You are on page 1of 3

ፋጤን ጅርቲ

በአንድ አነስተኛ የገጠር ከተማ ስሟ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ጋር ተያይዞ እሚነሣ አንዲት ወጣት ሴት አለች፡፡ ፋጤ
ትባላለች፡፡ ትምህርቷን እስከ 12 ኛ ክፍል ተከታትላለች፡፡ ቀደም ሲል በአፍላ ዕድሜዋ ከወለደችው አንድ ሕፃን ልጇ ጋር
ትኖራለች፡፡ በሰፈሩ አንዳች የአስገድዶ መድፈር አሊያም ግርዛት መሰል ተግባራት ሲከናወን ከሰማች የድርጊቱን
ፈፃሚዎች በአፋጣኝ ታሳስራለች፡፡ ተጎጂዎቹንም ወደ ሆስፒታል እንዲታከሙ ትልካለች፡፡ ፖሊሱም ጤና ጣቢያውም
ይታዘዛታል፡፡ ከቀበሌው ሊቀመንበር በላይ፣ ከሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤቱ በላይ ትከበራለች፤ ትፈራለችም፡፡ እንደውም አንዳንድ
ሰዎች በአካባቢው በሚፈራ አንድ ፖሊስ ስም ለወጥ አድርገው ካሱ መጣችልህ እተባባሉ ስሟ ገኗል፡፡ ገራዦችማ ፋጤ
ተዘዋውራ ባስተማረችበት ሰፈር ግርዛት አይፈጽሙም፡፡

በቅርቡ አንዲያ የምትፈራው ሴት አንድ ልጇን ማን እንደወሰደባት ሳይታወቅ ታፍኖ ት እንዳለ ማወቅ አልተቻለም፡፡
የልጇን መታፈን የሰማችው ስለጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እያስተማረች ባለበት ሰዓት ስብሰባ እየመራች ነበር፡፡ ሆኖም
ስብሰባውንና ትምህርቱን ጨክና ለመጨረስ ሞከርች አንጂ ወደ ልጅዋ አልሮጠችም፡፡ በመጨረሳ ግን መልእክተኛው
ሲበዛባት ይቅርታ ጠይቃ ስትነሳ ተሰብሳቢው ሁሉ ሰማና ከፊሉ አዘነላት፡፡ ከፊሉም ‹‹በገዛ እጇ ነው›› እያለ ፈረደባት፡፡

እስዋ ግን ያን እለትም ሆነ በተከታታይ ቀናት ስራዋን ውስጣዊ ጉዳቷን ችላ የየዕለት ችግር የሆነውን ግርዛት፣ አስገድዶ
መድፈር፣ እጥል ማስቧጠጥ፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በተለይም ሚያበሳጫት በሚስት ላይ ሚስት ማግባትን
ለማስቀረት በተለያዩ ገተር ሰፈሮች በእግር እየተጓዘች ስራዋን ለማስራት ትጥራለች፡፡ የልጇን ጉዳይ ፖለስ ጣቢያው
አንደሚከታተልላት ቃል ገብተውላት እየተከታተሉ በየጊዜው እየነገሯት ነው የደረሱበት ውጤት፡፡ እስዋም ‹‹አርፈሽ
ብትቀመጪ ይሻልሻል፡፡›› እያሉ በተለያየ ስውር መንገድ መልእክት ሚያደርሷት ሰዎች አሉ፡፡ ለማንም ባትነግርም
በቅርቡ እየተቀራረቡ አብሮ በፍቅርና በትዳር ተሳስሮ ስለመኖር የሚወያዩት አካሌ የተባለ ወጣት ባለባጃጅ ለእሱ ብቻ
ነግራዋለች፡፡ እሱም ጉዳዩን ከፖሊሶች ጋር እየመከረበት ነው፡፡

በዚህ መሃል ምግበ በአግባቡ ባለመመገብና በድካም ሳቢያ አንድ ቀን አልጋ ላይ ተኝታ ትውላለች፡፡ ከራሷ ልጅ ሌላ የታላቅ
ወንድሟ ሁለት ልጆች አንዲሁም አንድ ታናሽ ወንድሟን ምግብ እመታበስለው ፋጤ ነች፡፡ አባቷ ከሞተ አምስት ዓመት
አልፎታል፡፡ እናቷን ያጣችው ገና በልጅነት ነው፡፡ ቤታቸው ገጠር ብትሆንም አገር አቋራጭ አስፓልት የሚተላለፍባት ቦታ
ስለሆነች አንዳንድ ዕቃዎች ለመሸጥ ምቹ በመሆኗ በዓል ሲቃረብ ሕፃናቱ ዶሮ እንቁላል ከፍ አድርገው ዘው ለአላፊ
አግዳሚ መኪኖች ያሳያሉ፡፡ ወንድሞቿም ጉቶ ጠርበው የመኪና ታኮ ደርድረው ይሸጣሉ፡፡ ገበያው ግን ያን ያህል
የሚያወላዳ አልሆነም፡፡

ፋጤ ጠዋት ማታ ወደ ሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ትሮጣለች፡፡ ወደ ፍርድ ቤት ትሄዳለች፡፡ የተጎዱ ቤተሰቦችን ትጤቃለች፡፡
አግልግሎቷና በሕብረተሰቡ መሃል ያላት ተቀባይነት ከከፍ ያለ ቢሆንም የምታገኘው ጥቅም የለም፡፡ በዚህ ሳቢያ አዲሱ
እጮኛዋ ይህንን ስራ ተይ እያለ ይጎተጉታታል፡፡ ደውላም ስትጠራው እየተበሣጨ ነበር ሲበር ወደ እስዋ የመጣው ፡፡
አቅራቢያው ወዳለች ከተማ ለህክምና ሲወስዳት ከተማው መሃል አንዲት እናት ልጇን ይዛ በባጃጁ ትሳፈራለች፡፡
እሚያወሩትንም ትሰማለች፡፡ እናት ልጇን አስገድዳ ለሰው ቤት ስራ ልታስቀጥራት እንደሆነ ፋቴ አወቀች፡፡ ልጁን
አናገረችው ህፃኑ ልጅ ‹‹አውቅሻለሁ ካሱ አይደለሽ›› ይላታል፡፡ ስልክ ደወለች፡፡ አንድ ፖሊስ በሞተር ተከተላት፡፡ ሲወርዱ
ይዘሃቸው ሂደ ትለዋለች፡፡ እስዋም ወደ ሆስፒታል ትገባለች፡፡ ሴትየዋ ሲወርዱ ትሰድባታለች፡፡

ፋጤ ተኝታ ሴትዬዋ የሰደበቻት ስድቦች ይረብሷታል፡፡ ስክ በተደወለ ቁጥር የተለያዩ ሰዎችን ችግር ከመስማት ውጪ
አንዳቸውም ‹‹አላህ ይማርሽ›› እሚላት ሰው አይገኝም፡፡

ምርመራ ተደረገላት፡፡ እንዲህ ስትታይ ቁመናዋ ዘለግ ብሎ በጥም ፊቷ ላይ ንቅት ያሉ ጠያቂ መርማሪ ዓይኖች ያላት
የከተማ ልጆች በብዙ ዘዴ ሊያመጡት እሚጥሩት ቀጭንና ዘለግ ብሎ ሞላ ያለ ሰውነት አላት፡፡ ብዙ ግዜ እጇን ና ረጃጅም
ጣቶቿን በፊቷ ደገፍ አድርጋ በአትኩሮት ነገሮች መከታተልና ማዳመጥ ይቀናታል፡፡ አዲሱ እጮኛዋ ኩርፍ ያለ ሰው ነው፡፡
በምትሰራው ስራ ደስተኛ አለመሆኑ ያስታውቅበታል፡፡ አንደውም ያበሣጨዋል፡፡

ፋጤ ግሉኮሷን እየወሰደች እንደማሸለብ አድርጎ ያቃዣታል፡፡


በልጅነቷ ከአባቷ ጋር ነበራት ፍቅር ልዩ ነው፡፤ አብዛኛውን የዛሬውን ስብእናዋን የገነባላት አባቷ ነው፡፡ በሰፈሩ ከግብርና
ስራው ውጪ ልጆችን ፊደል በማስቆጠር እንዲሁም በጤና ጣቢያው በልዩ ልዩ አገልግሎት የተሰማራ ሰው ነበር፡፡ ልጆቹን
ከአካባቢው ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች ተቆጥበው አንዲያድጉ በግልጽ ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያ አንደ አባገዳ ተከብሮ
ግን ደግሞ በኤነ ቁራኛም ይታይ ነበር፡፡ ልጆቹ ግን በነፃነት ስላደጉም ብዙ ጥያቄ ይጠይቁት ነበር፡፡ ፋጤም በልጅነት
ካልተገረዝኩ ብላ ማስቸገሯ ትዝ ይላታል፡፡ አባትዬው ግን በሰፈሩ በሚያደርገው ስራ ከአንዳንድ ባህላዊ ጉዳዮች ይገለል
ነበር፡፡

አባቷ ከሚነግራት ውጪ አንዳንድ የውጪ ድርጅቶች ከአዲሳባ ሲመጡ በሚያስተላልፏቸው መልእክቶች በትምህርት
ቤት በሚሰጠው የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ግለሰባዊና ማህበራዊ ብሎም አገራዊ ጉዳት ሳቢያ ፋጤ ሳታስበው ከሴቶች
ጉዳይ ሰራተኞች በላይ ሙሉ ግዜዋን በተለይ ለሴቶችና ሕፃናት ደህንነት በመስጠት አቅሟ ፈቀደውን ትጥራለች፡፡

አንድ ቀን የሰፈሩ ሴቶች ሰፈሩን በዕልልታ ሲያቀልጡት ሮጣ ትሄድና አብራ እልልል … ትላለች፡፡ እስዋ ደርሳ እልል ስትል
ግን ሴቶቹ ሁሉ እልልታውን ትተው ገለል ገለል ሲሉ…አይታ ትደነግጣለች፡፡ እቤትዋም ሄዳ ታለቅሳለች፡፡ ከዚያ በማግስቱ
በቀበሌ ገበሬ ማህበሩ ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስለጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በሰፈራቸው ስላለው አደጋ በተለይም ገራዥ የሆኑ
ሴቶች እነማን አንደሆኑ ፊትለፊት እንዲናገሩ በማድረግ የምታደርገውን ትምህርት ከፍ ወዳለ ደረጃ አደረሰችው፡፡
ኮሚቴ አቋቁማ ጎጂ ድርጊቶች በይፋ ማጋለጥ ቀጠለች፡፡ በዚያው አጋጣሚ ስለጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሚተላለፍ ድራማ
የሚከታተሉ ልጆች በክበብ አደራጀች፡፡ በተግባራዊ ስራም እንዲሳተፉ በማድረግ ቀደም ሲል በግልፅ ይደረጉ የነበሩትን
ተግባራት ከአካባው አስወገደች፡፡ ሆኖም በድብቅ ድርጊቶቹ አንዳልቀሩ ስለሚታወቅ እስዋን ባዩ ቁጥር የሚባንኑ ድርጊቱ
ፈፃሚዎች መሸማቀቃቸው አልቀረም፡፡

ሕክማናዋ እየተወሳሰብ ቢሄድም ሆስፒታል ድረስ ሊጠይቋት እሚመጡትን ስታይ ከእነዚያ ሰዎች ጋር ነበራት ግንኙነት
ትዝ ይላታል፡፡ አንዲት ልጅ ብቻውን ሊጠይቃት ይመጣል፡፡ ልጁ ቀጫጫ ነው፡፡ የቅጥነቱ ምክንያት ቶንሲል ነው ብለው
ያምናሉ ቤተሰቦቹ፡፡ ልጁም በእርግጥ እየቆየ የሚነሳ ቶንሲል አለበት፡፡ በአንድ ወቅት አንዲት ቶንሲል ትቧጥጣለች
እምትባል ሴት ቤታቸው መጥታ ከጨዋታ ሲገባ ተዋወቃት አክሰትህ ናት ተብሎ ከተዋወቃት በኋላ ቡናው ተፈልቶ
አርማጉሳው ተዘጋጅቶ አፈር ተቆልሎ ልጁን አባብለው ወደጓሮ ወስደው ጉሮሮውን አክስት ተባለችዋ ሴት ስትቧጥጠው
የልጁ አፍ ተከፍቶ ሙሉ ለመሉ እጇን አፉ ውስጥ ከታ ስትቧጥጠው ልጆ አፉን አንደከፈተ ይጮሃል… ሰፈቱ ጩኸቱን
ሰምቶ. ይሰበሰባል… የልጁ ጉሮሮ ደም በደም ሆኖ ደሙ ብዙ ሰዓት ይፈሳል… ሴትዬዋ እጅዋ ላይ ጓንት ሳይሆን የአርማ
ጉሳውን ቅጠል ነበር፡፡ ይህንን ጉድ ፋጤ ሰምታ በጣም አዘነች፡፡ ልጁን በሌላ ግዜ ሰዎች አገኙአት፡፡ ወደትምህረት ቤት
እሚሄደው በፋጤ በር ላይ ነው፡፡ በሌላ ግዜ ታሞ ድጋሚ ያቺን ሴትዮ ቤት ውስጥ ሲያያት ሮጦ ፋጤ ቤት ይሄዳል፡፡
ፋጤም ልጁን ይዛ ሰዎቹ ዘንድ ሄዳ ይህ ድርጊት ወንጀል መሆኑን ነግራ ሴትዬዋን ና ቤተሰቡን አስተምራ ልጁን ከተማ
ወስዳ በአንድ መርፌና በጣፋጭ ከረሜላ ያበጠ ጉሮሮው በአንድ ቀን አንዲመለስ አደረገች፡፡ ልጁም ከስቃዩ ተረፈ፡፡

ፋጤ ልጁን ስታይ ልጇ ትዝ ብሏት ማልቀስ ጀመረች፡፡ ልጁም እንባዋን እየጠረገ ቆየ፡፡ ፋጤ ሆስፒታል መግባቷን ያወቁ
የልጇ ጠላፊዎች፡፡ ወደ ሆስፒታል እሚገባውን ሰው እየጠበቁ ማንን ለመጠየቅ ነው እያሉ ይጠይቁ ነበር፡፡ ያኔም ያንን
ሕፃን ልጅ አግኝተውት ነበርና አንድ ወረቀት ሰጥተውታል፡፡ ፋጤ ልጇን አስታውሳ ስታለቅስ ልጁ ሰዎች ሰጡትን ወረቀት
ሰጣት፡፡ ያንን ወረቀት እያነበበች ይሄን ስራሽን ካልተውሽ እንደዚህ ወረቀት የልጅሽን ሬሳ እናስረክብሻለን፡፡›› ይላል፡፡
ሳይታሰብ እሪታዋን አቀለጠችው ፡፡ ሆስፒታሉ ተረበሸ፡፡ በሆስፒታሉ ያሉ አስታማሚዎች ሮጠው ወደ እስዋ ያለችበት
ክፍል ገብተው ሞሉት፡፡ ከእነዚያ መሃል አንድ ወንድ ገባ ብሎ ሲወጣ ማንም አላየውም፡፡ ያ ሰው ሁኔታዋን አይቶ
አስታማሚና ጠያቂ እንዲሁም ለወሬ የመጣ መስሎ በርቀት ቆመ እስዋም እየተወራጨች ‹‹ ልጅን አንድ ልጄን…››
ስትል… ሰዎች ሲያባብሏት … መለስ ስትል ድንገት አይን ለዓይን በርቀት ተገጣጠሙ… እሱ ወዲያው ዞር ብሎ ሄደ፡፡
እስዋ ግን ሰዎቹ ወደየክፍላቸው ከሄዱ በኋላ… ያ ያየችው ሰው መልኩ ፊቷ ላይ ይሳልባታል… ቆይቶም ውል ይላታል..
ትንሽ ሲቆይ የሚናገረው ነገር ይሰማታል ወዲያው ብንን ትላለች… አብረዋት አንድ አልጋ የያዙ ሰዎችን ትኬር ብላ
ታያቸዋለች፡፡ ….

አንዲት ልጅ ጫካ ውስጥ ተደፍራ ከጓደኞቿ ጋር በምሽት ጩኸት ሰምተው ሄደው አንስተው ወስደው ያሳክሟታል፡፡ ያ
ወንድ ነኝ ባይ ማን እንደሆን ወይ እንማን እንደሆኑ ክትትል አድርጋ ትደርስባቸውና ፍርድ ቤት አቁማ ታስቀጣቸዋለች፡፡
ደፋሪው አንድ ሰው ነበር፡፡ ጎይቶም ይባላል፡፡ ይባላል፡፡ ቀደም ሲል ደፍሯታል እናቷ ቤት፡፡ በድጋሚ ደግሞ ወደ ጫካ ወስዶ
ሲደፍራት ነው ያኔ ልጅቱ ድረሱልኝ ስትል የጮኸችው፡፡ ….. የእሱ ብልግና በቆንጨራ እያስፈራራ በጥፊው እየጠፈጠፈ
ፊቷን ማድማቱ ነው ፋቴን ያንገበገባት፡፡ ወንድሞቿ ይዘን እንዴት አንደሚያም ጠፍጥፈን እናሳየው ሲሏት እምቢ ብላ
ነው፡፡ እሷ ሁሌም በህግ ከማስፈረድ ውጪ የበቀል እርምጃ አንዲወሰድ አትፈቅድም፡፡

ወንድሞቿ የህታቸውን ልጅ ለማግኘት አደን ከወጡበት አልተመለሱም፡፡ ጤቃዋትም አያውቁም፡፡ የዚያን ዕለት ግን
ደወሉላት፡፡ ዱካቸውን እንዳገኙም ነገሯት፡፡ ተስፋም አደረገች፡፡ እስዋም በተለይ ያንን ያስፈረደችበትን ሰው
እንዲከታተሉ ነገረቻቸው፡፡ እሱ መሆኑን በም አወቅሽ አንቺ.. ብለው ተገረሙ ወንድሞቿ፡፡ ሆስፒታል መጥቶ እንደነበር
አላወቁምና፡፡ ሆነችወንም አልሰሙምና፡፡

ጎረቤት የታመመችዋን ልጅ እሚያስታምሙት ሁለት ሴቶች ፋጤ አንዳንዴ ጤናማ ጥያቄ አንዳንዴም የቅዠት
እሚመስል ጥያቄ ትጠይቃቸዋለች፡፡ ለካንስ ሁለቱ ሴቶች አንድ ምስኪን ቀችን ሰውዬ ሚስቶች ናቸው፡፡ ሰውዬው ሲጋራ
ስለሚያጨስ ወደክፍሏ ሲገባ ቤቱ ሲሸት ፋጤ ትቆጣዋለች፡፡ ምነ ደርግልሃል.. ሁለት ሚስቶች ይዘህ… እዚያ ሆና ስለ
አንድ አጎቷ ትነግራቸዋለች፡፡ አጎቷ አራት ሚስቶች ስላሉት ብዙ ቦታ ስታስተምር በእሱ ምክንያት ትወቀሳለች፡፡ ታማ
መጥቶ አልጠየቃትም፡፡ ከሚስቶቹ ሶስቱ መትተው ጠይቀዋታል፡፡ አንዷ ግስላረጀች ከቤትም አትወጣ፡፡

ፋጤ ሕክምናዋን ጨርሳ መውጣት ቢገባትም ልጇን ካላገኘች ጥሩ አይደለም ተብሎ ፖሊስ አዛዡ እዛው አንድትቆይ
ከሆስፒታሉ አመራሮች ጋር ይመካከራል፡፡ ሆኖም አንድ ብሩህ ቀን እጮኛዋ ቀድሞ ሲሮጥ ይመጣል፡፡ የሆኑ ሰዎች
ሊመጡ ነው በደንብ ልበሺ ይላታል፡፡ በደንብ ትለብሳለች፡፡ ተስተካክላም ትጠብቃቸዋለች፡፡ ምንድናቸው ጋዜጠኞች
ናቸው እንዴ እነሱ ኮ ሁሌም በህልሜ እየመጡ እየጠየቁኝ ነው ትልና ታስቀዋለች፡፡ አይደለም እነዚህ በጣም የተከበሩ
ናቸው፡፡

ያስገባቸዋል፡፡ ትንሹ ልጇ በአዲስ ልብስና ጫማ በመኮንኖች አለባበስ አጊጦ በፖሊስ አዛዡና በሁለት ዋርድያዎች ተከቦ
ይገባል፡፡ ፋጤ አልልል ትላለች ልትነሳ ስትል ልጁ ቀድሞ ጥምጥም ይልባታል፡፡ ሁሉም በደስታ ይዋጣሉ፡፡ እስዋ
ታለቅሳለች፡፡ ትለፈልፋለች፡፡ አስበልቼህ ነበር ልጄ ትለዋለች፡፡

አብረው ከእስር ቤት ሊወጡ ይወጣሉ፡፡ የሰፈራቸውም ሴቶች ቤትዋን አሰማምረው ይጠብቋታል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት
ያገኘቻቸውን ምስክር ወረቀቶች ለጣትፈው ቤቷን አስውበው ወለሉ ሳር ተጎዝጉዞበት ወደ ቤቷ ትገባለች፡፡ በሯ ላይ
ፋጤን ጅርቲ ዋ…. የሚል ጽሁፍ ተጽፎበት ፎቶዎቿ በባነር ተሰቅለው ግቢውን አጊጠውታል፡፡ ያን ዕለት ባለባጃጁ
ቀለበት ይዞ ሊመጣ ሲል…. ባጃጁ ከትልቅ መኪና ጋ ተጋጭታ ወዲያው ፋፍሰው ወደ አዲሳባ ወስደውት ቢጠበቅ ቀረ….

ጉዞ ወደ አዲሳባ ፡፡

(ተፈጸመ)

You might also like