You are on page 1of 1

ቀን

ለአልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮልጅ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ዲን


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የምረቃ ሴሪሞኒ ላይ ለመሳተፍ ስለመጠየቅ፣

በአልፋ ትምህርትና ስልጠና አክሲዮን ማህበር ስር በሚገኘው የአልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በማስተርስ ፕሮገራም የ2013 2ተኛ
ተርም ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ፕሮጀክት ማኔጅመንትና አካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎች ለተከታታይ ሦስት ተርም
ትምህርታችንን በአግባቡ ስንከታተል የቆየን ሲሆን አሁን ግን የመጨረሻውና የመመረቂያ ፅሁፍ የምንሰራበት ተርም እንደሚቀረን
ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በሦስቱም ዲፓርትመንት ያለነው ተማሪዎች በመስማማት በመደበኛ የክረምት የምርቃት ዝግጅት ብንሳተፍ እኛም ሆነ
ቤተሰቦቻችን፣ጓደኞቻችን ደስተኛ የምንሆን መሆናችንን እየገለጽን ነገር ግን የምርቃት ፕሮግራሙን ስለተሳተፍን ብቻ የመመረቂያ
ፅሁፍ ጨርሰን ድፌንስ ሳናደርግ ምንም አይነት የማስተርስ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ ላንጠይቅ የተስማማን ሲሆን ዩኒቨርሲቲ
ኮሌጁ ባስቀመጠው ፕሮግራም መሰረት የመመረቂያ ጽሁፋችንን ሰርተን ድፌንስ ካደረግን በኋላ የማስተርስ ጊዜያዊ የትምህርት
ማስረጃ የምንጠይቅ መሆኑን ቃል እየገባን በላይ በተገለጸው ጉዳይ የተስማማነው የተማሪዎች ስም ዝርዝር፣ መመዝገቢያ
ቁጠር፣ሴክሽን እና ፊርማችንን የያዘ ገፅ ሽኝ አድርገን ያስገባን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ//

➢ ለዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

➢ ለፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

➢ ለም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

➢ ለሬጅስትራር ጽ/ቤት

You might also like