በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
የሁለተኛ መንፈቅ አመት የ6ኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ሞዴል ፈተና
የተሰጠው ሰዓት 1፡ 00
መመሪያ፡-
1. ይህ የአካባቢ ሳይንስ ፈተና ነው፡፡ፈተናዉን ለመስራት የተሰጠ ጊዜ1ሰአት
ሲሆን ከሰዓት በላይ መስራት አይፈቀድም፡፡ከተፈቀደዉ ጊዜ ቀድመህ/ሽ
ከጨረስክ/ሽ የሰራኸዉን/ሽዉ መመለስ ትችላለህ/ሽ፡፡
2. የጥያቄ መመሪያዎችን በጥንቃቄ አንብቡ፡፡ስለፈተናዉ ጥያቄ ካላችሁ
ፈተናዉ ከመጀመሩ በፊት ፈታኙን/ኟን መጠየቅ ትችላለህ/ሽ፡፡
3.እያንዳንዱ ጥያቄ አራት ምርጫዎች አሉት፡ጥያቄዎቹን በጥንቃቄ ካነበብክ/ሽ
በኋላ መልስህን/ሽን የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ አጥቁር/ሪ፡፡
A B C D
4.መልስህን/ሽን ለመቀየር ከፈለክ/ሽ የመጀመሪያዉን መልስ ሙልጭ አድርገህ/ሽ
አጥፋ/ፊ በመቀጠል የተቀየረዉን መልስ አጥቁር/ሪ፡፡
5. ፈተናዉን ለብቻህ/ሽ መስራት ይኖርብሀል/ሻል፡፡በማንኛዉም መንገድ
ለማጭበርበር መሞከር ዉጤቱ በሙሉ ይሰረዛል፡፡(አይያዝም)፡፡
6. ማጥቆር የሚቻለዉ በእርሳስ ብቻ ነዉ፡፡
ፈተናውን መስራት ጀምሩ ሳይባል መጀመር አይፈቀድም!
2016 ዓ.ም/ 2024G.C
መመሪያ፡- ከተራ ቁጥር 1 - 40 ያሉትን ጥያቄዎች ከቀረቡት አማራጮች መካከል በይበልጥ
ተስማሚ የሆነውን መልስ በመምረጥ በመልስ መስጫው ወረቀት ላይ አጥቁሩ፡፡
1. የኢትዮጵያን ፍፁማዊ መገኛ በትክክል የሚገልፀው የቱ ነው?
ሀ. 12 ዲግሪ ሰሜን ኬክሮስ እና 51 ዲግሪ ምስራቅ ኬንትሮስ
ለ. 18 ዲግሪ - 22 ዲግሪ ኬክሮስ እና 6 ዲግሪ - 48 ዲግሪ ምስራቅ ኬንትሮስ
ሐ. 3 ዲግሪ ሰሜን - 15 ዲግሪ ሰሜን ኬክሮስ እና 33 ዲግሪ - 48 ዲግሪ ምስራቅ ኬንትሮስ
መ. 10 ዲግሪ - 19 ዲግሪ ሰሜን ኬክሮስ እና 45 ዲግሪ - 50 ዲግሪ ምስራቅ ኬንትሮስ
2. አንፃራዊ መገኛን መግለፅ የማንችልበት መንገድ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. አቅጣጫዎችን በመጠቀም ለ. ተራራዎችን በመጠቀም
ሐ. የውሀ አካሎችን በመጠቀም መ. የዲግሪ ልኬትን በመጠቀም
3. በምጋት ሂደት አየር ወደ ሳንባችን ለመድረስ የሚያልፍባቸው የመተንፈሻ አካላት በቅደም
ተከተል ሲቀመጡ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የአፍንጫ ቀዳዳ፣ድህረ አፍ፣ሰርን፣አብይ የአየር ቧንቧ፣ተገንጣይ የአየር ቧንቧ፣ደቂቅ
ትንቧ፣የአየር ከረጢት
ለ. የአፍንጫ ቀዳዳ፣ሰርን፣ድህረ አፍ፣አብይ የአየር ቧንቧ፣ተገንጣይ የአየር ቧንቧ፣የአየር
ከረጢት፣ደቂቅ ትንቧ
ሐ. የአየር ከረጢት፣የአፍንጫ ቀዳዳ፣ሰርን፣ድህረ አፍ፣አብይ የአየር ቧንቧ፣ባላ ትንቧ፣ደቂቅ
ትንቧ
መ. የአፍንጫ ቀዳዳ፣የአየር ከረጢት፣ደቂቅ ትንቧ፣ባላ ትንቧ፣ድህረ አፍ፣ሰርን፣አብይ የአየር
ቧንቧ
4. በየብስና በአየር ላይ የሚንቀሳቀሱ አካላትን አቅጣጫ ለመቆጣጠር የሚያገለግለው መሳሪያ
ምን ይባላል?
ሀ. ካርታ ለ. ጎግል ማፕ ሐ. ጂፒኤስ መ. ጎግል ኸርዝ
5. የእጅ ስልክ ወይም በኮምፒውተር በመጠቀም በመሬት ላይ የምንፈልገውን አካባቢ
ለማግኘት የሚያገለግለን --------------- ነው፡፡
ሀ. ጎግል ኸርዝ ለ. ጎግል ካርታ ሐ. ጂፒኤስ መ. ማይክሮስኮፕ
6. በኦክስጂን የበለፀገ ደምን ከፑልማነሪ ቬይን ተቀብሎ ለግራ አቀባይ ልበገንዳ
የሚያስተላልፈው የልብ ክፍል የቱ ነው?
ሀ. ቀኝ አቀባይ ልበ ገንዳ ለ. ግራ ተቀባይ ልበገንዳ
ሐ. ቀኝ ተቀባይ ልበገንዳ መ. ግራ አቀባይ ልበገንዳ
7. ከሚከተሉት የደም ህዋሶች ከ100 - 120 ቀናት እድሜ ያላቸው የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ቀይ የደም ህዋስ ለ. ነጭ የደም ህዋስ ሐ. ፕሌትሌቶች መ. ፕላዝማ
8. ከሚከተሉት በኮረዳነት ጊዜ የሚታዩ ስነ-ህይወታዊ ለውጥ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የወር አበባ መታየት ለ. የጡት ማጎጥጎጥ ሐ. የድምፅ መጎርነን መ. የዳሌ መስፋት
9. ከሚከተሉት ለኦክስጅንና ካርቦንዳይኦክሳይድ ወደ ደም ውስጥ መግቢያና መውጫ ሆኖ
የሚያገለግል የስርዓተ ትንፈሳ አካል ክፍል የትኛው ነው?
ሀ. ድህረ አፍ ለ. ትንከርት ሐ. ሰርን መ. አፍንጫ
10. ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ ፈሳሾችን በነጥብ ፍሌት ለመለየት የሚያገለግለን የድብልቅ
መለያ ዘዴ የቱ ነው?
ሀ.ጥሊያ ለ. ቀረራ ሐ. ትነት መ. ንጥረት
11.ከሚከተሉት ታዳሽ የጉልበት ምንጭ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የፀሀይ ጉልበት ለ.የተፈጥሮ ነዳጅ ሐ. የባትሪ ድንጋይ መ. ቤንዚን
12. ከሚከተሉት የጉልበት ጥቅም የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ስራን ለመስራት ለ. ምግብ ለማብሰል መ. ለመጓጓዣ መ. ሁሉም መልስ ነው
13. ሰንደቅአላማን ለመስቀልና ውሀን ከጉርጓድ ለማውጣት የሚያገለግል ቀላል መኪና የቱ
ነው?
ሀ. ሽብልቅ ለ. መፈንቅል ሐ. ሽክርክሪትና ዘንግ መ. መፍቻ
14. ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሞዛምቢክና ታንዛኒያ የሚታየው የአየር ንብረት ክልል
የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የሳር ምድር ሞቃታማ የአየር ንብረት ለ. የሀሩር ሞቃታማ የአየር ንብረት
ሐ. የደጋ አየር ንብረት መ. የበረሃ አየር ንብረት
15. በደጋ የአየር ንብረት ክልል ውስጥ ባሉት ሀገራት በተራራ ተፅእኖ የሚፈጠረው የዝናብ
አይነት ምን ይባላል?
ሀ. ግንባር ዝናብ ለ. ጉባገብ ዝናብ ሐ. ሳይክሎኒክ መ. ስግረት ዝናብ
16. ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በዩራኒየም ማዕድን የምትታወቀው ሀገር የቷ ናት?
ሀ. ታንዛኒያ ለ. ሶማሊያ ሐ. ኢትዮጵያ መ. ኬንያ
17. ከሚከተሉት የተፈጥሮ ሀብት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የዱር እንሰሳት ለ.ማዕድናት ሐ. ውሀና አፈር መ. የአክሱም ሀውልት
18. በምስራቅ አፍሪካ በማዕድናት አጠቃቀም ላይ ተግዳሮት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ቴክኖሎጂ እጥረት ለ. አነስተኛ የውስጥ ፍላጎት
ሐ. የሰለጠነ የሰው ሀይል አለመኖር መ. ማዕድናትን መጠቀም ፍላጎት መጨመር
19. ከምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቨርቲሶል የአፈር አይነት የሚገኘው የት ነው?
ሀ. ዛምቢያ ለ. ሶማሊያ ሐ. ኢትዮጵያ መ. ኤርትራ
20. ከሚከተሉት የአፈር መሸርሸር መንሴዎች ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. ዳግም ድነና ለ. ቁልቁል ማረስ ሐ. ድነና መ. እርከን መስራት
21. ከሚከተሉት ወንዞች ወደ ህንድ ውቅያኖስ የማይገባው የቱ ነው?
ሀ. ሩቩማ ለ. ታና ሐ. ገናሌ መ. ዋቢሸበሌ
22. ከምስራቅ አፍሪካ ወንዞች ከታንዛኒያ የሚነሳና ትልቁ የቪክቶሪያ ፏፏቴና ሁለት ሰው
ሰራሽ ግድቦች የሚገኙበት ወንዝ የቱ ነው?
ሀ. ታና ለ. ዛምቤዚ ሐ. ሩፋጂ መ. ሩቫማ
23. በጥልቀቱ በአፍሪካ አንደኛ በአለም ሁለተኛ የሆነው የስምጥ ሸለቆ ሀይቅ የቱ ነው?
ሀ. ካሪባ ለ.ታንጋኒካ ሐ. ቱርካና መ. ማላዊ
24. የአርክቲክ ክበብ የሚገኘው በስንት ዲግሪ ላይ ነው?
ሀ. በ661/2 ዲግሪ ሰሜን ለ. በ231/2 ዲግሪ ደቡብ
ሐ. በ231/2 ዲግሪ ደቡብ መ. በ231/2 ዲግሪ ሰሜን
25. ከሚከተሉት ውስጥ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ያልሆነችው የቷ ነች?
ሀ. ኤርትራ ለ. ኬንያ ሐ. ሌሴቶ መ. ኡጋንዳ
26. ከሚከተሉት የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች በከፍተኛ የህዝብ ብዛትና በትንሽ የህዝብ ብዛት
በትክክል የተጣመሩት የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ሶማሊያና ኤርትራ ለ. ዩጋንዳና ሩዋንዳ
ሐ. ኢትዮጵያና ሲሼልስ መ. ኤርትራና ጅቡቲ
27. በ4ኛው ክፍለ ዘመን የአክሱም መንግስት ንጉስ የነበረው ማን ይባላል?
ሀ. ኢዛና ለ. ካሌብ ሐ. ኩሽ መ. አፄ ዮሀንስ
28. በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ከቅርስ ቦታዎች የማይካተተው የቱ ነው?
ሀ. የአክሱም ሀውልት ለ. የአስመራ ጥንታዊ ከተማ
ሐ. የጥያ ትክል ድንጋዮች መ. የጥምቀት በዓል ትርኢት
29. ከሚከተሉት የቅርሶች ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የስራ ዕድል መፈጠር ለ. የፈጠራ ስራን አለማስፋፋት
ሐ. የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት መ. የገቢ ምንጭነት
30. በምስራቅ አፍሪካ የቅርስ አጠቃቀምን ከሚቀንሱ ምክንያቶች የማይካተተው የቱ ነው?
ሀ. በቂ እቅድ አለመኖር ለ. በቂ ቁጥጥር አለመኖር
ሐ. ለተፈጥሮና ለሰው ሰራሽ አደጋዎች መጋለጥ መ. የተሟላ ጥበቃ ማድረግ
31. ከሚከተሉት ከተፈጥሮ የቱሪዝም ቦታዎች የማይካተተው የቱነው?
ሀ. የጀጎል ግንብ ለ. የኮሞሮስ ደሴት
ሐ. የታንጋኒካ ሀይቅ መ. አዋሽ ብሄራዊ ፓርክ
32. ነጭ የደም ህዋሳችንን በማጥቃት የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም የሚያዳክም
ቫይረስ ምን ይባላል?
ሀ. ኢንፉሌንዛ ቫይረስ ለ. ኮሮና ቫይረስ
ሐ. ኤችአይቪ ቫይረስ መ. በርድ ፍሉ ቫይረስ (ጉንፋን)
33. የምስራቅ አፍሪካ ዋና ዋና የድርቅ ምክንያቶች ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ከብቶችን ለብዙ ጊዜ በአንድ ቦታ አለማሰማራት ለ. የህዝብ ቁጥር መጨመር
ሐ. የአየር ንብረት ለውጥ መ. የአካባቢ መራቆት
34. ከሰው ሰራሽ መስህቦች ውስጥ አምስት በሮች ያሉት ጥንታዊ ቅርስ የቱ ነው?
ሀ. ላሊበላ ለ. የአክሱም ሀውልት ሐ. የሀረር ጀጎል ግንብ መ. ሶፍዑመር ዋሻ
35. የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (IGAD) ድርጅት መቀመጫ ሀገር የቷ ናት?
ሀ. ጅቡቲ ለ. ኬንያ ሐ. ኤርትራ መ. ኢትዮጵያ
36. ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አንዲትን ሴት ልጅ ያለ ፍላጎቷ አስገድዶ ለጋብቻ መውሰድ ምን
ይባላል?
ሀ. አስገድዶ መድፈር ለ. ግግ ማስወጣት ሐ. ጠለፋ መ. ያለዕድሜ ጋብቻ
37. ከሚከተሉት አደናዛዥና ሱስ አምጪ እፆችና ኬሚካሎች ከውህዳቸው ጋር በትክክል
ያልተጣመረው የቱነው?
ሀ. አልኮል - ኢታኖል ለ. ጫት - ካቴኒን
ሐ. ትምባሆ - ኢታኖል መ. ሲጋራ - ኒኮቲን
38. የአፍሪካ አህጉር ከኤስያ አህጉር ጋር የሚያደርጉት የንግድ አይነት ምን ይባላል?
ሀ. የውስጥ ንግድ ለ. የሀገር ውስጥ ንግድ ሐ. የውጭ ንግድ መ. ህገ ወጥ ንግድ
39. ከናይል ተፋሰስ ሀገሮች 86 በመቶ የውሀ ድርሻን የምታበረክተው የምስራቅ አፍሪካ ሃገር
የቷ ናት?
ሀ. ታንዛኒያ ለ. ኢትዮጵያ ሐ. ኬንያ መ. ጅቡቲ
40. በምስራቅ አፍሪካ በታንዛኒያ የሚገኘው ትልቁ ተራራ ማን ይባላል?
ሀ. ሩዋንዞሪ ለ. ኪሊማንጀሮ ሐ. ኤልጎን መ. ሜሩ