You are on page 1of 4

የችቦዋንየእውቀትእናየእሳትጨ ዋታልቀጥላትእስቲ:

ትንሽእን
ጫ ወት

ያንጊዜማለቴየ5ክፍልተማሪእያለሁ፡

መምህርጌታቸው ስለችቦዋአብራርተው ከነገሩንወዲያእኔበቀጣይአመትችቦውንከአዲስመምህርተቀብዬ


በተማሪው መሀልችቦውንይዤለመዞርከፍተኛጉጉትስላደረብኝማድረግእን ደምችልእናማድረግእን ዳለብኝም ራሴን
አሳምኜነ በር፡
፡በስነጥበብክበብጥሩተሳትፎስለነ በረኝበቀጣዩአመትሀሳቤንለማሳካትአልከበደኝም ነ በር፡
፡ችቦውን
በተማሪመሀልይዤው ዞርኩ፤ ከፍያለስሜትነበረው፡፡በእርግጥ ብቻዬንአልነበረም ይዤው የዞርኩትችቦውንእን ደበራ
ለኔየሰጠኝአዲስትምህርትቤቱንየተቀላቀለው የሒሳብመምህር፡መምህርያሬድከአጠገቤሆኖየችቦውንእሳት
እየተከታተለድጋሜ በተማሪዎችመሀልከኔጋርዞሮነ በር፡
፡በአጀብም ቢሆንግንዋናው ነ ገርያሰብኩትንአሳክቻለሁ፡፡

መምህርያሬድየትምህርትቤቱዘናጭ ወጣትመምህርነ በር፡


፡በሚያደርገው ጥቁርመነ ፅርእናበወቅቱእን ደፋሽን
ይታይበነበረው የሸሚዝኮሌታንሳያጥፉቀጥ እን ዳለበመልበስበትምህርትቤቱማህበረሰብዘን ድበልዩነትይታወቅ
ነበር፡
፡ችቦውንይዤስዞርስላጀበኝመሠለኝከዚህመምህርጋርበቀላሉነ በርየተግባባነ ው፡፡ይህመምህርየ6ኛክፍል
የሂሳብአስተማሪያችንሆኖተመድቦስለነ በር፡
ከሌሎችመምህራንየተለየቀረቤታከዚመምህርጋርነ በረኝ፡
የሚያስተምረንንነ ገርበደን
ብእስኪገባንደጋግሞ ስለሚያስረዳን፡ልክእን ደታላቅወን ድም እያጫ ወተስለሚያስተምረን
ትምርቱንእሱንም እወድነ በር፡
፡በዛላይሲያስተምረንክፍልውስጥ ን ቁተሳታፊነ በርኩ፣የክፍልስራም ሆነ፡የቤትስራ
ሲሰጥ በሚገባነ በርየምሰራው፡እንደውም ጥያቄሰጥቶቀድሞ ለጨ ረሰሶስትተማሪማርክእሰጣለሁካለ
በእርግጠኝነትከሶስቱአን ዱእኔነበርኩ፡
፡ብቻየሌለተመችቶኝነ በር፡፡በፈተናም በዚህየትምህርትአይነ ትምን ም ስህተት
አልሰራም ነ
በር፡
፡እን ደውም ከፈተናበኃላመልስለማረጋገጥ ተማሪዎችከበው ይጠይቁኝነ በር፡
፡ከዚየተነሳ
በመጀመሪያው መን ፈቀአመትበዚህትምህርት100/100ነበርያመጣሁት፡ ፡እንደው ምንም" x
"አልገባብኝም ለማለት
ሳይሆንበጉርሻየሠበሠብኩትነ ጥብከ" x
"በጣም ይበልጥ ስለነበረነው፡፡

ሁለተኛው መን ፈቀአመትተጀምሮየመጀመሪያውንየሂሳብፈተናተፈትነ ንስንወጣ፡እንደተለመደው ከክፍልጓደኞቼጋር


ስለፈተናው ጥያቄዎችእየተወያየን፡ከአንዱጓደኛዬጋርበ3ጥያቄዎችመልሳችንአልተመሳሰለም ነ በር፡
፡በዚህም የተነ

ሁለታችንም የየራሳችንንምልከታእየሰጠንስንከራከርአብረውን ከቆሙ ትጓደኞቻችንአንዱ የኔመልስልክመሆኑን
ደግፎኝተናገረ፡ሁላችንም ወደሱዞርን፡ባን
ጠይቀውም ወደሡ የዞርነ
ው የመልሱንትክክለኛነትእን ዲያስረዳንነ
በር፡

ከአሁንአሁንየመልሱንልክመሆንበደብተርወይመፀሀፋአመሳክሮያሳየናል፡ ፡ብለንስንጠብቅእን ዲህአለን፡

"ትምርትየተጀመረእለት፡ከሒሳብአስተማሪችቦውንየተቀበለው እሱእኮነው፡
፡አስተማሪው የሚያውቀውንያውቃል፡
ትክክለኛው መልስየእሱነው::
" ብሎ፡
፡ወደእኔጠቆመ ፡
፡ሁላችንም እን
ዲህያለመልስስላልጠበቅንእን ደመደናገር
ብለንአየነ
ው፡ ፡

ሌላኛው ጓደኛችንቀልጠፍብሎ "አዎ፡እውነ


ቱንነ
ው፡፡በአን
ደኛሲሚስተርእኮ100ነ
ው ያመጣው፡
፡"አለ፡

የተቀሩትም እየተቀባበሉሀሳቡንአጎሉት፡

"
እውነ
ትችቦውንስለተቀበልኩነ
ው?"በውስጤ ጥያቄተጫ ረ፡

ሲከራከረኝየነ
በረው ጓደኛዬመልሱንእኔልክእን
ደሆን
ኩአምኖ፡በመሳሳቱሆድብሶትእን
ባእን
ባሲለው፡ክርክሩንረስተን
እሱንማፅናናትጀመርን
፡፡ብዙማፅናኛቃልተጠቀምን

"
ገናየመጀመሪያፈተናነ
ው፡በቀጣይታሻሽላለህ፡
፡"አን
ዱይላል፡
፡ሌላው የራሱንእያሰበ፡

"ኧረከዚየባሰ"
X"የገባበትም አለ፡
፡"ይላል፡
፡የቀረውም

"
አንተእኮበህብረተሰብትበልጠዋለህ፡
፡" ይለዋል፡
፡ሁሉም የራሱንቃልያዋጣል፡

ከሳምን ትበፊትህብረተሰብተፈትነ ንስንወጣ መልስመሳሳቴንተረድቼ ሆድሲብሰኝእኔ ንሲያፅናኑኝነ በር፤አንድም ሆድ


ይብሰንየነበረው መበለጥንስለምን ጠላይመስለኛል፡ ፡ማንመበለጥንይፈልጋል?ስለዚህእን ደዚም ማፅናናት ይቻል
ነበር፡
፡በድክመቱላዘነ ው ጥን ካሬውንእያስታወስክታፅናናዋለህ፡የተበለጠበትንበበለጠበትእያስረሳህ ታፅናናለህያው
ማፅናናትለሀዘናችንመርሻማግኘትአይደል፡ ፡በጎደለው ነገርያዘነ ንባለው ነገርጉድለቱንታስረሳዋለህ፡ ፡ከሳምንትበፊት
እኔሳዝንየተፅናናሁትበሂሳብየተሻለውጤትማምጣትእን ደምችል፡አስታውሰውኝነ በር፡፡እሱንም ለማፅናናትጥሩ
የሠራበትንእናስታውሰዋለን ፡
፡በዚመበለጥ ሁሉን ም እንደማይወክል፡እደነ ገርንእናፅናናለን፡፡ለዚሁሉደግሞ የሚያበቃን
በመካከላችንትልቅየፉክክርስሜትስለነ በርነው፡፡የፉክክሩቃናው ለበለጠ ስራየሚያበረታታ፡እን ድናነ
ብበደንብ
እንድናውቅየሚያበረታታነ በር፡፡ን
ፁህየልጅነ ትልቦናችንየሚያስበው እን ዴትብሰራ፡ እንዴትባነ ብ፡እንዴትብማር፡ተሽሎ
ስለመገኘትእን ጂ፡ሌላው ከኛዝቅስለማድረግአናስብም ነ በር፡እንደውም ከዚህየተነ ሳከመምህራኖቻችንአስቀድመን
ስለምን ማረው ነገርእነዘጋጅነበር፡፡ይህንትጋታችን ንየተረዱትየሳይን ስመምህራችንመምህርግርማ ሁሌፈተና
ሲፈትኑንእኛንለማበረታታትቀጣይከምን ማረው/ካልተማርነ ው /የመፀሀፋክፍል1ወይም 2ጥያቄበጉርሻመልክ
ያወጡ ነበር፡፡ያው እነ
ዚያንጥያቄዎችየሰራተጨ ማሪነ ጥብያገኛል፡ ፡እንደዚህያሉየጉርሻጥያቄዎችመፅናኛዎቻችን
ነበሩ፡
፡ጓደኛችን ንለማፅናናትየዚችየጉርሻነ ገርም ተነስቷል፡ ፡ነገርግንማን ም

"ማንያውቃልአን ተልክትሆናለህ፡የእሱመልስስህተትሊሆንይችላል፡
፡"ብሎ ለማፅናናትየሞከረአልነ
በረም፡

ምክኒያቱም የችቦዋነገርአሳማኝነበረች፡

ፈተናው ታርሞ ሲመለስም ውጤ ቱእን ደጠበቅነውነበር፡


፡ውስጤ የቀረችው ጥያቄግንምላሽሳታገኝእን ደውም
እየጠነከረችሄደች፡፡በዚያአመትከሌላጊዜበተለየ የከፍያለውጤ ትአስመዝግቤአጠናቀቅኩ፡ ፡ግንየችቦዋነገርመልስ
አልተገኘለትም ነ
በር፡፡በወቅቱጓደኛዬያነሳው ሀሳብአሳምኖኝስለነበር፡የምርም ችቦዋንበመቀበሌየመጣ እን ጂ፡
ከአልሸነፍባይነትከመነ ጨ ው ጥረትእናትጋትየመጣ መሆኑንለመገን ዘብጊዜመፍጀቱአልቀረም ነ በር፡

አመለካከታችን ፡የተሞክሮዎቻችንእናየልምምዳችንጥገኛነ ው፡፡በህይወታችንእን ደክስተትከሚያጋጥሙ ንነ ገሮች፡


ወይም ከትምህርትእውቀትእናገኛለን ፡
፡አንዳን
ዴም ከልምምድወይም በተደጋጋሚ ካጋጠሙ ንነ ገሮችየምን ገነዘበው
ነገርእውቀታችንላይይጨ መራል፡ ፡በህይወታችንየሚያጋጥሙ ን ንክስተቶችንልን ረዳው እናልን ገነዘበው የምንችለው
ደግሞ በአለንእውቀትልክነ ው፡፡ሠፊእናጥልቀየሆነእውቀትያለው ሰው፡አመለካከቱም የዛኑያክልጥልቅይሆናል፡
እይታው ሰፊይሆናል፡ ፡ያንጊዜእኛከተሞክሮዎቻችንተነ ስተንበሂሳብትምህርትጥሩውጤትማምጣቴችቦውን
ከአስተማሪው የመቀበሌውጤ ትነ ው ብለንአምነንነበር፡
፡ብዙጊዜበህይወታችንውስጥም እን ደዚህበምክኒያትእና
ውጤትየምናስተሳስራቸው ነ ገሮችከእውነታው የራቁሊሆኑይችላሉ፡ ፡በገባንልክትርጉም እን ሰጠዋለን፡የእውቀታችን ን
እናየአረዳዳችን ንሚዛንየሚያዛባወይም የሚነ ቀንን
ቅሌላሀሳብእስካላገኘንድረስያን ኑሀሳባችን ንተቀብለንእና
አምነ ነው እን
ኖራለን ፡
፡እኔም ችቦውንከመምህርመቀበልበተማሪጉብዝናላይተፅኖእን ዳለው አምኜከርሜያለሁ፡ይህን
እምነ ቴንግንጥያቄውስጥ የከተተው 8ኛክፍልከገባንበኃላበነ በርኩበትትምህርትቤትእን ደቀድሞው ትምህርትቤት
ችቦውንማን ኛውም ተማሪሳይሆንከመምህሩየሚቀበለው፡ከትምህርትቤቱየተማሪትራፊክአባልከሆኑትመካከል
ነበር፡እናም በዚህአመትችቦውንከመምህርተቀብሎ በተማሪመሀልየዞረውንልጅከጎበዝተማሪዎችተርታጠብቄው
የነበረቢሆን ም እንደጠበኩትሳይሆንበተቃራኒው በትምህርትእስከዚም ነ በር፡
፡ከነበረኝአመለካከትጋርየሚጋጭ እውነ ታ
፤እንግዲህወዳጄየችቦዋ፡የእሳትእናየእውቀትንትስስርየማወቅፍላጎቴየመነ ጨ ው ከዚህየእውነ ታዎችግጭ ትነ ው፡

የሠው ልጅየማወቅፍላጎቱየሚመነ ጨ ውም በተቃርኖዎችመሀልመኖሩይመስለኛል፡ ፡ከምንውቀው እውነ ታጋር
የሚጋጭ ሌላእውነ ታሲገጥመንአዲስነ ገርለማወቅ፡የበለጠ ስለጉዳዩጠልቆለመረዳትፍላጎትያድርብናል፡ ፡ልክ
አናፂቤትሲሰራውሀልኩንለማያትበተለያየአቅጣጫ ርቆእን ደሚመለከተው፡የእሳቤያችን ንውሀልክለማረጋገጥ
ወይንም ለማስተካከልበሁሉም አቅጣጫ እየ ራቅንትክክለኛው እውነታላይለመድረስእን ፈልጋለን
፡፡በእርግጥ ወደዛ
ወዲዝህእያሉነ ገሮችንለመረዳትየሚደረገው ጥረትአድካሚ ሊሆንይችላል፡ ፡በቅንነትእናበክፍትአእምሮሀሳቦችን
ማሰስእናመመርመርንሊጠይቅይችላል፡ ፡ይሄንአድካሚ ሂደትሰነፎችአይመርጡትም፡ለዚህም እነ ሡ ከቆሙ በትእሳቤ
በተቃራኒያለውንመጋረድምርጫ ቸው ይሆናል፡ ፡በቅንነትእናበክፍትአእምሮነ ገሮችን፡ሀሳቦችንመርምሮእውነ ታው ላይ
ለመድረስከመሞከርይልቅ፡የሌላው ሀሳብበማን ቋሸሽሲከፍም የ ተቃርኖሀሳብአመን ጪ ውም ሆነአራማጆችንአሳዶ
እስከማጥፋትበሀይልአስገድዶበራሱእሳቤግርዶሽውስጥ ለመኖርይፈልጋል፡ ፡የነ
ፍስንየእውነትፍለጋጥያቄ
በስንፍናው ይገታዋል፡፡

የፍልስፍናመገለጫ ው የተለያዩሀሳቦችንበአመክኒያዊእይታመዝኖእውነ ትላይ ለመድረስየሚደረግጥረትየያዘመሆኑ


ነው፡፡በዚህም የተነ ሳብዙፈላስፎችእውነ ታነ
ቱሚዛንየደፋባቸውንከማህበረሰቡወጣ ያለአስተሳሰብይዘው ሲቀርቡ፡
እንደእብድእየተቆጠሩከህብረተሰቡይገለላሉ፡እን ደማህበረሰቡየኖሩበትየእምነትመሰረትእን ዳይናድበመፍራት
የሌላውንሀሳብይገፋሉ፡አልፎም ተደማጭ ነ ትእንዳያገኝየተቻላቸውንሁሉያደርጋሉ፡፡በሃይማኖትበኩልም
ብንመለከተው አን ዳችንንከአንዳችንልዩነታችንጎልቶእንዲሰማንእናመከባበርእን ዳን ችልያደረገንያለመደማመጣችን
ነው፡፡አንድክርስቲያንየሙስሊም ወን ድሙንአስተምሮቢያነ ብእናቢረዳከሙ ስሊም ወን ድሙ ጋርበቀላሉተግባብቶ
መኖርይችላል፡ ፡የሙ ስሊም ወንድሙ ንአረዳድእናአመለካከትለመገን ዘብእንደሱማመንአይጠበቅበትም፡ ፡
ሙስሊሙ ም እን ዲሁየክርስቲያኑንአስተምሮቢረዳበመከባበርይኖራሉ፡ ፡የአን
ደኛው መኖርለሌላው ብርታትእን ጂ ስጋት
አይሆን ም፡፡ነ
ገርግንእምነ ታችንጎደሎ ስለሆነከኛበተቃራኒያለው እሳቤየቆምን በትንመሰረትእን ደሚንደው ይሰማናል፡፡

ስለዚኛው ሀሳብሌላጊዜበሰፊው ተመልሼእን


ጫ ወቸዋለን
፡ወደችቦዋጨ ዋታዬልመለስ፡

የልጁእንደጠበኩትያለመሆንየሀሳብተቃርኖውስጥ ከቶኝስለነ በርችግሬንለመፍታትሁነ ኛሰው እፈልግነ በር፡፡ለዚህ


ጥያቄዬተገቢውንምላሽየሚሠጡኝመምህርጌታቸው ነ በሩ፤ሆኖም ግንየቀድሞው ትምህርትቤታችንከህዝብ
ትምህርትቤትነ ትወደመንግስትሲዞር፡ሁላችን ም ማለትተማሪዎችም መምህራን ም በየመንግስትትምህርትቤቱ
ስለተበተንንመምህርጌታቸው የትእን ዳሉእንኳንአላውቅም ነበር፡፡ጥያቄዬንበውስጤ ይዤየሚመልስልኝእስካገኝ
መጠባበቅጀመርኩ፡ ፡ታዲያበአዲሡ ትምህርትቤትምን ም እንኳንሁለተኛአመትእየተማርኩቢሆን ም ከትምህርትቤቱ
ስፋትእናከተማሪው ብዛትየተነሳየቀደመውንያህልታዋቂነ ትበዚህትምህርትቤትአልነ በረኝም፡እንደውም በምማርበት
ክፍልውስጥ ራሱያለኝታዋቂነ ትእስከዚም ነበር፡
፡ታዲያበዚህወቅትያስተምሩንከነ በሩትመምህራንአን ዱ በእድሜ
ጠናያሉትእናከ30አመትበላይበመምህርነ ትሙ ያየቆዩትየአማርኛመምህራችንመምህርተስፋዬነ በሩ፡፡እኚህ
መምህርበትምህርትቤቱበግርማሞገሳቸው፡በኮስታራነ ታቸው፡እናበእድሜ ብስለታቸው በትምህርትቤቱማህበረሰብ
የሚፈሩም የሚታፈሩም መምህርነ በሩ፡፡እኚህመምህርከእድሜያቸው እናበሙ ያው ለረጅም አመትበማገልገላቸው
ለጥያቄዬትክክለኛውንምላሽእን ደሚሰጡኝብተማመን ም ኮስታራስለነበሩበቀላሉየምግባባቸው አልነ በሩም፡ግን
ከሳቸው ጋርተግባብቼጥያቄዬንለማቅረብአጋጣሚ እፈልግነ በር፡

ተናፋቂዋንአጋጣሚ ስጠባበቅበመጀመሪያመን ፈቀአመትማገባደጃሠሞንመምህርተስፋዬበአማርኛትምህርትከ


ሃምሳያስመዘገብነ ውንውጤትእያሳወቁሳለየኔ ንስም ጠርተው ውጤቱንከተናገሩ፡በኃላ"ማንነሽእስቲቁሚ"አሉ፡፡
ተማሪዎቹ መሳቅጀመሩ፡ ፡መምህሩ አይናቸውንከወረቀቱወደተማሪው አዙረው ሲመለከቱተማሪው ፀጥ አለ፡ ፡ስሜን
በድጋሚ ጠርተው "የለችም እንዴ"አሉ፡፡አጠገቤየተቀመጠው ጓደኛዬገፋገፋእያደረገኝእንድነሳሲያበረታታኝተነስቼእኔ
ነኝአልኳቸው፡፡"
እንዴት"አሉ፡፡እሳቸው ሴትተማሪጠብቀው፡ሰለነ በረገርሟቸው ፡ምን
ም እንኳንስሙ በተለምዶየሴት
ስም ከሚባሉትየሚመደብቢሆን ም ፡የምጠራው በዚስም እንደሆነነገርኩቸው፡፡
"
ማንነ
ው ያወጣልህ?
"አሉኝ፡

"
አባቴ"ብዬመለስኩ፡

"
ታላቅእህትአለህ?
"አሉ

"
አዎ"መለስኩ

በግርምትእየተመለከቱ"
እንዴትታዲያ!
"ብለው እን
ደመሳቅአሉና፡

"እኔእኮፈተናሳርም፡ማንናትእልነ
በር፡
፡"ብለው ፊትለፊትየምትቀመጠውን፡ጥያቄሲጠይቁ፡እጇንእን
ደባን
ዲራ
እያውለበለበችየምትሳተፈውንልጅ

"ቆይአን
ቺስምሽማንነ
ው?"አሏት፡


ገረቻቸው፡

"
እኔእኮአን
ቺነበርየምመስይኝ፡
፡"ብለው፡ወደእኔዞረው ውጤ ቴንበድጋሜ ተናግረው፤እስጨ በጨ ቡልኝእና

"
ተቀመጥ!
"አሉኝ

"እን
ደዚአይነ
ትተማሪየኩበትእሳትይባላል፡
፡"አሉእናየሌላተማሪዎችንስም እየጠሩውጤ ትመናገራቸውንቀጠሉ፡

የአማርኛክፍለጊዜተጠናቆመምህራችንከክፍልሲወጡ የእረፍትክፍለጊዜስለነ
በርተከትያቸው ወጣሁእና

"ቲቸርየኩበትእሳትለምንድንነው ፡ያሉኝ?
"ብዬጠየኳቸው በእርግጥ የኩበትእሳትመባሌአልነበረም ፡ጉዳዬከሳቸው
ጋርለመግባባትእናለዋናው ጥያቄዬ(ስለችቦው)በርለመክፈትነ በር፡
፡ነገርግንየዚጥያቄመልስበዝግታ
ብንራመድም እስከመምህራንማረፊያስላደረሰችንሁለተኛዋንእናዋናዋንጥያቄአልጠየኩቸውም ነ በር፡የኩበትእሳቷን
ጨ ዋታሌላጊዜእን መለስበታለሁ፡

ትኩረቴንችቦዋላይአድርጌጭ ዌውንልቀጥል፡

ምንም እን
ኳንዋናውንጥያቄባልጠይቅም መልሴንለማግኘትወደፊትመጠጋቴስለተሰማኝበደስታወደመማሪያክፍሌ
ተመለስኩ፡በቀጣይቀንምሳሰዓትላይመምህርተስፋዬንከተማሪዎችጋርመምህራንማረፊያው ደጅላይአይቼቻው
ተቀላቀልኩ፡፡ተራዬንጠብቄ፡ጉዳዬንአስረድቼጥያቄዬንአስከተልኩ፡
፡በጥሞናሲያደምጡኝከቆዩበኃላበፈገግታ
ተመልክተውኝ፡

"እን
ዴትአገጣጠምከው ባክህ!
"አሉእናጥሩውጤ ትማምጣት፤ ጠን
ክሮበመስራትእናበትጋትየሚገኝእን
ጂ እውቀት
ችቦበመቀባበልከአን
ዱወደሌላው እንደማይተላለፍያስረዱኝጀመር፡

"በእርግጥ እውቀትየሚገኘው በመገለጥ ወይም በመጋለጥ ነ ው፡


፡እዚደግሞ እውቀትየሚገለጥበትሳይሆንወደ
እውቀትየምን ጋለጥበትቦታነው፡፡እውቀትበመገለጥ የሚገኘው ደግሞ በመን ፈሳዊቦታላይነ ው እሱም ለተመረጡ
ብቻ፡፡እኛግንበማንበብ፡በመጠየቅበመነ ጋገር፡በህይወትውጣ ውረድራሳችን ንለእውቀትአጋልጠን ፡የእውቀትን
ብርሀንነትለመልበስእንሞክራለን፡፡እንጂ እንደዛቢሆንማ ችቦውንለሁሉም ተማሪእየሰጠንእያዞርንወደቤተቹ
አንመልሳቹም ነበር፡
፡ችቦውንይዘንየምን ቀባበለው በምሳሌነትእውቀትንእን
ደምን ጋራ፡እናየእውቀትንብርሀንነት
ለማስረዳትምሳሌበማድረግነ ው፡፡"ብለው በተቃርኖመሀልሲባዝንየነበረውንሀሳቤንወደሌላኛው ጥግአሻገሩእና
አሳረፉልኝ፡
፡ከዚያወዲያበዚበኩልያለውንገፅታእየቃኘሁአለሁ፡ ፡

You might also like