You are on page 1of 2

ቀን /ጌርክ/ -18/03/2015 ዓ.

ቦታ/ብቲ/ - እንጅባራ ከተማ

ሰአት -9፡00

ተሰብሳቢ አባላት/ ኩፓንትካ አባልካ /

1.ተሻገር ሙሉነህ - ሰብሳቢ /ኩፕፃንቲ/

2.አምሳሉ ንጋቱ -አባል

3.ወንድማለም ዳኛው -አባል

4.ይርጋለም ፈንቴ -አባል

5.አይነታው አባዋ -አባል

6.እሱባለው ክንዴ -ፀሐፊ/ፃፋንቲ/

አጀንዳ/አጀንዲ/፡- የተግባራትን እቅድ አፈፃፀም መገምገምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ መወያየት፡፡

የዕለቱን ስብሰባ የአገው ምሁራን ማህበር የዞን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተሻገር ሙሉነህ በሰላምታ
አስጀምረውታል ፡፡ በመቀጠልም በዕለቱ የምንወያይባቸውን ዋናዋና አጀንዳዎች ቃለጉባኤ አስይዘዋል ፡፡
በዚህም የአገው ምሁራን ማህበር ከዚህ ቀደም የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን በዋናነትም አባላትን
ለማፍራት፤ ስለ ማህበሩ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በማስጨበት ህዝባዊ ለማድረግ ፤ የተመዘገቡ አባላት
ዝቅተኛውን የአባልነት ክፍያ እንዲፈፅሙ ለማድረግ እንዲሁም የአገውኛ ቋንቋ የዞኑ 2 ኛ የስራ ቋንቋ
እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መስራትን አቅዶ እንደነበር አቶ ተሻለ አንስተዋል ፡፡ እነዚህን
ተግባራት ከግብ ለማድረስ ግን ያሉት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ከማህበሩ አባላትም ሆነ ከሌሎች አጋር
የመንግስት አካላት ያለው ቁርጠኝነት የላላ እንደሆነ አስረድተዋል ፡፡ የዞኑም ሆነ የወረዳው ኮሚቴዎች
ማህበረሰቡ ከማህበሩ በሚፈልገው ልክ እየተንቀሳቀስን አይደለም ፡፡ ፕሬዝዳንታችን ዶክተር ታምሬ
አንዷለም የሚለፋውን ያህል እየሔድን አይደለም ፡፡ ሁሉም የዞን ኮሚቴዎች በወረዳ ደረጃ የተቋቋሙ
ኮሚቴዎችን በመከታተል በኩል ያሳየነው ተሳትፎ ደካማ እንደነበርና የወረዳ ኮሚቴዎችም ተመሳሳይ
ችግር እንዳለባቸው ያስገነዘቡ ሲሆን በዕለቱ ተሰብሳቢዎች የሚከተሉት ሃሳቦች ለችግሮቹ
እንደመፍትሔ ተቀምጠዋል፡-

 ሁሉም የዞንና የወረዳ ኮሚቴዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የማህበሩን አባላት ቁጥር
ማሳደግ፡፡
 የዞንና የወረዳ ኮሚቴዎች የተመዘገቡት አባላት አመታዊ የአባልነት ክፍያ እስከ ታህሳስ 15 ድረስ
እንዲከፍሉና ይህም በማህበሩ የቴሌግራም ገፅ እንዲገለፅ ማድረግ፡፡

 አገውኛ 2 ኛ የስራ ቋንቋ እንዴት ይሁን የሚለው ጉዳይ በዋናነት ከቀበሌ ጀምሮ ካሉ የመንግስት
አመራሮች ጋር በትብብር በመስራት ያለውን ጠቃሜታ ማስረዳትና አገውኛ የስራ ቋንቋ ይሁን
ሲባል አማርኛ ቋንቋና አማርኛ ተናጋሪ ከአዊ ይጥፋ ማለት እንዳልሆነ ማስረዳት ፡፡

 አገውኛ በስፋት በሚነገርባቸው ሁሉም የዞኑ አካባቢዎች ከቀበሌ ጀምሮ አገውኛን 2 ኛ የስራ
ቋንቋ አድርጎ ያለውን ጠቀሜታ ቀስበቀስ ማስረዳትና ጥያቄውን ህዝባዊ ማድረግ ፡፡ ለምሳሌ
አሚኮ አገውኛን ጨምሮ በብዙ ቋንቋዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፤ በአዊ ውስጥ ያሉ በርካታ
ትምህርት ቤቶች በሁለቱም ቋንቋ ከነችግሩም ቢሆን እያስተማሩ ይገኛሉ፤ እንጅባራ መምህራን
ኮሌጅ በሁለቱም ቋንቋ እያስተማረ ይገኛል ፡፡ በአሁኑ ፖሊሲ መሻሻል ያለበት እንደተጠበቀ ሁኖ ፡፡
እነዚህ አገውኛን 2 ኛ የስራ ቋንቋ ማድረግ መብት ቢሆንም ለማስረዳት ቀላል ማሳያዎች ናቸውና
እንጠቀምባቸው፡፡

 የማህበራዊ ሚድያ አንቂ የአገው ልጆች በሚፅፏቸው ፁሁፎች የራስን መብት የሚጠይቁ እንጂ
የሌላውን መብት የሚነኩ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ፡፡

 ለአገውኛና ለአገው ምሁራን ማህበር ያለውን አመለካከት ሁላችንም በስርአት መረዳትና


ማስረዳት፡፡

 የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት አባላት አገውኛ 2 ኛ የስራ ቋንቋ የሚለውን አጀንዳ ጉዳዩ ቀጥታ
የሚመለከታቸው ስለሆነ ራሳቸው አንስተው እንዲወያዩት ማስገንዘብ ፡፡

 ቋንቋን ለማሳደግ ከሚያስችሉ ጉዳዮች አንዱ ሚድያ ስለሆነ ከዞን ጀምሮ ያሉ የኮምንኬሽን
ተቋማት በአገውኛ ዜናና የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመስራት ተደራሽ እንዲያደርጉ የእንጅባራ
ዩኒቨርስቲ አዊኛ ቋንቋናስነፁህፍ ትምህርት ክፍል በኩል ከአገው ጥናት ተቋም ጋር በመሆን
ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠናዎችን ለመስጠት ቢዘገይ እስከ ታህሳስ 15 ፕሮፖዛል
ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ውይይት ተደርጎባቸው ውይይታችን ተጠናቋል፡፡

You might also like