You are on page 1of 2

ጭውውት አንድ

(ሽምግል ያሉ ሰው ወንበር ላይ ተቀምጠው ሬድዮናቸውን ያስተካክላሉ። በወጣትነታቸው ዘመን ፈርጣማ


እንደነበሩ ቁመናቸው ያስታውቃል። ከራሰ በራነት የተረፈ ፀጉራቸውን ሽበት ወርሶታል። በመድረኩ ሌላ ጥግ
ባለቤታቸው ተቀምጠው ተክዘው ይታያሉ። እርሳቸውም አርጅተው ጎብጠዋል። ነጠላቸውን ይቋጫሉ።
በየሆነ ደቂቃው ከንፈራቸውን ይመጣሉ። ራዲዮኑ ሲንሿሿ ቆይቶ አንድ ጣቢ ያ ላይ ያርፋል። ተግ ብለው
ማዳመጥ ይጀምራሉ ሁለቱም።
ራዲዮኑ ውስጥ ያለው ጋዜጠኛ - ይህ የአብዮታዊት ሶሻሊስት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ድምጽ ነው።
ሊቀመንበር ማኦ ዜዱንግ ከኩባው ፕሬዝደንት ጋር ባደረጉት ውይይት ምክንያት በሩስያዋ ዋና ከተማ
በተፈጠረው የመንገድ መዘጋጋት ነገ በመላው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የሶሻሊዝም እንቅስቃሴ በመደገፍና
የአሜርካ መራሹን አቆርቋዥ ቡርዧ ካፒታሊስት ሥርዓት ለማውገዝ አብዮት አደባባይ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ
እንደሚካሄድ ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለ ማርያም አስታውቀዋል። በዕለቱም ከዩጎዝላቭያ፣ ከምስራቅ
ጀርመን እና ኸሊብያ የሚመጡ የወንድም ሃገራት ላባአደሮች ትርኢት እንደሚያሳዩ ይጠበቃል።
በተያያዘ ዜና አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ አህያ በር እየተባለ በሚጠራው ቦታ በሕገ ወጥ መልኩ
አህዮቻቸውን ሲያደራጁ የነበሩ አህያ ነጂዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወሰደ። የአህያ በር ወረዳ አስተዳዳሪ
የሆኑት ጓድ ማበሉ የትናየት እንደተናገሩት አብዮታችን በማንም ፋንድያም ውርንጭላና አድሐሪ ምክንያት
አይደናቀፍም። ይህንንም ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እንሰራለን ብለዋል።
ይህንን አብዮታዊ እርምጃ በማክመልከት 'የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት ያልታደለች
ፍየል ሁለት ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች።' የሚለውን አብዮታዊ ዜማ አዳምጠን
እንመለሳለን። "
ወይዘሮ - አበስኩ ገበርኩ! አበስኩ ገበርኩ! እንዴት ያለ ሰው በላ ዘመን ላይ ደረስን አንቱ! እንደው አንደኛውን
ባይነካኩት ይሻል ነበር!
አቶ - ምኑን? (ጀርባቸውን ሰጥተው ጀመራት ደግሞ ዓይነት ይገረምሟታል)
ወይዘሮ - አብዮቱን! ይኸው የማይነካ ነካክተው አፈነዱት! ኋላ ማን ይመልሰው! ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆመው
ማውረድ ይቸግራል አሉ።
አቶ -አንገበገብሽኝ አለ ዘፋኙ (ይላሉ እንደማጉረምረም)
ወይዘሮ - ምንምን?
አቶ - ሰለቸኝ መረረኝ እኔን
አልቻልኩም እንደምን ልሁን
አልቻልኩም ንዝንዝሽን አልቻልኩም
ምን ልሁን እኔ ለእኔ አልሆንኩም!
(በራሳቸው ዜማ ያዜሙታል)
ወይዘሮ - ኤድያ የዘንድሮ ዘፈን ደግሞ ከጩኸት ውጪ አያውቅም።
አቶ - የት ሰምተሽ የምታውቂውን። ራድዮኑ እንደሁ የእኔ። አለ አሰኔ አንደበቱም አይላወስ
ወይዘሮ - አውቃለሁ እንጂ ምነው አላውቅ። ዋይ ዋይ ሲሉ ነው የሚል አለ አንድ። ጩከኸቴን ብትሰሙ ይኸው
አባት አቤት እላለሁ የሚለው አለ ይበሉ። ስንቱን ስንቱን ቆጥረን እንችለዋለን።
አቶ - አንቺ ሴት በይ አድቢ! በዘመኑ አንድ በጎ ነገር ቢገኝ እርሱንም ጩኸት ብቻ ትላለች እንዴ ሆሆ
ወሮ - ጩኸቱን ርንዳይሆን በጎ ነገር የሚሉት። ይሄ ራድዮን ሳያበላሽዎት አልቀረም በመቁረቢያ ዘመኑ!
አቶ - አድቢ ብያለሁ አድቢ። ደግሞ ሙዚቃውስ ጨዋታውስ ብትዪ... ይሄ ማነው የሚሉት ማንጎ ነው
ታንጎ...ምን ሊወጣለት ነው።
ወሮ - እርስዎ ደግሞ መልሶ እንደጎረምሳም ያደርግዎታል ልበል? (በማሽሟጠጥ)
አቶ - ምን ያንሰኛል በይ? ሙች!
ወሮ - ኧረ እንደው ነገሩን ብዬ ነው እንጂ
አቶ - ድሮም ቢሆን አንቺን እንዳትላወሺ አድርጌ በፍቅር የጣልሁሽ በዚህ የመኳንንት ዘር መልኤ እና በጨዋታ
አዋቂነቴም አይደል። እድለኛ ነሽ እኮ በውነቱ! እግዚሃርን አመስግኚ። ሙች! እንጂ እንደሰዉማ ቢሆን ያ ሁሉ
ኮረዳ ሲሻማብኝ መች አንቺ እጅ ይጥለኝ ነበር።
ወሮ - (ከት ብለው ይስቃሉ።አፋቸውን በነጠላ ሸፍነው) እኮ እርስዎ
አቶ - እንዴታ
ወሮ- እኮ እርስዎ የመኳንንት ዘር፤ ኮረዶች ሁሉ የሚሻሙብዎት
አቶ - ምን ትላለች!
ወሮ - ማነው የመኳንንት ዘር ያደረግዎት! አጎትዎ የአባቴ ጭሰኛ አልነበሩ እንዴ ኋላ ዳሩልኝ ብለው ሽማግሌ
ቢልኩአባቴ ጥንብ እርኩስዎን አውጥተው ሲመልስዎ አይደል ጠልፈውኝ ከሃገር የጠፉት። ሆሆ...
አቶ - በርግጥ ጠልፌፌ ነው ያገባሁሽ። ነገር ግን ይሄ ጭሰኛ ያልሽው ነገር አይዋጥልኝም። ዘመን ተቀይሯል
አሁን። አሁን እኔ ላብ አደር አንቺ አቆርቋዥ ቡርዧ ነው የምንባለው።
(ለአፍታ ጸጥ ይባባላሉ)
አቶ - (ከንክኗቸው ኖሮ በምሬት እየተንገፈገፉ) ደግሞ ብጠልፍሽስ ፤ ደም ግባቴን አይተሽ ወደሺኝ ፈልገሽ
አይደለ እንዴ የከረምሽው... ለምነሽኝ! በስንት አማላጅ በስንት አሌ ባይ
ወሮ - ኡኡቴ! እኔ እርስዎን ስለምን ይታይዎ! ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል አሉ !
እንደው መልክዎ ትንሽ ተጉሬዛ መለስ ማለቱን አይቼ ነው እንጂ አሁን ለእርስዎ ደም ግባት የሚል ቃል
ይነገራል?
አቶ - አንቺ ሴት አድቢ ብያለሁ አድቢ። ቀድሞ ጅብ! ለጥቆ ጉሬዛ! ስደቢው ብሎ የላከሽ አለ እንዴ ዛሬ! ጉድ
እኮ ነው! ደግሞ ዋናው የውስጥ ውበት ነው። አዎ። የውጪውንማ አየነውከእርጅና ጋር ጣጥሎ ሲሄድ! ታድያስ!
ወሮ - እኔም እርሱኑ ብዬ ነበር የከረምሁት! ኋላ ሲታይ ግን ቁመት እንጂ የውስጥ ቁመት የሚባል ነገር የለ።
መቼም አፍዎን ሞልተው ውጪው ምን ያደርጋል! ውስጤ ረዥም ነው ምናምን አይሉኝም።
አቶ - ኧረ በጫጭቁናይቱ ማርያም ተዪኝ አንቺ ሴት!ገና ለገና አርጅቷል! ምንም አያመጣም! ብለሽ ነው
አይደለም የምትነዘንዢኝ! ተይ አትነካኪኝ። ሰይጣኔን አታምጪው!
ወሮ - ምን ሊሆኑ?
አቶ -ምን ሊሆኑ?
ወሮ - አዎና እስኪ ዛሬ እንኳ ተሳክትዎሎት እንደወንዶቹ ደብድበው ያስጩሁኝና ወንድ ይውጣዎት።
አቶ - እኔን ወንድ ይውጣዎት?
ወሮ - አዎ
አቶ - ምን እንደማደርግ ተመልከቺ! (መዝፈን ይጀምራሉ።የጥላሁንን አልቻልኩም ወይም ጩኸቴን
ብትሰሙት)
ወሮ - (ድንግጥ ብለው)ኧረ አንቱ ሰዓት እላፊ ነው ሰው ተኝቷል! በውድቅት ሰው አይበጥብጡ!
አቶ - ምን አገባሽ ምንም አታመጣም አላልሽም።
ወሮ -ኧረ ይተዉ ሰው ምን ይላል? ለጎረቤት እኮ እየደበደብኩዎት ነው የሚመስለው!
አቶ - (እየዘፈኑ መጨፈርም ይጀምራሉ። እንደዛርም ያደርጋቸዋል)
ወሮ - አንቱ ዛርዎ ተነሳብዎ መሰል...
(ይኼኔ ከዛራም ጭፈራቸው ድንገት ተገትው ይወድቃሉ። በዚህ ጊዜ ወይዘሮዋ ኡኡ ኧረ የሰው ያለህ እያሉ
ራሳቸውን ይዘው እየጮኹ ይወጣሉ)
አቶ - (እስክትወጣ ይጠብቁና ከወደቁበት ተነስተው ልብሳቸውን እያራገፉ ያስተካክላሉ። ከዚያም ወደሄደችበት
ቀኩል እያዩ በማሽሟጠጥ) የታባሽ... እንግዲህ ማደርያሽን ፈልጊ... ማን ጅብ እንደሆነ ይለያል አሁን! 'የፍየል
ወጠጤ ልቡ ያበጠበት' አለ ዘፋኙ!
(በሌላኛው በኩል ይወጣሉ)
(መብራት ይጠፋል።)

You might also like