You are on page 1of 12

Chapter 2

📖SENSATION AND PERCEPTION

በዚህ ቻፕተር ስር የምናየው👇

📍The sensory laws:

▪️Sensory thresholds

▪️Sensory adaption

📍Perception

▪️Selectivity of perception

▪️Form perception

▪️Depth perception

▪️Perceptual Constancies

▪️Perceptual Illusion

🌷The meanings of sensation and perception

#Sensation is the process whereby stimulation of receptor cells in the eyes, ears, nose, mouth,
and surface of the skin sends nerve impulses to the brain.

🔰Sensation (ስሜት) በእርግጥ ለማብራራት ቢከብድም እንኳ፦ በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ውስጥ ያሉት
የ receptor cells

Stimulation ወደ አይምሮአችን Nerve impulse ኡን ሲልኩ ያለው ሂደት ነው ስሜት ሚባለው።


አልገባቹማ😇 ቆይ በኃላ በምሳሌ ስነግራቹ በደንብ ግልፅ ይሆናል።

📍Sensation is therefore the process that detects the stimulus from the environment.

📍Examples of sensation

✧Color

✧brightness

✧the pitch of tone

✧bitter taste...
Sensation እና Perception

ልዩነታቸው ምንድነው??🤨

እነዚህ መነጣጠል በጣም ከባድ ነው። ሆኖም ግን እስቲ እንያቸው

ለምሳሌ እኔ ድምፄን ከፍ አድርጌ "Moshe" ብል እናንተ በጆሮአቹ ይህን ድምፅ ሰምታችኋል፣ መስማታቹ
Sensation ይባላል።

ግን ደግሞ ቶሎ ወደ አይምሮአቹ የሚመጣው ምንድነው? እኔ ወደ አይምሮዬ ሚመጣው "__"

የሚል ነው😁 (ወደ አይምሮአችሁ የሚመጣውን ባዶ ቦታው ላይ ሙሉት) ስለዚህ ያንን ቃል (Moshe)
ሰምታቹ ወደ አይምሮአቹ የሚመጣውን ነገር perception ማለት እንችላለን።

ይቺን የ perception definition እዩልኝ በጣም ግልፅ ታረጓለች👇

📍Perception is the process that organizes sensations into meaningful patterns.

It is the process whereby the brain interprets sensations, giving them order and meaning.

አይምሮአችን አካላችን የሰማውን፣ ያየውን፣ የቀመሰውን ትርጉም ወዳለው ነገር ሲለውጥ ያን ጊዜ

Perception ‍♂
ይባላል‍
🤷‍️️ ♂
‍♂️

📖The sensory laws

📍Sensory threshold is the minimum point of intensity a sound can be detected.

ድምፅን ለይትን የምናውቅበት አነስተኛው (minimum ኡ) ነጥብ ማለት ነው Sensory Threshold ማለት።

ሁለት አይነት የ Sensory Threshold ህጎች አሉ

1️⃣Absolute Threshold

2️⃣Difference Threshold

🌷The absolute threshold The minimum amount of stimulation a person can detect is called
the absolute threshold, or #Limen.

ለምሳሌ ሻይ ውስጥ ግማሽ ማንኪያ ስኳር ተጨምሮ ልክ

ስትቀምሱት ጣዕም ካለው🥰 ለዚኛው Stimulus ግማሹ ማንኪያ ስኳር እንደ Absolute threshold ነው
የሚወሰደው።

🙌Stimulus ማለት ምን እንደሆነ ገብቷቸዋላ አምስቱ የስሜት ህዋሳት ከውጫዊ ነገር ጋር ግንኙነት
ሲኖራቹ(Eg. እጃቹን እሳት ላይ ጭናቹ እሳቱ እያቃጠላቹ
እንደሆነ አይምሮአቹ ሲረዳ፣ ስኳሩን ቀምሳችሁ ጠዓም እንዳለው ስትረዱ ምናምን this is stimulus😇)



‍I think


‍️ ️ it's clear abt Absolute threshold let's proceed♂
‍♂
‍️ ️ 🚶
🚶️‍ 🚶‍
️‍
♂️

🌷Difference Threshold

In addition to detecting the presence of a stimulus, you also detect changes in the intensity of a
stimulus. The minimum amount of change that can be detected is called difference threshold.

ይሄ ደግሞ ለምሳሌ ዕሩብ ማንኪያ ስኳር ለሻይው እንደማይበቃ ስታቅ (ሳትቀምሰው) ስኳሩን ተጨምርበታል።
በ Fm ኳስ እየሰማ ድምፁ አናሳ ከሆነ

ትጨምርበታለህ🤷 So, እዚጋ የድምፁን ለውጥ detect ስናረግ difference threshold ይባላል።

By the way Absolute ም ሆነ Difference threshold እንደየ ሰውና እንደየ ሁኔታው ሊለያይ ይችላል። እኔ
ስቀምስና ሌላ ሰው

ሲቀምስ አንድ ላይሆን ይችላል🤷

📖Sensory Adaptation

🔰The tendency of our sensory receptors to have decreasing responsiveness to unchanging


stimulus is called sensory adaptation.

ይሄ ደግሞ የማይለወጠውን stimulus Adapt ስታረጉት (ስትለምዱት) ያለው ሂደት ነው።

‍ምሳሌ‍
♂ ️‍♂️ ♂
‍♂️‍♂
♂️ 🏃‍️🏃😁
‍️ ..ሻወር ስትገቡ
ውሃው ቀዝቃዛ ሊሆን ይችላል፣ ከዚያ ግን ቀስ በቀስ ውሃውን ትለምዱታላቹ (ይበርዳቹ የነበረው እየቀነሰ
ይመጣል ምንም እንኳ የውሃው ቅዝቃዜ ባይለወጥም) አሁን ተመልሳቹ Definition ኡን አንብቡ👆Of course,
ሁሉን ነገር adapt አናረግም፣ ለምሳሌ ከባድ በሽታ😞

📚PERCEPTION

በዚህ Sub-Chapter Major Characteristics of Perception የሆኑትን👇 እናያለን

📌Selectivity of Perception

📌Form Perception

📌Depth Perception

📌Perceptual Constancies

📌Perceptual illusion
እነዚህን ዘርዘርን መንዝረን አንድ በአንድ እናያቸዋለን፣ ነገር ግን ውስብስብ ስለሚመስል አንዱን ስትይዙ ሌላው
እንዳያመልጣቹ😇

1️⃣Selectivity of Perception

(Attention!)

📍Note that at any given time, our sense organ is bombarded by many stimuli.

📌እንደምታውቁት ሁልጊዜ የስሜት ህዋሳቶቻችን ከተለያዩ ብዙ ክስተቶች ጋር ይገናኛሉ፣ ነገር ገን እኛ


attention ሰጥተን Response የምንሰጠው ለጥቂቱ ብቻ ነው።

ይሄ አንዱ ላይ Focus አድርገን ሌላውን stimuli ደግሞ ignore የማድረጉ ነገር(Selective Perception),
#Attention ይባላል።

What does this selectivity of perception imply?🤔

🌹Selectivity of Perception

📍Imply የሚያደርገው, የልምምዳችን ሁኔታ ከየትኛውም ነገር በላይ ሁለት ነገር ላይ ነው የተመሰረተው።

📌Focus

📌Margin

Events or Stimuli that you perceive clearly are the #focus of our experience.

Events or stimuli that you perceive dimly or Vaguely are #Margin of our experience.

ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ላስረዳችሁ ለምሳሌ በ DSTv ቤት ሆናችሁ የሰዎች ጫጫታ ብርድ ባለበት ስፍራ
ሆናችሁ የኳስ ጨዋታ️⚽
️ እያያቹ አይናቹ የሚከታተለው ኳሱን የያዘው ሰውዬ ላይ ነው፥ ይሄ Focus ይባላል። ነገር
ግን Still የሰዎቹ ጨጫታ፣ብርዱ ምናምን አለ፣ ነገር ገን እናንተ ለእነዚህ ነገሮች ሙሉ ትኩረት አልሰጣቹም፤
ማለትም በቃ Dimly/Vaguely ነው ትኩረት ያረጋቹት እንዲህ ሲሆን #Margin ይባላል።

ልብ በሉ👆ጫዋታው ካለቀ በኃላ ግን ቅድም ትኩረት ያልሰጣቿቸው ነገሮች አሁን ትኩረት ማድረግ
ትጀምራላችሁ።(ምንድነው ብርዱ ምንድነው ጫጫታው ትላለህ😺)

So, አያቹአ ቅድም Focus አቹ የነበረው(ኳሱ) አሁን ሲያልቅ ብዙም ትኩረት ስላልሰጣቹት Margin አቹ እየሆነ
መጣ። ደግሞም ቅድም #Margin አቹ የነበሩት አሁን Focus አቹ ሆነዋል። 🤚ይሄ ምንድነው ሚያሳየው
Attention Constantly shifting ‍♂
እንደሆነ‍
🤷‍️️ ♂
‍♂️

What factors do you think determine your attention?

ሰው ለምንድነው በአንድ ነገር ትኩረቱ የሚሳበው?🤨🤨


🌹Paying attention is in general a function of two factors: factors external to the perceiver and
factors internal to the perceiver.

External Factors የሚባሉት

📌Size and Intensity

📌Repitition

📌Novelty(Newness)

📌Movement

🔸Size and intensity👉 Bigger and Brighter የሆኑት ነገሮች ከ smaller እና ደብዛዛ ከሆኑት ነገሮች ይልቅ
ትኩረት ሳቢ ናቸው። ለዚያኮ ነው፣ Bolded የሆኑ Letters እንዲሁም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ትኩረታችንን
የሚያገኘው።

🔸Repitition👉repeatedly or frequently የሚደረገው ድርጊት አንዳንዴ ትኩረታችንን ይስባል። ለዚያ ነው


መፈክሮች(Slogans)፤ Advertisements የሚደጋገሙት።

❗️ነገር ግን አንዳንዴ ነገሩ ምንም ያክል ትልቅ ቢሆን ነጭ ቢሆን ቢደጋገም ትኩረት ላንሰጥ እንችላለን😒
ምናልባት ይሄ የሚሆነው ነገሩን Adapt ስላደረግነው ይሆናል፣ This is Called Sensory
Adaptation[Habituation]. ባለፈው አይተናታል እቺን😎

🔸Novelty(Newness)👉ይሄ ማለት አንድ ነገር በ Environment ኡ ውስጥ ካሉት ነገሮች ጋር Contrast


ሲያደርግ ትኩረታችንን ያገኛል። ለዚያ ነው ቤት ውስጥ ካሉት ሰዎች ይልቅ ህፃን(First born)
attention አችንን የሚያገኘው😘

🔸Movement👉እንደምታውቁት Moving objects ከ Non-moving/stagnant objects በላይ ቶሎ ትኩረት


ይስባሉ። ለዚያ ነው ቢራቢሮ🦋 ወዲህ ወዲያ ስትል የምንመሰጥባት😁

Internal Factors የሚባሉት

📌Set or Expectancy

📌Motive or needs

🔸Set refers to the idea that you may be "ready" and "primed for" certain kinds of sensory
input.

ህፃን ልጅ ያላት ‍👩
እናት
‍ ‍ ሁሌ የምትጠባበቀው "ልጄ አለቀሰ ወይስ አላለቀሰም" የሚለው ከሆነ..የሚያለቅስ
የህፃን ድምፅ በሰማች ቁጥር ልጄ ነው ወይ ትላለች😍😍 Because እየተጠባበቀችው ስለሆነ እንግዲህ ይሄ ነው
"Set" ሚባለው።
🔸Motive(Needs):- ሰው ትኩረት የሚያደርገው ውስጥ ባለው ፍላጎት Motive ላይ ተመስርቶ ነው። ለምሳሌ
የራበው ሰው Focus የሚያረገው Food ላይ ነው፣ አሁን እናንተ የመማር ፍላጎት በውስጣቹ ስላለ ነው፣ ለዚህ
tutorial ትኩረት የሰጣቹት።

ገብቷቸዋል🙌🙌

በቀጣይ ጊዜ የቀረውን እናያለን።

2⃣ Form Perception

🌷The meaningful shapes or patterns or ideas that are made perhaps out of meaningless and
discrete or pieces and bites of sensations refer to form perception.

🪄ይሄ meaningless ከሆኑ ነገሮች ማለትም ከምናያቸው፣ ከምንሰማቸው..ነገሮች ትርጉም ያለው ነገር
መመስረት ነው Form perception የሚባለው።

ለዚህ ደግሞ Object ኡን[figure] ከ Surrounding ኡ[Ground] መለየት ያስፈልገናል።

Figure-Ground Perception

በግድግዳ ላይ የተሳለ ስዕል ብንወስድ፦ ስዕሉን እንደ figure ግድግዳውን ደግሞ እንደ ground ነው
የምንወስደው ሌላ ደግሞ በመሬት ላይ የፃፈ ፁፍ እዚጋ ደግሞ መሬቱ እንደ Ground ሲሆን ፅሁፉ ደግሞ እንደ
figure 🤷‍
ነው‍‍♂
‍♂ ♂

የሆነው ሆኖ How Can we separate the figure from the general Ground and Form Perception?

ለዚህ 2 ዘዴዎች አሉ😊

📌Contours

📌Organization

Contours in Form Perception

🔰Contours are formed whenever a marked difference occurs in the brightness or color of the
background. Figure ን ከ ground ለይታችሁ የምታውቁት Contour ኡን ስታውቁ ነው!

ለምሳሌ በጥቁር እስክሪብቶ🖊 Blackboard ላይ ብትፅፉ፣ ጥቁሩን ፁፉ ከ blackboard ኡ የለያችሁ ጊዜ


Contour ኡን ታገኛላችሁ። ከዚያ በኃላ ፁፉ Figure, blackboard ኡ ደግሞ ground እንደሆነ ማወቅ
አይከብዳችሁም👍

ሌላ ምሳሌ፣ ጥቁር ሰው ጥቁር ልብስ ለብሶ አስቡት🙈🙉 ሰውዬውን ከልብሱ የለያችሁ ጊዜ Contour ኡን
ታገኛላቹ።

ላችሁ ከዚያን ሰውዬው figure, ልብሱ ደግሞ ground እንደሆነ ይታወቃል።


Organization in form perception

🌷Organization in perception partially explains our perception of complex patterns as unitary


forms, or objects.

ይሄ ደግሞ የተለያዩ ተመሳሳይነት ያላቸውን ነገሮች አንድ ላይ አምጥተን አንድ ትርጉም ያለው ነገር መፍጠር
ማለት ነው።

🌻Some of the laws of perceptual organization

Proximity👉 items which are close together tend to be perceived as belonging together.

Similarity👉items which are the same tend to be perceived as forming an organized group.

ለምሳሌ °

° °

ይሄንን ሶስቱ rings ተመሳሳይ ስለሆኑ Organize ታረጓቸውና Triangle እንደሆነ guess ታረጋላችሁ።

Continuation👉the tendency to perceive a line that starts in one way as continuing in the same
way. የዚህን ምሳሌ Handout ኡ ላይ ማየት ትችላላችሁ፣ ቀላል ስለሆነ...

Closure👉refers to perceptual processes that organize the perceived world by filling in gaps in
stimulation.

ይሄ ደግሞ ያላለቀ ነገር ግን pattern ያለው ከሆነ gap ኡን በመሙላት perception form ማድረግ እንችላለን።

3⃣ Depth Perception

🌷Depth Perception is the abilitiy to see things in three dimensions (length, width and depth)
and it is to mean to judge how far away an object is.

🪄For accurate depth perception, we generally need to have binocular (two-eyed) vision

ይሄ የ Perception Charecteristics ከሌሎቹ ይልቅ ትንሽ ከበድ የሚል ይመስላል፣ ፈጣሪ ይርዳችሁ🌝

እስካሁን ያየነው ነገሮችን በ 2Dimensions ማየት ነው depth perception ግን 3D dimension ያጠቃልላል።

🪄ደግሞ ጥሩ የሆነ Depth perception (የጠለቀ መረዳት) እንዲኖረን ሁለቱ አይኖቻችን ጤናማ ሊሆኑ ይገባል፣
አለበለዚያ በአንድ አይን ብቻ blurry የሆነ እይታ ነው የሚኖረን።

🗝ለምሳሌ:- አንድ Straight በሆነ መንገድ ላይ ቆማችሁ፣ በቀጥታ አርቃችሁ ወደ መንገዱ ስትመለከቱ፣
መንገዱ እየጠበበ እየጠበበ የሚሄድ ይመስላል አ ነገር ግንኮ መንገዱ ያው ነው😀..ይሄ አጋጥሞአችሁ
አያቅም?🙌 አሁን ይሄ ለ Depth Perception(ጥልቅ እይታ/መረዳት) ምሳሌ ሊሆን ይችላል
🌹Depth perception depends on the use binocular cues and monocular cues.

🔸Binocular cues are Visual informations taken in by two eyes

🔸Monocular cues are Visual informations taken in by one eye.

🌷Monocular cues require only one eye. ይህ ማለት አንድ አይኑ የማያይ ሰው ምንም እንኳ ከባድ
ቢሆንም good perception ሊኖረው ይችላል ማለት ነው።

Kinds of monocular Cues

📌Accommodation

📌Motion parallax

📌Pictorial cues

📌Texture gradient

🌻Accomodation is the change in the shape of the lens that lets you focus the image of an
object on the retina.

ለምሳሌ ቅርብ ያለው ነገር ላይ ስታፈጡ ቆይታችሁ🥺 ...ከዚያ ራቅ ያለ ነገር ስታዩ፣ ነገሩ ከራቀው በላይ በጣም
ርቆ ይታያቿል። ይሄ የሆነው የመጀመሪያው እይታ lens አችሁ ላይ ተፅኖ ስላሳደረ ነው።

🪄Prolonged accommodation can alter your depth perception!

🌻Motion Parallax is the tendency to perceive ourselves as passing objects faster when they are
closer to us than when they are farther away.

ለምሳሌ ገጠር አከባቢ በ Bus እየሄዳችሁ በመስኮት ውስጥ እያያችሁ እሩቅ ካለችው መኖርያ ቤት ይልቅ ቀረብ
ያለውን የቆመ የማብራት pole ቶሎ ሽው ብለን እናልፋለን...ገጠር ያሉት/የሄዱት ታድሏል ይሄ ትምህርት
አይከብዳቸውም😋

🌻Pictorial Cues፦ Leonardo da Vinci formalized pictorial cues 500 year ago!

ግን ቆይ cue ምንድነው🤔

Cue ማለት ስለሆነ ነገር hint መስጠት ወይም ምልክት ማለት ነው። እንዲህ አድርግ ለማለት የምሰጠው
ወይም የማሳየው ምልክት ነው።

🌷እና በ Pictorial cue ስር የምናየው ያው depth perception distance judge ስለ ማድረግም ነው


የሚያጠናው ብለን ዬለ...እና እዚህ ስር ከ distance ጋር አያይዘን ነው የምናየው።

➡ ️He(Da vinchi) noted that an object that overlaps another object will appear closer, a cue
called #interposition.
ለምሳሌ Lecturer ኡ🤵 ከ blackboard ኡ ፊትለፊት ከቆመ (ሁለቱ overlap ካደረጉ) ከ Blackboard ኡ ይልቅ
lecturer ኡ ነዋ ቅርብ መስሎ ሚታየን፥ እንደዛ እንዲታየን ያደረገው interposition የተባለው cue (ምልክት)
ነው።

➡️If two people are about the same height and one casts a smaller image on your retina. You
will perceive that person as farther away.

እዚህጋ ደግሞ አጭር መስሎ የታየን ከሌላኛው ይልቅ የራቀ መስሎ እንዲታየን ያደረገው Cue ወይም ፍንጭ
ምንድነው ካላችሁ #Relative_size 🤷‍
ነው።‍‍♂
‍♂ ♂

➡️Objects that are higher in your visual field seem to be farther away.

በአይምሮአችሁ ትልቅ አድርጋችሁ ያሰባቹት ነገር እሩቅ መስሎ ይታየናል። እንደዛ መስሎ እንዲታየን ያደረገው
Cue ደግሞ #Elevation ይባላል።

➡️Areas that are in shadow tend to recede, while areas that are in light tend to stand out.

በጥላ ስር ያሉ ቦታዎች ቅርብ ሲመስሉን ብርሃን ያለበት ቦታው ደግሞ ርቆ ይታየናል። አንዲህ እንዲመስለን
ያደረገው Cue #Shading_Patterns ይባላል።

➡️Closer objects seem clearer than more distant ones. A distant mountain will look hazier than
a near one.

ለዚህ ደግሞ Cue የሆነው #Aerial_Prespective ነው።

🌻The final monocular cue, the texture gradient

It implies that the nearer an object, the more details we can make out and the

farther an object, the fewer details we can make out.

ለምሳሌ ከሩቅ ሆናችሁ ለምለም ሳር ሊታያችሁ ይችላል ነገር ግን ቀረብ ስትሉ ሳሩ ምን አይነት ነው
የሚለውን in detail ማወቅ 🤷‍
ትችላላችሁ‍‍♂
‍♂ ♂

🌻There are two kinds of binocular cues:

📌Retinal disparity

📌Convergence

🌻Retinal disparity is, the degree of difference between the image of an object that are focused
on the two retinas.

🖇Retina ምንድነው?🙄
Retina ብርሃንን ተቀብሎ ምስልን ወደ አይምሮ የሚልክ የአይን አካል ነው። ያው ሁለት Retina ብቻ
(2Dimensions) እንዳለን የምታውቁ ይመስለኛል😊

Retinal Disparity ማለት ከስሙ እንደምትረዱ በ retinas ላይ focus ያደረገ በአንድ ነገር ላይ ያለን ምስል
ልዩነት መጠን ነው። ለምሳሌ "እስቲ እንዲህ አድርጉ ጣታችሁን በሁለቱ አይኖቻችሁ መካከል Vertically
አቁሙ፡ አደረጋችሁ?😊 ከዚያ የግራ አይናቹን ጨፍኑና በቀኙ ብቻ እዩት...አሁን ደግሞ የቀኙን ጨፍናችሁ በግራ
አይናችሁ ብቻ እዩት..የሆነ የ image ልዩነት አለአ😯...ይሄ አሁን የ Retinal disparity Eg. ነው፣ ማለትም
ሁለቱም Retina አዎች የተለያየ፣ ልዩነት ያለው ምስል ነው የሰጡን።

📌The closer the object, the greater is the retinal disparity. ጣቱን👆 ወደ አይናችሁ👁 ባስጠጋችሁ
ልክ ሁለቱ image ኦችም disparity አቹ እየጨመረ ይመጣል። ከፈለጋችሁ Check አርጉ😎

🔖Convergence is the degree to which the eyes turn inward to focus on an object. የአንድአንድ
ሰዎች አይን አንድአንዴ ወደ ውስጥ turn አድርጎ👀 ምናምን አይታቹ አታውቁም። ማለትም ለምሳሌ
እንደቅድሙ እስቲ ጣታቹን Vertically ወደ ላይ አቁሙና ቀስ በቀስ ወደ አፍንጫችሁ አስጠጉት...የሆነ
አይናችሁ ላይ ልዩነት አልፈጠረም😃

🌻You should notice an increase in ocular muscle tension as your finger approaches your nose!

🌻the closer the objects are the greater the convergence of the eyes. ጣቱን ወደ አፍንጫችሁ
ባስጠጋችሁ ቁጥር Convergenc ኡም እየጨመረ ይመጣል።

ለዛሬ ይህን ይመስላል ። በቀጣይ Perceptual Constancies እና Perceptual Illusion እናያለን።

📒Sensation and Perception

[...continued]

4⃣Perceptual Constancies

🌷 It is the tendency to see familiar objects as having standard shape, size, color or location
regardless of changes in the angle of perspective, distance or lightning.

ይሄ ማለት Object ኡ ምንም ያክል የተወሰነ ልዩነት ቢኖረውም እኛ ግን ምንም ልዩነት እንደሌለው አድርገን
በአይምሮአችን ስንስል ነው።

ቆይ አይነቶቹን እንይና በደንብ ይገባቹሃል ።

📑Types of perceptual constancies

1. Size Constancy

📌Size constancy involves recognising that an object's actual size remains the same, even
though the size of the image it casts on each retina changes.
🌻አያቹ ይሄ ለምሳሌ የባቡር መንገድም ላይ ቆማቹ ባቡሩ🚈 ወደ እናንተ እየመጣ ቢሆን በ Retina
የሚፈጠረው image እየጨመረ ይመጣል፣ ነገር ግን እኛን እንደዛ መሰለን እንጂ Still የባቡሩ መጠን (Size)
አልተለወጠም።

📑Size constancy can be disrupted by alcohol.

አንዳንድ ጊዜ መጠጥ የሚጠቀሙ ሰዎች ይህ "Size constancy" ላይሰማቸው ይችላል። ለምሳሌ ከላይ
የወሰድነውን ምሳሌ ለእነሱ (መጠጥ ለሚጠቀሙት) በተቃራኒው ሊታያቸው ይችላል። (የባቡሩ መጠን እየቀነስ
እየመጣ እንደሆነ ሊሰማቸው ይችላል።)

2. Shape Constancy

📌is the tendency to perceive an object as having the same shape regardless of its orientation
or the angle from which we view it.

🌻ለምሳሌ ከታች በ Photo1 ይለቀኩላችሁን ተመልከቱት!

ምንም እንኳ በ Retina አችን የሚሳለው ምልከታ (Image) የአንዱ ቀጥ ያለ Rectangle ሌላው ደግሞ
Trapezoid ቢሆንም ነገር ግን እኛ ሁለቱንም Rectangle አድርገን ነው የምናስባቸው።

3. Brightness Constancy

🔰This involves Eventhough light reflected from a given object can vary, we perceive the object
as having a constant brightness.

እኛ የምናየው ነገር 'የብርሃን' ልዩነት ቢኖረውም እኛ ግን እንደተመሳሳይ እና ምንም አይነት ልዩነት


እንደሌለው አድርገን ስንወስደው ነው። ለዚህ ደግሞ ቀጥሎ ያለውን Photo2 ተመልከቱ! ሌላ የ White shirt
ምሳሌ Handout ኡ ላይ አለላችሁ👍

5⃣ Perceptual illusion

Handout ኡ ላይ የወሰደው ምሳሌ "አንድ ሰውዬ በመስኮቱ በኩል አሻቅቦ እያየ ተራራ ላይ የሆነ ትልቅ አስፈሪ
ፍጡር (Monster) ያየ መስሎት ደነገጠ፣ ግን ፍጡሩ እየበረረ ልክ መስኮቱ ጋር ሲደርስ ለካ ነፍሳት (insect)
ነው😂😂

🖇This shows how the misapplication of a visual cue, in this case perceived size constancy, can
produce a visual illusion.

እሺ ለዚህ ደግሞ የ Franz Muller-Lyer ን ምሳሌ እንውሰድ

ከታች በ(photo3) ላይ ያሉትን መስመሮች ስንመለከት የመሀልኛው የሚበልጥ ይመስላላ..ግን measure


ሲደረጉ እኩል ናቸው😎 ይሄ ነው እንግዲህ "Illusion" የሚባለው።

📑In general, perception is the act of knowing through sensation.


ግን ደግሞ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸው ሰዎች አሉ፣ without any sensory contact (ሳያዩ፣ ሳይሰሙ፣ ሳይዳስሱ)
አንድን ነገር/ሰው የሚገነዘቡ/የሚያውቁ። ነገሮችን የሚረዱበት ተጨማሪ [Extra] የስሜት ህዋስ አላቸው።
እኔን አጋጥመወኝም ሰምቼም አላውቅም😊፥ ነገር ግን እንዲህ አይነት ሰዎች እንዳሉ በሳይንስ ተረጋግጧል።

ይህም ESP ወይንም "Extra Sensory Perception" ይባላል።

You might also like