You are on page 1of 1

40/60 ክራውን ሳይት የጋራ ህንፃ ባለቤቶች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማህበር

የጥበቃ ሰራተኛ/ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት፤

1. ወደ ግቢ ውስጥ የሚገቡ ሰዎችን ማንነት በማረጋገጥ ያልተፈቀደላቸው ሰዎችና ያልተፈቀዱ ነገሮች እንዳይገቡ መከልከል እና
በተመሳሳይ ሁኔታ ከግቢ የሚወጡ ንብረቶች የማን እንደሆኑ ማረጋገጥና እንደ አግባብነቱ ከማህበሩ አስተዳደር በሚሰጠው
የማውጫ ፍቃድ መሰረት ማስተናገድ፣
2. በግቢውና በህንፃዎቹ ውስጥ በባለቤቶቹም ሆነ በሌሎች አካላት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል ለየት ያለ
እንቅስቃሴ ሲኖርም እንደ አስፈላጊነቱ ትኩረት ሰጥቶ መከታተልና ሙሉ መረጃ መያዝ፣
3. ግቢው ውስጥ የሚገኝ የማንም ይዞታ የሆነ ንብረት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ማድረግ፤ ግቢው ሰላማዊ እና ከደህንነት
ስጋት የጸዳ እንዲሆን የሚያስችል ስትራቴጂ በመቅረጽ እና አስፈላጊ የሆነ ቁሳቁስም ሆነ የሰው ኃይል ካለ እንዲሟላ
በማድረግ የግቢው ደህንነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፣
4. የማህበሩን ዋና መተዳደሪያ ደንብ፣ የቤት እድሳት ጊዜያዊ ውስጠ ደንብ ቁጥር 002/2010 እና ሌሎች በተለያዩ ጊዜያት
የሚወጡ ውስጠ ደንቦችን ጠንቅቆ ማወቅ እና ማስከበር፣
5. ጊዜያዊ ውስጠ ደንብ ቁጥር 002/2010 ለማስከበር በህንፃው በተለያዩ ክፍሎችና በዙሪያው ተንቀሳቅሶ ምልከታ በማድረግ
ደንቡን የተላለፉ ቤቶች ካሉ የቤት ቁጥሩን በመያዝ ለማህበሩ አስተዳደር ቢሮ በጽሁፍ ማሳወቅ ወይም በማህበሩ አስተዳደር
መዝገብ አዘጋጅቶ በመዝገቡ ላይ በየዕለቱ ያጋጠሙ መተላለፎችንና ችግሮችን ማስፈር፣
6. ግቢው እና በግቢው ውስጥ ያለው ንብረት ሁሌም በጥበቃ እይታ ውስጥ እንዲሆን የጥበቃ ሰራተኞችን ውጤታማ በሆነ
መልኩ ማሰማራት፣
7. በግቢው ውስጥ በሰው ወይም በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ወዲያው ለግቢው አስተዳደር ወይም ለስራ አመራር ቦርድ
ማሳወቅ፤ የደረሰው ጉዳት በጥበቃ ክፍተት ከሆነም የሚመለከተውን ጥበቃ ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ፣
8. የስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓትን ማክበር፣ በስራ ሰዓትም በአግባቡ መስራት፣
9. ለግቢው ማህበረሰብ መልካም ስነምግባር ማሳየት፣
10. ከማህበሩ ስራ አስኪያጅ ጋር በጥምረት መስራት፤ ከስራ አመራር ቦርድ የሚሰጡ ማናቸውንም ትእዛዞችን በመቀበል ተግባራዊ
ማድረግ፣ ሲሆን
11. የጥበቃ ኃላፊ ተጠሪነቱ ለዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆን ክስተቶችን (incident) ለምሳሌ በሰውና ንብረት ላይ የደረሰ አደጋ፣
ስርቆት ወዘተ ወዲያውኑ ለስራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር ሪፖርት ያደርጋል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት Page 1 of 1

You might also like