You are on page 1of 2

አንድ ሰው

በእድላዊት ደስታ

በስንት ጥበቃ የመጣው ታክሲ የሞላ አንድ ሰው የቀረው…….. እያለ መጥራት ከጀመረ እራሱ አንድ ሰአት
አልፎታል ታክሲ ዉስጥ ከኔ በተጨማሪ አስራ አራት ሰዉ አለ እቺን ለ አስራ ሁለት ሰው የተሰራች ታክሲ
በግርግር አዉቶብስ አረጎት እኮ።

አዉቶብስ ስል ሁሌም ትዝ የሚለኝ የቀድሞ አከራዬ ወ/ሮ በላይነሽ ሞገሴ ምትኩ የነገሩኝ ታራክ ነዉ ለምን
የቀድሞ ማለት አስፈለገ እኔ ከእሳቸው ቤት መከራየት አቆምኩ እንጂ እሳቸው ቤት ማከራየት አላቆሙ ለቀድሞ
ለማለት ያለ ጉጉት አያታቸው ባወረሶቸዉ 1000 ካሬ ግቢ መሀል እንደ ኮረዳ ጡት ከሚታየው ሰርቪስ ጀርባ 1
ሰባት ቤቶች አከራይተው ሌላውን ግቢ ነግሰዉበታል እኔም ከሰባቱ በ አንዶ መሽጌአለው ታዲያ አንድ ቀን የቤት
ኪራይ ልሰጣቸው ከቦርሳዬ ስገባ የአንበሳ አዉቶብስ ትኬቱ ዱብ ምን አስደነገጠኝ ግን ውይ ውይ ዳር እስ
ከዳር…….. አቤት የስሜ ርዝመት ሳስበዉ ያኔ ቤተሰቦቼ ስራ አልነበራቸውም…..አሁን ለእኔ 40 ኪሎ ከቦርሳ ጋር
ለማትሞላ ልጅ ዳር አይበቃም ወይ እስከ አቤት ርዝመት ስንት ቦታ የአባት ስም ሳይጠይቁኝ እሱም ይባስ ብሎ
የአያት ሳይጠይቁኝ አለፈ….ዳር እስከ ዳር አሉኝ በግራ እና በቀኝ እንደ ፈሬቻ የሚያበሩ የወርቅ ጥርሳቸውን
እያሳዩኝ አሁንም በ አዉቶብስ ነዉ የምትሄጅዉ አዎ እማማ አልኩ መሬት መሬት እያየዉ አሁን የሄ መልክ ሸኝ
አቶ ነው ዝም ብዬ ፈገግ መሬት እያየዉ (እንቺ አሮጊት ገንዘብሽን ሰጠዉሽ ሌላው ምን አገባሽ በሆዴ እላለሁ)
ከእኔም ባትበልጪ ቆንጆ ነሽ ። አሁንም እህህ እላለዉ እኔ ባንቺ ግዜ ልሸኝሽ የሚለዉ ብዛቱ በእግሬ ስሄድ ሁላ
ልዘልሽ የሚሉኝ ነበሩ አይ እንደዉ ሚስጥር ነዉ አሉ ፈገግ እያሉ ጃንሆይ እራሳቸዉ ወደ ለንደን ሊሄዱ ወደ
ኤርፖርት እየሄዱ መኪና ዉስጥ ሆነው አይተዉኝ ከሚሄዱት ቀርተዉ እኔን ሸኝተዉኝ ነበር አሂሂሂ ረጅም ሳቅ
እኔም ማጀብ ጋባዥ እና አከራይ ሲስቅ ማጀብ ግዴታ ነዉ ።

ለመሆኑ ዛሬም ያ አንበሳ ባሱ በር ላይ አሁንም አለ አዋ እማማ ለመሄድ እየተቻኮልኩ ለመሆኑ አዉቶብስ


ለምን እንደተባለ ታዉቂያለሽ እረ አላዉቅም እማማ (ምን አለ አዉቃለዉ ብዬ በተገላገልኮቸዉ ) ያኔ አዲስ አበባ
ጋሪ፣ቮልስዋገንና ሴቼንቶ ነበር የነበረው ታዲያ….. ወይኔ ዳር እስከዳር የቮልስዋገንና እና ሴቼንቶ ታሪክ ይቀረኛል
እያልኩ አወራለዉ በሆዴ ታዲያ ብለው ቀጠሉ ይሄ የናንተዉ አንበሳ እንደገባ አንድ ሴትዮ 2 ሰአት ጠብቀዉት በ
3 ተኛዉ መጣ ሲገብ አሰፍስፈው ሳይጭናቸዉ እብስ ቆመዉ በማማር ይሄ ምን መኪና ነዉ አዉቶብስ ነዉ እንጂ
አሉ በዛው ቀረ አዉቶብስ ተብሎ ሂሂሂ ረጅም ሳቅ እኔም አብሬ ማጅብ ማን በነገራችው አሁን አንድ አዉቶብስ
17 ሚሊዮን ብር እንደገባ ጀቴ ነበር ማለት ይሄን ባስ…… ከ ሀሳቤ ስመለስ ታክሲዉ 14 ሰዉ የነበረው 24 ሆኖል
ወደ ሰፈሬ ደረስን ቀን 10 ብር የነበረው መንገድ ማታ 20 ብር ከፈለን ቆይ ማታ መንገዱ ይረዝማል እንዴ ወይስ
ለመብራቱ እያስከፈሉን……።

ግልምጫዉን እንደ ሰላም ግቢ ወሰድኩለት አንድ ሰዉ አንድ ሰዉ ቆይ ስንት ነው ነገሩ priority እንዲሆነ ሠዉ
መብዛት አለበት ማለት ነው ለአብዛኞቻችን statics የሆነው አንድ ሰዉ ለቤተሰቦቹ እንደዛው ነዉ አንድ አባት
ለቤተሰብ አንድ ብቻ ነዉ በሀገራችን መብት የቡድን እንጂ የግለሰብ አይደለም ግለሰብን ያላከበረ ቡድንን ማክበር
…..የአናሣዋችን ድምፅ በብዙሀን መሻር….. በ አንድ ስብሰባ 50 ሰዉ ቢኖር እና በስብሰባው አጀንዳ ተስማምተዉ
አንዱ ባይስማማ ምንም ስለ አንዱ አለመስማማት አይጠይቅም ስለ 49 እንጂ ሰዉነትን በቁጥር ገድበነዋል
imphaty አተናል ሁሉ ነገር ቁጥር ቁጥር ቁጥር ይሄ ህመም ነዉ የመኪና አደጋ ቢደርስ ስንት ሰዉ ሞተ ነዉ
ጥያቄው ዜናዉም ዛሬ የትራፊክ አደጋዉ ቀለል ያለ ነዉ አንድ ሰዉ ብቻ ነዉ የሞተዉ/የሞተችው አንድ ሰዉ ብቻ
በዛ አደጋ አንዲት 8 ልጃች የምታሳድግ እናት ብትሞት በመኪናዉ አንድ ሰዉ ብቻ ነዉ የሞተዉ የግለሰብን መብት
አለማክበራችን የግለሰብን ዋጋ አለመመዘናችን የቡድንም መብት ለመጣስ መንገድ ሰቶናል አንድ ቦታውን
የማላስታውሰው ቦታ የነበርኩበትን ነገር የአንድ ሰዉ መሞት ሞት ነዉ የብዙሃን ግን statics ነዉ ይላል
አብዛኞቻችን statics ሆነናል እኔ ግን እላለሁ የአንድ ሰዉ መብት ባልተከበረበት የብዙሀኑ ዘበት ኸረ ግጥም
ተመስገን ሀሳቤን የፈጠረ ጌታ ቤቴ ደረስኩ ሀሳቡ ይቀጥላል 1 ሰው 1 ሰው 1 ሰዉ ……………….

You might also like