You are on page 1of 25

የሐምሌ 2005 / July 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 5

~1~

ለ አእምሮ ፥ ቁ– I-05/7-5
ለ አእምሮ ፥ ቁ– I-05/7-5

የሐምሌ 2005 / July 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 5

ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ

ርዕሰ አንቀጽ፣ አብዮት ሲፈነዳ !

የግእዝ ፊደል ስረ፥መሰረት – Origins and Usage of Ge’ez

ጸሐይ ስትጠልቅ፣ መጽሐፍ ሳገላብጥ

~2~

ሀሌታው “ሀ” ከሁሉም በፊት የነበረ በግሪክ ወይም በላቲን “አልፋ”የሚባለው ቃል ነው።
የግዕዙ”ሀ” አገርም “ሀገርም” ማለት ነው።

ለ — ለአ እምሮ ነው ።
የባህላችን ዕድገት ፣ የምንኮራበትና ልናጌጥበት የምንችለው፣ አንዱ ነገር ቢኖር (እሱ ብቻ
አይደለም) በፊደላችን ነው። ጥቂት አገሮች ናቸው የራሳቸው ፊደል ያላቸው። አንደኛው
ደግሞ እኛ ነን።
ይህ የፊደል መጀመሪያው – “ሀ” – ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ታሪክ ያዘለው ፊደላችን፣
እንኳን ለኛ፣ ለዓለምም እንደ ሰው ልጅ “ባህላዊ ቅርስ ተጠብቆ” የሚቆይ ነው።
በነዚህ በምንኮራባቸውና ከማንም ህዝብ ያላነሰ ልንታይባቸውና ልንገለገልባቸው
በምንችለው ፊደሎቻቻን፣ ብዙዎቹ ያልቻሉትን፣ እኛ ግን ማንም እንደሚያውቀው ፣
መጽሐፍ ቅዱሱን ፣ ቅዱስ ቁራኑን፣ መጽሐፈ ቁልቁልን ፣ ሰምና ውርቁን፣ ቅኔውን፣
ድርሰቱን ፣ዜማውንና ቅዳሴውን ፣ ታሪካችን ሳይቀር ተጽፎበት ዛሬ እናነበዋለን። በመቶና
ከዚያም በሚበልጡ ፊደሎች ደግሞ ጋዜጣ አትሞ ማውጣትም ይቻላል።
በጥቂት ፊደላትም ብዙ ነገር መናገር ይቻላል። “ሰምና ወርቁ” ልዩ ምስክር ነው። ወስጠ
ወይራና አሽሙር፣ ሽሙጥና ቅኔ፣ ግሩም ነገሮች ናቸው። አዝማሪው ይችልበታል።
ገጣሚው በቃላት መጫወትን ያውቅበታል። ጋዜጠኛው፣ ጸሐፊው፣ ተቺው፣ ዕድሉን
ቢያገኙት እንደ ሌሎቹ ፣ፊደሉን ያሽከረክሩታል።…
ከአንድ መቶ በላይ የሆኑ ፊደላት ሲገጣጠሙ ደግሞ ፣ እላይ እንደተባለው መጽሐፍ ቅዱስን
፣ ከዚያም አልፎ (ደካማ ምላሶች እንደሚሉት ሳይሆን) ቅዱስ ቁራንን፣ መጽሐፈ ቁልቁሉን፣
በግዕዝ ፊደል ተርጉሞ መጻፍም ይቻላል። እንግዲህ ብዙ ፣የሚቀራረቡና የማይራራቁትን
ቋዋንቋዎችንም ማስተናገድ (በትውልዱ መካከል መስማማት ቢኖር) ጨርሶም ባልከበደው
ነበር 1)። ከመቶ በላይ በሆኑ ፊደላት እንደ “ፍቅር እሰከ መቃብርን ” የመሰለ ልብ ወለድ
~3~

ድርሰት ተደርሶአል። ” የኢትዮጵያ ታሪክን”፣ “የሔሮዶቲስን” ጥንታዊ ጽሑፍ ፣
የቮልቭጋንግ ጉተን ሥራዎች ተርጉሞ ማቅረብም ተችሎአል።
ግን ፊደላትና ቃላትን ዝም ብሎ መገጣጠም ብቻ ሳይሆን ( ያ! እንዳየነው ወደ ጥራዝ
ነጠቅነት ይወስዳል) አንድን ነገር ጽፎ ለንባብ ማቅረብ ፣ በመጀመሪያ ማሰብንና ማሰላሰልን
፣ረጋ ብሎ ማጥናትን ፣ ከሒሊና ጋር መሟገትን፣ ፕላን ማውጣትን ፣ መሰረዝ መደለዝን ፣
መጠንቀቅን ፣እረስንቱን….ይጠይቃል።
ፊደል :-የእራሱ ፊደል ያለው ሕዝብ፣ መዓት ዕለታዊ፣ ነጻ-ጋዜጣዎችንም ከነ መጽሄቱ፣
አሳትሞ ማውጣት ይችላል። ይህ ግን አልተቻለም። ለምን?
የዛሬውም ጽሑፋችንም በዚሁ” በፕሬስ ” ጉዳይ ላይ ያተኩራል።
ለምንድነው በምዕራቡ ዓለም “በካፒታሊዚም ሥርዓት” ነጻ -ጋዜጣ ፣ ማለት የፕሬስ ነጻነት
የተስፋፋው፣ የተፈቀደው?…የተከበረው? ለምንድነው በተቃራኒው ይህ የጋዜጠኞች
መብት፣ በምሥራቁ ዓለም ፣ በኮሙኒዝም፣የአገዛዝ ዘመን የተከለከለው? እንደ ወንጄልም
ተቆጥሮ ጋዜጠኛን የሚያስከስሰው? ለምንድነው ኮሙኒዝምና ስታሊንዚም እንደዚሁ
ፋሺዚም፣ ነጻ ፕሬስን ፣ ነጻ-አስተሳሰብን ሁለቱ ሥርዓቶች ተመካክረው ይመስል ፣ ፈጽሞ
የማይወዱት? አሳደውም፣ ሁለቱም የሚያጠፉት?
ለምንድነው በምዕራቡ ዓለም ሰው በነጻ- መደራጀት የሚችለው? የፈለገውንም ድርጅት
መምረጥ፣ለእሱ የተፈቀደለት?
ለምንድነው የምርምር ነጻነት ፣ የመጠየቅ መብት መቃወምና መተቸት እዚህ ፣ አውሮፓ
እዚያ አሜሪካ የተፈቀደው? በተቃራኒው፣ ቻይናና ሰሜን ኮሪያ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ
የተከለከለው?
እንግዲህ እነዚህን ሁሉ ጥያቄዎች ቀስ እያለን ተራ በተራ መለስ ብለን እንመለከታቸዋለን።
እንዳልነው ዛሬ በፕሬስ ነጻነት እንጀምራለን።
መልካም ንባብ፣ መልካም ቆይታ!
አዘጋጁ ይልማ ኃይለ ሚካኤል።
___________________________________

~4~

ስለ ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ፤ ስለ ጋዜጣና ጋዜጠኛነት፣የፕሬስ ነጻነት
***
“የሰው ልጆች በሙሉ ፣ በትውልድ
ነጻ እና አኩል መብት በሕግ ፊት አላቸው።” 1789 የፈረንሣይ ሽንጎ አዋጅ።

እንዴት ደሰ ይላል ቅዳሜና እሁድ ወይም ከሥራ መልሰ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ከቤተሰብ ጋር
እየተወያዩ የዕለቱን (የተለያዩ) ጋዜጣዎች ሲያገላብጡ።
እጅግ ደስ ይላል ቡና ቤት ቁጭ ብሎ ጋዜጣዎችን፣ ከቢራ፣ ወይም ከሻይ፣ ወይም ከአፕሬቲፍ ጋር፣
የተለያዩ ሐሳቦችን ሲያጣጥሙ። በጣም ደስ ይላል አውሮፓና አሜሪካ መጽሔትና ጋዜጣ እቤት ድረስ
በፖስታ መጥቶ የቁርስ ጠረጴዛ ላይ ሲዘረገፍ። የለመዱት ጽሑፍም ተከትሎ ያደሩበት ሆቴል ከተፍ
ሲል እንዴት ደስ ይላል።

~5~

ግን ደግሞ እንደምናቀወቀው፣ይህን የመሰለ ሁኔታ ሁሉም ቦታ አይታይም። አንዱ “ጉልበተኛ
አምባገነን” መጥቶ፣ ሁሉንም ጋዜጠኞችን እሥር ቤት ወርውሮ ቢሮአቸውን ዘግቶ „…ከዛሬ ጀምሮ
የቡርጃ የአደሃሪዎች ቅጠሎች ፣ እንዳይታተሙ በአዋጅ ተከልክሎአል” ሊልም ይችላል። በእጁም
የተገኘውን አብሮ ሊቀጣውም ይህ ፍርደ ገምድል ይችላል ።
ብዙ ቦታ እንደዚህ ተደርጎአል። ብዙ ቦታም የጋዜጠኞች ሥራ እንደ ወንጄል ተቆጥሮ ታስረዋል።
ተገድለዋል። ያመለጡትም ተሰደዋል።
የቀረውን ለማንበብ እዚህ ይሂዱ…
ስለ ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ፤ ስለ ጋዜጣና ጋዜጠኛነት፣የፕሬስ ነጻነት
________________________

1)

http://leaimero.com/2013/07/03/origins-and-usage-of-geez/

ርዕሰ አንቀጽ፣ አብዮት ሲፈነዳ !
Posted on July 11, 2013

አብዮት ሲፈነዳ !
የዘንድሮው አብዮት ደግሞ ፍጹም ሌላ ነው። ይህ ነገር ሳይታሰብ ብድግ ብሎ ብራዚልን
መቶታል። ቱርክን አገላብጦአታል።ካይሮ ላይ ደግሞ ተመርጠው አንድ አመት በገዙ
ማግሥት ፕሬዚዳንት ሙርሲን አብዮቱ ይዞአቸው ሄዶአል። ከእሳቸውም ጋር “በእስላም
ሃይማኖት” ስም የተጠቀለለውን የ”ፖለቲካ አጀንዳና ፕሮግራም” አብሮም ወስዶ አብዮቱ
ሌላ ትምህርት ጥሎ ( ነገር ለሚገባው ሰው) ዞር ብሎአል።
በካይሮ የተካሄደው “ኩዴታ ነው? ወይስ አብዮት?”ይህ አሁን፣ አብዛኛውን ሰውን ሁሉ
የሚያነጋገር አርዕስት ነው። አንድ “በሕዝብ የተመረጠን ፕሬዚዳንት የሥራ ዘመኑን
ሳይጨርስ ” በአደባባይ ሰልፍና በወታደር ትዕዛዝ ከቤተ-መንግሥቱ ማባረር፣አባሮም
“እሱንና ተከታዮቹን ማሰር ፣ ይህ ይቻላል ?ይህ ተገቢ ሥራ ነው? ” ብለው እራሳቸውን
የሚጠይቁም ሰዎች ቁጥር ትንሽ አይደሉም።ለመሆኑስ ይቻላል? ይህ ከሆነማ የዲሞክራሲ
ምርጫ ትርጉሙ ምንድነው?
“የምዕራቡ ዲሞክራሲ ሞዴል”፣ እንደ አልጄሪያው ፣በዚሁ “ተንኮል” ብዙዎቹ
እንደሚሉት “አለቀለት ” ባዮቸ፣ ተበራክተዋል። እንደዚህ ዓይነትና አስተያየቶችና
ጥያቄዎችም ከያለበት፣ እኛ እንዳዳመጥነው፣ በተለይ ከአረብ አገር ወጣቶች ይወረወራል።
ዕውነት አላቸው?
~6~

የእስልምና ሃይማኖትና ዲሞክራሲ አብረው የሚሄዱ፣ “ትምህርቶችና የኑሮ ዘይዜዎች”
አይደሉም፣ ብለው ይህን የሚጠራጠሩም ሰዎች አሉ። እነሱስ እውነት አላቸው?
ሌላ ቦታም ፣ የሁሉም ችግር አንድ ስለአልሆነ ሌላም ጥያቄ ይነሳል። ለምሳሌ፣ በምርጫ
ማጭበር የሕዝብ “አናት” ላይ የተቀመጠውን ድርጅት በተቃውሞ ሰልፍ ፣በአደባባይ
አመጽ እነሱን ማባረር ይቻላል? እንዴት? ሌሎችስ እንዴት ወደቁ? ሊወድቁ ቻሉ? ለዚህስ
መልስ አለን?
እንዴት ነው? ለምንድነው? ኳስ የሚወደው ፣እንዲያውም “ማምለክ” የሚቃጣው
የብራዚል ሕዝብ ፣ በኳስ ጨዋታ ወራት ፣ በምርጫ ሥነስርዓት ሕዝቡ በመረጠው በአንድ
መንግሥት ላይ፣ በፕሬዚዳንቲዋ፣ አንበል በግራ ሴትዮዋ ላይ እንደገና ሕዝቡ ሊያምጽ
የቻለው?
ምንጎደለብኝ ብሎ ነው የቱርክ ወጣትስ፣ እራሱ በመረጠው ፕሬዚዳንቱ በኤርዱዋን ላይ
አሻፈረኝ ብሎ የተነሳው? ጥያቄዎቹን በኑሉ መመለስ አስቸጋሪ ነው። ግን ደግሞ መልስ
አለው።
አብዮት ሳይታሰብ፣ አድፍጣ እንደ ጣረ ሞት ፣ “ዓለም ጤና ነው ተብሎ ሲጨፈር ሲደነስ
“፣ እንደ አሱዋ እነደ እሱ ተደብቃ ነው ፣ከተፍ የምትለው። አንዴ በጨለማ፣ብቅ ትላለች።
አንዴ በጡዋት። አንዴ ጊዜ ደግሞ በጠራራ ጸሓይ ። አንዴ በክረምት፣አንዴ በበጋ፣ በጸደይ
ወይም በገብርኤል ወይም በማሪያም ቀን በድንገት አለ-ቀጠሮ ከተፍ አብዮት ትላለች።
ከመጣች ደግም በዓለም ታሪክ ላይ እንደተጻፈው ፣ ፖሊስ አያቆማትም። ወታደር
አይመክታትም። ቦንብ ፣ጠበንጃ፣ አይሮፕላንና ሰላይ አያስፈራራትም።መጣች ማለት
መጣች ነው። እርግጥ ሙከራ ሳያደርጉ ተፍጨርጭረው እጃቸውን የሰጡ ጥቂቶቸ ብቻ
ናቸው። የሁዋላ ሁዋላ ግን አብዮት አሸናፊ ነው። ቁም ነገሩ ምን ዓይነት አብዮት? የሚለው
ጥያቄ ነው። “ብሔራዊ ዲሞክራሲ? አብዮታዊ ዲሞክራሲ? አዲሱ ዲሞክራሲ? …የአንድ
ታርቲ ዲሞክራሲ?” …ምን ዓይነት ዲሞክራሲ?
ግብጽ በአሁኑ ሰዓት ከሦስት-ተመልካቾች እንደሚሉት- አማራጮች ፊት ቆማለች።
አንደኛው ወታደሩ እንደሚለው፣ ሊበራሎቸና ሌሎች ዘመናዊ ሰዎች እንደሚመኙት፣
በቅርቡ(መቼ?በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ?) የሸንጎ ምርጫ ተካሂዶ፣ አክራሪዎቹ ሳይሆኑ፣
ሊበራሎቸ በምርጫ አሸንፈው ሥልጣኑን ሲረከቡ ነው ይባላል።
ሁለተኛው የእርስ በእርስ ጦርነት ተከፍቶ አገሪቱ ከቁጥጥር ውጭ ትሆናለች የሚለው፣
አስፈሪው ግምት አብሮ ያን አካባቢ እናውቃለን ከሚሉ ሰዎች አንደበት ተሰምቶአል።
ሦስተኛውና የመጨረሻው መላ-ምት ደግሞ፤፤ ይህን ሁሉ ትርምስ ማየት የማይፈልገው ፣
የአገሪቱ የጦር መኮንንኞችና፣ ማለት የወታደሩ ቡድን ” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” አውጆ ፣
እንደዱሮ አገሪቱን ለመግዛት ብድግ ብሎ “ሥልጣኑን” -ሁላችሁም አትችሉም ብሎ
ይረከባል።
~7~

ከሦስቱ ወይም ከአራቱ ወይም ከእዚያም በላይ ያሉ አማራጮች እንዳሉ ግልጽ ነው። ግን!
አዝማሚያው ግን አሁን -ነገር ለማሳጠር- ግብጽ ወደዚያ ወደ የሚፈስራው ፣ ወደእርስ
በእርስ ጦርነት እያመራች ነው። ምክንያቱም የእስላም ወንድማማቾቸ ለሙርሲ ወደ
ሥልጣን መመለስ እንታገላለን ባዮች ናቸው። እንዲያውም እንሰዋለታለን እስከማለትም
ሄደዋል። ሥልጣኑ ለእኛ ወይም ለማንም። እነደዚህ የሚሉ በዚህች ዓለም ብዙ ናቸው።
ብቻ ያ እንዳይሆን ወታደሩ እንደተለመደውና እንደሚታወቀው “ሥልጣኑን” መልሶ እጁ
አስገብቶ “ሁኔታውን ማረጋጋት ነው” የሚለው ግምት ተጠናክሮ፣ በምዕራቦም ዘንድ
ወጥቶአል።
ግን ደግሞ ያ እንዳይሆን አንድ ሕዝቡ የሚለውንና የሚያስበውን እዚህ ላይ ማስታወስ
ያስፈልጋል።
“…ሙባራክን ጥለን ” ሰልፈኞቹ እንዳሉት “ሙርሲን አመጣን። እሱ ግን የእራሱን
መንገድና የእራሱን ድርጅት ዓላማ ሌላውን የሕብረተሰብ ክፍል ረስቶ በሥራ ለማዋል
ሞከረ። አሁንም እንደገና ተነስተን እሱንም እንደሙባራክ ጣልነው። ወታደሩም እንደገና
ሥልጣኑ ላይ ጉብ ብሎ አልወርድም ከአለ፣ እነሱንም ታግልን እናውርዳቸዋለን…” ይህ
እንግዲህ የአብዛኛው ወጣት ሰልፈኞቸ አስተሳሰብ ነው።።
ይህ አነጋገር ደግሞ በሌላ በኩል “…ቆመን የሰቀልነውን ፣ ቁጭ ብለን ማውረድ
አልቻልንም ” የሚለውን የፊታውራሪ ሐብተ-ጊዮርጊስን አነጋገርም ለእኛ ፣ ያስታውሰናል።
ያም ሆነ ይህ ፣ የግብጽ ዕጣ ዕድል ወሳኝ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ፣ ሌሎቸ ኃይሎችም ናቸው።
በተለይ ውጭ ኃይሎች እንዳሉበት መገመት አስቸጋሪ አይደለም። ብዙ ገንዘብ እዚያ
ለማፍሰስ ሁሉም እጁን ዘርግቶአል።
ቱርክና ብራዚል ያሉበትና የገቡበት ችግር እንደ ግብጽ አገር ባይሆንም፣ መጪው ምርጫ
አሁን ሥልጣን ላይ ያሉትን፣ የብራዚል ፕሬዚዳንቱዋንና ለጠቅላይ ሚኒስተር ኤርዱዋን
እነደማያሸንፉት የታወቀ ነው። ሁለቱም እንደገና አይመረጡም።
ዲምክራሲ ማለት “ምርጫና በምርጫ ሥነስርዓት” ላይ ብቻ ተሳትፎ እቤት መግባት፣
ተመልሶ ገብቶ “ገዢው መደብ አእስከሚመጣው ምርጫ የፈለገውን ያድርግ “ማለት
አይደለም። በዲሞክራሲ በምርጫም ሥልጣን ላይ መውጣት ማለት ደግሞ ፣ የሌሎቸንም
መብትና ክብር ፣ ጥቅምም ጭምር ረግጦ የእራስን፣ የአንድ ድርጅትን ጥቅምና አላማ በሥራ
ላይ ማዋልም አይደለም። አብሮ ከሌሎቹ ጋር ፣ የሌሎቸን መብት፣ መጠበቅ ፣ መንከባከብ
፣ ማስተናገድ ማለት ነው። ሥልጣንን ለሌላውም ክፍል ማጋራት፣ በሕግ መገዛት፣ ሌላውን
ማዳመጥና የሌላውንም መብት አለመጋፋት ማለት ነው።
ይህን ያላዩ ይህን ያልተገነዘቡ ዕብሪተኛ፣ ጥጋበኛ ማለት እንችላልን ” መሪዎች”፣ ይኸው
እንደምናየው ችግር ውስጥ አሁን ገብተዋል። አንደኛው ሙርሲ ነው። ሁለተኛው እንደ
ሙርሲ አንዴ ስለ ተመርጥኩ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ የሚለው የቱርኩ ኤርዱዋን
ነው። ሦስተኛው የብራዚሊያ ፕሬዚዳንት ናት። ነገ ደግሞ ማን ይሆን?
~8~

እንደዚህ ዓይነቱን በዕብሪት ላይ የተመሰረተውን፣ ልቡ ያበጠውን የ 20ኛውና የ19ኛውን
ክፍለ-ዘመን የመሪዎችን ጥጋብ ፣ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ወጣቱ ትውልድ እንደ አባቶቸ
ከእንግዲህ ዝም ብሎ ፣ አፉን ይዞ አይመለከተውም። ሞገደኛ ነው። ለመሆኑ አንተስ ማንነህ
? ብሎ የሚጠይቅ ደፋር ትውልድ ነው።
አንድ አዛውንት ካይሮ ላይ እንደዚህ ብለዋል። “እኛ ደፍረን ተነስተን ያልሞከርነውን
ልጆቻችን ተነስተው የሙባራክን፣ አሁን ደግሞ የሙርሲን ሥርዓት ገርስሰው እነሱ ጥለዋል፣
ተነስተን ፣ ለእነሱ (ዕውነታቸውን ነው) እጅ መንሳት ይገባናል…” የሚለውን የምስክርነት
ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ነገ ደግሞ ማን ይሆን?
ምናልባት የቻይና ዕብሪተኞች ? ምናልባት የሰሜን ኮሪያው ጎልማሳ? ወይስ
ኪዩባ?….ወይስ የኤርትራው ገዢ ? ወይስ ኢትዮጵያ? እኛ ጠያቂዎች ነን እንጂ መልሱ
ያለው ሌላ ቦታ ነው። እሱም “ሳይታሰብ እንደ ሞት ብቅ የምትለው አብዮት ላይ ነው።”
“አብዮት ለመሆኑ ምንድነው?” ብለን አንድ ቀን እራሳችንን መጠየቃችን አይቀርም።
መልሱ ደግሞ በእጃችን ላይ ነው። እሱም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርኩ እንደ
ማንኛውም “ነጻ ሰው ነኝ” የሚለው አስተሳሰብና እምነት፣ ጠንክሮ ሲወጣ ብቻ ነው።
የግብጽ ወጣቶች፣ የቱርክ ልጆች፣ የብራዚል ጎልማሣዎች፣ ሕዝቡ ሁሉ በገዢዎቻቸው ላይ
ያውም በመረጡዋቸው ላይ የተነሳው “….አሁንስ አበዛችሁት” ብሎ ደፍሮ፣ ተነስቶ
ገደባቸውና ልካቸውን አሳይቶአል። አዛውንቱ እንደአሉት ባርኔጣ አንስቶ ደፋሩን ትውልድ
እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ተገቢ ነው። የሦስቱም አገር ልጆች ጥያቄ ፣ እንደ እኛዎቸ
“የመገንጠልና የመገነጣጠል” ጥያቄም አይደልም ። የእነሱ ዓለም ሌላ ነው። የእኛ ግን ገና
የስታሊን የ19ኛው ክፍለ-ዘመን “የዕውቀት”ደረጃ ላይ ነው ተገትሮ የቀረው።
የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ጥያቄና መልሶቹ ፍጹም ሌላ ነው።
አብዮት፣ ስለአረፈደች የቀረች ትመስላለች እንጂ ፤ ግን አለጥርጥር የትም አትቀርም። ነገ
ከተፍ ትላለች። ነገ ከአልመጣች፣ ተነገ ወዲያ አለጥርጥር ብቅ ትላለች። ግብጽና ቱርክ፣
ብራዚልና ቡልጋሪያ…ምስክሮች ናቸው።

~9~

ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ
Posted on July 11, 2013

ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ
ጋዜጣና ጋዜጠኛነት፣የፕሬስ ነጻነት

“የሰው ልጆች በሙሉ ፣ በትውልድ ነጻ እና አኩል መብት በሕግ ፊት አላቸው።” 1789
የፈረንሣይ ሽንጎ አዋጅ።

እንዴት ደሰ ይላል ቅዳሜና እሁድ ወይም ከሥራ መልስ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ከቤተሰብ
ጋር እየተወያዩ የዕለቱን አንድ ሳይሆን የተለያዩ ጋዜጣዎችን ሲያገላብጡ።
እጅግ ደስ ይላል ቡና ቤት በረንዳ ላይ ጋዜጣዎችን፣ ከቢራ፣ ወይም ከሻይ፣ ወይም ደግሞ
ከአፕሬቲፍ ጋር፣የተለያዩ ሐሳቦችንና አመለካከቶችን አምዱ ላይ እየመተሩ አብረው
ሲያጣጥሙ።
እኔን ማንንም በጣም ደስ ይላል አውሮፓና አሜሪካ መጽሔትና ጋዜጣ እቤት ድረስ በፖስታ
መጥቶ የቁርስ ጠረጴዛ ላይ ሲዘረገፍ። የለመዱት ጽሑፍም ተከትሎ ያደሩበት ሆቴል ከተፍ
ሲል። እንዴት ደስ ይላል፣ እየተዝናኑ፣ እየተንጠራሩ ሁሉነም ሲፈትሹት።
ግን ደግሞ እንደምናቀወቀው፣ይህን የመሰለ ሁኔታ ሁሉም ቦታ አይታይም።
አንዱ “ጉልበተኛ አምባገነን” ባልታወቀና በአልተሰማ ስም ከየትም መጥቶ፣ ሁሉንም
ጋዜጠኞችን እሥር ቤት ወርውሮ ቢሮአቸውን ዘግቶ „…ከዛሬ ጀምሮ የቡርጃ የአደሃሪዎች
ቅጠሎች ፣ እንዳይታተሙ በአዋጅ “ከልክዬዋለወ ሲል። በእጁም አንድ ጽሑፍ የተገኘውን
ሰው አብሮም እዚያው እሱን ሲቀጣው፣ሲያባረው፣ ሲያስፈራራው።
~ 10 ~

የለም እንዳይባል ብዙ ቦታም እንደዚህ ተደርጎአል። ብዙ ቦታም የጋዜጠኞች ብዕር እንደ
ወንጄል ተቆጥሮ ታስረዋል። ተደብድበዋል ። ቆስለዋል። ተገድለዋል። በአጋጣሚ
ያመለጡትም ተሰደዋል።
በጣም ደስ ይላል ፣ ሱቅ ተገብቶ ከአንድ ሺህ ጋዜጣና መጽሓፍት ውስጥ ከእነሱም መካከል
አንዱን ደስ ያለውን ሳብ አድረጎ ገንዘቡን ከፍሎ፣ አለፍርሃት ከእዚያ ሲወጣ!
አእምሮን እንዴት ደስ ይለዋል፣ መንፈስም እንዴት ይረካል፣ ከሃያና ከመቶ ሺህ መጻሕፍት
ውስጥ አሥሩን ሃያውን ከአንድ መጽሓፍት ቤት ተውሶ ወደ መኖሪያ ቤት ማታ ሲገባ!
ግን እዚያም፣እዚህም ከታሪክ እንደምናውቀው፣ አንዱ መጥቶ፣ „…አንጎል የሚያበላሹ
ድርሰቶች “ብሎ በአደባባይ ላይ መጽሓፍቶቸን ሰብስቦ ቤንዚን አርከፍክፎ በክብሪት
ሲያቀጥል።
ሒትለርና ሞሶሊኒ፣ ስታሊኒንና ሌኒንን፣ ማኦና ፖልፖት፣ሞኝ አንሁን ከእንግዲህ ቀንድ
አናበቅልም ….ካስትሮና፣ ኪም ኢልሱንግ ፣ ኢሳያስና ….ዝርዝራቸው ረጅም ነው፣
…ጋዜጦች እንዳይሰራጩ ፣ መጽሓፍቶች እንዳይታተሙ፣ ቲያትር መድረክ ላይ አለ እነሱ
ፈቃድ ሰዎች እንዳይጫወቱ፣ ፊልሞች እንደገና ከአለእነሱ ፈቃድ እንደይቀረጹ፣ እላይ
የተጠቀሱ ሰዎችና ሌሎቸ ግብረ አበሮቻቸው፣ ከልክለዋል፣ ደምስሰዋል፣ ከመጽሓፍት
ቤትም ግሩም መጽሓፍቶች አውጥተው አቃጥለዋል። በአዋጅም አንዱም ደፍሮ
እንዳይጽፍም ፣ ሥዕልእንዳይስልም፣ ዘፈን እንዳይዘፈንም፣ እነሱ አግደዋል።
እንዴት ደስ ይላል፤ እቤት ተገብቶ ከሁለት መቶ ፣ ሦስት መቶ የራዲዮና የቴለቪዢን
ፕሮግራሞች ውስጥ እያማረጡና እያወዳደሩ፣ የፈለጉትን፣አንዱን ወይም ሁለቱን ፣
እያፈራረቁ ሲመለከቱት። እረ! እንዴት ደስ ይላል ከግል የመጽሓፍት መደርደሪያ ውስጥ
አንዱን መጽሓፍ ሳብ አድረገው ሲያገላብጡት። ዘንድሮማ ኢንተርኔት ውስጥ ተገብቶ
ከአንዱ ውቅያኖስ ወደ ሌላው ጠረፍ አለፍርሃት ሲዋኙ፣ ጽሑፍ ሲሰበስቡ እንዴት ደስ
ይላል።
ግን እንደምናውቀው፣ አንዱ አምባገነን መጥቶ፣ ሁሉንም የመገናኛ መስመር ከስልኩ ጋር
ጥርቅም አድርጎ ብዙ ቦታ በጉልበቱ ዘግቶአል።
የት ነው ? ከመሆኑ ያለነው? በስንተኛ ክፍለ-ዘመን ውስጥ ነው አሁን እኛ የምንገኘው?
ለማገድ ማን ፈቀደለት? ማን አይዞህ አለው?

የሰው ልጆች በተፈጥሮአቸውና በባህሪያቸው፤ እንደ መላእክት ከክፉ ነገር የራቁ ፣ ንጹህና
የተባረኩ ርህሩህ ፍጡሮች አይደሉም። በዚህ አትታለሉ።
~ 11 ~

ግን ደግሞ ይህ ስለተባለ እንደ ሰይጣንም እርኩስና አረመኔዎች አይደሉም። በሁለቱም
መካከል የሚገኙ፣ ግን በጥቅሉ እንደዚህ ናቸው ተብለው ፣ በድፍኑ፣ በጅምላው ፣
„የማይያዙና የማይጨበጡ ፍጡሮች“ ናቸው።
” እንደዚህ ዓይነት አረመኔዎች” በየአለበት አሉ ስንል፣ ደግሞ” ደህና ሰው ” በዚህች ዓለም
የለም ማለት አይደለም።ድህና ሰዎች ብዙ ቦታ አሉ። በሌላ አካባቢም እናገኛለን። ሁሉም
ደህና ናቸው ብለን ስናምናቸውና ልባችንን ገልጠን ስንሰጣቸው ደግሞ “ቀጣፊ ሌቦች”
ሁነው እስርቤት ሲወርዱ እናያቸዋለን።
„ቁጥጥር“ ከአልተደረገባቸው ፣ብዙ ሰዎቹ፣ ከአረመኔ ድርጊታቸው አይመለሱም ። እርግጥ
በመልካም ቤተሰብ በጥሩ እንክብካቤ ተኮትኩተው ከአደጉ ደግሞ ደግና ርህሩይ ሰው
ስለሚወጣአቸው፣እንደነሱ አይነት ሰዎች አረአያ ናቸው። ያም ቢሆን ምንም እርግጠኛ
የሚያደርገን ነገር የለም። ጤነኛ ያልነው ሰው “ነገ አውሬ”ነው። ሰው “ዛሬም ሰይጣንም”
ነው።
ለዚህም የአለፉት ዘመናት ብቻ ሳይሆኑ የቅርቡም ጊዜ የሰው ልጆች ታሪኮች በቂ ምስክሮች
ናቸው። በሥልጣኔ ስም፣ ስንት በደል፣በዓለም ላይ ተፈጽሞአል። በሃይማኖት ስም የስንት
ሰው ደም ፈሷል። በኮሙኒዝምና በሶሻሊዝም ስም የስንት ሰው ሕይወት፣ በከንቱ
አልፎአል። „በነጻነት ትግል“ ስም ደግሞ የስንት ሰው ንብረት፤ የስንት ሰው ሕይወት ወድሞ
ጠፍቶ፣ እናቶች መካን ሁነው ቀርተዋል። በፋሺዝም ስም ሰዎች በመርዝ ጢስ አልቀዋል።
„ሰው አረመኔም፣ ሰይጣንም፣ ርህሩህም ፣ ደግም ሰው:- ሁለቱንም፣ሦስቱንም ነው።“ ምን
አልን? በተለያዩ ስሞች፣ የሰው ልጆች ሕይወት ጠፍቶአል። ለምን? ማን ናቸው እነሱ ይህን
ለማድረግ?
ሰው ማለት በአንድ በኩል እላይ እንደቆጠርናቸው …. እነ ሒትለርና ሞሶሊኒ ፣ ስታሊንእና
…ኢዲ አሚንን፣ ሞቡቱንና ፖል ፖትን፣ ፒኖቼ እና ማኦ ሴቱንግ፣… መንግሥቱ
ኃይለማሪያምንና…ሌሎች ብዙ መሰሎቻቸውን ያካተተ ነው። አብረሃምና ሣራ፣ አቡነ
ጴጥሮስንና፣ ማሪያ ቴሬዛን… በርካታ ….ሰማዕታትና ጻድቃን፣ በሌላ በኩልም ማለት
ነው።
ለምንድነው አንደኛው „የአረመኔ ባህሪ ያለው? ሌላው በተቃራኒው ቅዱስ የሆነ ነገር
የሚሰራው?“ለምንድነው በምዕራቡ ዓለም ነጻ-ጋዜጣ፣ ራዲዮን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች
መክፈት፣ ማውጣት የሚቻለው? ለምንድነው በኮሚኒሰትና በሌሎች ቶታሊቴሪያን ሥርዓት
በሕግ የሚከለከለው?
ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ከፊሉን ሳያኮሎጂስቶች ከፊሉን ደግሞ የፖለቲካ ፈላስፋዎችና
የሕብረተሰብ ተመራማሪዎች፣ የባህል ልዩነት ጠበበቶች በቂ መልስ( ትክክል ይሁን አይሁን
መመራመሩ የሁሉም ፋንታ ነው) ሰጥተውበታል። ሁለቱም፣ ሶስቱም፣ እላይ የተጠቀሱት
~ 12 ~

ክፍሎች የደረሱበት የሰው ልጅ በእራሱና በሌላው ላይ አደጋ ከማድረሱ በፊት “ቁጥጥር „
ይደረግበት በሚለው ሐሳብና ተመክሮ ላይ ሁሉም ይስማማሉ።
ጋዜጣና ጋዜጠኞች፣ ደራሲና ጸሓፊዎች፣ ተቺና የፖለቲካ ተንታኞች፣ ፈላስፋና የሕብረተሰብ
ተመራማሪዎች….የሥልጣን ባለቤቶች፣ የሆኑትን ገዢዎች ( ይመረጡ አይመረጡ፣
ዘውዱን ይውረሱ ወይም ይንጠቁ፣…አይዉረሱ፣ ከየትም ይምጡ) እነሱን “የሚቆጣጠሩ
ሰዎች“ ናቸው። ማን ፈቀደላቸው? ልንል እንችላልን። ተገቢ ጥያቄ ነው።

„ቁጥጥር „ የምትለውን ቃል ደግሞ ከአረመኔ ሥራ የማይመለሱት አምባገነኖቹ፣ ለተንኮል
አላማቸው፣ በአንድ በኩል ስለምታመች፣ በሌላ በኩል “ጀሌውን ተከታይ ለማሳመን ”
ስለሚያመች ፣ በጣም አድረገው ይህቺን ቃል እነሱ ይወዷታል።
„…እሱን አይደለም እንዴ! እሱን እኮ ነው፣ እኛ ለእናንተ የምንመኘው“ ብለው አንዴ
እነሱ ሥልጣኑን ከነከሱ፣ ጠበቅ አድርገው፣ቀጥጥሩን ይይዟታል። በዚያም ስም ያገኙትን
ደፍጥጠው ፣እድሜአቸውን ለማራዛም ይህቺን ቃል እንደፈለጉት ያንከባልሉዋታል። በሌላ
በኩል ሥልጣን ላይ እስከሚወጡ ድረስ፣ እንደ እነሱ የግንባር ቀደም ቦታ ይዞ
„…ለዲሞክራሲ፣ ለነጻ-ጋዜጣ፣ ለነጻ- ንግግር ፣መብቶች በሙሉ መከበር „ የሚታገል ሰው
የለም።
ሁሉም አምባገነኖች ፣….ሒትለርና ሞሰሊኒ፣ ሌኒንና ስታሊን፣ ማርክስ፣ ማኦ ፖልፖት….
ዮሴፍ ጎብልስ ፣ ያውም እነሱ ግንባር ቀደም ሁነው፣ ለዚህ መብት መከበር፣ መታወቅ፣
በሥራ ላይ መተርጎም፣ (ታሪካቸውን አንብቡ) እነሱ እንደ ሌሎቸ ዲሞክራቶች አብረው ፣
እነሱ ጎን ቆመው ታግለዋል።
በሁዋላ ግን አንደምናውቀው ዞር ብለው ሁሉም „የቡርጃው ዲሞክራሲ“ “የበዝባዦች
ፕሮፓጋንዳ ጋዜጣ ” ብለው ጥለውት በቦት ጫማቸው እነሱ ፕሬሱን አፍነው፣ ረግጠው፣
ዘግተው ይዘዋል።
„ቁጥጥር „ ሲባል ምን ማለት ነው? ምን ዓይነት ቁጥጥር?ማን ነው ተቆጣጣሪው?
ቁጥጥርስ እንዴት?
በድፍኑ „ትችት እንደ ሙያ“ ያልነው በጋዜጣ ሚና እና በጸሓፊ- ጋዜጠኞች ላይ
ያተኩራል። ይህ ሙያም ደራሲና የፖለቲካ ጸሐፊዎችን፣ የታሪክና የሕብረተሰብ
ተንተኞችን፣ ፈላስፋዎችንም ይጨምራል።

~ 13 ~

የሓሳብ ነጻነት፣ የመናገርና የመጻፍ ነጻነት፣ በአጭሩ የፕሬስ ነጻነት፣ በአሥራ ስምንተኛው
ክፍለ ዘመን በስንት መከራ በትግል የተገኘ መብት ነው። ለዚህም የፈረንሣይና የአሜሪካን
አብዮት ምስክር ናቸው።
በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን አንዳንድ የአውሮፓ መንግሥታት፣ የፕሬስ ሕግ በይፋ
ሳያውጁ የፈረንሳዩ አብዮት ፣ያ አለፍርድ የብዙ ሰዎችን ሕይወት ይዞ የሄደው፣ ዓይነት
የሞት ጽዋ ለእነሱም በድንገት መጥቶ እንዳይቀምሱት፣ እንደይጨርሳቸው፣ ጋዜጠኞች
የተወሰነ ነገር (በገደብ)በቅጠሎቻቸው ላይ አንስተው እንዲጽፉ “ገዢዎቸች” ፈቅደዋል።
በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ ላይና በሃያኛው ክፍለ-ዘመን የፕሬስ ነጻነት
በአብዛኛው የአውሮፓ አገሮች ታውጆ ብዙ ጋዜጣዎች፣በያለበት ታትመው መውጣት
ይጀምራሉ።
ግን አረመኔ አምባገነኖች በፋሺዚምና በኮሚኒዝም ስም ፣በስታሊንም ስም ብቅ ብለው
እላይ እንዳልነው፣ ጋዜጠኞችን አባረው፣ ሐብታቸውን ወርሰው፣ ከአለ እነሱ ጽሑፍ
የሌሎቹን ማተሚያ ቤቶች ዘግተው፣ ድራሻቸውንም እንዳለ አጥፍተው “ዘለዓለማዊ
መረባቸውን” መስሎአቸው በዓለም ላይ ለመዘርጋት ተፍጨርጭረዋል። ሒትለርና
ሞሲሊን በሁለተኛው አለም ጦርነት ድል ተመተው ፕሬስ በአውሮፓ እጅና እግሩን ታስሮ
ከነበረበት እሥርቤት ነጻ ይወጣል። ይህም እንደምናውቀው የምዕራቡን ዓለም ብቻ
ያጠቃልላል።
ከሰባና ሰማንያ አመት በሁዋላ ደግሞ ኮሚኒስቶቹ አምባገነኖች ሳይታሰብ በተራቸው
ተንኮታኩተው ሲወድቁ፣ ነጻ -ጋዜጠና ጋዜጠኞች እንደገና አሸናፊ ሁነው በምሥራቅ
አውሮፓ ከተቀበሩበት መቃብር ብድግ ብለዋል። ከእነሱም ጋር የኮሚኒስቶቹም ጋዜጠኞች
ሳይከለከሉ እዚህ አውሮፓ- ይህ ነው ዲሞክራሲ- እነሱም ዕለታዊ ሥራቸውን
እንዲቀጥሉበት ተደርገዋል።

ፕሬስና የፕሬስ ነጻነት እነሱንም የሚያጅበው ሳንሱር ግን መለስ ብለን ስንመለከተው በጣም
ረጅም እድሜ ፣ ይህ ነገር አለው።
“ሳንሱር” የሚባለው ነገር ይፋ ሁኖ የወጣው ዮሓን ጉትንበርግ የሚባለው የጀርመኑ
ተወላጅ1 ( 1450) አስቸጋሪውን በእጅ እየተገለበጠ ለንባብ የሚቀርቡትን ጥቂት
መጻሕፍቶች፣ ከኒኬል ተሰርተው በወጡ „ዘመናዊ ፊደሎች“ እሱ ከተካቸው በሁዋላ ነው።
እነዚህ በእጅ ተለቅመው የተገጣጠሙ ፊደሎች በአንድ ጊዜ በእንድ ቀን ውስጥ፣ ከአንድ
የበለጡ መጻሕፍቶችን አንድ ሰው አትሞ ማውጣት መቻሉን የተመለከቱ የቤተክርስቲያን
ሃይማኖት አባቶችና ትላልቅ የመንግሥት በአለሥልጣኖች „ማንም ሰው አለ ልዩ ፈቃድ „
(መጪውን የጥብብና የዕውቀት መስፋፋት አይተው ) “አለ እነሱ ፈቃድ እንዳይገለገልበት”
– ዛሬ ከእንተርኔት ጋር ማወዳደር ይቻላል – እነሱ ከልክለዋል። ይህ የሳንሱር ቁጥጥርም
~ 14 ~

በህትመት ላይ በሕግ ተከልክሎ እስከ ፈረንሣይ አብዮት ድረስ ይፋ ሁኖም (ሁሉም)
“ሲገለገልበት” ቈይቶአል።
የፈረንሣይ አብዮት ለመጀመሪያ ጊዜ የሳንሱር መጋረጃውን ገርስሶ ጥሎ የፕሬስ ነጻነትን
ያውጃል። ይህ ፣ እንግዲህ በአውሮፓ ነው።
የ ደሴቱዋ የእንግለዚና የአሜሪካ ሁኔታ ደግሞ ለየት ያለ ነበር።
ጆን ሚሊተን በእንግሊዝ አገር (1644) /2 ሳንሱር እነዲነሳ ከጠየቀ ወዲህና በቨርጂኒያ፣
በአሜሪካን አገር በ1776 በሕገ-መንግሥታቸው ላይ የፕሬስ ነጻነትን ከአውጁ ወዲህ
የአውሮፓ ምሁሮች ይህን መብት እነሱ እንዲኖራቸው፣ እንዲፈቀድላቸው ገዢዎቻቸውን፣
መንግሥታቶቻቸውን ጠይቀዋል። መልስ ያላገኙትም በስውር ሐሳባቸውን ወደ ማተሙና
ወደ ማሰራጨቱም ተሸጋግረዋል።
በ1865 አውሮፓ ውስጥ ብቅ ያለው አዲሱ ተሽከርካሪው የሕትመት መሣሪያ በሺህና
በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ጋዜጣዎች ታትመው አደባባይ ላይ ብቅ ለማለት ይህነው የማይባል
ዕድል ይከፍታል። ይህን ያዩ ሁለት ቀልጣፋ ክፍሎች ቶሎ ብለው ሜዳውን ተሻምተው
እነሱ ይይዛሉ።
በአንድ በኩል የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በሌላ በኩል ትርፍ ፈላጊ “ነጋዴዎች “ትላልቅ
አሳታሚዎች ሁነው ሜዳውን ተካፍለው የፖለቲካ መድረኩ ላይ ብቅ ይላሉ። ይህን ጊዜ
በአለሥልጣን ገዢዎች፣ ብዙ ነገሮች ከእጃቸው አፈትልከው ከመውጣታቸው በፊት “ሕግ”
ወደማውጣትና በሕግ ወደ መቆጣጠሩ እሰኑም ይሸጋገራሉ።
በአዋጅ በተለያዩ አገርና መንግሥታት በ ሕገ- መንግሥታቸው ላይ “የፕሬስ ነጻነት፣… ምን
እንደሆነ?…. ይህ ሕግ ምን እንደሚፈቀድ?… መብትና ግዴታውን፣ የሥራ መስኩና
የሥራ አድማሱን ፣… ሥርጭቱና እንቅስቃሴው፣….የሚያሳዩ ፣ዝርዝር ደንቦችን ደንግገው
ያወጣሉ። …ማንም ያለፍርድ ቤት ውሳኔና ትዕዛዝ (ይህቺን ነገር ሁለት ጊዜ ማንበብ
ያስፈልጋል) የማንንም በፈቃድ የሚሰራውን የጋዜጣ ቢሮ መክፈትና መዝጋት
እንደማይችልም በሕገ – መንግሥታቸው ላይ ( በተለያዩ ጊዜያት) እያሻሻሉና እየአረሙ ፣
ከጊዜውም ጋር አብረው አየተራመዱ አዳዲስ ሕጎችና ደንቦችን አወጡ። እንግዲህ የጸሐፊው
“መደብ” የብዕር ሰው፣ ከደራሲ ጭምር ብቅ ይላሉ። ግን ለማስታወስ የደሪሲና የጸሓፊ
ዕድሜ ከዚያም ከፍ ይላል። የአቴንን ታሪክ ተመልከት።
ያም ሁኖ እላይ እንዳልነው በሃያኛው ክፍለ ዘመን በሩሲያና በጣሊያን ፣ በጀርመንና በድፍን
ምሥራቅ አውሮፓ አረመኔ አምባገነኖች ተነስተው፤ የፕሬስ ነጻነትና ሕግቹን ሽረው
ጋዜጠኞችን እያሳደዱ፣ ማተሚያ ቤቶችን እየዘረፉና እየዘጉ የራሳቸውን
/አንድወጥ/ቶታሊቴሪያን አስተሳሰብ የሚያስፋፉ የእነሱን ጋዜጣዎች ብቻ “ሕይወት”
የሚጠብቅ አዲስ ሕግ አውጥተው በያለበት በሕዝቡ ላይ መቀለድ ጀመሩ። እነሱም እዚህ
እላይ እንደጠቆምነው በሁለት መንገድ ፣፣ተራ በተራ ከፖለቲካው ዓለም ፣ይክበር ይመስገን
፣ዓይናችን እያየ ተወገዱ።
~ 15 ~

በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ ፋሺሽቶቹ ድል ሲመቱ ነጻ-ጋዜጣዎች እንደ ገና
በብዛት እዚያና እዚህ በምዕራብ አውሮፓ እንደ አሸን ፈሉ። ከበርሊን ግንብ ጋርም
ኮሚኒስቶቹ እዚህ አብረው ሲወድቁ ፣ በምሥራቅ አውሮፓ ነጻ-ጋዜጣዎች – አሁንም
ይክበር ይመስገን – እንደገና በየአለበት፣ …ከነጻ-ራዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር
አብረው አበቡ።
አፍሪካስ አሁን እንዴት ናት? ….ኢትዮጵያስ በዚህ በያዝነው 21ኛው ክፍለ-ዘመን በጋዜጣ
ሕትመት የት ትገኛለች?

ወደዚያ ከመዝለቃችን በፊት ሁለት “አዋጆቸን ” እንመለከት።እነዚህ አዋጆች በሁለተኛው
ዓለም ጦርንት ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ዓለም አቀፋዊ አዋጆች ናቸው።
ኪዚህ ሁሉ የመከራ የጋዜጠኞች ዘመን በሁዋላ አንዱ አዋጅ ታሪክን መሰረት አድርጎ
እንደዚህ ብሎ ይጀምራል። “…ሰበአዊ መብቶችን ችላ ማለትና መናቅ የሰውን ሒሊና
የአስጨነቁ አረመኔያዊ ተግባሮችን በማስከተላቸውና የተራ ሰዎችም ሁሉ ፣ ዋነኛው ጉጉት
የሰው ልጆች ሁሉ የንግግርና የእምነት ነጻነት የሚጎናጸፍበት ፣ ከፍርሃትና ከችግር ነጻ
የሚወጣበት ዓለም እንዲመጣ ….በመሆኑ
ሰዎችም በክፉ አገዛዝና በጭቆና የተነሳ ያላቸው የመጨረሻ ምርጫቸው አመጽ እንዲሆን
እንዳይገደዱ፣ ሰበአዊ መብቶች በሕግ እንዲከበሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት…”
ይህን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ በ1948 በጋራ አውጀናል ይልና፣ ይህ
ትልቁ ሰነድ። የሚታወቀውና ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት አባል አገሮች ደግሞ
በፊርማቸው ያረጋገጡት (የፈረሙት) ሰላሳ አንቀጾችን ያዘለው አዋጅ ወረድ ብሎ
የሚከተሉትን ፍሬ ሐሳቦች ይደረድራል። ።
ሁለቱንም የአምባገነኖች ሥርዓት ፣ የፋሺስቱንም የኮሚኒስቱንም ፣ተራ በተራ የቀመሰው
የጀርመን ሕዝብ ሕገ-መንግሥትም፣ ከአንድ አመት በሁዋላ በ1949 ተመካክሮ
በአወጣውና በአወጀው አዋጁ ላይ፣ በአንቀጽ አምስት ላይ ስለ ነጻ – ዜና መሰራጨት፣ ስለ
ነጻ-አስተሳሰብ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ መስፋፋት፣ በአጠቃላይ ስለ የፕሬስ ነጻነት
የሚከተለውን አረፍተ ነገር ፣በሕገ-መንግሥቱ ላይ፣ መከራም ያስተምራል ፣ እንዲሰፍርም
አድርጎአል።
“…ማንም ሰው” ይላል ደንቡ” ሓሳቡንና አስተያየቱን በድምጽ፣ በቃላትና በጽሑፍ፣
በሥዕል ጭምር ፣ በማንም ሳይታገድ የማስፋፋትና የማሰራጨት መብት አለው። እነዚህንም
ለእሱ አስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚገምታቸውን ዜናዎችና መረጃዎች ለመሰብሰብ መብት
አለው። የፕሬስ ነጻነትና ሓሳብን አለ አንዳች ገደብ በሙሉ ነጻነት በራዲዮና በፊልም
አዘጋጅቶና አቀነባብሮ ማሰራጨት በሕግ የተፈቀደ ነው። የሳንሱር ቁጥጥር ( ቁም ነገሩ ላይ
ደረስን ፣ አምባገነኖች ይህቺን ቃል ይወዳሉም/ ይፈራሉም ) በምንም ዓይነት አይኖርም ”
የጀርመን ሕገ- መንግሥት ይላል።
~ 16 ~


ትችትና ነጻ አስስተሳሰብ ፣ ጋዜጣና ጋዜጠኛነት ትላንት የተጀመረ ሙያ አድርገው የሚቆጥሩ
ሰዎች አሉ። ወይም ይህ መብት ለነጮች እንጂ ለጥቁር አፍሪካ ለእነዚያ የራሳቸው የሆነ
ፊደል እንኳን ለሌላቸው”ፍጡሮች! ለእነሱ አይገባም የሚሉም ኃይሎች አሉ።
ሌሎቸ ማርክስና ሌኒንን ፣ማኦ ሴቱንግንና ስታሊንን እየጠቀሱ፣ ይህ መብት፣ “ለላብ አደሩ
መደብ እንጅ ለማንም ፣ከበርቴና አቆርቋዥ መደብ ፣ ለኢትዮጵያዊ፣ ለኢትዮጵያኖች
አይገባቸውም” የሚሉም አሉ። ይህን ከሚሉት መካከል አንደኛው “ማሌሊት- ሕዝባዊ
ወያኔ” ነው።
“…የመዝባሪዎችም የተመዝባሪዎችም መብትና ጥቅም” በሚለው “ትንተናው”ሁለቱን ”
ባንድ ላይ አስጠብቆ መሄድ አይቻልም። የሁለቱ መብቶችና ጥቅሞች ተጻራሪ ናቸው።
አንደኛውን ለመጠበቅ የግድ ሌላኛውን መርገጥ ያስፈልጋል። ስለዚህ ዲሞክራሲን ከጠባብ
ክልል አውጥቶ ለማስፋት የመጠቀ ዲሞክራሲን ተግባራዊ ለማድረግ ዲሞክራሲ የሕ/ሰቡ
አብዛኛው ክፍል ሃቀኛ ተግባራዊ መብት እንዲሆን ለማድረግ ከተፈለገ ገደብ የለሽ
ዲሞክራሲ ማወጅ አይቻልም። እንደዚህ ዓይነቱ የመጠቀና የሰፋ ዲሞክራሲ ተግባራዊ
ለማድረግ ከተፈለገ መዝባሪ መደቦችን ከዲሞክራሲ ማግለል በነሱ ላይ ገደብ ማስቀመጥ
የግድ አስፈላጊ ነው። ዲሞክራሲ ከጠባብ የቡርዠዋ ክልል ለማውጣት የላብ አደሩ
አምባገነንነት መስርቶ ቡርዡዋውን ከዲሞክራሲ ማግልለ ያስፈልጋል።” ማሌሊት ማርክስሌኒን ሊግ ትግራይ ገጽ 39. 1984 ዓ.ም
እንግዲህ ይህ ነው ያኔ ለአገሪቱ ፕሬስ ለኢትዮጵያ የተነደፈው የውስጥ ፕሮግራማቸው።
ይህ ፕሮግራም ደግሞ አሁንም አልተሰረዘም። እንዲያውም በሥራ እየተተረጎመ ነው።
የሚያሳዝነው ከወታደሩ መንግሥት ከደርግ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለአለፉት አርባ
አመታት በተከታታይ የፕሬስ ነጻነት አለምንም ገደብ በአገሪቱ ፣እንደ ኬኒያና እንደ ጋና እንደ
ናይጄሪያና እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽና ቱኒዚያ አለመኖሩ ነው የችግሮች ሁሉ መነሻ ነው።
ለምን?

በኢትዮጵያ የጋዜጣና የመጽሓፍት ማተሚያ መኪና አዲስ አበባ የገባው በ1879 ዓ.ም
ነው። “ዳግማዊ ምኒልክ በሙሴ ሽፋኔ በኩል አንድ ትንሽ የጽሕፈት ማተሚያ መኪና
ከአውሮፓ አስመጥተው በጸሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ጽሕፈት ቤት አጠገብ አቆሙት።
ከዚያም በሁዋላ ሥራው በሹሙ በአቶ ደኀኔ ወልደ ማርያም ሥር ሁኖ፣ አንዳንድ
መንግሥታዊ ጉዳይ በአማርኛ ፊደል ይታተምበት ነበር። አንድ ትንሽ ጋዜጣም በተወሰነ ጊዜ
ሳይሆን፣ አልፎ አልፎ እየቆየ በነአቶ ደስታ ምትኬና በነሙሴ እንድርያስ ከዋዲያ አዘጋጅነት
ይታተምበት ነበር። በዚህ ጊዜ ዳግማዊ ምኒልክ ጋዜጣውን “አእምሮ” ብለው ሲሰይሙት
ማተሚያ ቤቱንም “መርሐ ጥበብ” ብለውት ነበር።
~ 17 ~

አጼ ምኒልክ ታመው እቤት ከዋሉ በሁዋላ ግን ሥራው ተቋርጦና ማተሚያው ሥራ ፈትቶ
እንደ ተቀመጠ ትዝ ይለኛል።”
አቶ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ እዚሁ ላይ ረመድ ብለው ስለ በ1900ዓ.ም
በፈረንረሳዊው በሙሴ ደባዥ አዲስ አበባ ስለ ገባው ሌላው የላቲን ፊደል መምቻው
(አሳቸው የፈረንጅ ፊደል ይሉታል) የማተሚያ መኪና ፣ በታሪክ ደብተራቸው ላይ
አትተዋል። በሁዋላም በ1904 ዓ.ም የንግድ ማተሚያ ቤትን ስለ አቋቋሙት፣ ስለ እነ ሙሴ
ሽፋኔና ስለ እነ ሙሴ ባልደሣሪያ ፣ ሙሴ አትናቴዎስም ቀጥለውም አንስተው ተርከዋል። ።
የተላያዩ የጸሎት መጽሓፍት፣ የንግድ ካረርኒዎች፣ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ አጫጭር ድርሰቶችና
ግጥሞች እየታተሙ ይወጡ እንደነበርም ጸሓፉው ዘርዝረዋል። የሐማሴኑ ተወላጅ ብላታ
ገብረ እግዚአብሔር “ስለ አገር ፍቅር ” የተጻፈውን ግጥማቸውንም እዚያ ማተሚያ ቤት
እያሳተሙ ያወጡ እንደ ነበረም አቶ መርስዔ ኀዘን ጠቅሰዋል።
በልዑል አልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንን ጊዜ ደግሞ እንደ እነ ብላቴን ጌታ ኀሩይ ወልደ
ሥላሴ ያሉ ጸሐፊዎች ድርሰታቸውን የሚያሳትሙበት ፣ ጋዜጣዎች የሚወጡበት ”
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “ይቋቋማል።
አንዳነድ ጸሓፊዎችም በርትተው፣ ትችት፣ሐተታና አስተያየት፣ በአስተዳደርና በቤተ ክህነት
ላይ፣ አልፈውም በመንግሥት ሰራተኞችም ላይ ጉድለት ሲያዩ ፣እነሱ እንዲታረሙ
ይሰነዝሩም እንደ ነበር፣ እዚሁ የአቶ መርስዔ ኀዘን መጽሐፍና/3 ሎሎች ቦታዎች ላይም
እንመለከታለን። “ቄሣሩ ንጉስ” በሚለው መጽሐፋቸው ላይም አቶ ብርሃኑ ድንቄም
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አንዳንድ ጉድለቶችን ይተቹ እንደ ነበረና ንጉሱም ይህን አይተው
እንደ አቀረቡአቸውም የቀድሞው አምባሳደር አስታውሰው ጽፈዋል።
ሥልጣን ላይ እስከሚወጣ ድረስ ሁሉም በአለ ሥልጣን እንደ ችሎታውና እንደ ፍላጎቱ፣
እንደ አቅሙም “የፕሬስ ነጻነትን” – ወታደሪዊ ደርግም ለትንሽ ወራት ፈቅዶአል ። ወያኔና
ሻቢያም እስከሚጠናከሩ ድረስ፣ ሜዳውን ለጥቂት ጊዜ ለቀዋል። ሁሉም ትንሽ ቆይቶ ይህን
የፕሬስ ነጻነት ገፈው እጫማቸው ሥር ወርውረውታል።
ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ጠቅላይ ሚንስተር ሲሆኑ ለፕሬስ ነጻነት ቅድሚያ ሰጥተዋል።
ግን ትንሽ ቆይቶ ብቅ ያሉት ኃይሎች “ዲሞክራሲ በገደብ/አለገደብ…” ብለው
ተበጣብጠው ሥልጣኑን ለሻለቃ መንግሥቱ ኃይለማሪያም አሳልፈው ሰጥተው ፣ያ
የኢትዮጵያ ደራሲ፣ …ጸሓፊ፣ ተቺ፣ ነጻ አስተሳሰብና አመለካከት በአገሪቱ ማስፋፋት
የሚፈልገው ምሁር፣ ፈላስፋ፣ ፖለቲከኛ፣ አፉ ተለጉሞ እንዲቀር ተደርጎአል። እንግዲህ
በእሱ ፋንታ በአገሪቱ ምን ዓይነት ፍልስፍና ነገሠ?
ከዚያስ?
አረ ለመሆኑ የፕሬስ ነጻነት ምንድነው? የሐሳብ አገላለጽ በኢትዮጵያ እንዴት ነው? ማነው
መናገር መጻፍ፣ሐሳቡን ማሰራጨት የተፈቀደለት? ለመረመረድነው የግራው ክንፍ
~ 18 ~

በስታሊን ትምህርት ዓይኑ የታወረ ሰው “የፕሬስ ነጻነነትን” የሚፈራው ? ወይም ደግሞ
ግፋ ቢል እስከ ተወሰነ ደረጃ ድረስ ብቻ “ሥልጣን እስከ የሚይዝ ድረስ የሚደግፈው”?
ኦ ያገሬ ልጆች ! “…አጋንንቶቹ ከገሃነም እሳት አምልጠው” ዊልያም ሼክስፒር እንዳለው
“… እኛው መካከል ነው ፣ ተሰግስገው ያሉት!”
ይቀጥላል፣ ወዳጄ ገና ይቀጥላል….
“ሚዲያ ፣…ፕሬስ፣ ጋዜጣና ጋዜጠኛነት አላማቸውና የሥራ መስካቸው ሰፊ ነው። የተለያዩ
ዜናዎችን ማቅረብ አንደኛው ነው። የተለያዩ አስተሳሰቦችንና ሐሳቦችን ማስተናገድ ሌላው
ነው። ስህተትን ጉድለትን ፈልፍሎ አውጥቶ ማጋለጥ ሌላው ሦስተኛ የሥራቸው መስክ
ነው። ከእዚሁ ጋር በሥልጣን መባለግን ፣ ሙስናንና ሌብነትን፣ የዘመድ ሥራና አገር
ዘረፋን፣ … ፍርድና ፍትህ ሲጓደል ማጋለጥና አደባባይ አውጥቶ ሰው እንዲነጋገርበት
ማድረግ የጋዜጣና የጋዜጠኞች ኃላፊነት ነው። ዓይኑም ሥልጣን ላይ በተቀመጡት ሰዎች
ላይ እንደ አነጣጠረ ሁሉ፣ ተቃዋሚዎቹም ሲያጠፉ ዝም ብሎ አያያቸውም፤ እነሱም
የትችቱ ኢላማዎቹ ናቸው። ዕውንተኛ ጋዜጣና ጋዜጠኛ ፣ ነጻ ፕሬስ ዋና ሥራው ትችት
ነው።
እግረ መንገዱን አንባቢዎቹንና አድመጮቹን ፣ተመልካቾቹን ያዝናናል። ያስተምራል። ምክር
ይሰጣል። ያስጠነቅቃል። …ዲሞክራሲ ሥረዓት በአንድ አገር የሚገነባውም በዚሁና
በሌሎቸ መሰረት ላይ ብቻ ነው።” (ከጸሐፊው የማስታወሻ ደብተር)
ከሁለት ዓለም አስተሳሰቦች ፣ ከሁለቱ ዓለም አመለካከቶች አንደኛው በኢትዮጵያ ከነገሰ
ይኸው ከአርባ አመት በላይ አልፎአል። አንደኛው ከሁለት መቶ አመት በላይ ዕድሜ ያለው
የነጻው ሕዝብ አስተሳሰብ ነው። ሁለተኛው ገና ትላንት የተፈጠረ ግን ደግሞ ወድቆ
የተንኮታኮት የዕብዶች ሥራና ቅጀት ፣ የተባበሩት መንግሥታት ሰነድ እንደሚለው
“የአረመኔዎች ” አስተሳሰብ ነው። ነው።
——1/ Johannes Gutenberg
2/ John Milton

~ 19 ~

ጸሐይ ስትጠልቅ፣ መጽሐፍ ሳገላብጥ
Posted on July 11, 2013

ጸሐይ ስትጠልቅ
ጸሐይ :-የቀድሞ ተማሪ፣ አሁን ዕድሜው ገፍቶ ከአልጃጀ በስተቀር ፣ ማንም በደንብ
እንደሚያስታውሰው ” …በብርቲሽ ኢምፓየር ፣ በታላቁዋ ብርታኒያ ላይ ጸሐይ ትንከራተታለች እንጂ
ምንጊዜም አትጠልቅም ” ይባላል ። አሁን ግን ጀምበር ሌላው አገር እንደምትጠልቀው ሁሉ፣
በእንግሊዝም ላይ ማታ ማታ ትሰወራለች። እዚያም ጨለማውም ነግሶ፣ እሱዋን ሲያሸብራት እናያለን።
ኮከቦችንም አልፎ አልፎ አዚያ ደሴት ላይ ተቀምጦ መቁጠርም ይቻላል።
መቼም ሰሞኑን እጄ የገባው መጽሐፍ /1 አርዕሰቱ ብቻ ሳይሆን ይዘቱም ጭምር ግሩም ነው። በዚህ
አመት ከአነበብኩአቸው “በርካታ/ ጥቂት” መጽሓፍቶችም ውስጥ በእርግጠኛነት ለመናገር ይህኛው
አንደኛው አስደናቂ መጽሐፍ ነው።
ለምን ለአለፉት አምስት መቶ አመታት፣ ማንም ሳይቀድመንና ሳይበልጠን የዓለምን የልብ ትርታ የወሰንን
ሰዎች፣ አሁን ዓይናችን እያየ የበላይነቱን ከእጃችን ተነጠቅን ? ብሎ ጸሓፊው Naill FERGUSON
እራሱንም፣ አያይዞም አንባቢውንም አብሮ ይጠይቃል። በሁለት መንገድ ጸሓፊው መልስ ከመስጠቱ
በፊት የአውሮፓ ሥልጣኔና አመጣጥ በምን ላይ እንደተመሰረተ ይተርካል። ቆየት ብሎም፣ እራሱ
የወረወረውን ጥያቄ ወደ መመለሱም ይሸጋገራል።
“ሚስጢራችንን” (ይህን እሱ FERGUSON “Killer-Apps ,… Applications” ብሎ
የሚጠቁመውን ቃል በሌላ ቋንቋ መተርጎም አቅቶኝ!) ሚስጢራችንን ሌሎቹ አድፍጠው ቀድተው፣
በሥራ ተርጉመው “እኛን ጉድ አደረጉን “፣ ይላል።
እዚህ ጀርመን መጥቶ ጸሓፊው መጽሐፉን ለማሰተተዋወቅ በአደረገው ንግግሩም ላይ፣ ነገሩን ሁሉ
ሰብሰብ አድርጎት፣ እንደዚህ አድረጎ ለማወቅ ለሚፈልግ ሰው አስቀምጦታል። እናዳምጠው።
… ጃፓንና ሕንድ ፣ ብራዚልና ደቡብ ኮሪያ ፣ ቻይናም ጭምር …አሥራ አንዱ የምዕራቡ አገሮች፣
ብቻቸውን ጨብጠውት ይዘው የነበረውን “ሚስጢራዊ፣… ጥበብና ዕውቀት” ፣ እነሱ እላይ
የተጠቀሱት ወጣት፣ መጤ ፣ ታዳጊ አገሮች ለቀም አድርገው ቀድተው ለእራሳቸው ጥቅም አዋሉት፣
ይላል። በዚህ ጉዞም አሁን በቅርቡ፣ አሜሪካ በቻይና (በኢኮኖሚ ዕድገት) ትቀደማለች። የዋሆች ግን
በተለይ የእኛዎቹ ፣ ቻይና እዚህ የደረሰችው፣ “በሶሻሊዝም ፍልስፍና ነው” ሊሉ ይችላሉ! እውነቱ ግን
እሱ ላይ አይደለም !
ለአለፉት አምስት መቶ አመታት አውሮፓ፣ የምዕራቡ ዓለም “ዓለምን ለመቆጣጠር” የቻለችው
በስድስት አብይ ነገሮች ላይ ተመስርታ እንደሆነ (–ሌሎቹ ጸሐፊዎች ቀጥሩን ከፍ ያደርጉታል– )
ጸሐፊው ይጠቅሳል። ከእዚያም ውስጥ “በአራቱ ምሶሶዎች” ላይ ደህና አድርጎ ይመላለሳል።
አንደኛው፥ በእሱ ዓይን፣ “የሐሳቦችና የፈጠራዎች ፉክክር፣ ውድድር ” የሚለው ብልሃት፣ እንደሆን
ይገልጻል።

~ 20 ~

ሁለተኛው፥ የ”ትምህርት መስፋፋት፣ የሳይንስና የምርምር ነጻነት ምሁሩ አግኝቶ፣ ለፈጣን ለውጥ፣
ለአእምሮና ለቴክኒክ አብዮት” በሰፊው በር በመከፈቱ ነው፤ ብሎ የታሪክ ጸሐፊው ያስረዳል።
ሦስተኛው፥ በእሱ እምነት፣ (ይህቺን ቀጥላ በቅ የምትለውን ቃል አምባገነኖች ፈጽሞ መስማት
አይወዱም) “የሕግ በላይነት፣ ነጻ ፍርድ ቤት፣ የዳኞች፣የነገረ ፈጆች፣ የጠበቃዎች መምጣት ነው”፤
ይላል። ማለት በሕግ ፊት “የእኔና የአንተ/አንቺም እኩልነት”!
አራተኛውና አምስተኛውን ፣ ስድስተኛውን ጭምር፥ እናንተው ፍላጎት ከአላችሁ፣ መጽሐፉን
ጨብጣችሁት እንድትከታተሉት እንጋብዛችኋለን።
የፍርጉሶን መጽሐፍ ከጀርመኑ ጸሐፊ፣ ከኦስቫልድ ስፔንግለርም ከዚያ ከ”..የምዕራቡ ዓለም
ውድቀት”/2፣ ከሚለው መጽሐፉ ጋር አንድ አድርገው የሚያዩ ሰዎች አሉ። ግን ሁለቱ መጽሐፎች
ፍጹም አንድ አይደሉም። እሱም፣ ምሁሩም በትክክል አንድ አይደሉም፣” ይለያያሉ “ይላል። ፍርጉሶን
መሰረታዊ ወደ ሆነው ፣ የአውሮፓ ሥልጣኔ ወደ ተገነባበት ወደ ጠርዞቹ “ድንጋዮች”፣ አንመለስ ብሎ
እነሱን ለማስተዋወቅ:- እንግዳ ለሆኑ አንባቢዎቹ ምንድናቸው? ብሎ ይጠይቃል። እንግዲህ መልሱን
መጽሐፉ ላይ ተከታትሎ ማንበቡ የእናንተ ፋንታ ነው።
በሚቀጥሉት እትመቶቻችን “በባህልና በሥልጣኔ ” ዙሪያ እስከ ዛሬ ድረስ የተጻፉትን መጻሕፍቶች ተራ
በተራ ከመደርደሪያችን እያወጣን በአጭሩ፣ በአጭሩ ፍሬ ፍሬ ነገሮቹን እንዲትመለከቱት
እንጋብዛችኋለን።ከዚያም ውስጥ ወደፊት የኦስቫልድ ስፔንግለርም መጽሐፍ -”የምዕራቡ፣ የኦክሲደንት
ውድቀት” የሚለው አንደኛው ነው።
“እኛ ማን ነን?” የሚለውን ትልቁን ጥያቄ ሰንዝሮ ግሩም ጥራዝ የጻፈውን፣ የሳሙኤል ሐንትግተንን/3
“ፍሬ ሐሳቦች”( ብዙዎቻችሁ ምናልባት ታውቁታላችሁ) ከብዙ በጥቂቱ በመጀመሪያ እሱን አስቀድመን
ሸብ አድርገን እናልፈዋለን። …ለምን አሜሪካ? ለምን ቻይና አይሆንም ? የምትሉ አትጠፉም። ስለ
እነሱም ጊዜው ሲደርስ እናነሳለን።
አሜሪካንን የምናስቀድምበት ግን ሌላ ምክንያት አለን። የከርሞ ሰው ይበለን!
————————1/ Niall Ferguson- The Great Degeneration: How Institutions Decay and Economies Die (2012)

2/Oswald Spengler; The Decline of the West /1922; 1923
3/ Samuel P. Huntington – Who Are We? The Challenges to America’s National Identity (2004)

~ 21 ~

የግዕዝ ፊደል ስረ፥መሰረት – Origins and Usage of Ge’ez
Posted on July 11, 2013
“The history of the Ge’ez writing system is not as easy to trace as the Roman, owed
primarily to widely accepted but inaccurate scholarship based on Euro-centric assumptions.
As Amadou-Mahtar M’Bow has written there was a refusal to see Africans as creators of
original cultures which flowered and survived over the centuries in patterns of their own
making and which historians are unable to grasp unless they forego their prejudices and
rethink their approach.”(see below, our italics)

ባጭሩ የግእዝ ፊደል ስረ መሰረት ሶስት ገጽታዎችን፣ የሚያመለክት አጭር
ጥናት ነው። ማለትም ግእዝ

1ኛ ሥዕላዊ ገጽታ
2ኛ ርዕዮታዊ/ሃሳባዊና
3ኛ ሰማያዊ/ መንፈሳዊና መለኮታዊ ገጽታ እንዳለው፤ በዚህም ከዘመን መቁጠሪያ ጋር
በተያያዘ አልፎም ከኮከቦች አቀማመጥ ቀምር ጋር የተመላከተና የረቀቀ መሆኑን ያሳያል።

~ 22 ~

i.e. “Astrography, or the charting of the stars and hence, the calendar, is the third
property of the Ge’ez system. The system, with it’s 26 classes and 7 variations
provide its total of 182 syllographs. One hundred and eighty two, being half of
364, represents a half-year or one equinox.”
….
“Each of the syllographs have a corresponding number value from 1-5600.The
number values associated with each syllo graph also contains codes of the
Ethiopian knowledge (mystery) system. “
Geez-origin & system-of-usage

Origins and Usage of Ge’ez
Read More:
wWw.thisisgabes.com/documents/paper_gabriella.pdf

~ 23 ~

~ 24 ~

~ 25 ~