Professional Documents
Culture Documents
Fiat Money1
Fiat Money1
ከጊዜ በኃላ የወረቀት ገንዘብ ላይ የህግ አስገዳጅነትን የሚገልጽ ህግ መጻፍ ተጀመረ፡፡ ይህም
ማለት የወረቀትን ገንዘብ አልቀበልም ማለት በህግ የሚያስቀጣ ሆነ፡፡ ይህም ህግ በሀገራት
ውስጥ የሚተገበር ህግ በመሆኑ በዛ ሀገር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ወርቅ የመያዝ ልምዳቸው ቀስ
በቀስ መቀነስም ጀመረ፡፡ ለአለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ግን ከሳንቲም እጅግ የላቀ ክብደት
ያለው ወርቅ እንደመገበያያ መጠቀም ተጀመረ፡፡ ከጊዜም በኃላ እንግሊዝ ባላት የፖለቲካ
ኃያልነት እና ቅኝ ግዛተዋን ከማስፋፋት (1717) ጋር በተያያዘ የወረቀት ገንዘብ ወርቅ ነው
የሚለው እሳቤ በአብዛኛው አለም ሀገራት ማህበረሰብ አእምሮ ውስጥ ሰረጸ፡፡ በናፖሊዮን
አገዛዝ መባቻ ላይ (1815) አብዛኛው መገበያያ የተመሰረተው በወርቅ ወይም በብር (የብረት
አይነት) ነበር፡፡ በ 19 ኛው ክፍለዘመን ወርቅ በብር(ሲልቨር) መተካት ጀመረ፡፡ ወደ ወርቅ በቀላሉ
የመቀየር ጠባይ፤ የገንዘብ ኖት ልኬት ከወርቅ ጋር ያለው ዝምድና፤ ዜጎች እንደፈለጉ ወርቀን
የመያዝ፤ ኤክስፖርት እና ኢምፖርት የማድረግ መብት አንድ ላይ ዘ ጎልድ ስታንዳርድ የሚል
ስያሜ ተሰጠው፡፡ በ 1880 እና በ 1914 ጎልድ ስታንዳርድ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ ተንሰራፋ፡፡
ይህም ለአለም አቀፍ ንግድ ጎልድ ስታንዳርድ የተለመደ አሰራር ሆነ፡፡ የወረቀት ገንዘብ ዋጋ እና
ወርቅ የሚያገበያይበት ዋጋ የተረጋጋ መሆን የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ንግዶች ከትንሽ
ካፒታል ኪሳራ ኢንቨስትመን ጋር ተዳብሎ በወረቀት ገንዘብ ላይ እና በጎልድ ስታንዳርድ ላይ
ያለው አመኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ በወርቅ የታተመው ሳንቲም አሁንም
ውስጣዊ ዋጋ ያለው በመሆኑ በራሱ አመኔታውን እንደያዘ ነው፡፡ ሆኖም የወረቀት ኖቶች ያለው
መተማመኛ ይህንን ወረቀት ክፈለን ባልከኝ ጊዜ እከፍለሀለሁ የሚል የመተማመኛ ህግ ብቻ
ነበር፡፡ ይህም በአታሚው ማእከላዊ ባንክ ባለው የጎልድ ስታንዳርድን ህግ በመከተል እና
ባለመከተል ሙሉ በሙሉ ጥገኛ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከላይ የዘረዘርናቸው ጎልድ ስታንዳርድ
ስምምነት የማይተገበሩበት ጊዜ ነበር፡፡ የወርቅ ዋጋ መውረድ፤ክልከላዎች እና እገዳዎች ነበሩ፡፡
እንደምሳሌ 1. እንግሊዝ በናፖሊዮን ጦርነት ጊዜ አስከፊ የሚባል የዋጋ መናር ወይም ግሽበት
ስላጋጠማት የወረቀት ገንዘብ በወርቅ በተፈለገ ጊዜ መቀየር ላይ እገዳ አስቀመጠች፡፡
ተከታታይነት ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመከላከል ስትል እንግሊዝ በ 1819 ባወጣችው ህግ ላይ
ወርቅ አስቀድሞ በተወሰነለት ውስን ዋጋ ከመቀያየር ወጋውን የማርኬት ዋጋ እንዲወስነው
ደነገገች፡፡
በዚህ በብሪትን ውድስ ስምምነት መሰረት አንድ ዶላር 1/35 ጥሩ ጥራት ያለው ወቄት ወርቅ
ተሰጠው(ይህ ማለት አንድ ወቄት ወርቅ ከ 35 የአሚሪካ ዶላር ጋር እኩል ነው)፤፤ አሜሪካ በዚህ
ስምምነት መሰረት ይህንን የዋጋ ተመን ለመጠበቅ እና ማንኛውንም የይክፈለኝ የዶላር
ጥያቄን በማንኛውም ጊዜ በተጠቀሰው የወርቅ እኩሌታ በ ዘ ጎለደ ዊንዶወ ለመመንዘር
ዋስትና ሰጠች፡፡ሌሎች የመገበያያ ገንዘቦች ከዶላር ጋር የተተመነላቸውን ዋጋ ይዘው
ለመቀጠል ቃል ገቡ፡፡ይህንንም የሚቆጣጠር ኢንተርናሽናል ሞንትሬ ፈንድ ተቃቃመ፡፡ ከዚህ
በኃላ የማንኛውም የገንዘብ መገበያያ ወረቀት ወደ ወርቅ መመንዘር ተከለከለ፡፡ምንም እንኳ
ወርቅ በዚህም ጊዜ እንደ መጠባበቂያ ቢያገለግልም የአሜሪካ ዶላር ዋንኛ የመጠባበቂያ ሰነድ
በመሆን በሌሎች የማእከላዊ ባንኮች ማገልገል ጀመረ፡፡ እንዲሁም ሁሉም አለም አቀፍ
ንግዶች በዶላር መገበያየት ተጀመረ፡፡የሀገሪቱ ማእከላዊ ባንኮች ብቻ ናቸው ለ ጎልድ ዊንዶው
ዶላር በማቅረብ ወደ ወርቅ እንዲመነዘርላቸው መጠየቅ የሚችሉት፡፡
ነገር ግን አሜሪካ የበጀት ጉድለቷን ለሟሟላት የወርቅ መጠባበቂያ ሳታስቀምጥ ዶላር በገፍ
ማተም ፤የንግድ ልውውጥን መቆጣጠር እና የማእከላዊ ባንኮችን የአሚሪካ የፋይናንስ
ንብረትን ወደ ወርቅ እንዳይቀየር ማስገደድ እና ተጽእኖ ማሳደር ጀመረች፡፡ በ 1970
መጨረሻዎቹ ላይ አሜሪካ በሌሎች ሀገራት የክፍያ ይገባኛል ጥያቄ በወርቅ መጠባበቂያ ካለት
ወርቅ ሁለት እጥፍ በላይ ነበር፡፡አሜሪካ ፊቷ የተደቀነው ከባድ አደጋ እንደማይቀርላት
በመፍራት የአሜሪካ መንግስት ትልቅ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
እሁድ ኦገስት 15 ቀን 1975 አሚሪካ የጎልድ ዊነዶዋን ዘጋች፡፡ ከዚህ ቀደም የገባችውን ቃል
አጠፈች፡፡ በብሪትን ዎድስ ስምምነታቸውን ያሰፈሩት ሀገራት አንድ ላይ ስምምነቱን ማጽናት
ተሳናቸው፡፡ ለ 26 አመታት የዘለቀው የብሪትን ዎድስ ስምምነት በጊዜ ተቀበረ፡፡ ከዚህ በኃላም
ቢሆን የአሜሪካ ዶላር በነጻነት በአለም ደረጃ ይዘዋወራል፡፡ ሌሎች ሀገራት ገንዘብም እንደዚሁ፡፡
ይህ ደግሞ በወርቅ መገበያያነት ለሶስተኛ ጊዜ የተከሰተ ክስተት ሆነ፡፡ ክስተቱ ወርቅ
ከመገበያያነት የነበረውን ዝምድና ለመጨረሻ ጊዜ የወረቀት ገንዘብ እንደወርቅ በመሆን
ማገልገሉን ያቆመበት ጊዜ ሆነ፡፡
ከ 1971 በኃላ
ከዚህም ጊዜ በኃላ መገበያያ የተስፋ ሰነድ እንደሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሀገራት የራሳቸውን
መገበያያ በወርቅም ይሁን በሌላ ዋጋ ባለው ንብረትም ሆነ በሌላ ሀገር ገንዘብ ላለመቀየር
ራሳቸውን ከተጠያቂነት አገለሉ፡፡ ይህን ተንሳፍፎ የቀረውን የወረቀት ገንዘብ ያለው
መተማመኛ ዜጎች አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ያላቸው መተማመን ብቻ ነው፡፡ ዜጎች
የወረቀት ገንዘብን አልቀበልም ያሉ ጊዜ ትልቅ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ
እነዳይሆን የህግ ከለላ አለው፡፡ የወረቀት ገንዘብ ህግ የሚጠብቀው እና የሚገርም ቅዠት
እንደሆነ ነው፡፡
በ 2002 አውሮፓ እንዱን ቅዠት በሌላ ቀዠት እንዲተካ አደረገ፡፡ የ 12 ሀገራትን የተለያየ
መገበያያ ገንዘብን በአንድ ተካ፡፡ በአንዲት ሌሊት ዲሴምበር 31 2001/ጃነንዋሪ 1 2002 በአለም
ትልቅ ዋጋ ያለውን የጀርመን ገንዘብ ማርክ ከፈረንሳይ ከኔዘርላንድ፤ከቤልጂመ ከኢታሊያ እና
ከሌሎች ሀገራት ጋር ይገበያዩበት የነበረ ምንም ጥቅም የሌላቸውን 12 መገበያ ገንዘብ በሌላ
ምንም ጥቅም በሌለው አንድ መገበያያ (ዩሮ) በህግ ከለላ ተተካ፡፡ የአለም ህዝብ ለቁጥር
በሚያታክት በጭነት መኪናዎች የድሮ ገንዘቦች ተሰብስበው ሲቀደድ እና ወደ ወረቀትነት
ሲቀየረ በቴሌዢዥን ለማየት በቃ፡፡ ይህ ወረቀት በኃላ ላይ ወደ ሽንት ቤት ወረቀትነት ተቀየረ፡፡
ሳንቲሞቹ እንዲቀልጡ ሆነው ውስጣዊ ጠቀሜታቸውን ሳይለቁ የብረትነት ዋጋቸው
እነዳላቸው ለሌላ አገልግሎት ዋሉ፡፡
በ 1985 የአሜሪካ ዶላር ፌዴራል ሪሰርቭ ኖት በመባል በይፋ ጸደቀ፡፡ በኖቱ ላይ የሀገሪቱ ስም፣
የዶላሩ ስም፤የገንዘቡ መጠን፡፤ የኖቱ ቁጥር፤ የህግ አስገዳጅነት አረፍተ ነገር እና የሀገሪቱ
የገንዘብ ሹም ፊርማ እንዲታተም ሆነ፡፡
የካናዳ ዶላር በ 1973 በካንክ ፈ ካናዳ ስም እና የባንኩ ገዥ በሆነው ኦታር ተፈረመ፡፡ በዶላሩ ላይ
ይህ ኖት ህጋዊ አስገዳጅ ነው የሚል አረፍተ ነገር አለው፡፡
የወርቅ ዋጋ
ከ 1945 እስከ 1971 የሁሉም ሀገራት ገንዘብ ከዶላር ጋር የተወሰነ ዝምድና አላቸው፡፡ ዶላር
በተራው ከወርቅ ጋር እንዲሁ የተወሰነ ዋጋ ዝምድና አለው፡፡ 35 ዶላር የአንድ ጥራቱ ደህና
የሆነ የወርቅ ወቄት ዋጋ አለው፡፡ በዚህ መሰረት የትኛውም ሀገር ያለ አንድ ምርት በወርቅ
የሚተመን የተለየ ዋጋ አለው፡፡ ነገር ግን ወርቅ በራሱ እንደ አንድ ምርት በማናቸውም ሀገራት
የሚለካ የራሱ ዋጋ የለውም|፡፡ ወርቅ በራሱ ገንዘብ ነው፡፡የሚለካውም በክብደት ነው፡፡አንድ
ወቄት ወርቅ አንድ ወቄት ወርቅ ነው፡፡ ማኝኛውም የወረቅ ብዛት ያንኑ የወርቅ ብዛት እኩል
ነው፡፡35 የአሜሪካ ዶላር ከአንድ ወቄት ወርቅ ጋር እኩል ነው እንጂ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 35
የአሜሪካ ዶላር ነው ማለት አይደለም፡፡
ልክ እነደ አንድ ምርት ወርቅ በዚህ ሂደት የራሱ ዋጋ (ከ 35 ዶላር ዋጋ የተለየ) ኖረው፡፡ ህዝቡም
ወርቅን አንደ እንድ ምርት ይቆጥረው ጀመር፡፡ ምንም እንኳ ወርቅ ከ 35 ዶላር የተለየ ዋጋ
ቢኖረውም ዋጋው ያን ያህል ክፍተት ያለው አልነበረወም፡፡ አስደንጋጭ የወርቅ ዋጋ ልዩነት
የታየው በ 1971 በአንዴ ሲለጠጥ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ በኃላ የወርቅ ዋጋን ወደላይ ከመምዘግዘግ
የሚያግደው ነገር አልተገኘም፡፡ በ 2019 የወርቅ ዋጋ 1,526.00 ዶላር ለአንድ የወርቅ ወቄት
ደርሷል፡፡
ትልቁ ጥያቄ የወርቅ ዋጋ ነው ወደላይ እየወጣ ያለው ወይስ የዶላር ዋጋ እየወረደ?ይህ ጥያቄ
ሲነሳ አይስተዋልም፡፡ የወርቅ ዋጋ ወደላይ የወጣው ወርቅን ፈላጊ በመብዛቱ ነው ( አቅርቦቱ
አነስተኛ በመሆኑ) ወይስ ገንዘብ ዋጋው እየወረደ? ይህን በምሳሌ እስኪ እንየው፡፡ሁለት ጎን
ለጎን ወይም ትይዩ በሆነ አቅጣጫ የቆሙ መኪናዎች ቢኖሩ እና በአንዱ መኪና አንተ
ተቀምጠኃል እንበል፡፡ የዛኛው መኪና ሾፌርን ማየት በማትችልበት ሆኔታ መኪናው መንቀሳቀስ
ቢጀምር ላንተ የሚሰማህ ያንተ መኪና ሳታስበው ዕየተንቀሳቀሰ ነው የሚመስልህ፡፡ የዶላር እና
የወርቅ ጉዳይም እንዲህ ነው ማናቸው፡፡ እንደቀነሱ ወይም ማናቸው እንደጨመሩ ለማወቅ
ትቸገራለህ፡፡የጨመረው የወርቅ ዋጋ ነው ወይስ የገንዘብ ዋጋ ነው የወረደው?
በተለምዶ ወር ከወር የሚመዘገበው የዋጋ ግሽበት አንድ አይነት ሊሆን አይችልም፡፡ አንዳንዴ
ምንም ለውጥ ላይኖር ይችላል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከፍም ዝቅም ሊል ችላል፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ
ልዩነቱ ኔጌቲቭ ሊሆን ይችላል፡፡በዋናነት የወቅቶች መፈራረቅ ለልዩነቶች እንደምክንያትነት
ይነሳል፡፡ ፍራፍሬ እና አትክልት በጣም ሚወደዱበት እና የሚረክሱበት ወቅቶች ይለያያል፡፡
የየወራቶች ልዩነት ተደምሮ የአመት ውጤት እናገኛለን፡፡በአመቱ መጨረሻ አጠቃላይ የምግብ
ፍጆታችን ብር 620 ቢሆን የዋጋ ለውጡ ብር 120 ነው፡፡ የመቶኛ ስሌቱ ደግሞ 100*120/500
=24% ይሆናል፡፡ 24%ን ለ 12 ብናካፍለው የምናገኘው 2 ፐርሰንት አማካይ ወርሃዊ የዋጋ
ግሽበት ነው፡፡
የአንድ ሀገርን የዋጋ ግሽበት ለማወቅ ከፈለግን የእያንዳንዱን ቤተሰብ የምግብ ፍጆታ ወጪ
በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ በየሳምንቱ፤ በየወሩ ወይም በየአመት መሰብሰብ ይኖርብናል፡፡
ይህን ለማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በመሆንም ልዩልዩ እሳቤዎችንና የአማካይ ስሌቶችን
መጠቀም ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡
የመጀመሪያ ስራ መሆን ያለበት የህዝብን የምግብ ልማድ ማጥናት ነው፡፡ የሁሉንም ቤተሰብ
ጸባይ ማጥናት ስለማይቻል በስታስቲክስ የማጥናት ዘዴን እንጠቀማለን፡፤ በዚህ ዘዴ የተወሰነ
ቤተሰብ ወይም አባወራ ይመረጣሉ፡፡ ይህም በስታስቲክስ ሳምፕል ይባላል፡፡ እነዚህ የተመረጡት
ቤተሰቦች የአንድ ሀገርን ቤተሰብ የምግብ ልማድ ይገልጻሉ በሚል እሳቤ ነው፡፡የምንመርጣቸው
የቤተሰብ ብዛት ለጥናቱ በሚወጣው ወጪ እና ጊዜ ሊወሰን ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ የቤተሰቡ
አይነት አዛውንት፤ወጣት፤ብዙ ልጅ ያለው ቤተሰብ፤ አንድ ልጅ ያለው ቤተሰብ እና የመሳሰሉት
እሳቤዎችም ተጽእኖ አላቸው፡፡የቤተሰቡ ማህበራዊ ስብጥርም ሌላው መመዘኛ ነው፡፡
የቤተሰቡ የገቢ ሁኔታ፤ ሀይማኖት እና ባህል የቤተሰብን ምግብ ልማድ ሊወስኑ የሚችሉ ሌሎች
ምክንያቶች ናቸው፡፡ከላይ የዘረዘርናቸው ምክንያቶች በአንድ ሀገር ላይ ተመሳሳይ ጸባይ ያለው
ከሆነ የምንመርጣቸው የቤተሰብ ብዛት ጥቂት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በዚህ ተቃራኒ ከሆነ ደግሞ
የሚመረጡት ቤተሰብ ብዛት ከፍ ማለት አለበት፡፡
የአንድ ሀገር የዋጋ ግሽበትን ለመለካት የምንፈልግ ከሆነ ገጠራማውን ከከተማ፤አነስተኛ ከተማ
ከትላልቅ ከተማ፡ተራራማ አካባቢን ከሜዳማ አካባቢ፡የኢንዱስተሪ ከተማን ከግብርና ከተማ
እና ሌሎችም ምክንያቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን፡፡
ለተከታታይ ቀጣይ አመታትም የሚታዩ የምግብ ፍጆታ ዋጋን መሰረት በማድረግ ብቻ መረጃ
ይሰበሰባል፡፡
የዋጋ ማውጫ፤ የዋጋ ለውጥ እና የለውጥ መቶኛ ልዩነትን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ማውጫው
ከ 100 ወደ 112 በመጀመሪያ አመት እና ከ 112 ወደ 120 በሁለተኛው አመት ነው፡፡ይህም ማለት
ማውጫው ወደ 12 በመጀመሪያ አመት ከፍ ሲል በ 8 ነጥብ በሁለተኛው አመት ከፍ ብላል፡፡
ነገር ግን የዋጋው መቶኛ የተለወጠው በመጀመሪያ አመት በ 12 ፐርሰንት ሲሆን በሁለተኛው
አመት ግን 7.14 ፐርሰንት ነው፡፤የዋጋው መቶኛ ለውጥ የዋጋ ግሽበት ነው፡፡
የመረጃ አሰባሱ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ብርቱካን በመኪና በኩንታል በተለያየ ጣእም በልዩ
ጸባይ እና የተለያየ ዋጋ አለው፡፡ብርቱካኑ የሀገር ምርት ሊሆን ይችላል አልያም ከውጭ
ኢምፖርት ተደርጎ ሊገባ ይችላል፡፤ከውጭ ሲገባም ከተላያየ ሀገር በተለያየ ዋጋ ሊመጣ
ይችላል፡፡ብርቱካኑ በነጠላ ፡በኪሎ ወይም በኩንታል ሊሸጥ ይችላል፡፡የምናወራው ብርቱካን
ጥሬውን የሚበላ እንጂ ጨምቁ ወይም በሌላ ሂደትን የተቀየርን አይደለም፡፤ልዩ ልዩ አምራቾች
አስመጪዎች አከፋፋዮች ብርቱካኑን የሚሸጡት በራሳቸው ዋጋ ነው፡፡ በተጨማሪም
ብርቱካንን ከሱፐርማርኬት ከግሮሰሪ ከአዝዋሪ እና በሌላ መልኩ ልናገኘው እንችላልን፡፡
በመሆኑም ከላይ የዘረዘርናቸውን ሁኔታዎችን የዋጋ መረጃ በምንሰበስብበት ጊዜ ከግምት
ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡
የግሽበት መንስኤዎች
1. ዋነኛ የግሽበት መንስኤ የሚከሰተው የመንግስት ወጪ በሚጨምርበት ጊዜ ነው፡፡
ይህንንም የበጀት ጉድለት ለመሙላት መንግስት ገንዘብ ያትማል፡፡ የታተመው ገንዘብ
አቅርቦት ሲጨምር ግዥ ይበረክታል፡፡ ለዚህ ግሽበት ተጠያቂ መንግስት ነው፡፡
በታዳጊ ሀገር ከውጭ ሀገር የሚላክ ገንዘብ ባለበት ሀገር የተላከውን ገንዘብ ህዝቡ
ለግል ፍጆታ የሚያውል ከሆነ ግሽበትን ያስከትላል፡፡በዚህ ጊዜ ደግሞ ተጠያቂ
የሚሆነው ተጠቃሚው ነው፡፡
2. ሌላው መንስኤ ደግሞ የአቅርቦት እና የፍላጎት መጠን ባለመጣጣም የሚመጣ
ግሽበት ነው፡፡ይህ አለመጣጣም በህዝብ ብዛት መጨመር እና የከተሞች
መስፋፋት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡ለዚህ ጉዳይ ዋነኛ ተጠያቂ ማህበረሰቡ
ነው፡፡በሌላ መልኩ የአቅርቡት እጥረት ሌላው ምክንያት ነው፡፡የአቅርቦት እጥረቱ
የተከሰተው በራሱ ጊዜ ተፈጥሮን ተጠያቂ ከማድረግ ውጭ አማራጭ የለም፡፡
3. የዋጋ ግሽበት በደመወዝ ጭማሪ ፤ መንግስት ቀጥተኛያልሆነ ታክስ ሲጭን
(በቅርቡ ያረጁ መኪናዎች ቅንስናሽ በመነሳቱ ምክንያት የመኪና ዋጋ መጨመሩ
ይታወሳል)፤ ስግብግብ ነጋዴዎች ከመጠን ያለፈ ትርፍ ለማጋበስ በሚያደርጉት
ድርጊትም ግሽበት ሊከሰት ይችላል፡፡ የነጋዴዎች ማህበር፡መንግስት እና ነጋዴው
ለእነደዚህ አይነት ጭማሪዎች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
4. በአለም አቀፍ ጉዳዮች የገንዘብ ዲቫሊዌሽን በሚኖርበት ጊዜም የዋጋ ግሽበት
ይከሰታል፡፡
5. አንዳንድ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ከሌላ ሀገር ኢምፖረት ልናደርገው እንችላልን፡፡
6. ባንኮች ብድር በሚሰጡበት ጊዜ ግሽበት ይከሰታል፡፡ በዚህ ጊዜ ባንኮች
ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ግሽበጽ የህግ አንቀጽ የማያውቀው የዝርፍያ ድርጊት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ሆኖም
ድርጊቱን አጨቃጫቂ እና አጠራጣሪ በሆነ መንገድ ለማከም ከመሞከር ይልቅ ሸሪአዊ
በሆነ መንገድ መፍትሄ መሻት ይገባል፡፡ ከዚህ ቀደም በቺሊ የሆነውን እርምጃ ማየቱ
ጠቃሚ ነው ፡፡ ቺሊ መንግስ የመንግስት ወጪን በማስተካከል እና የውጭ ሀገራት ገንዘብ
ምንዛሪ ማስተካከሉ ግሽበትን መቀነስ ችላለች፡፡