You are on page 1of 2

አላውቃትም

እድሜያቸው ገፋ ያለ የደስ ደስ ያላቸው ፂማቸውና ጉራቸን ጥጥ የመሰለ አባት የአስፓልቱን መንገድ ጥግ ይዘው፣ስስ ጋቢያቸውን መስቀለኛ
አጣምረው ፣ከዘራቸውን በግራ እጃቸው እየተመረኮዙ ቀስ ብለው ይራመዳሉ። በአፋቸው ፀሎት ይሁን ሌላ ያልታወቀ ነግር እያነበነቡ ነው። አብደው
ነው እንዳይባል የለበሱት ልብስ ንፅህናው እና ንጣቱ እንኳን አብደዋል የቸገራቸው ናቸው ለማለትም አያስደፍርም። እሳቸው እያለፉበት በሚገኘው
መንገድ ጥግ ጥጉን መሰረቱን ይዘው አልፎ አልፎ ጥንድ ጥንድ ሆነው የተቀመጡ ፣ መሄጃ የጠፋቸው ጎረምሶች አለፍ ሲል ደሞ ኑሮ የከበደው
ወጣት ብቻውን ተቀምጦ ያለቀች ሲጋራውን እያጨሰ አላፊ አግዳሚውን ብሎም መኪናዎችሁን በተከዘ አስትያይት ይመለከታል። አባታችንን
ጥንዶቹም ሆኑ ጎረምሶቹ እራሳቸው ጨዋታና ፌሽታ ተይዘው ያስተዋላቸው አልነበረም። አልፎ ብቻውን የተቀመጠው ወጣት ግን ሊታዩት ከቻሉበት
መንገድ ጀመሮ ምን እያሉ እያወሩ እንደሆን በአግራሞት እየተመለከታቸው አጠገቡ እስኪደርሱና እንስኪሰማቸው በጉጉት እየጠበቀ ነበር። አጠገቡም
ሲደርሱ ግን ሊሰማው የቻለ ነገር አልነበረም። አልፈውት ሄደው ከአሁን አሁን ጮክ ይላሉ ብሎ የመስማት ጉጉቱ አይሎ እያጨሰ የነበረውን ሲጋራ
ጥሎ ከጀርባቸው ይከተላቸው ጀመር። እሳቸው ያስተዋሉትም አይመስለም። ከንፈራቸው እያነበነቡ መንገዳቸውን ቀጠለዋል። እሱም ከጀርባቸው
እየተከተለ ሳያሰበው መዳረሻቸው ደርሰው ሲቆሙ አብሯቸው ቆመ። የደረሱበት ጋረ ቆም በለው ጣቶቻቸውን መስቀለኛ አድረገው ወደ ግንባራቸው
ከዚያም ወደ ደረታቸው ሲያወርዱ የመጡበት ግራ ገብቶት ቀና ሲል የቆሙት ቤተክርስቲያን ደጅ መሆኑን አስተዋለ። ምን ያህል ርቀትና ሰዓት
እንደተከተላቸው እንኳን ማስተዋል አቃተው። መሳለማቸውን ጨርሰው ወደውስጥ ሊገቡ እንደሆን ሲያውቅ እስከአሁን የተከተለበትን ምክኒያት
ሳያገኘው መቅረቱ እንደሆነ ሲሰማው እንደምንም ከበሩ ሳይርቁ ለማናገር ወሰነ።

“ አባባ” አላቸው። በድጋሚ አባቴ ብሎ ሲጣራ “አቤት” ብለው ዞሩ። “አቤት የኔ ልጅ ምን አልከኝ?’ አሉት ወጣት መሆኑን ሲያውቁ የአባትነት ፍቅር
ባዘለ ድምፅ። እንዴት እንደሚጠይቃቸው እና ምን አልባት ጥያቄ ቢያበሳጫቸውን ብሎ ስለሰጋ እንዴት እንደሚጀምር ግራ በመጋባት ስሜት ቆሞ
ሲያያቸው እንደጨነቀው የተረዱድ አባት ወደርሱ ጠጋ አሉና “ምነው የኔ ልጅ ምንሆንክ? ግራ የተጋባህ ትመስላለህ።”አሉት።

“አይ አይደልም እንደው አንድ ጥያቄ ልጠይቆት ነበር ስከተሎት የነበረው። እና ምን አልባት አስከፋዎት ይሆን ብዬ ሰጋሁ >’ አለ የሞት ሞቱን

“ኧረ የምን ማስከፋት የኔ ልጅ ከቻልኩ እመልሳልው ያልዚያም አላውቀውም እልሃልው።” ብለው መለሱለት

“ክቅድም ጀመሮ ያየየሆት ነበር እዚ እስኪደርሱ ድረስ አፎት ዝም አላለም። የሚሉትን ለመስማት ብሞክርም አልሰማም አለኝ። ችግር ይሆናል
እንዳልል የሚቸግሮት አይነት አባት አይመስሉም።” ብሎ ተነፈስ።

ፈገግ አሉለት ለዚ ነው ይሄን ያህል በሚል አይነት አስተያየት እያዩት። “ አይ የልጅ ነገር ለዚሁ ነው እንዲህ ቁና የተነፈስከው። እዛው እኮ አቁመህ
ብጠይቀኝ በመለስኩልህ ነበር። እንዲያው ለጠያቄህ መልስ እያወራሁ ያለሁት እውነት ብለሃል ቸግሮኝም አይደለም በሞላ ቤት ልጆቼ እያሉ ምን
ሊቸግረኝ ብለህ።”

“እና ምን ነበር የሚያወሩት?” አላቸው ወጣቱ። በጣም መጓጓቱ ቢያስገርማቸውም ለመናገር ግን አልተግደረደሩም። “እኔማ ወደ ቤተስኪያን ስመጣ
መንገድ ላይ አይምሮዬ እንዳይሰረቅ እና ሌላ ነገር እንዳላስብ ከፈጠሪ ጋር እየወራሁ ነው የምመጣው።” አሉት

ሲናገሩ ድምጻቸው ውስጥ የሚሰማው እርጋታና ትህትና ከሳቸው አልፎ ለሚያወሩት ሰው ይጋባል። ግርማ ሞገሳቸው የሚወደድ አይነት ነው። ከላይ
የለበሱት ስስ ጋቢ ጋቢ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር አምላክ በስሱ የደረበላቸው ነጭ የትህትና ክንፍ ይመስላል። ወጣቱ ልጅም የመለሱለት ቃል ግራ
እንደገባውና እባክዎ ማብራሪያ ስጡኝ በሚል ፊት አይን አይናቸውን እያየ ፊት ለፊታችው እንደቆመ ነው። “ ያልኩህን አልሰማኸኝም የኔ ልጅ ?” አሉት
ዝምታው ግራ ቢገባቸው።

ከሃሳቡ ባኖ “ ኧረ ሰምቻለው ግን እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር ሊነጋገሩ ቻሉ ብዬ ነው። ያውም መንገድ ላይ። ምን ብለው ነው የሚያናግሩት ? ግን
እግዚብሄርን እንዴት አወቁት?” አላቸው። ግራ ያጋቡትን ጥያቄውች እያከታተለ።

ለስለስ ያለ ፈገግታ ፈገጉና “አይ ይኔ ልጅ የዋህ ነህ። እግዚአብሄርን እማ እኔ አውቀዋለው ማለት ከባድ ነው። እኔ አላውቀውም እሱ ነው
የሚያውቀኝ።”አሉት

ወጣኡ ልጅ ይበልጥ ግራ ተጋባ። “ካላወቁት እንዴት መነጋገር ይቻላል ? “ በልቡ የተናገርው መስሎት በአፉ ግን ተንሾካሽኮ ኖሮ “ ምንው ምን
አልክኝ?’ አሉት ፊት ለፊታቸው የቆመው ውጣት ግራ መጋባት የተጋባባቸው ይመስል። “እ እ .. አይ እንደው ግራ ሰለገባኝ ነው አባቴ። እኔ
አላውቀውም ካሉ እንዴት ያነጋግሩታ? ደግሞስ ካላወቁት እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን መጡ?” አላቸው። ጥያቄው ከልቡ እንደሆነ ያስታውቃል። ይሄን
የተረዱት ትሁት አባት በሚገባ ማብራራት እንደሚገባቸው አውቀው በሰፊው ለመጫወትና ለማብራራት እንዲመቻቸው ወደ አንድ ዛፍ ጥላ ስር
እንዲሄዱ ወሰኑ። ከዛ በፊት ግን “ኦርቶዶክስ ነህ የኔ ልጅ?” ብለው ጥያቄ አቀረቡ።እንግባ እና ተቀምተን እናውራ ከማለታቸው በፊት ክርስቲያን
መሆኑን ለማረጋገጥ ብለው አንገቱን ቢመለከቱ ማህተም ስላጡበት ለማረጋገጥ ፈለገው ነበር። ያልጠበቀው እና እሱ ከጠየቀው ጋር የማይሄድ ጥያቄ
በመጠየቃቸው ግራ ቢጋባም ለጥያቄው መመልስ ነበረበትና ”አዎ ነበርኩኝ አሁን ግን ነኝ ለማለት ያስቸግራል።” አላቸው።

ግድ የለም እዛች ዛፏ ስር ተብቀኝ ተሳሜ ልምጣና በሚገባ እንጫወታለን። ብለውት ሊሳለሙ ወደ አውደ ምህረቱ ሲጠጉ እሱ እንደታዘዘው ወደዛፏ
ስር ሄዶ ካገኘው ድንጋይ ላይ አረፍ አለ። እሳቸው እየዞሩ ሲሳልሙ እሱም አብሯቸው በአይኑ እየዞረ ይከተላቸው ጀመር። በደርባ በኩል ሄደው ከአይኑ
ሲጠፉ ደሞ ጊቢውን ሰላሙን ጸጥታውን እያስተዋለ በአግራሞት ይመለከታል። ምንም እንኳን በልጅነቱ የሚያውቀው አይነት ጊቢ ቢሆንም እንደአዲስ
ዙሪያ ገባውን እየቃኘ በአድናቆት እና በመገረም ያሰተውለው ጀመር።

ዞረው ተሳልመው ወጣቱ ወደተቀመጠበት ቦታ ሲመጡ ተመልክቶ ቆሞ ይጠብቃቸው ጀመር።

You might also like