You are on page 1of 10

የWellington ጽርሃ ጽዮን

ቅ/ማርያም Wellington ጽርሃ


ጽዮን ቅ/ማርያም ቤ/ክ ሰ/ት
ም ቤ/ክ ሰ/ት

የሰኔ ማርያም በዓል መዝሙሮች


ለቤተ ክርስቲያን ልዑል ቤተክርስቲያን ዘክርስቶስ
ለቤተ ክርስቲያን ልዑል ሐነጻ /2/ የጸጋው ግምጃ ቤት ማኅደረ መለኮት
በጽድቁ ሓወጻ እምነጸሃ ይበርህ ገጻ የሰማይ ደጅ ነሽ የጽድቃችን ፍኖት
ምስካየ ሕዙናን ታዛ መጠለያ
አንድነት ሦስትነት መሰረትሽ ሆኖ
ዘመናት አለቁ ሚስጥርሽ ጠቅሎ በምድር የተተከልሽ የሰማይ አምሳያ
የአበው ምሳሌ የነቢያት ተስፋ
ባንቺም ተገለጠ በአንቺም ተስፋፋ ቤተክርስቲያን ዘክርስቶስ
አዝ.. ማይልሽ መንፈስ ቅዱስ
አብ በቃሉ የቀደሰሽ
ቤቴልሔም አንቺ ቀራንዮም አንቺ
የማትጠገቢ የማትሰለቺ ቅድስቷ ቤት አንቺው ነሽ
የድሕነት በራችን የሚስጥራት ዓውድ
ቤተክርስቲያን ነሽ አካሉ ለወልድ ከልጅነት ስልጣን ጠርተሽን በቃሉ
አዝ.. ከውኃ ከመንፈስ ተወልደን በስሙ
ከብረናል በቤትሽ በሥጋ ወደሙ
አህዛቡ ሕዝቡ አንድ የሆኑብሽ
ኃይል ቤዛ ሆኖን ነገረ መስቀሉ
ቤተክርስቲያን ሆይ የሁሉም እናት ነሽ
ለሊቃውንት ዜማ ለቅዱሳን ጸሎት አዝ
መሰላሉ አንቺ ወደ አምላክ ጸባዖት የአብራክሽ ክፋይ ደም እያፈሰሰ
አዝ.. ተመልሷል ጠላት ቀስት እየጨረሰ
ስምሽን የያዙ ተጋድሎአቸው ገኖ
የተማጸነብሽ አንቺን የተጠጋ
ይልቅ አከበሩሽ ደማቸው ዘር ሆኖ
የክብር ባለቤት ነው በጸጋ ላይ ጸጋ
ተብለናልና ወደ እርሷ ገስግሱ አዝ
ወገኖቻችን ሆይ ይህንን ቃል አትርሱ የአትናቴዎስ ስብከት የአበው ኪዳናቸው
ቤተክርስቲያን ነሽ አምባ መጠጊያቸው
እንመሰክራለን ያንቺን ልዕልና
ሠላም ለኪ እንበል ይገባሻልና
ማርያም ድንግል መክሆን አንቺ የወይን ሐረግ
ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ/2/
ይእቴኬ ቤተ ምስአል ዘአስተአጸቡ ታቀልል
ምግብ ሆኖ/2/ ተሰጠን ፍሬሽ ለኛ ቤዛ/2/ ኧኸ
ለኩሉ ፍጥረት ትተነበል በአክናፈ መላእክት ትትኬለል
ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፊል
ባንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣው ፀሐይ /2/
ማርያም ድንግል መመኪያቸው የደናግል ብርሃን ነው /2/ ለጻድቃን ስሙም አዶናይ /2
እርሷም እኮ የምልጃ ቤት ናት የሚያስጨንቀውን የምታቃልል ኧኸ
አዝ...
ለፍጥረት ሁሉ ትማልዳለች በመላእክት ክንፎችም ትጋረዳለች
እርሷ ትበልጣለች ከኪሩቤል ደግሞም ትልቃለች ከሱራፌል ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ
/2/
ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል ለመላእክት /2/ የማይቻል ነበልባሉን የቻልሽ /2/
ይእቴኬ ቤተ ምስአል ዘአስተአጸቡ ታቀልል ኧኸ
ለኩሉ ፍጥረት ትተነበል በአክናፈ መላእክት ትትኬለል አዝ...
ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፊል
የመሶብ ምሳሌ ድንግል የኮከብ መገኛ /2/
በሥጋችን በነፍሳችን እንዳንራብ አንቺ አለሽን ለኛ
/2/ ኧኸ
ወደ ምስራቅ እዩ ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
ወደ ምስራቅ እዩ ወደ ጸሃይ መዉጫ ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
ድንግልን ክበቧት እንበል ሃሌሉያ የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
ለአምላክ እናት ላዛኝት የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
እልል እንበል እንዘምርላት/2/ የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ

ወገኖች ተነሱ እናታችን መጣች ሁሉንም በሁሉ በሚሞላ ጌታ


ስሟን ስንጠራ መች ትቀራለች ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ
የተከዘን ልታጽናና በክብር በሞገስ በፀጋ ተሞልታ
ነይ ስንላት ትመጣለችና /2/ ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ /2/
አ.ዝ-- አዝ
የጽጌው ማህሌት በፀሎት ሲጀመር ዲያቢሎስ ቢጨርስ ቀስቶችን በሙሉ
ማርያም ትመጣለች በደመና በአየር ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዟችን ሁሉ
ንዒ ስንል በሰዓታት እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን
ልትባርከን ትመጣለች በእውነት /2/ አንዳች አይነካንም እሱን ተደግፈን/2/
አ.ዝ-- አዝ
ፍስለታ ሲጀመር ቃል ኪዳን ገብታለች በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት
የሌሊት ውዳሴ ንዒ ትሰማለች ስለስሙ መኖር በስሙ መሞት
ህፃናትን በበረከት ጠላት ዲያቢሎስን ምን ባያስደስት
ልትጎበኝ ትመጣለች በእውነት/2/ ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ሕይወት/2/
አ.ዝ-- አዝ
በፍፁም ቸርነት እንዲምረን ጌታ ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው
በአማላጅነትሽ ሁኝልን መከታ ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው
እናታችን አለኝታችን አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት
እንድናለን ድንግል አንቺን ይዘን/2/ ሃይማኖታችን ነው የኛ ርስት ጉልት/2/
ጸምር ጸዓዳ ከክርስቶስ ፍቅር
ጸምር ጸዓዳ መሶበ ወርቅ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማነው(2)
እንተ መና መሶበ ወርቅ መከራ ችግር ሥቃይ ወይስ መራቆት ነው(2)
በትረ አሮን እንተ ሰረጸት/2/ መሶበ ወርቅ
አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም (2)
ቀዳማዊት ምድር ያላረፈብሽ የዘር ምልክት እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም(2)
ዘላለም ድንግል የታተምሽ ለመዳን ምክንያት
እናትነትን ያስማማሽ ከድንግልና
ለዓለምም ሁሉ የወለድሽ የሕይወትን መና የሰማይ ቤታችን አማኑኤል የሰራው
አዝ.. ግንቡ ንጹሕ ውሃ መሰረቱ ደም ነው/2/
የዓለምን መድኃኒት የጸነሽ መዝገበ ምስጢር
ዘባነ ኪሩቤል የተመቸሽ ሀገረ እግዚአብሔር
ሳይነጋ ተራምደን እንግባ በጠዋት(2)
ፀሐይን ያስገኘሽ እመ አምላክ ብርህት ሰማይ
የነቢያት ትንቢት ማህተም ዕንቁ ባህርይ በደሙ መሥርቶ ከሰራልን ቤት(2)
አዝ..

የቅዱሳን መዓዛ አክሊላቸው ሞገሳቸው ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት(2)


መሶበ ሕይወት የኖሩብሽ ስምሽን ጠርተው የውሃ ግድግዳ የደም መሠረት(2)
ለጽጌ ድንግል ያሬድ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም
የብርሃን ፋና ሆንሽላቸው ድንግል ማርያም
የውሃ ግድግዳ የደም መሠረት(2)
ይኸው እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት(2)
ደስ ይበለን
ደስ ይበለን/2/
አምላክ አለ መሐላችን
ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
ገናና ነው አምላክ ክብርህ
ምሕረቱን አይተናልና
አድርሶናል አምላክ በጤና
ይችን ዕድሜ ለጨመረልን
ለንስሐ ጊዜ የሰጠን
አ.ዝ-----------------------
ኃጢአትህን ይታገስሃል
በቸርነት አምላክ ያይሃል
ደስታ ነው በሰማያት
በአንድ ኃጥእ የፅድቅ ሕይወት
አ.ዝ-----------------------
እልል በሉ የጎበኛችሁ
በምሕረት አምላክ ያያችሁ
በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ
አመስግኑ ዝምም አትበሉ
አ.ዝ------------------------
ድንግል ማርያም ትጸልያለች
ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች
በድንግል ክብር እንኖራለን
በጽኑ ፍቅር አንድ ቢያደርገን
አጭር መዝሙሮች
ንጽህተ ንጹሃን
ንጽህተ ንጹሃን ከዊና ከመ ታቦተ ዶር ዘሲና
ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና ነበረት (2)
ሲሳያ ህብስተ መና ወስቴሃኒ ስቴ ጽሞና (2)

ዝንቱ ኩሉ ኮነ
ዝንቱ ኩሉ ኮነ /2/ በጽርሐ ጽዮን
በፈቃደ (4) እግዚአብሔር

ሰዓሊ ለነ
ሰዓሊ ለነ(3) ማርያም እመ ብዙሃን (4)
ለምኝልን (3) ማርያም የሁሉም እናት (4)
አይኑ ዘርግብ (3) ሚካኤል ሃመልማለ ወርቅ (4)
ክንፉ ጸለላ (3) ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ (4)

እንተ ተሐንፀት በስሙ


እንተ ተሐንፀት በስሙ ወተቀደሰት በደሙ ቤተክርስቲያን /2/
ወተአትበት /2/ በዕፀ መስቀሉ
እስመ ኃይለ እግዚያብሔር ላዕሌሃ/2/

ሀባ ሰላምከ ለኢትዮጵያ
ሃሌ /2/ ሃሌ ሉያ /2/
ሀባ ሰላምከ ለኢትዮጵያ/2/
ሃሌ/2/ ሃሌ ሉያ /2/
ስጣት ሰላምህን ለኢትዮጵያ/2/
አጭር መዝሙሮች
ውስጤታ ታቦት
ውስጤታ ታቦት በውስጤታ ኦሪት በውስጤታ (2)
ይኬልልዋ በወርቅ ይኬልልዋ (2)

ፅላት ዘሙሴ ፅላት


ፅላት ዘሙሴ ፅላት/2/ ፅላት ዘሙሴ ፅላት/2/ማርያም ቅድስት
ሙሴ ከፈጣሪው የተቀበላት አስርቱ ትዛዛት የተፃፈባት
ፅላት ዘሙሴ ፅላት/2/

ይእቲ እፀ መዳኒት/2/
ይእቲ እፀ መዳኒት/2/ ማርያም ቅድስት

አንዲት ናት
አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥላት ክርስቶስ
በደሙ የመሠረታት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

ርዕይክዋ
ርዕይክዋ ለቤተክርስቲያን አፍቀርክዋ ለቤተክርስቲያን
ዘኢትዮጵያ (x2) ቤተክርስቲያን
አጭር መዝሙሮች
ሐመልማለ ወርቅ
ሐመልማለ ወርቅ/3/
ማርያም /3/ ሐመልማለ ወርቅ

ማርያምሰ
አኸ ማርያምሰ አኸ እንተ በምድር/2/
አኸ በሰማያት ታንሶሱ በሰማያት /2/

መሠረተ ሕይወት
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድሃኒት ዘእምቀዲሙ /2/
ለወልድኪ /2/ አምሳለ ደሙ /2/

ማርያም ተዐቢ
ማርያም ተዓቢ እምኲሉ ፍጥረት
ኢያውአያ እሳተ መለኮት /2/
አጭር መዝሙሮች
መዓዛ ሰናይ
መዓዛ ቅዱስ /2/ መድሃኒአለም መዓዛ ቅዱስ /2/
መዓዛ ቅድስት/2/ ድንግል ማርያም መዓዛ ቅድስት /2/
መዓዛ ሰናይ /2/ ሚካኤል / ገብርኤል መዓዛ ሰናይ /2/

አመ ትትሐነፅ
አመ ትትሐነፅ ቤተክርስቲያን
በዕንቈ ሰንፔር ወበከርከዴን በዕንቈ ሰንፔር /2/

ዓረፋቲሃኒ ለቤተክርስቲያን ወማኅፈዲሃኒ


በወርቅ ንጹሕ ወመርኅባሰ ለኢየሩሳሌም/2/

በምድራዊ ሕይወት
በምድራዊ ሕይወት በፈተና ቦታ/2/
ማርያም ትጠብቀን እጆቿን ዘርግታ ድንግል ትጠብቀን እጆቿን ዘርግታ /2

በሰላም
በሰላም በሰላም ንኢ /2/ እኸ ማርያም (2) እኽ ምስለ ሚካኤል
እኸ ማርያም (2) እኽ ምስለ ገብርኤል

You might also like