣ መንፈስ ቅዱስም
በማይገባ ልብስ ስንሸለም መውቀሱን ይታወቅ ዘንድ ሲያፍሩ፣ አጠር ብለው የለበሱትን ሲጎትቱና ወይም
በልዩ ልዩ ዘዴ የተራቆተውን የሰውነት ክፍል ለመሸፈን ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ በተለያዩ የዓለም መድረኮች ዛሬ
አልፎ አልፎ በቤተ ክርስቲያናችንም በስርዓቱ ሰውነት ላይ የማይቀመጠውን ልብስ እየለበሱ አስር ጊዜ
እያስተካከሉ የሰውን ሕሊና የሚሰርቁ ብዙ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ሰይጣን ብዙ ስራ ይሰራል የወጣቱን
ትኩረት በመሳብ በዝሙት ፈቃድ እንዲወድቅ፣ በሰዓቱ የቆመበትን ዓላማ እንድዘነጋ ማድረግ፣ እሷ ደግሞ
ለሌሎች ውድቀት ምክንያት እንድትሆን በማድረግ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ይጥላል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣን
ድንጋይ ሲወረውር ከመታ በኋላ ተመልሶ ደግሞ ሌላውንም ሰው እንዲመታ ማድረግ ጥበቡ ነው፡፡ ዛሬ
አጫጭርን ነጠላን አስተውሉ፣ የቤተ ክርስቲያናችን አኮ አልነበሩም፤ የኛማ ረጅም፣ ወፍራም ሰውነት
ያማያሳይ ነበር፡፡ የአሁኖቹ ደግሞ የሴቶችን ዳሌ እና እራቁት የሚያሳዩ ወንዶችን ለፍትወት የሚያነሳሱ
ናቸው፡፡ ለመሆኑ አስተውለን እናውቃለን? ይህ ክርስቲያኖችን ሕገ ወጥ ለማድረግ የተሠራ የዓለም ሴራ
ነውና እንወቅበት፡፡ እንደ ነጠላው ሌሎችንም አለባበስ እናስተውል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ሴቶች
ክርስቲያኖች ከፀጉራቸው ጀምሮ እስክ እግራቸው ድረስ ስለሚሸፋፈኑ የዓይን ዝሙት ለተጠናወታቸው
ሰዎች ምቹ አይደለም፡፡ይህ አካላቸው እንዲጋለጥ ቀጭን ነጠላ፣ የሰውነት ቅርጻቸው እንዲታይ ደግሞ
የሚያጣብቅ ቲሸርት እና ሱሪ እንዲለብሱ የዓለም የዘወትር ተግባሯ ነው፡፡ እኛስ?
ለወንዶችም ሠለስቱ ምዕት በሃይማኖተ አበው ‹‹አለባበስህ በጥንቃቄ ይሁን፡፡››በማለት አዘዋል፡፡ የኖኅ
መራቆት የልጅ ልጁን ከነዓንን ለእርግማን ዳርጓል፡፡ ዘፍ. 8፡22፣ የቤርሳቤህ ከልብስ መረቆት ራሷንና
ዳዊትን ለዝሙት ዳርጓል፡፡ በዘዳ.22፡5 ላይ ‹‹ወንድ የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ
በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና፡፡››
ልብስ የጸጋ እና የክብር ምሳሌ ነው፡፡ አዳምና ሔዋንም የእግዚአብሔር ክብር እንደራቃቸው ያወቁት
ልብሳቸው (የጸጋ ልብስ) በመገፈፉ ነው፡፡ ልብስ የክብር ምልክት ነው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ
ንዋያተ ቅድሳትንና ምስጢራትን በሙሉ በማኅፈዳት እና በመንጦላዕት (በመጋረጃ) በመሸፈን
እናከብራቸዋለን፡፡
የሚገባ ልብስ
በ 1 ጢሞ. 2፡10 ‹‹ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራስን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ››
ይላል፡፡ የማይገባ ልብስ ማለት አካልን ለእይታ የሚያጋልጥ ፀረ ክርስትና መልእክት ያለው ልብስ ሁሉ
ነው፡፡ በላዩ ላይ የዝሙት መልእክት ያለው ሥዕልና ጽሑፍ ያዘለ ከሆነ፣ ስስና ዘርዛራ ወይም ከገላ ጋር
የሚጣበቅ ሆኖ ገላን የሚያሳይና ቅርጽን የሚያወጣ ከሆነ፡፡ በተለይ ባሁኑ ጊዜ የአውሬው ምልክት እና
መልእክቶች በሰፊው ልብሶች ላይ እየታተመ የሚወጣበት ጊዜ ላይ ስለሆን ፋሽን ከመከተል የኛን ማንነት
የሚገልጸውን ልብስ ዓይነት መልበሱ የተሻለ ነው፡፡

[Type text] Page 30


የማይገባ አለባበስ የሚባለው የሴቶች ሱሪ መልበስ ብቻ አይደለም፡፡ ቀሚስም የማይገባ ልብስ ሆኖ
የሚይገኝበት ብዙ መንገድ አለ፡፡ ለምሣሌ እጅግ ቢያጥር፣ ተሰንጥቆና ሳስቶ ሰውነትን ለእይታ ካጋለጠ
የማይገባ ነው፡፡ አንዲት ልጃ ገረድ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ በሰውነቷ ላይ የሚታይ ለውጥ ለአቅመ አዳም
የደረሱ ወጣቶችን በኃይል የሚማርክ ይሆናል፡፡ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን የሰውነትሽን ክፍሎች
ለማሳየት ቁምጣና አጣብቂኝ የሆኑ ጉርድ ቀሚሶችን፣አጭር ቀሚስና ጠባብ ሹራቦችን፣ ስስና ዘርዛራ ልብስ፣
ጠባቃ ሱሪ መልበስ ለምንዝር ጌጥ መጋለጥ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለ ደግሞ የተቃራኒ ጾታዎችን ፍትወተ ሥጋ
የመቀስቀስ ሚና ይጫወታል፡፡ ለማሸነፍ ደግሞ ምን ያህል በቁ ነሽ? አለባበስሽን አይቶ የመጣ ወንድ ደግሞ
ከዝሙት በቀር ባልሽ ሊሆን አይችልም፡፡ስለዚህ አለባበስሽ ለምንዝር ሆነ ማለት ነው፡፡
ባሎች የሚስቶቻቸውን አለባበስ በጥንቃቄ ይከታተላሉና ሚስቶች ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ምክንያቱም ባሎች
ሌሎች ወንዶች ሚስቶቻቸውን በዝሙት ዓይነት እንድመለከቷቸው አይፈልጉም፡፡ ያን ጊዜ በልቡ
ይጠርጥርሻል ከዚያ ከእሱ የምታገኚውን ተድላ ታጫለሽ፣ትነቀፊያለሽ፣ ከባልሽም ተለይተሸ ትሄጃለሽ
(ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡
አንዳንድ ሴቶች ደግሞ ባላቸው ወደ ውጭ ውጭ እንዳይልባቸው ልብሰ ዘማ ይለብሳሉ፡፡ ይህ ግን ባልን
የበለጠ ሴሰኛ ማድረግ ነው፡፡ የተለበሱ ልብሶችን እያየ ከሚስቱ ጋር ወሲብ የሚፈጽም ባል ነገ ደግሞ
ከሚስቱ አስበልጣ የምታጌጥ ሴት ካየ ሚስቱን ትቶ መሄዱ አይቀሬ ነው፡፡ ይልቅ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍል ማስተዋሉ ይሻላሉ፡፡ 1 ጴጥ. 3፡1-6፡፡ እንዲሁም ‹‹ባልሽ ሴሰኛ ከሆነ ግን ምንም በጌጦች ዓይነት
ሁሉ ብታጌጪ ካንቺ ወደ ሌላ መሄዱ አይቀርም›› (ተግ.ዘዮሐ. 28)፡፡
ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት የሚያጋልጥ ለብሶ ወደ ገበያ እና ሥራ ቦታ መሄድ ምን ለመሆን
ነው? ለሥራ ነው ካልን ለሥራም አይመችም በተለይ ለክርስቲያን የሚያሳፍር ነው፡፡ ከቤት ለአንድ ዓላማ
ቢወጡም እግረ መንገድሽ ቤተ ክርስቲያን ሆነ ሌላ ቦታ መድረስ ያስፈልግ ይሆናል፡፡ እንዲሁም በመኪና
መሄድ አለ፣ ቢሮ ውስጥ መስራት አለ፣ አጎንብሶ የወደቀን ማንሳት አለ፣ ልብስ ማጠብ አለ፣ ወዘተ፡፡
ዘመኑ ከሚያመጣው ፋሽን ጋር ለመሄድ ተብሎ ራስን ለአደጋ ማጋለጥ አያስፈልግም፡፡ ለኩራት ብለው
የሚለብሱ ደግሞ አሉ፡፡ ‹‹ልብስ በሌላቸው ላይ ልትመኩ፣ በፈታቸው ልትታበዩ፣ ልቡናቸውን በቅንአት
እንደ ሰም ልታቀልጡ፣ ሰውነታቸውን በቅንአት ልታሳምሙና በኃዘናቸው ላይ ኃዘን ልታመጡባቸው እንጂ
በሌላ ምክንያት አይደለም፡፡›› (ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡
አለባበስ ስለ አንድ ሰው ማንነት ይናገራል
ውጫዊ ቁመና ከውስጥ ምን ዓይነት ሰው እንደሆኑ መቶ በመቶ ባያስረዳም የቀረበ ግምት ለመስጠት
ይረዳል፡፡ ሴቶች እያደጉ ሲመጡ ስለ ልብስ አመራረጥ፣ ስለ ፀጉር አያያዝ፣ በውስጣቸው ምን ዓይነት ሰው
እንደሆኑ ይለያሉ፡፡በነገ. 1፡2-6 ንጉሥ አካዝያስ መልእክተኞቹን ወደ ኤልያስ ልኮ የለበሰውን ልብስ
ሲነግሩት ንጉሡ ኤልያስ መሆኑን አውቆ ነበር፡፡ የይሁዳ ምራት ትዕማርም አማቷ ይሁዳ በዚያ መንገድ
ሲያልፍ በለበሰችሁ ልብስ ጋለሞታ መሰለችው፡፡ (ዘፍ. 38፡13-15)፡፡እህቶች እና እናቶች ለብሳችሁ
ያላችሁት ልብስ ለመሆኑ ምን እንዳስመሰላችሁ ለራሳችሁ መልሱ፡፡ ዘማ? አሮጊቷን ወጣት?የውጭ
ሰው?...

[Type text] Page 31


አጭር ምክር፡- የለበሳችሁት ልብስ ትክክል መሆኑን ለማወቅ ይህን ጥያቄ ጠይቁ፡፡ እኔ የለበስኩት ልብስ
እግዚአብሔር ይደሰትበታል? ለምን ዓላማ ነው የለበስኩት? የክርስቲያን ልብስ ነው? ሰዎች ይህን ለብሼ
ስያዩ ምን ይሰማቸዋል? ስለ ለበስሽው ልብስ ሕሊናሽ ምን አለ? በለበስሽው ልብስ ድንግል ማርያም ትደሰት
ይሆን? ወዘተ ጠይቂና መልስ ስጪ፡፡ ከዚያ ነፍስሽ የነገረችሽን ተግብሪ፡፡ መልስ ከከበደሽ ደግሞ ጹሚ፣
ጸልዪ፣ ስገጂ፣ ከቻልሽ ደግሞ ወደ ገዳማት ሂጂና ከስፍራው እና ከቅዱሳን በረከት ቅመሺ ያን ጊዜ የምንዝር
ጌጥ በሽታ ለቆሽ ይሄዳል፡፡ በመጨረሻም ልብስ መቀያየርሽ በሰዎች ለመወደድ አይሁን በተለይ በወንዶች፤
በመልካም ስራሽ ይውደዱሽ እንጂ በልብስሽ አይሁን፡፡ በልብስሽ የወደዱሽ ለዝሙት ካልሆነ በቀር
ሚስታቸው እንድትሆኚ አይፈልጉም...፡፡
አፍአዊ ጌጥ መውደድ ‹‹አምልኮ ጣዖት ነው››
መታበይ፣ መኩራራት፣ ማማረጥ፣ተስፋ መቁረጥን የመሳሰሉ ኃጢአቶች በሙሉ በአብዛኛው አፍአዊ ጌጥን
ከመውደድ ይወለዳሉ፡፡ ሰዎች ይህን ሲያገኙ እንደሚኮሩና ደስ እንደሚላቸው ሁሉ ያጡትም እንደሆነ
በሕይወታቸው አንድ ታላቅ ነገርን እንዳጡ በመቁጠር ያለ መጠን ሲማረሩና ሲያዝኑ ይገኛሉ፡፡ አልፎ
ተርፎም በተገቢው መንገድ የሚሹትን አፍአዊ ጌጥ ካለገኙ በመስረቅ፣ በመዋሸትና ፍላጎታቸውን ሊያሟሉ
ለሚችሉ ሀብታም ሰዎች በመገዛት ያሟሉታል፡፡ ይህ መገዛታቸው ልክ በማጣቱ ሐሳባቸው ይሟላላቸው
ዘንድ ለዝሙት ከመንበርከክና ከመግደል አንሥቶ ለማንኛውም የኃጢአት ተግባር ወደ ኋላ አይመለሱም፡፡
አፍአዊ ጌጥ ያጡበትንም ሰው እስከ መካድ ይደርሳሉ፡፡
ጌጥን መውደድ ባርነት ብቻ ሳይሆን ‹‹ጣዖት ማምለክ›› ነው፡፡ በተለይ ያለጌጥ ምንም ነገር የማይሆንልሽ፣
ጌጣ ጌጦችሽን ዐሥር ጊዜ ሣጥን ከፍተሸ የምትመለከቺ፣ ዕጣን የምታጭሽ፣ ሽቶ የምትቀቢ፣ የምታናፍሽ
ከሆነ ይህ ጣዖት ሆኖብሻል፡፡ ጣዖት የሚያመልኩ ሰዎች ከዚህ የተለየ ምን ያደርጋሉና፡፡ በእግዚአብሔር
ፊት ሞገስ የሚያሰጠው የዋሕ እና ዝግተኛ መንፈስ እንጂ በሽቶ፣ በቅባትና ማኳኳያ ነገሮች አይደለም፡፡
2 ጢሞ.4፡5፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ ያለው ጌጣ ጌጥና ኮስሞቲክስን ተመለከትሽ ለጊዜው ያሳመሩ ይመስሉና
ከጊዜ በኋላ ግን በተፈጥሮ ያለንን ነገር ላይመለስ አበላሽቶ ይሄዳል፡፡ ከዚህ ከተረፈ ደግሞ ይህም እንደ
ልብስ ዘማ ያስብልሽ ይሆናል እንጂ ሌላ ትርፍ የለውም፡፡ ዘማዊያንስ የሚያደርጉት ይህን አይደለም እንዴ?
የሽቶ ገበያ ለምን እንደተወደደ ታውቂያለሽ? ለዝሙት ዓለም ስለሚውል እኮ ነው፡፡
አፍአ ጌጥን አለመጠቀም ያስመሰግናል፡፡ ለዚህም በመልክዐ ማርያም ‹‹እንሶስላ መጠቀምና ሌላ ምድራዊ
ጌጥን ላልፈቀዱ የእግር ጥፍሮችሽ ሰላምታ ይገባል›› ይላል፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የመጋጌጫ ነገሮች
ከክርስትናዬ ጋር ይሄዳል ወይ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
ስለ ፀጉር አያያዝ
የፀጉር አያያዝ ሕገወጥ እንዳይሆን ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ለእናንተ ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል
ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፡፡›› 1 ጴጥ. 3፡3 1 ጢሞ. 2፡10፡፡
በ 1 ቆሮ. 11፡15 ‹‹ፀጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተስጥቶአታል›› ስለዚህ ፀጉርዋን ማስረዘም ተገቢ ነው፡፡
ፀጉርዋን መቁረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍራት መስሎ ካልተሰማት መቁረጥ ወይም መላጨት መብቷ
ነው፡፡ ፀጉርዋን ካስረዘመች ግን በጸሎት ጊዜ ራሷን መሸፈን/ መከናነብ አለባት፡፡ 1 ቆሮ. 11፡6

[Type text] Page 32


ወንድ ግን ፀጉሩን ቢያስረዝም ነውር ይሆንበታል፡፡ ሠለስቱ ምዕት ስለ ፀጉር በተናገሩበት በፍትሐ ነገሥት
‹‹ፀጉርህን ስበህ እስክታየው ድረስ አታሳድገው›› ብለዋል፡፡ ሐዋ. 18፡18 ያንብቡ፡፡ ካህናት ፀጉራቸውን
አያሳድጉ የሚለው ናዝራውያንን አይመለከትም፡፡ እነ መልከጼዴቅ፣ ሶምሶን፣ ነብዩ ኤልያስ፣ መጥምቁ
ዮሐንስ ፀጉራቸውን አይላጩም፡፡ ዘኁ. 6፡5 መሳ. 13፡5፡፡ ወንዶች ፀጉራቸውን ስያሳጥሩ ጋሜ፣ ቁንጮን፣
ጌጥን ልዩ ልዩ ቅርጽ ማውጣት የለባቸውም፡፡ ዛሬ በየፀጉር ቤቱ የምናየው የፀጉር ስታይል፣ ወንዶች
እየተቆረጡ ያለው ፀጉር ስታይልስ ሕገወጥ መሆኑን እናስተውል አባቶች ግን ‹‹በፀጉርህ ላይ ጌጥ አትተው››
ይላሉ፡፡
ስለ መልክ ካነሳን ደግሞ መጨነቅ አያስፈልግም፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንን በአግባቡ ከመያዝ ውጭ
ልንጨነቅ አያስፈልግም፡፡ ምሳ. 11፡22 ውበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው፤እግዚአብሔርን
የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች፡፡

ክፍል አስራ ሦስት


ምዕራፍ ሰባት
መዝናናት እና መደሰት
መጽሐፍ ቅዱስ መዝናናት እና መደሰትን አይቃወምም፡፡ ዋናው ነገር መዝናናት እና መደሰት በምን መልኩ
የሚለው ነው፡፡በአግባቡ መዝናናት እና መጫወት ከመንፈሳዊነት አንጻር ባይነቀፍም ነገር ግን ይህን
ባያደርጉ የሚመከሩና ቢያደርጉ የሚገሠጹ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ካህናት፣ መነኮሳት፣
ሽማግሌዎችና ባልቴቶች ወዘተ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ሌሎች ግን በልክ እና በመልክ መዝናናትና መጫወት
ይኖርባቸዋል፡፡ (ተግ.ዘዮሐ.አፈ. 7) ወጣቶች በልክ መዝናናት ተገቢ ነገር ቢሆንም ጫወታና ቀልድን
ማዘወተር መልካም አይደለም፡፡ ‹‹ጫወታና ተድላ ደስታን ዘወትር የሚያደርግ ሰው በሥጋውም በነፍሱም
ዘማዊ ነው›› (አረ.መን.ድር.1) እንዲሁም 2 ጢሞ. 3፡4 ‹‹ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ
ይሆናሉ›› የሚለውን የእግዚአብሔርን ፈጻሚ መሆንም አለ፡፡

[Type text] Page 33


እውነተኛ ደስታ ግን የመንፈስ ፍሬ ነው፤ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ነው እንጂ ከሥጋ ጫወታ አይደለም፡፡ያዕ.
5፡13 ‹‹ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር›› መዝፈን አይገባም፡፡ ፊል. 4፡4 ላይም ‹‹በጌታ ደስ
ይበላችሁ፡፡›› ማለቱ እውነተኛ ደስታ ከእግዚአብሔር እና ከእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ከየትኛውም ዓይነት
መዝናኛ በላይ ነገረ እግዚአብሔርን መጫወት እንዲሁም መዘመር እና መጸለይ የበለጠ ያዝናናል፡፡ ዘዳ. 11፡
18-19 ልጆች የእግዚአብሔር ቃል አንዲጫወቱ የማስተማር የወለጆች ኃላፊነት ነው፡፡ 2 ሳሙ. 6፡22
ያንብቡ፡፡
ሌሎች መዝናኛዎች
 ጉብኝት፡- መዝናናት ከተቻለና ካስፈለገ ታሪካዊ ቦታዎችን እየተዘዋወሩ መጎብኘት ቀዳሚውን
ስፍራ ሊይዝ ይችላል፡፡ ለሌላ ገንዘቦችንና ጊዜያችንን ከምናጠፋ የተለያዩ ቅዱሳን ቦታዎች እየሄዱ
መዝናናት ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ከሥጋ ደስታ ይልቅ የነፍስ ደስታ ይገኛልና፡፡ ሐዋ. 8፡27-40
ላይ የኢትዮጵያ ጃንደረባ ያደረገውን ጉዞ ማስተዋል እና መለማመድ መልካም ነው፡፡ ወደ ታሪካዊ
እና የበረከት ቦታዎች በደመ ነፍስ መጓዝ ሳይሆን መጀመሪያ ያለፈጣሪ ረድኤት እና ፈቃድ
እንደማይቻል ማመን ያስፈልጋል፡፡ ዮሐ. 10፡40-42፡፡ ዛሬ በሀገራችን ብዙ የጉዞ ማስታወቂያዎች
ተለጥፈው ታገኛላችሁ ነገር ግን የመጀመሪያ ዓለማቸው ይዘው ከሚሄዱት ሰዎች ገንዘብ
ለመሰብሰብ አቅደው እንጂ ለሕዝቡ ብቻ ታስበው እንዳልሆነ የሚሄደው ሕዝብም መሠረታዊውን
የገዳማት እና የአድባራትን ሥርዓት ጠብቀው ሳይሆን ለመዝናኛ ብቻ አስበው እንደሆነ ባሁኑ ጊዜ
በቦታው ያለው የሥርዓት ጠፍቶ ማግኘታችን ለዚህ አማላካች ነው፡፡ እኛ ግን ወደ እነዚህ ቦታዎች
ስንሄድ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ፤ ሰው ስለሄደ ብቻ አንሂድ ካልሆነ ለበረከት
ሄደን መርገምን ይዘን እንመለሳለን፡፡
 ድራማ፡- አስመስሎ መስራት፣ ማድረግ ነው፡፡ ለማዝናናት፣ ለማስተማር፣ ለተወሰነ ዓላማ
ለማነሣሣት፣ ለማሳመንና እንዲሁም በሰው ላይ ስጋት ለማሳደር ሊሠራ ይችላል፡፡
(ሀ) መንፈሳዊ ተውኔት (ድራማ)፡- በሰንበት ትምህርት ቤቶች አካባቢ መንፈሳዊ መልእክቶችን በተውኔት
መልክ ማስተላለፍ በስፋት የተለመደ ነው፡፡ ጥንቃቄ ግን ያስፈልጋል፡፡ ለማስተማር እንጂ ለፌዝ እና ሰዎችን
ለማዝናናት መሆን የለበትም፡፡ ማዝናናት፣ ማሳቅና ማጫወት የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ አይደለምና፡፡ አሁን
አሁን ግን መሠረታዊውን የወንጌል ትምህርት የተጋፋ ሆኗል፡፡ የወንጌል ሰዓት ተቀንሶ በተውኔት
እስከመመደብ ወይም ትምህርቱን ጨርሶ እስከማስታጎል ይዘልቃል፡፡ ከትምህርተ ወንጌል በኋላ አንድ
ተውኔት ዝግጅት የሚቀርብ ከሆነ አቅራቢዎቹ ቁጭ ብለው አይማሩም፤ታዳሚዎቹም እንዲሁ፡፡ በሰንበት
ትምህርት ቤት መድረክ ላይ ከአዝናኝነቱ ይልቅ አስተማሪነቱ የሚያመዝን መሆን አለበት፡፡ የሚያስቅ መሆን
የለበትም፡፡
ወጣቶች መንፈሳዊ ድራማ ሲሰሩ ማሳዘንም ዓይነት ሊኖረው ይገባል፡፡ መንፈሳዊ ተውኔት የሚጽፉ ሁሉ
ነገረ ሃይማኖትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በሚገባ የተማሩና ቋንቋና ዘይቤውን በሚገባ የተረዱ መሆን
አለባቸው፡፡የዓለምን ነገር እንዳለ አምጥቶ የቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ ማውጣት አይቻልም፡፡
የመናፍቃንን ትምህርት ያሳየን መስሎን በቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ኑፋቄና ዘለፋ ማቅረብ
አያስፈልግም፡፡ የመንፈሳዊ ተውኔት መመዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ መሆን አለበት፡፡ ወጣቶችም በዚህ ዓይነት
መርሐግብር ሲሳተፉ ጥንቃቄ አድርገው ካልቀረቡ መንፈሳዊ ስራ ሰራን እያሉ መቀሰፍ እንዳይሆን፡፡

[Type text] Page 34


 (ለ) ዓለማዊ ተውኔት (ድራማ)፡-አንድ ሰው ተውኔትን እመለከታለሁ ካለ መራጭና አስተዋይ
መሆን ይኖርበታል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ተዋናይ ሃይማኖቱን የሚጻረር ገጸ ባሕርይ ተላብሶ መጫወት
የለበትም፡፡ ሲጋራ በማጨስ፣ ጫት በመቃም፣ በመዳራትና በአደባባይ በመሳሳም ለመተወን
መድፈር አይገባም፡፡ ከከርስቲያን የሚጠበቀው ክርስቲያን መሆን ብቻ አይደለም፡፡ ለክርስቲያን
የታዘዘውን በሙሉ ሳናጓድል መፈጸምና የሚቻለንን አግልግሎት መስጠት ስንችል ነው፡፡ክፉ ክፉ
ገጸ ባሕርይ ተላብሶ በመተወን ክፉ ሰው መሆን ብቻ ሳይሆን መምሰልም ያስጠይቃል፡፡ ሮሜ. 12፡
2 ‹‹ይህን ዓለም አትምሰሉ 0›› ይላልና፡፡ ክፉ ሆነህ በተደጋጋሚ ከሰራህ ያንተ ማንነት ወደ መሆን
ሊለወጥ ይችላል፡፡ በኮምፒዩተር ቅንብር የሠራኸው ትወና አንተን ባይጎዳም ተመልካቹን ጎድቷል፡፡
ይህ ደግሞ ራስ ወዳድነት ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተምህሮ ጋር የማይጋጩና
ከሃይማኖት ጋር የማይጻረሩ ተውኔቶችን እየመረጡ መስራት ኃጢአት አይደለም፡፡ ነገር ግን ዛሬ
ወዴት እያመራ ነው እናስታውል፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መልካም ነገር ነው፡፡ የአካል ቅልጥፍና እንዲኖረን፣ ሰውነታችን እንደልብ
እንዲታዘዝል ለማድረግ ጡንቻችን ብርታትና ጥንካሬያችን እንዲዳብር ይረዳል፡፡ በርግጥ ጤናን የሚሰጥ
እግዚአብሔር ነው፡፡ 1 ጢሞ. 4፡8፣ 2 ጢሞ. 4፡3 ላይ ‹‹ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት
ይጠቅማልና እግዚአብሔር መምሰል ግን የአሁኑና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ነገር ሁሉ
ይጠቅማል፡፡›› ዛሬ ዛሬ የአብዛኛዎች ስፖርታዊ ውድድሮች የደስታ መንፈስና መዝናኛነት እየተቀየረ
በአመዛኙ የገንዘብ ምንጭነታቸው እየጎላ መጥቷል፡፡ ይበልጥ የሚያስደስተው ተመልካቹን ነው፡፡ ለዚህም
ብዙ ወጣቶች ቆስለዋል፣ ጥርሳቸው ረግፏል፣ አጥንታቸው ተስብሯል፣ ጥቂት የማይባሉ ሞተዋል፡፡
ስፖርት ከራሳቸው ድክመት ጋራ ተደምሮ ከጾም፣ ከጸሎትና በሚገባ ለፈጣሪ ከመገዛት እንዲለዩ ምክንያት
የሚሆንባቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በበጎ ጎኑ ከመጠጥ፣ ከጫት፣ ከስጋራና ዝሙት ከመሳሰሉት እንድንቆጠብ
እንደሚያደርግ ሁሉ ለዝሙት ለትዕቢትና ለኩራት የሚያጋልጥበት ሁኔታም አለ፡፡ ‹‹ከንቱ ውዳሴን ዝሙት
ይላካታል፤ ያገለግላታልና›› ይላል ማር. አን.ቀዳ. ምዕ. 4፡፡
ብረት የሚያነሡ ወጣቶች እንደ አካላቸው አንዲሁ ልባቸው እንደይደነድን መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ ማን
ይችለኛል! እያሉ በትዕቢት የሚነፉ ከሆነ ለሠይጣን እንደተገዙ እንኳን አያስተውሉም፡፡
በስፖርት ስም ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት እና ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ከሚቀሩ ስፖርቱ ራሱ ቢቀር ይሻላል፡፡
ስፖርተኛ ሆነህ ትሕትና፣ ንጽሕና መልካም አስተሳሰብ ከምታጣ ስፖርተኝነት ቢቀር ይሻላል፡፡ የስፖርት
አፍቃሪያን (ተመልካቾች) ደግሞ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ለስፖርት ብለው ትምህርት፣ ስራን ቸል
የሚሉ በስተዋል፡፡ ለመሆኑ ሳይሰሩ መብላት አለ እንዴ? ትምህርትን በስርዓቱ ሳይማሩ የሚፈልጉት ደረጃ
አለ እንዴ? ለዚህ አይመስላችሁም ኩረጃ የበዛው፡፡ መኮረጅ ደግሞ ኃጢአት ነው፤ አትስረቅ፣ የባልንጀራህን
ቤት አትመኝ የሚሉ ሕጎች አሉና፡፡ ሌሎች ደግሞ ለስፖርቱ ብለው የሚናደድ፣ ቁማር የሚጫወቱ፣ ብዙ
መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ብዙ ናቸው፡፡

 አጭር ምከር፡- ውድ ወጣት ስፖርት ለምን እንደምትሰራ በትክክል ንገረኝ! ለጤና ወይስ ጡንቻህን
እና ደረትህን ነፍተህ በሰው መሀል ለመሄድ ወይስ ለምን? ብረት በማንሳት ባሳበጥከው ደረትህ

[Type text] Page 35


አንድ ኃጢአት በየቀኑ እየሰራ እንደሆነ ታውቃለህ? (ርቱዓ ሃይማኖት አንብብ):: የተነፋው
ደረትህን እያዩ በዝሙት የሚወድቁ ሴቶች እንዳሉ አስበህ ታውቃለህ?
ለመሆኑ የትኛው ስፖርት ዓይነት ደጋፊ ነህ እውነት በስፖርቱ መርሐግብር ነው ወይስ በራስህ መርሐግብር
ነው የምትመራው? ግን ምን ተጠቀምክ? እዚያ ያጠፋሀቸውን ሰዓቶችስ፣ ከዚያ ወጥተህ ደግሞ ስለ
ጫወታው ለማውራት ያጠፋኸውን ሰዓት አስብ፣ ምናለበት ያንን ዓለማዊ ትምህርት አንብበህበት እንደ
ቅጣው እጅጉ ሀገር ብታስጠራበት፣ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ብትደፍን፣ የብዙ ስፖርተኞችን ስም ከነ
ክለባቸው፣ ደሞዛቸው፣ እድሜያቸው ማወቅን እንደ እውቀት ከምትቆጥር በሀገርህ ያሉ ቅዱሳንን ብታውቅ
ምን አለበት? ይህ የሰይጣን ሴራ ነውን ተወው፡፡
ብለው ትምህርት፣ ስራን ቸል የሚሉ በስተዋል፡፡ ለመሆኑ ሳይሰሩ መብላት አለ እንዴ? ትምህርትን በስርዓቱ
ሳይማሩ የሚፈልጉት ደረጃ አለ እንዴ? ለዚህ አይመስላችሁም ኩረጃ የበዛው፡፡ መኮረጅ ደግሞ ኃጢአት
ነው፤ አትስረቅ፣ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ የሚሉ ሕጎች አሉና፡፡ ሌሎች ደግሞ ለስፖርቱ ብለው
የሚናደድ፣ ቁማር የሚጫወቱ፣ ብዙ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ብዙ ናቸው፡፡

 አጭር ምከር፡- ውድ ወጣት ስፖርት ለምን እንደምትሰራ በትክክል ንገረኝ! ለጤና ወይስ ጡንቻህን
እና ደረትህን ነፍተህ በሰው መሀል ለመሄድ ወይስ ለምን? ብረት በማንሳት ባሳበጥከው ደረትህ
አንድ ኃጢአት በየቀኑ እየሰራ እንደሆነ ታውቃለህ? (ርቱዓ ሃይማኖት አንብብ):: የተነፋው
ደረትህን እያዩ በዝሙት የሚወድቁ ሴቶች እንዳሉ አስበህ ታውቃለህ?
ለመሆኑ የትኛው ስፖርት ዓይነት ደጋፊ ነህ እውነት በስፖርቱ መርሐግብር ነው ወይስ በራስህ መርሐግብር
ነው የምትመራው? ግን ምን ተጠቀምክ? እዚያ ያጠፋሀቸውን ሰዓቶችስ፣ ከዚያ ወጥተህ ደግሞ ስለ
ጫወታው ለማውራት ያጠፋኸውን ሰዓት አስብ፣ ምናለበት ያንን ዓለማዊ ትምህርት አንብበህበት እንደ
ቅጣው እጅጉ ሀገር ብታስጠራበት፣ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ብትደፍን፣ የብዙ ስፖርተኞችን ስም ከነ
ክለባቸው፣ ደሞዛቸው፣ እድሜያቸው ማወቅን እንደ እውቀት ከምትቆጥር በሀገርህ ያሉ ቅዱሳንን ብታውቅ
ምን አለበት? ይህ የሰይጣን ሴራ ነውን ተወው፡፡

 ሲኒማና ቴሌቪዥን
ተንቀሳቃሽ ስዕል ፊልም ይባላል፡፡ በሲኒማ የምናያቸው ነገሮች ተዋሕደውን የኛ አንድ አካል ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ፊልም ላይ ያየኸውን ለጊዜው ልትጠላው ትችላለህ፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን በቅጽበት ማሰብ
ትጀምራለህ፡፡ ሰይጣን ደግሞ ልዩ ልዩ የኃጢአት ሥራዎችን እንድትመለከት በር ይከፍታል፡፡
ወደፊት በምዕራባውያን የሚሠሩ ፊልሞች የሀገራችንን የማይውጥበት ምክንያት የለም፤ አሁንም እያየን
ስለሆነ፡፡ ብዙ ፊልሞች ትዕቢትን፣ የዘር ልዩነትን፣ አድልዎን፣ ጭካኔንና ግፍን፣ ቅንጦትን፣ ግለኝነትን፣ የራስ

[Type text] Page 36


ጥቅምን ማስቀደምን፣ የሥልጣን ሽሚያንና ስግብግብነትን፣ ምንዝርን፣ ዝሙትን፣ ግብረ ሰዶምን፣ ዓመፅን፣
ስርቆትን፣ ቂምንና የሕዝብ መጨፍጨፍን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ፊልም የሰው ልጆችን ሊጎዳ የሚችለው በብዙ አቅጣጫ ነው
 መጥፎ ድርጊቶችን የሚያንጸባርቁ ፊልሞችን ደጋግሞ ማየት ውጤቱ ያው ነው፡፡
መተሻሸት፣መተቃቀፍ፣ ብዙ ተራክቦን የሚያሳይ ካየህ ለፍትወት መነሳሳትህ አይቀሬ ነው፡፡
እግዚአብሔርን በደልክ ማለት ነው፡፡
 በፊልሙ ላይ ከሚታዩት ዓይነት ሰዎች ጋር እንደዋለ ያህል ሊቆጠር ይችላል፡፡ መዝ. 17፡26
‹‹ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ፡፡››
 ምንም እንኳን በተግባር ባትፈጽመውም ክፉ ነገርን በደስተኛ ልብ መቀበል በራሱ መርከስ ነው፡፡
በሥጋ የሚፈጸመው በልቡና ወጥቶ ወርዶ የተወሰነ ሐሳብ ነው፡፡
 ዝሙት የሞላባቸውን ፊልሞች መመልከትህ ወደ ክፉ ኃጢአት ይወስድሃል፡፡ አጠገብህ ሰው
ስለሌለ የዝሙት ፊልሞችን ታይህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የማታየው እግዚአብሔር ካንተ ጋር መሆኑን
አትርሳ፤ ቅዱሳንም በዙሪያህ ናቸውና ተው ይቅርብህ፡፡
 ፊልምን አዘወትሮ መመልከት ሱስ የመሆን ባሕርይ አለው፡፡ 1 ቆሮ. 6፡12 ‹‹ሁሉ ተፈቅዶልኛል
አንድስ እንኳን በእኔ ላይ አይሰለጥንብኝም›› ጊዜን ማጥፋት፣ ነገሮችን ችላ ማለት ይከተላሉ፡፡
 በፊልም ያዩትን በትዳራቸው በመተግበር ትዳራቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሰዎች አሉ፡፡
 ፊልም አዘወትሮ መመልከት እንደ ፊልሙ ተዋናይ የመኖር ምኞትን በማሳደር ተግቶ በመሥራት
የማግኘት ወኔን ይሰልባል፡፡ ወጣቶች በሕልም ዓለም እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡
 ፊልም ወጣቱ ሁሉን ነገር ያለ ረድኤተ እግዚአብሔር ለማግኘት የሚያስቡ ትዕቢተኞች
ያደርጋቸዋል፡፡
 ፊልም ዘወትር የሚመለከት ወጣት ነጻ ተመልካች መሆን አይችልም፡፡ እርሱ ራሱ በአንድ አቅጣጫ
በፊልሙ ውስጥ ይተውናል፡፡
 መልካም ነው ከተባለው ፊልም እንኳን ባላሰብከው መንገድ አንድ መልካም ባሕርይህን ታጣለህ፡፡
ሌብነትን፣ ዝሙትን፣ ጉልበተኛነትን፣ ውሸትንና የመሳሰሉትን ሳታወድስ አትቀርም፡፡መዝ. 9፡23

ምክር፡- እኛ ክርስቲያኖች ዓለማውያን ፊልም የሚሠሩት ገንዘብ ለማግኘት እና የሠይጣንን አሰራር


ማሰረጨት ስለሆነ ልንርቀው ያስፈልጋል፡፡ ከዘፈን ይበልጥ የሰውን ሕይወት ወደ ክፉ ጎዳና ሊወስድ
የሚችል እንደሆነ የሚካድ አይደለም፡፡ ብዙ ለማግኘት ብለው ፊልም የሚያከራዩ ክርስቲያኖችም አሉ ግን
ይህ ስራቸው ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጋር አይሄድም፡፡ ስለዚህ ከወዲሁ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ከፊልም
ሱስ ነጻ ለመሆን መጀመሪያ ከፊልም ጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያዘነብል ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የቀረውን ደግሞ
ከ‹‹ሕይወተ ወራዙት ክፍል 2 አንብብ፣ ንስሐ አባትህን አማክራቸው››

ክፍል አስራ አምስት


ምዕራፍ ስምንት
ወጣት እና የሚያሠክር መጠጥ መጠጣት

[Type text] Page 37


... መጽሐፍ ቅዱስ መስከርን እና ለብዙ የወይን ጠጅ መጎምጀትን እንጂ በልክ መጠጣትን አይቃወምም፡፡
ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን በቃና ገሊላ በእናቱ አማላጅነት ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ የለወጠው፡፡
ክርስቶስ ለውጦ የሰጣቸው የወይን ጠጅ አልኮልነት የሌለውና የማያሳክር ሆኖ አይደለም ነገር ግን
ልካቸውን አውቀው መጠጣት የሰዎቹ ድርሻ ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን ወጣቶች መጠጥ ሲጠጡ አእምሮኣቸው
እስኪስት ድረስ መጠጣት ኃጢአት ነው፡፡ ምክንያቱም መስከር ያስቀጣልና፡፡በአግባብ ከተጠጣ መልካም
መሆኑን ሲገልጽ ቅዱስ ጳውሎስም የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ ሲጽፍ ‹‹ስለ ሆዲህ ስለ ብሽታህ ብዛት ጥቂት
የወይን ጠጅ ጠጣ፡፡›› (1 ጢሞ. 5፡23) በሌላ መልኩም ወይን በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም ይቀርብ
ነበር፡፡ ማቴ. 26፡17-29፣ ሉቃ. 10፡34፣ ጦቢ. 4፡15፣ ሲራክ. 34፡24-26፣ ቲቶ. 2፡3፣ 1 ጢሞ. 3፡8፡፡
እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡ ስለ መጠጥ ብዙ ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡ ለማንኛውም ግን ሁሉም ነገር በግባብ
ካልሆነ ጉዳቱ የከፋ ነው፤ መጠጥም እንዲሁ፡፡
 የአልኮል መጠጥ የሚያስከትለው ጉዳት
መጠጥ ከመጠን በላይ ከሆነ ያሰክራል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ሰው ከመጠን በላይ መጠጣቱን ና መስከሩን
እንኳን ላይገነዘበው ይችላል፡፡ የስካርን ጉዳት ሲገልጽ ‹‹ዋይታ ለማን ነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን
ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው? የወይን ጠጅ
በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈትኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን? ወደ
ወይን ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ፥ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ፥ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ። በኋላ እንደ
እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል።ዓይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን
ይናገራል።›› (ምሳ. 23፡29-33)
ስካር ማስተዋልን ያሳጣል፤ የራስን ተድላ እንጂ የሌላን አያሳስብም፡፡ ሰካራም ስለማያስተውል የተመከረውን
በሙሉ አይሰማም ይረሳል፡፡ ሰው ከሰከረ ሕዋሳቱ እንደማይቀናጁለት ሁሉ አእምሮውም በትክክል
አያስብም፡፡ አዝወትሮ የሚሰክር ከሆነ ደግሞ የአእምሮ ስራ ይዛባል፡፡ ለዚህ ነው ነብዩ ሆሴዕ ‹‹ግልሙትናና
የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል›› (4፡11) ያለው፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሶሎሞን በምሳሌው
‹‹የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፥ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በዚህም የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም››
(ምሳ. 20፡1) ሉቃ. 21፡34፡፡
ስካር ወደ ዝሙትና ወደ ጉልምትና ነው የሚያመራው፡፡ ይህም ጠቢቡ ሶሎሞን እንዲህ ይላል ‹‹ወደ ወይን
ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ፥ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ፥ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ። በኋላ እንደ እባብ
ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል። ዓይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን
ይናገራል›› (ምሳ. 23፡31-33)፡፡ አንድ ነገር ልንገራችሁ በየመጠጥ ቤቱ የሚያስተንግዱ እህቶች
መስፈርታቸው ወንዶችን በዝሙት መሳብ የምትችል መሆን አለባት፡፡ ሎጥ ላይ የደረሰውን ማስታወስ ግድ
ይላል፡፡ በኃጢአት ምክንያት ሰዶም እና ጋሞራ ሲጠፉ ሚስቱም፣ ልጆቹን ሊያገቡ የሚችሉ ወንዶችም
ጠፉ፡፡ ነገር ግን ልጆቹ በወይን ጠጅ አስክረውት ከእርሱ ጋር ተኝተዋል፡፡
ስካር የስጋ ስራ እንጂ የመንፈስ አይደለም፡፡ (ገላ. 5፡19፣ ሮሜ. 13፡13) ንስሐ ካልገቡ የስካር መዘዙ
በምድር ብቻ የሚቀር አይደለም ‹‹ሰካራሞች የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› (1 ቆሮ. 6፡10)፡፡
እንዲሁም ኢሳ. 28፡1-8፣ ምሳ. 23፡29፣ ኢዮ. 1፡5፡፡ሌሎችንም በዚህ መልኩ እናስብ የጤና፣
ሱስ፣የሰላም፣ የወጭ...፡፡ሌላውን ከሕይወተ ወራዙተ ክፍል 2 ያንብቡ፡፡
[Type text] Page 38
ክፍል አስራ ስድስት
ምዕራፍ ዘጠኝ
ዘፈንና ወጣቶች
ዘፈን በቅኔና በግጥም ከልዩ ልዩ የድምጽ መሣሪያ ጋር እየተቀነባበረ የሚቀርብ ስልት ያለው ጩኸት ወይም
ድምጽ እና የተውኔት ዲቃላ ሲሆን ዓለማውያን ሰዎች ደስታቸውን የሚገልጡበት ነው፡፡ ዘወትር ለሥጋ
ፍላጎት የተሟላ ኃላፊ ፍቅርን ያወሳል፡፡ስለዚህም ፈጣሪ ሳይሆን ሰው እንዲመለክ በማድረግ የሰይጣን
ተገዥ መሆን ማረጋገጫ ነው፡፡ አሁን አሁንማ በግልጽ ሰይጣንን የሚያወድሱ ሰዎች ተነስተዋል፡፡
ዘፈን ከአካል እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ትስስር ከመረመርክ ይጮኻሉ፣ ተንቀሳቃሽ ፊልሞችም እንዲሁ
በድምጽ የታጀቡ ናቸው ለመቀስቀስ እና ተጽእኖ ለመፍጠር ነው፡፡ ዘፈንም እንዲሁ ሰውን የመግዛት ኃይል
አለው፡፡
 ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና (ኢሳ. 13፡21) እንዲሁም በ 1 መቃ. 36፡27-28
‹‹... እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ
ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› እስኪ በሀገራችንም ሆነ ሌሎች ሀገሮች ዘፋኞች ፀጉራቸውን አንጨብረውና
በመጠጥ እና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛው የባለዛሮች
ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ሐዊ ትምህርት ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ ነው፡፡ እንዲሁም የጭፈራ ዓይነት
ሁሉ ምንጮች አጋንንት ናቸው፡፡
 ዘፋኝነት የሰጋ ስራ ነው፡፡ (ገላ. 5፡21) ሮሜ. 13፡13፣ 2 ጴጥ. 2፡13-15፡፡ ዘፈን በዜማው፣
በግጥሙና ከእርሱ ጋር በተጎዳኘ ባሉ ነገሮች ማለትም በስካር፣ በዳንስ፣በጭፈራ፣ በእስክስታና
በአጠቃላይ ውዝዋዜን በመሳሰሉ አጋሮቹ በመታገዝ ወደ ዝሙትና ወደ ከፋ ኃጢአት የሚያመራ
ነው፡፡ ዛሬም የምናየው ይህንን ነው፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ከዚህ መራቅ አለበት፡፡ ዘፈን የሰይጣን ነው፡፡
ሱስ ወደመሆን ያድጋል ያን ጊዜ መላቀቅ ይከብዳል መንፈሳዊነትን ይጋፋል፤ ለጸሎት ለመዝሙርና
ለምስጋና፣ ለመንፈሳዊ ነገር ያለን ፍቅርና ትጋት እንድበርድ ያደርጋል፡፡ ከዚያም የረከሱ የአጋንንት
ማደርያ ያደርጋል፡፡ (1 ሳሙ. 16፡23) ንጉሡ ሳዖል ላይ ያደረው አጋንንት በደዊት በገና ይርቅ
ነበር፡፡
 የዘፈን አድማጭ የዘፈን ተባባሪ ነው፡፡ዘፋኙ ዘፈንን ከውስጡ በአንደበቱ አማካኝነት አውጥቶ
ለሌሎች ያጋራል፡፡ አድማጩ ደግሞ በጆሮው ይጋራል፡፡ እንደውም የአድማጩ ይብሳል፡፡ ስለዚህ
ዘፈን ባለመስማት ከፈለግን ልባችንን ለዘፈን መስጠት አያስፈለግም፡፡ መስማት እና ማዳመጥ
ይለያያልና፡፡ በዘመናት ዘፈን ጎጂ እንጂ ጥቅሙ ታይቶ አያውቅም ስለዚህ እንዝፈን አንስማ፡፡ (ዘፍ.
4፡21፣ መሳ. 16፡23-31፣ ዘጸ. 17፡31)
የመናፍቃን መዝሙር
ዘፋኝነት እና ዘፈን መስማት ለመንፍቃን መዝሙር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የመናፍቃን መዝሙር
ከሚያስጨፍር ዘፈን አይለይምና፡፡ዘፈን መስማት ኃጢአት ነው የመናፍቃንን መዝሙር መስማት ግን
ዓመፅና ክህደት ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው ብዙ ዘፋኞች ወደ መናፍቃን የሚሄዱት ዋና ስራቸው ግጥም መቀየር

[Type text] Page 39


ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ሁለቱም የአጋንንት ስለሆኑ ማለት ነው፡፡ የክርስቶስ ስም ስለተጠራበት አትመን ክርስቶስ
አይደለም፡፡ በክርስቶስ ስም የመጣ የሠይጣን ትምህርት እና ተቋም ማኅበር ነው፡፡ ብዙ ዕውቀት ለማግኘት
እነዚህን አንብባቸው (1 ቆሮ. 10፡18፣ ኤፌ. 4፡5፣ 2 ቆሮ. 11፡13፣ ዘጸ. 23፡13፣ 2 ቆሮ. 11፡14-15)፡፡
 ዘፋኝነት የአደባባይ ኃጢአት ነው ቤተ ክርስቲያንም ታወግዛለች፡፡ የተጠመቀ ሁሉ ከዘፈን የተለየ
መሆን አለበት ክርስቲያን ሆኖ ዘፋኝ የለምና፡፡ ዛሬም ብዙዎች በዚህ ሕይወት ሲኖሩ እንመለከታለን
ትክክል ግን አይደለም፡፡ ዘፋኝ እና ዘማሪ መሆን አይቻልም፣ ዘፋኝ እና ክርስቲያን መሆን
አይቻልም፡፡ በሕዝብ ፊት ዘፋኝነትን ትተናል ብለው ከተመለሱ ብቻ ቤተ ክርስቲያን
ትቀበላቸዋለች፤ ማስተማሯን ግን አታቋርጥም፡፡ ካልሰመዋት ግን እግዚአብሔርን ትተው የዘፈን
አባት የሆነውን ሰይጣንን ሰምተዋልና ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላሉ፡፡ ገላ. 6፡7፣ 1 ሳሙ.
15፡22፣ ሮሜ. 2፡3

ክፍል አስራ ሰባት


ምዕራፍ አስር
ወጣት እና አደንዛዥ ዕፀዋት
በዘማናችን የሰው ልጆች አደንዛዥና አፍዛዥ ወይም ከመጠን በላይ አነቃቂ የሆኑ መርዛማ ዕፀዋትን ባሉበት
ሁኔታ ከመጠቀም ማለትም አኝኮ ከመዋጥና ጨምቆ ከመጠጣት አልፈው ሄደዋል፡፡ ዕፀዋቱን ንጥረ ነገር
ለይተው በማውጣት በመርፌ ለመጠቀም በሚመች መንገድና በሚዋጡ እንክብሎች መልክ አዘጋጅተው
ይጠቀሟቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ከአንድ ወር በላይ ሊያነቁ ወይም አንድን ሰው ችግሩንና ጉዳቱን እንዲረሳ
ሊያፈዙት የሚችሉ ናቸው፡፡
ዛሬ ዛሬማ አደንዛዥ፣ መርዛማና አደገኛ ዕፀዋት ከተጠቃሚዎቻቸው አኀዝ መበርከት ባሻገር በግለሰብእና
በአገር ደረጃ ዋነኛ የሀብት ማግኛ መንገድ ሆነው እየተቆጠረ ነው፡፡ በፊት በድብቅ ወደ ከተሞች ይገባ የነበሩ
ዕፀዋት ዛሬ ግን በይፋ ይጫናሉ፣ በአደባባይ ይቃማሉ...፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ለዘመናት ስታወግዝ
ኖራለች፡፡ ወደፊትም ትኖራለች፡፡
ትንባሆ ማጨስ፣ ጫት መቃም፣ ሺሻ መማግ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገቢ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም እኛ
የአግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ደግሞ የሚታጠነው ዕጣን እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
እንዲሁም በስጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ የሚለውን የእግዚአብሔር ሕግ መጣስ ይሆንብናል፡፡ 1 ቆሮ.
6፡20፣ 1 ቆሮ. 3፡17፡፡
ሲጋራ፣ ጫት እና የመሳሰሉት ሁሉ ሱስ በመሆን የሰው ልጆች በተፈጥሮ ያገኙትን ነጻ ፈቃድ ስለሚጻረሩ
ሰው ሊጠቀምባቸው አይገባም፡፡ባሪያ ያደረገን ነገር ደግሞ ከእግዚአብሔር ይለየናል፡፡ 1 ቆሮ. 6፡12 ‹‹ሁሉ
ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ
አይሠለጥንብኝም፡፡›› ይህን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ ደግሞ ‹‹አእምሮንና አካልን ሁሉ
የሚጎዳና የሚገድሉ ተክሎች የተከለከሉ ናቸው፡፡›› (ፍ.ነ.አን.23፡804-807)

[Type text] Page 40

You might also like