You are on page 1of 1

Ethiopia – the risk and benefits of pure floating exchange rate

Classification of Exchange rate regimes

“Even though we have attained extraordinarily great achievements, there is no reason to


be arrogant. Modesty makes you move forward, arrogance makes you go backwards. I
should always remember this truth.”

'I have nothing to offer but blood, toil, tears and sweat.’

አንድ ጭዌ ላውጋችሁ፡ - በፈረንጆቹ ከ 1927 እስከ 1928 ነው፡፡ አሜሪካ ኢኮኖሚዋ ጦዟል (ቡም አርጓል)፡፡
የካምፓኒዎች የሂሳብ ሰነድም ለኢንቨስተሮች አጓጊ ሆኗል፡፡ ነፍ አሜሪካውያንም እየተበደሩ ሁሉ ሰቶክ ገዝተዋል፡፡
ይሄኛው ጉዳይ ከአዲስ አበባ የመሬት ዋጋ ተመን ጋር በእጅጉ የሚመሳሰል ነው፡፡ የአዲስ አበባን መሬት ውድ ያረገው ነዳጅ
ስለሚወጣበት አይደለም፡፡ ይልቁን ሰው የሚረባረበው ጨምሬ እሸቅለዋለሁ በሚል እሳቤ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
የስቶኩም ልክ እንደዛው ነበር፡፡ እንጂ፣ ከሚገኘው ትርፍ (ዲቪደንድ) አንፃር ዋጋው ተጋኗል፡፡ በመሆኑም 1929 ላይ
የስቶክ ዋጋ እየጋሸበ ይቀጥላል የሚለው ኮንፊደንስ ዝቅ ማለት ጀመረ፡፡ በሚሊዮን ዶላሮች ስቶክ የገዙ ሰዎች ወደ
ሽያጭ አመሩ፡፡ ይሄን ተከትሎም፣ ዋጋው ማቆልቆል ጀመረ፡፡ በሂደትም የዋጋው በፍጥነት መቀነስ ስቶኩ የተገዛበትን
ዋናውን እንኳ መመለስ የማይችል እና የማይፈለግ አደረገው፡፡ ባንኮች ያበደሩት ገንዘብ ውሃ በላው፡፡ ካምፓኒዎች ስራ
አቆሙ፡፡ ስራ አጥነቱን ተከትሎ ብዙዎች ጎዳና እስከመውጣት ደረሱ፡፡
እዚህ ጋር የዘመኑ ፕሬዝዳንት ኸርበርት ሁቨር ነው፡፡ ነገርየውን በቁም ነገር ለመውሰድ ያነበበው የአዳም ስሚዝ መፅሃፍ

(‘Market adjusts itself in the long run’) የፈቀደለት አይመስልም፡፡ የቢዝነስ ሳይክል አንድ አካል ነው አለ፡፡ ይባስ
ብሎ ከአንድ ሁለት ዓመት በኋላ በራሱ ይጠፋል በሚል ችግሩን ችላ አለው፡፡ እዚሁ ጋር ብሪታንያዊው ሊቅ ኬይነስ

ይመጣል፡፡ “In the long run we all are dead” በማለት ይሳለቅባቸዋል፤ ገቢያ አምላኪዎቹን ቅዠታሞች፡፡
ታሪኩን እዚህ ጋር እንያዘውና፤ ወደ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንመለስ፤
ስራ አጥነት ሰፍኗል፤ ድህነት ተንሰራፍቷል፤ ቤ/መንግስት ይገነባል፡፡ ፋብሪካ ይዘጋል፡፡ የኢኮኖሚ ስኬት ብርቅ እየሆነ፣
የፖለቲካ አለመረጋጋት ስጋት ሆኗል፡፡
ጠሚው ግን ከ 20 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ሀገራት ከሁለቱ ሃያላን አንዷ ትሆናለች ይልሃል፡፡ ከሳቅን

በኃላ የምንረዳው በመደመር ሃልዮት መሰረት የትኛዋ ኢትዮጵያ?!

You might also like