You are on page 1of 1

አሚና ቧሏ በወባ በሽታ ሞቶባት አንድ ልጇን ለብቻዋ የምታሳድግ ምስኪን ናት፡፡ መሀን እህቷ “ልጅሽ

ካንቺ ጋር በድህነት እየኖረ ከሚጎዳ እኔ አዲስ አበባ ወስጄ ላሳድግልሽ” ብላ ደገግማ ታስጨንቃታለች፡፡
አሚናም ሳትወድ በግድ ለልጇ የተሻለ ህይወት በማሰብ እምባዋን እየዘራች ልጇ ወደ አዲስ አበባ ላከች፡፡

ቀናት ቀናትን እየወለዱ ስለልጇ አንዳች ነገር ሳትሰማ 3 አመታት አለፉ፡፡ በዚህ ጊዜ አሚና ልጄን አዲስ
አበባ ሂጄ ማየት አለብኝ ብላ ቆርጣ ተነሳች፡፡ ድሬደዋ ባቡር ጣቢያ ለተሳፋሪዎች ፓፓያ እየሸጠች
ከምታገኝው ገንዘብ ላይ እየቆጠበች 19 ብር ያክል ደረሰች፡፡ ወደ አዲስ አበባ ለመሳፈር ሁለት ሽልንግ (
አንድ ብር ) ይጎድላታል፡፡

አሚና ዛሬ እድል ቀንቷት ፓፓዪ ሽጣ ሁለት ሽልንግ እንደምታገኝና ልጇን ለማየት ወደ ሸገር
እንደምትሳፈር ተስፋ ሰንቃለች፡፡ ባቡሩ ጡሩንባውን እየነፋ መጣ፡፡ ሙዝ ቡርቱካን እና ፓፓያ በትክሻቸው
የተሸከሙ ሴቶች ተሳፋሪዎች አንዲገዟቸው መሽቀዳደም ጀመሩ፡፡ አንደኛው ተሳፋሪ አንገቱን ከባቡሩ
መስኮት አሾልኮ ከአሰሚና ፊት ቡርቱካን የያዘችውን ሴት ቡርቱካኑን በሽልንግ ትሸጠው እንደሆነ
ይጠይቃታል፡፡ እሷም ምትሸጠው አንድ ብር እንደሆነ ትመልስለታለች፡፡ በዚህ ጊዜ የቸገራት እና ልጇን
ለማየት የጓጓችው እናት የያዘችውን ፓፓያ በሙሉ በሽልንግ እንዲገዛት ትጠይቀውና በሀሳቧ ይስማማል፡፡

ከኪሱ አንድ ብር አውጥቶ የምትመልስለት ሽልንግ እንዳላት ይጠይቃታል፡፡ እሷም አንድ ብሩን ተቀብላ
ሽልንግ ትሰጠዋለች፡፡ ተሳፋሪው ፓፓያዎቹን በትክሻዋ ከተሸከመችው ሰፊድ ላይ እያነሳ ከመልሱ ጋር
አብራ በሰጠችው ፊስታል ውስጥ መጨመር ይጀምራል፡፡ እየጨመረ ሳለ በመሀል አንደኛውን ፓፓያ
አገላብጦ ሲመለከተው ከቆየ ቡሀላ በብስጭት ፓፓያዎቹ የተበላሹ ስለሆነ እንደማይገዛት ይነግራታል ፤
ያመናጭቃታል፡፡

“ፓፓያው በስሎ እንጂ ተበላሽቶ አይደለም” እያለች ልብ በሚነካ ንግግር ልታስረዳው ሞከረች፡፡ ፓፓያውን
ወደ ሰፊዷ መልሶ ብሩን እንድትመለስ ሲጠይቃት ልቧ ተሰበረ፡፡ በርካሽ ሽጣ አንድ ሽልንግ ለማግኝት
ብትሞክርም የወደቀ አንጨት ሁነና ነገሩ ሳይሳካላት ቀረ፡፡ ተቆጥቶ አንድ ብሩን እንድትመልስ ሲጠይቃት
ሰጠችው፡፡ እሷም ሽልንጓን እንዲመልስላት በተራዋ ተሳፋሪዎን ጠየቀችው፡፡

ከሷ መልስ መቀበሉን የረሳው ይህ ሰው “የምን ሽልንግ ነው የምታወሪው? አጭበርባሪ” ብሎ ሰደባት፡፡


ባቡሩ ጡሩንባውን እየነፋ ተነሳ፡፡ አሚና መጮዃን ጀመረች “ሽልንጌን …… ሽልንጌን ……ሽልንጌን
ስጠኝ”፡፡ ባቡሩን በሩጫ የቻለችውን ያክል ተከተለች፡፡ ጥሏት ሲሄድ መሬት ላይ ተደፍታ ማልቀስ
ጀመረች፡፡

ተሳፋሪው ርቆ ከተጓዘ ቡሀላ ኪሱን ዳበሰ፡፡ ኪሱ ውስጥ ባቡር ከመሳፈሩ በፊት ያልነበረ ሳንቲም
ተቀምጧል፡፡ እጁን ወደ ኪሱ ልኮ ሲያወጣው ሺልንግ ነው፡፡ ሺልንጌን ስጠኝ እያለች በጩኸት ስትከተለው
የነበረችው የፓፓያ ሻጯ ሴት ሽልንግ፡፡

You might also like