You are on page 1of 4

👉መግቢያ

አንድ የምታውቃት ሴት በድንገት መሬት ላይ ወድቃ ራሷን ሳተች። ሰውነቷ ግትርትር ያለ ሲሆን ጭንቅላቷ እንዲሁም
እግሮቿና እጆቿ መንዘፍዘፍ ጀመሩ። በአፎቿም አረፋ መድፈቅ ጀመረ…..

ታዲያ አንተ ወይም አንቺ ይህችን ግለሰብ የሚጥል በሽታ እንዳለባት ካወቅህ/ሽ ምን አይነት የሕክምና እርዳታ
ትሰጣታለህ/ትሰጫታለሽ ?

ወይስ እነደነዚህ ሰዎች ሽሽትን ትመርጣለህ/ትመርጫለሽ

/////////////////////////////////pause1

በውይይት መሃል ወይም በእንቅስቃሴ ላይ ልትሆን ትችላለህ ድንገት ግን ወደ አዕምሮህ ጏዳ ይህን ነገር የት ነበር
የማውቀው ተመሳሳይዩን ነገር በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ አድርጌያለው በሚል ስሜት ትዋጣለህ

ነገር ግን እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ ይህን ነገር ልትፈፅመው እንደቻልክ ልታውቅ ስላልቻልክ አማትበህ ወይም
የምታምነውን የፈጣሪ ስም ጠርተህ ቅዠት እንደሆነ በማሰብ ታልፈዋለህ፡፡

//////////////////////////////////pause2

ክቡራን አድማጮች በዛሬው ፕሮግራም ስለሚጥል በሽታና ተዛማጅ የሆኑ ችግሮችን እንዳስሳለን እናንተም
እንደተለመደው ቻናላችንን ላይክና ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ብትጀምሩ ለኛ መበረታታትን ለናንተ ደግሞ ስለጤናዎ
መረጃ የማግኘት ጥምን ይቆርጣል፡፡

🌿🌿ይህ ስለርስዎ ጤና እየተጋ የሚገኘው ጥበበ ሰሎሞን የባህል ህክምና ማዕከል ነው፡፡

መልካም ቆይታ

👉የሚጥል በሽታ (የመንዘፍዘፍ ችግር )

በሃገራችን ኢትዮጵያ ከያንዳንዱ 1000 ሰዎች መሃል 5 ከመቶ የሚሆነው የህዝብ ቁጥር በሚጥል በሽታ እንደተያዘ
አንዳንድ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ይህ ቁጥር አሁን ካለን ህዝብ ቁጥር አንጻር ሲቃኝ ከ 360 እስከ 400 ሺህ የሚደርሱ
የሚጥል በሽታ ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ከድህነት ወለል በታች በቂ ህክምና ሳያገኙ እንደሚኖሩ ይገመታል።ይህ ችግር
ከ 10 እስከ 19 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ብሶ እናገኘዋለን፡፡

የሚጥል በሽታ፤- ለአካል ጉዳት፣ ለመገለል፣ ለአድልኦ፣ ለሰብአዊ መብት ጥሰትና ያለ ዕድሜ ለመሞት ከፍተኛ ዕድልን
ይፈጥራል፡፡
ክቡራን አድማጮች መቼም ባካባቢያችን ወይም በቤተሰብ ውስጥ ይህ ችግር ሲከሰት ተመልክተን ይሆናል ነገር ግን
ለጉዳዩ ያለን አመለካከት ወይም እውቀት ዝቅ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ትልቅ ትኩረት ተሰቶት አያውቅም ቢባል ድፍረት
አይሆንብንም፡፡

👉ለመሆኑ የሚጥል በሽታ እንዴት ይከሰታል

በአደጋ ወይም በስነልቦና የሚከሰት የሚጥል በሽታንና በመንፈሳዊ ችግሮች የሚከሰትን የሚጥል በሽታን እንዴት መለየት
እንችላለን በህክምና ማእከላችንስ የሚታከመውና የማይታከመው የሚጥል በሽታ አይነት የትኛው ነው ?

ተከታተሉን

👉በአደጋ ወይም በስነልቦና የሚከሰት የሚጥል በሽታ

የሚጥል በሽታ በተደጋጋሚ የሚያንቀጠቅት የአንጎል ሕመም ነው ። የሚጥል በሽታ በሁሉም ፆታዎች፣ ዘሮች፣ ጎሣዎችና
የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ያጠቃል።

የመንቀጥቀጥ ምልክቶቹ ይለያያሉ።

አንዳንድ ሰዎች ላይ አንድ ጊዜ ብቻ መንቀጥቀጥ ሊያጋጥማቸው ይችላል ይህ ማለት ግን የሚጥል በሽታ አለባቸው
ማለት አይደለም።

ትክከለኛው የሚጥል በሽታ ግን ቢያንስ በ 24 ሰዓት ውስጥ ሁለቴና ከዛ በላይ ያህል የሚያንቀጠቅጥ ስሜት ያለው በሽታ
ነው፡፡

👉ዋና ዋና ምልክቶቹ

የሚጥል በሽታ የሚከሰተው በአንጎል ውስጥ በሚከናወኑ የተዛቡ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ስለሆነ የአንጎል
የስራ ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖን ያሳድራል። ዋና ዋናዎቹ የመንቀጥቀጥ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ

👉ጊዜያዊ የሆነ የግራ መጋባት ስሜት

ትኩር ወይም ትክ ብሎ መመልከት

የጡንቻዎች መገታተር።

ይህም ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ በእጆችና በእግሮች ላይ የሚካሄደውን ትክክለኛ ዕንቅስቃሴ መቆጣጠር አይቻልም ፡፡

ራስን የማጣት ስሜት ።

የሚጥል በሽታ ያለባቸው ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ጠባያቸው ፍፁም ተለዋዋጭ ሊሆንና ግራ ሊያጋቡ ይችላሉ።

በፍርሃትና በጭንቀት ሊዋጡ ይችላሉ ፣ ወይም ደግሞ ከላይ በመግቢያችን ላይ ላይ ያነሳነው አይነት ስሜት ሊሰማቸው
ይችላል፡፡
ደጃቩ (déjà vu) ምን ማለት ነው

(የሥነ ልቦና ችግር)

በግምት 97% የሚሆኑ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ déjà vu አጋጥሟቸዋል። déjà vu ፈረንሳይኛ
ቃል ሲሆን ትርጉሙን ወደ አማርኛ ስንመልሰው "ቀድሞ የታየን ነገር" ይገልፃል፡፡

👉ደጃቩ ማለት በውይይት መሃል ወይም በእንቅስቃሴ ላይ ልትሆን ትችላለህ ድንገት ግን ወደ አዕምሮህ ጏዳ ይህን ነገር የት
ነበር የማውቀው ተመሳሳይዩን ነገር በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ አድርጌያለው በሚል ስሜት ትዋጣለህ ነገር ግን እንዴትና
በምን አይነት ሁኔታ ይህን ነገር ልትፈፅመው እንደቻልክ ልታውቅ ስላልቻልክ አማትበህ ወይም የምታምነውን የፈጣሪ
ስም ጠርተህ ቅዠት እንደሆነ በማሰብ ታልፈዋለህ፡፡

በደጃቩ ላይ ጥናት ያደረጉ አንድ ዶ/ር “Déjà vu ማለት የውሸት የመተዋወቅ ስሜት ነው” ብለው ገልፀውታል።

"አእምሮህ አንድ ዓይነት ሁኔታ ከዚህ በፊት እንደኖርክ ስሜትን ይፈጥራል፣ ነገር ግን ከትውስታህ ውጪ ምንም መውጣት
አትችልም እናም ደግሞ ትክክለኛውን ሁኔታ መለየት አትችልም።"

déjà vu እንዲከሰት የሚያደርገው ምንድን ነው?

የ déjà vu ስሜት ሲያጋጥምህ፣አእምሮህ ቅዠትን እየፈጠረ እንደሆነ ሊሰማክ ይገባል። ምክንያቱም ይህ ሁኔታ
የሚፈጠረው በሁለት የአንጎል ክፍሎች መካከል ትንሽ አለመግባባት ሲፈጠር ነው ተብሎ ይታሰባል።

"Déjà vu የሚከሰተው የማስታወስ ችሎታን እና ትውውቅን ሚና በሚጫወቱ የአንጎል ክፍሎች መካከል ባለው ግንኙነት
ምክንያት ነው" ሲሉ ዶክተሩ ያብራራሉ።

የሚጥል በሽታ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ መንቀጥቀጥ እና ሌሎች የጡንቻ እንቅስቃሴዎችን ያስከትላል። ከዚህ አይነት
የሚጥል በሽታ ጋር የተያያዘው Déjà vu ብዙውን ጊዜ የግንዛቤ ማጣት፣ የመንቀጥቀጥ፣ ምላስን የመንከስ፣ ሽንትን
አለመቆጣጠር እና ከንዴት በኋላ ግራ ከመጋባት ስሜት ጋር ይያያዛል።

👉ከመንቀጥቀጥ በፊት ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች

የመንቀጥቀጥ ችግር ያለባቸው አንዳንድ ሰዎች መንቀጥቀጥ ከመጀመሩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አንዳንድ
የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ያያሉ።

የማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ በሚታዩበት ጊዜ በጨጓራ ውስጥ የማቃጠል ስሜትን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ወይም ደግሞ
የፍርሃት ስሜቶችን ሊጨምሩ ይችላሉ።
በአንድ የአንጎል ክፍል ውስጥ ብቻ በሚከናወነው እንቅስቃሴ ምክንያት የሚያንቀጠቅጥ በሽታ ሲከሰት በሁለት ምድቦች
ከፍለን ማየት እንችላለን

የመጀመሪው ተለዋዋጭ የሆኑ ስሜቶችን የማንፀባረቅ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡ የመልክ፣ የሽታ፣ የስሜት፣ የጣዕም ወይም
የድምፅ ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ። በተጨማሪም ይህ ዓይነቱ መንቀጥቀጥ እንደ ክንድ እና እግር ያሉ የሰውነት
ክፍሎችን እንዲዝሉ ሊያደርግ ይችላል። እንደ ማቅለሽለሽና የመሳሰሉ አይነት ስሜቶችንም እንዲከሰቱ ያደርጋል።

ሌላኛው የመንቀጥቀጥ ስሜት ደግሞ በሕልም አለም ላይ ያለን ያህል ስሜት ይፈጥራል ። ቀና ብለው ወደላይ ብቻ
አተኩረው ሊመለከቱ ይችላሉ ይህን ሲደርጉ ግን አካባቢያቸው ላይ ያለውን ክንዋኔ በመርሳት ነው፡፡ለምሳሌ እሳት ቢነሳና
ሰዎች እየጮሁ ቢያመልጡም አነዚህ ሰዎች ግን እርዳታ ካለገኙ በስተቀር በእሳት ሊበሉ ይችላሉ.......ይቀጥላል

👉አድራሻ:- አዲስ አበባ ጀሞ አንድ ኮንዶሚንየም መስታወት ፋብሪካው አካባቢ በኖላ ህንፃ እና በሳውዝ ዌስት ት/ቤት
መካከል ብሎክ 39/01 ወይም ሲኤምሲ አደባባይ ፀሀይ ሪል እሰቴት ፊት ለፊት የተባበሩት ማደያ አጠገብ እጅጋየሁ
ዲባባ ህንፃ 1 ኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል፡፡

☎️☎️0920519323

You might also like