You are on page 1of 3

አክሚን እማማ

ታመናል ታመናል ታመናል በጠና፣

ኢትዮጵያ እናታችን አክሚን እንምጣና፣

ካንሰሩ ይታከም ደባብሰሽ አድኚው፣

ማዳን ትችያለሽ ይቆረጥ አትበይው፣

ታመናል ልጆችሽ ካንሰሩ ተስፋፍቷል፣

መላው አካላችንን ሊያጠፋ ተቃርቧል፣

መድሃኒቱ በእጅሽ እንዳለ እናውቃለን፣

ረፍዷል እንዳትይን ጊዜ ገና አለን፣

በሰበብ በአስባቡ እየተቧጨቅን ፣

እየተቋሰልን እየተቧደንን፣

እጅጉን ታመናል በጣምም ደከምን፣

ማእበሉ ሳይበላን ጀምበር ሳይጠልቅብን፣

ተቆጭን ገስጭን አልያም ምከሪን፣

ዝም ግን አትበይን፤

እጆችሽን ዘርጊ እስኪ ወደ አምላክሽ፣

ፍፁም አይተውሽም ትልቅ ነው አባትሽ፣

ቃል ኪዳን ነውና ይህ ነው የሚያምርብሽ፤

እየደጋገምን ብንበድልሽም ብናስቀይምሽም፣

እኛ ከአንቺ ሌላ አማራጭ የለንም፣

ቤታችን ነሽ አንቺ ወዴትም አንሄድም፣

እማማ ኢትዮጵያ ማሪን እናታችን፣

በድለናል ብለን ከእግርሽ ስር ወደቅን፣

ማዕበሉ በዝቶ ባህሩ ሊበላን ፣

ማስተዋል አልቻልንም በጅጉ ታመናል ፣


አፋጣኝ የሆነ መድሃኒት ያሻናል፣

መድሃኒት ነው ብለው መርዝ እንዳያበሉን ፣

ከአንቺ ውጭ ያለ መድሃኒት ይቅርብን፣

አስቸኳይ የሆነ መድሃኒት ያሻናል፣

በቃ ሁላችንም እጅጉን ታመናል፣

ወይ አለመታደል!!!!!!
ባይሞላልኝ እንኳን እንደታደሉቱ፣
አንቺን ለመጠበቅ የተጋደሉቱ፣

አንቺን ለመገንባት የተቋሰሉቱ፣

አፈርሽን ፈጭቼ ቅጠልሽን በጥሼ፣

ወድቄ ተነስቼ ቦርቄ አልቅሼ፣

አፈርሽን እምነት ውሃሽንም ፀበል አድርጌ ታብሼ፣

ምንስ ቢቸግረኝ ምንስ ሆድ ቢበሰኝ፣

አለማወቄ እንጂ ውድቀትሽን የምመኝ፣

ኢትዮጵያ አገሬን ትውደቅ በይ ለሚለኝ

አትወድቂም እንጂ ጊዜ ሳያባክን አገር አልባ ሊለኝ፣

እኔን የገረመኝ ያለማወቄ ነው ያለ መረዳቴ፣

በሩቅ ሀገር ሆኜ ትንፋሽሽ እርቆኝ ውደሚ ማለቴ፣

You might also like