You are on page 1of 23

ሁላችንም ነን

እናት አባት ሽር ጉድ እያሉ ጎረምሳ ልጅ ተኝቶ ቲቪ ሲመለከት እናያለን ፡፡ እናት የተኛውን ልጅ ተቆጥታ
ታስነሳዋለች ፡፡

እናት

አንተ ተነስ ሰዓት ደርሷል

ልጅ

ታዲያ እኔ አልመጣ የሚመጡት እኘሱ አባየየ ወጥቼ ልደባደብ እንዲ

አባት

እሱማ ወግ ነበር .... ለመሆኑ ድብድቡ ከማ ጋር ነው

ልጅ

እህቴን እንዴት ብታስብ ነው የተመኘሀት እኔ ሳላውቅ ሳልፈቅድ ያናገርካት ዘራፍ ወንዱ ይባል

እናት

ወንዶቹ ማጨው ቀሩ እቴ ...... አሁን ተነስና የሚጠጣ ቢራ ላሰላሳ ገዝተህና

አባት

ቢራውን አይነቱን ቀልቀል አርገው ፡፡ ወይኑን ደግሞ ነጭ ና ቀይ

/ልጅ ገንዘብ ተቀብሎ ይወጣል /

አባት

እናትና አባትሽ ቤት ልተዋወቅ ስሄድ የፈራሁትን ፍርሃት አንቺ አታቂውም

እናት

አንተ ደግሞ ፍርሃት ታቃለህ አንዴ

አባት

ኩራቴን ዋጥ አርጌያት ነበር .... ዛሬ ልንገርሽ የሆነውን ..

እናት
ካልሞቱ መቼም የማይሰማ ነገር የለም

አባት

ማታ ለአባቴ ነገርኩት ... ቤተሰቦችሽን ልተዋወቅ ልሄድ እንደሆነ

እናት

አባዬ መቼም ታሪካቸው አያልቅም ... እንዳትሄድ አሉህ

አባት

እሱ ያባት ... አባትዋ ማን እንደሆኑ ባወክ ይህን ልታደርግ አለኝ

እናት

ምን አውቆ

አባት

አንተ እሷን እንዳጨህ ከነግርከኝ ቀን ጀምሮ ስለማንነትዋ ሳጠና ነበር አለ

እናት

/ስረዋን ትታ ማዳመጥ ጀመረች /

አባት

የመጀመሪያው ጥያቄ መቼም ከልጅትዋ ጋር አንሶላ አልተጋፈክም አለ ..... ሳላገባት አልኩት ..


ተርፈሀል አለኝ

እናት

ከምኑ

አባት

አይ ይገልህ ነበር ይህን አርገህ ቢሆን

እናት

የምርህን ነው

አባት
ኮራ ብዬ በምን ያቃል ይህን ባረግስ አልኩት እሱም እሱ የማያቀው ነገር የለም ... ለማንኛውም
እሰካሁን ለምን እንደታገሰ ባላቅም በልቡ አይቶ የተመኛት እንኳን ብዙ ስቃይ ደርሶበት ተገርፎ ተሰቃይቶ ከስሯ
ነው እንደመንፈስ የሚጠፋው

እናት

አይ አባዬ ... እኔ እኮ ስወዳቸው ... ከዛስ

አባት

ምን አልባት አንተን ፀጥ ያሉህ እቤት ስትሄድ ሊገርፉህ አስበው ይሆናል አለኝ

እናት

እና ታዲያ እንዴት መጣህ /በጣም ትስቃለች /

አባት

እኔማ ይቅርብኝ አልሄድም ቢያንስ የምወዳት ሴት ፊት አልዋረድም ብዬ ነበር ... እሱ ግን ብትቀርማ ግርፊያው
ወደ መሳሪያ ተቀይሮ እግርህን በአንድ ጥይት ነው የሚልህ ... እንዴት ቢንቀኝ ነው የቀረው ከሱ ምን
እንደሚያረግህ እሱ እራሱ አያቀውም

እናት

እየሳቀች ... ተጫውቶብሀል ....

አባት

ስጨነቅ ስንቆራጠጥ መሸ..... ኃላ መጣና መኝታ ቤቴ አስቤበታለው መዳኛህ አንድ ነው አለኝ .... ጠንካራ
መንፈስ ይዞ ሂድ .. በራስ መተማመን ይኑርህ .... እኔም እንዳንተ የኮራ አባት አለኝ የሚል አቋም ይኑርህ
በውስጥህም በአለባባስህም ቅብርር ኩርት በል ... ቢያንስ ምን ታመጣና ነው ይልሀል ... አይዞህ እኔ ደጁ
እጠብቅሀለው ችግር ከተፈጠረ ብሎ ተጫወተብኝ

እናት

እየሳቀች ... አባዬ ነፍሳቸውን ይማረው ...ጨዋታ አዋቂ ነበሩ ... ለካ ያ ሁሉ ኩራት መንቀባረር የፍረሃት ነበር ...
አባቴ ያኔ ምን እንዳለኝ ታውቃለህ ልበ ሙሉነቱ ወንዳወንድነቱ የሚያረገውን ነገር እንደሚያቅ ምስክር ነው ነበር
ያለኝ

አባት
ስመለስ የሆነውን ስነግረው ከእናቴ ጋር ወር ሙሉ ነበር የሳቁብኝ ...... ታመስግነኛለህ .... ተልፈስፍሰህ
እንዳትሄድ ብዬ ነበር ያለኝ

ልጅ

/ልጅ መጠጦቹን የወዞ ይገባል / እታች ሰፈር የሆነች ልጅ ሞተች ተብሎ ሰፈሩ ታሞቷል

እናት

ለምን

ልጅ

ባዶ ቤት ሞታ ተገኝታ

/መጠጥ ተሰናዳ ምግብ ይደረደራል እንግዶች ከውጭ ይገባሉ/

/አንዲት ቆንጆ ሴት እና ወጣት ይገባሉ/ አባት እና እናት በር ላ ቆመው ይቀበሏቸዋል ገብተው ይቀመጣሉ /

አባት

ሙቀቱ እጅግ ከባድ ነው አረፈ በሉ

ሴት

መንገዱ ተዘግቶ መኪና ውስጥ ተቀቀልን

እናት

እስቲ የሚወደውን ነገር ቅጂለት

ሴት

ውሀ ይሻለዋል በረድ እንዲል ..../ውሀ አምጥታ ትቀዳለች /

እናት

ስላወኩህ ደስ ብሎኛል ሴና ስላንተ ብዙ አውርተኛለች ...

ወጣት

እኔም የራሴ እናት ያህል ነው የማውቆት ሁሌም ስለእናትዋ መልካምነት አውርታ አትጠግብም ከናትና ከልጅ
ከፍ ያለ ጓደኛ ናት አለችው....
አባት

ካባት ጋር ጓደኛነት የለኝም አለችህ እንዴ

ወጣት

ሚስጥረኛዬ ነው ስትል ነው ምሰማው .... ከጓደኝነትም ከፈ ሳይል አይቀርም

ልጅ

እንግዲህ የሰርጉ ቀን ጥቂት ቀን ነው የቀረው እኛም ወገባችንን አሰረናል ... ሽብ ረብ ብለን ልድር

ሴት

ሰርጌ መቼም ከኔ በላይ ነው የናፈቀህ

ልጅ

እንዴታ እንዴት አይናፍቀኝ .... ሁሌችንም እኮ ነው ነፃ ምንወጣው

እናት

አንተ ...... መናጢ ..... የቀልድ ቦታ ለይ

ሴት

ቆይ ቆይ ቆይ ይጨርስ የምን ነፃነት ነው

ልጅ

እኔ ካንቺ ህግ ነጻ በመውጣት የቤቱ እንደኛ ልጅነትን ክብር .... እንቺ ከልጅነት ወደ ቤት እመቤትነት

/እናት ተነስተው ምግብ ጠረጴዛ ላይ ሰሀን መደርደር ይጀምራሉ/

ወጣት

አባቴ ትንሽ ጨንቆት መልክት ቢጤ ልኳል

አባት

ምንድነው ...

ወጣት
ምንም እንኳን የኔ ትልቅ ዝግጅት የሚደገሰው በከተማው አለ በተባለው ሆቴላችሁ ቢሆንም ወጪውን ባግዝ
ብሏል

አባት

ሰው እቤቱ የሚያዘጋጀውን ምሳ ከመቼ ወዲህ ነው ላግዝ የሚባለው .... አታስቡ በልልኝ .. ሁሉ በጃችን
ሆሌሉም ቢሆን የራሳችሁ ነው .... ለናንተ ሰርግ ካልተደገሰበት ለማን ሊሆን ነው

/በሀይል በር ምንኳኳት ድምፅ ይሰማል / ሁሉም ተደናግጠው ይታያያሉ/

ሴት

የጠራችሁት እንግዳ አለ

እናት

እንደውም .... ማንንም አትጥሩ ስላልሽ ማንንም አልጠራንም

/በሩ መልሶ ይንኳኳል ልጅ ተነስቶ በሩን ይከፍታል / በሩ እንደተከፈተ ተፈናጥሮ ገብቶ ቤት ውስጥ እንግዳውን
ይቆማል

ልጅ

ይቅርታ ... ግን እኮ አላወኩህም ማን በር ዘጋ አረገህ

መርማሪ

ይቅርታ ... መርማሪ ታሪኩ እባላለው

ልጅ

አልጠየኩህም እኮ ማንነትህን ..... ምንም ሁን ሰው ቤት ዘው ተብሎ አይገባም

መርማሪ

ዛሬ ጠዋት እንዲት ሴት በቤትዋ ሞታ ተገኝታለች

እናት

የፈረደበት የቀብር መዋጮ .... እባክህ ሰጠውና ይሂድ ይህን ውብ ቀን እያበላሽብን

አባት
በዚህ ስነ ምግባር ነው የምሰጠው ... እባክህ የኔ ወንድም ይሄ የቤተሰቡ ልዬ ቀን ነውና ሌላ ደረጃ ሳንደርስ
ቤቴን ለቅቀህ ብትወጣ

መርማሪ

ነገሩ ከዚህም ትንሽ ከፈ ያለ ነው ... የአማሞቷን ሁኔታ ለማጣራት በመርማሪነት ነው የተመደብኩት


የመጣሁትም እንዳንድ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ነው

ሁሉም

/በአንድ ድምፅ እኛ ደግሞ ከአንድ ደሀ አሟሟት ጋር ምን አገኛኝቶን /

መርማሪ

እሱን ስንነጋገር የምንደርስበት ነው

ሁሉም

ግራ በመጋባት ይተያያሉ

አባት

ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ ... በአንድ ስልክ ለዚህ ድፍረትህ ብዙ ቅጣት እንደደረስብህ ማድረግ እችላለው

መርማሪ

ማድረግ የምትችሉትን የማትችሉትን ማንነታችሁን ጭመ፣ር ጠንቅቄ አውቃለው.... እኔ ስራዬን እየስራው ነው


....10 ደቂቃ ላናግዎት እና ከዛ መደወል ካለቦት ይደውላሉ ያኔ የሚያስደርጉትን ያረጋሉ

/መርማሪው የምግብ ጠረጴዛው ሄዶ እየተቀመጠ ለአባትየው ወንበር ይሰብለታል /

/አባትዬው ግራ በመጋባት እያየው ሲቆም

መርማሪ

5ደቂቃ ብቻ ይቀመጡ ትንሽ መረጃ ነው ምፈልገው

/አባት እንደተቀመጠ መርማሪው ከኪሱ ፎቶ አውጥቶ ጠረጰዛው ላይ ሲያስቀምጠው አባትየው በአግራሞት


ሲያይ ሁሉም ካሉበት ተነስተው ወደ አባትየው ሲመጡ መርማሪው ይቆምና /

መርማሪ

ማንም ወደ ዚህ እንዳይመጣ እዛው ሶፋ ላይ ለግዜው ጠቀመጡ ተራችሁ ሲደርስ ትመጣላችሁ


/ግራ በመጋባት ይቀመጣሉ አንገታቸውን አዙረው ወደ ነሱ ያያሉ/

አባት

ይቺን ልጅ መልኳ አዲስ አይደለም

መርማሪ

/ፎቶውን አንስቶ ኪሱ እየከተተ/ እርሶ መስርያ ቤት ተቀጥራ ትሰራ ነበር ይሄ ዛሬ ባለ5 ኮኮብ የሆነው ሆቴል
መስርያ ቤት ነበረች .....

አባት

አስታወስኳት .... ፈርሶ ሳይሰራ በነበርው አሮጌው ሆቴል ውስጥ ትሰራ ነበር..... ታዴያ የዛሬ 6 አመት እኔ ጋር
ትሰራ የነበረች ዛሬ ብትሞት ከኔ ጋር ምን አገናኘው

መርማሪ

አገናኝቶ ነው የመጣሁት

አባት

እንዴት

መርማሪ

ልጅትዋ እጅግ ታታሪ ሰራተኛ ነበረች

አባት

አዎ በጣም ጎበዝ የሆቴል አስተዳዳሪ

መርማሪ

ሆቴሉ ከመክሰርና ከዝንብ መጫወቻ ከመሆን በከተማው ያለ ታዋቂ ምግብ ቤት እንዲሆን ትልቅ አስተዋፅኦ
አርጋለች

አባት

እውነት ነው .... ሆኖም

መርማሪ

እርሶ ጋር የነበሩት ሰራተኞች ለ5 አመት ኪሳራ ላይ ነኝ በሚል ደሞዝ ሳይጨመር ኖረዋል


አባት

አዎ

መርማሪ

ይቺ ሴት ድርጅቱን እጅግ ትርፋማ ካረገች በኃላ ለሰራተኞቼ ደሞዝ ይጨመር ብላ ጠየቀች

አባት

ምን ጠየቀች አሳደመች

መርማሪ

በአምስት አመት ውስጥ 500 ብር ይጨመርላቸው ትርፋማ ነን ብላ አስጨመረችላቸው

አባት

አማራጭ ስላልነበረኝ ነው የጨመርኩት

መርማሪ

ሆኖም ለሁሉም ሰራተኞች ደሞዝ ጨምረው ለ10 አመት ለፍታ ካቆመችው ሆቴል ያለምንም አገልግሎት
ባሰነምግባር ከስራ አባረሯት

/ቤተሰቡ በሙሉ ጭንቅላቱን ይይዛል /

ሴት

ማናት እሷ አላቃትም

እናት

ጎበዝ ሰራተኛ ነበረች .... እኔ ግን የማቀው የተሸለ ስራ አግኝታ እንደለቀቀች ነው

መርማሪ

ይቅርታ ፀጥታ

አባት

በሰላም ማባረሬ እራሱ እኔ ሆኘኜ ነው...

መርማሪ
ጨርሻለው

/ቤተሰቡ መንጫጫት ይጀምራል አባት ተነስቶ ወይን ቀድቶ ወደ ሶፋው እየመጣ/

አባት

ጨርስክ ምረመራህን .... አሁን እንደተከበርክ ቤቴን ለቅቀህ ውጣ .... የልጄ እጮኛ ትውውቅ ቀን ላይ ነኝ

እናት

እንዴ እሷ ግን እሯሷ ለቃ አይደል የወጣችው

ሴት

አባዬ እንደዚህ አርገህ ከሆነ ግን ልክ አይደልህም

እናት

እውነት ነው ድርጅቱ ተዘጋ ሲባል እኮ ነው አዲስ አሰራር አዲስ የምግብ አይነት ፈጥራ በራሷ ጉልበት
ማስታወቂያ ሰርታ ያኘሳችው

አባት

ድርጅቱን አንስታ መልሳ ስትገለው አማራጭ አልነበረኝም እሷን ፀጥ ብላ ሁሉም እየተነሳ በየወሩ ያሳድምብኝ
ነበር

እናት

የኔ ግን አሁን እዚህ ሰፈር ከሞተችው ሴት ጋር ምን ያገናኘዋል .... ደሀ ነች አላሉም

አባት

እሱ የራሱ ችግር ነው ተገናኘ አልተገናኘ አሁን ለምን ቤቴን ለቆ አትወጣም ከጨረስክ

መርማሪ

አልጨረስኩም ገና እንደውም ልጀምር ነው

ሁሉም

ማለት .... ወጣት .... ለፈለክ ሌላ ቀን ቀጠሮ ይዘህ ስራህን መስራት ትችላለህ ... ካልሆነ አባቴ ጋር ልደውል
እችላለው ያለቀህ አለቃ ነው

መርማሪ
ይቺ ሴት ከሆቴል ተባራ መውደቂያ አልነበራትም የቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻልዋ አከራዮችዋ አስወጧት
በዚህም ሁኔታ ከፈተኛ የሆነ የመንፈስና የጭንቀት በሽታ ይዟት ጠበል ለጠበል ስትንከራተት ከረመች ... ተንሽ
ሻል ሲላት ተመልሳ ስትንከራተት መጥታ በአንድ ትልቅ ታዋቂ ልብስ ቤት ተቀጥራ መስራት ጀመረች በስራዋ
በጣም ታታሪ ስለነበረች ማናጀር ለመሆን ብዙ ግዜ አልፈጀባትም ኑሮዋ ተሸሻለ ህይወቷ እንደበፊቱ ሆነ

ሴት

ከዛስ

መርማሪ

ከዛማ አንዴ እዚህ ወንበር ላይ ትመጪ

ሴት

ማን እኔ

መርማሪ

አዎ አንቺ ቀጥሎ ጥያቄ ያለን እኔ ነኝ

ሴት

እኔ ደግሞ በዚች ሴት ጋር ምን ያገናኘኛል ካገናኘስ ደግሞ እንዳባዬ አልቀጠርኳት አላባረርኳት

/ሴት በልባ ሙሉነት ተነስታ አባትዋ ተቀምጦ የነበረበት ቦታ ላይ ትቀመጣለች /

/መርማሪ ከሌላ ኪሱ ፎቶ አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ ያስቀምጣል /

/ሴት በአትኩሮት እና ግራ በመጋባት ታያለች /

መርማሪ

ወደፎቶም እየጠቆመ ይችን ሴት ታስታውሻታለሽ

ሴት

አላስታውሳትም

መርማሪ

አንድ ቀን ኤም ኤንድ ኤም የሚባል ታዋቂ ልብስ ቤት ልብስ ልትገዢ ሄደሽ .... ልብስ አስወርደሽ ስትለኪ የቤቱ
ሴቶች ሁሉ ሲሰግዱልሽ ነበር
ሴት

ሁሌም ልብስ የምገዛው ከዛ ነው

መርማሪ

የቤቱ ክቡር ደንበኛ እንደሆንሽ ቢያንስ በአንድ ግዜ ከ30,000 ብር በላይ ግብይት እንደምታረጊ ስለሚታውቅ
ሁሉም ስጋጅሽ ነው

ሴት

ይህን አላውቅም

መርማሪ

ለማንኛውም ይቺ ሴት እንደሌሎቹ አልሰግደችልሽም ሆኖም የማይሆን ልብስ ሊያስገዙሽ ሲሉ ይቅርብሽ ይሄ


አያምርብሽም ብላ ሌላ ሰጠችሽ እልህ ስለያዘሽ ያምራል እወስደዋለው አልሽ

ሴት

አስታወስኩት ቀኑን

መርማሪ

ይቺ ሴት የዛን ለት የሳቀችው አንድ በአይንዋ የምትወደው ደንበኛዋ በምልክት ቀልዶ ሲወጣ ነበር አንቺ ግን በኔ
ላይ ነው የሳቀችው ብለሽ በማስብሽ ማሰብ ብቻ አይደለም አለቀዋ ጋር ሄደሽ ንቃኛለች አዋርዳኛለች ብለሽ
በመክስስ የዛኑ ለት ከፊትሽ ከስራዋ እንድትባረር አደረግሽ እሷን አባረሽ አንቺ ተናደደኩ በሚል ሰበብ ልብሱን
እንኳን ሳትገዢ ወጣሽ..... ተመልሳ ለመግባት ብዙ ሙከራ ብታደረግ ደንበኛችን ድንገት ተመልሳ መጥታ
ብታይሽ ትናደዳለች ተብላ ተከለከለች

ሴት

ጥፋት እናዳጠፋው ያኔውኑ ታውቆኝ ነበር በስራዬበ ስላፈርኩ ደግሜ እንኳን እዛ ቤት ልሄድ አልቻልኩም

ወጣት

የኔ ፍቅር ትክክል አላደረግሽም .... አንዲት ደሀ ሴት እውነት በነገረችሽ ... ከወዳጅ ጋር በሳቀች ከስራ ማባረር

ልጅ

አየሽ ሁሌም ችኩልና ስሜታዊ ነሽ የምልሽ ለዚህ ነው... ያንቺ ስሜታዊነት የሚበርደው ሰው ከሞተ በኃላ ነው

ወጣት
እና ከዛ በቃ ተባረረች

አባት

የኔ ልጅ እኔስ በጉሮሮዬ መጥታብኝ ነው እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ያ በራስ መተማመንሽን እንዴት አንድ
ልብስ ሻጭ ሸረሸረችው

ሴት

እባካችሁ ተውኝ በወቅቱ በጣም ተፀፀቼ እና አፈሬ ነው የሰነበትኩት

ወጣት

ቢያንስ ይህ ፀፀት እንደተሰማሽ ሄደሽ ወደ ስራዋ ማስመለስ ነበረብሽ

ልጅ

እልህዋ ምላጭ ያስውጣታል .... ትሞታታለች እንጂ አታረገውም

ወጣት

ከዛስ ግን እንዴት ሆነች .... አሁ የኔ እዚህ ሰፈር ሞተች ከተባለችው ልጅ ጋር የሚገናኝ ነው

መርማሪ

ለዛም እጅግ ተማራ አገር ቀይራ ሌላ ቦታ ሄደች ስራ ብትፈልግም ልታገኝ ባለመቻልዋ አንድ ትልቅ ሆቴል
ውስጥ ሴተኛ አዳሪ ሆና መስራት ጀመረች

/መርማሪው ወደ ወጣቱ እየጠቆመ/

መርማሪ

እንዴ ከዚህ ጋር ትነሺልኝ ... እባክህ የኔ ወንድም አንተ ደግሞ ወደ ዚህ ና

ወጣት

እንዳታስቀኝ እኔ ደግሞ እዚህ ውስጥ ምን አገባኝ

መርማሪ

እሰቲ እንዴ በኃላ እንዴት እንደሚያገባህ እና እንደማያገባህ እራስህ ትነግረናለህ

/ሴት በንዴት ተነስታ ወንበሩን ለጮኛዋ ትለቃለች ሁሉም በጉጉት ያፈጣሉ እጮኛዋ ወንበሩ ላይ በተደናገጠ
እና ተጠራጠረ ስሜት ሄዶ ይቀመጣል
መርማሪ

/ፎቶ እያወጣ ጠረጰየዛ ላይ ያስቀምጣል ፎተፐውን ከሌላ ኪስ ያወጣል

/ወጣቱ እንዳየው ይደነግጣል ላብ ላብ ይለዋል እሚገባበት ይጠፈዋል /

መርማሪ

ይቺን ሴት ታውቃታለህ

ወጣት

እርግጠኛ አይደልሁም

መርማሪ

በነበርህ አዲስ ከቻይና ጋር በምትሰራው ኢንቨስትመንት አዋሳ ትመላላስ ነበር

ሴት

ያለፉት 4 አመታት ያልተጋባንበት ምክንያት እራሱ የአዋሳው ስራ ባለማለቁ ነው አዎ አዋሳ ይመላለስ ነበር

መርማሪ

አንቺን ሰይሆን እሱን ነው የጠየቅሁት

ወጣት

አዎ አዋሳ ስራ ነበረኝ

መርማሪ

ይቺን ሴት ቡና ቤት አትስሪ ብለህ ከቡና ቤት ስራዋ እንድታቆም አርገሀል አላረክም

ወጣት

የቡና ቤት ስራ እጅ አፀያፊ በመሆኑ እንድታቆም ነግሬያታለው

መርማሪ

መንገር ብቻ አይደ ለም ቤት ተከራይታ ቀለብ ሰፍረህ የጠሞላቀቀ ኑሮ ለ3 አመት አኑረሀታል

ወጣት
መልስ አይሰጠውም

መርማሪ

ለስራ በሄድክ ቁጥር እንደ ንጉስ እየተንከባከበችህ እሷ ጋር ነበር የምታርፈው በሌላ አማርኛ ቅምጥህ ነበረች
፡፡ ሆኖም ባላሰበችውና ባልጠበቀችው ሰዓት አሁን ሚስቴ አግባኝ እያለች ስላስጨነቀችኝ ላገባ በመሆኑ
እና የአዋሳውን ስራ ለሌላ ሰው ልሸጠው ስለሆነ እንደፈለግሽ መኖር አልያም ቡና ቤትሸ መመለስ ትችያለሽ
ብለህ የሆነ ቀን ኮመዲና ላይ 20,000 ብር አስቀምጠህ ጥለሀት ሄድክ

ወጣት

የሚናገረው አጥቶ ይንተባተባል

ሴት

አንተ ከሀዲ .. እኔ እኮ እጠረጥረ ነበር.... ከሷ ጋር ተኝተህ መጥተህ ነው ከእኔ ጋር የምትተኛ የነበረው......

አባት

አንተ ወራዳ ..... አንተ ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ የማንን ልጅ እናዳዋረድክ

ልጅ

ከሀዲ ነህ የኔ እህት ብቻ አይደለም ይቺን ምንም ተስፋ የሌላት ሴት .... ከቦታዋ አንስተህ የማታስበውን ኑሮ
አኑረህ መስበር ምን አይነት እራስ ወዳድነት ነው ..... ጨካኝ ነህ

ሴት

/ቀለበትዋን ከእጅዋ እያወጣች ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠች / አሁኑኑ ቤቴን ለቀህ ውጣልኝ

መርማሪ

እኔ ሳልጨርስ ማንም ከዚ ቤት አይወጣም

እናት

ገና የቀረ አለኝ ነው ምትለው

መርማሪ

አልጨረስኩም ነው የምለው ... ሁላችሁም በፀጥታ ተቀመጡ ስወጣላችሁ ስድድቡንም ሆነ ማባረር መባረሩን
ትቀጥላላችሁ፡፡
ልጅ

ቆይ ከዛ በኃላ ሴተኛ አዳሪ ሆነች

መርማሪ

አልሆነችም .... ባስቀመጠላት 20ሺ ብር አዲስ አበባ መጥታ ንግድ ለመነገድ ሞከረች ከዛም አንዲት አነስ
ያለች ጫት ቤት ከፍታ መስራት ጀመረች

መርማሪ

/ወጣቱን እንዲነሳ ያዘና ልጅ መጥቶ እንዲቀመጥ ያደርጋል /

መርማሪ

መቼም ይቺን ሴት ታውቃታለህ ...

ልጅ

አቃታለው በእርግጠኝነት ግን እስካሁን ካወራሁት ሴት ጋር ምንም ግንኑነት የላትም ይቺ ሴት የህይወት ታሪኳ


ሌላ ነው ነግራኛለች

እናት

እስቲ ዝም በል እና ምታቃት ከሆነ ያረካትን ስማ

መርማሪ

ጫት ቤት ከፍታ በምትሰራበት ግዜ ደንበኛዋ ሆንክ .... ባልሳሳት ከቤት ተጣልተህ ዱርዬነትህ አስችግሮ የዛሬ
አመት አካባቢ ከቤት ተባረህ ነበር

አባት

ማን ያባረረው እራሱ ጥጋቡን አልችል ብሎ ወጣ አንጂ

መርማሪ

በዛን ወቅት ቤቷ ገባህ አብረን ሰርተን እናድጋለን ብለህ ጓደኛችህን ሰብስበህ የጫት ቤቱን ገበያ አደራህ ...
እሷም የሚወደኝ የሚያግዘኝ ሰው አገኘው ብላ አምናህ መኖረ ጀመረች ትንሽም እንደቆያችው አረገዘች

እናት

እግዜዬ ማህረን ክርስቶስ ..... ከዚህ ከኔ ልጅ ነው ያረገዘችው ......


መርማሪ

ማርገዟን ስታውቅ እድታስወርድ ተጨቃጨክ እንቢ ስትልህ የ6ወር እርጉዝ እያለች ጥለሀት ወደ ቤት ተመለስክ
የጫት ቤቱም የመሰረትካቸው ደንበኞች አንተን ተከትለው ቀሩ ገቢያውም ቀዘቀዘ አንድ ቀን ደንቦች መጡና
ቤቱን አሽገው እሷን ወደ እሰር ቤት ወደዷት

ልጅ

እንደታሰረች እኔ አላውቅም

መርማሪ

ብዙም ሳይቆይ መውለጀዋ ሲደርስ ተፈታች ወለደች ልጇን ይዛ ልመና ወጣች ከልጅ ጋር በረንዳ ላይ ብዙ
ተሰቃየች

ልጅ

እኔ ይህን ሁሉ እንደሆነች አላውቅም

መርማሪ

ልጅ ጥለህባት ስትሄድ ምን እንደውትሆን ጠብቀህ ነበር

እናት

አንተ እርኩስ ልጅህን ... የልጅህን እናት እንዲህ አርገህ ግፍ የምትሰራ አውነት አንተ የኔ ልጅ ነህ

መርማሪ

አይፍረዱ እናት .....

ልጅ

ጉርምስና ነው ... እኔ እንዲህ ትሆናለች መች አልኩ .. በዛ ላይ ስራ ነበራት እኮ ልጁን እፍልገዋለው ብላ


ነው .....

አባት

አጠፋህ ልጄ ዘር ወዴት ይጣላል

ልጅ

እሺ አሁን የት ነው ያለችው
መርማሪ

ሰማይ ቤት ገነት ውስጥ

እናት

ልጂስ

መርማሪ

ልጇ ልመና ላይ እያለች በጠና ታመመባት በኃላም አጠያይቃ አንድ እናቶችን እና ልጆችን የሚረዳ በጎ አድራጎት
አለ ብላ ፈልጋ አግኝታ ወደዛ ሄደች

ልጅ

እኔ ልሙትልሽ ...... የት ላግኝሽ አሁን

መርማሪ

አሁን ይህንን ቦታ ለእናት ልቀቅና ሶፋ ላይ ሄደህ አልቅስ

እናት

/በደመ ነፍስ ከመቀመጫዋቸው እየተነሱ/ ብቻ የኔ ልጅ እኔ ብቻ እዝች ልጅ ነፍስ ውስጥ እንዳታስቆጥረኝ

/እናት መጥተው ይቀመጣሉ መርማሪው ፎቶ አውጥቶ እናት የው ፊት ያስቀምጣዋል እናትየው ፎቶውን


አንስተው እያዩ አንባቸው ይወርዳል /

መርማሪ

ሊሞት እያጣጣረ ያለውን ልጇን ይዛ እርሶ ባቋቋሙት የህፃናት እና እናቶች መረጃ ጣቢያ ሄደች ... አንቺ ሰርተሸ
ማደር የምትችይ ወጣት ነሽ የትም ስትንዘላዘይ ያመጣሽውን ዲቃላ ይዘሽ ሂጂ ብለው ስድበው አባረሯት

ሴት

ለምን እማዬ ለምን ........

መርማሪ

በቦታው ደርሶ እናትየውን ስታይ በፎቶ አይታቸው ያስረገዛት እናት መሆናቸውን ስታውቅ እንዲሁም መጀመሪያ
ከስራ ያባረራት ሰውዬ ሚስት መሆንዋን ስትለይ እሷም ስሜታዊ ሆና ሳትናገሮት አትቀርም

እናት
እሰቲ ተወኝ እስቲ ተወኝ የኔ ልጅ

መርማሪ

መጀመሪያ ቦታ ለግዜው ሞልቷል ስትባል በንዴት ሰውን እየገደላችው ሀጢያታችሁን ለመሸፈን የተቸገሩ
መርጃ ብላችው እግዜርን ምታታልሉ አይመስላችሁ አለችዋለች ተናደው ውጪልኝ አሏት ... ይሄ የእርሶ ልጅ
ነው ቢፈልጉ ያድኑት ካልሆነ እግዜር ያለለትን ይሆናል ስትል አይ የኔ ልጅ ካንዳንቺ አይነቱ ባለጌ ወራዳ
ተያይቶም አያቅ ብለው በዘበኛ አስይዘው እንደዛ ሊሞት እያጣጣረ ያለ ህፃን እያዩ አባረራት

እናት

እኔ መች አወኩ..... ቦታውም እኮ ሞልቶ ነበር

መርማሪ

ቦታ ቢያጡ ገንዘብ አላጡም ቢያንስ ለልጇ መታከሚያ የሚሆን ትንሽ ብር ቢሰጧት ልጇ እንድታቀፈችው እጇ
ላይ በረሀብ እና በበሽታ አይሞትም ነበር

ልጅ

እዩ ልጄ እዩ ....ወይ ካፌ

መርማሪ

ከዛም በኃላ ሀዘንና ለቅሶ ብዙም ሳያቆያት አንድ ለነፍሱ ያስጠጋት ሽማግሌ ሰውዬ ትንሽ ክፍል ውስጥ ሞታ
ተገኘች

እናት

አንተ ይህንን ሁሉ አንዴት አወክ

መርማሪ

የኔ ማወቅ ነው ወይስ የናንተ ህሊና ፍርድ ነው ለጥያቄ መቅርብ ያለበት ዋናው ጥያቄ አሁን የተጠየቃችሁትን
ሁሉ አርጋችሃል አላረጋችሁም

ሁሉም

/አንገታቸውን አቀርቅረው መልስ መስጠት ያቅታቸዋል /

መርማሪ
እንግዲያውስ የዝችን ልጅ ህይወት የቀጠፋችሁ አስቃይታችሁ የገደላችሁ ሁላችሁም ናችሁ ሁላችሁም በነፍስ
ማጥፋት ወንጀል ተከሳችሃል

ሁሉም

ይንጫጫሉ.............

መርማሪ

እኔ ጨርሻለው አሁን የፈለጋችሁት ቦታ መደወል የፈለጋችሁትን ማድረግ ድግሳችሁን መቀጠል ትችላላችሁ


እኔ እናንተን የማስሪያ ትዕዛዝ ይዥ እመለሳለው

/መርማሪው የማናቸውንም መልስ ሳይጠብቅ ይወጣል /

/ቤቱ በፀጥታ ይዋጣል የሚያወራ ይጠፋል /

አባት

ግን ሁላችንም ያየነው ፎቶ አንድ አይነት ባይሆንስ

ወጣት

አይታችሁ ከሆነ ከተለያየ ኪስ ነበር ፎቶ ሲያወጣ የነበረው

እናት

ለምን ለየብቻ እየጠራ አሳየን ... ለምን አንድ ላይ አልጠየቀንም

ልጅ

የእውነታችሁን ባልሆነ ..... ልጅቷ እና ልጄ እኮ በእኔ እራስ ወዳድነት ሞተዋል

ሴት

ወዳድንም ጠላንም ፎቶ ተለያየም አንድ ሆነም ሁላችንም ወንጀሉን መፈፀማችን አናምናለን ...

አባት

ስልክ አንስቶ ይደውላል ስልኩ ይጠራል / አሎ ወንጀል ምርመራ ነው

ስልክ

አዎ......
አባት

እባክህ አዛዡን አገናኘን ... የዳላስ ሆቴል ባለቤት ነኝ

ስልክ

እንዴት ዋሉ የተከበሩ ምነው ችግር አለ የምረዳዋ ነገር ካለ

አባት

አዠዡን አገናኘኝ

አዛዥ

አለቃዬ እንዴት ሰነበትክ

አባት

እዚህ እኛ ሰፈር በሞተችው ሴት ጉዳይ መርማሪ ወደ ኔ ቤት ልከህ ነበር

አዛዥ

እረ በፍፁም ... ደብዳቤ ፅፊ እራስሸን ላጠፋች ሴት ምን ብዬ ነው አንተ ጋር ምልከው ሆቴልህ ውስጥ እራሷን
አላጠፋች ..... ቢሆንስ እኔ እመጣለው እንጂ እንዴት አንተን ወዳጄን ለመርማሪ አሳልፌ አሰጣለው

አባት

አመሰግናለው ... ደውልልሀለው

አዛዥ

ችግር አለ ሰው ቢላክ

አባት

እንደው ሁሉም ሰላም ነው ... ለቀብር ስነስርአትዋ ሆነ ለማናቸውም ነገር ወጪውን ለመሸፈን
ፍቃደኛ ነኝ

አዛዥ

እስካሁን እኔ ነኝ ያለ ቤተሰብ ባለመኖሩ መንግስት እንዲቀብራት ሊወሰን ነው

አባት
ሰላም ዋል

/ስልኩ ይዘጋል /

አባት

ቤተሰብ ስሌላት መንግስት ሊቀብራት ነው

እናት

ቢያንስ አምጥተን በሰላም እንድትሸኝ እናድርግ ቀብሩን እናስፈፅም

አባት

በፍፁም አይሆንም ገዳይ ሲፀፀት ይኖራል እንጂ ቀብሯን አሳምሮ ከህሊና ጠባሳው አይድንም

ወጣት

አንድ ያስክሬን ሳጥን ሻጭ ያለውን አስታውሰከኝ ... ባጋጣሚ ሄጄ የሳጥን ዋጋ ስጠይቀው ከ200,0
00እስከ12,000 አለ አለኝ ..የሁለት መቶሺ የሚገዛ አለ ስለው .... ሰውየውን በቁሙ ይገሉትና ዞር ብለው ሳያዩ
ይኖሩና የሞቱ ቀን መጥተው በውድ ዋጋ ገዝተው ቀብሩን የሚያሳምሩ ብዙ ሀብታሞች አሉ፡፡ብሏን .... እነሱን
እንዳንሆን

ሴት

ቀለበትዋን አንስታ ...ለማውራትም አቅም አለህ ለመራቀቅ ቀለበትህን ይዘህ ውጣልኝ

ወጣት

የኔም ያንቺም ግፍ በዝች ሴት ላይ እኩል ነው ... ሁላችንም እስክትሞት ታግላን የቻልነውን ያህል አንቀናታል

/ወጣት ቀለበቱ አንስቶ ይወጣል /

/ሄጄ እራስዋን አልቅሼ ልሰናበተው/

ሴት

ሁላችንም ሀጢያታችን ግፋችን ይከታለያል ክፋቱ መቼ ዋጋ እንደሚያስከፈለን እናውቅም .... አባዬ ምናለ
ባታባርራት ኖሮ ይሄኔ ሁላችንም ከዚህ መቅፀፍት ተርፈን ነበር

እናት

ምናለ ብሰማት ኖሮ ሁላችንም ከዚህ ሀጢያት አነፃችሁ ነበር


/በር ይንኳኳል ይገባል /

ሰው

እላይ ሰፈር የሞተችዋ ሴት ስሞት ይሄ ዳየሪ ለእርሶ እንዲሰጥ ብላ ተናዛለች

አባት

/ሲቀበሉ ያልቃል /

..

You might also like