You are on page 1of 2

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዲሱ የከፍተኛ

ትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት በዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብዕ ኮሌጅ የቅድመ
ምረቃ ፕሮግራሞች የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፕ በዲላ ዩኒቨርስቲ ከሚያዝያ 9-10/2013 ዓ.ም
ይካሄዳል።
ከመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትና ከሌሎች
ባለድርሻ አካላት በወርክሾፑ ይሳተፋሉ።

በማህበራዊ ሳይንስና ሰነ-ሰብዕ ዘርፎች የቅደመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሀገራዊ የሥርዓተ-ትምህርቶች ግምገማ
ወርክሾፕ እየተካሄደ ይገኛል
ዲዩ፤ሚያዝያ 9 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር
በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች የቅደመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሀገራዊ
የሥርዓተ-ትምህርቶች ግምገማ ሀገራዊ ወርክሾፕ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ወርክሾፑን በንግግር የከፈተቱት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕ እና የፕሬዚዳንቱ
ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ ከዚህ ቀደም የነበረው የተደራሽነት ሥራ ወደ ጥራት ተኮር ስለመሸጋገሩ የከፍተኛ
ትምህርት ፍኖተ ካርታ፣ የሥርዓተ ትምህርቶች ቀረጻና በትምህርቶች አግባብነትና ጥራት ዙሪያ እየተሠራ ያለው
ሥራ ማሳያ ነው፤ብለዋል፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ክፍሌ፤ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት
ሚኒስቴር በማህበራዊ ሳይንስና ሰነ-ሰብዕ ዘርፎች የቅደመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሀገራዊ የሥርዓተ-ትምህርቶች
ግምገማና ወርክሾፕ እንዲያዘጋጅ፣ 26 ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲያስተባብርና ይህን በመሰለ ወርክሾፕ ከዘርፉ ምሁራን
ግብረ መልስ ለማግኘት ዩኒቨርሲቲው ዕድል በማግኘቱ መደስታቸውን ገልጸው፤ በሂደቱም ለሥርዓተ ትምህርቶች
የተሻለ መሆን ዩኒቨርሲቲው የበኩል አስተዋጽኦ እንደሚያደረግም አስታውቀዋል፡፡ አክለውም የሥርዓተ
ትምህርቶች ቀረጻ ያስፈለገበት በዋናነት ለ 21 ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን የዘመነ የትምህርት አሰጣጥ
ለማዘጋጀትና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የሰው ኃይል ወደ ኢንዱስትሪው ለማገባት ወሳኝ በመሆኑ እንደሆነም
አስታወቀዋል፡፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የፕሮግራሞችና የስርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ
የሆኑት አቶ መኮንን ታደሰ በበኩላቸው ዲላ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ያለውን የሰው ሃይልና ልምድን
ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በብቃት እንደሚወጣ በመተማመን ይህ ኃላፊነት ለዩኒቨርሲቲው እንደተሰጠው
ጠቅሰው፤የተሰጠውንውም ኃላፊነት በአግባቡ እንደተወጣ ገልጸዋል፡፡
በወርክሾፑ ከ 26 ስድስት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘርፉ ምሁራንና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት
ሚኒስቴር ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የስርዓተ ትምህርቶች ግምገማ ወርክሾፕ ተጠናቀቀ


ዲዩ፤ ሚያዝያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር እና በዲላ ዩኒቨርሲቲ
አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ዘርፍ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የስርዓተ
ትምህርቶች ግምገማ ተጠናቀቀ፡፡
በወርክሾፑ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች
እንዲሁም ከግል ሚዲያ ተቋማት የተጋበዙ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የትምህርትን ጥራት ከማስጠበቅ አንፃር የስርዓተ ትምህርቶቹ መቀረፅና መሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ ሚንስቴር
መስሪያቤቱ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ ማድረጉ ተገቢ መሆኑን ምሁራኑ አንስተዋል፡፡
ከምሁራኑ የተገኘውን አስተያየት በአጭር ጊዜ በስርዓተ ትምህርቶቹ ላይ ተጨማሪ በማድረግ በአጭር ጊዜ
ለሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲልኩ አቅጣጫ መቀመጡን አቶ መኮንን ታደሰ በሳይንስና ከፍተኛ ት/ር
የፕሮግራሞችና የስርአተ ት/ት ከፍተኛ ባለሙያ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ሃላፊነት ከተጣለባቸው ሃያ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በወርክሾፑ የተሳተፉት ሃያ
ዩኒቨርስቲዎች መሆናቸውን ገልፀው ቀሪ ስድስቶቹ በነበረው የመረጃ ክፍተት አለመሳተፋቸውን ገልፀዋል።
ባለሙያው አክለውም ለስርዓተ ትምህርቶቹ መዳበር በግምገማ ሂደቱም ሆነ በቀረጻው የተሳተፉት ምሁራን እና
ሂደቱን በማስተባበር ዲላ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋናን አቅርበዋል።

You might also like