You are on page 1of 74

FIRAA'OL M DIBAABAA

❤️❤️❤️ፍቅር_ሲፈርድ ❤️❤️

ክፍል_አንድ(1)

#በጣም__አስተማሪና__ልብ__አንጠልጣይ__ትረካ

ሳራ ትባላለች የሀረር ልጅ ናት እዚህ ከተማችን


አዲስ አበባ መኖር የጀመረችው አባቷ በስራ ምክንያት
ሀረርን ለቆ ሸገር ሲገባ ነው ... ታድያ ሳራ እድሜዋ
13 ን ሲያልፍና ከህፃንነት ወደ ታዳጊ ወጣት ስትሸጋገር
ውበቷ እንደልጅነቷ እዩኝ እዩኝ አይልም ነበር ሳራ
በአንፃሩ ... አፍንጫዋ ጎራዳ ፀጉሯ ገባ ገባ ያለ
ከመሆንም አልፎ ከርዳዳና ከለሯ የቀይ ዳማ የማይሉት
ወደ ነጭነት ያደላ ነበር በዚህም ሁሌም ቢሆን
ከቆንጆዋ የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ቤቲ ጋር ስትሆን
ብዙ ተማሪዎች ሙድ ይይዙባት ነበር ...

ሳራ በራሷ የማትተማመን ሴት ናት 7 ኛ ክፍልን


ተፈትነው ክረምት ሲገባ ሳራ ደስታዋ ወደር
አልነበረውም ከቤት ለመውጣት ምክንያቷ ትምህርት
ስለነበር ትምህርት አለመኖሩ ለሷ ትልቅ ደስታ ነው
አባቷ ይህን ቢያውቅም ምንም ማድረግ አልቻለም
እናቷን አታውቃትም ይሄ ተፅኖ አሳድሮባት ይሆናል
ሲል አባቷ በስተርጅና ሚስት ለማግባት ወስኖ አንዲት
በእድሜ በሰል ያለች ግን ስራዋ ገና የሀያቤቶች
መጀመርያ ላይ ያለች ልጃገረድ የምትመስል ሴት
አመጣ ... መጀመርያ ያየቻት ቀን ሳራ ደስ አላላትም
ቢሆንም ግን አባቷን ስለምታከብር በይሁንታ
ተቀበለች...
ወራቶች አለፉ የስምንተኛ ክፍል ሩብ አመት ፈተና
ደርሶ ሳራ ለሊት ተነስታ ለማጥናት ከመተኛ ክፍሏ
ወደሳሎን አመራችና መብራቱን አበራች ይሄኔ
ያየችውን ማመን አልቻለችም አባቷ በደም ተነክሮ
መሃል ወለሉ ላይ ተዘርሯል የእንጀራ እናቷ ማርታ አፏ
ታፍኖ ከበሩ ስር ካለው አግዳሚ ላይ ታስራለች ... ሳራ
መጮህ ጠፋባት ድንጋጤ ጭር ካለው ለሊት ጋር
ተደምሮ በፍርሃት ራደች አባ ብላ ልትቀሰቅሰው
ሞከረች ግን ያለናት ያሳደጋት አባቷ ላይመለስ
እስከወዲያኛው አሸልቧል ...

ሳራ የአባቷ ገዳዮች ሌቦች እንደሆኑ ፖሊስ


መረመርኩ ሲል አሳወቃት ውስጧ ግን አንድ ነገር
ይላታል የእንጀራ እናትሽ ማርታ እንዴት ተረፈች
ስለምንስ ይህ ሁሉ ሲፈፀም ድምፅ አልሰማሁም ቤት
ውስጥም የጠፋ አንድም ንብረት የለም ይህ ሁሉ ፈች
አልባ እንቆቅልሽ በሳራ አይምሮ ውስጥ ይመላለሳል
የአባቷ አርባ አልፎ ትምህርቷን ቀጠለች የእንጀራ እናቷ
ማርታም እንደእናት ሆኜ አስተምራለው ስትል ቃል
ገብታ ኑሮ ቀጠለ... ሳራ ህልሟ አንድ ሆነ ተምራ
ስትጨርስ የተበዳዮች ጠበቃ መሆን ህግ አጥንቶ
ወንጀለኛን ፈልፍሎ ለህግ ማቅረብ!!!

ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ሀሙስ ቀን እሷና


ቆንጂዬዋ ጓደኛዋ ቤቲ ወደቤት እያመሩ ሳለ የግቢው
ቆንጆና ቀለሜ ተማሪ ቤቲን ለመጀንጀን ወደነሱ
ተጠግቶ ሰላምታ ሰጣቸውና ተቀላቀለ ... ሶስቱም
ስለትምህርት ሲያነሱ ና ስለወደፊት እቅዳቸው
ሲነጋገሩ በመሀልም ቀልድ ቢጤ ጣል ሲያደርጉ
ሰፈራቸው ደርሰው መለያየት ግድ ሆነና ወደየቤታቸው
ሄዱ ... በሁለተኛውም ቀን አንድላይ ሄዱ ከዛማ
ሶስቱም ጥሩ ጓደኛሞች ለመሆን በቁ...

ይህ በዚ ብቻ አላበቃም ልኡል በቤቲ ውጫዊ ውበት


ተማርኮ የነበር ቢሆንም ሳያስበው ለካ ሳራን ወዷታል
ሳራ ስትስቅ ስታወራ ስታኮርፍ ... ብቻ ምንም ስትሆን
ለሱ ስሜት ይሰጠዋል ካላገኛት ይከፋዋል ይህን
ስሜቱን ግን ሸሽጎ መዝለቅ አልቻለም ለሳራ ፊት
ለፊት ከምነግራት ብሎ ለቤቲ እንድትነግርለት ነገራት
ይሄኔ ቤቲ በጓደኛዋ መበለጧ ውስጧን ቅናት አናወፀው
እሷ ቆንጆ ሆና በልኡል ሳትፈቀር ሳራ መፈቀሯ
አበሳጫት ... ሳራንም ከዚ ልጅ ጋር መሄድ እናቁም
ስትል ስለሱ መጥፎ ነገር አልፎም በመልኳ
እንደሚቀልድ ነገረቻት ሳራም ቤቲና ታምናትና
ትወዳት ስለነበር ልኡልን አይንህን ላፈር አለችው
ልኡልም ቤቲን ምን ሆና ነው ብሎ ሲጠይቅ እንዴት
የፍቅር ጥያቄ ይጠይቀኛል ብላ ነው ስትል
አራራቀቻቸው ... በትምህርቱ ጎበዝ የነበረ ልጅ ፈዘዘ
ሳራም ልኡልን እንደወደደችው የገባት ሲራራቁ ኖሮ
መልኳን የፈጠረውንና አባቷን ያሳጣትን አምላክ
እያማረረችና የማታውቃትን እናቷ ፎቶ ላይ አፍጥጣ
ማደር ጀመረች...

አንድ እለት ሳራ ትምህርት ቤት ሄዳ ራሷን በጣም


ሲያማት ግማሽ ቀን ላይ አስፈቅዳ ወደቤት አመራች
የውጪው በር በሰራተኛ ተከፍቶላት ገብታ በረንዳ ላይ
ጫማዋን ስታወልቅ ቤት ውስጥ ብዙ ሰው እንዳለ
ተረዳች ይሄኔ ድንገት አንድ አረፍተ ነገር ጆሮዋ ውስጥ
ጥልቅ አለ "እሷንም እንዳባቷ ቀብረን በነፃነት
እንኖራለን!!" ካካካካ( እረጅም ሳቅ)
ክፍል 2 ይቀጥላል.....

❤️ፍቅር_ሲፈርድ....✍

❤️ክፍል_ሁለት (2)

❤️እውነተኛና_____አሳዛኝ_____እንዲሁም_____አ
ስተማሪ...✍
።።።።።።
ሳራ አሁን ሁሉም ነገር ገባት የእንጀራ እናቷ
አባቷን ማስገደሏን አረጋገጠች በረንዳ ላይ ተቀምጣ
ለረጅም ሰአት በንዴት ተንገበገበች ምን አይነት እድለ
ቢስ ነኝ ግን ስትል እራሷን አማረረች ይሄኔ ሳታስበው
"ሳራ መቼ መጣሽ" አለች ማርታ ሳራም ለምን ይሁን
ባታውቅም ድንግጥ ብላ ቆመች ነይ ሰው ላስተዋውቅሽ
አለችና ተመልሳ ገባች ድንጋጤዋን ልብ ያለችውም
አትመስልም ነበር ... ሳራ ግራ ገባት ማን ይሆን እያለች
በውስጧ ተከትላት ወደውስጥ ገባች ስትገባ ሁለት
ሴትና አንድ ወጣት ወንድ ሶፋው ላይ ተቀምጠዋል
በየተራ ጨበጠቻቸውና ቆመችኝ ...

ሳራ ማለት እሷ ናት አለች እሷን


እያስተዋወቀቻቸው ትመስላለች እነሱ ጓደኞቼ ናቸው
እሱ ደግሞ... ብላ ንግግሯን ሳጨርስ ስልኳ ጠራ ይሄኔ
ሳራ ወደመኝታ ክፍሏ ገብታ ጋደም አለችናና
የማታውቃትን እናትንና ሳትጠግበው ያጣችውን
አባቷን ፎቶ እያየች ማልቀስ ጀመረች ፈጣሪ የረሳት
አልፎም የማያውቃት መሰላት... በመሃል ደሞ ልኡልን
ስታስታውስ ሉሌ ምናለ ባላውቅህ ትላለች... እንዲው
እያለች እንቅልፍ ይዟት ተኛች ግን ከወትሮው በተለየ
ፈርታለች በየደቂቃው ትባንናለች ልክ እንደአባቷ
እሷንም ልትገላት ማቀዷ እርግጥ በመሆኑ ቀኗን
መጠበቅ ወይስ ቤቱን ጥላ መጥፋት ሁለቱም ለሷ አደጋ
ነው ብትጠፋም መሄጃ ስለሌላት ብትኖርም ሞት
ስለታቀደላት ምርጫ የላትም ... ሳራ ከቀን ወደቀን
ዝም ፍዝዝ ማለት ጀመረች ይባስ ብላ ማርታ
ባልዋ(የሳራ አባት) ከሞተ 4 ወር ሳይሞላው እንኳ
በእድሜ ግማሽ የሚያንሳትን ባል አገብታ አረፈችው...

ባል ተብዬው ሳራን ያስጠናታል ልክ እንደ ታላቅ


ወንድምም ይንከባከባት ጀመር ሳራ ይበልጥ ግራ ገባት
ይህ በንዲህ እንዳለ የሚኒስትሪ ፈተና ደረሰ ይሄኔ ልኡል
ለሳራ የተወጋ ልብ የሚል ልቦለድ መፅሃፍ ሰጣት
ሳራም።ቤት ገብታ እስክታነበው ጓጓች ... ልክ እቤት
ስትገባ የመጀመርያ ስራዋ መፅሃፉን መግለጥ ነበር ይሄኔ
በጥንቃቄ የተጣጠፈች ወረቀት ከውስጡ አገኘች ከፍታ
ማንበብም ጀመረች...
"ሳሪቲ ትምህርት ተዘግቶ ከመለያየታችን በፊት
ስላለፉት ስህተቶቻችን ይቅር እንባባል!! ይገርማል እኔ
አንቺን አፈቀርኩ ማፍቀሬ ልክ ነበር ባንቺ እይታ ደግሞ
ስህተት ነበር የሰጠሁሽ መፅሃፍ ቆንጆ የፍቅር ህይወትን
ያስተምርሻል የኔ ውድ ማፍቀሬ ቢያስከፋሽም ማቆም
አልችልምና አሁንም ወደፊትም አፈቅርሻለሁ ...."
ይላል አምብባ ስጨርስ የደስታም የሀዘንም ስሜት
ተፈራረቁባት ደስታዋ ልኡል ሲሆን ሀዘኗ ደግሞ ጓደኛዋ
ቤቲ ናት...

ሳራ ለልኡል መልስ መፃፍ አልፈለገችም በነጋታው


የፈተና ፈረቃቸው ይለያይ ስለነበር ሳይገናኙ ቀሩ
ከ 2 ቀን በላይ ግን መታገስ አልቻለችም ሰፈሩ ድረስ ሄዳ
ከቤቱ አስጠራችው ልኡል ልክ ሲያያት ደንግጦ ቆመ ከዛ
ግን አይኖቻቸው ተግባቡ ቃል ሳይወጣቸው ልቦቻቸው
ፍቅርን ተጋሩ... ከዚ ቀን ጀምሮ ሳራና ልኡል አንድ ሆኑ
ሳራ ብሞት እንኳ ብላ ለልኡል ስለአለፈው ሁሉ
ህይወቷ አጫወተችው ቅስሙ ተሰበረ በቅርብም ከዛ
ቤት መውጣት እንዳለባት አብረው ወስነው ነገሮችን
ማመቻቸት ጀመሩ...

ሀምሌ አልቆ ነሀሴ ተራውን ሊረከብ ደርሷል አንድ


ክፉ ጠዋት ማርታ ከቤት ወጥታለች በቤት ውስጥ
ያሉት ሳራና የማርታ ባል ነበሩ ሳራ ሰውየውን
ባታምነውም ትወደዋለች ለዛም እሷን እንጂ እሱን
አትፈራውም ያን ቀን ግን ይህ ወጣት ሳራን ለስጋዊ
ስሜቱ ተመኛት ተመኝቶም አልቀረም በብዙ ልፋት
የእንቅልፍ ኪኒን እንድትውጥ አረገ ሳራም ድብን ያለ
እንቅልፍ ተኛች ይሄኔ ሊደፍራት ልብሶቹን ለማውለቅ
ይጣደፍ ጀመር...✍
#ክፍል 3 ይቀጥላል.....

❤️ፍቅር________ሲፈርድ

❤️ክፍል_ሦስት
❤️እውነተኛ___አሳዛኝና__አስተማሪ.....✍

ልብሱን አወላልቆ ሊደፍራት የሷን ልብስ


ማውለቅ ሲጀምር በሩ በሀይል ተንኳኳ ደንግጦ እላይዋ
ላይ ዘግቶባት ልብሱን ሰብስቦ ወደሻውር ቤት ገባና
መታጠብ ጀመረ ሰራተኛዋ በር ከፍታላት ማርታ ገባች
ባሌ ዛሬ ደሞ እንዴት ቀደምከኝ አለች የሻውሩን ድምፅ
ሰምታ ስላልሰማት መልስ ሳይሰጣት ቀረ... ብቻዋን
እያወራች ኪችን ገብታ ምግብ አቅርባ እየበላች
ሰራተኛዋን ስሚ ሳራ አልመጣችም እንዴ? ስትል
ጠየቀቻት ሰራተኛዋም የሳራን መግባት ተናገረች ...
ሳራ ለሰአታት ተኛች ማርታ ግራ ገብቷት እየከፈተች
ታያት ጀመር ባልየውም ስራውን ስለሚያውቅ ፈራ
ከ 10 ሰአታት ቡሃላ ነቃች ስትነሳ እራሷ በጣም ከበዳት
ማርታም ምን ሆነሻል አንቺ ስትል ጠየቀቻት ሳራም
ለማርታ ምንም ሳትመልስላት መታጠብያ ቤት ገብታ
ለማስታወስ ጥረት ታደርግ ጀመር ይሄኔ ውሃ
ሳይጠማት ውሃ ካልጠጣሽ ብሎ ያስጠጣት
ያለምክንያት አለመሆኑ ገባት ይህን ለማረጋገጥም
አንድ ዘዴ ፈጠረች ማርታ ዞር ስትልላት ልትደፍረኝ
እንደነበር ለማርታ ልናገር አለችው ደንግጦ አይ እባክሽ
ይቅርታ.... ቀባጠረ አሁን እርግጠኛ ሆነች ለማርታ
መናገሩንም ተወችውና ለፍቅረኛዋ ልኡል ልትነግረው
ወሰነች...

ልኡል ይሄን ሲሰማ አበደ እረጅም ሰአት ራሱን


አመመው በሳምንት ውስጥም ቤተሰቦቹን አሳምኖ
ሳራን እነሱ ቤት እንድትኖር አመቻቸ በሰአቱ ፍቃደኛ
አልሆነችለትም ነበር ቡሃላ ግን እናቱ ለምለምንና
ታናሽ እህቱን ልእልና ሲያስተዋውቃት እነሱም በደስታ
ከነሱ ጋር እንድትኖር ሲጋብዟት የፍቅረኛዋ ቤተሰብ
ሳይሆን የራሷ መሰሏት በሀሳባቸውም ተስማምታ
ከነሱ ጋር ለመኖር የአባቷን ቤት ለእንጀራ እናቷ ጥላላት
ወጣች ...

ልኡል ያደገው ከእናቱ ጋር ነው በጣም ሀብታም


ስለሆኑ ስለምንም መጨነቅ አይወዱም እናቱ ስለልጇ
ልኡል አብዝታ ትጨነቅለታለች ፈፅሞ ያለው መሳካት
አለበት ብላ ነው የምታምነው አባቱ አሜሪካ ነው
ያለው እህቱን በአንድ አመት ቢበልጣትም እሷ የ 11 ኛ
ክፍል ተማሪ ናት በርግጥ እሱ ትንሽ እያለ አቋርጦ
ስለነበር ነው የቀደመችው ያቋረጠበት ምክንያትም
ታሞ ስለነበር ነው። ስለልኡል ይህን ካልኩ ይበቃል
ወደዋናው ታሪክ ስገባ...

ሳራና ልኡል 9 ኛ ክፍልን ጨርሰው 10 ን መማር


ቀጥለዋል ሁለቱም የማይነጣጠሉ ጥንዶች ናቸው
እነሱን አይቶ ያልቀና የለም አብረው እስፖርት ይሰራሉ
ፊልም ያያሉ ያጠናሉ... ሳራ ለመጀመርያ ግዜ ደስተኛ
ሆነች ደምግባቷ ወጣ ቅርጿ ደግሞ ሞዴል ያስብላት
ጀመር የወንዶች አይን ውስጥ በቀላሉ መግባት ጀመረች
አላማዋ ላይ ትኩረት አድርጋ በደስታ ኑሮን ቀጣለች ...
የሚያሳዝነው ግን ደስታዋ ከወራት አልዘለለም ያቺ
ክፉ ማርታ አፈላልጋ የልኡልን እናት በማግኘት ስለሳራ
መጥፎ ነገር ነገረቻት ከዛም አልፋ እቤቷ እንድትመለስ
ካላረገቻት ልጄን ሰረቀች ብላ እንደምትከሳት
አስጠነቀቀቻት በዚ ግራ የተጋባችው ለምለም ጭንቀቷ
ልክ አጣ ልኡል እግሩ ሲወጣ ጠብቃም ሳራን አስጠርታ
መኝታ ቤት ዘግታ ታወራት ጀመር...

ሳራ ለልጄ ስል እንደሆነ እቤቴ የምትኖሪው


ገብቶሻል? ልጄ በጣም ካዘነ ወይ ከተናደደ ወይ
ከተጨነቀ አልያም በጣም ከተደሰተ እራሱን ይስታል
ይሄ ብቻ አይደለም ይሞትብኛል ለዚ ነው ያለው ሁሉ
የሚደረግለት በቅርብ አባቱ ነገሮችን አመቻችቶ
ይወስደናል ከዛም ይታከማል እስከዛ ግን ልጄ አንድ ነገር
እንዲሆንብኝ አልፈልግም አንቺ ለአባትሽ መሞት
ምክንያት እንደሆንሽ አሳዳጊሽ ማርታ ነግራኛለች ግን
በልጄ ቀልድ አላውቅምና እንዲጠላሽ አርገሽ በቶሎ
ቤቴን ለቀሽ ሂጂልኝ ስትል የሳራን ልብ ሁለት ቦታ
ከፈለችው በመጨረሻዎቹ አረፍተ ነገሮች እንባዋ ባይኗ
እየሞላ ፈሰሰ ይህች አለም የአጭበርባሪዎችና
የውሸታሞች ብቻ ናት አለች በውስጧ ይሄኔ እንባሽን
ጥረጊ ልጄ ያስከፋሁሽ መስሎት ደግሞ ... ብላ ተነስታ
ወጣች...

ከዛ ቀን ቡሃላ ህይወት ጭልምልም አለባት ማትሪክን


እንደምንም ተፈተነችና እንደተባለችው እንዲጠላት
እያያት ከወንዶች ጋን መላፋት አልፎም መሳሳም
ጀመረች ልኡልም በተደጋጋሚ እንደዛ የምታፈቅረ ልጅ
በመቀየሯ ምክንያቷን ማጣራት ጀመረ ግን ምንም
ፍንጭ አላገኘም ሳራም ብቻዋን ስትሆን ደም እምባ
እያለቀሰች ልኡሌ ላንተ ስል ነው ትላለች በሆዷ...
ታድያ አንድ ቀን ልኡልና እናቱ እቃ ሊገዙ ወጡ ይሄኔ
እህቱ አንድ ጎረምሳ እቤት በማምጣት ሳራን ልክ
ማሚና ሉሌ ሲገቡ እቅፍ አርገሽ ጭኑ ላይ ተቀመጪና
የምትስሚው ምሰይ አለቻት ሳራም የተባለችውን
ለማድረግ ሳትወድ በግዷ ተስማማች እንደተባለውም
ልክ ሲመጡ የተባለችውን አረገች ልኡል ያየውን ማመን
አቃተው ሳራን ጎትቶ ከልጁ ላይ በማንሳት ስሚ ሳራ
ካሁን ቡሃላ ላይሽ አልፈልግም ጭራሽ ከቤተሰቤ ከእናቴ
ፊት??? ሲል ጮኸባት ሳራም ምንም ሳትመልስለት
ስልኳን ይዛ እምባዋን እያዘራች ቤቱን ለቃ እግሯ
ወደመራት መጔዝ ጀመረች...
_ፍቅር___ሲፈርድ

ክፍል________4

#እውነተኛ______አሳዛኝና_____አስተማሪ

ሳራ እያነባች መንገዷን ቀጠለች ወዴት


እንደምትሄድ መድረሻዋን ግን ፈፅማ አታውቀውም
ብቻ ትሄዳለች ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ምን
እንደሚጠብቃት ታውቃለች ለዛም ወደዛ መሄድን
አታስብም ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ነገር ትዝ አላት
ስልኳን ሸጣው እስክትረጋጋ አልጋ ይዛ ማደር እንዳለባት
አሰበች ... እንዳሰበችውም ስልኳን አንድ ሞባይል ቤት
ሄዳ በርካሽ ገንዘብ ሸጠችላቸውና ሆቴል ውስጥ አልጋ
ተከራየች የዛን ቀን እዛው ሆቴል ውስጥ ስታለቅስ
አደረች በነጋታው ግን ነገሮችን ለመርሳት መጠጥ ቤቱ
ውስጥ ብቻዋን ገብታ መጠጣት ጀመረች...

የሚገርመው መጠጥ ጠጥታ የማታውቅ


አትመስልም ገንዘብ እንደሌላት እያወቀች ታዛለች
ይሄኔ ስክር ብላ እራሷን አታውቅም ይሄኔ የወንዶቹን
ሁላ ትኩረት ሳበች አብሯት መዝናናት የሚፈልገው በዛ
ይሄኔ ነበር ልኡል ከየት መጣ ሳትለው ያለባትን ከፍሎ
ከጭፈራ ቤቱ ይዟት ወጣ ከዛም አልጋ ይዞ አስገብቷት
ወቶ ሊሄድ ሲል በሰከረ አንደበቷ ምላሷ ተሳስሮ ለምን
መጣህ ለምን ትሄዳለክ እእእ ለካ ከቤታቹ አባረከኛል
አለችና ከት ብላ ሳቀች ልኡልም ተመልሶ ወደ ሳራ ዞር
አለና እንደማፈቅርሽ ስለምታውቂ ነው አይደል እንዲህ
የምትሆኚው እስቲ ንገሪኝ ምን ነበር ያጎደልኩብሽ
ምንድን ነው ከኔ ያጣሽው ሌላ እንድትመኚ ያረገሽ
ምንድን ነው ... ቃላቶች አጠሩት ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ
ጀመር ...

ሳራም እንባዋ እየጎረፈ ላንተ ስል ነው አንተን


ላለማጣት እናትህና እህትህ እንድትጠላኝ ይፈልጋሉ
ሁሉም ነገር የነሱ ሴራ ነው እንጂ እኔ ካንተ ውጪ ...
አለችና ወይኔ የኔ ነገር ለካ እንዳልነግርክ
አስጠንቅቀውኛል ብላ እፏን ያዘች ልኡል ግራ ገባው
ሰክራ ነው አብዳ ወይስ እውነታውን ነው እየሰማው
ያለሁት?? እራሱን ጠየቀ ሳራም ሉሌ እባክህ ሳመኝ
ፍቅር ስጠኝ ስሞትልክ ለዛሬ ብቻ እንደፍቅረኛህ እየኝ
ከዛ ከነገ ጀምሮ እናትህ እንደሚፈልጉት እንለያያለን ...
እያለች ተዘጋችው ልኡል ያለችውን አደረገ ይሄኔ
የፍቅር የበላይነት ነገሰ በዛች ለሊት ሳራ እራሷን አሳልፋ
ሰጠችው ለመጀመርያ ግዜ አንሶላ ተጋፈፉ ድንግልናዋን
ለምታፈቅረው ሰው አስረከበች...
ጠዋት ስትነቃ ልኡል ከጎኗ ክንዱን አንተርሷት
ተኝታለች ማመን አቃታት ማታ የተፈጠረውን
በጠቅላላ እረስታዋለች ከተኛችበት ተነስታ ልትወርድ
ስትል ፍቅር ቆይ ተረጋጊ አለና ቀድሟት ወርዶ
ነጠላጫማ ሰጣት ግራ እንደተጋባች ገብቶታል ከዛም
ሻውር ገብተው አንድ ላይ ታጠቡና ደም የነካውን
አንሶላ አንስተው አልጋው ላይ ተቀመጡ ፍቅር ማታ
ያልሽውን አሁን በደምብ አስረጂኝ አላት ደነገጠች
ሰክራ መቀባጠሯ አሳፈራት የኔ ውድ እኔ በጣም
አፈቅርሻለው የኔ በሽታ ካንቺ መለየት ነው የኔ ደስታ
ካንቺ ጋር መኖር ነው ስለዚህ እባክሽ ... ሲል አቋርጣው
በቃ ሁሉም ነገር የሆነው ላንተ ሲባል ነው እናትህ
ስለምቶድህ የመሰላትን አርጋለች በኔ ምክንያት
ደግሞ... ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ በቃሽ አሁን ከዚ
ወተን ቤት እንከራያለን ከዛም እየሰራው አኖርሻለው
እመኚኝ ትምህርትሽንም አስተምርሻለው
እንደምትመኚው ምርጥ ጠበቃም ትሆኛለሽ አለ ይህን
ሲል እንባዋን መቆጣጠር ተሳናት...
ሁለቱም በየራሳቸው ሀሳብ ተውጠው ክፍሉ ላይ
ዝምታ ሰፈነ ሳራ ምን አይነት እድለኛ እንደሆነች
ስታስብ የደስታ ሲቃ ተናነቃት ውዴ ይሄ አይሆንም
አሁን እናትህ የምትልህን ስማና እቤትህ ተመለስ
ትምህርትህን ተማር አባትህ ጋርም ሂዱ እኔ ምንም
አልሆንም ከዛ ወደፊት... ስትል አላስጨረሳትም እቅፍ
አርጎ እየሳማት ትላንት ከቤት ወተሽ ስትሄጂ ስከተልሽ
ነበር አንቺን አጥቼ መኖር አልችልም እውነቴን ነው
የምልሽ እሞትብሻለው ሲል ዝም አስባለችውና በሀሳቡ
ተስማማች...

ሳራና ልኡል ከሰፈራቸው በጣም እርቀው ቤት


ተከራዩ መጀመርያ አካባቢ ሁለቱም ፈርተው ነበር ግን
ደግሞ አንዳቸው የአንዳቸው እስትንፋስ ሰለሆኑ
ቤታቸውን በፍቅር ምሰሶ አቆሙት ልኡል አባቱ
አካውንት ከፍቶ በስሙ ብር ስለሚልክለት ምንም
አልተቸገሩም ነበር እንዲህ እያለ ቀኑ በሳምንት ሳምንቱ
በወር ተቀይሮ ሁለት ወር ሆናቸው ይሄኔ ሳራ የወር
አበባዋ ሲዘገይባት ግራ በመጋባት ተመረመረች የ 2 ወር
ፅንስ መሸከሟንም ነገሯት ልኡል ይህን ሲሰማ ሁለት
ስሜት ተሰማው አንዱ ደስታ ሲሆን አንዱ ደግሞ
ትምህርቷ ላይ ተፅኖ እንዳይፈጥርባት የሚል ፍራቻ
ነበር...

ኑሮ በደስታ ቀጠለ ሳራም የህግ ትምህርቷን ማጥናት


ቀጠለች ፅንሱ ስድስት ወር ሞላው... አንድ ቀን ምሽት
ላይ ሳራ ከልኡል ጋር የተገናኙበትን 4 ኛ አመት
ምክንያት በማድረግ ስጦታ ገዝታና ቤቱን አበባ
አስመስላ ሰርፕራይዝ ልታደርገው መብራት አጥፍታ
ሻማ አብርታ ትጠብቀው ጀመር ልኡል ከወትሮው
በተለየ አመሸ ሳራም እዛው በተቀመጠችበት እንቅልፍ
ያዛት ... ከሰአታት ቡሃላ ሳራ ስትነቃ ቤቱ በጭስ
ታፍኗል ሻማው ከጠረጴዛው ጨርቅ ጋር ተያይዞ ኖሮ
ቤቱስጥ እሷት ተፈጥሯል ሳራ እርዱኝ እያለች መጮህ
ጀመረች እኩለ ለሊት ነው...

ይቀጥላል....
❤️ፍቅር_ሲፈርድ

❤️ክፍል_______5

እውነተኛ____አሳዛኝ_____እንዲሁም____አስተማሪ

ሳራ የታፈነ ጩኸቷን የሚሰማ አንድም ሰው


አልነበረም እንደምንም ብላ በሩን ከፍታ ወጣችና ማሳል
ጀመረች ይሄኔ ሰው ደርሶ እሳቱን አጠፉት ለሳራም ውሃ
ሰተው አረጋጓት ሳራ ግን ከምንም በላይ ያሳስባት
የነበረው የባልዋ ወቶ መቅረት ነበር ... ጎረቤት አደረች
አይኗ እንደፈጠጠም ነጋ ይሄኔም በለሊት ተነስታ
ልኡልን ማፈላለግ ጀመረች ያለምክንያት አያድርም
እናቱ አግኝታው ቢሆን እንኳ ጥሎኝ አያድርም ስትል
ጭንቀቷን አባባሰችው አንድ ነገር እንዳይሆን አምላኳን
እየለመነች ፈለገችው ... አየሁት የሚል ስታጣ
የመጨረሻ አማራጯ የሆነው እናቱን መጠየቅ ነበር
ቤታቸው ሄዳ በር ስታንኳኳ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ነበር
...

የልኡል ቤተሰቦች ቤት ተከፈተ የከፈተችው እህቱ


ነበረች እንዴት ነሽ ልእልና አለች ሳራ በሰለለ ድምፀት
ልእልናም ምን ፈልገሽ መጣሽ አንቺ ዘረቢስ ድሃ
ቤተሰቦችሽን ገፍተሽ ጨረሽ አሁን ደግሞ የኛን
ቤተሰብ... እያለች ስትዘረዝር እባክሽ ስለማታውቂው
ነገር አዘባርቂ ለነገሩ ብዘባርቂም ግድ አይሰጠኝም አሁን
ልኡል እዚ መኖርና አለመኖሩን ለማወቅ ነው የመጣሁት
አለቻት ይሄኔ የልኡል እህት ፊቷ እየተቀያየረ ምን
ወንድሜን ምናባሽ አረግሽው ልጁን ምናምን
አስነክተሽ ልቡን ካጠፋሽው ቡሃላ የት አደረሽው ብላ
ጉሮሮዋን አነቀቻት በዚ ሰአት ነበር እናትየው ሰምታ
የወጣችው...
ልኡል ቢፈለግ ቢፈለግ የውሃ ሽታ ሆነ
ቤተሰቦቹም ሳራ ላይ ዛቻቸውን ቀጠሉ ... የሳራ ሆድ
ገፋ በዚን ግዜ እንዳይገሏት በመፍራት ሀዘኗንና ችግሯን
ዋጥ አጋ ወደተወለደችባት ክልል ሀረር ተሰደደች ሆኖም
እርጉዝ ሴት ብቻዋን ያለምንም ገንዘብ ህይወት ምን
ያህል ከባድ እንደሆነ ለማወቅ መገመት ቀላል ነው ሳራ
እራሷን ማጥፋት ተመኘች ግን ልኡል ምን ሆኖ ነው
ቆይ ግን ፈጣሪ ምን ብበድለው ነው?? የሳራ መልስ
የሌላቸው ጥያቄዎች ናቸው...

ሀረር ስትሄድ ሁሉንም እቃዋን ሸጣ ነበር እና እዛ


ደግሞ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮችን ገዝታ የተረፈውን
የ 3 ወር ኪራይ ከፈለችው ቤቷ ውስጥ የሚላስ
የሚቀመስ ሳይኖር ኑሮን ሀ አለች በርግጥ ሀረር ከሸገር
የምትሻልበት ትልቅ ነገር አለ ማህበረሰቦቿ አንድን
የተቸገረ ሰው እንደራሳቸው ነው የሚያዩት ባጠቃለይ
ቤቴ አይባልም ቤታችን እንጂ ለዛም ሳራ አንዱ ቤት
ቁርሷን ከበላች አንዱ ቤት ምሳ አንዱ ጋር እራት ብቻ
ሁሉም የየራሱን ድርሻ ይወጣል ሀረር እየኖሩ ጭንቀት
አይታሰብም ሁሉም ያፅናኗታል ልጇን በሰላም
እስከምትገላገል ይንከባከቧታል...

የልጃቸውን ልጅ በማህፀኗ የልጃቸውን ፍቅር በልቧ


የያዘችላቸው የልኡል ቤተሰቦች ሳራን መግደል ይመኛሉ
ለዛም ያፈላልጓታል ሆኖም ግን አድራሻዋን አጡት ሳራ
ከልኡል ጋር በተከራዩበት ግቢ ውስጥ ይኖር የነበረ አንድ
ብዙነህ የሚባል ሰው ነበር ከሱ ውጪ ሳራ ሀረር
እንዳለች ማንም አያውቅም እሱም አልፎ አልፎ
ስትደውልለት ነው ስለልኡል ቤተሰቦች የሚነግራት ....

ልኡል ሳይገኝ ሳራ ወለደች ታድያ ስትወልድ


ጎረቤቶቿ ቢያርሷትም በዘነጓት ግዜ ግን የምትበላው
ስታጣ ሙቅ ውሃ አፍልታ በስኳር በጥብጣ ጡት ቢሆነኝ
እያለች ትጠጣለች ... በሯን ዘግታ የልጇን አይን እያየች
የልኡሌ ቀሪ ብቸኛ ስጦታዬ እያለች ታነባለች ... ሳራ
ወገቧ እንኳ ሳይጠና የምትበላውና የቤት ኪራይ ስታጣ
ተመላላሽ ለመስራት ወሰነች ይሄኔ ያከራዩዋት ሴትዮ
ልጇን ይዘውላት ልብስ አጠባ ሄደች... ይህች ችግር
የተዛመዳት ሴት ታድያ ልብስ ስታጥብ ውላ ወደቤቷ
ስትሄድ ብዙነህ ጋር ለመደወል ወደሱቅ ጠጋ አለች ገና
ስልኩ ከመጥራቱ አንስቶ ሳሪቲ ምነው ድምፅሽ ጠፋ
ስልክ የለሽ እኔ እንኳ እንዳልደውል ሳሪዬ ልኡልን እኮ
አገኘሁት ሲል ልኡል አለች በድንጋጤ አዎ ይገርምሻል
ታስሮኮ ነው .... ንግግሩን ሳይጨርስ ሰማይ ምድሩ
ዞሮባት እራሷን ስታ ወደቀች ...✍
❤️❤️ፍቅር ሲፈርድ❤️❤️

👉ክፍል________6...

እውነተኛና___አስተማሪ___እንዲሁም___አሳዛኝ

ሳራን የሰፈሩ ሰዎች ተሰብስበው ውሃ


ሲያረጉላት ቆይታ ነቃች ስትነቃ ሰው ከቧታል ደንግጣ
ከተንጋለለችበት ብድግ ብላ ልጄ ብላ እየሮጠች ወደ ልጇ
አመራች ልክ ስትደርስ ልጇ ከአከራይዋ ሴትዮ ጋር
ፍንክንክ ትላለች ልጇን ስታይ ደስስ አላት ሌላ አለም
ደርሳ የመጣች ያህል ናፍቃት ነበር ... ሳራ ትንሽ
ከተረጋጋች ቡሃላ ስለልኡል የሰማችው ትዝ አላት
አከራይዋንም እማማ እባክዎትን በስልክዎ ልደውል
አለች ከመጀመርያ ጀምሮ ላያት እቺ ልጅ አበደች እንዴ
ያስብላል ግን ግራ ተጋብታ ነው ...

በድጋሚ ብዙነህ ጋር ደወለች ብዙነህም አነጋገሩ


ተጨንቆ እንደነበር ያስታውቃል ገና ሄሎ ከማለቷ
ስልክሽን ስጠብቅ ነበር ሳራ ተረጋጊ እንጂ ቅድም
በደወልሽበት ስልክ ስደውል የተፈጠረውን ነገሩኝ እኔኮ
ልኡል ታስሮ ስለነበር ነው የጠፋው ነው ያልኩሽ አሁን
ሊያገኝሽ ጓጉቷል ባንቺ ተጎድቷል ታስፈልጊዋለሽ...
ንግግሩን እስኪቋች መታገስ አቃታት እሺ ዛሬ ለሊት
አዲስ አበባ እደርሳለው አለች እንባዋ አላሶራ እያላት ...
አይ አይ እኛ ነገ እንመጣለን እዚ መታየት እንደሌለባቹ
እያወቅሽ አለ ብዙነህን ፈጣሪ የላከላት ያህል ተሰማት
በጣም ጥሩ ሰው ነው...
ለሊቱ ሳምት የሆነባት ሳራ ስትቁነጠነጥ አድራ
መንጋት አይቀርምና ነጋ ይሄኔ ከጎረቤት ስኒና ጀበና
ተበድራ ቡና አፍልታ ምግብ ሰርታ ስልክ ትጠባበቅ
ጀመር...በመጨረሻም ተደወለ እየተጣደፈች
ልትቀበላቸው ወጣች ገና ሳታገኘው ያለማመን ይሁን
የደስታ እንባዋን ታጎርፈዋለች ... ከደቂቃዎች ቡሃላ
አቶቢስ ተራውጋር ደርሳ በዓይኗ መፈለግ ጀመረች...

ልክ ሲገናኙ ልኡል ከስቷል ፀጉሩን ተላጭቷል እሮጣ


ተጠመጠመችበት እረጅም ሰአት ተቃቅፈው ተላቀሱ
አንዲት ሴት አብራው እንዳለች ልብ ያለችው ከረጅም
ደቂቃ ቡሃላ ነው ግን ማንነቷም ምንነቷም
አላሳሰባትም እሷንም ብዙነህንም ሰላም ብላ ወደቤት
ሄዱ ልኡል እናቱን እንዳገኘ ህፃን እንባው አላቆም አለ
ሳራ ከስታለች ኑሮ ፊቷን እንዳዞረችባት ታስታውቃለች
... እቤት ገብተው ልጁን ሲያይ ደግሞ ይባስ ከፋውም
ደስም አለው የሱ ምኞት ይህ አልነበረም አንድ ቀን
እንኳ አማረኝ ብላው ከጎኗ ሆኖ ሳያደርግላትና ችግሯን
ሳይካፈላት ዛሬ ላይ መድረሱ ቅስሙን ሰበረው ...
ሁሉም ሰው በየራሱ ሀሳብ ተጠምዶ ከቆዩ ቡሃላ ሉሌ
አለች ሳራ ዝምታውን ለመስበር ወዬ አለ ልኡል ከሀሳቡ
እንደመባነን እያለ በስስት እያየችው አብራክ
የመጣችው ሴት ማናት ለምንስ ነበር የታሰርከው አለች

እሷ ራሄል ትባላለች ያንቀን በሷ ምክንያት ነበር


የታሰርኩት ማለቴ እሷን መንገድ ላይ አስገድደው
ሊደፍሯት ሲሉ አጋጣሚ ወዳንቺ እየመጣው መንገድ
ላይ አገኘዋት አሳዘነችኝ ፍቅር ታስታውሻለሽ ያኔ የኔና
ያንቺን ሶስተኛ አመት ምክንያት አርጌ ቀለበት
ላረግልሽ ጓጉቼ ነበር ደስተኛ እንደማረግሽ
አልተጠራጠርኩም ነበር ... ብቻ እሷን ለማስጣል
ከጎረምሶቹ ጋር ስጣላ ከየት መጣ ያልተባለ መኪና
አንደኛው ልጅ ላይ ወጣበት ግን አመለጠ ይሄኔ
በአካባቢው ስንጣላ ያዩ ሰዎች ጠቁመውብኝ ተያዝኩ
አሁንም እሷ ነች ብዙ ለፍታ ያስፈታችኝ ... አለ ይሄኔ
ብዙነህ መደወል ነበረብህ እሷ አንተን ስትጠብቅ በቁሟ
ልትቃጠል ነበር.... ሁሉም ስላለፈው ብዙ ካወሩ ቡሃላ
ራሄል እኔ በናንተ ፍቅር ቀናው እውነቴን ነው
ሁለታቹም መንፈሳቹ ተሳስሯል ...አለች...

ፍቅር እንደገና የበላይነቱን አሳየ ብዙነህ ወደ ቤቱ


ሲመለስ ራሄል እዛው ከነ ልኡል ጋር ሰነበተች ልኡል
ሳራን ያቅሙን ያህል ይክሳት ጀመር በለጋ እድሜዋ
ያብራኩን ክፋይ በሆዷ ተሸክማ የገፏትን እናትና
እህቱን ከልቡ አወጣቸው ... ከቀናት ቡሃላ ግን ራሄል
የምታሳየው አክት ለሳራ አልጥምሽ አላት ይባስ ብላ
አንድ ቀን ሳራ ልጇን አስከትባ ስትመለስ እርቃን
ገላቸውን ሆነው ልኡል ላይ ተኝታበታለች ሳራ የሰው
ቤት የገባች መሰላት እይኗን ማመን አልቻለችም ...✍

ክፍል____7

❤️እውነተኛ____አሳዛኝና_____አስተማሪ .....
ሳራ ልጇን እንዳቀፈች አዞራት የአመታት ፍቅሯ
አልፎም የልጇ አባት አጋጣሚ አስተዋወቀን ካላት ሴት
ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ከማየት በላይ ምን ሞት አለ???
እራሷን ለማረጋጋት እንደምንም ተቀመጠች ይሄኔ
የክትባቱ መርፌ ምቾት የነሳው ህፃን ቤቱን በለቅሶ
አወከው በዚን ግዜ ራሄል ድንግጥ ብላ ተነሳችና
እንደመሸማቀቅ አለችና ልብሷን ቶሎ ለበሰች
ልኡልንም በፍጥነት አልጋ ልብሱን አለበሰችው ሳራም
ከድርጊቷ ማስመሰሏ አበሳጫትና ቀስቅሽው አለቻት
ጮክ ብላ ልኡልም የህፃኑ ጩኸት ከሳራ ጩኸት
ተደምሮ አባነነው አይኑን እያሸም ወደሳራ ዞሮ ... የኔ
ውድ ሳላካሂድሽ አስከትቤ መጣሁ ብቻ እንዳትይኝ አለ
ሳራም ብሶቷ እየተባባሰና እንባዋ ቃል አላሶጣ እያላት
ተመለከተችው...

ደንግጦ ከተኛበት እየተነሳ ምን ሁነሻል ማር


እያለቀሽኮ ነው ቤቢ ደና አይደለም እስቲ ንገሪኝ
ምንድን ነው የተፈጠረው አለ ግራ ተጋብቶ ይሄኔ ሳራ
ንዴቷ ጣርያ ነካ በቃህ ቢያንስ ደንግጥ በል እስቲ ልኡል
ባንተ ምክንያት ህልሜም እውኔም መከነ ችግር
ተዛመደኝ ባንተ ምክንያት ሀገር ለቀኩ አንተ ማለት
ስትፈልግ ህይወቴ ውስጥ ትገባና ስትፈልግ ወተህ
እንዳሻህ ትፈነጫለክ አሁን ግን በቃህ መተወን አቁም
እውነት እልሃለው ልጄን ማሳደግ አይከብደኝም ...
ይበልጥ ግራ ገባው ፍቅር ምን ሆነሻል ምንም
የምትይው አልገባኝም ተረጋጊና እስቲ አውሪኝ አለ
ሳራም ህፃኑን አልጋው ላይ ወርውራ ልኡልን በጥፊ
አለችውና በቃህ ምስኪን ከምትላት ሴት ጋር የገዛ
አልጋዬ ላይ ብላ ተናግራ ሳጨርስ ራሄል አንዴ ልኡልን
አንዴ እራሄልን እያየች ኧረ እንደምታስቢው አይደለም
እውነቴን ነው ስትል አንቺ ውጪልኝ ብላ ጉሮሮዋን
አነቀቻት...

ልኡልም እንደምንም አስለቅቋት ሳራ ምን ሆነሻል


እባክሽ ፍቅር ተረጋጊ እስቲ ምንም አልገባኝምኮ የኔ
እናት ሲጀመር እሷን ብፈልግ እዚ ምን አስመጣኝ
እሷኮ ንፁ እህቴ ናት አለ ሳራም ለዛ ነዋ እኔ ስወጣ
ጠብቃቹ እርቃናቹን ተጣብቃቹ ያገኘኋቹ አለች
ልኡልም በሚስቱ አስተሳሰብ ተበሳጭቶ እኔ መቼ ነው
ልብስ ለብሼ ተኝቼ የማውቀው ሙቀት እንደማሎድ
ታውቂያለሽ እሷ አጠገቤ መተኛቷንም አላየው ቆይ
እንዴት ጠረጠርሽኝ አለና ወለሉ ላይ እራሱን ይዞ ቁጭ
አለ ልኡል ባልፈፀመው ወንጀል መከሰሱ አናዶታል ሳራ
እናቱ ያለቻትን አስታወሰች ልኡል መናደድ የለበትም
ስለዚም ቶሎ ብላ ባይዋጥላትም ራሄል የጠነሰሰችው
ሴራ እንዳለ ቢገባትም ልኡልን ማረጋጋትና እሺ በቃ
ይቅርታ ስለምወድህኮ ነው ማለት ጀመረች...

ከተረጋጉ ቡሃላ ራሄል ወጣ ብዬ ልምጣ ብላ


ወጣች ይሄኔ ሳራ የኔ ውድ ራሄል ልታጣላን ትፈልጋለች
እኔ ስገባኮ እላይክ ላይ ተለጥፋ ነው ያገኘዋት አለች
ሰከን ባለ ድምፀት ልኡልም ሳሪቲ ማንም እንደሌላት
ነግሬሻለው እንዴት ሰው ምንም ሳይኖረው ውጡ ከቤቴ
ይባላል ሲቀጥል ደግሞ እሷ ብትፈልግ እንኳ እኔ እንዴት
እንደዛ አደርጋለው ለምን ትጠራጠሪኛለሽ ሲል ሳራን
ለማግባባት ሞከረ ሳራም ይሁን ብላ ተቀበለችና ኑሮ
ቀጠለ...
ልኡል ለልጃቸው ሞግዚት ቀጠረ ከመጀመሪያው
የተሻለ ቤትም ተከራዩ አባቱንም በስልክ ከሳራ ጋር
አስተዋወቃቸው ሳራም የህግ ትምህርት መማር
ጀመረች ራሄልም ትንሽ ቀን ልቀመጥና አዲስ አበባ
እሄዳለው ስትል ሳራን ሸነገለቻት ከሀረር ጎረቤቶቿ ጋር
ደስተኛ ህይወት መኖር ጀመረች ልኡልም ሚስቱንና
ልጁን በፍቅር መንከባከቡን ቀጠለ ወራት ተቆጠሩ...
የልጃቸውን ልደት ለማክበርና በዛውም ቀለበት
ለማድረግ ዝግጅት ጀመሩ....

አንድ ቀን ታድያ ሳራ ከትምህርት ቤት ተመልሳ


ልጇን ጡት ስታጠባ የልጇ ሞግዚት አንድ የተጣጠፈ
ወረቀት ሰጠቻት ልጇ እስኪተኛ ተቀብላት
አስቀመጠችውና ልጇን አስተኝታ ማንበብ ጀመረች
"ይቅርታ ሳራ ይህን ባንቺ ላይ ማድረግ ክፉ ሀጥያት ነው
ግን ከልቤ ይቅርታ እጠይቅሻለው ልኡልም ይሄን ፈልጎ
ሳይሆን እኔ ገፋፍቼው ነው ...ማለቴ በቃ እርጉዝ ነኝ
ከባልሽ የ 3 ወር እርጉዝ ነኝ በዚም ስራዬ አፍሬ ነው
ከቤታቹ የወጣሁት" ይላል

ሳራ በህልሟ መሰላት ወረቀቱን ስትገለብጠው


የራሄልን እርግዝና ማረጋገጫ ወረቀት መሆኑን
አስተዋለች ይሄኔ እየተጣደፈች መሳብያውን ከፍታ
ብዙ መዳኒቶችን አወጣችና ከንግዲ አላለቅስም
አለችው ለራሷ ከዛም ኪኒኖቹን በአንድ ብርጭቆ ውሃ
በጥብጣ ጨለጠችው ከዛ ቡሃላ እራሷን አታውቅም
ተዝለፍልፋ ወደቀች በአፏ አረፋ ትደፍቅ ጀመር ... በዚ
ቅፅበት ልኡል በር ከፍቶ ገባ ሳራ ወድቃለች አይኖቹን
ማመን አቃተው ከፍተኛ እራስ ምታት ለቀቀበት...✍
❤️❤️ፍቅርሲፈርድ❤️❤️

❤️ክፍል______8

እውነተኛ__አሳዛኝና__አስተማሪ__ታሪክ...✍
ልኡል ሳራን ሲያይ እራስምታቱ አይሎ ተዝለፍልፎ
ወደቀ ይሄኔ የህፃኑ ሞግዚት ልብስ አስጥታ
እየተመለሰች ኖሮ ስትገባ ባል ለብቻ ሚስት ለብቻ
ተዘርረዋል ደንግጣ እየሮጠች በመውጣት እሪታዋን
አቀለጠችው ሁሉም ሰው ተሰበሰበ በእውን ላያቸው
እንባ ያስፈስሳሉ ባፋጣኝ አምቡላንስ ተጠራና
ሁለቱንም አፋፍሰው ወደ ሀኪም ቤት ወሰዷቸው
ድንገተኛ ክፍል ገብተው ሁለቱም ህክምናቸውን ጀመሩ
ሳራ በመድሃኒተ የተመረዘውን ጨጓራዋን በፍጥነት
አጠቧት ከሁለት ቀን ቡሃላ ነብስ ዘራች ... በሳምንቷ
በደምብ ድና ከሆስፒታል ወጣች...

ልኡል ግን በቀላሉ የሚሻለው ነገር አልነበረም ወደ


አዲስ አበባ ተልኮ እንዲታከም ተወሰነ ሳራም ልኡል
ምንምኳ ቢያሳዝናት ልታስታምመው ቀርቶ ልታየው
ፍቃደኛ አልሆነችም ልኡልን በትዝታዋ ሰንቃ ልጇን ይዛ
ወደ ባህር ዳር ተሰደደች እዛ እንደደረሰችም ማረፍያ
ሆቴል ተከራየች በሁለተኛው ቀን ባጋጣሚ ግን የድሮ
ጓደኛዋ የነበረችውን ቤቲን አገኘቻት ያለቀጠሮ
መገናኘት ማለት ይሄ ነው ኤልሳ የባህርዳር ዩንቨርስቲ
የመጨረሻ አመት ተማሪ ናት ያኔም አጋጣሚ ቅዳሜ
ስለነበር ነው ከግቢ የወጡት ወደ አንድ ካፌ በመሄድ
ተቀመጡ ቤቲ ሳራን ወልዳና ተጎሳቁላ ስታያት
አለቀሰች ያኔ ልጅ እያሉም በሷ ቀንታ ከልኡል ጋር
ልታለያይ የነበረው ቆጫት ... ሳራም በውስጧ
ያፈነችውን ሁሉ ብሶት ነገረቻት ቤቲ ይበልጥ ለሳራ
አለቀሰች...

አገኝሻለው ብዬ አላሰብኩም ነበር ስለገጠመሽ


ችግርና ስለሁሉም ነገር በጣም አዝኛለው ግን ሳሪቲ
ልኡልን ትተሽው መምጣት አልነበረብሽም አለቻት
እንባዋን በሶፍት ለማድረቅ እየጣረች... እኔ አመት
ያልሞላው ልጅ ለማን እጥለዋለው ብዬ እንጂ የመኖር
ተስፋዬ ከመነመነ ቆየ ምድር ላይ ያለኝ ብቸኛ ሀብትና
ተስፋ ልኡል ነበር እሱም ከዳኝ ይባስ ብሎ ከሌላ ልጅ...
አለች ቁጭትና ተስፋ ማጣት እየታየባት... ሳራ ካንቺ
ባላቅም ልኡል ከልቡ ያፈቅርሻል እመኚኝ በፍቅር
የሚቀናው ጠላት ሰይጣን ነው መሀላቹ የገባው እባክሽ
አንድ ነገር ቢሆን እድሜ ዘመንሽን ትፀፀቻለሽ ስትል
ተማፀነቻት...

ሳራ ግን ከራሄል ጋር እርቃን ገላቸውን ያገኘቻቸውን


አጋጣሚና የእርግዝና ማረጋገጫ ወረቀት እያሰበች
አሻፈረኝ አለች ይባስ ብላም እሱን ለመርሳት መጣር
ጀመረች ቤቲም ቤት አፈላልጋ ተከራየችላት ትምህርት
ሳይኖራትም እየመጣች ታስተዳድራታለች ያለቻት
ገንዘብ እስክታልቅ ድረስ ሀረርን መልቀቋ ምንም
አልመሰላትም ነበር ከዛ ግን ኑሮ መክበድ ጀመረ ስራ
ፍለጋ ደላላ ለደላላ ተንከራተተች ግን ልጇን እያዩ ምን
ልሰሪልን እያሉ ያባሯታል...በዚም ስራ ማግኘት
አልቻለችም ህይወት ከበዳት ... ይህን የተመለከተችው
ቤቲ ትምህርቷን አስፈቅዳ ልኡልን ለማግኘት ሃረር
ሄደች ሀረር ደርሳ ስታጠያይቅ አዲስ አበባ ጥቁር
አምበሳ ሆስፒታል መተኛቱን ሰማች ግዜ ሳታጠፋም
ወደ ትቁር አምበሳ ሆስፒታል አመራች...
ስትደርስ የተኛበትን ያልጋ ክፍል ነገሯትና ቀጥታ
ገባች ሁለት ሴቶች በክፍሉ ውስጥ ነበሩ ልኡል ግሉኮስ
ተሰክቶለት ተኝቷል እራሱን ከሳተበት አልነቃም
ስታየው እምባዋ ቁልቁል ወረደ ይሄኔ አንዷ ሴት የኔ ልጅ
አታልቅሽ ሉሌ ምንሽ ነው? ስትል ጠየቀቻት ቤቲም
ጓደኛው ነኝ ስትል መለሰች ይሄኔ እኔ እናቱ ነኝ ልጄ
እንዲህ እንዲሆን ያረገችውን ሴት ታውቂያታለሽ?
አለችና መልስ ሳትጠብቅ ባታውቂያት ነው የሚሻለው
እቺ እርጉም ምንም የማያውቅ ልጄን ምናምን
አስነክታ ልትነጥቀኝ ሴትየዋ ማልቀስ ጀመረች ቤቲም
እና አሁን አልተሻለውም ስትል ጠየቀቻት የልኡል
እናትም እንባዋን በቀሚሷ ጫፍ እየጠረገች ነገ ወደ
አሜሪካ በረራ አለው ታክሞ እዛው ከአባቱ ጋር ይኖራል
ከዛች መተተኛም ይገላገላል ስትል ቤቲ ልቧ ስንጥቅ
አለ... በችግር እየማቀቀች ያለችው ሳራን በህሊናዋ
እየሳለች ከልቧ አለቀሰች... አለምንቃቱ ደግሞ ይባስ
አወሳሰበው ...✍
❤️❤️ፍቅርሲፈርድ❤️❤️

❤️ክፍል_____9

እውነተኛ____ላይ___የተመሰረተ____አሳዛኝ___ታሪ

ልኡል ለህክምና ወደአሜሪካ ሲሄድ ቤቲም


ሸኝታው ተመልሳ ባህርዳር ሄደች ለሳራም የሆነውን
እያለቀሰች ነገረቻት ሳራም ልኡልን እስከመጨረሻው
እንደማታየው ስታረጋግጥ ሰማይ የተደፋባት መሰላት
ቤቲን አልቅሳ ስራ እንድታስገባት ለመነቻት ቤቲም
በሀዘን ለተጎሳቆለች ሴት ስራ መፈለግ ቀላሉ እርዳታ
ነበርና በባህር ዳር ማርያም ቤተክርስትያን
ለሚያገለግሉ አባት ነገረቻቸው ቄሱም በነጋታው
ለቤቱ ደውለው የነብስ ልጃቸው የሆኑ አንዲት እናት
ልጆቻቸው ሁሉ ውጪ ስለሚኖሩና ባላቸው ከሞተ
ስለቆየ ከብቸኝነት የምትገላግላቸውን ሳራን በደስታ
አብራቸው እንድትኖር መፍቀዳቸውን ነገሯት ...

ሳራም ከሴትየዋ ጋር መኖር ጀመረች ሳራ በዚ


እድሜዋ ስቃይን ማሳለፏና ለፍቅር ስትል እራሷን
መስዋዕት ማቅረቧ እማማን ከልባቸው እንዲወዷት
አደረገ ቤቲም ትምህርቷን መማር ቀጠለች ሳራ
እማማን እንደናት ነው የምታያቸው እሳቸውም ሳራን
ከነልጇ እንደልጅ ፍቅር ይሰጧታል ቀናት ለሳምንታት
ሳምንታት ደሞ ለወራት ተራቸውን አስረከቡ ሳራ ልጇ
ድክ ድክ ማለት ጀምሮላታል እማማም የሳራን ልጅ
በአምላክ አሉት በአምላክ ልኡልን እንደሚመስል ያየው
ሰው ሁሉ ይናገራል ለዚህም ነው ሳራ ልጇን ባየች ቁጥር
በትዝታ ልኡል ጋር የምትነጉደው... እማማ ሳራን የህግ
ትምህርት እንድትማር ግፊት አረጉባት ሳራም ህግ
ሳልማር ፍርድ መስጠት እፈልጋለው ቅድሚያ እንጀራ
እናቴን እገላታለው ስትል እማማ ተቆጥተው ክርስቶስ
የሞተው ለሀጥያተኞች መሆኑን አትርሺ የበደሉንን
ይቅር ማለት የጠሉንን መውደድ ትልቅነት ነው ነገ
አላማሽን አሳክተሽ ማየት በራሱ ለጠላቶችሽ ሞት
ነው ብለው መከሯት ሳራ እናት በማግኘቷ ለፈጠራት
ምስጋና አቀረበች...

ህይወት ቀጠለ ሳራም እየቆየች ልኡልን ትረሳዋለች


ሲባል ጭርሱን ከሱ ውጪ ማሰብ ተሳናት ይሄኔ ቤቲ
ለእረፍት ስትመጣ ጠብቃ አዲስ አበባ ሄደው የልኡልን
ሁኔታ ከቤተሰቦቹ መስማት እንደምትፈልግ ነገረቻት
ቤቲም ተስማምታ ሄዱ ከዛም አዲስ አበባ እንደደረሱ
ሳራ አንድ ሃሳብ መጣላት እራሷን ቀይራ እነልኡል ቤት
ገብታ እናትየው ለቤቲ ስለልኡል ሲያወሩ መስማት
ፈለገች ከዛም ከቤቲ ጋር ተመካክረው ሳራ አይኗ ሲቀር
ሙሉ አካሏን ሸፍና የእስልምና እምነት ሀከታዮች
የሚለብሱትን ጀለብያ ለበሰች ስሟም ልክ ደርሰው
ሲያንኳኩ የልኡል እህት በር ከፈተችና ለቤቲ ሞቅ ያለ
ሰላምታ ሰጠቻት ሳራንም ጨብጣት ግቡ አለቻቸው
ልክ ገብተው ወደ ሳሎን ለመዝለቅ ጫማቸውን
እያወለቁ እያለ ...
እኔማኮ እንደ ሰይጣን ለመለያየት ያልፈጠርኩት ነገር
የለም በመጨረሻ እንዲ ሊሳካ ....ካካካ ቀላል አንቺንም
አንከራተትኩሽ ... የሁለት ሴቶች ቃለምልልስ ነው
አንዷ የልኡል እናት ስትሆን አንዷ ደግሞ ለሳራ ድምጿ
አዲስ አልሆነባትም እየኖርን እያለ ያለውማ እራቁቴን
ደረቱ ላይ ተኝቼ እያለ እሷ ሳትገባ እሱ ነቅቶ ካሁን
አሁን በጥፊ አጮለኝ ስል እሷ ጎተት እያለች አልገባች
መሰለሽ... አለች አሁን ሳራ አረጋገጠች ይሄ ድምፅ
የራሄል ነው ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ ይሄኔ ግቡ እንጂ
አለችና የልኡል እህት ቀድማቸው ገብታ ማሚ ቤቲ ናት
የሉሌ ጓደኛ አለች የልኡል እናትም ተነስታ ሰላም
አለቻት ቤቲም ፈገግ ብላ ሶፊ ትባላለች አለች ወደሳራ
እያየች ሳራ ግን ሶፋው ላይ እግሯን ሰቅላ
የተቀመጠችውን ራሄልን እያየች ፈዛ ቀረች ይሄኔ ቤቲ
ሶፊ ልኡል ብዬ ያጫወትኩሽ ልጅ እናት ናት ሰላም
በያት አለች እየተርበተበተች ሳራም እንደምንም
ቀልቧን ሰብስባ እሺ ብላ እጇን ለልኡል እናት ዘረጋች...
ተቀምጠው ማውራት ቀጠሉ ልኡል እንዴት ሆነ
አለች ቤቲ ፈጣሪ ይመስገን ድኖ ከአባቱ ጋር ሀገር
እየጎበኘ ነው አለች ሳራ እንባዋ ቢመጣም እንደምንም
ብላ ተቆጣጠረችው ደስስ የሚል ዜና ነው የልኡል እናት
አለች ቤቲ እሷ ሳራን ብቶን ምን እንደምቶን እያሰበች
ቀጥላም እና መች ይመለሳል ጠየቀች ኧረ አይመለስም
በነገርሽ ላይ እሷ የልኡሌ ሚስት ናት ነብሰ ጡር ነች
ቀኗ ሲደርስ እዛው ሄዳ ትወልድና አብረው ይኖራሉ
ከዛ...ሳራ ይሄን መቋቋም አልቻለችም ቤቲ እንሂድ ብላ
ተነሳች ቤቲም ደንግጣ እንሂድ እንዴ ለካ ሰው
ይጠብቀናል ብላ ሳራን ተከተለቻት ...

ተያይዘው ሲወጡ ሳራ እንደእብድ እያረጋት ነበር


የልኡል እናት አንድ ነገር ጠርጥረው እስቲ ብቅ ብለሽ
እያቸው ልእልና አለች ልጇን ልእልናም ተከትላ
ስታያቸው ሳራ እመኚኝ ቤቲ እነዚህን አውሬዎች
እጨርሳቸዋለው ብላ ፊቷን የሸፈነችበትን ልብስ
ስታወልቅ ተመለከተቻት ሳራ እንደነበረችም ለእናቷ
እሩጣ ነገረቻት የልኡል እናትም ከት ብላ በመሳቅ
እርሟን አወጣች በይኛ አለች... ሳራ ባህር ዳር
ላትመለስ ወሰነች ቤቲም ምንም ማድረግ ስላልቻለች
ወደባህርዳር ተመለሰች ሳራ ግን በቅርብ እርቀት ሆና
ራሄልን መከታተል ጀመረች ዳግም ህይወቷ ተመሰቃቀለ
መጠጣትና ማጨስ ጀመረች ...

ታድያ አንድ ቀን ሳራ መጠጥ ጠጥታ ሞቅ ብሏት


አስፓልት ዳር ላይ ወክ ታደርጋለች የጨረቃዋ ድምቀት
ከአስፓልቱ ዳር ፓውዛ ጋር ተደምሮ ምሽቱ ቀን
መስሏል ይሄኔ ራሄል ከልኡል እህት ጋር ወደቤት እየሄዱ
አገኘቻቸው ሳራም ልክ ስታያት ሰውነቷን ነዘራት
ንዴትና በቀል አይምሮዋን ሞላው በርምጃ ተከትላት
የውሃ ቦይ ጋር ስትደርስ ያደናቀፋት መስላ ገፍተረቻት
ራሄል ተዘረረች ሆዷ የገፋች ነብሰ ጡር ስለነበረች
ወድያው በደም ተነከረች ጩኸት አካባቢውን አወከው
በአቅራቢያው ያሉ ፖሊሶች ሳራን ያዝዋት...
❤️ይቀጥላል...✍
F
ይርሱ ♥❤️❤️ፍቅርሲፈርድ❤️❤️

ክፍል______10

❤️በእውነተኛ__ላይ___የተመሰረተ___አሳዛኝና___አ
ስተማሪ

ፖሊሶች ይዘዋት አምፑላንስ ተጥርቶ ራሄልን


በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ወሰዷት ሳራም ይቅርታ
ሳላውቅ ነው አለች ለፖሊሶቹ ፖሊሶቹም ተበዳይዋ
ክስ ካልመሰረተችብሽ ትፈቻለሽ ካለበለዝያ ግን
አሳክሚ ብቻ ነው የምትባይው ባጭሩ ግን እሷ ነብሰ
ጡር በመሆንዋ እሷም ሆነች ፅንሱ ምንም እንዳይሆኑ
ፀልይ አላት ፖሊሱ ሳራም እልህ ፊቷን ደም
አስመስሎት ህይወቷ ተመሰቃቅሎ የኔ ስቃይ እንዲገባት
ሳላደርግማ አልታሰርም አለች በልቧ... በድንገት ይሁን
በበቀል ተነሳስታ እንዲሁም ራሄል ላይ የደረሰው አደጋ
አስከፊ ይሁን አይሁን እስኪጣራ ማረምያ ቤት ገባች ...

ራሄል ልጇን ካለቀኑም ቢሆን በሰላም ተገላገለች ...


ሳራ ላይ ግን ክስ መመስረት እንደማትፈልግ ገልፃ ሳራን
እንደፈለጋቹ አድርጓት አለች ራሄል ከቀናት ቡሃላ
ከሆስፒታል ወጣች እነልኡል ቤትም መታረስ ጀመረች
ሳራንም በዋስ ለቀቋት በሰአቱ ዋስ የሆናት ደግሞ
የሁልግዜ ባለውለታዋ ብዙነህ ነበር ... ሳራ ልጇ በጣም
ስለናፈቀቻት ባህርዳር ሄደች ብዙነህም በተፈጠረው
ነገር ሁሉ አዘነ ልኡልን ኢንተርኔት ላይ ፈለገው
በርግጥም ራሄል ከልኡል ከወለደች ልኡል መጥፎ ሰው
ነው ሲል ደመደመ ...

ሳራ ቤት ዘግታ እያለቀሰች ወራት ተቆጠሩ ቤቲም


ምርቃቷ ደረሰ በዚ መሀል ነበር ልኡል ወደ ኢትዮጵያ
መቶ ከራሄል ጋር ሊጋቡ መሆኑ የተሰማው ይሄኔ ሳራ
እራሷን ለማጥፋትም ትፈልግና ልጇን ስታስብ ሃሳቧን
ትቀይራለች ይህች አለም የአጭበርባሪዎች ናት ስትል
ፈጣሪዋን ካደች የፈጠራት አምላክ የሰጣትን ሁሉ
ሲነሳት እንጂ ያሳጣትን ሲሰጣት አይታ አታውቅም
ለዚም ነው አምላክ የለም ብላ የወሰነችው ... ታድያ
እማማ ሳራን ወደራሷ ተመልሳ ጥሩ ህይወት
እንዲኖራት መድከም ጀመሩ ...

የልኡል ሰርግ ሁለት ሳምንት ቀረው ይሄኔ እማማን


ከሀገር መውጣት እንደምትፈልግ ነገረቻቸው እማማም
ለምን ጥለሽኝ አላሉም እንዲያውም እሷ መንፈሷ
የሚታደስ ከሆነ ለልጇ እንድትኖርላት ሲሉ በደስታ
እስራኤል ወዳለው ልጃቸው ሊልኳት ፕሮሰስ ጀመሩ ...
ሁሉም ሰው ግን በልኡል ተገርሟል በተለይ በጣም
እንደሚያፈቅራት የሚያውቁት ሁሉ እንዴት ልኡል
ሳራ ላይ ይማግጣል እንዴት በሴት ይቀይራታል ሲሉ
መነጋገርያ አረጉት ... ቤቲ በተመረቀች በወሯ ሳራ ወደ
እስራኤል ሄደች ልጇን ከእናት በላይ ለሆኑላት እማማ
ትታት ነበር የሄደችው ...
የመጨረሻ ሽኝቷ ቀን እማማ እንዲህ አሉ ሳራ ልጄ
ዛሬ ማህተብሽን አርጊ ምክንያቱም ፈጣሪሽን መካድሽ
ልክ አይደለም እመኚኝ ይህ ቀን አልፎ ልኡል ተሳሳተ
እንዳልሽው ሁሉ ስህተቱ ያንቺ ሆኖ ልታገኚውና
ልትፀፀቺ ትችያለሽ ልጄ እመኚኝ
#ፍቅር___ሲፈርድ___እያዳላም___ፍቅር___ደግሞ_
_የፈጠረን___አምላክ_ነው!! አልዋት ሳራም
የበጠሰችውን ማህተብ መልሳ አረገችው የእማማን
ጉልበት ስማ ልጇን አደራ ብላቸው ሄደች...

ልኡል መቶ ሰርጉ ተደገሰ የሚገርመው ራሄልን ሳራ


እያለ መጣራቱ ሳያንስ ልጃችን እስካሁን ገና ትንጥዬ
ነች ደስስ ሲል ብዙም ጥዬሽ አልቆየሁም አይደል???
ደግሞ እነማሚ እንደዛ ሊለያዩን እንዳልነበር ዛሬ
እንዴት እንድንጋባ ፈቀዱ?? እያለ አከታትሎ ይጠይቃል
ግራ የተጋባችው ራሄል የአእምሮ ሀኪም ስታማክር
ልኡል በደረሰበት በሽታ ከመቶ 80 ፐርሰንት የመርሳት
በሽታ ገጥሞት ነው ማድረግ ያለብሽ ሳራ የሚላትን
ሴት ስለመሰልሽው ሳታስነቂ መስሎ መኖር ነው ሲል
አረዳት ... ይህ በዚህ አላበቃም ራሄል ዱብዳ ገጠማት
ልጇ በጠና ታመመ ይሄኔ ሆስፒታል ሲሄዱ የወላጅ አባቱ
ደም በአፋጣኝ ያስፈልጋል ተባሉ ልኡልም እኔ አባቱ ነኝ
ብሎ ደም ሊለግስ ሲነሳ ራሄል እራሷን ስታ ወደቀች ...

❤️❤️ፍቅርሲፈርድ❤️❤️

❤️ክፍል___11

እውነተኛ____ላይ___የተመሰረተ___አሳዛኝና__አስ
ተማሪ...✍

ራሄልን ዶክተሮቹ አንስተው ውሃ አደረጉላት ከዛም


ከ 30 ደቂቃ ቡሃላ ነቃች ይሄኔ ዶክተሮቹ ራሄል
ያለምክንያት እንዳልወደቀች ስለገባቸው ምን
እንደሆነች ለብቻዋ ጠየቋት እሷም ልኡል የልጇ አባት
እንዳልሆነና የልጇ አባት ሌላ መሆኑን ይሄንም ልኡል
እንደማያውቅ ካወቀ ግን ቤተሰቦቹም ሆኑ እሱ እሷ ላይ
ጉዳት እንደሚያደርሱባት ነገነቻቸው ይሄኔ የልጇን
አባት ማግኘት ከቻለች በሚስጥር እሱ እንደለገሰ
ተደርጎ ልጇ እንደሚድንላት ነገሯት...

ራሄል ብዙነህ ጋር ደወለችለትና ልትነግረው


የምትፈልገው ሚስጥር እንዳለ ነገረችው ብዙነህ
እራሄልን ለመጀመርያ ግዜ ያወቃት ልትደፈር ሙከራ
ሲደረግባት ልኡል አስጥሏት ... ከዛ ሲታሰር እሱን
ለማስፈታት ስትሯሯጥ ብዙነህ አግዟት ነበር ከዛም
አንድ ላይ ሳራን ፍለጋ ሀረር ሄደው ነበር ታድያ በዚ
መሀል ብዙነህ ራሄልን የፍቅር ጥያቄ አቅርቦ
አልተሳካለትም ከዛ ግን ሳራ ላይ ባሴረችው ሴራ ከልቡ
ጠልቷታል ዛሬ እንደምትፈልገው ስትነግረው አመነታ
ሊያገኛት ባይፈልግም ሚስጥሩን መስማት ግን ፈለገ
እናም ቦታ ተቀጣጥረው ተገናኙ ...
ብዙነህ ሲያያት ሳራንና ልኡልን አስቦ እዛው እንቅ
ቢያረጋት ደስስ ይለው ነበር ያለመደባትን ስታየው ፈገግ
ብላ ቡዜ እንዴት ነህ አለችው ብዙነህም ፈጣሪ
ይመስገን እባክሽ ቀጥታ ወደጉዳይሽ ትገቢልኝ አላት
ችግር ውስጥ ነኝ ማለቴ እርዳታህን እፈልጋለው
አለችው ከት ብሎ እየሳቀ አንቺም ችግር ይገጥምሻል
እንዴ አላት እንባዋ እየፈሰሰ ልጄ ሊሞትብኝ ነው
የወላጅ አባቱ ደም ካልተገኘ ስትል አቋርጧት እና ይሄ
እኔን ምን ይመለከተኛል አለ አውቃለው ተቀይመኸኛል
ግን ትዝ ይልሃል ልኡል ሊፈታ አንድ ቀን ሲቀረው
ሁለታችንም ሰክረን አብረን አድረን ነበር... ደነገጠ
አልገባኝም እና እናማ ልጁ ያንተ ነው እባክህ ማንም
ሳይሰማ ለልጅህ ስትል ... ብላ ተናግራ ሳትጨርስ
ተነስቶ በጥፊ አጮላትና ከስህተትሽ የማትማሪ አውሬ
ከጥቅምሽ ውጪ ለሰው ሞራል ቅንጣት ታህል ርህራሄ
የለሽም ቆይ እንዴት ብታስቢኝ ነው እወድሻለው ስልሽ
አይንህን ላፈር ብለሽኝ ዛሬ ልጅህ ምናምን ስትይኝ
አምኜ የምቀበልሽ ይመስልሻል ድሮም ልኡል
እንዳላስረገዘሽ ጠርጥሬ ነበር በይ በግዜ አባቱን
ፈልጊለት... ብሎ ትሏት መንገድ ጀመረ..
ራሄል ቀወሰች እሩጣ ተከትላው እግሩ ስር ተደፍታ
ለመነችው የሰው ሁሉ አይን እነሱ ላይ አተኮረ ከዛም
ተነሺ አላትና አንድ ነገር ልንገርሽ ልጁን እንዳልሽው የኔ
ከሆነ አድነዋለው ግን ይሄን ሁሉ ነገር ቅድሚያ ለልኡል
ትነግሪዋለሽ ሳራን ምን እንዳረግሻትም አንድ በአንድ
ታስታውሺዋለሽ አላት ይሄን እንዳደርግ ያዘዘችኝኮ
እናቱ ናት እመነኝ እኔ ልኡልን አፈቅረው ነበር እንጂ
ህይወቱን መበጥበጥ አልፈልግም ነበር እናቱ ግን
በታመመችው እናቴ ይዛኝ ልኡልን ከሳራ እንዳለያየውና
ከሱ እንዳረግዝ አዘዘችኝ እኔ ማንም አልደፈረኝም
ሁሉም ድራማ ነበር ልኡል በማያውቀው ነገር
የታሰረውም ፖሊሶቹን ከፍላቸው ነው... ብዙነህ
በግርምት ይሰማት ጀመር ከዛ ግን ልኡል ፈፅሞ ሳራን
መክዳትም ሆነ ሌላ ሴት አቅፎ ማደር እንደማይችል
ስረዳ አንተን አሳሳትኩህ እናም አረገዝኩለት ብዬ
ለእናቱ ስነግራት በጣም ተደሰተች ይሄው ነው ይሄን
ሚስጥር ለራሴ ራሱ ደግሜ ማውራት አልፈልግም ነበር
ግን ... አለችና ዝም አለች....
ብዙነህ ግራ ገባው በማን ላይ ምን መፍረድ አለበት
?? የልኡል እናት ግን ምን አይነት እርኩስ ነች በስንት
ሰው ህይወት ላይ ነው የተጫወተችው ልጄ የኔ
አለመሆኑ ተነግሮኝ ከማመን በላይ ምን ሞት አለ
ብዙነህ ራሄልን ትቷት እቤቱ ሂዶ ማሰብ ጀመረ ሳራ
ልኡል የገዛ ልጁ ሁሉንም በአይነ ህሊናው እየሳለ
ማልቀስ ጀመረ ... አሁን ግን መፍጠን ላለበት ነገር
መፍጠን እንዳለበት ወሰነ በነጋታውም ሆስፒታል ሄዶ
ልጁን ለማዳን ደም ሰጠ ይሄን ብዙነህ በጣም ፈራ
ለልኡል መናገር እንዳለበት ልቡ ያውቃል በዚም
ለመናገር ወስኖ ልኡልን ሊያገኘው ስልክ ደወለ ስልኩ
ጥሪ አይቀበልም ይሄኔ ቤታቸው ሲሄድ ቤቱ በለቅሶ
ተሞልቷል ደንግጦ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቅ ልኡል
ልጅክ አይደለም ሲባል ተናዶ የት እንዳለ አይታወቅም
አሉት ይሄኔ ብዙነህ እንዳልቸኩል ብዬ አረፈድኩ አለ
በቁጭት ...✍
ይቀጥላል...✍
ሱ...♥❤️ፍቅር___ሲፈርድ

❤️ክፍል___12

👉
በእውነተኛ___ላይ____የተመሰረተ____አስተማሪ__
_ታሪክ

ራሄል የልኡልን እናት ዶክተሮቹ ተሳስተው


እንደነበርና አሁን ግን በልኡል ደም ልጇ እንደተረፈ ነግራ
አሳምናቸዋለች ይህን ሲሰማ ብዙነህ በንዴት እንባቸው
እንደጎርፍ የሚወርደውን የልኡልን እናት ወይዘሮ
ለምለም አለ ሳራ በድንጋጤ ክው አለች ቤት ውስጥ
ያሉት ሁሉ ወደብዙነህ ዞሩ እርሶ የልኡል እናት ለመሆን
ፈፅሞ አይመጥኑም ኧረ የማንም እናት ምክንያቱም
እናትነት አልገባዎትም እናት ማለት ከሷ ይልቅ ልጇን
የምታስበልጥ ናት እርሶ ግን ... ይቅርታ እንዲ መናገር
ከሌለብኝ ግን እውነቱ ይሄ ነው ... አለ ይሄኔ ለምለም
ተነስታ ጋጠ ወጥ ነህ እንዴት እንደዚህ ትናገራለህ አለች
ቱ እኔ ለሴት በተለይም ለእናት ክብር ስላለኝ ነው
እንጂማ ልጆትን የልጅ ልጆትን እንዲህ ባልቀጡ ነበር
የልጆትን ልጅ የወለደችውን ሳራን ለጅብ ሰተው ሲል
የቤቱ ስልክ ጥሪ አስተጋባ...

የልኡል እህት ስልኩን አንስታ ሀሎ አለች ቀጥላም


ዳዲ እኔ አላምንም ሰርፕራይዝ ልታረገን ነው አለች
ሁሉም ዞረው ሲመለከቷት ማሚ ዳዲ ኤርፖርት
ከ 2 ሰአት ቡሃላ እደርሳለው አለ አለች ና ስልኩን
ዘጋችው ተመልሰው ወደ ብዙነህ ሲዞሩ ወቶ ሄዷል
ራሄል ደንግጣለች ነገሮች ሁሉ ተወሳሰቡባት ህሊናዋ
ተረበሸ እውነቱን አፍረጥርጣ መናገር አማራት የልኡል
እናት ውስጧ በጭንቀት ታመሰ አባቱ ልኡልን እንደ
እንቁ ነው የሚያየው አሁን ሲመጣ ልጅህ ጠፍቷል
ቢባል ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ቀላል ነው...
ይህ በንዲህ እንዳለ የልኡል አባት ከአሜሪካ መጣ
ሁሉም ለመናገርፈርተው ስለ ልኡል ውሸት መጠንሰስ
ጀመሩ በእቅዳቸው መሰረትም ልኡል ከጓደኞቹ ጋር
ወጣ ብሏል አሉት የልኡል አባት ምንም ሳይመስለው
ቀረ እንዲያውም ተውት ይዝናና ግን የልጄን ልጅ ማየት
እፈልጋለሁ አለ ይሄኔ ሁሉም ሰው በደስታ ራሄልን
ጠርተዋት ሊያስተዋውቋቸው ጉድ ጉድ ማለት ጀመሩ
የልኡል አባት ራሄልን ሲያያት ምንም ፈገግታ
አይታይበትም ይህን የተመለከቱት የልኡል እናትና እህት
ግራ ተጋብተው አባዬ እሷኮ የወንድሜ ሚስት ናት ህፃኑ
ደሞ ልጃቸው ነው አለች ልእልና ይሄኔ እንደመቆጣት
ብሎ የልጄ ልጅ ትልቅ እንደሆነች አውቃለው አሁን ግፋ
ቢል 3 አመት ይሆናታል ስለዚህ ልትዋሹኝ ፈልጋችሁ
ነው ወይስ ምን ሆናለች አለ ሁሉም ደነገጡ ራሄል የገዛ
ምራቋ አነቃት...

በነጋታው ጠዋት ተነስተው ሳራን ማፈላለግ ጀመሩ


ልኡልንም እንዲሁ ግን አየኋቸው የሚል ሰው ጠፋ
አፋልጉን ብለው ፎቶ መስቀል ቀራቸው ... ከቀናት
ቡሃላ ራሄል እንደምንም አይኗን በጫው አጥባ ብዙነህ
ቤት ሄደች ልክ ስትገባ ያልጠበቀችው ክስተት ገጠማት
ልኡል ብዙነህ ቤት ተቀምጧል ልብሱ እላዩ ላይ
ከመብከት አልፎ ተቀዳዷል እራሱን ጥሏል ደንግጣ
ደርቃ ቀረች ልኡልም ልክ ሲያያት ውጪ ሲል ጮኸባት
ብዙነህም እውነቱን ነው ውጪ ወይስ ደሞ ምን
ልታረጉት ፈለጋቹ ከዚ በላይ አለና እየጎተተ አሶጣት የት
አገኘኸው አለች እንባዋ እየቀደመ ምን አገባሽ ልኡል
አሁን ሁሉንም ማስታወስ ይችላል ሳራን እንጂ
እንዳንቺ አይነቷን ሴጣን አይፈልግም ካሁን ቡሃላ
አትድረሱብን ሂጂ እባክሽ አላት ... አባቱ ሊያዩት
ይፈልጋሉ እና ስትል ልኡል እኔ ማንንም ማየት
እንደማልፈልግ ንገሪያቸው ደሞ ልንገርሽ ሲል ብዙነህ
ካፉ ነጥቆ የት እንዳለ ልጁ ላንድ ሰው ትንፍሽ ብትይ
እደፋሻለው አላት...

ራሄል ፈርታ ልኡል የት እንዳለ ለማንም ሳትናገር


ቆየች አባትየውም የልጄን ልጅ አምጡ ሲሉ ቤቱን
ቀውጠውታል ... ይህ በንዲህ እንዳለ ነበር ታድያ
እማማ ሳራን ስትደውል ጠብቀው ልጇ ስለታመመች
ዛሬ ነገ ሳትል ሀገር እንድትመጣ አትብቀው የነገሯት
ሳራም ልጇ በጠና መታመሟ ስላሳሰባ ሀገር ለመመለስ
ወሰነች ግን ደግሞ ሳራ ከእማማ ልጅ ሳሚ ጓደኛ ፍቅር
መጀመሯን ለቤቲ የነገረቻት ከሳምንት በፊት ነበርና
ቤቲ ለማንም ሳትናገር ፀጥ ብላለች ... ሳራ ከሳሚ ጋር
ፍቅር የጀመረችው በሚያረግላት እንክብካቤ ተስባ ነው
እናም ምንምኳ ባታፈቅረው ሰው ሃገር ላይ ብዙ
ውለታን ስለዋለላት የፍቅር ጥያቄውን አለመቀበል
አልቻለችም ነበር...✍

❤️ይቀጥላል...✍
n1❤️ፍቅር_____ሲፈርድ....✍

❤️ክፍል____13
❤️በእውነተኛ____ታሪክ_____ላይ____የተመሰረተ__
_አሳዛኝና_____አስተማሪ...✍

ሳራ ጓዟን ጠቅላ ሀገር ቤት ልትገባ መዘጋጀት


ጀመረች ይሄኔ ሳሚ ቃል ተገባብተውና ቀለበት
አድርገው እንትሄድ በጓደኞቹ አስጠየቃት ሳራ ግን ባሁን
ሰአት ቃል የምትገባባበት ግዜ እንዳልሆነና ልቧ
ለመጣመር ዝግጁ እንዳልሆነ አረዳችው ይሄኔ ሳሚ
በጣም ተናደደ ልብሽ ሳይወደኝ ነበር አብረን የቆየነው
ሲል ጠየቃት እሷም ውለታው ስለከበዳት ምርጫ አታ
እንደሆነ ነገረችው ሳሚም የውሸት ተስፋን
ስለሰጠችው በጣም ከፋው ሊበቀላትም ፈልጎ ቤተሰብ
ልጠይቅ በሚል ተልካሻ ምክንያት አብሯት ኢትዮጵያ
እንደሚሄድ ነገራት ሳራም መቃወም ስላልፈለገች
እብረው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ...
ሳራና ሳሚ አ.አ ኤርፖርት እንደደረሱ በቃ ቻው እኔ
ወደ ባህር ዳር ነው የምሄደው አለችው ሳሚም አብሬሽ
መጥቼ ልጅሽን መተዋወቅ እፈልጋለሁ እናም ደግሞ
የጓደኛዬ እናት እማማን መጠየቅ አለብኝ አለ ሳራ
በግዜው የልጇ መታመም ስለነበር ያስጨነቃት መልስ
ሳትሰጠው እነማማጋ ደውላ መምጣቷን አበሰረች
እማማም ዛሬ ስለመሸ ነገ ትመጫለሽ ልጄ እዛው እደሪ
አልዋት እሷም ያን ቀን በጣም ስለመሸ አንድ ሆቴል
ውስጥ ሁለት የተለያየ ክፍል ይዘው አደሩ ...

በነጋታው ጠዋት ኮንትራት ታክሲ ይዘው ወደ ባህር


ዳር ተጓዙ በመንገዳቸውም ላይ ሳራ በትዝታ ተዋጠች
ከልኡል ጋር ያሳለፉትን ግዜ እያሰበች ሳታስበው እንባዋ
መውረድ ጀመረ የእንጀራ እናቷን መበቀል አለመቻሏ
እንዲያውም በተቃራኒው ህይወቷ መመሰቃቀሉና
ክፉዋን ለሚመኙት ሁሉ ማሸነፍ አለመቻሏ
ተደማምሮ ደም እምባ አስለቀሳት ሳሚም እንደህፃን
ደረቱ ላይ ለጥፎ አባበላት የሱን እምባ መውረድ እንኳ
ያስተዋለው ሳራ ስትጠርግለት ነው ...
ባህር ዳር እንደደረሱ ሳራ ልቧ ይመታ ጀመር የሆነ
አዲስ ነገር ያለ ይመስላታል ልክ በራፋ ላይ ደርሰው
የውጪ በር ስታንኳኳ ቤቲ ነጭ በነጯን ለብሳ በጣም
አምራና ተውባ በር ከፈተችላቸው ሳራም ቤቲንና
የግቢውን ዲኮር ስታይ ግራ ገባት እንዴ እኔን ለመቀበል
ነው ይሄ ሁላ ነገር ብላ ቤቲን ሰላም እያለቻት ሳለ
ትንጡና ፍልቅልቁ ልጇ በአምላክ እየተሯሯጠ ሲጫወት
ተመለከተች በሰአቱ ልጇን ስታይ ታሞአልና ቶሎ ድረሺ
መባሏ ትዝ አላላትም ነበር እንባዋ እየቀደመ ልጇን
እሩጣ አቅፋ እያገላበጠች ሳመችው ሳራ በሁኔታዋ
ሁሉንም አስለቀሰች ይህ እየሆነ እያለ ቤቲ ከሳሚ ጋር
ታወራ ነበር ይሄኔ ሳሚ ለቤቲና አጠገቧ ላሉት የሳራ
ፍቅረኛ ነኝ እሷን ብዬ ነው የመጣሁት ልንጋባም
ወስነናል አለ ይሄኔ ሁሉም ሰው ሲንጫጫ ሳራ ልጇን
እንዳቀፈች ወደነሱ ዞር ስትል ውሃ አምጡ ደሞም
ንፋስ ስጡት ....ሲባል ደንግጣ ቀረበቻቸው አይኗን
ማመን አቃታት ልኡል እራሱን ስቶ ወድቋል...
አፋፍሰው ሀኪም ቤት ወሰዱት
ነገሩ እንቆቅልሽ ሆነባት እማማም እያለቀሱ ልጄ
በልጅሽ አሟርቼ የጠራሁሽ ታሪኩ ቢረዝምም ብቻ
የልኡል አባትና ብዙነህ ልኡልን ይዘውት መተው አንቺን
ሰርፕራይዝ አርገን ሁለታቹን ልናገናኝ ነበር ግን ልጄ ክፉ
እድል አለሽ መሰል አንቺ እዛ ያጨሽው እጮኛሽ
ልትጋቡ እንደሆነ ሳይጠየቅ ዘባርቆ ... ሲሉ ምን እማማ
ሳሚ ምኔም አይደለም ቆይ ምንድን ነው ነገሩ እኔን
የፈጠረኝ አምላክ ዙርያዬን የሚያስቀምጣቸው ሰዎች
ሁሉ እንዲገሉኝ ነው እንዴ ይሄ የቁም ቅዠት ህልም
መሆን አለበት እያለች በእልህ መጮህ ጀመረች ሳራ
ሰው ሁሉ እያያት ፀጉሯን አንጨባራ ልብሷን እላይዋ
ላይ መቀዳደድ ጀመረች የሚያይዋት ሁሉ ያበደች
መሰላቸው እማማም አታፍጡ አስቁሟት እንጂ እያሉ
ሰውን መቆጣት ጀመሩ...✍
❤️ፍቅር_____ሲፈርድ
❤️ክፍል___14
❤️በእውነተኛ____ላይ____የተመሰረተ___አሳዛኝና
_አስተማሪ___ታሪክ

ሳራ እንደ እብድ ስትጮህና ልብሷን ስትቀድ ሰዎች


ያዟትና አስቆሟት ሳሚም በጣም ደነገጠ እግሯ ላይ
ተንበርክኮ ይቅርታ እንድታረግለት ለመናት እማማም
በአምላክን አቅፈው ያለቅሳሉ ሳራ ልኡል
ወደተወሰደበት ሆስፒታል ሄደች ነገር ግን ልኡል
ማንንም ማየት እንደማይፈልግ ተናግሮ ስለነበር
ዶክተሮቹ እንዳትገባ ከለከሏት ትሄኔ ወደቤት ተመልሳ
ተቀመጠች ሳራ ከቀን ወደቀን እየገረጣች መጣች
ምክንያቱ ደግሞ ምግብ ስለማትበላ ነበር...
የሳራን መምጣትና የልኡልን በሷ ምክንያት ሆስፒታል
መግባት የሰማችው የልኡል እናት እየከነፈች ባህር ዳር
ገባች ሳራን አፈላልጋም ልትገላት ፈለገችና ባሏ ጋር
ደወለችለት ባልየውም ባህር ዳር ሆቴል ይዞ ስለነበር
ልኡልን እያስታመመ የነበረው ወደ ሆቴሉ ቀጠራት
ከዛም ለምን መጣሽ አላት ለምለምም የልጄን ህይወት
እያመሰች ያለችውን ሴት ልገላት አለች አባትየውም
ትንሽ የምፀት ፈገግታ ፈገግ ብሎ ቆየና ቆየሽኮ
ከገደልሻት ምን እሷን ብቻ ልጅሽንም ገለሽዋል ሲል
ካፉ ነጥቃ እንደዚ አትበለኝ እኔ ልጄን ስለምወደው ነው
ለሱ ብዬ ነው አለች እንባ እየተናነቃት ....
ለምለም እስቲ ንገሪኝ እጅግ በጣም ከሚያፈቅራት
ልጅ ነጥሎ ለውሸታምና አስመሳይ መዳር ነው
መውደድ እስቲ መልሺልኝ ከገዛ ልጂ ይልቅ የሌላን ልጅ
የእንጀራ አባት ሆኖ እንዲያሳድግ መፍረድ ነው ነው
መውደድ ሲል ምንድን ነው የምታወራው ራሄልኮ
የልጄን ልጅ ነው አቅፋ ያለችው እራሱ ታሞ በልኡሌ
ደም ነው የተረፈው ሲል ከት ብሎ ስቆ ስሚ ለሌባውም
ከሱ የተሻለ ሌባ እንዳለ አትርሺ ራሄል አንቺን ፈራታ
እንጂ ልጁ የብዙነህ ነው በድንጋጤ የምትጠጣው ውሃ
ትን አላት ይሄኔ እረጅም ሰአት አስላ ጋፕ ሲልላት የሳራ
አሳዳጊ ሳራ ገፊ እንደሆነች ነግራኛለች ቤተሰብ
የላትም ይሄን ታውቃለህ በሷ ምክንያት ሞተዋል ሲል
ለምለም እኔ ይህን ካንቺ አልጠብቅም ምን አይነት
እራስ ወዳድ ነሽ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ይኖርሻል
ብዬ አስቤም አላውቅም!!!
ሳራ ፍትህ የተጠማች ሴት ናት አሳዳጊዋ ነኝ ብላ
የመጣችው ሴት ሀብት ፍልጋ አባቷን በግፍ የገደለች
ሴት ናት ከአባቷ አልፋ እሷን በጎረምሳ ልታስደፍራት
ስትል ነው ሳራ ቤቱን ለቃላት የጠፋችው ግን ሳራ
ማንም ሰው ስላልነበራት እንዴትም ብላ ፍትህ
ማግኘት አልቻለችም ለልጄም ቢሆን ታማኝ
አፍቃሪው ነች ህግ ተምራ የእንጀራ እናቷን ለፍርድ
ልታቀርባት ህልም ነበራት ግን ውዴ አንቺ መሀል
ገብተሽ የምስኪኗንም የልጅሽንም ህይወት አበላሸሽ
... እያለ ስለሳራ ሲነግራት ፀፀትና ሀዘን ፊቷ ላይ ጥላ
አጠሉ እራሷን ወቀሰች .... ባሏ የተከራየው ሆቴል
ክፍል ውስጥ ለ 3 ቀናት አለቀሰች እሷን ለማፅናናት
አቃተው ከዛም ከምታለቅስ ይቅርታ ጠይቃ
ብትክሳቸው እንደሚሻል ደጋግሞ መከራት እሷ ግን
ልጄስ ልጅ ነው እሷ
ትዝ ይልሃል እኔ ሴተኛ አዳሪ ነበርኩ ከዛ አንተ እኔን
አፈቅርሻለው ብለህ አገባኸኝ ከዛ ግን እኔ ልኡልን ስትል
አቋረጣትን አንቺ ልኡልን ከሌላ ወንድ አርግዘሽው ነበር
ይሄን ላመታት ደበቅሽኝ እኔ ግን እጠረጥር ስለነበር የ
DNA ምርመራ አረኩ ልኡል ልጄ እንዳልሆነ ሳውቅ
ላብድ ነበር ግን ለ 15 ቀን ገዳም የቆየውትን አስታወሽ
አለና መልሷን ሳይጠብቅ ያኔ እዛ ሄጄ ስቆይ ነገሮችን
ማገናዘብ ጀመርኩ ልኡልን ልጄ ብዬ አምኜ ተቀበልኩ
አንቺም እንዳትጨናነቂ ሳልነግርሽ ዝም አልኩ
ምክንያቱም በጣም አፈቅርሻለሁ... አለ ለምለም
ማመን አቃታት የሷን ስራና የባልዋን መልካምነት
እያሰበች በራሷ አፈረች...
በነጋታው ጠዋት ተነስታ አ.አ ሄደች እንደደረሰችም
ቀጥታ የሳራን እንጀራ እናት ማፈላለግ ጀመረች
እንዳገኘቻትም በዚ ሁለት ቀን ውስጥ እጇን ካልሰጠች
ሰው በመግደል ወንጀል እንደምትከሳት አስጠነቀቀቻት
የሳራ እንጀራ እናትም ደነገጠች ስለፈራችም
ሳትቀድመኝ ልቅደማት ብላ ለምለምን በስለት
ወጋቻት...✍

ነገ______________________መጨረሻው ...✍

ሊያል 1 ክፍል ብቻ ቀረው ክፍል 15 የቀጥላል ...✍


ለአስተያየት 👉 @torera1
❤️ፍቅር____ሲፈርድ....✍

❤️ክፍል___15___እና____ፍፃሜው...✍

እውነተኛ___አሳዛኝና___አስተማሪ__ታሪክ

በጩቤ ስትወጋ ተዘረረች ይሄኔ የነሳራ ግቢ


ተከራዮች ይመለከቱ ስለነበር በጩኸት ሰፈሩን
አደበላለቁት ሁሉም ከዛ የሳራ እንጀራ እናት ለማምለጥ
ስትሞክር ባካባቢው የነበሩ ሰዎች ያዟት ወደጣብያም
ተወሰደች ... ሰው በመግደል ሙከራ ተከሳ ወደ ማረፍያ
ቤት ተላከች... ለምለምንም ወደሀኪም ቤት ከወሰዷት
ቡሃላ ለልኡል አባት ደወሉለት የልኡል አባት ደግሞ
ብዙነህ ጋር ደውሎ እሱ ከባህርዳር እስኪመለስ
ለምለም ጋር እንዲቆይለት ጠየቀው ብዙነህ ኧረ ችግር
የለውም ሲል የለምለምን ክፋትና በደል እረስቶት ነበር
...

ብዙነህ ለምለም የገባችበት ሆስፒታል ደርሶ


ቀጥታ ወደ ድንገተኛ ክፍል አመራ በሩ ላይም ራሄል
ልጇን አቅፋ ታለቅሳለች ብዙነህም አይቷት አለቃሽ
በመታመሟ ነው እንዲ እምባሽ የሚዘምበው አላት
ቡዜ እስቲ ዛሬ እንኳ ላሳዝንክ እኔኮ የልጅህ እናት ነኝ
አለችው እሱም ትቷት ለምለም ጋር ሊገባ ሲል
ዶክተሮቹ ብዙ ደም ስለፈሰሳት ባፋጣኝ ሌላ ሀኪም
ቤት ሄዳ መታከም አለባት ብለው ሪፈር ፃፉላት
ብዙነህም ለልኡል አባት ሁኔታውን አስረድቶ ወደ
የካቲት ሆስፒታል ተወሰደችና አልጋ ያዘች ብዙነህና
ራሄል ውጪ ቆመው ሳለ እሺ ለምን ነበር
የምታለቅሽው አላት ራሄልም ልጇን በስስት እያየች
ወ/ሮ ለምለም ልጄ የልጇ እንዳልሆነ አወቀች እናም
አይንሽን እንዳላይሽ አለችኝ ማንም ምንም እንደሌለኝ
እያወቀች ...ስትል ድሮስ እውነት ተደብቆ የሚቀር
ይመስልሻል ራሄል አሁንም ልምከርሽ ከጥፋትሽ
ተመለሽ ውሸት ይብቃ ተመልከች ሁሉም
የስራውን...ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ የልኡል አባት
ደወለና ስንት ቁጥር ናቹ አለ ብዙነህም ያሉበትን
ነገረው...

ልክ ወደ ክፍሉ ሲሄዱ ራሄል ደንግጣ ቆመች


ብዙነህም ድንጋጤዋ አስደንግጦት ምን እንዳየች
ለማየት አይኗን ተከትሎ ዞረ ይሄኔ እሱም ተገረመ ሳራና
ልኡል ከልኡል አባት ፊት ፊት ይሮጣሉ ብዙነህ በደስታ
ሰከረ እሩጦ ሁለቱም ላይ ተጠመጠመ ምንድን ነው
የማየው በፈጣሪ እውነት ነው ግን እያለ ሁለቱንም
በየተራ ሳማቸው የመጡበትን ጉዳይ ለትንሽ ደቂቃ
እረሱትና በብዙነህ ሁኔታ እንባቸው ፈሰሰ ከዛም የልኡል
አባት ናልጄ በቃቹ እናትህን እንይ አለ ... ብዙነህም
ውስጥ ዶክተሮቹ ስላሉ ሲወጡ እንገባለን አለ ሁሉም
መንቆራጠጥ ጀመሩ ...
በመሀልም ሳራ ግንኮ አልገባኝም ወይዘሮ
ለምለምን ማን ሊወጋት ይችላል አለች ሁሉም ቀጥ
ብለው ወደሷ ተመለከቱ ልኡልና ሳራ በርግጥም
አላወቁም ነበር ... አብረው የመጡት እማማ ሳራን
እያረጋጉና በቀን በቀን ቤተክርስትያን እየሄደች
እንድትፀልይ አድርገው ወደራሷ ሲመልሷት ሳሚ
ደግሞ ልኡል የተኛበት ሆስፒታል ድረስ ሄዶ ያኔ
ባለማወቅ ስለሚያፈቅራት ብቻ እንደዛ እንዳለና እሷ
ግን ካንተ ውጪ ማንንም አታፈቅርም ባለማወቅ ለዚ
ስለዳረኳቹ ይቅርታ በማለት ልኡል በድጋሚ ከሳራ
እንዲገናኙ አድርጎ ልክ የልኡል አባት ልኡልን ይዘው
እነሳራ ቤት ደርሰው ልኡልና ሳራ ሲተቃቀፉ ነበር
ለምለም ተጎድታለች ተብሎ ለልኡል አባት
የተደወለው...

ዶክተሩ ወቶ የለምለም ቤተሰቦች አለ ሁሉም


አቤት አሉ ወደዶክተሩ እየተጠጉ ለምለም ከፍተኛ ደም
ስለፈሰሳት ደም የሚለግስ ሰው ያስፈልጋል ከመሀላቹ
ሲባል በቅድሚያ ባሏ ገባ ግን ባልየው መስጠት
አይችልም ምክንያቱ ደግሞ የደም ታይፓቸው አንድ
አይደለም ቀጥሎ ልኡል ገባ ልኡል ደግሞ ሙሉ ጤነኛ
ባለመሆኑ እንደማይችል ነገሩት ብዙነህ እኔ እሰጣለው
በቃ ብሎ ሲገባ የሱም እንደማይሄን ተነገራቸው ይሄኔ
የልኡል አባት ዘመድ ጋር ለመደወል ስልካቸውን ሲያነሱ
ሳራ እኔ አለው አለች ሁሉም ደነገጡ ያን ሁሉ በደል
ያሳለፈች ሴት እንዴት ዛሬ ለበደለቻትና ህይወቷን
ላበላሸች ሴት ደም እለግሳለው ትላለች እውነትም ሳራ
እንቺን ያገኘሽ ልጄ ፈጣሪ ልቡን አይቶ ነው ተባረኪ
አላት አጋጣሚ ደግሞ የሳራና የለምለም ደም
ተመሳሳይ ነበርና ዶክተሮቹ ከሳራ ደም ወስደው
ለለምለም ተኩላት ለምለም ስትነቃ ካጠገቧ
የተኛችውን ሴት ሳራን ተመለከተች ለምን ከጎኗ
እንደተኛች ለማወቅ ግዜ አልፈጀባትም ...

ለምለም መቃብሯን የቆፈረችላት ሴት ዛሬ


ህይወቷን ስታድናት ከማየት በላይ ምን አለ ፀፀት
ውስጧን አሰቃየው በተንጋለለችበት እምባዋ ቁልቁል
ወደጆሮዋ ፈሰሰ... ለምለም ድና ስትወጣ በቅድሚያ
ሳራንና ልጇን ድል ባለ ሰርግ ለመዳር መዘጋጀት ጀመረች
ባሏንም ለልኡል አባቱ እንዳልሆንክ ይነገረው ስትል
የልኡል አባት ግን በፍፁም አለ ልጄ የኔ እንደሆነ
ይቀጥላል እስከዛሬ ያልተነገረውን ዛሬ መናገር የለብንም
አለ ለምለምም በቃ አንተ እንዳልክ አለች ...

ለምለም ጠበቃ ቀጥራ የሳራን እናት በመግደል


ወንጀል ከሰሰቻት ሳራም የአባቷን ሀብት ይገባሻል ሲባል
ተፈረደላት ከብዙ ምርመራ ቡሃላም በለምለም ጥረት
የሳራ እንጀራ እናት እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት
ልኡልና ሳራም ድል ባለ ሰርግ እንዳዲስ ተጋቡ
...እማማም ባህር ዳርን አለቅም ብለው የነበረ ቢሆንም
በሳራ ልፋት የአባቷን ቤት ሰታቸው መኖራቸውን
ቀጠሉ ለምለምም ካሳ ይሁነኝ ስትል ጥሩ ቤትና መኪና
ገዝታ ለሳራና ለልኡል ስጦታ ሰጠቻቸው ... የልኡል
አባትም አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ፍቅር ያሸንፋል
ሲሉ ራሄልን አፈላልገው ከብዙነህ ጋር በማስታረቅ
ለልጃቸውም ሲባል አብረው እንዲኖሩ አደረጉ ... ደስታ
በየቤቱ ገባ .........
።።።ይህ___ነው____ፍቅር___ሲፈርድ ።።።
።።።።።።።።።።።ተፈፀመ።።።።።።።።።።።።

❤ FIRAA'OL M DIBAABAA

You might also like