Professional Documents
Culture Documents
ተማሪና መምህር-
ተማሪና መምህር-
እኔ እየረበሽኩት እሱ የሚመክር
ታዛዥ ባለፀጋ
ግን ይህ ሁሉ የኖረው ባለፀጋ ሳለ
እኔና ዘመኑ
አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ አንድ ትልቅ አባት ጺማቸው ነጭ ፀዓዳ የሆነ ከእርግናቸው የተነሳ ግርማቸው የሚያስፈራ ፣
ንግግራቸው የአዘነውን ሰው የሚያረጋጋ ፣ ከአንደበታቸው የሚወጡት ቃላት የታመመች አንደበትን የሚያክሙ ጽኑ
መድኃኒት ነበሩ ፣ ታዲያ ይህ አባት ድንገት ከአጠገቤ ከተፍ ብለው ይመጡና ሰላማደርክ ልጄ አሉኝ በአባትነት ለዛ፣ አ አባ
ደህና አደሩ አልኩ አፌ አየተሳሰረ ፣ልጄ ምን ሆንክ አይዞህ አትፍራ አሉኝ በሚያጽናና ቃላቸው እሺ አባ ምን ልታዘዝ
አልኩ አሁንም በፍርሃት መንፈስ ፣ ልጄ እኔ የመጣሁት ጥያቄ ልጠይቅህ ነው አሉኝ ልብን በሚያረሰርስ ቃላቸው ፣ልጄ
ለምን እስካሁን ተኛህ አሉኝ ፣ አይ አባቴ አሁን እኮ ገና ጧት ደግሞ የዘመኑን ነገር ያውቁታልጭንቀቱ ቀን ከሌት
የሚያስተኛ አይደለም ፣ ግን አባ ታዝበውታል ምን አይነት ዘመን እንደደረስን ሰው ከሰው ጋር ተግባብቶ እማይኖርበት ፣
ፍቅር እሚባል ጠፍቶ ሰው አርስ በእርሱ ካልተጣላ መኖር የማይችል የሚስልበት ፣ አባ አሁንስ ሳስበው ዘመኑ ያረጀ
ይመስለኛል ፣ አልኩ መናገር በማይችለው በዚህ ኮልታፋ አንደበቴ ፣ ልጀ መልካም መስራት ቢያቅትህ ስህተትህን ለምን
ታሳብባለህ ፣ ተማሪ ስትሆን ከማንበብ ይልቅ ሁሌ ከመዝለል በቀር እራስክን ለማሻሻል የማትጥር ፣ የመፈጠርህ አላማ
ሰወችን መርዳት ሲሆን አንተ ግን እኔ ብቻ ይድላኝ ብለህ የምታስብ ፣ እውነትን እረግጠህ ሀሰት ማውራት የሚቀናህ ፣
ለሰዎች መልካም ነገር ከማሰብ ይልቅ ሀሜት የሚቀድምህ የ አንተ ማንነት ባረጀ ቁጥር ትናንት የነበርኩ ዛሬ ያለሁ ነገም
የምኖር እኔን ለምን ፣አረጀ ትለኛለህ ፣ አንተ ያረጀ ስራ በሰራህ ቁጥር የዘመን ሽፋን ይቅርብህ ፣ ልጄ እኔ ትናንት የነበርኩ
ዛሬ ያለሁ ነገም የምኖር የአንተ ታዛቢ ነኝና ምክንያቱ ቀርቶ መልካም ስራ ስራ ሲሉኝ አፈርኩ፣ አዎ አባ ልክ ነዎት
በእርሰዎ እያመካኘሁ እኔ ነበርኩ ያረጀሁ ፣ የፍቅር ጠብታ የሌለው ደረቅ ጭንጫ መሬት የኔ ልብ ነበር ያረጀ ፣ አባ ልክ
ነዎት ንግግሬ እንደ እሾክ የሚኮሰኩስ የኔ አንደበት ነበር ያረጀ ፣ አልኩና ለአባ ተናግሬ መለስ ብየ ሳስበው ለካስ
የምንሰራውን ስራ ከሰው በንሰውረው ከህሊናችንና ከጊዜ አንሰውረውም፣ ጥፋትን ስንሰራ ሰወች ከመውቀሳቸው በፊት
እኛን የኣሚወቅሰን ህሊና የሚባል ታላቅ ዳኛ አለ ብዬ እኔ ያላወቅኩት እርሱ ግን የሚያውቀኝን ዘመን እያሰብኩ ሥራየን
ጀመርኩ።
ሰው
እኔና ዘመኑ
ምንም አልሰራህም