You are on page 1of 44

የመዛግብትና ጽሑፍ ቅርሶች አጠባበቅ

ተግዳሮትና ዕድል ፈንታ


ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ
መግቢያ
 መዛግብቶችና የጽሁፍ ቅርሶች ለቀጣይ ትውልድ መተላለፍ የሚገባቸው
ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ናቸው፡፡ እነዚህ ብርቅና የማይተኩ ቅርሶች ያለፈውን፣
የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ በማስተሳሰር የመንግስታዊና ሕዝባዊ
ሥራዎችና እንቅስቃሴዎች የታሪክ አሻራ ማኖሪያ ምስክር እና ቅርስ
እንዲሆኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ ደህንነታቸው መጠበቅና ማረጋገጥ አለበት፡፡

 መዛግብቶችና የጽሑፍ ቅርሶች በአንድ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ተሰባሰበው


ጥበቃ ካልተደረገባቸው ሊወድሙ ይችላሉ፡፡ መዛግብቶቹን ያመነጫቸው
ተቋም አስተዳደራዊ ጠቀሜታቸውን ስለጨረሱና ተፈላጊነታቸው ስላበቃ
በቀጣይ የመዛግብትነት ፋይዳ የሚኖራቸውን ሪከርዶች ሃላፊነት በጎደለው
መልኩ ሊያስቀምጧቸው ወይም ከተቋም ውጪ አውጥቶ ሊያወድሟቸው
ይችላሉ
የቀጠለ….
 በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚገኝ ለዓመታት በአባወራ ወይም እማወራ
ተጠብቆ የቆየ የጽሑፍ ቅርስ በልጅ ወይም በልጅ ልጅ ከቤት ተጠርጎ
ሊጣል ይችላል፡፡
 አብያተመዛግብትና አብያተመጻሕፍት እነኚህን ተንቀሳቃሽ ውድ

ቅርሶች ተሰባስበው፣ ተደራጅተው፣ ተጠብቀው ለጥናትና ምርምር


ዋነኛ ምንጭ እንዲሆኑና እና ለማህበረሰብ ዕውቀት መበልፀጊያ
ቁልፍ የመረጃ ሃብት እንዲሆኑ ለአገልግሎት የሚውሉባቸው
ማዕከላት ናቸው፡፡
 አብያተመዛግብትና አብያተመጻሕፍት ከተለያዩ ምንጮች

ያሰባሰበቸውን መዛግብትና ጽሁፍ ቅርሶች ደረጃውን የጠበቀ


የጥበቃና እንክብካቤ ሥርዓት መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የመዛግብትና ጽሑፍ ቅርስ አጠባበቅ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳቦች
የአጠባበቅ ወይም የመከላከል ሥርዓት /Preservation/ ምንድን
ነው?
 የአጠባበቅ ወይም የመከላከል ሥርዓት የሚለው ፅነሰ ሃሳብ

የአብያተመዛግብት እና የአብያተመጻሕፍት መሰረታዊ ሳይንሳዊ


አሰራር ሥርዓት አተገባበር /Principles and paractice/ አንዱ
ክፍል ነው፡፡
 ተቋማቱ ባላቸው አጠቃላይ ስብስብ ላይ ያለምንም አካላዊና

ኬሚካላዊ ንክኪ እና ህክምና ጠቀለል ያለ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ


መዛግብትና ጽሑፍ ቅርሶችን ከስጋትና አደጋ መጠበቅ ማለት ሲሆን፡፡
የቀጠለ….
 ይህም ፖሊሲን፣ የቅድመ አደጋ መከላክል ፕሮግራሞችንና
ሌሎች የመመሪያ ዝግጅቶችን፣ የግብአት አቅራቦቶችን፣
የክምችት ቦታ ደህንነት ክትትሎችን፣ የመደርደሪያና አቃፊዎች
ጥራት ወይም ደረጃ፣ የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን
ወዘተ… ማዘጋጀት፣ ማሟላትንና ክትትል ማድረግንና የተቀናጀ
አሰራር ሥርዓትን መዘርጋት ያጠቃልላል፡፡
የመዛግብት እንክብካቤና ህክምና /ኮንዘርቬሽን/
 የመዛግብቶችና ጽሑፍ ቅርሶች የአፈጣጠር ቅደም ተከተል
ሳናፋልስ ሊመጣ ከሚችል ጉዳት የምንጠብቅበት እና ያላቸውን
የመዛግብትነት ፋይዳ ወይም የመረጃ ይዘትና ጥራት
/Content/ ሳይቀንስ ባለበት እንዲቀጥል የምናደርግብት፣
የተጎዱ ስብስቦችን ካልተጎዱት የምንለይበት፣ ለጥናትና
ምርምር እና ኤግዚቢሽን አገልግሎት መዋል የሚችሉ
መሆናቸውን የምናረጋግጥበት እና በስብስቦች ላይ ተከታታይና
የማያቋርጥ ቁጥጥርና ክትትል የምናደርግበት እንዲሁም
እርምጃ የምንወስድበት ሥርዓት ነው፡
የመዛግብት ጥገና እና ህክምና
 ይህ ፅንሰ ሃሳብ እያንዳንዱን የተጎዱ ነጠላ መዛግብቶችን ወይም
የጽሑፍ ቅርሶችን በመለየት ሲመነጩ ወደ ነበሩበት ቀድሞ
ሁኔታ /ኦርጂናል አፐራንስ/ የምንመለስበት፣ የምንጠግንበት
ወይም ያላቸውን ሥነ ውበትና ጥራት የምናሻሽልበት ሥርዓት
ሲሆን ለአብያተ መዛግብት እና መሰል ተቋማት አቅም ፈታኝና
ውድ ነው፡፡
መዛግብትን በሌላ ቁስ መቀየር /Reformatting/
 ይህ ዘዴ የመዛግብቶችንና የጽሑፍ ቅርሶችን ይዘት ወደ ሌላ
ቁስ በተለያዩ ዘዴዎች በመገልበጥ የምናስቀምጥብት ወይም
ለረዥም ጊዜ ተጠብቀው እንዲቆዩ የምናደርግብት ከዘመናዊ
ቴክኖሊጂ ጋር የተሳሰረ ስርዓት ነው፡፡ ይህ ሥርዓት
መዛግብቶችን ረዥም ዕድሜ ጠብቆ ለማቆየት ከሚሰጠው
ጥቅም ባሻገር ዋና ቅጂዎች እንዳይጎዱ አማራጭ በመሆን
አገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናል፡፡
መዛግብትን ጠብቆ የማቆየት ታሪክ

 የመዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች አጠባበቅ ሥርዓት ሙያ ሆኖ


መታወቅ የጀመረው ከ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንደነበር
መረጃዎች ያመላክታሉ፤ ይሁንና የአጠባበቅ ባህሉና አተገባበሩ ግን
በተለያዩ የዓለማችን ህዝብ ጋር እጀግ የቆየ ነው፡፡
 የተለያዩ የዓማችን ማህበረሰቦች ጥንታዊ የተደጎሱና ጥቅል

መጻሕፍትን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከእሳት፣ ከነፍሳት እና


ሌሎች ጉዳት አምጪ አደጋዎች ይጠብቁ ነበር
 ግብፃውያን የጽሑፍ ውጤቶችን ለመጠበቅ ስካራብ የተባለ

ህጽዋት ይጠቀሙ ነበር


የቀጠለ….
 ባቢሎናውያን ናቡ የተባለ ጣኦትን የጽሑፍ ሀብቶቻቸው ጠባቂ
አድርገው የወስዱ ነበር
 በክርስትና ማህብረሰብ የጽሑፍ ሃብቶች ጠባቂ ተደርገው

የሚወሰዱ ሶስት ቅዱሳን ነበሩ እነርሱም ቅዱስ ላውራንስ፣ ቅዱስ


ጄሮም እና አሌክሳንዲሪያ ቅዱስ ካትሪን ናቸው
 በአንዳንድ ክርስቲያን ገዳማት በጥንታውያን መጻሕፍትን

ከእስርቆት ለመከላከልና የቅዱሳን ምስሎች እና መቅሰፍት


የመጨረሻ ገፅ ላይ ያስቀምጡ ነበር፡፡ ይህ የመጻህፍት መቅሰፍት
ወይም እርግማን/book curse/ በመባል ይታወቅ ነበር፡፡
የቀጠለ….
 በጥንታውያን ቻይናውያን ዘንድ ዊ ታዎ/Wei T'O/ የተባለ
ጣኦትን የጽሑፍ ሀብቶቻቸው ጠባቂ አድርገው የወስዱ ነበር
 ከ500 ዓመት በላይ ባስቆጠሩ የቻይናውያን ጥንታዊ እጅ ጽሑፍ

ውጤቶች ውስጥ ስለ ዊ ታዎ የሚያወሱ ጽሑፎች ይገኛሉ፤


በተለይም ዊ ታ ዎ የጽሑፍ ቅርሶችን ከእሳት ይጠብቃል የሚል
ዕምነት ነበር፡፡
 ዛሬም በቻይና ወረቀቶችን ከአሲድ ነጻ የሚያደርገው ዘመናዊ ቁስ

ለክብሩ መገለጫ በዚሁ ጣኦት ተሰይሞ ይገኛል፡፡


የቀጠለ….
 አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የሰው ልጅ መረጃዎችን
በዋሻ ውስጥ በመቆርቆር መያዝ ወይም ማስፈር የጀመረው
ከ32,000 እስከ 40,000 ዓመታት በፊት ነበር፡፡ መረጃዎችን
በቃል ከማስተላለፍ ባሻገር በጽሑፍ መያዝና ማስተላፍ ግን
የጀመረው በ4,000 ዓመት ዓለም አካባቢ እንደነበር የታሪክ
ድርሳናት ያመለክታሉ ይህን ተከትሎ ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ
እና ታሪካዊ ጉዳዮችን በጽሑፍ በማስፈር የመጠበቅ
ተግባር፣ይህን ሥራ የሚሰሩ ሰዎች /Scribe/ የተለዩና
የሚጽፉበት ሥፍራም /Scriptorium/ እየተለየ መጣ፡፡
የቀጠለ….
 በእኛም ሃገር የቁም ጽህፈት ችሎታና ዕውቀት ያላቸው ሰዎች
በንጉሳውያን በተዘጋጀላቸው ሥፍራዎች ታሪኮችን ይጽፉ
መጻህፍት ይገለብጡና ለትውልድ ወደ ትውልድ ያሻግሩ ነበር ነበር
፡፡ ለአብነትም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በ250 በግ የብሉይ
ኪዳን መጻሕፍትን በ5 ቁም ጸሐፍት አሰገልብጠዋል፡፡
 በመካከለኛው የአውሮፓ ታሪክ ህዳሴ ዘመን የጽሑፍ ሃብቶችን

ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ከማስተላለፍ ወርቃማ ዘመን ሲሆን


በጆን ጉተንበርግ የተፈጠረው ማተሚያ ማሽን የዚሁ ዘመን
ውጤት ነበር፡፡
የቀጠለ….
 በእኛም ሀገር የጽሑፍ ሥራ በ1000 ዓመተ ዓለም አካባቢ
ከሳበውያን ጋር አብሮ እንደመጣ ጥናቶች ያመላክታሉ፤ ዛሬም
ድረስ በሳባውያን ቋንቋ በድንጋይ ላይ ተቀርጸው የሚገኙ
ጽሑፎች በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ይገኛሉ፡፡ በአርግጥ ድንጋይን
ብቻ ሳይሆን ብረቶችንም ሃሳባቸውን ለመግለጽ ታሪካቸውን
ለመጠበቅ ተጥቅመውበታል
 በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በእንጨት እና ሸክላዎች ላይ

መረጃዎችን ሪከርድ ማድረግም ተጀምሯል


 በላስላሳና ተጣጣፊ ቁሶች መጻፍ የተጀመረው ከዘጠኙ ቅዱሳን

መምጣት በኋላ እንደተጀመረ የታሪክ ድርሳናት ያመላክታሉ


የቀጠለ….
 በተለየም ኢትዮጵያውያን ትኩስ የፍየል፣ የበግ፣የፈረስ ቆዳን
በመጠቀም በስፋት ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊና ታሪካዊ ክንውኖችን
በብራና ላይ ይጽፉ፣ይመዘገቡና ይጠብቁ ነበር /ብራና /Vellum/
የሚለው ቃል menberana ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ነው/
 ወረቀት ወደ ሃገራችን እስኪገባ ድረስ ለ1500 ዓመት ያህል ብራና
ላይ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊና ታሪካዊ ክንውኖችን ለመያዝና
ለመጠበቅ እና የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ዋነኛ ቁስ ሆኖ
አገልግሏል፡፡
 ዛሬም ድረስ እጅግ ውድ ቢሆንም ሃይማኖታዊ መጻሕፍት በዚሁ
ለስላሳ ቁስ ይፈጠራሉ፡፡
የቀጠለ….
 የብራና መጻሕፍት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሻገሩና ረዥም
እድሜ እንዲኖራቸው እና በጉድጓድ ውስጥ በአፈር እንዳይበሉ
ሽፋናቸው እጅግ ጠንካራ በሆኑ የወይራ፣ የጥድና የዋንዛ እንጨት
የሰራ ነበር፡፡ የብራና መጻህፍቱን በበሬ አንጀት በመስፋትና
በመደጎስም ጥበቃና እንክብካቤ ያድረጉ ነበር፡፡
 ኢትዮጵያውያን የወይራ ቀንበጦችን፣የዝግባ ቅጠሎችን፣ጤና

አደም፣ የኮሶ ቅጠሎችን /በማድረቅ/ የመሳሰሉ ህጽዋቶችን


በብራና መጻሕፍቱ ውስጥ በማስቀመጥ እንዲሁም በየወቅቱ በነጭ
እጣን በማጠን.....ወዘተ ባህላዊ በሆነ ዘዴ ጥበቃና እንክብካቤ
ያደርጉ ነበር
የጥበቃና እንክብካቤ ህሳቤን የቀየሩ ክስተቶችና ሥራዎች ወሳኝ ታሪካዊ ሂደቶች

 በ1933 ዓ.ም ዊሊያም ባሮ ከወረቀት ጋር በተያያዘ ያሉ የአሲዲ


ችግሮችን በመለየት የጽሑፍ ስራ ማሳተም ችሏል፤ ከ1900
እስከ 1949 የታተሙ መጻሕፍትን በማጥናት በ40 ዓመት
ቆይታቸው 96 በመቶ የሚሆነውን ቅደመ መልካቸውንና
ይዘታቸው እንደጠፋ በጽሁፉ አረጋግጧል ይህም ከወረቀቱ
አሲዳማነት ጋር የተያያዘ መሆኑን በማረጋገጡ ከአሲዲ ነጻ የሆኑ
ወረቀቶችን የመጠቀም ልማድ እንዲጀመርና ቀደሞ የተፈጠሩትን
ወይም የታተሙትን የጽሑፍ ሃብቶች በላብራቶሪ የማከምና
ከአሲዲ ነጻ የማድረግ ሥር እንዲጀመር አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
የቀጠለ….
 በ1966 በኢጣሊያ የተከሰተ ጎርፍ፡- በኢጣሊያ ፍሎረን ግዛት
በተከሰተው ጎርፍ እጅግ በርካታ ታሪካዊ ውድ የጽሑፍ ሃብቶች
ሊወድሙ ችለዋል
 በ1967 ዓ.ም የኮሎራዶ ግዛት ዩንቨርሲቲ በከፍተኛ ጎርፍ

በመጠቃቱ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የመረጃ


ሃብትና ቁሶች ሊወድሙ ችለዋል
 በ1789 ዓ.ም በናፖሊዮን ቦናፓርት የተቋቋመው የግብፅ

ሳይንስ ጥናትና ምርምር ተቋም በ2011 ዓ.ም በእሳት ተያያዞ


ከነበሩት 200,000 የመረጃ ሃብቶች 30,000 ብቻ ማዳን
ተችሏል
የቀጠለ….
 በ1992 UNESCO የዓለም ዶክመንተሪ ቅርሶችን እንዲጠብቅና
እንዲመዘግብ የተቋቋመው Memory of the World በ1995
ባስጠናው አንድ ጥናት በ35 ሃገራት የሚገኙ በርካታ
አብያተመጻህፍት በእርስ በእርስ ግጭት፣ በመጠነ ሰፊ ጦርነት፣
በእሳት አደጋ፣ በጎርፍ ሙሉ ለሙለና በከፊል ሲወድም
በውስጣቸው የሚገኙ የማይተኩ ውድ የጽሁፍ ቅርሶች ላይገኙ
ተሸኝተዋል፡፡
የቀጠለ….
 በዚሁ ጥናት በ105 ለሚገኙ የዓለም አቀፍ መዛግብት ም/ቤት
/ICA/ አባል አገራት በቀረበ መጠይቅ 6250 የመዝግብትና
ጽሑፍ ቅርስ ክምችቶች ውስጥ 6000 ተፈጥሮአዊና ሰውሰራሽ
በሆኑ ምክንያቶች በስብስቦቻቸው ላይ ጥፋት እንደ ደረሰ ምላሽ
ሰጥተዋል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-
መጻሕፍትም ሰው ሰራሽ በመሆኑና ጥንቃቄ በጎደለው አያያዝ
ምክንያት ጥፋት እና ውድመት እየደረሰ መሆኑን ምላሽ ከሰጡና
ክምችቱ ካላቸው የአፍሪካ ሃገራት ተቋማት ውስጥ አንዱ ነበር፡፡
 ይህም በአብያተመዛግብትና አብያተመጻሕፍት እና መሰል መረጃ
ማዕከላት ዘመናዊ የጥበቃና እንክብካቤ ሥርዓት መዘርጋት ወሳኝና
ግዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን አመላክቷል
የቀጠለ….
 በ2001 ዓ.ም መስከረም 11 በኒውዮርክ የዓለም ንግድ ማእከል
የደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት 2750 በላይ ሰዎች ቢሞቱም ከ10
ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመት መሰረተ ልማት ቢወድምም፣
ህንፃዎች ቢደረሱም ፣ፔንታጎን ከፊል ህንጻ ቢፈርስም ተቋማቱ
ያለምንም እንከን ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለቸው በመረጃ
አያያዝና አጠባበቅ አምሳያ ቅጂ/Back up/ በተለያዩ ስፍራዎች
መያዛቸው ነበር፡፡ ይህ ክስተት በዘመናዊ የመረጃ ስራ አመራር
አዲስ አቅጣጫና እስቤን የወለደ ነበር፡፡
በመዛግብት እና ጽሑፍ ቅርሶች አጠባበቅ ላይ የተደቀነ አደጋና ቀጣይ ዕድል ፈንታ

በሪከርድ አመንጪ ተቋማት ሪከርዶች አጠባበቅ


 በተቋማት ሪከርድ ሥራ አመራር ሥርዓት ውስጥ የሪከርድ ክምችት

ሥፍራና ሥርዓት፣ የሚፈጠሩበት ቁስ እና አካላዊ ጥበቃና


እንክብካቤ የሚደረግበት ሁኔታ ትኩረት ከሚያሻቸው ጉዳዮች
ዋነኞቹ ናቸው፡፡
 ለሪከርዶችና መዛግብቶች ጉዳት መዳረግ የተለያዩ ምክንያቶች

ቢኖርም፤ ሪከርዶቹና መዛግብቶች እራሳቸው ለጉዳታቸው መነሻ


ምክንያቶች ሊሆኑ ይላሉ፡፡ ሪከርዶችና መዛግብቶች የተፈጠሩበት
ቁስ አሲድ በውስጡ በብዛት ይዞ ይገኛል ይህም ሪከርዶቹና
መዛግብቶቹ በቀላሉ ለጉዳት እንዲዳረጉ ያደርጋቸዋል፡፡
የመዛግብት መፍጠሪያ ቁሶችና ማስቀመጫ አቃፊዎች
 ሪከርዶችን የምናስቀምጥበት አቃፊ ጥራቱን ያልጠበቀ መሆኑና
ሪከርዶችን መሸከም ወይም መያዝ አለመቻሉ ፣ ከፍተኛ አሲዲ
በውስጥ መያዙና ወደ ሪከርዶቹ መዛመቱና ለሻጋታ ማጋለጡ፣
ለነፍሳት መፈጠር በቀላሉ የተመቸ መሆኑ፣ የሚሰሩበት ከእህል
ነክ ግብአት ስለሚሰራ ወረቀት የሚመገቡ አይጦችን መጥራቱ
 ሪከርዶችን በምንፈጥርበት ጊዜ የምንጠቀማቸው ወረቀቶች

ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና ከፍተኛ የሆነ የአሲድ መጠን ያላቸው


ናቸው፡፡
 አግራፍ፣ እስፒል፣ፋስትነር፣ስቴፕልስ የመሳሰሉ ብረት ነክ

ማያያዣዎች በቀላሉ ለሻጋታ የሚያጋልጡ አደገኛ ቁሶች ናቸው


ደካማ የሆነና ቸልተኛ አያያዝ
 በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በርካታ ተቋማት ወደ ፊት
የመዛግብትነት ፋይዳ ላቸውን ሪከርዶች የሚይዙበት መንገድ እጅግ
ደካማና ሪከርዶቹን የሚያወድም ነው፡፡ በህንፃ ምድር ቤት፣
በጋራዥ፣ በህንፃ ጓሮ፣ ደረጃውን ባልጠበቀ ቆርቆሮ ቤትና በኮንቴነር
ከተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ጋር እንዲሁም በሪከርድና ማዕደር ቤት
መመገብና መጠጣት፣ ባልጸዱና በረጠቡ እጆች መነካካት፣ በባዶ
እጅ ፎቶግራፎችን መነካት፣ መቅደድና መስረቅ ወዘተ
 ከፍተኛ ሙቀት፣ የአየር እርጥበት፣ ያልተመጠነ ብርሃን፣ የተበከለ

አየር፣ የተሰበረ የውሃ ማስተላለፊያ ባንቧ ሪከርዶችን ለጉዳት


ሊዳርጋቸው ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡
በቤተ እምነቶች የጽሑፍ ቅርሶች አጠባበቅ

የዘረፊና የአገር ውስጥ ግጭቶችንና ጦርነቶችን ከመፍራት አንጻር


በዋሻ ውስጥ ቅርሱን መደበቅና ቀፍሮ በመቅበር፣ በሐይመኖት
ተቋሙ ኃለፊ ቤት ወይም ግለሰብ እጅ ማስቀመጥ እና ከቦታ ቦታ
ያለ በቂ እንክብካቤና ጥንቃቄ ማዘዋወር በርካታ ቅርሶች ለከፍተኛ
ጉዳት ተዳርገዋል፡፡
በዋሽ ውስጥ ቅርስን መደበቅ
 የደበቀው ግለሰብ በድንገት ቢሞት ቅርሱ እስከጭራሹን ሊጠፋ

ይችላል
 በእርጥበት ሊወረዛ፣ ሊበሰብስ፣ በነፍሳትና ተባያት ሊበሉ የችላሉ
 ተገቢውን ብርሃን ስለማያገኝ ሻጋታ በማውጣት የፊደላቱ ይዘትና

ውበት ይጠፋል
የቀጠለ….
በግለሰብ ቤት ሲቀመጡ
 በየጊዜው ስለማይጸዱ በአይጥና በነፍሳት ሊጠቁ፣ በእንግልት

ምክንያት በቀላሉ ሊቀደዱ ይችላሉ


 ማስቀመጫው ወይም መደርደሪያው ደረጃውን ያልጠበቀ

በመሆኑ ለከፍተኛ ጉዳትና መታፈግ ይጋለጣሉ


 ለተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ጉዳቶች በእጅጉ የተጋለጡ

ናቸው
በነፍሳትና እርጥበት ጉዳት የደረሰባቸው የጽሑፍ ቅርሶች
የአመለካከትና የግንዛቤ ክፍተት

 የመዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች አጠባበቅ ሌላኛው ግን አደገኛው


ተግዳሮት የአመለካከት ችግር ነው፡፡ በተለይም ይህ ችግር
በአብያተመዛግብት፣ አብያተመጻሕፍት እና መረጃ ማዕከላት አነስተኛ
በሚመስልም ችግሩ የከፋ ነው፡፡
 እነኚህን ውድና የማይተኩ ቅርሶች የሚያደራጁና የሚጠብቁትና
የሚንከባከቡት በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎች ባለመሆኖቸው
የሚኖራቸው የባለቤትነትና የተቆርቋሪነት ስሜት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ
ይኖረዋል፡፡
 እንደዚሁም በነዚህ ተቋማት የሚሰሩና ውሳኔ የሚያሳልፍ ሃላፊዎች
የሙያው ጥልቀትና የጉዳዩን አንገብጋቢነት ባለመረዳት ወይም ቸልተኛ
በመሆን በቂ ግብአትና በጀት ለመመደብ ፍቃደኛ አለመሆን ይስተዋላል፣
ዲጂታይዜሽን / አምሳያ ቅጂ ፈጠራ/ ስጋትና መልካም አጋጣሚ

 ዲጂታዜሽን መረጃዎችን ወደ ኤሌክሮኒክ ቁስ የምንቀይርበት ወይም


የማናዛውርበት ወይም አምሳያ ቅጂ የምንፈጥርበት ሂደት ነው፡፡ ይህ
ዘመን ወለድ አምሳያ ቅጂ ፈጠራ መዛግብቶችንና የጽሑፍ ቅርሶችን
ረዥም ጊዜ የምናቆይበት እና የአገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ተደራሽ
ለማድረግ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡
 ዲጂታይዜሽን አስተማማኝ የጥበቃና እንክብካቤ አማራጭ ነው

ማለት ባይቻልም፤ የዲጂታል ኮፒ መፈጠር ግን ዋና ቅጂ


ዶክሜንቶችን ለተዳጋጋሚ ጉዳት እንዳይጋለጡ ያደርጋል፣ ደንበኞች
የመረጃ መረብ ተደራሽ ከሆነበት ማናኛውም ቦታ ሆነው አገልግሎት
እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣል፣ የመዛግብት ተቋማት ያላቸውን ስብስብ
በቀላሉ ለማስተዋወቅ ምቹ ነው፡፡
ተግዳሮትና ዕድል ፈንታ

 አምሳያ ፈጠራ ብዙ ጊዜ ወሳጅ፣ ውድ እና የመዛግብትና የጽሑፍ


ቅርሶችን የማጥፋት አቅም ያለው ነው ፣
 ዲጂታይዜሽን በተገቢ መልኩ ታቅዶ፣ በግልጽ መመሪያና ፖሊሲ

ካልተመራ እና ለተገልጋዮች ይፋ ሆኖ ካልተከናወነ የደንበኞችን


ዕምነት ማጣትንም ያስከትላል፤ ተገልጋዮች አንድ ጊዜ የተቋሙን
የመረጃ ቋት ፈትሸው የሚፈልጉትን ካጡ ምንም አይገኝም
ብለው ስለሚያምኑ ዲዚ
 ዲጂታዝ የተደረጉና ያልተደረጉ ቁሶች ግልጽ መሆን አለበቻው፣
የተክኖሎጂ መለዋወጥ

 በዲጂታል ቅጂ አምሳያ የተፈጠረላቸው መዛግብቶች


በማንበቢያ ማሽን ወይም ኮምፒውተር የሚነበቡ ናቸው፡፡
የማንበቢያ ማሽኖች በየጊዜው የመቀያየሩ በመሆናቸው
ለውጡን ተከትሎ አምሳያ ቅጂዎቹን ወቅታዊ ማድረግ
ይጠይቃል ይህም ከፍተኛ የገንዘብ አቅም የሚጠይቅ ነው፡፡
የሰለጠነ የሰው ሃይል አለመኖርና ደካማ ጥራት

 አምሳያ ቅጂ ፈጠራ በቢሮ እስካኒንግ ማሽን የሚሰራ ቀላል ተግባር


እድርገው የሚወስዱ አሉ ይሄ ግን የተሳሳተ ግምት ነው፡፡
 በዚህም ምክንያት በሙያው የሰለጠነ ሰው ስለማይሰራው በከፍተኛ

ደረጃ የጥራት ችግር ይገጥመዋል ይህም ለድጋሚ ቅጂ የሚጋብዝ


በመሆኑ ዋና ቅጂዎች እንዲጎዱ ያደርጋል፣
 ወደ ዲጂታይዜሽን ሂደት ሲገባ የሚቀመጥበት /የሚከማችበት/

በቂ የሰርቨር አቅም፣ የሚደራጅበትና የቀጥታ አገልግሎት/on-


line/ የሚሰጥበት ደረጃውን የጠበቀ ሶፍትዌር ፣ ደረጃውን የጠበቀ
ዲጂታል ማሽን፣ የአማስያ ቅጂ ፈጠራ ደረጃ እና እነዚህን የሚመራ
የሰው ሃይል አቅምና አደረጃጀት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ለውጦችን
እየተከተለ በቂ በጀት የሚመድብ አመራር ወይም ተቋም ያስፈልጋል
የኮፒ መብትና ታማኝነት አደጋ
 ወደ ዲጂታል ኮፒ የተቀየሩ መዛግብት በተለያዩ መልክ ሊቀየሩ
ይችላሉ ይህም የመረጃውን ታማኝነት አደጋ ውስጥ የሚከተው
ሰሆን በሌላ መልኩ የዋናው ቅጂ ባለቤትነት መብትንም የሚገፍ
ይሆናል፤ በተቻለ አቅም ለሕዝብ ክፍት የሆኑና የባለቤትነት መብቱ
የሕዝብ የሆኑ የመረጃ ሃብቶችን ዲጂታዝ ማድረግ ተመራጭ
ይሆናል ይህ ሲሆን ግን ለደንበኞች ግልጽ መሆን ይኖርበታል
ለስረቆት የተጋለጠ መሆን
 

 አምሳያ ቅጂ ፈጠራ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ስርዓት


ይፈልጋል፤ በዲጂታል ኮፒ የሚሰባሰቡ እና የሚቀየሩ /የሚቀየሩ/
መዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች የሚመሩበት ወይም የሚተዳደሩበት
ስርዓት መዘርጋት ያስፈልገል፤ በማን፣ በምን፣ እንዴት፣እስከ መቼ
መያዝና መቀመጥ አለበት የሚሉ ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ
ይኖርባቸዋል፣
 የዘመኑ አምሳያ ፈጠራ ቅጂ የሚያማልል፣ ውድ እና ለእኛ ሃይነቱ
አቅም አጠር ሃገር የማይደፈር ቴክኖሎጂ በመሆኑ ነጮቹ ጥንታውያን
የብራና መጻህፍት የሚገኙባቸውን አካባቢዎችን በማሰስ አባቶችን
እያታለሉ እና እያግባቡ በርካታ የጽሁፍ ቅርሶቻችን መዝረፊያ
ስልትም ሆኗል፤ አንዳንድ ተቋማትም የዚህ ሰለባ ሆነዋል፡፡
መፍቴሔ
በዓላማ የተገነባ የማከማቻ ቦታ
 የመዛግብትና ጽሑፍ ቅርስ ክምችት ክፍል
 ለተገልጋዮች ግልፅ ሆኖ በሚታይ
ስፍራ/አማካይ ቦታ/ ላይ የሚገኝ
 መዛግብቱን ለመያዝ በቂ ቦታ ያለው
 ግድግዳው ሆነ ወለሉ ለእሳት አዳጋ በቀላሉ
የማያጋልጥና ውሃ በማያስተላልፍ
ማቴሪያል የተሰራ
 የእሳት ማጥፊያዎች የተገጠመለት
 ለቀጥተኛ የፀሐይ ብርሃን ያልተጋለጠ
 የእሳትና ጭስ ስጋትና ክስተት ማንቂያ
ያለው
 የደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ ያለው
የቀጠለ….

 የቅድመ አደጋ መከላከል ዕቅድ እና ፖሊሲ


ሪከርዶችን የመጠበቅና የመንከባከብ ሥራ ውጤታማ የሚሆነው
ቅድመ አደጋ መከላከል ሥርዓት ሲኖር ነው፡፡ አደጋ ከተከሰተ
በኋላ መዛግብቶችን ከማከምና ከመጠገን ይልቅ ቀድሞ አደጋ
ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን መለየትና መዛግብቶቹ
የሚገኙበትን አካባቢ መቆጣጠርና መቃኘት የሚያስችል አሰራር
መዘርጋት ወሳኝ ነው፡፡
 የጥበቃና እንክብካቤ ሥራ የሚሰራ የሰው ሃይልና አደረጃጀት

መፍጠር
- ግልፅ ሃላፊነትና አደረጃጀት
የቀጠለ….
 ከፍተኛ የአመራር ድጋፍ መኖርና በቂ በጀት መመደብ
- በዓመታዊ በጀት ላይ ለጥበቃና እንክብካቤ ሥራ የተያዘ በቂ በጀት መያዝ
- ከ10 እስከ 15 ፐርሰንት ለዚህ ተግባር መዋል ይገባዋል
- ሳይንሳዊ አሰራሮችን መከተልና ግብአት ማማላት
- ከአሲድ ነጻ የሆኑ አቃፊዎችንና ክላሲሮችን መጠቀም
- ከመሬት ከፍታቸው እስከ 20 ሴንቲ ሜትር የሚርቁ ከዝገት ነፃ
የብረት መደርደሪያ መጠቀም
- መዛግብቱን ከብረት ነክ ከሆኑ ማያያዣዎች ማላቀቅና
በፕላስተክ ወይም ገመድ መተካት
- ለጥበቃና እንክብካቤ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ቁሶችን ማማላት
የቀጠለ….
 ተከታታይ ክትትልና ቁጥጥር በክምችቱ ላይ ማካሄድ
- ሙቀት መቆጣጠር፡- 20 እስከ 25 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ
- ማናፈሻ መሳሪያ መጠቀም
- አባራ መከላክልና በየወቅቱ በዓመት/ ሁለት ጊዜ/ የማናፈስና
የማጽዳት ሥራ ማከናወን
 መዛግብቶችን Ÿxታ vታ uU“”kdpeuƒ ¨pƒ እÍ‹” Ÿqhh ¾ìÇ

SJ’<” T[ÒÑØ& እ`Øuƒ "K¨<U TÉ[p‘


 uS³Ówƒ TŸT‰ ¡õM UÓw ŸSSÑw“ hà u<“ ŸSÖ׃

SqÖw'
 ¾መዛግብት ¡U‹ƒ ¡õK<”U J’ }ÁÁ» ¾Y^ ቦታ­‹” Ÿ›vD^“

Ÿqhh Tîዳƒ'
የቀጠለ….
 u¡U‹ƒ xታ
 ማህደሮች /óÃKA‹U J’ ›nò­‹ Ÿ}Ñu=¨< SÖ” uLÃ

›KSÚ“’n†¨<”T[ÒÑØ'
 ¾¡U‹ƒ xታ¨<” u›Óvu< TÅ^˃'
 KØmƒ Åmn­‹ Ÿ¡U‹ƒ ¡õK< uU“¨×uƒ ¨pƒ ua‹ S²Òታ†¨<”

T[ÒÑØ' እ“
 መዛግብቶች ÁK<v†¨<” ›nò­‹ u¾Ñ>²?¨< ðƒ„ uT¾ƒ ’õd„‹

S^vƒ ›KS^vታ†¨<” Sð}i ÃÑvM'


የቀጠለ….
 u›ÑMÓKAƒ Ñ>²?/u›ÖnkU Ñ>²?
 መዛግብት ለአገልግሎት Ÿ›nòÁ†¨< እ”Ç=¨Ö< c=Å[Ó K[ÏU Ñ>²?Áƒ
Kw`H” }ÒMÖ¨< ›KSqየታ†¨<” T[ÒÑØ'
 u›nò ¨<eØ ÁKA መዛግብቶችን uU”U ›Ã’ƒ SMŸ< S_ƒ Là ŸTekSØ SqÖw'
 ¾›”É መዛግብት u`"ታ pÍ=­‹ ŸT>ðKÑ<uƒ Ñ>²? Ÿ*`Ï“K< Là ¾}’d¨<”
¾SËS]Á pÍ= uSÖkU k]­‡” ö„ u¢ú­‹ T²Ò˃'
 ለአገልግሎት ¾¨Ö< መዛግብቶች uT>SKc<uƒ ¨pƒ ወደ አቃፊያቸው በትክክል
መግባታቸውን ማረጋገጥ
 KY^ ¡õKA‹“ K}ÑMÒÄ‹ u}Ñ–¨< ›Ò×T> G<K< ስለመዛግብቶች ›ÁÁ´“
›ÖnkU Ó”³u? KSõÖ` ¾T>Áe‹M ÑKí TÉ[Ó ÃÑvM'
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

You might also like