You are on page 1of 5

በደ/ፀቅ/ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀ የድራማ ትዕይንት

የድራማው ርዕስ፡-እምነት

ትዕይንት 1

 አባት፡-አለሚቱ ናይማ ልጀ ስሚኝ እኔ እንግዲህ እንደሚታወቀው ለዕረፍት ነበር የመጣሁት እና አሁን እረፍቴን ጨርሻለሁ
ስለዚህ አሁን ወደ ስራየ እመለሳለሁ አሁንም ምናልባት በሰላም እስክመለስ ድረስ ወንድምሽን አደራ ተንከባከቢው፡፡
 አለሚቱ፡-እሽ አባየ አንተ አታስብ ምንም አይሆንም አንተ ብቻ ራስህን ጠብቅ፡፡
 አይተነው፡-አወ አባየ ለምን ለእኔ ትጨነቃለህ አይዞህ እኔ ምንም አልሆንም፡፡ ከአንተ በላይ ስለ ልጆቹ የሚጨነቅ አባት አለና
ስለዚህ እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ነገር ግን አንተ ራስህን ጠብቅ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡
 እናት፡-ዝም ብለህ ካለ መጨነቂያህ ትጨነቃለህ እነሱ ምን ይሆናሉ ብለህ ነው የልቅስ አንተ ራስህን ጠብቅ፡፡
 አባት፡-በሉ እንግዲህ እኔ ሌሊት በጧት ስለምሄድ አሁን አረፍ ልበል እናንተም አረፍ በሉ፡፡

ትዕይንት 2

 እናት፡-አንች አለሚቱ አይተነው ተነሱ ነግቷል እኮ ቁርሳችሁን ብሉና አንች ከዚህ አንዳንድ ስራ ታግዥኛለሽ አይተነው
ደግሞ ሂድና አትክልቱን ኮትኩተኸው ትመጣለህ፡፡
 አለሚቱ፡-አባየ ሂዶ ነው እንዴ
 እናት፡-ከምቀሰቅሳቸው ብሎ ሌሊት በጧት ነው ወጥቶ የሄደ፡፡
 አለሚቱ፡-እንዴ ደግሞ እማየ አይተነው እንዴት ብሎ ነው ሂዶ የሚኮተኩተው ባይሆን እሱ ከዚህ ያለውን ስራ እያገዘሽ
ይቆይ እኔ ሂጀ ኮትኩቸው ልምጣ፡፡
 እናት፡-ዝም በይ አንችን ማን አለሽ የታዘዝሽውን……….
 አይተነው፡-ችግር የለም እኔ እሄዳለሁ እግዚአብሔር ሁሉን ያዘጋጃል፡፡
 እናት፡-በሉ አሁን ሁላችሁም ወደየ ስራችሁ ሂዱ፡፡
 አይተነው፡-አለሚቱ/2/ እስኪ መቆፈሪያው የት እንዳለ ፈልጊና ስጭኝ፡፡
 እናት፡-አንች አሁን ይኸ ጠፍቶት ነው አንች ወደታዘዝሽበት ሂጅ፡፡ እንካ አንተ ደግሞ ሂድና ተሎ ኮትኩተህ ተመለስ፡፡
 አይተነው፡-እሽ ስጭኝ……...እባክህ አምላኬ መንገዴን አቅናልኝ በሰላምም አድርሰኝ፡፡
 በሪሁን፡-እህ አይተነው ደህና ነህ ወዴት እየሄድክ ነው ደግሞ መቆፈሪያ ይዘሀል፡፡
 አይተነው፡-እግዚአብሔር ይመስገን አዎ ልክ ነህ ወደ አትክልቱ ቦታ ሂጀ የሚኮተኮት አለ እሱን ኮትኩቸ ልመለስ ነው፡፡
 በሪሁን፡-እኔ የምልህ ገና አባትህ ከመሄዱ እንደዚህ አይነት ስራ መስራት አለብህ ተባልክ፡፡
 አይተነው፡-አባቴ መሄዱን እንዴት አወክ
 በሪሁን፡-አይ እኔስ በጧት ስራ ታዝዠ ስሄድ እየሄደ በመንገድ ላይ አግኝቸው ነው፡፡
 አይተነው፡-ለማንኛውም ልክ ናት መስራት አለብኝ ያልሰራ ደግሞ መብላት አይችልም ስለዚህ አሁን በጣም ሳይረፍድ ሂጀ
መስራት ስላለብኝ መሄዴ ነው ደህና ሁን፡፡
 በሪሁን፡-እሱማ ልክ ነህ እኔ እኮ እንደሱ ሆነህ በዚህ በገደላማ ቦታ ሂደህ መስራት አትችልም ብየ ነው እንጅ፡፡
 አይተነው፡-እግዚአብሔር ያውቃል ሁሉንም የፈጠረ እሱ ነው ስለዚህ በእርሱ ቸርነትና ፈቃድ ሰርቸ እመለሳለሁ፡፡
 በሪሁን፡-ልክ ነህ ያለ እርሱ የሚሆን ነገር የለም መቆፈሪያውን አምጣውና እኔ ኮትኩቸልህ እመጣለሁ አንተ ከዚህ
ከደልዳላው ቦታ ላይ ቆየኝ፡፡
 አይተነው፡-አይ አይሆንም እኔ እሄዳለሁ ሌላ ስራ እንዳለህ ደግሞ ቤተሰብም ሊፈልግህ ይችላሉ፡፡
 በሪሁን፡-ችግር የለም ተሎ ኮትኩቸልህ እመለሳለሁ አንተ ብቻ ከዚህ ቆየኝ፡፡
 አይተነው፡-እሽ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን….

ትዕይንት 3

 አለሚቱ፡-ወንድሜ እስካሁን ቀረሳ ይኸው የምሳ ሰዓት አለፈ እኮ ደግሞ አባቴ ወንድምሽን አደራ ብሎኝ ከመሄዱ…..
እግዚአብሔር ሆይ ወንድሜን ሰላም አድርግልኝ፡፡
 አይተነው፡-አምላኬ ይህንን መልካም ሰው በሰላም መልሰው አንተ ሁሉን ታዘጋጃለህ አንተን ያመነ እና ተስፋ ያደረገ ሰው
ማን ወድቆና አፍሮ ያውቃል፡፡
 በሪሁን፡-አይተነው /2/ ጨርሸ መጣሁ ቆየውብህ አይደል መንገዱ በጣም እሩቅና ውጣ ውረድ የበዛበት ነው ለአንተማ
በጣም ይከብድህ ነበር ለማንኛውም እንካና መቆፈሪያውን አሁን ወደ ቤትህ ሂድ፡፡
 አይተነው፡-በሪሁን መጣህ እንግዲህ እግዚአብሔር ውለታህን ይክፈልህ ሌላማ ምን እላለሁ፡፡
 በሪሁን፡-ችግር የለውም በል አሁን ሳይመሽብህ ተሎ ሂድ፡፡
 እናት፡-አለሚቱ ወንድምሽ አልመጣም እንዴ እስካሁን ለነገሩ በዚያ በአንዱ ጥላ ስር ቁጭ ብሎ ነው የሚሆን ስራውንስ
እንዳልሰራው ነው፡፡
 አለሚቱ፡-ተይ እንጅ እማየ ለምን እንደዚህ ትያለሽ በአንዱ ገደል ወድቆ ቢሆንስ……እስኪ ለማንኛውም ዘልቄ አይቸው
ልምጣ………..እንዴውም ያው እየመጣ ነው፡፡
 እናት፡-አሁን እውነት ሰርቶት መጥቶ ነው በአንዱ ተኝቶ ውሎ ነው እንጅ……
 አይተነው፡-እንዴት ዋላችሁ
 እናት፡-እስካሁን ድረስ የት ነው የዋልክ..
 አይተነው፡-እናቴ መንገዱ እኮ በጣም እሩቅ ነው በዚያ ላይ ደግሞ ገደላማ እና ውጣ ውረድ የበዛበት ነው፡፡
 አለሚቱ፡-እናቴ አሁን ደክሞታል ይረፍና ነገ ትነጋገራላችሁ፡፡
 እናት፡-ለማንኛውም ይንጋና አንች ሂደሽ የሰራውን እንድታይው፡፡

ትዕይንት 4

 እናት፡-አለሚቱ ተነሽ ሂጅና አትክልቱን አይተሽ አልተኮተኮተ እነደሆነ ኮትኩተስው እንድትመጭ አይተነው ምናልባት ሰርቶ
ከሆነ ትንሽ አረፍ ይበል፡፡
 አለሚቱ፡-ነግቷል እንዴ እሽ እሄዳለሁ፡፡
 በሪሁን፡-አለሚቱ እንዴት ነሽ መቆፈሪያ ይዘሽ ወደየት ትሄጃለሽ፡፡
 አለሚቱ፡-እግዚአብሔር ይመስገን ወደ አትክልቱ ነው ትናንት ወንድሜ እንዲኮተኩት ታዞ ነበር ምናልባት አልተኮተኮተ
እንደሆነ ኮትኩቸ ልመጣ፡፡
 በሪሁን፡-እንደዚያ ነው በይ ደርሰሽ ተመለሽ፡፡
 አለሚቱ፡-በል እሽ ደህና ሁን…….እንዴ ተኮትኩቶ አይደል እንዴት አድርጎ ኮተኮተው በጣም የሚገርም ነው ለማንኛውም
ወደ ቤቴ ልሂድ፡፡
 እናት፡-አንተ አይተነው በል ተነስ በጣም እረፍዷል እኮ፡፡
 አይተነው፡-እሽ ነግቷል እንዴ…አለሚቱስ የት ሂዳ ነው፡፡
 እናት፡-ትናንት አንተ ስትንከባለልበት የዋልከውን አይታ ልትመጣ ሂዳለች፡፡ አሁን ተነስ አንዳንድ የሚሰራ ስራ ስላለ
እንድታግዘኝ፡፡
 አለሚቱ፡-እንዴት አረፈዳችሁ….. አይተነው ተነሳህ እንዴ ደህና ነህ ድካሙ እንዴት አደረገህ፡፡
 እናት፡-ምነው ተሎ ተመለስሽ እሳ እንዴው በደንብ ተሰርቶ አገኘሽው፡፡
 አለሚቱ፡-አወ ስራው በደንብ ተሰርቶ አገኘሁት ስለዚህ ተሎ ብየ ተመለስኩ፡፡
 እናት፡-አይተነው እንደሚለው በደንብ ተኮትኩቷል ነው ወንድምና እህት እየተለባበሳችሁ ነው፡፡
 አይተነው፡-እናቴ ለምን እንደዚህ እናደርጋለን ይህን እኮ እግዚአብሔርም አይወደውም እውነቱን እውነት ሐሰቱን ደግሞ
ሐሰት በሉ ነው ያለን፡፡
 አለሚቱ፡-አይተነው እውነቱን ነው እማየ ለሁሉም ነገር እኮ እውነት እንጅ ሐሰት ለማን ይጠቅማል ብለን እንዋሻለን፡፡
 እናት፡-ለማንኛውም አሁንም ትንሽ ይቆይና ድጋሜ መኮትኮት አለበት፡፡
 በጋራ አለሚቱና አይተነው፡- እሽ እማየ እንኮተኩተዋለን፡፡ ከ 5 ቀን በኋላ

ትዕይንት 5

 እናት፡-አለሚቱ ነይ እስኪ ይኸው አትክልቱ ከተኮተኮተ ዛሬ አምስተኛ ቀኑ ነው ስለዚህ አይተነው ይሂድና ኮትኩቶት ይምጣ
አንች ከዚህ ስራ አለሽ፡፡
 አለሚቱ፡-እማየ ባይሆን ዛሬ እኔ ልሂድና ኮትኩቸው ልምጣ ገደሉ በጣም ከባድ ነው፡፡
 እናት፡-አንች ከዚህ ስራ አለህ አልኩሽ አይደል ደግሞ የማማክርሽ አንድ ነገር አለ አሁን አይተነውን ጥሪውና ይሂድ፡፡
 አለሚቱ፡-አይተነው /2/ እማየ ና ተሎ እያለችህ ነው፡፡
 አይተነው፡-እማየ ምነው ጠርተሸኛል፡፡
 እናት፡-አዎ አትክልቱ ከተቆፈረ ዛሬ አምስት ቀኑ ነው ስለዚህ ሂድና ኮትኩተኸው ና፡፡
 አይተነው፡-እሽ እሄዳለሁ መቆፈሪያውን ስጡኝ፡፡
 አለሚቱ፡-እንካ ግን እንደ ባለፈው እንዳታመሽ ተሎ በጊዜ ተመለስ፡፡
 አይተነው፡-እሽ እመለሳለሁ በቃ አንች ሂጅ እማየ እየጠራችሽ ነው፡፡
 አለሚቱ፡-እማየ ጠራሽኝ
 እናት፡-አዎ ቁጭ በይ አንድ ሀሳብ ላማክርሽ ነው
 አለሚቱ፡-እና ሀሳቡ ምንድን ነው
 እናት፡-ምን አስቸኮለሽ ልነግርሽ አይደል ቀስ በይ ለምን እንደዚህ አናደርግም ይህን ወንድምሽን ወዲያ በዚያ በአንዱ ጫካ
ወይም ገደል ላዝናናህ ብለሽ ጥለሽው ናይና ከዚህ አባትሽ ያስቀመጠውን ወርቅ ለምን አንሸጠውም በዚህ ላይ አባትሽ
የሚመለስ አይመስለኝም ምን ትላለሽ…
 አለሚቱ፡-ኧረ በስመ አብ እናቴ ምን ነካሽ ይህን ሀሳብ ምን አይነት ሰይጣን አሳሰበሽ እኔ አላደርገውም….
 እናት፡-ዝም ብለሽ ስሚኝ አንችም ሁልጊዜ እሱን የእጎተትሽ ከመኖር ትላቀቂያለሽ ደግሞ አንች ጥሩ ልጅ ስለሆንሽ ነው
ያማከርኩሽ…
 አለሚቱ፡-እናቴ ግን እኮ በጣም ከባድ ነው እስኪ ለማንኛውም መመለሱን አይተን…..
 እናት፡-በይ አሁን ግቢ እና ምሳሽን ብይ፡፡
 አይተነው፡-አምላኬ ሆይ የቀኑን ብርሃን የምትሰጥ አንተ ነህ ሌሊቱም የአንተ ነው እኔ ባርያህ እለምንሀለሁ መንገዴን
አቅናልኝ በሰላም አድርሰህ መልሰኝ አሜን፡፡
 በሪሁን፡-አይተነው ደህና ነህ ወደዚያ አትክልት ደግመህ እየሄድክ ነው፡፡
 አይተነው፡-አወ ደርሸ ልምጣ እስኪ
 በሪሁን፡-አምጣው መቆፈሪያውን አንተ ከዚህ ቆየኝ፡፡
 አይተነው፡-በሪሁን እስከ መቸ ሁልጊዜ እንደዚህ ተብሎ ይዘለቃል ባይሆን ምንገዱን እያሳየኸኝ አብሬ ልሂድ፡፡
 በሪሁን፡-አይሆንም ሌላ ቀን አብረን ሂደን እየለመድከው ስትሄድ አንተ ትሰራለህ ዛሬ ግን ከዚህ ቆየኝ፡፡
 አይተነው፡-እሽ ወንድሜ እግዚአብሔር በሰላም ይመልስህ፡፡

ትዕይንት 6

 እናት፡-እንዴ ዛሬ ደግሞ ተሎ መጣ እሳ
 አለሚቱ፡-እናቴ አይተነው መጣ እንዴ
 እናት፡-አወ እየመጣ ነው በይ ያንን ያልኩሽን ዛሬ መጀመር አለብሽ
 አይተነው፡-እንዴት ዋላችሁ…..
 እናት፡-ዛሬ ደግሞ ተሎ መጣህ እውነት ከአትክልቱ ደርሰሃል፡፡
 አለሚቱ፡-እናቴ አሁን ይግባና ምሳውን ይብላና በኋላ እየተዝናናን ሂደን እናየዋለን፡፡
 እናት፡-በሉ ግቡ እና እንግዲያ በኋላ ሂዳችሁ እንድታዩት፡፡
 አለሚቱ፡-እሽ አይተነው ና እንግባ፡፡
 አለሚቱ፡-እማየ በይ እኛ ልንሄድ ነው፡፡
 እናት፡-ተሎ ደርሳችሁ ተመለሱ እንዳይመሽባችሁ፡፡ …….
 አለሚቱ፡-እሽ አንቆይም ተሎ እንመለሳን አይተነው ና በል እንሂድ ትንሽ ተዝናንተን ወዲያው አትክልቱን አይተን
እንመጣለን፡፡
 አይተነው፡-አለሚቱ እኔ ደክሞኝ ነበር ትንሽ አረፍ ብየ ብንሄድስ፡፡
 አለሚቱ፡-ሳይመሽ ፊት እየተዝናናን ደርሰን እንምጣ በኋላ አንድያህን ታርፍ አይደል፡፡
 አይተነው፡-በይ እሽ እንሂድ እና ተሎ እንመለስ……..አለሚቱ ደረስን እንዴ፡፡
 አለሚቱ፡-አወ እየደረስን ነው ና ከዚህ ቁጭ ብለህ ቆየኝ ሽንት ቤት ደርሸ ልምጣ…. ከገደሉ አፋፍ ትቶት ይሄዳል፡፡

ክፍል ሁለት

ትዕይንት 1

 አይተነው፡-ምነው እስካሁን ቆየች ምን ሁና ይሆን እህቴ አለሚቱ/2/ ሲል ሽመሉን ትቶ ወደታች ወደገደሉ ይወድቃል፡፡
ኧረ እህቴ የት ሂደሽ ነው በገደል ወዲቄያለሁ ነይ አውጭኝ እህቴ /2/ ከዚያ አንገቱን ደፍቶ ከገደሉ ውስጥ ይቀመጣል
 አባ ኪሮስ፡-ይህን ሽመል ከዚህ ምን አመጣው ደግሞ የምን ድምጽ ነው የሚሰማኝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ
ቅዱስ አሐዱ አምላክ ልጀ ማን ነው የጣለህ እንካ እስኪ መቋሚያየን ያዝ አይዞህ ምን ስታደርግ ነው የወደክ፡፡
 አይተነው፡-አባየ ከእህቴ ጋር ነበር መጣን ከዚህ ቆየኝ ብላኝ ቆየች ብየ ተነስቸ እሷን ስጣራ ነው የወደኩ ደግሞ እህቴ
ወደየት እንደሄደችስ ምንስ ሁና ይሆን፡፡
 አባ ኪሮስ፡-አይዞህ ልጀ እግዚአብሔር ባለችበት ይጠብቃት እግዚአብሔር አንድ ነገር ሳያዘጋጅ መከራ /ፈተና/ በሰዎች
ላይ አያመጣም ለዚህም ነው አንተን ከገደል ለማውጣት ሲፈልግ እኔን በዚህ መንገድ እንድመጣ አደረገኝ ስለዚህ
አትጨነቅ ምንም አትሆንም፡፡
 አይተነው፡-እሱማ ልክ ነዎት አባ እንግዲህ እሱ ያለው ይሆናል፡፡
 አባ ኪሮስ፡-በልና ልጀ ወደ እኔ ቤት እንሂድ
 እናት፡-አለሚቱ መጣሽ በየት ጥለሽው መጣሽ፡፡
 አለሚቱ፡-እንጃ እማየ የሚተርፍም አይመስለኝ ከገደሉ አፋፍ ላይ አስቀምጨው ሽንት ቤት ወጥቸ ልምጣ ብየው ነው
የመጣሁ፡፡
 እናት፡-የታባቱ ጥሩ አድርገሽዋል ማን እሱን ዘላለም ሲጎትት ይኖራል በይ ነይ ግቢ አረፍ በይ ደክሞሻል፡፡
 አባ ኪሮስ፡-ልጀ በል አሁን እንረፍና ነገ በጧት ወደ ፀበል ሂደን ትፀበላለህ እግዚአብሔር የማይፈውሰው ህመም የለም፡፡
 አይተነው፡-እሽ አባቴ አሁንስ በጣም አደከምኩዎት፡፡
 አባ ኪሮስ፡-ችግር የለም ልጀ ፍቅር ካለ የማይደረግ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ፍቅር ስቦት ነው ወደዚህ
ዓለም የመጣ ስለዚህ በዚህ ምድር ስንኖር እርስ በርስ ተሳስበንና ተከባብረን በፍቅር እንድንኖር ነው የታዘዝን በል አሁን
ተኛ ነገ በጧት ነው የምንሄድ፡፡

ትዕይንት 2

 አባ ኪሮስ፡-አይተነው /2/ ልጀን ደክሞታል አይዞህ ተነስ ከፀበሉ ደርሰን እንምጣ፡፡


 አይተነው፡-እሽ አባቴ እሩቅ ነው እንዴ?
 አባ ኪሮስ፡-አየ ልጀ ፈውስ ካለ እሩቅ ቢሆንስ እግዚአብሔር አምላካችን በወንጌሉ “በጊዜውም ያለ ጊዜውም ፅና”
ብሏል፡፡ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያለብን ሲመችን ወይም ፈተና ሲገጥመን ብቻ አይደለም ሁሌም ወደ ቤቱ
መቅረብና መፅናት ያስፈልጋል፡፡
 አይተነው፡-እሽ አባቴ ምክርዎትና የሰጡኝ ትምህርት ልብ የሚነካ ነው፡፡
 አባ ኪሮስ፡-በል አሁን ከፀበሉ ደርሰናል፡፡
 አይተነው፡-አባቴ አይኔ በራልኝ አሁን ሁሉንም ማየት ችያለሁ ይህ ሁሉ የሆነው በእረሰዎ ድካምና ልፋት እንዲሁም
በእግዚአብሔር ቸርነት ነው፡፡
 አባ ኪሮስ፡-ልክ ብለሀል ልጀ ይህ ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡
 አባት፡-እንዴት ዋላችሁ፡፡
 አባ ኪሮስና አይተነው፡-እግዚአብሔር ይመስገን እንዴት ዋልክ
 አባት፡-አይተነው ልጀ ለማመን የሚከብድ ነው እንዴት ልትድን ቻልክ፡፡
 አይተነው፡-አባየ በሰላም ተመለስክ በገደል ወድቄ አባቴ አግኝተውም ከእሳቸው ካር ወደ ቤት ወስደው አሁንም ፀበል
ስጠመቅ በእግዚአብሔር ኃይልና በአባቴ መልካምነት ለዚህ በቃሁ፡፡
 አባት፡-በሉ አሁን ወደ ቤት እንሂድ አባታችን ይምጡ፡፡
 እናት፡-አለሚቱ በይ አሁን አባትሽ ያኖረውን ወርቅ አምጭውና ሽጠን የፈለግነውን ነገር እንግዛ፡፡
 አለሚቱ፡-እሽ እማየ እኔ ግን በጣም ፍራት ፍራት እያለኝ ነው፡፡
 እናት፡-ምን ሁነሽ ነው የምትፈሪ አባትሽም አይመጣ ያወንድምሽም ከዚህ በኋላ አይመለስ እና ምን አስፈራሽ፡፡
 አለሚቱ፡-እኔ እንጃ እስኪ ቆይ በውጭ ሁሉን ነገር አይቸው ልምጣ…….ኧረ እማየ በዚያ ግድም ሶስት ሰዎች ወደ
እኛ ቤት እየመጡ ነው፡፡
 እናት፡-እነማን ናቸው……
 አለሚቱ፡-አላወኩአቸውም አንዱ ግን ቄስ ይመስላል፡፡
 እናት፡-ልጀ ጉዳችን ፈላ አባትሽና ወንድምሽም አሉ አብረው…..ብላ ትብረከረካለች
 አለሚቱ፡-እናቴ ወደየት እንግባ አባቴ ወንድምሽን የት ነው የጣልሽው ካለኝ ምንስ ልል ነው፡፡
 እናት፡-አይዞሽ አንች ገፍተሽ ገደል አለቀቅሽው ምን አስጨነቀሽ፡፡
 አለሚቱ፡-እማየ በይ እንግዲህ እየደረሱ ነው መላ እናዘጋጅ፡፡
 አባ ኪሮስ፡-ጤና ይስጥልን እንዴት ዋላችሁ፡፡
 አለሚቱ፡-እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ዋላችሁ እንዴ አባየ፣ እማየ ማለቴ ወንድሜ እንዴት መጣችሁ ማለት መቸ
መጣችሁ፡፡ አስሩን ትዘባርቃለች
 አባት፡-ደህና ነሽ ልጀ ምነው ሰላም አይደለሽም እንዴ፡፡
 እናት፡-ኸረ እልልልል ተመስገን ፈጣሪ አባቴ ደህና ነዎት ይግቡ ኑ ግቡ አይተንየ ደህና ነህ በጣም የሚገርም ነው
አይንህ እንዴት በራልህ፡፡
 አባት፡-አለሚቱ አባን እግራቸውን እጠቢያቸውና ስለደከማቸው ምሳ ይብሉና አረፍ ይበሉ፡፡
 አለሚቱ፡-እሽ አባየ፡፡

ትዕይንት 3

 አባ ኪሮስ፡-አይተነው ባለፈው ያስጨነቀችህ እህትህ ይች ናት፡፡


 አባት፡-አለሚቱ ምን ሁና ነበር አይተነው
 አለሚቱ፡-አባቴ ይቅርታ አድርግልኝ
 አባት፡-ምን ሁነሽ ነው ልጀ ቅድም አንስተሽ እኮ ልክ አይደለሽም ምነው የተደበቀ ነገር አለ እንዴ አይተነው እንደሆነ
አይናገርም ሁሉንም ዝም ነው የሚል፡፡
 እናት፡-አወ ይቅርታ አድርጉልን አባታችን እኛ በድለናል እግዚአብሔርንም አስቀይመናል አባታችን ወደ እግዚአብሔር
ፀልዩልን፡፡
 አባ ኪሮስ፡-ምንድን ነው ልጀ ሁሉንም አንድ በአንድ ንገሩኝ እግዚአብሔር ኃጥያትን እንጅ ኃጢአተኛን አይጠላም
ለልብሳችን ሳሙና እንደሚያስፈልገን ሁሉ ለልባችንም መቆሸሽ ንስሐን ሰጥቶናል፡፡
 እናት፡-አባቴ እንዲህ ነው ነገሩ ይህን መጥፎ ሐሳብም ያመጣሁት እኔው ነኝ አለሚቱ ምንም አላደረገችም እኔ ነኝ
እንድትሳሳት ያደረኩዋት፡፡ ወንድምሽን እንዝናና ብለሽ ወስደሽ በዚያው ጥለሽው ነይ አልኩዋት አባትሽም
አይመለስም ከዚያ ያኖረውን ወርቅ ሽጠን የፈለግነውን እንገዛለን በማለት ይህን ምስኪን አሰቃይቸዋለሁ ከባድ
ስራም በማዘዝ በዚያው እንዲቀር ብዙ ጊዜ ስራ አዘዋለሁ እሱ ግን የታዘዘውን ሁሉ በቅንነት ይሰራል ስለዚህ
አባታችን ይቅር ይበሉን፡፡
 አባ ኪሮስ፡-ልጀ በአንድ ሰው ንስሐ መግባት በሰማይ በመላዕክት ዘንድ ታላቅ ደስታ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ኃጥያትን ይቅር
የሚል እግዚአብሔር ነው ተነሱ፡፡ ልጆቸ ሰው ብዙ ነገር ይሆናል መስሎት በተሳሳተ መንገድ ይሄዳል ነገር ግን ጥፋትን
አውቆ ተፀፅቶ ንስሐ መግባት ትልቅ ሃብት ነው አሁንም ወደፊት መልካም ስራ መስራት እንጅ ወደኋላ መመለስ
የለባችሁም አሁን ይህን ላደረገልን ለእግዚአብሔር ምስጋና እናቅርብ፡፡

You might also like