You are on page 1of 5

ሠው በምድር እስከመቼ?

ኢሎን መስክ የተወለደው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1971 በደቡብ አፍሪካ ሲሆን አባቱ ደቡብ አፍሪካዊ እናቱ ደግሞ
ካናዳዊት ናት፡፡ ገና በልጅነቱ ብዙ መፅሀፍትን ያነብ ነበር፡፡ የሚያበው መፅሀፍ ሲያልቅበት ትላልቅ ኢንሳይክሎፒዲያዎችን
(የእውቀት መፅሀፍ ማለት ነው) በ 9 አመቱ ያነብ ነበር፡፡ ግዜውን በአብዛኛው ብቻውን እያነበበ ነበር የሚያሳልፈው፡፡
ትምህርት ቤት ውስጥ ልጆች ይቀልዱበትና ያሰቃዩት ነበር፡፡ አንድ ግዜ እንዲያውም ነገሮች ከረው በመደባደቡ ሆስፒያል
እስኪገባ ድረስ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ለትምህርቱ ያለው ፍቅር እያደገ ሄደ፡፡ የ 10 አመት ልጅ እያለ
ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እራሱን አስተምሮ ከ 2 አመት ቦሃላ የኮምፒውተር ጌም መስራት ቻለ፡፡ ለአንድ ትንሽ
ድርጅት ጌሙን ሽጦም 500 ዶላር ማግኘት ቻለ፡፡ ያኔ የሰራው ጌም እስካሁን ድረስ ኢንተርኔት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ልጅ አሁን ትልቅ ሰው ሆኖ የግዜውን ሳይንስ ወደፊት እየገፋ ያገኛል፡፡ አስኪ ስለዚህ ሰው ህይወት አብረን
እንመልከት፡፡
ሳይንስ በታሪክ የሰውን ልጅ ህይወት ወደፊት ካራመዱት መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ ተቀዳሚው ነው፡፡ በየ ዘመናቱ
የሳይንስ ፈጠራዎችን ቀድሞ ከነበረበት ደረጃ የሚያሳድጉ፣ ከዘመናቸው በላይ ማሰብ የቻሉ ሰዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ
በታሪክ ውስጥ በ 1900 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ታዋቂው አልበርት አንስታይን ለሳይንስ ማደግ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱ
ተመራማሪዎች የሚጠቀስ ሲሆን የጀነራል እንዲሁም እስፔሲፊክ ሪሌቲቪቲ ቲዮሪዎችን (General and specific
Theory) በመፈልሰፍ አሁን በዚህ ግዜ የምንጠቀምበትን የጂ.ፒ.ኤስ (GPS) ቴክኖሎጂ እንዲገኝ መሰረት ጥሏል፡፡ በ
ጂ.ፒ.ኤስ (GPS) አማካኝነት ከቦታ ቦታ በቀላሉ መንቀሳቀስ እንችላለን፤ አውሮፕላን ሁሉ መብረር የሚችልው በዚህ
ቴክኖሎጂ አማካኝነት ነው፡፡ በ 1680 ዎቹ የነበረውን ግራቪቲን ህግ አይሳክ ኒውተንን፣ በ 1600 መጀመሪያዎቹ
የነበረውን ለህዋ ሳይንስ ማደግ ትልቅ ሚና የተጫወተውን ጋሊሊዮ ጋሊሊን፣ በ 1870 ዎቹ የነበረውን የመብራት
አምፖልን ለሁላችንም በሚደርስ መልኩ የሰራውን ቶማ ኤዲሰንን እነዚህን እና በርካታ ሰዎችን ማንሳት እንችላለን፡፡

ዛሬ ልናስተዋውቃችሁ የምንወደው በዚህ በኛ ዘመን አዲስ ነገርን ሊያመጣልን እየሰራ ያለውን ኢንጅነር እና የቢዝነስ
ሰው አሎን መስክን ነው፡፡ ይህ ሰው በቀዳሚነት በ 2025 የሰውን ልጅ በማርስ ለማሳረፍ እቅድ ይዞ ከመንቀሳቀሱም
በላይ በነዳጅ የሚሰሩ ለአየር ንብረት ብክለት ምክንያት የሆኑ መኪኖችን አስወግዶ በኤሌክትሪክ ብቻ የሚሰሩ መኪኖችን
ሰዎች እንዲጠቀሙ ለሁሉም ሰዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ሊዳርስ በሚችል መልኩ ሲሰራ ቆይቷል፣ እየሰራም ነው፡፡ እስቲ
ስለዚህ ሰው ህይወት አና ውጣ ውረዱ እንንገራችሁ፡፡

የኢሎን መሰክ መንግስት መገንባት የጀመረው በፈረንጆቹ በ 1999 ከወንድሙ ኪምባል ጋር ከሰሩት ሶፍትዌር
ቦሃላ ነው፡፡ ይህ ሶፍትዌር ከተማ ውስጥ ያሉ ቢዝነሶችን ሁሉ በአንድ ላይ አድርጎ ተጠቃሚዎችን ከሻጮች ጋር
በቀላሉ ያገኛኝ ነበር፡፡ ይሄን ሶፍትዌር ከወንድሙ ጋር ሆነው በ 22 ሚሊየን ዶላር መሸጥ ቻሉ፡፡ ኢሎን መስክ
በ 27 አመቱ ያገኘውን 22 ሚሊየን ዶላር ኤክስ ዶት ኮም የሚባል ካምፓኒ ላይ መልሶ ኢንቨስት አድርጎት
የገንዘብ ዝውውርን በአዲስ መልኩ ለአለም ማስተዋወቅ ቻለ፡፡ ይህ ካምፓኒ አሁን ፔይ ፓል (Pay Pal) በመባል
ይታወቃል፡፡ ትንሽ አመታት ቆይቶ ኢሎን መስክ ይሄንን ፔይ ፓል (Pay Pal) የተባለ ካምፓኒ ሽጦ 165
ሚሊየን ዶላር የራሱ ማድረግ ቻለ፡፡ ለዚህ ወጣት ይህ ሽያጭ መድረሻው ሳይሆን መንደርደሪያው ነበር፡፡

ብዙም ሳይቆይ ፊቱን ወደ ሰማይ ከፍ አድርጎ የህዋን ምርምር ለማሳገድ ቆርጦ ተነሳ፡፡ ባገኘው ገንዘብ መሪ ሀሳቡ የሰውን
ልጆች በሌላ ፕላኔቶች ላይ ማሳረፍ የሆነውን ስፔስ እክስን (SpaceX) ለማቋቋም ቻለ፡፡ ኢሎን መስክ ይሄንን አዲሱን
ድርጅትቱን ለማቋቋም ስላነሳሳው ሀሳብ ሲናገር "ሰዎች ወደፊት ይሆናል ብለው የሚጠብቁት ትልቅ ተስፋ
ያስፈልጋቸዋል፡፡ የህይወት ትርጉም ችግርን ስለመፍታት ብቻ መሆን የለበትም፣ ከዛ ማለፍ አለብን፡፡ ጠዋት
ከእንቅልፋችን ተነስተን "ዛሬ ይሄንን አሳካለሁኝ" ብለን ትልቅ ነገር ማሰብ መቻል አለብን" ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡

የኢሎን አዕመሮ የሚያስገርመው የስፔስ ኤክስ ድርጅት ከከፈተ ቦሃላ በኤሌክትሪክ የሚሰራን እራሱ በራሱ መንዳት
የሚችል መኪና የሚያመርት ካምፓኒ ለማቋቋም ተነሳ፡፡ ቴስላ የሚባልን አብዛኛውን በነዳጅ ምክንያት የሚነሳውን
ጦርነት ሊያስቀር የሚችል የኤሌክትሪክ መኪና ለህዝብ አስተዋወቀ፡፡

የዚህ ወጣት ጉዞ ግን ቀላል አልነበርም፡፡ ይልቁንስ ብዙ ተስፋ አስቆራጭ የነበሩ፣ ያለውን ሁሉ ሊያሳጡት የሚች ብዙ
አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ እስኪ በአጭር በአጭሩ እነዚህን አጋጣሚዎች በየተከሰቱበት አመት እንመልከት፣

 1999- የሱ ንብረት የነበረው ፔይፓል በሀገሪቷ 10 ቀሽም የጅማሮ ቢዝነስ ሀሳቦች ውስጥ ተካቶ
ነበር፡፡
 2001- ከሩሲያ መንኮራኩር ለመግዛት ቢፈልግም ሊሸጡለት ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡
 2002- አሁንም ከሩሲያ መንኮራኩር ለመግዛት ቢሞክርም- "አንተ ጎረምሳ ላንተ አንሸጥም" ብለው
ቅስሙን ሲሰብሩት፣ አኛ እራሳችን መንኮራኩር መስራት እንችላለን ብሎ አሰበ፡፡
 2006- ስፔስ ኤክስ ለመጀመሪያ ግዜ ያስወነጨፈው መንኮራኩር ከጠመነጠቀ በትንሽ ሰከንዶች ውስጥ
ፈነዳ፡፡
 2007- ሁለተኛ መንኮራኩር ወደ ጠፈር ለማመንጠቅ ቢሞክርም አሁንም እንደገና ፈነዳ፡፡ አዚህ ጋር
ትግሉን አቁሞ ሌላ ስራ ይፈልጋል ብለን ብዙዎቻችን ብናስብም አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ አንድ ግዜ
ለመሞከር ወሰነ፡፡
 2008- ሦስተኛ መንኮራኩር ወደ ጠፈር ለማመንጠቅ ቢሞክርም የናሳን ሳተላይቶችን ይዞ ብው አለ፡፡
አይበቃውም?
 2008- በዛኑ አመት የኤሌክትሪክ መኪናው ካምፓኒ ቴስላም ስፔስ ኤክስም የፋይናንስ ችግር
(Bankruptcy) ውስጥ ገብተው ሊዘጉ ደረሱ፡፡

የኢሎን መስክ ስኬት እነዚህን ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ፈተናዎች አልፎ የመጣ ነው፡፡ በ 2008 ኢሎን 4 ተኛውን
እና የመጨረሻውን መንኮራኩር ለማመንጠቅ ሙከራ ለማድረግ ወሰነ፡፡ ካለፉት 3 ውድቀቶቹ ተምሮ በዚህ ግዜ
መንኮራኩሯ በስኬት ከምድር ከባቢ አየር መውጣት ቻለች፡፡ ይቺ መንኮራኩር ፋልከን 9 ስትባል የመጀመሪያዋ
በግል ድርጅት ወደ ህዋ የተላከች መንኮራኩር ያደርጋታል፡፡ ኢሎን ሲናገር ይሄ ሙከራ ከሽፎ ቢሆን ኖሮ ድርጅቱ
በኪሳራ ምክንያት ይዘጋ ነበር ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡
በ 2008 መጨረሻ ላይ የአሜሪካው የህዋ ምርምር ጣቢያ ናሳ ለስፔስ ኤክስ 1.8 ቢሊየን የሚያስከፍልን
ኮንትራት አስረከበ፡፡ በዚህ ኮንትራት መሰረት በምድር ክበብ ዙሪያ (Low Earth Orbit) ተመራማሪዎችን ይዞ
ለሚሽከረከረው አለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ (International Space Station/ISS) ስፔስ ኤክስ የካርጎ ጭነትን
ማድረስ ነው፡፡ የዚህ ኮንትራት ጥቅም ወደፊትም ቢሆን ይሄን የግል ድርጅት በመጠቀም የጠፈር
ተመራማሪዎችን ወደ ህዋ መላክ እንደሚቻል ያሳየ ነው፡፡ ከ 2 ሳምንት በፊትም ይሄንን ማየት ችለናል፡፡ የስፔስ
ኤክስ መንኮራኩር ሁለት ጠፈር ተመራማሪዎችን ይዞ ወደ አለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ ማድረስ ችሏል፡፡

የኢሎን መስክ ስፔስ ኤክስ ሌላ ልዩ የሚያደርገው መንኮራኩሮችን እንደገና መጠቀም መቻሉ ነው፡፡ ከዚህ በፊት
ወደ ህዋ የተላኩ መንኮራኩሮች ወይ እዛው ጠፈር ለይ ይጣላሉ ወይም ወደ ምድር ሲመለሱ ውቅያኖስ ላይ
ይወድቁና እንዲነሱ ይደረጋሉ፡፡ ኢሎን መስክ ግን ይህ ተግባር የሀብት ብክነት ነው ብሎ ስለሚያምን ይናደዳል፡፡
እንዚህን መንኮራኩሮች እንደገና መጠቀም አለብን ብሎ በማሰበም ወደ ጠፈር የተላኩትን መንኮራኩሮች ወደ
አንድ ቀድሞ ወደ ታቀደላቸው ቦታ ቁጭ እንዲሉ ማድረግ ችሏል፡፡ ከብዙ የከሸፉ ሙከራዎች ቦሃላ ከሰማይ
የመጡ መንኮራኩሮችን ቀስ ብሎ ቦታቸው ላይ ሲያስቀምጣቸው ብዙዎች . . . "ይህማ ፊልም ነው እንጂ
የእውነት አይደልም ብለው ነበር፡፡"

ኢሎን መስክ በ 2025 ሰዎችን 'ቀይ' በሆነችው ማርስ ላይ ለማሳረፍ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ የሱ አላማ ጥቂት
ሰዎችን ከማሳረፍም በላይ ብዙ ሰዎችን ወደዛ እየላከ እራሷን የቻለች ከተማ ለመገንባት እና ወደፊትም
የሰዎች ሁለተኛ ቤት እንድትሆን ያቅዳል፡፡ ቀደም ብለን እንደነገርናችሁም እራሱ በራሱ መንዳት የሚችል
መኪናን ለሰው መሸጥ ችሏል፡፡ ወደ ፊትም የነዳጅ መኪኖች ሙሉ በሙሉ ተተክተው ሰው ሁሉ ይሄንን መኪና
መጠቀም እንዲችል ድርጅቱ እየሰራ ነው፡፡
ኢሎን መስክ ከዚህ በተጨማሪ ቦሪንግ የሚባልን ካምፓኒ አቋቋቁሞ መኪና አሽከርካሪዎች የትራፊክ ግፊያን
ትተው በመንገድ ስር ተቦርቡሮ በተዘጋጀ መንገድ ውስጥ በፍጥነት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲደርሱ እየሰራ
ነው፡፡ ሌላው ከምድር ሀገር ወደ ሌላ ሩቅ ሀገር ቢበዛ በ 30 ደቂቃዎች ብቻ በርካሽ ዋጋ ለማድረስ እየሰራ ያለ
ካምፓኒም ባለቤት ነው፡፡ ይህ መንኮራኩር እስከ 100 ሰዎችን መያዝ ይችላል፡፡

ይህ ሰው የወደፊት የምድር ተረካቢ ለሆኑ ወጣቶች ጥሩ ምሳሌ የሚሆን እና ከተራ አስተሳሰብ ወጥተው
ትልልቅ ነገሮችን በማሰብ ተስፋም ባለመቁረጥ በመትጋት ስኬት እንደሚመጣ የሚያሳይ ነው፡፡ ለአለም
መሪዎችም ቢሆን የምንኖርባት ምድር በጋራ ተከባብረን ከተራ ፖለቲካ ወጥተን የሰውን ልጅ ህይወት
ሊያሳግድ እና ሊቀይር የሚችሉን ሰዎች ለማብቃት እና ለማገዝ መስራት እንዳለባቸው የሚያሳስብ ነው፡፡

You might also like