You are on page 1of 41

በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈጻጸም

ላይ የተደረገ ሱፐርቪዥንና የመስክ ምልከታ


አጭር ሪፖርት
ታህሳስ /2016

አዲስ አበባ
ይዘት
1. መግቢያ
2. የሱፐርቪዥኑና የመስክ ምልከታው ዓላማ
3. በቅድመ ዝግጅት የተከናወኑ ተግባራት
4. አጠቃላይ መረጃዎች
5. በምልከታው የተከናወኑ ተግባራት
6. ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች
7. ማጠቃላያ
1.መግቢያ
 በሀገራችን የተለያዩ የፓለቲካ እና የሀሳብ መሪዎች እንዲሁም

የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች

ላይ ልዩነቶችና አለመግባባቶች በሰፊው ይስተዋለል፡

 እነዚህ አለመግባባቶች መልካም የሆኑ እሴቶችን በመሸርሽር ሀገራዊ

መግባባት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደፈጠሩ ይታወቃል፡፡

 በመሆኑም አለመግባቦቶችን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል የኢፌዴሪ

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ

ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት ሀገራዊ ምክክር

ኮሚሽንን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡


የቀጠለ……
 ኮሚሽኑ ወደ ስራ ከገባ በኋላ በርካታ የቅድመ-ዝግጅት ተግባሮችን
ሲያከናውን ቆይቶ በአሁኑ ወቅት የተባባሪና የተሳታፊ ልየታ ስራ
እየሰራ ይገኛል፡፡
 ስለሆነም የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሚሽኑን ስራ
መሬት ላይ ምን እንደሚመስል ለማረጋገጥና በሂደቱ የሚታዩ
ጥንካሬዎችን እና ክፍተቶችን ለመለየት ሁለት ቡድኖችን
አደራጅቶ የሱፐርቪዥን እና የመስክ ምልከታ ስራ ሰርቷል፡፡
 በዚህ መሰረት የታዩትን ጥንካሬዎች፣ እጥረቶችና ቀጣይ
ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን እንደሚከተለው አቅርቧል።
2.የሱፐርቪዥኑ ዓላማ
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባር
እና ኃላፊነቶች በአግባቡ እየተከናወኑ መሆኑን
ለማረጋገጥ፣
የተባባሪና ተሳታፊ አካላት ምርጫ አሳታፊ፣ አካታችና
በአዋጁ የተደነገጉ መርሆዎቹን የተከተለ መሆንን
ማረጋገጥ፣

እስካሁን በተከናወኑ ተግባሮች ያሉትን ጥንካሬዎችና


ክፍተቶች በመለየት ለቀጣዩ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ
ነው፡፡
3. በቅድመ ዝግጅት የተከናወኑ ተግባራት
ቋሚ ኮሚቴው ሱፐርቪዥንና የመስክ ምልከታ
የሚካሄድበትን ቼክ ሊስት አዘጋጅ aል፡፡
በተዘጋጀው ቼክ ሊስት ላይ ሱፐርቪዥንና የመስክ ምልከታ
ለሚያደረጉ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና ባለሙያዎች ኦሬንቴሸን
ተሰጥቷል፡፡
የመስክ ምልከታ ፕሮግራሙን ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ
አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት በማካሄድ ዝግጅት
እንዲደረግ ተደርጓል፡፡
4. አጠቃላይ መረጃዎች
4.1 የመስክ ጉብኝት የተደረገባቸው አካባቢዎች
ተ.ቁ ከልል/ የዞን/ክ/ከተማ የወረዳ/ክ/ከተማ የታዩ ወረዳ /ክ/ከተ/ አስተዳደር
ከ/አስተዳደር ብዛት ብዛት

1 ሲዳማ 11 45 ታቦር ክ/ከተማ እና


አዲስ ከተማ ክ/ከተማ

2 ሀረሪ - 9 አባድር ወረዳ እና


አሚር ኑር ወረዳ

3 ቤንሻንጉል 3 27 ባምባሲ ወረዳ


ጉሙዝ

4 አ/አበባ ከተማ 11 119 ለሚኩራ ወረዳ 6


4.2 ሱፐርቪዥኑ የተካሄደበት ጊዜ

ተ. ክልል/ከ/አስተዳደር ጉብኝት የተካሄደበት ጊዜ


1 ሲዳማ ከህዳር 23-29/2016 ዓ.ም


2 ሀረሪ ከታህሳስ 2-7/2016 ዓ.ም

3 ቤንሻንጉል ጉሙዝ ከህዳር 24-27/2016 ዓ.ም

4 አዲስ አበባ ከታህሳስ 2- 4/2016 ዓ.ም

5 የኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት ታህሳስ 15/2016 ዓ.ም


4.3. በውይይቱ የተሳተፉ አካላት
 በክልሎቹና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተግባሩን
ለመደገፍ በርዕሰነ መስተዳድሮቹና በከንቲባዋ
የተወከሉ የስራ ሀላፊዎች፣
 የክልል/ ከተማ አስተዳደሩና የወረዳ ተባባሪ አካላት፣
 የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተሳታፊ አካላትና
ከነዚህ ውጭ ያሉ የየአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው፡፡
5. በታዩ አካባቢዎች የኮሚሽኑን አፈጻጸም
በተመለከተ
በመስክ ስምሪቱ ኮሚሽኑን ወክለው የተሳተፉ
ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድኖቹ በተሰማሩባቸው
በሁሉም አካባቢዎች ሪፖርት አቅርበው ውይይት
ተካሄዶበታል፡፡
በውይቱም በጥንካሬ የታዩና መሻሻል የሚገባቸው
ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
5.1 በጥንካሬ የታዩ
 ጥራት ያለው ሪፖርት ተደራጅቶ፣ መረጃዎች በአግባቡ
ተይዘውና በበቂ ዝግጅት ሪፖርቱ መቅረቡ፣
 ኮሚሽኑ በአስቀመጠው የአሰራር ስርአት መሰረት የክልልና
የወረዳ ተባባሪ አካላትን እንዲሁም ተሳታፊዎችን
ተለይተውና ለስራው የሚያስፈልገው ስልጠና ተሰጥተቸው
በተልዕኳቸው ላይ ግንዛቤ እንዲይዙ መደረጉ፣
 ለአጀንዳ ማሰባሰብ የሚሳተፉ አካላት የአሳታፊነትና
አካታችነትን መርሆዎችን ተከትለው ከነተጠባባቂ የሰው
ሀይል እንዲመረጡ መደረጉ ፣
ይቀጥላል…..
 በየአካባቢው ብዝሀነትን መሰረት በማድረግ በተለያዩ ቋንቋዎች
መልእክቶችን ተዘጋጅተው የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ያደረጉት
ጥረት የሚበረታታ ነው (ሲዳማ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ) በተለይም
በሲዳማ ክልል ቋንቋ ብሮሸር እና ልዩ ልዩ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ግንዛቤ
ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፣
 ከየአካባቢው የስራ ሀላፊዎችና ተባባሪ አካላት ጋር ያላቸው መልካም
ግንኙነት ለስራው ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር አግዟል፣
 ከተባባሪ አካላት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማስቀጠል የቴሌግራም
ቻናል ከፍተው መረጃ ይለዋወጣሉ (ቤንሻንጉል ጉሙዝ) የሚሉት
በአወንታ የታዩ ናቸው፡፡
5.2 በእጥረት የታዩ
 በሁሉም አካባቢዎች በአገራዊ ምክክሩ ተግባር ላይ
ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ የተፈጠረ አለመሆኑ፣
 ምንም እንኳን ተባባሪ አካላት የሚጋበዙት አደረጃጀትን
መሰረት በማድረግ ቢሆንም በተለይ በክልል ተባባሪ
አካላት የሴቶች ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑ፣
 ተሳታፊዎች የግማሽ ቀን ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው
በቀሪው ግማሽ ቀን የአጀንዳ ልየታ ተሳታፊዎችን
እንዲመርጡ ሲደረግ መንጠባጠብ ታይቷል (ሀረሪ)፣
የቀጠለ……
በስልጠና ወቅት ሰነዶች በአካባቢው ቋንቋ
ተተርጉመው አለመቅረባቸው (ሀረሪ)፣
የውሎ አበል አከፋፈል የሩቅና የቅርብ
ወረዳዎችን ያልለየና አልፎ አልፎ አሁንም አበል
ያልተከፈላቸው መኖራቸው በስራው ላይ
ተጽእኖ ያሳድራል (ሲዳማ፣ ሀረሪ)፣
የቀጠለ……
 በአጀንዳ ተሳታፊዎች ልየታ ወቅት ያልተገኙ የተወሰኑ
ቀበሌዎች መኖራቸው (ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባንባሲ ወረዳ)፣
 ከአቅም በላይ ችግር ያጋጠመ በመሆኑ ግንዛቤ
ያልተፈጠረላቸው አካባቢዎች መኖራቸው (ቤንሻንጉል
ከማሺ ዞን)፣
 ለአጀንዳ ማሰባሰብ የተመረጡ ተወካዮችን ህዝቡ
እንዲያውቃቸው የተደረገበት አሰራር ባለመኖሩ የቅቡልነት
ችግር እንዳያመጣ ስጋት መኖሩ (በሁሉም ክልሎችና
ከተማ አስተዳደር)፣
ለኮሚሽኑ ተወካዮች ግብረ መልስ ሲሰጥ
.

5.3 የክልሎችና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስታት ትብብርን በተመለከተ

5.3.1 በጥንካሬ
 በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሩ ያሉ
የመንግስታት የስራ ሀላፊዎች ለኮሚሽኑ ተልዕኮ
መሳካት ያላቸው ፍላጎትና ቀና ትብብር
የሚመሰገን ነው፣
የቀጠለ......
 ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ፣ በሎጅስቲክስ
ድጋፍ ማለትም የመሰብሰቢያ አዳራሾችን
በማመቻቸት፣ አስፈላጊም ሲሆን የተሸከርካሪ ድጋፍ
በማድረግና የአካባቢ ሰላምና ጸጥታ በማስከበር
በትጋት ይሰራሉ፣

 በጀት በማፈላለግ ጭምር የአባሎቻቸውን ግንዛቤ


ለማሳደግ እንዳሉ ታይቷል (ሲዳማ ክልል)፣
የቀጠለ……
 በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት የየማህበረሰብ ተወካይ
ተሳታፊዎች የአካታችነት መርህን ተከትለው እንድመረጡ
አድርገዋል፡፡ በዚህ ረገድ በሁሉም አካባቢ የተነሳ ቅሬታ የለም፣
 የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ከሴቶች ፌደሬሽን ጋር
በመተባበር ለሴቶች ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረት አድርገዋል (ሀረሪ)፣
 ለአገራዊ ምክክሩ መሳካት ያላቸው ፍላጎትና ተስፋ ክፍ ያለ
ነው፣
 የክልል ተባባሪ አካላት በሁሉም ክልሎች በተልዕኳቸው ላይና
በኮሚሽኑ ተልዕኮና ተግባር ላይ የተሻለ ግንዛቤ ያለቸው
መሆኑ(ከሓይማኖት ጉባኤ ተወካይ ውጭ) የሚሉት በአወንታ
የታዩ ናቸው፡፡
5.3.2 በእጥረት የታዩ

 በወረዳ ደረጃ የመንግስት ውክልናን የያዘ ተባባሪ


አካል አልተገኘም(ሲዳማ እና ሀረሪ)፣
 የወረዳ ተባባሪ አካላት እርስ በርስና ከኮሚሽኑ
ጋር ያላቸው ግንኙነት የላላ መሆኑ (ሲዳማና
ሀረሪ)፣
 በወረዳ ተባባሪ አካላት ውይይት ላይ የሀይማኖት
ተቋማት የጋራ ጉባኤ ተወካዮች አልተገኙም
(ሲዳማና ሀረሪ)፣
የቀጠለ......
 ተልዕኳቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከኮሚሽኑ ጋር ያለን
ግንኙነት ተዳክሟል ይላሉ (አዲስ አበባ፣ሀረሪ፣
ሲዳማ)፣
 በክልሎች በተሰራው ስራ ላይ ጥርጣሬ አላቸው፡፡
ለአብነት የአዲስ አበባ ተወያዮች አካባቢዎችን
እየጠቀሱ በቂ መረጃ ሳይኖራቸው የመንግስት
ጣልቃ ገብነት አለ ብለው ያነሳሉ፣
የቀጠለ…..

 ሂደቱ አልተፋጠነም የሚል ተስፋ መቁረጥ ይታይባቸዋል

(አዲስ አበባ፣ ሀረሪ፣ ሲዳማ)፣


 ወቅታዊ አጣዳፊ ችግሮቻችንን በፍጥነት መፍታት አለበት

የሚል የመቻኮል ስሜት ይታይባቸዋል (በሁሉም አካባቢ)፣


 በሀረሪ ክልል የሲቪክ ማህበረሰብና የሲቪል ማህበራት ላይ

በአደረጃጀት ለመካተት የግልጸኝነትና የፍትሀዊነት ጥያቄ

ያለ መሆኑ በእጥረት ከታዩት መካከል ዋና ዋናዎቹ

ናቸው።
ከተባባሪ አካላት ጋር ውይይት ሲደረግ
የቀጠለ......
5.4 የተሳታፊዎች ሁኔታ፣ ልየታና ስልጠና

5.4.1 በጥንካሬ
 አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ምልከታ በተደረገባቸው
በሁሉም ክልሎች ከ36 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ከ4 ሺህ በላይ
የአጀንዳ ልየታ ተወካዮች ተመርጠዋል፣
 የምርጫ ሂደቱ አካታች ከመሆኑም በላይ የመንግስትም ሆነ የፓርቲ
ጣልቃ ገብነት የሌለበትና በነጻነት የተከናወነ መሆኑን አረጋግጧል፣
 በምክክር አጀንዳውም ላይ ያላቸው ተስፋም ከፍ ያለ ነው፣
 ወደ መሰብሰቢያ ማዕከል ጥሪ ሲደረግላቸው ፈጥነው ተገኝተው
ሀሳባቸውን በግልጽና በነጻነት አንስተዋል የሚሉት በአወንታ የታዩ
ናቸው፡፡
5.4.2. በእጥረት የታዩ

 ሁሉም ችግሮች በአገራዊ ምክክሩ ይፈታሉ ብሎ ማሰብ


በሁሉም አካባቢዎች የሚታይ ዝንባሌ ነው (ክልላዊና
ከባቢያዊ አጀንዳዎች እንዴት እንደሚለዩና ምክክር
እንደሚደረግባቸው ግልፅነት የሌለ መሆኑ)፣
 ከተሳታፊዎችና ተወካዮች ምርጫ በኋላ ኮሚሽኑ ትቶናል
ውይይቱንም ምክክሩንም በማካሄድ ረገድ መቀዛቀዝ
ታይቷል የሚል ቅሬታ በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ያነሳሉ
(አዲስ አበባ፣ሀረሪ)፣
 በተወካዮች ልየታ ጊዜ ተሳታፊዎች ተሟልተው
የቀጠለ....
 በየሚወክሉት የህብረተሰብ ክፍል የመረጃ ልውውጥና
የህዝብ ግንኙነት ስራ በመስራት ረገድ ውስንነት አለ
(በሁሉም)፣
 አንዳንድ ቀበሌዎች ተሳታፊ አለመሆን (ቤንሻንጉል
ባንባሲ ወረዳ)
 ስልጠና ያላገኙ ተሳታፊዎች መኖራቸው (ቤንሻንጉል-
ከማሸ ዞን) የሚሉት በተሳታፊ ልይታ ላይ የታዩ
እጥረቶች ናቸው፡፡
ቤንሻንጉል ጉሙዝና ሀረሪ ክልል ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ሲደረግ
5.5. የህብረተሰቡ ሁኔታ
 ምንም እንኳን በሁሉም አስተዳደር አካባቢያዎች
በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን አመለካከት
የሚወክል በቂ ናሙና ያልተወሰደ ቢሆንም
በየወረዳዎቹ ባነጋገርናቸው ነዋሪዎች ጠቋሚ
ዝንባሌዎችን ለመረዳት በተደረገው ጥረት ተግባሩ
ትልቅ አገራዊ አጀንዳ የመሆኑን ያህል በቂ
ግንዛቤ ያላቸው ሆኖ አልተገኘም፡፡
በሀረሪ ክልል ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ
በቤኒሸንጉል ጉሙዝ ክልል ለአካባቢው ነዋሪዎች ቃለ-
መጠየቅ ሲደረግ
6. የመስክ ግኝቶች ተጠቃለው ሲታዩ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች

 ምክክሩ አገርን ማሻገርና በመሰረታዊ የጋራ


ጉዳዮቻችን ላይ መግባባትን መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ
የመሆኑን ያህል ሂደቱም የዜጎችን ተሳትፎ ያረጋገጠ
ይሆን ዘንድ ህብረተሰቡን የማስገንዘብና የማሳተፍ
ጉዳይ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር
ነው፣
የቀጠለ.....
 የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም የተግባር አፈጻጸም ሂደት
ሙሉ ሊሆን ይገባል፣
 በየክልሎቹ ተግባሩን በቋሚነት የሚያስተባብሩ ቢኖሩ
የኮሚሽኑ ጫና የሚያቃልል ከመሆኑም በላይ የተግባሩን
ቀጣይነት ስለሚያረጋግጥ በተቻለ ፍጥነት ቢደራጁ፣
 በአጀንዳ ማሰባሰብና ቀረጻ ተግባሩ ለመሳተፍ የተመረጡ
ተወካዮች ጊዜው እየዘገየ በሄደ ቁጥር መቀዛቀዝና
የፍላጎት ማጣት ሊያስከትል ስለሚችል ወደቀጣዩ ተግባር
ለማሸጋገር በተቻለ ፍጥነት ቢሰራ፣
የቀጠለ…..
 የተሟላ ስልጠና ባልተሰጠበትና የግንዛቤ ፈጠራ ስራው
አስቸጋሪ ሆኖ በቆየበት እንደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ
ከማሺ ዞንና ባሉ አካባቢዎች የማጠናከሪያ ስራ
መስራት አስፈላጊ ስለሆነ ተጨማሪ ስራ መስራት
ያስፈልጋል፣
 የበለጠ አሳታፊና ሁሉም አካባቢ ተወክያለሁ የሚል
የባለቤትነት ስሜት እንዲኖር ሁሉም ቀበሌዎች
ተሳታፊ እንዲሆኑ ሊደረግ ይገባል፣
የቀጠለ.....
 ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተሳታፊዎች በአጀንዳ ቀረጻ

ተሳታፊዎች ምርጫ ላይ ተሟልተው እንዲገኙ ማድረግ ትኩረት

ሊሰጠው ይገባል፣

 በምክክሩ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች

ግልፅ ውክልና የሌላቸው በመሆኑ መፍትሄ ቢፈለግለት፣

 የተሳትፎ ጥያቄ ያላቸው ተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ውክልና

አላገኘንም የሚሉ እውቅና ያልተሠጣቸው ብሄረሰቦች፣ የዩኒቨርስቲ

ተማሪዎች፣ የቀድሞ የሰራዊት አባላት እና የፖሊቲካ ፓርቲዎች(የጋራ

ምክር ቤቱ ያልገቡ እንዲገቡ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ቢቀጥል)፣


የቀጠለ......
 የምክክሩ ዓላማ ሀገራዊ መግባባትን መፈጠር ስለሆነ
ተከታታይ የሆነ የሚዲያ እና የተግባቦት ስራ ሊሰራ የሚገባ
መሆኑ፣
 ምክክሩ ሁሉንም ክልሎች ተደራሽ ማድረግ ስለሚገባው እና
ለምክክሩ ስራ የተመቸ አውድ ለመፍጠር የሰላም እና ፀጥታ
ችግር ያላባቸውን ክልሎች ወደ ስላማዊ ሁኔታ የሚመጡበት
መንገድ ቢፈለግ፣
 ለኮሚሽኑ ስራ ውጤታማነት የሚያስፈልጉ እንደ በቂ የሰው
ሀይል፣ ዳታ ቤዝ ማደራጀት እና ሌሎች ግባዓቶች እንዲማሉ
ቢደረግ የሚሉት ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች ናቸው፡፡
7. ማጠቃለያ
 በኮሚሽኑ እቅድ መሰረት አስቀድሞ በተቀመጠና ወጥ
በሆነ አቅጣጫ፣ እንዲሁም በጥንቃቄና ጥራት ባለው
የስልጠናና የሰነድ አያያዝና አደረጃጀት ተግባሩን
ለመምራት የተደረገው ጥረት ኮሚሽኑ ለጉዳዩ የሰጠው
ትኩረት ማረጋገጫ ነው፡፡
 ከክልልና ከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ያሉ ተባባሪና
ተሳታፊ አካላትን ግንዛቤ በስልጠና ለማሳደግና ሂደቱን
እንዲያሳልጡ የተደረገበትና የተፈጠረው መልካም
ግንኙነት እስከተልእኮው ፍጻሜ ድረስ አጠናክሮ መዝለቅ
ያስፈልጋል፡፡
የቀጠለ….
 አስቸጋሪና የጸጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ጭምር
የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ሳይቀሩ ራሳቸውን ለመስዋእትነት
አዘጋጅተው ተልእኳቸውን ለመፈጸም ያደረጉት ጥረት
ለህዝብና ለአገር ያላቸው ታማኝነት ማረጋገጫ ስለሆነ
ይህ ቁርጠኝነት እስከመጨረሻው እንደሚዘልቅ ተስፋ
እናደርጋለን፡፡
 የተሳትፎ ደረጃውን ክፍ ለማድረግ በአጀንዳ ቀረጻ ላይ
የሚሳተፉ ተወካዮቹንም ጭምር የሚያውቅበት ሁኔታ
በመፍጠር የሂደቱን ዴሞክራሲዊነት ማረጋገጥ አስፈላጊ
እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው ያምናል፡፡
የቀጠለ……
በመጨረሻም ኮሚሽኑ በርካታ ውጣ ውረዶችንና
አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ አገርና ህዝብ የጣሉበትን
ታሪካዊ ሀላፊነት ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት
እያደነቅን ቀሪው ተግባር የበለጠ ቁርጠኝነትን
የሚጠይቅ በመሆኑ የምክር ቤቱ ክትትልና ድጋፍ
ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ተጨማሪ አቅጣጫዎች
እንዲቀመጡ ቋሚ ኮሚቴው በአክብሮት ያሳስባል፡፡

የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ


አመሰግናለሁ!

You might also like